ᒪEYᒪᗩ тяυтн_ѕєитιиєℓ
Статистика- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 17
- Тип
- открытый
- Язык
- русский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 510
- 1/48двое суток
- 584
- 1/72трое суток
- 630
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
እስልምና ወይስ Feminism ነው ለሴቶች ጠቃሚው ?? Part 2 🎆1 የወሊድ እና የቤት ውስጥ ስራን እንደ ጭቆና ማየት (Anti-Natalism & Domestic Labor) የፌሚኒዝም እሳቤ: ልጅ መውለድ፣ ማሳደግ እና የቤት ውስጥ ኃላፊነቶችን መወጣት ሴቶችን ከተወዳዳሪነት የሚያገዱና የኢኮኖሚ ጥገኛ የሚያደርጉ የጭቆና ቀንበሮች ናቸው። የእስልምና ምላሽ: እስልምና እናትነትን እጅግ የላቀና ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ መለኮታዊ ክብር አድርጎታል። ቤት ማስተዳደርና ትውልድ ማነጽ ማህበረሰብን የሚገነባ ታላቅ ኃላፊነት እንጂ የበታችነት አይደለም። አላህ በቁርአኑ እናትን በተለየ ሁኔታ እንድናከብር አዟል ፡ "وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍ وَفِصَالُهُ فِي عَامَيْنِ أَنِ اشْكُرْ لِي وَلِوَالِدَيْكَ إِلَيَّ الْمَصِيرُ ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፡፡ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡ [📗ሱረቱ ሉቅማን፡ 14። ] ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ለሙአዊያህ ቢን ጃሂማህ ተንከባከባት ጀነትን ከፈለክ የእናትህ እግር ስር ነው ያለው። አሉት [📚ሱነን ኢብኑ ማጃህ 2781] 2 የሃይማኖት የበላይነትን አለመቀበል (Secular Individualism) የፌሚኒዝም እሳቤ: ለአንዲት ሴት የመጨረሻው የውሳኔ ሰጪ አካል ራሷ ግለሰቧ ብቻ ናት። ሃይማኖት፣ ባህል ወይም መለኮታዊ ህግጋት በእሷ ምርጫ ላይ ጣልቃ የመግባት መብት የላቸውም። የእስልምና ምላሽ: ሙስሊም ማለት ለአላህ ትዕዛዝ ሙሉ በሙሉ እጅ የሰጠ ማለት ነው። ወንድም ሆነ ሴት ምርጫቸውን ከአላህና ከመልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ውሳኔ በታች የማድረግ ግዴታ አለባቸው። አላህ በቁርአን ግልጽ ድንጋጌ አስቀምጧል፡ وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُّبِينًا አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ " [📗ሱረቱ አል-አሕዛብ፡ 36] 3 የወንዶች መብት (Patriarchy) ፍጹም ክፋት ነው ማለት። የፌሚኒዝም እሳቤ: በወንዶች መሪነት የሚመራ ማህበረሰብ በሙሉ (Patriarchical system) ሴቶችን ለመጨቆን ብቻ የተዋቀረ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ መፍረስ አለበት። የእስልምና ምላሽ: እስልምና በጾታዎች መካከል የጠላትነት ወይም የይገባኛል ትግል (Class Struggle) ሳይሆን የትብብርና የመደጋገፍ ግንኙነትን ነው የገነባው። ወንድና ሴት እርስ በርሳቸው የሚረዳዱ ወዳጆች ናቸው። አላህ እንዲህ ይላል፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ [📗ሱረቱ አት-ቶውባህ] 4 ፍፁም እኩልነት : ፌሚኒዝም በወንድና በሴት መካከል ያለውን የተፈጥሮና የተግባር ልዩነት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርጋል። እስልምና ግን : እኩልነትን ሳይሆን ፍትህን[ Equity]ን ያፀድቃል። ምክንያቱም ሁሉም እኩልነት ፍትሃዊ ስላልሆነ ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ሁለት ሰዎች ታሞ ሀኪም ቤት ቢሄዱ በEquality ሕግ መሰረት ሁለታቸውም ተመሳሳይ ወይም እኩል የሆነ ሰዓት ሊሰጣቸው ይገባል ግን በEquity[ፍትሃዊነት] ሕግ መሰረት እንደየ በሽታቸው ክብደት የሚያስፈልጋቸውን ሰዓት ያክል ሊሰጣቸው ይገባል። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ ۖ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ [📗ሱረቱ አሊ-ዒምራን፡ 36] 5 የቤተሰብ መሪነት እና ኃላፊነት (ቀዋማህ): የፌሚኒስት ንቅናቄዎች፦ የወንድን የቤተሰብ መሪነት (ሀላፊነት) ሙሉ በሙሉ ማጥፋትን ይሻሉ። ይህ ደግሞ ከቁርአን ግልጽ ጥቅስ ጋር ይጋጫል፡ الرِّجَالُ قَوَّامُونَ عَلَى النِّسَاءِ بِمَا فَضَّلَ اللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَا أَنفَقُوا مِنْ أَمْوَالِهِمْ ۚ ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ 📕[ሱረቱ አን-ኒሳእ፡ 34] 🎆6 የውርስ እና የምስክርነት ህግጋት: የፌሚኒዝም አስተሳሰቦች በእስልምና ውስጥ ያሉትን የውርስ ድርሻዎች እና የምስክርነት ልዩነቶች እንደ አድሎ ያያሉ። ነገር ግን እስልምና ይህንን የወሰነው ወንዱ ላይ በሚጣለው የኢኮኖሚና የቤተሰብ ማስተዳደር ግዴታ (ነፈቃህ) ላይ ተመስርቶ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡ يُوصِيكُمُ اللَّهُ فِي أَوْلَادِكُمْ ۖ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ الْأُنثَيَيْنِ ۚ አላህ በልጆቻችሁ (ውርስ በሚከተለው) ያዛችኋል፡፡ ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው፡፡ [ 📕ሱረቱ አን-ኒሳእ፡ 11] 🎇7 Transgender[ ፆታን መቀየር]፦ የፌሚኒስት ንቅናቄዎች፦ ሴት ፆታዋን መቀየር መብት አላት ብሎ ሲያስቡ እስልምና ግን፦ ተፈጥሮን መቀየር ሸይጣን መከተል እና ሐራም የሆነ ተግባር እነደሆነ ያስተምራል አላህ ሸይጣን እንዲህ ብሎ እንደዛተብን ይነግረናል፦ وَلَآمُرَنَّهُمْ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلْقَ اللَّهِ ۚ وَمَن يَتَّخِذِ الشَّيْطَانَ وَلِيًّا مِّن دُونِ اللَّهِ فَقَدْ خَسِرَ خُسْرَانًا مُّبِينًا አዛቸውምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ፤ (ያለውን ይከተላሉ)፡፡ ከአላህም ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ሰው ግልጽ ክስረትን በአርግጥ ከሰረ፡፡ [📗ሱረቱ አን-ኒሳእ] ነቢያችን እንዲህ አሉ عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمُتَشَبِّهِينَ مِنَ الرِّجَالِ بِالنِّسَاءِ، وَالْمُتَشَبِّهَاتِ مِنَ النِّسَاءِ بِالرِّجَالِ" ወንድ ሆኖ ከሴት ጋር ራሱን የሚያመሳስል ሴት ሆና ከወንድ ጋር ራሷን ምታመሳስልን ሴት አላህ ረግሟል [📕Sahih al-Bukhari,5885] Part 3 ይቀጥላል...
Feminism [ የሴቶች መብት ተሟጋችነት] Part 1 ፌሚኒዝም (Feminism) በግርድፉ ሲተረጎም "የእንስትነት ንቅናቄ" ወይም "የሴቶች እኩልነት መብት ታጋይነት" ማለት ነው። ፌሚኒዝም : ማለት ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ግላዊ መብት እንዲሁም እኩል እድል ሊኖራቸው ይገባል የሚል የጽንሰ-ሀሳብ እምነት እና ማህበራዊ ንቅናቄ ነው። በአባታዊ (Patriarchal) ማህበረሰብ ውስጥ የሚፈጸሙ የጾታ መድልዎዎችን፣ ጭቆናዎችን እና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም የሚደረግ ሁለንተናዊ ጥረት ነው። [🌐📗 Encyclopædia Britannica ] መቼ እና እንዴት ተመሰረተ? ፌሚኒዝም በአንድ ጀንበር ወይም በተወሰነ ቀን የተመሰረተ ተቋም ሳይሆን በሂደት ያደገ ታሪካዊ ንቅናቄ ነው፦ የቃሉ አመጣጥ: Feminism (féminisme) የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው Charles Fourier የተባለ ፈረንሳዊ ፈላስፋ በ1837 ነበር። (First-Wave Feminism) : ዘመናዊው እና የተደራጀው የሴቶች መብት ንቅናቄ በይፋ የተጀመረው በ1848 በአሜሪካ ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደው የሰኔካ ፎልስ ኮንቬንሽን (Seneca Falls Convention) ላይ ነው። [🌐📗 History.Com] 🎆 Feminism 4 ደረጃዎች ወይም ሞገዶች አሉት፦ First-wave feminism(የመጀመሪያው ሞገድ: ከ19ኛው እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የነበረ ሲሆን በዋናነት በሕጋዊ መብቶች፣ በተለይም በሴቶች የመምረጥ ፣ መመረጥ እና በንብረት ባለቤትነት መብት ላይ ትኩረት አድርጎ ነበር። Second Wave feminism( ሁለተኛው ሞገድ) ከ1960ዎቹ እስከ 1970ዎቹ የነበረ ስርዓት ሲሆን ማህበራዊ እኩልነቶችን፣ የስነ-ተዋልዶ መብቶችን፣ በስራ ቦታ የሚፈጸሙ መድሎዎችን እና ባህላዊ የጾታ ሚናዎችን በማካተት ክርክሩን አስፋፋ። Third Wave feminisim (ሦስተኛው ሞገድ) ከ1990ዎቹ እስከ 2000ዎቹ የነበረ ሲሆን ግለሰባዊነትን እና ብዝሃነትን የተቀበለ ሲሆን፣ የፌሚኒዝምን ትርጉም በማስፋት ከተለያየ ዘርና የኢኮኖሚ ዳራ የመጡ ሴቶችን ማካተት ላይ ትኩረት አድርጓል። Fourth Wave Feminism (አራተኛው ሞገድ) (የአሁኑ ዘመን)፦ በዲጂታል ሚዲያ እና መድረኮች የሚመራ ሲሆን፣ በትስስራዊነት (intersectionality)፣ ጾታዊ ትንኮሳን በመዋጋት እና በጾታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን በመቃወም ላይ ያተኩራል። 🎇የፌሚኒስም አይነቶች ሊበራል ፌሚኒዝም[ Liberal Feminism] ፦ ባሉት ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅሮች ውስጥ እኩል ዕድል እና ውክልና እንዲኖር ይጠይቃል። ራዲካል ፌሚኒዝም[ Radical Feminism]፦ የወንዶች የበላይነት በማህበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደደ ነው ብሎ የሚያምን እና ባህላዊ የጾታ ሚናዎችን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ የሚጥር ነው። ሶሻሊስት / ማርክሲስት ፌሚኒዝም፦ ካፒታሊዝም ከጾታ እኩልነት እጥረት ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ጥገኝነትን እንደ ትልቅ እንቅፋት ይመለከታል። Part 2 ይቀጥላል....
ሀሳብ አስተያየት በcomment ማስቀመጥ ይቻላል
እውን ሴቶች ለወንዶች ጠላቶች ናቸውን ?? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ وَإِن تَعْفُوا وَتَصْفَحُوا وَتَغْفِرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብተምሩዋቸውም አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ 📗 ተጋቡን 64:14 ሚሽነሪዎች ከላይ ያለውን የቁርአን አንቀፅን በመጥቀስ በእስልምና ሴቶች የወንዶች ጠላቶች ናቸው ብሎ ዉኃ የማያነሳ ሙግት ያነሳሉ፡፡ ለመሆኑ አንቀፁ ሴቶች የወንዶች ጠላቶች ናቸው ይላልን??? በፍፁም አይልም፡፡ የቁርአን አንቀፁ የሚለው ከሚስቶች እና ከልጆች ጠላት የሚሆኑ እንዳሉ እንጂ ሙሉ በሙሉ ሴቶች የወንዶች ጠላት ናቸው የሚል ሃሳብ የለውም፡፡ ሙፈሲሮች ምን ብሎ አብራሩ የሚለውን እንመልከት 🎆ኢማሙል በገዊይበተፍሲራቸው ላይ እንዲህ ብሎ አስቀምጠዋል : [ ኢብኑ አባስ እንዲህ አለ : እነዚህኮ ከመካ የሰለሙ ወንዶች ናቸው ወደ መዲና መሰደድ(ሂጅራ) መውጣት ፈልጎ ከዛ ሚስቶቻቸው እና ልጆቻቸው ከለከሏቸው በመስለማቹህ ታገስን እናንተን በመለየት መታገስ አንችልም አሏቸው ከዛ ታዘዟቸው ሂጅራ መውጣትን ተዉ ከዛ ከላይ ያለው የቁርአን አንቀጽ ወረደ ] 📗ተፍሲሩል በገዊይ ቅፅ 8 ገፅ 142 🎆ኢብኑል አረቢይ እንዲህ ይላሉ ከኢብኑ አባስ በቲርምዚይ እና ሌሎች ዘጋቢዎች በዘገቡት ዘገባ እንደፀደቀ አንድ ሰው ከዚህ አያህ ጠየቀ { يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ } ከመካ የሰለሙ ወንዶች ናቸው ወደ ነቢያችን መሄድ ፈልጎ ሚስቶቻቸው እና ልጆቻቸው እነሱን ጥለዋቸው ወደ ነቢዩ መሄዳቸውን እምቢ አሉ ወደ ነቢያችን መጥቶ ሰዎች ስለዲን ቡዙ ተምሮ ባዩ ጊዜ እነሱን ሊቀጧቸው ፈለጉ ከዛ አላህ { يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ } የሚለውን የቁርአን አወረደ፡፡ 📗 Ahkamul Quran ቅፅ 4 ገፅ 263 🎇በተጨማሪም ሶስተኛ ነጥብ : አንቀፁ የጠላት ሁኔታውን ያብራራል, ጠላት ተብሎ የተጠቀሱት አካላት በመሰረቱ ጠላት ሆኖ ሳይሆን ጠላት የሆኑት በሥራዎቻቸው ነው፡፡ አንዲት ሚስት ወይም ልጅ የጠላትን ተግባር ከፈፀመ ጠላት ይሆናል በባርያው አምላኩን በመታዘዝ መሃከል ከመግባት የበለጠ አፀያፊ ተግባር የለም፡፡ 📗 Ahkamul Quran ቅፅ 4 ገፅ 264 የቁርአኑ አንቀፅ ምን ለማለት እንደፈለገ እና ለምን እንደወረደ ካየን የሚሽነሪዎች ብዥታ እዚሁ ወድቋል፡፡ 🎇አሁን ደግሞ ክርስትና ለሴቶች ያለውን አምለካከት እንመልከት ሴት ባልዋን ብትመግበው ቁጣን አለማክበርንና ብዙ ዘለፋን የተሞላች ትሆናለች። ለልብ ቁስል ናት ለፊትም ጥቁረት ናት ለነፍስም ሀዘን ናት እንዲሁ ባልዋን የማታከብር ሴት እንደ ሽባ እጅና ልምሾ እንደሆነ እግር ናት። 📗መፅሐፈ ሲራክ 25:22 -23 እግዲህ ይሄን መፅሐፍ ይዛቹህ እስልምናን ለመተቸት እንዴት እንደበቃቹህ እኔንጃ አላህ ቀልብ ይስጣቹህ ።
Part 2 በተጨማሪም ጥያቄ :ለአንድ አንቀፅ ብዙ ብዙ ሰበበኑዙል ሊኖረው ይችላል እንዴ ?? መልስ : ለብዙ ሰበቦች አንድ የቁርአን አንቀፅ ብቻ መውረዱማ ተገኝቷል, የሆነ ክስተት ይከሰታል, ከዛም ሌላ ክስተት ይከሰታል ከዛም ሌላ ሶስተኛ ክስተት ይከሰታል በነዚህ ክስተቶች ሁሉም ውስጥ አንዲት አያህ ብቻ ትወርዳለች 📗አት-ተስሂሉ ሊተዕዊሊተንዚል የሙጃደላ ጁዝ ተፍሲር ገፅ 350 ነቢያችን ማርያን በራሱ ላይ እርም ያደረገው ዓኢሻ እና ሐፍሷ በጣም ስለቀኑ ነበር። ግን በዘይነብ ቤት በተራዋ እና በፊራሿ ላይ ማርያን ሲገኛት ዘይነብ እንዴት ይሄን በቤቴ በቀኔ እና በፍራሼ ላይ ይሄን ታደርጋለህ እንዴ አለችው የሚሉ ዘገባዎች ሁላቸውም ዶኢፍ ናቸው። ሰሂህ ቢሆኑ እንኩዋን ባርያውን ሐላል የምትሆንለትን ባርያውን ነው የተገናኘው ምንድነው ይሄ ይገርማቹሃል እንዴ የመፅሐፍ ቅዱስ ትርክት እያለ ?? እስኪ የነቢያቶችን ጉድ እንመልከት[ነቢያቶች እንደዛ ናቸው ባልልም] ክርስትያኖች እጅ ያለው መፅሐፍ የሚለውን ልበል። 🎆ሶምሶንከአንዲት አመንዝራ ሴት ጋር ዝሙት ፈፅሞ ነበር 1: ሶምሶንም ወደ ጋዛ ሄደ፥ በዚያም ጋለሞታ ሴት አይቶ ወደ እርስዋ ገባ። 2: የጋዛ ሰዎችም ሶምሶን ወደ ከተማ ውስጥ እንደ ገባ ሰሙ፥ ከበቡትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ በከተማይቱ በር ሸመቁበት፡— ማለዳ እንገድለዋለን፡ ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ። 3: ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሥቶ የከተማይቱን በር መዝጊያ ያዘ፥ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያውም ጋር ነቀለው፥ በትከሻውም ላይ አደረገ፥ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ በዚያም ጣለው። 📗መፅሐፈ መሣፍንት 16:1-3 🎆ሎጥ ከሴት ልጆቹ ጋር ዝሙት ፈፅሟል 30: ሎጥም ከዞዓር ወጣ፤ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስለ ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፤ በዋሻም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ተቀመጠ። 31: ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፡— “አባታችን ሸመገለ፥ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም፤ 32: ነዪ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” 33: በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋም ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። 34: በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፡— “እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” 35: አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። 36: የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። 📗ዘፍጥረት 19: 30-36 🎆ይሁዳ በልጁ ሚስት ላይ ዝሙት ፈፅሟል 15: ይሁዳም ባያት ጊዜ ጋለሞታን መሰለችው፤ ፊትዋን ተሸፍና ነበርና። 16: ወደ እርስዋም አዘነበለ፡— “እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ፡” አላት፤ እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፡— “ወደኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው። 17: “የፍየል ጠቦት ከመንጋዬ እሰድድልሻለሁ፡” አላት። እርስዋም፡— “እስክትሰድድልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህን?” አለችው። 18: እርሱም፡— “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርስዋም፡— “ቀለበትህን፥ አምባርህን፥ በእጅህ ያለውን በትር፡” አለች። እርሱም ሰጣትና ከእርስዋ ጋር ደረሰ፥ እርስዋም ፀነሰችለት። 📗ዘፍጥረት 38:15-18 🎇ዳዊት በጎረቤቱ ሚስት ላይ ዝሙት ፈፅሟል 2: እንዲህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፥ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፤ በሰገነቱ ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም መልከ መልካም ነበረች። 3: ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፡— ይህች የኤልያብ ልጅ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን? አለ። 4: ዳዊትም መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፥ ከርኵሰትዋም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤትዋም ተመለሰች። 5: ሴቲቱም አረገዘች፥ ወደ ዳዊትም፡— አርግዤአለሁ፡ ብላ ላከችበት። 📗2ኛ ሳሙኤል 11:5 እና የነዚህ ነቢያቶች ተግባር ፅድቅ ሆኖ ነው እነሱ ያልተተቹት ?? እብካችሁን ወገኖቼ ‼️የራሷ እያረረባት የሰውን ታማስላለች እንዳሉ አትሁኑ ቅድምያ የራሳቹሁን አማስሉ።
ማርያ ወይስ ማር ወይስ ሁለቱም ??? يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِي مَرْضَاتَ أَزْوَاجِكَ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ 📗ተህሪም 66:1 ከላይ ያለው የቁርአን አንቀፅ ሰበበኑዙሉን በተመለከተ ሙፈሲሮች የተለያየ ሃሳብ ያስቀምጣሉ ፡፡ ①︎ ከፊሎቹ ከሶውዳ ቤት የበላውን ማር አስመልከቶ የወረደ ነው ነው እንጂ ባርያውን(ማርያን) በራሱ ላይ እርም አድርጎ አይደለም ይላሉ፡፡ ②︎ ከፊሎቹ ደግሞ አይ ነብዩ በራሱ ላይ እርም ያደረገው ማርያን እንጂ ማርን አይደለም ይላሉ፡፡ ③︎ ከፊሎቹ ደግሞ ማርም ሆነ ማርያ ዋናው ነገር አላህ ለሱ ሐላል ያደረገውን በራሱ ላይ ሐራም አርጎ ነው ፡፡ ④︎ ከፊሎቹ ደግሞ ነቢያችን ሁለቱንም ( ማርንም ማርያንም ) በራሱ ላይ እርም በማድረጉ ሊሆን ይችላል የሚል ሀሳብ ያነሳሉ፡፡ والله أعلم ከማስረጃ አንፃር አንቀፁ የወረደው ለሁለቱም ክስተት መሆኑ ምክንያቱም ለሁለቱም ክስተት ለመውረዱ ሰሂህ የሆነ ዘገባ ስላለ ማለት ነው፡፡ የወረደው ማርን በተመለከተ ለመሆኑ ዓኢሻ እንደተረከችው ነቢያችን ዘይነብ ቢንት ጃህሽ(ሚስቱ) ጋር ቆይቶ ማር በልቶ ይወጣል ከዛ እኔና ሐፍሷ ማንኛችንም ጋር ሲመጣ መጋፊር በልተሃል ከአፍህ ላይ የመጋፊር ሽታ ይሸታል እንበለው ተባባሉ ከዛ ነቢያችን አንደኛዋ ላይ ገባ እንደተባባሉት አለችው ሌላኛው ጋርም ገባ እንዲሁ አለችው አይ ዘይነብ ጋር ማር በልቼ ነው አላት ካሁን ቡኃላ አልመለስበትም አላት ከዛ ያየቁርአን አንቀፅ ወረደ.... 📗Sahihal Bukhari 5267 በተጨማሪም 📕Sahih muslim 1474a 📕Sunan An-Nasai 3421 📕Sunan Abu Dawud 3714 ማርያን በተመለከተ ለመሆኑ ደግሞ "أَخْبَرَنِي إِبْرَاهِيمُ بْنُ يُونُسَ بْنِ مُحَمَّدٍ، حَرَمِيٌّ - هُوَ لَقَبُهُ - قَالَ حَدَّثَنَا أَبِي قَالَ، حَدَّثَنَا حَمَّادُ بْنُ سَلَمَةَ، عَنْ ثَابِتٍ، عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَتْ لَهُ أَمَةٌ يَطَؤُهَا فَلَمْ تَزَلْ بِهِ عَائِشَةُ وَحَفْصَةُ حَتَّى حَرَّمَهَا عَلَى نَفْسِهِ فَأَنْزَلَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ አነስ እንደተረከው ነቢያችን صلى الله عليه وسلم አንድ የሚገናኛት ባርያ ነበረችው በራሱ ላይ እርም እስኪያደርጋት ድረስ ዓኢሻ እና ሐፍሷ አልተዉትም ከዛ አላህ { يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ } إِلَى آخِرِ الآيَةِ ." የሚለውን አንቀፅ አወረደ፡፡ 📗 Sunan An-Nasai 3959 ሁለቱም ሐዲስ ሰሂህ ናቸው፡፡ እና እንዴት ነው የአንቀፁ ሰበበኑዙል የማሩ ጉዳይ ብቻ ሊሆን የሚችለው ?? በተለይ ደግሞ አንድ የቁርአን አንቀፅ ሁለት ሰበበኑዙል ሊኖረው አይችልም ማለት ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ አንቀፅ ለሁለት ለተለያዩ ክስተቶች ሊወርድ ስለሚችል በተለይ የሁለቱ ክስተት ጊዜ የሚቀራረብ ከሆነ 💥ኢብኑ ሐጀር : አንቀፁ ለሁለቱ ሰበብ(ምክንያት) ሊወርድ ይችላል ብለዋል 📗Fathul Bari ቅፅ 11 ገፅ 7 💥ሸይክ ሙሀመድ አሊ አደምእንዲህ ይላሉ : አንቀፁ በሁለት ክስተቶች የወረደ ነው የማሩ ክስትተ እና የባርያው ክስተት ነው, ለአንድ አንቀፅ ቡዙ ሰበበኑዙል ከመኖር ከልካይ የለም... 📗ዘኪረቱል ዑቅባ ፊሸርሂል ሙጅታባ ቅፅ 28 ገጽ 230 💥ኡስታዝ ሱለይማን ኢብኑ ኢብራሂም እንዲህ ይላል ከፊል ኡለሞች የማርያን ጉዳይ ተርጂህ አደረጉ [ ቡዙ ቀደምት ሙፈሲሮች ] ከፊሎቹ የማርን ጉዳይ አሰበጡ ምሳሌ [ ኢማሙል ቁርጡቢ, ኢብኑ ከሲር...] ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጧበሪ : ደግሞ ዋናው ነገር አላህ ሐላል ያደገለትን በራሱ ላይ ሐራም ማድረጉ እሱ በላጭ ሃሳብ ነው ale ይላል ሾውካኒ : እነዚህ ሁለቱም ክስተቶች ለአንቀፁ መውረድ ትክክለኛ ሰበብ ናቸው ብለዋል ይላል 📗 ኦውኑረሕማን ፊተፍሲሪል ቁርአን ቅፅ 22 ገጽ 439 💥ኢማሙ አስ-ሱዩጥይ ኢብኑል ሐጀር: አንቀፁ ለሁለቱ ሰበብ(ምክንያት) ሊወርድ ይችላል ብለዋል ይላል 📗ሉባቡኑቁል ፊ አስባቢኑዙል ገፅ 242 Part 2 ይቀጥላል.....
𝙲𝚘𝚗𝚝𝚛𝚘𝚕 𝚞𝚛 𝙽𝚊𝚏𝚜✨ Your nafs is just like your enemy once it finds you serious, it obeys you. If it finds weakness from you, it will take you as a prisoner "Ibn al qayyim rahimaullah"
ታውቁ እንደሆነ ቀደምት የኢስላም አበዎች ወደ መካ ሲመጡ አንዴም ለፈትዋ ሁለትም ሀዲስ ለማስተላለፍ ይቀማመጡ ነበር። አንድ ጊዜ ታለቁ ዓሊም አብዱረዛቅ ኢብን ሐማም አ'ሰንዓኒይ መካ ሲገባ የዒልም መጅሊስ ከፍቶ ነበር ብዙ ሰዎችም ሊማሩበት ቀጭ ብለው ነበር። በቀጣዩ ቀን ሲመጣ ግን ማንም የለም በዚህ ነገር ተገርሞ “ሰዎች የታሉ"? ብሎ ሲጠይቀ “ወኪእ ኢብን ጀራህ መጥቷል" እዛ ሄደው ነው አሉት ! “አልሀምዱሊላህ! ሀዲሴን የተው መስሎኝ ነበር” አለ። ይህ ማለት ከኔ የተሻለ ሀፊዝ መጥቶ ከሆነ እሱ በቅቶናል እኛ ጋር ያለው እሱ ጋር አለ እንደማለት ነው። ዓጂብ እኮ ነው! ቀደምቶች ልቦናቸው ከሂስድ ከሂቅድ የጸዳ ነው። የዛሬ ሰው ቢሆኝ እኛ እያለን ሌላ መጅሊስ ለምን ይከፈታል ብሎ ሊያለቅስ ይችላል። ቀደምቶች ግን ለሚበልጣቸው ይተናነሳሉ ይዋደቃሉ ያለምንም መጣበብ ለሚበልጣቸው እውቅና ይሰጣሉ። https://t.me/forbeginnerss
ግብፅ ላይ በአንድ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ የሚሰራ ኡስታዝ ነበር። ኢማን አለው( ﻛﺬﺍﻟﻚ ﻧﺤﺴﺒﻪ ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺣﺴﻴﺒﻪ ) የልብ በሽታ በጣም ያስቸግረውም ነበር... በሽታው ሲፀናበት ወደ እንግሊዝ ሀገር ለህክምና ይሄድና ዶክተሮችም ያልጠበቀውን ነገር ዱብዳ ያሰሙታል። "ልብህ ደክሟል ቀዶ ጥገና ይደረግልሀል ግን ወይ ትሞታለህ ወይም ትተርፋለህ"አሉት። እሱም፦"እሺ ልጆቼን ተሰናብቼ የአደራ ንብረቶችን ለባለቤቱ መልሼ እመጣለሁ"ይላቸውና ቶሎ እንዲመለስ አስጠንቅቀውት ወደ ሀገሩ ግብፅ ተመለሰ። ልጆቹንም ሰብስቦ ያፅናናቸው ጀመር... "ምናልባት ዳግም ላንተያይ እንችላለን ቀዶ ጥገናው ላይሳካ ስለሚችል ልሞትም እችላለሁ ሰብር ማድረግ አለባችሁ...." እያለ አፅናናቸው። ቤተ ዘመዶቹንም መሰናበት ያለበትን ሁሉ ሄዶ ተሰናበተ አላህንም ለመገናኘት መዘጋጀት ጀመረ። አሁን እስቲ ታሪኩን ሰውየው ራሱ ይተርክልን፦ ___ "አንድ ጓደኛየን ልሰናበተው ስራ ቦታው ሄጄ እያወጋን ሳለ ከጎን ባለው ስጋ መሸጫ ቤት በር ላይ አንድ ሴት ተመለከትኩ። ከታፊው ሲከትፍ ሚጥለውን እሷ ትለቅማለች በጣም ተገረምኩ ወደ ሴትየዋ ጥጋ አልኩና ለምን እንደምትለቅም ስጠይቃት እንዲህ አለችኝ፦ "አምስት ሴት ልጆች አሉኝ ስጋ ሚባል ነገር ከቀመሱ አመት አልፏቸዋል ስጋ ለመብላት ባይታደሉ እኳን እችን የለቀምኳትን ጠብሼ ሽታውን ያግኙ ብዬ ነው" በጣም አዘንኩኝ ልቤ ተነካ ሁኔታዋ አስለቀሰኝ.. ወደ ስጋ ቤቱ ይዣት ገባሁና "የፈለግሽውን ያህል ውሰጂ እኔ እከፈላለሁ" አልኳት እሷም፣ "አንድ ኪሎ ይበቃኛል" አለች እኔም ወደ ውስጥ ገባሁና ለስጋ ቤቱ ባለቤት "በቀን በቀን ሁለት ሁለት ኪሎ ስጋ ስጣት" ብዬ የአንድ አመት ከፍየው ለሷም ነገሪያት ስወጣ.. እንባ እየተናነቃት አንገቷን አቀርቅራ እዛው ዱዓ ታደርግልኝ ጀመር... እዛው በቆምኩበት የጤንነት ስሜት ተሰማኝ በዱዓዋ ሁኔታየ መቀያየር ጀመር። ነገ ጉዞ ስላለብኝ ለመዘጋጀት ወደ ቤት አቀናሁ.. ቤት ከመግባቴ ትንሿ ልጄ በግርምት እያየችኝ "አባቴ ፊትህ ተቀይሯል ደስታ ይነበብብሀል ምንድነው እሱ"አለችኝ ከልጆቼ አስተዋይ ለኔ አሳቢ ስለሆነች በጣም እወዳታለሁ የገጠመኝን ነገርኳት... በእዝነት እያየችኝ እንባዋን ታረግፍ ጀመር "ባባ ሴትየዋን ከችግር እንዳወጣህ አላህ ከችግርህ ያውጣህ" አለችኝ። በማግስቱ በቀጠሮዬ መሰረት ወደ እንግሊዝ ተጓዝኩ ዶክተሮችም ለቀዶ ህክምናዬ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው አስገቡኝ...ዶክተሩ ቼክ አረገኝና በጣም በመገረም.. "የት ነው የታከምከው?" አለኝ "እንዴት ምን ለማለት ፈልገህ ነው?" አልኩት በተደጋጋሚ ቼክ አረገኝ...ከዛም "ለህክምና ከኛ ሌላ የት ሄደህ ነበር?" አለኝ በመገረም እያየኝ "ወላሂ የትም አልሄድኩም ልጆቼን ተስናብቼ ብቻ ነው የመጣሁት" አልኩት በጣም ግራ ተጋባ.. "ይሄማ እንዴት ይሆናል ልብህ ንፁህ ነው..."እያለ ፋይሌን ያገላብጥ ጀመር... እኔም በሰውየው ሁኔታ በመደናገጥ "ሰውዬ ምንድነው ምትለው ብዬ ጮህኩ?" በትኩረት ተመለከተኝ..."አንተ ወይ ሌላ ሰው ነህ...ወይም ሌላ ከኛ የተሻለ ሆስፒታል ሄደህ ነው" እያለ የሄድኩበትን ሆስፒታል እንድነግረው ይማፀነኝ ጀመር...ያ አላህ!!! በዛ ሰአት የዛች የምስኪን ዱዓ ትዝ አለኝ...የዛች የትንሿ ልጄ እንባ ታወሰኝ... ሁሉንም ለዶክተሩ አጫወትኩት ወደ ልጆቼም በስላም ተመለስኩኝ። ከ tiktalk የተወሰደ ✍️✍️
ይጋጫልን ???? (ሙሳም) «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም» አለው፡፡ 📗Suratu-taha 12 :52 መናፍቃንና መናፍቃት ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው፡፡ በመጥፎ ነገር ያዛሉ ከደግም ነገር ይከለክላሉ፡፡ እጆቻቸውንም (ከልግስና) ይሰበስባሉ፡፡ አላህን ረሱ፡፡፤ ስለዚህ (እርሱ) ረሳቸው፡፡ መናፍቃን አመጸኞቹ እነሱ ናቸው፡፡ 📗 ሱራቱል-towbah 9:67 ይጋጫልን ?? በፍፁም አይጋጭ ፡፡ ✨️ ምክንያቱም መርሳት ሲባል መዘናጋትትን ብቻ የሚሳይ አይደለም። በል እንደውም ፦ 📗ሙዕጀሙል ወሲጥ ፦ በተሰኘው አረቢክ dictionary ላይ " نسيان " ማለት የሆነን ነገር በመዘንጋት መርሳትን ወይም አውቆ መተውን ሊያመላክት ይቺላል ይላል። ⛳️ ስለዚህ አላህ የሆነን ነገር ረሳ ሲባል ሳይፈልግ መዘናጋቱን የሚያሳይ ሳይሆን ሆን ብሎ የሆነን ነገር መተውን የሚያሳይ ነው ። ✨️ምክንያቱም ሳይፈልግ መርሳት የሰው ድክመት(ጉድለት)ስለሆነ አላህ ደግሞ ከንዲህ አይነት ጉድለት የጠራ ነው። ⛳️ ለዛም አላህ ረሳቸው ሲል ተዋቸው ከነሱ አውቆ ችላ አለ ማለት ነው እንጂ ሳይፈልግ ረሳ ማለት አይደለም። ✨️➡️አይረሳም ሲባል ሳይፈልግ የሆነን ነገር አይዘነጋም ማለትን የሚያመላክት ነው። 📗ዳፍዑ ኢሐሚል ኢድጥራቢ ዓን አያቲል ኪታብ በተሰኘው መፅሐፍ ፦ ሙሳ ጌታዬ አይረሳም ያለው እና አላህ በሱረቱል አዕራፍ ላይ አላህ ሙናፊቃንን በተመለከተ እንረሳቸዋለን የሚለው አንቀፅ አይጋጭም ይላል ምክንያቱም አላህ እንረሳቸዋለን ሲል በእሳት ውስጥ እንተዋቸዋለን ሁሉንም ከይር እንነፍጋቸዋለን ማለት ነው እንጂ አላህ ያለፊቃዱ ረሳ ማለትን አያሳይም ይላል። ሙፈሲሮችም ያስቀመጡትን ሃሳብ ትንሽ እንመልከት 1 ኢማሙል በገዊይ፦ { نَسُوا اللَّهَ فَنَسِيَهُمْ }: تركو طاعة الله فتركهم من توفيقه وهدايته في الدنيا ومن رحمته في الآخرة وتركهم في عذابه አላህን መታዘዝ ተዉ አላህም በዱንያ ላይ እነሱን ሀቅን መግጠም እና ወደ ቀጥኛውን መንገድ መምራቱን ተዋቸው በአኪራም ለነሱ እዝነትን አያደርግም በቅጣቱም ውስጥ ተዋቸው ማለት ነው። 📗 ተፍሲሩል በገዊይ ቅፅ 4 ገፅ 71 2ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጧበ ሪ وأما قوله: ﴿ نَسُوا اللَّهَ فَنَسِيَهُمْ ﴾، فإن معناه: تركوا الله أن يطيعوه ويتبعوا أمره ، فتركهم الله من توفيقه وهدايته ورحمته «አላህን ረሱት እርሱም ረሳቸው» የሚለው ቃል ትርጉሙ፦ አላህን መታዘዝንና ትዕዛዙን መከተልን ተዉ አላህም እነሱን ሀቅን መግጠምን ፣ ቀጥተኛ መንገድ መምራትን እና ለነሱ ከማዘን ተቆጠበ (ተዋቸው) ማለት ነው። ” 📗ተፍሲሩ አጥ-ጧበሪ ቅፅ 11 ገፅ 549 ስለዚህ ሁለቱ ሃሳቦች በፍፁም የሚጋጩ አይሉም። ማስረጃ ከኪታብ 👉📚click ✍️ ሀምዳን https://t.me/Hamdan_islamic_defender
ተውሒድ ተውሒድ የተፈጠርንበት አላማ ነው። ተውሒድ በሰዎች ላይ የተጣለ የፈጣሪ ሐቅ ነው።(''አንተ ሙዓዝ አላህ በባርያዎቹ ላይ ያለው ሐቅ ምን እንደሆነ ታውቃለህ የሚለውን የመልእክተኛውን ንግግር አስታውስ)። ተውሒድ የነብያት ሁሉ ተልዕኮ ነው። ተውሒድ መለኮታዊ ራዕይ የወረደበት ትልቁ ምክንያት እና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ነው።ተውሒድ ወንጀልን ማሳበሻ በጀሐነም ውስጥ እንዳንዘወትር ብቸኛ መዳኛ ነው። ያለ ተውሒድ መልካም ስራ ሁሉ ከንቱ ነው።ተውሒድ የዱንያ የአኺራ ስኬት ሁሉ ምንጭ ነው።... ስለዚህ ንፅፅር የምንሰራ እህት ወንድሞቼ የደዕዋችን ዋና ማጠንጠኛ ፤ የዘወትር አጀንዳችን ይህ ይሁን ። የመጀመሪያ የምንጠራቸው አላህን አንድ ወደማድረግ በብቸኝነት ወደማምለክ ይሁን። ግን ደዕዋችን ፍሬ እንዲያፈራ በስራችን ላይ ኢኽላስ ይኑረን ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ አብዱልወሀብ ኪታቡ ተውሂድ ላይ ምን ይላል መሰለህ ባቡ:- ወደ ላኢላሀ ኢለ ላህ ምስክርነት ሰዎችን መጥራት በሚለው ርእስ ስር «ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡(ዩሱፍ 107) ይህን አንቀፅ አስቀመጡና ወደ ታች ወርደው ፊሂ መሳኢል (ከነሶቹ የምንወስዳቸው ጠቃሚ ነጥቦች የሚለውጋር) 1ኛ: ወደ አላህ(ወደ ተውሒድ) መጣራት ነብዩን የሚከተሉ ሰዎች መንገድ ነው። 2ኛ: (አንቀፁ የሚያስተምረን) በደእዋ ላይ ኢኽላስ ሊኖር እንደሚገባ ያሳስባል ምክንያቱም ብዙ ሰው ወደሐቅ እየተጣራ (ቃለላህ ቃለ ረሱል እያለ) ነገር ግን ወደ ራሱ የሚጣራ ይሆናል። ይላሉ እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ ደዕዋ ማድረግ ከጀመርን በኋላ ቪድዮዋችን ቫይራል አለመሆኑ፤ እንደትልልቆች ኡስታዞች ታዋቂ አለመሆናችን ውስጣችንን አደፍርሶት ከስራችን ወደ ኋላ አላደረገንም? ለምን ነበር የጀርነው ለምንድነው ያቆምነው ለአላህ ነበር? ኒያ ፣ ኢኽላስ የሚባሉ ነገሮች ሁሌ አሳሳቢ ናቸው ማለት ነው። ሁሌ ልብን መፈተሽ መገምገም ያስፈልጋል ማለት ነው። ሌላው ደእዋችን በእውቀት ላይ የተመሰረተ ይሁን ደዕዋ ልክ እንደጂሐድ ነው ትጥቅ ካልያዝን ባንገባ ነው የሚሻለው። ትጥቁ ደግሞ እውቀት ነው። ዝም ብሎ በወኔ ብቻ የሚሆን አይደለም። ሰው አተርፋለው ብለን ሄደን እራሳችን ተንሸራተን እንዳንወድቅ የኛንም የነሱንም በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። ያለ እውቀት የሚሰራ ከሆነ ከልማቱ ጥፋቱ ይበዛል። ሶስተኛው እዝነት ይኑረን የምንጠራቸው በመጀመሪያ እነሱን ለማትረፍ እንደሆነ እናስብ። እራሳችንን በነሱ ጫማ ውስጥ አድርገን እንመልከት አላህ ባይውልልን እና ከካፊር ቤተሰብ ተወልደን ቢሆን በቀላሉ የምንሰልም እንሆን ነበር? ከቤተሰባችን ያገኘነው ውርስ አይጎትተንም ነበር? ኢስላም ሀቅ መሆኑን ካወቅን በኋላስ ቢሆን ላለንበት ሀይማኖት ወገንኝነት ይዞን ኢስላምና ሙስሊሞችን እንሳደብም ነበር? ስለዚህ ሀቅ ክብደት ይኖረዋል በተለይ ለኖርክበት ህይወት የኔ ነው ላልከው ሀይማኖት ህይወትህን ሙሉ ስትምልበት ለነበረው አማልክት ተቃራኒ ሲሆን ስለዚህ እዝነት ሪፍቅ ትእግስት ይኑረን ልክ እንደነብያት አንዳንዴ እንደአውዱ በመጡበት ወልኩ ልንመልስ እንችል ይሆናል ነገር ግን የሁል ጊዜ ባህሪያችን አንደነሱ መሆን የለበትም ። ምክንያቱም እነሱ አርኣያዎቻችን አይደሉም።
ኡስታዛቺን eliyah حفظه الله ورعاه በቁርአን እና የታሪክ ፀሐፊዎቹ ዙሪያ ወሳኝ ትምህርት በ tiktalk ለቀዉልናል እየገባን የ እዉቀት አድማሳችንን ሰፋ እናድርገው በዛውም ኸደምደም እናድርግ ቶፒ link, repost 😉 አህባቢ https://vt.tiktok.com/ZS4APbqNB/
ተውሂድ بسم الله الرحمن الرحيم ⛳️ ተውሂድ የሚለው ቃል ቋንቋዊ ቱርጉሙ:wahhada( َوَحَّد) "አንድ አደረገ" ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን አንድ ማድረግ ማለት ነው። ሸሪዓዊ ቱርጉሙ አላህን በአምልኮ በመነጠል እሱን አንድ ማድረግ ነው። በአላህ አንድነት የሚያምን ሰው “ሙወሒድ” (مُوَحِّد) ይባላል። ⛳️ አላህ አንድና ብቸኛ አምላክ መሆኑን በቡዙ በቁርአን አንቀፆች ላይ ይነግረናል። ለምሳሌ ያህል {قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ} {በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡} [ سورة الإخلاص 112:1]📕 { فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مُتَقَلَّبَكُمْ وَمَثْوَاكُمْ } { እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡ አላህም መዘዋወሪያችሁን፣ መርጊያችሁንም ያውቃል፡፡ } [ سورة محمد 47:19 ]📕 ⛳️ የስላሴን አስተምሮት ከBible ለመፈለግ ሌተቀን የሚለፉ ምስኪን ክርስታኖች ተውሂድ(توحيد) የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ ስለሌለ ቁርአናዊ አስተምሮት አይደለም በማለት አስቂኝ ሙግት ያነሳሉ። ⛳️ ከላይ እንደተመለከትነው ተውሂድ(توحيد) ማለት አምላክን በአንደኝነቱ ማምለክ ከሆነ ተውሂድ የሚለው ቃል መጠቀሱ ጥቅሙ ምንድነው ?? ምክንያቱም አስተምሮቱ የአምላክን አንድነት እስከሰበከ ድረስ ቃሉ መጠቀሱ ግድ አይደለም። ⛳️ እንደው አስፈላጊ ነው ተብሎ ከታሰበም ተውሂድ የሚለው ቃል በሐዲስ ውስጥ ተጠቅሷል. ሐዲስ ደግሞ የነብዩ(ﷺ) ቃል ቢሆንም ምንጩ ከአላህ ነው ምክንያቱም ነብያችን የሚናገሩት የሚወረድላቸውን ራእይ እንጂ ከልቦለዳቸው ስላልሆነ። { وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ🔶️ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ } { ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ } [سورة النجم 4-3 : 53]📕 ናሙና ከሐዲስ 🎆 ነብያችን (ﷺ) ከታች ባለው ሐዲስ ላይ እንዲህ በማለት ይናገራሉ عَنْ عَائِشَةَ، وَعَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ كَانَ إِذَا أَرَادَ أَنْ يُضَحِّيَ اشْتَرَى كَبْشَيْنِ عَظِيمَيْنِ سَمِينَيْنِ أَقْرَنَيْنِ أَمْلَحَيْنِ مَوْجُوءَيْنِ فَذَبَحَ أَحَدَهُمَا عَنْ أُمَّتِهِ لِمَنْ شَهِدَ لِله بِالتَّوْحيد وَشَهِدَ لَهُ بِالْبَلاَغِ وَذَبَحَ الآخَرَ عَنْ مُحَمَّدٍ وَعَنْ آلِ مُحَمَّدٍ ـ صلى الله عليه وسلم ـ . It was narrated from ‘Aishah and Abu Hurairah that when the Messenger of Allah (ﷺ) wanted to offer a sacrifice, he brought two large, fat, horned, black-and-white, castrated rams. He slaughtered one on behalf of his nation, for whoever testified to Allah with monotheism and that he had conveyed (the Message), and he slaughtered the other on behalf of Muhammad and the family of Muhammad (ﷺ) 📕[ Sunan Ibn Majah, 3122 ] በተጨማሪም عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " يُعَذَّبُ نَاسٌ مِنْ أَهْلِ التَّوحِيدِ فِي النَّارِ حَتَّى يَكُونُوا فِيهَا حُمَمًا ثُمَّ تُدْرِكُهُمُ الرَّحْمَةُ فَيُخْرَجُونَ وَيُطْرَحُونَ عَلَى أَبْوَابِ الْجَنَّةِ . قَالَ فَيَرُشُّ عَلَيْهِمْ أَهْلُ الْجَنَّةِ الْمَاءَ فَيَنْبُتُونَ كَمَا يَنْبُتُ الْغُثَاءُ فِي حِمَالَةِ السَّيْلِ ثُمَّ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ" [. قَالَ هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ وَقَدْ رُوِيَ مِنْ غَيْرِ وَجْهٍ عَنْ جَابِرٍ .] ጃቢር እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ከተውሂድ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በእሳት ውስጥ ፍም እስኪሆኑ ድረስ ይቀጣሉ። ከዚያም የአላህ እዝነት ይደርስለቸዋል፣ ይወጣሉ እና በገነት ደጆች ላይ ይጣላሉ።» አለ። «የገነት ሰዎች ውሃ ያፈሱባባቸዋል ፣ የጎርፍ ፍርስራሾችም በጎርፍ ውስጥ እንደሚበቅልባቸው ይበቅላሉ፣ ከዚያም ወደ ጀነት ይገባሉ።» አለ። 📕[Tirmidhi, 2597 ] ወሰላሙ አለይኩም
ኢንሻአሏህ ራሳቺሁን በደምብ እምትጠቅሙበትን ጥሩ argument build ማድረግ እምትቺሉበት ሁኔታም ጭምር ነው ለ እናንተ አላህ እኔንም እናንተንም ይጠብቀን✨
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته✨ እስኪ በዚ ቻናል ውስጥ ሸብሀዎችን የክርስቲያን ሙግቶችን መልስ እንዲሁም አርቲክሎችን በደምብ እናያለን አሪፍ አሪፍ ለ comparative ጠቃሚ pdf ሚለቀቁም ይሆናል ኢንሻአሏህ عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ: «سِبَابُ الْمُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ» ሙስሊም ወንድሙን መስደብ ትልቅ ኃጢአት ነው፤ ከእርሱ ጋር መዋጋትም እጅግ ከባድ ኃጢአት ነው። stay tuned!
Channel created