tgindex
Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
5 409
−3 за 5 дн.
Сутки
+7
+0,13%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 369
24 постов
Вовлечённость
25,3%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 24
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
293
1/48двое суток
335
1/72трое суток
362

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • How I ENDED Jay Dyer's Career.. (FULL DEBATE) Orthodox Muslim VS Jay Dyer https://youtube.com/watch?v=6DjuCmuCoa0&si=6KUv0BYP0GMFNbJ8

  • 5 авг.1 898302

    አንዳንዴ ሰው መኾን ለሚችለው ትልቅ ነገር በዚህ ልክ ትንሽ ነገር አጥቶ ሲቸገር ማየት በጣም ልብ ይሰብራል። የልጁን ብቃት ያየ ገና ባፍላ ዕድሜው በትክክል የቅርብ ጊዜ የኢስላም ትውፊት ይኾናል ብሎ ማንም ማመን ይችላል። ግን መኾን ለሚፈልጋቸው ነገሮች ኹሉ ትንሽ ድጋፍ አነሰው... አነሰውናም ከነ ስጋ ቤተሰቡ ጭምድድ ብሎ መንገድ ላይ ቀረ... ያንን ልጅ ላየ ኹሉ ትንሽ አሰብ ካደረገ እንደ ኡማ የዛሬ ኪሳራችንና የወደፊት አራጣ ዕዳ ተሸካሚዎች መኾናችንን ዕርግጠኛ ይኾናል። የባሕር አሸዋ ምንም ያሕል ገዝፎ ቢከመር ትንሽ የንፋስ ሽውታ ብትንትኑን ያወጣዋል። አንዲት እፍኝ ሆጻእ (አሸዋ) ግን ከእፍኝ ሲሚንቶ ጋር ተዋህዳ ከባሕር ክምር አሸዋው በላይ ጉልበት አላት። ታዲያ በቁጥር ግማሽ ሕዝብ ነን የሚል የአልቦ ክምር (ባዶ ክምር) ተሳስሮ ሐገር መኾን እየቻለ በዚህ ልክ ነገን መሸከም የሚችሉ ተስፈኞቹን ሲያጣ ማየት የሚወራውንና የሚባለውን ኹሉ በጆንያ ሙሉ የቀረበ የፈንደሻ እራት ያስመስለዋል። ጆንያውን ላየ "ይሕማ ለሐገር ይተርፍ የለ እንዴ?!" ያስብላል። በቆለምሸሽ (ቆሎ ማቅረቢያ) የቀረበ ጊዜ ግን የሕጻን ጉንጭን እንኳ የማይሞላ ባዶ ዐየር ይኾናል። መኾንኽን በጥቂት እገዛ ማጣት ብቻ ለተነጠቅኸው ወዳጄ ሰላም በአንተ ላይ ይኹን። ስለ አንተ የምችለውን ኹሉ አደረግኹና የኾነ ቦታ ቆምኹ። ግማሽ ሕዝብ ነን የሚሉ መፈክር ብቻ አንጋቢዎች እኔ አይደለኹም ራስኽ ምላስኽን አላውሰኽ ችግርኽን ብትነግራቸው ሊያግዙኽ አይደለም ሊሰሙኽ እንኳ አይፈልጉም። ምክንያቱ ምን መሰለኽ ብላቴናው? ዛሬ ዛሬ ለመሰማት ራሱ በንዋይ ጓርነን ያለ ድምጽ ያስፈልጋል። ካልኾነ ግን ችግር ያሰለለው ድምጽ መስማት በማይፈልጉ የአሕያ ጆሮ ባለቤቶች ፊት የዝንብ ብዝዝዝታን ያሕል እንኳ አይሰማም። ስለዚህ የአዞ እምባህ የኾነ ቀን ጠራርጎ እስኪወስደን ድረስ አብረን ማዘን እንችላለን!!! سلام على الفقراء والمساكين الذين غفلت عنهم الأمة كأنهم لا وجود لهم

  • 4 авг.1 216151

    {የሴቶች ምስክርነት በኢስላም} በኣላህ ስም እጀግ ኣዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ነብይ ላይ የሰላምና እዝነት ዝናብ ይዝነብ ብለን እንቀጥላለን፡፡ወዳጄ እንደምን ከረሙ?እነሆ ዛሬ ወዳጃችን ዳዊት ክብረት ካነሳቸው ነጥቦች ውስጥ የመጨረሻውን ላወራሎ መልካም መስሎ ታየኝ፡፡ “ኢስላም ሴቶችን ደብድቡ ይላል” የሚለውን ሃሳብ ሌሎች ወንድሞች ስለጻፉበት አልደግመውም፡፡ ቀጥታ ወደ ሃሳቡ እንዝለቅ፡…

  • 4 авг.1 12162

    ወደ ጀመርነው የቁረኣን ጥቅስ ምልከታዎች እናቅና፡- 2ኛ) ከዘመናት ጀምሮ እስከ አሁንም ድረስ ሴቶች በንግዱ ዓለም እንደ ወንዱ ሁሉ ላቅ ያለ ተሳትፎ እንደሌለቸው ቅቡል ነው፡፡ ያ ሴቶችን የማሓበረሰቡ ኣካል አድርጎ በማይቆጥር ህብረተሰብ ውስጥ ደግሞ የሴቶች ምጣኔኣዊ ተሳትፎ ምንም እንዳልነበረ የታሪክ ዳራን ማየት የህሊና ምስክርነትን ይሰጣል፡፡ አዳምና ሃዋ (ዐ.ሰ) ወደ ምድር ለምድር ከተጣሉበት ቅጽበት ኣንስተን እስካለንበት ሃያ ኣንደኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በዘመን ቁልቁለት ተንደርድረን ብንወርድ በሃብታቸው ከቁጥር የገቡ ቱጃር እንስቶች የሉም፡፡ ይህ የሁላችንም ተግባቦታዊ እውነታ ደግሞ ሴቶች በንግዱ ዓለም ያላቸው ተምኩሮ እስከ የት ድረስ እንደሆነ በለሆሳስ እንድንገምት ያደርገናል፡፡ ችግሩ ወደ ኋላ የምናብ ጉዞ በማድረግና ዛሬን ከትላንቱ ጋር በማጣመር የምንደርስበት “ሴቶች ካላቸው የንግድ ተመኩሮ ኣንጻር ለምስክርነት አይበቁም” የሚል ስሁት ድምዳሜ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ በሚደረጉ ታላላቅ የንግድ ስምምነቶች ላይ ይህ ህሳቦ አሉታዊ ጠባሳውን በመጣል ሴቶች ከምስክርነት እንዲገለሉ ምክንያት ኾኗል፡፡ ኢስላም ይህንን ኢፍትሃዊ ፍልስፍና በመናድ ሴቶች ለንግድ ስምምነት እማኝ መሆን እንደሚችሉ አበሰረ፡፡ እማኝነታቸው ከውንዱ እማኝነት በጥቅሉ በኣንድ ደረጃ ያንሳል ብሎ ማሰብ ግን ምናልባት ጥቅሱን ከሌሎች ጥቅሶች ጋር አዛምዶ ባለማየት ወይም ለማየት ካለመፈለግ የመጣ ችግር ነው፡፡ ቁር 24/6 ላይ ባልና ሚስት በዝሙት ቢጠራጠሩና ለጥርጣሬው ማስረገጫ ግን እማኞች ቢጠፉ እያንዳዳቸው በኣሏህ ስም አራት ጊዜ ከማሉ በኋላ በኣምስተኛው “ከውሽታሞች ብኾን፤ የኣሏህ እርግማን ይኑርብኝ” ብለው እንዲምሉ ይደረጋል፡፡ ተፈጥሮኣዊ በሆነ መልኩ የሴት ምስክርነት ከወንዱ ግማሽ በነበረ ኖሮ፤ እዚህ ቦታ ላይ በአራት ፈንታ ስምንት ጊዜ እንድትምል በተደረገ ነበር፡፡ ወደ ዋናው ጉዳያችን ስንመለስ ጥቅሱ በንግድ ስምምነት ወቅት ሴቶቹ ሁለት ወንዱ ደግሞ አንድ መሆን አለበት የሚል አስገዳጅ መስፍረት እንደሌለው ልብ ይሏል፡፡ ኣንዳንድ የኢስላም ምሁራን “ከምትወዷችው” የሚለው ሃረግ አስመስካሪዎቹ የሚያምኑባቸውና የሚወዷቸውን ሰዎች ሁሉም ወንዶች ወይም ሁሉም ሴቶች ወይም ደግሞ ሁለት ወንድ አንድ ሴት ማስመሰከር እንደሚቻል ይጠቁማል ይላሉ፡፡ ወዳጄ እዚህ ቦታ ላይ ብቻ የሴቶች ምስክርነት ከወንዶች በግማሽ ያንሳል የሚለውን እኛ ሙስሊሞች በቀጥታ እንቀበለዋለን፡፡ ለምን?፣ እንዴት? የሚል ጥያቄ ከተነሳ፤ አቢ ሰዒዲኒል ኹድሪይ ባወሩት ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሃዲስ_ መልክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) “ …የኣስተሳሰባቸው ማነስማ የሁለት ሴቶች ምስክርነት ከኣንድ ወንድ ጋር እኩል ነው…” በማለት ያሰለፍነውን የቁርኣን ጥቅስ ለማስረጃነት መጠቀማቸው ዋቢችን ይኾናል ፡፡ ይህንን ጉዳይ ዛሬ ሳይንስ በደረሰበት እውነታ ስንመረምር ዶ/ር ዘንዳኒ እንዲህ ሲል ይናገራል “ ዘመናዊው ሳይንስ እንደ ደረሰበት ለወንዶችም ለሴቶችም ለመናገርና ለማስታወስ የሚረዳ ሁለት የኣእምሮ ጓዳ አላቸው፡፡ ወንድ ልጅ ሲናገር አንደኛውን ጓዳ በማሰራት ሲሆን፤ሌላኛውን ጓዳ ለማስታወስ ይጠቀምበታል፡፡ ሴት ግን ንግግር ላይ እያለች ሁለቱም ጓዳዎቿ በስራ ስለሚወጠሩ ስለምትመሰክርበት ጉዳይ ሙሉ ትውስታ አይኖራትም” በማለት የበርካታ ሳይንቲስቶችን የምርምር ውጤት ይፋ አድረጓል፡፡ ዚነት ዛይዲ የምትባል ሌላ የህክምና ተማሪ “Gender Differences in Human Brain” በሚል አርቲክል ላይ በርካታ ሳይንቲስቶች የተስማሙበተን እውነታ እንዲህ ስትል ጽፋለች፡- “Men have 4% more neurons than women, and about 100 grams more of brain tissue. Women have a more developed neuropil, or the space between cell bodies, which contains synapses, dendrites and axons. This may explain why women are more prone to dementia (such as Alzheimer's disease) than men, because although both may lose the same number of neurons due to the disease, in males, the functional reserve may be greater as a larger number of nerve cells are present, which could prevent some of the functional losses” ስንገረድፈው “ ወንዶች ከሴቶች 4% የሚበልጥ ሕዋሰ-ነረቭ እና 100 ግራም ተጨማሪ የኣእምሮ ህብረ-ህዋስ አላቸው፡፡ ሴቶች ደግሞ በህዋሶች አካላት መካከል በተሻለ መልኩ የበለጸገ ጋጥሚያ ህዋሳተ ነርቭ፣ናሜና ዘንግን የሚያቅፍ የኣእምሮ ክፍል ኣላቸው፡፡ ይህ ኹነት ሴቶች ለምን ለኣእምሮ መሳትና ለመርሳት በሽታዎች ከወንዶች በበለጠ እንደሚጋለጡ ያመላክታል፡፡ ከበሽታው አኳያ ምንም እንኳ ሁለቱም እኩል ቁጥር ያላቸውን ህዋሰ-ነርቮችን ቢያጡም፤ ወንዶች በርካታ ቁጥር ያላቸው የነርቭ ህዋሶች ስላሏቸው ኣእምሮኣቸው ሙሉ በሙሉ ቨከኣገልግሎት ውጪ እንዳይሆን ይታደጋሉ፡፡” ትላለች፡፡ መቼም ፍትሃዊ ኣእምሮ ያለው ካሳለፍናቸው ሳይንሳዊ መረጃዎች አኳያ ቁርኣን “አንድኛዋ ስትረሳ አንደኛዋን ታስታስውሳት ዘንድ…” ያለበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ይረዳል፡፡ በስተመጨረሻም በቀና ልብ ኾነን የወገኖቻችንን መጸሃፍ ዋቢ በመድረግ እንዲህ እንላለን፡- ውድ ወገኖች! ከኣእምሮ በላይ የኾነው ኣምላክ ከጥንተ-ተፈጥሮ ጀምሮ የሰው ልጅን በኣእምሮ ኣልቋል፡፡ በኣእምሮውም መረጃዎች ላይ በመንተራስ እውነታን እንዲመረምር ፈቅዷል፡፡ ኣእምሮ መረጃዎችን ሲመረምር ህሊና ይፈርዳልና በኣእምሮና በህሊና መካከልም ጥብቅ ትስስር ፈጥሯል፡፡ ሁለቱን በጣምራ ማሰራት የቻለ ውሸትን አሸንፎ አርነት ይወጣል`` እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል``የዮሐንስ ወንጌል 8/32፡፡ የሰው ልጅ ይህንን ተፈጥሮኣዊ ጸጋውን ትቶና ስቶ ከሄደ እንደ እንስሳዎች ያለ መረጃና እውቀት መኖር ይጀመራል፡፡ ባልቦ እውቀት ፍኖተ-ሕይወት ድቅድቅ ጽልመት ነው፡፡ ድቅድቁ የማሃይምነት ጽልመት በእውነት ብርኃን ደምቆ አይን ካላጥበረበረ፤ ጭለማን ብቻ የሚያውቀው አይናችን ድቅድቁን ጨለማ ብርኃን አድርጎ ማሰብ ይጀምራል፤ በስተመጨረሻም መመለሻውም ከከፋ ገደል ይዶለናል፡፡ “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል፡፡” (ሆሴዕ 4/6)፡፡ ፡፡ “ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፡፡ በመጨራሻ ግን ወደ ሞት ይመራል፡፡” ምሳሌ 16/25 የሰው ልጅ ስጋውን ለነፍሱ አሳድሮ ወደ ቀልቡ በመመለስ በነጻ ማሰብ፤ በነጻ መጠየቅ ከሰነፈ እየተጓዘበት ያለውን የሾኽ አሜኬላ ጎዳና ለኣጼ -ወ- እቴጌ ጫጉላ ሽርሽር ጥርጊያው እንደተቀና መንገድ ጨርቅ በጨርቅ መኾኑን ሳይመረምር መቀበል ይጀመራል፡፡ አስቀድሞ ለምርምር በሩን ዝግ ስላደረገ ዳግም መክፈት ይሳነዋል፡፡ “እናንተ ብስለት የሌላችሁ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወዱታላችሁ?” ምሳሌ 1/22 በራሱ ማሰብ ማሰላሰልና መመርመር የሰነፈ ትውልድ ደግሞ ሌሎች የቤት ስራውን እንዲሰሩለት ይፈቅዳል፤ከዚያም እንደ ወፍ ጫጩት መርዝም ኾነ ጠጠር ካፋቸው መልቀም ይጀምራል፡፡” ሕዝቤ ሆይ መሪዎችህ አሳስተውሃል፤ ከመንገድህም መልሰውሃል፡፡” (ኢሳያስ 3/12) https://t.me/E_M_ahmoud

  • {የሴቶች ምስክርነት በኢስላም} በኣላህ ስም እጀግ ኣዛኝ እጅግ ሩህሩህ በሆነው እንጀምርና በመቀምቀሚያው ነብይ ላይ የሰላምና እዝነት ዝናብ ይዝነብ ብለን እንቀጥላለን፡፡ወዳጄ እንደምን ከረሙ?እነሆ ዛሬ ወዳጃችን ዳዊት ክብረት ካነሳቸው ነጥቦች ውስጥ የመጨረሻውን ላወራሎ መልካም መስሎ ታየኝ፡፡ “ኢስላም ሴቶችን ደብድቡ ይላል” የሚለውን ሃሳብ ሌሎች ወንድሞች ስለጻፉበት አልደግመውም፡፡ ቀጥታ ወደ ሃሳቡ እንዝለቅ፡- ዳዊት “የአንድ ወንድ ምስክርነት ከሁለት ሴቶች ምስክርነት ጋር እኩል ነው፡፡” ለሚለው ግብታዊ ማሳረጊያው ኣሳላጭ ዋቢ አድርጎ የተጠቀመው በቁርኣን 2፡282 ላይ “ከወንዶቻችሁም ሁለትን ምስክሮች አስመስክሩ፡፡ሁለትም ወንዶች ባይሆኑ ከምስክሮች ሲሆኑ ከምትወዷችው የሆኑን አንድ ወንድና አንድኛዋ ስትረሳ አንደኛዋን ታስታስውሳት ዘንድ ሁለት ሴቶች( ይመስክሩ )፡፡ ” የሚለውን ጥቅስ ነበር፡፡ ዳዊት ወሬውን ይቀጥልና ጥቅሱ ግልብ በሆነ መልኩ ከወንዶች አንጻር የሴቶችን አሰላስሎኣዊ ማነስና ጎዶሎነትን ያሳያል በማለት በአራት ነጥብ ይደመድማል፡፡ እኛ ግን በነጠላ ሰረዝ እንቀጥልና እንዲህ እንላለን፡- 1ኛ) ይህ ጥቅስ በመጀመሪያ ደረጃ የሴቶችን ሰብኣዊ ማንነት ያውጃል፡፡ ከኢስላም ብስራተ-ነጋሪት በፊት ሴቶች ከነሕይወታቻው ይቀበሩ እንደነበር ልብ ይሏል፡፡ ለምስክረነት አይደለም በቤተሰብ ውስጥ መኖራቸው በራሱ ለቤተሰቡ የውረደት ማቅ መልበስ ምክንያተ-ጋኔል ተደርገው ይታሰቡ እንደበርም ያክሏል፡፡ በሴት ልጅ መወለድ የተበሰረ ኣባት “እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል” ቁር 16/58፡፡ሴት ልጅን ምንም ቁም-ነገር የሌላት የስራይ ውጤት ብቻ ኣድርጎ የያኔው ዘመን ሰው ከልቡ ያምናል፡፡ ምግባሯ ሁሉ በኣልቦ (በምንም) የሚባዛ በትልቅ ሰው ኣእምሮ የሚላወስ ግዕዘ-ህጻን (የህጻን ስራ) ተደርጎ ነበር ሚታሰበው፡፡ የዚህችን እንደ ጥንታውያኑ ኣባባል “ማራኪ መቅሰፍት” ፍጡር ሰብዓዊነት ደረጃን ኢስላም ፈጽሞ ፍትሃዊ በሆነ መስፈሪያዊ ሰፍሯል፡፡ “በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ…” በሚል መለኮታዊ ቃል በመታጀበ ከነህይወቷ ትቀበረ የነበረችዋን ምስኪን ፍጡር የእኩልነት ማማ ላይ ከሰቀለ በኋላ ለምስክርነት መጣድ የምትችል ፍጡር መኾኗንና በዘፍጥረትም ከወንዱ እኩል መኾኗን አጽንቷል፡፡ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ክርስቲያኖቹ ምዕራባውያን የድንቁርና ዘመን ውስጥ በነበሩበት ወቅት” ሴት ልጅ ህይወት ኣላትን?” የሚል መከራከሪያ ሃሳብ በመካከላቸው ይሸራሸር ነበር፡፡ ለምን ይህ ሃሳብ በነዚያ ክርስትያኖች መካከል ጥያቄ ሆነ የሚል ውልታ ካለቦ፤ መጽኃፋቸው እንደዚህ ይለናል፡- ሀ) ``ሰውም ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ ባሪያዎች እንደሚወጡ እርስዋ አትውጣ/ ዘጸአት 21/7 ወዳጄ ጥቅሱ ኣባት ሴት ልጁን ለባርነት መሸጥ እንደሚችል ፍንትው አድርጎ እንደሚያሳይ ልብ ይበሉ!፡፡ በሚሸጥበት ወቅት ግን ልጁ እንደሌሎች ባሪያዎች ከቤት መውጣት አትችልም፡፡ ስለዚህ አባት ልጁን ለባርነት ሊሸጣት ሲያስማማ ወይም ሲከጅል ከቤት እንዳትወጣ መመክርና መገሰጥ ከቻለ በቃ! በምድርም በሰማይም ኮናኒ ስለሌለበት እዳው ገብስ ነው፡፡ ለ) ``ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት…ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ መርገምዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት`` ዘሌዋውያን 12/2-5 ገና ከውልደተ-ታሪክ ጀምሮ ሴት ከወንድ በግማሽ እንደምታንስ ክርስትያናዊው መጽሃፍ ይናገራል፡፡ ወዳጄ እነዚህ የ“ሰብዓ-ሰገል” ጥቅሶች ቁርኣን ውስጥ ሰፍረው በነበር ወገኖቻችን ምንኛ እንደሚዘፍኑብን አስበውታል? ጉዳዩ ግን “አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል” ነውና ስለኢስላም በዋሹ ቁጥር ጉዳዩ ከነሱ ዘንድ ያለ እውነታ ኾኖ ያገኙታል፡፡ “ሴት ከወንድ በግማሽ ታንሳለች” በሚል ኢስላም ላይ ከእምኃበ-አልቦ (ካለምንም መረጃ) የሚለጥፉት የእብለት ዜና እነሱ ዘንድ የሚዘመር የ”መዳኛ” መዝሙር ኾኗል፡፡ ኣቤት!!! ሰው በቀጥታ ከራሱ ጋር ሲጻረር እንዴት ይሰቀጥጣል!!! ወንድ የወለደች ሴት አንድ ሳምንት ትረክሳለች፤ሴት ከወለደች ደግሞ ሁለት ሳምንት፡፡ እንግዲህ የነዳዊት አልጄብራ እዚህ ጋር ይሰራል፡፡ ሰባት ሲካፈል ለአስራ አራት እኩል ይኾናል ግማሽ!!! ( ወዳጄ ትምህረተ-ስላቅ ያክሉል) ሐ) ``ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና:: ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ`` 1ኛ ቆሮ 14/34 ወዳጄ ይኼኛው ጥቅስ ደግሞ ሴት ልጅ ምንም ህላዌ እነደሌላት፤የመናገር መብቷን ከመነፈጓ ባሻገር መናገሯ በራሱ ነውር እንደዚሁም ህግንም የሚጻረር መኾኑን ይነግረናል፡፡ መማር ብትፈልግ በመጀመሪያ ባል ሊኖራት የግድ ነው፡፡ ከዚያም ባሏ በመማሯ ደስተኛ ከሆነ ይፈቅድላታል፤ ካልፈቀደ ግን መማር ህልሟ ብቻ ሆኖ ይቀራል፤ ከዚያስ…? ከዚያም ባሏ የሚላትን ብቻ እየሰማች በመኃይምነት ትኖራች፡፡ ጥቅሱን በተን በማድረግ ሴት ልጅ ከአስራ ስምንት ዓመት በፊት እንድታገባ ከሚከለክለው “ዘመናዊው” ህግ ጋር ሲያዛምዱት፤ቢያንስ አስራ ስምንት ዓመት እስኪሞላት መማር እንደማትችል ይረዳሉ፡፡ ዛሬ በክርስትና የመናገር፣ የመማርና እንደ ልብ የመንቀሳቀስ፣ የፈለጉትንም የመልበስ ነጻነት እንዳገኘች የምታስብ እንስት ሁሉ ይህንንና መሰል ጥቅሶችን ብታነብ፤ በምታስበውና በክርስትና መካከል በጥቁርና ነጭ መካከል ያለ ለማጠጋጋት እንኳ የማይመች ልዩነት መኖሩን ትገነዘባለች፡፡ እያወቀች ከሆነ ደግሞ “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ነውና ሆድም ጾሙን እንደሚያድር፤ ዶሮ ፍትፍቱም ቅዥት ብቻ እንደሆነ ለኮናኒ-በፍትህ ኣእምሮ በድቅድቅ ጨለማ እንደሚንቦገቦግ የኣስራ ሶስት ቀን ሙሉ ጨረቃ ይኾንባታል፡፡ መ) ``ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።`` 1ኛ ቆሮ 7/39 ``ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ`` 1ኛ ቆሮ 11/3 እነዚህ ሁለቱ የመጨረሻ ጥቅሶች ሴት ልጅ ከባልዋ ጋር መኖር ቢያቅታት እስኪሞት ድረስ መፋታት እንደማትችል ከነገሩን በኋላ የሴት ራስ ወንድ እንደኾነም ያጸናሉ፡፡ ክርስትያን እንስቶች ሆይ! ለመሆኑ እነዚህ ጥቅሶች በናንተ ላይ ቢተገበሩ ትፈቅዳላችሁን? ስለእናንተ ሚያስቡት ባሎቻችሁ፤ የገባችሁበት ትዳር ባይጥማችሁ መፋታት የምትችሉት ባሎቻችሁ ሲሞቱ… ወዘተ፡፡ እውነት ነው! የትኛዋም ክርስትያን ሴት ባሏ በራሷ ላይ የአንበሳውን ድርሻ እንዲይዝ አትፈቅድም፡፡ ኣሳቢ ኣእምሮ እንደሌላት ሁሉ ኣእምሮ ሆኖ ሚያስብላት ባሏ እንዲሆን አትመርጥም፡፡ መለኮታዊ አድርጋ የያዘችው መጽሃፍ ግን ተቃራኒውን ይደነግጋል፡፡ በየትኛውም እምነት ውስጥ ያሉ ምዕምናን በመለኮታዊ ህግጋታቸው ውስጥ መኖር ካልፈቀዱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህግጋቱን እንደማይፈልጉ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ ታዲያ ወዳጄ እነዚህና መሰል ጥቅሶች ናቸው ኣንድ ወቅት ክርስትያኖቹን ምዕራባውያን “ሴት ልጅ ህይወት ኣላትን?” ብለው እንዲጠይቁ ያደረጋቸው፡፡

  • 2 авг.1 165363

    መቼም ጠላት ከሩቅ አይመጣም … ከሰሞኑ በሐገራችን ኢትዮጵያ ሐገራዊ ምክክር መጀመሩን ድፍን ሐበሻ ያውቀዋል፡፡ ታዲያ ይሕን ውይይት ተከትሎ ኹሉም አለኝ የሚለውን ጥያቄ ወደ መድረኩ ይዞ ቀርቦ እነሆ ውይይቱ እንደተቀጣጠለ አለ፡፡ እኛም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለዘመናት የተነፈግነውን መብታችንን አግባብ ባለው መልኩ በተወካዮቻችን አማካኝነት ለውይይቱ በሚመጥን መልኩ እያቀረብን እንገኛል፡፡ ለውይይት ከቀረቡ ሐሳቦች መካከል የኒቃብና የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ምን መምሰል አለበት የሚለው ይገኙበታል፡፡ እንደሚታወቀው የኒቃብ ጉዳይ በየትኛውም የመንግስት ስርዓት ውስጥ በስጋት የሚታይና በተደጋጋሚም እህቶቻችን ከተምሕርትና ከስራ ገብታቸው የሚፈናቀሉበት አጀንዳ ነው፡፡ የማትሪክ ተፈታኝ እህቶቻችን ጭምር ኒቃብ ካላወለቁ በስተቀር ለፈተና መቀመጥ እንደማይችሉ በማስገደድ ጭምር እየተነገራቸው በየዓመቱ ኒቃባቸውን እያወለቁ እንደሚፈተኑ ይታወቃል፡፡ ታዲያ የዚህ ዘመን ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ሊፈጽማቸው ከሚገቡ የቤት ስራዎች መካከል አንዱ የኒቃብ ጉዳይ ሲኾን ይኸውም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥያቄ ኾኖ እንዳይነሳ ማድረግና ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ከመኾኑ ባሻገር የምርጫና የፍላጎት ውጤት ስለኾነ አንዲት ሙስሊም ሴት በምርጫዋና ፍላጎታ የምታደርገውን ነገር አይኾንም፣ መልበስ የለብሽም ማለት በእርሷ ነጻ ምርጫና መብት ላይ ጣልቃ መግባት እንደኾነ አስረግጦ ማሳየትና ማሳመን ነው፡፡ ከዘመን አቆጣጠር አኳያ ያለውንም ኦርቶዶክሳዊ አካሄድ ስናይ የቀድሞ ክርስቲያናዊ ነገስታት ጉዳዩን ሃይማኖታዊ በማድረግ ዓመተ-ምህረት የሚል በቀጥታ የክርስቶስን ውልደት ከአዳም “የተወረሰው” ኃጢኣት በምህረት እንዲሻር የተረገበት ክስተት እንደኾነ በማመን መላው ኢትዮጵያዊ ያንን ወዶም ኾነ ጠልቶ እንዲቀበል ለማድረግ የተቀመረ እንደኾነ በትክክል ይታወቃል፡፡ ታዲያ ወዳጄ መሰል ወልጋዳ የታሪክ ትውፊቶችና ሕሳቦዎችን ለማቃናት ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በየትኛውም አጋጣሚ ድምጹን ለማሰማት ወደ ኋላ ባይልም በጣም በሚያሳዝን መልኩ ከኛ ወገን የኾኑ የብብት እሾኾች ጥያቄዎቻችን ጮክ ብለው እንዳይሰሙ የማፈን ስራ ሲሰሩ ማየታችን ነው፡፡ ከእለታት የኾነ ቀን አንድ ግለሰብ በኾነ አጋጣሚ የአባይ ወንዝ ተሟጋች ነኝ ብሎ ወደ ሚዲያው ብቅ አለ፡፡ ግብጾቹ በአረብኛ የሚያቀርቡትን ዛቻና ቀረርቶ በአማርኛ እየተረጎመ “ይኸውላችኹ እንዲህ… እንዲያ እያሉ ነው” እያለ እጅግ ኢትዮጵያዊነቱንና ተቆርቋሪነቱን ሊያሳየን በሚችለው መንገድ ኹሉ ሲያሳየን ቆየ፡፡ መንግስትም ለዚህ ጉምቱ ተርጓሚ በአደባባይ ዕውቅናውን ቸረ፡፡ እኛም ሐገረን እስከጠቀመ ድረስ ዕውቅናው ምንም አልከፋንም፡፡ ይሕ ግለሰብ ታዲያ ዕውቅናው የፈጠረበት ሙቀት ይኹን ወይም ከጀርባ እንደ ፈረስ “ቼ!” የሚለው ይኑር ፍጹም ዕርግጠኛ ባልኾንበት ኹኔታ ከዕውቅናው ማግስት በተለያዩ መድረኮቹ ላይ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የሙስሊሙን ጥያቄ ወደ ኋላ የሚጎትቱ ሓሳቦችን መምዘዝ ጀመረ፡፡ ሰሞኑን እየተደረገ ባለው ሐገራዊ ውይይት እንኳ የኒቃብ ጉዳይ ያን ያሕል አሳሳቢ እንዳልኾነና ዓመተ-ምሕረት የሚለውም አቆጣጠር በራሱ ኢየሱስ ለኛም ነብይ ስለኾነ ችግር ያለው አይመስለኝም የሚል በትክክል ንፍቅናን ያዘለ የሚመስል ቃል ሰጥቷል፡፡ ድሮ ነው አሉ፡፡ አንድ ግለሰብ ቆዳ ፋቂ ቡዳ ነው በሚል በሰፈሩ ሰዎች ይጠረጠር ነበር፡፡ የኾነ ቀን ሰው አላየው መስሎት ከማሳው ሜዳ ላይ ጥጉን ይዞ ጣውላ ዘርግቶ ቆዳውን ሲያርብ (ሲፍቅ) ሰዎች በግላጭ አገኙት፡፡ ከዚያም የዘላለም ማስታወሻ እንዲኾን “ድሮም ሲሉኽ ቡዳ ቆዳ ይዘኽ ከሜዳ” ብለው ተረቱበት፡፡ በአጭሩ የምትጠረጠርበትን ጉዳይ ይፋ አወጣኸው እንደማለት ነው…ግልጽ ነው ወዳጄ? የኣባይ ተሟጋቻችን ከሚያነሳቸው ሐሳቦች አኳያ ድሮም ስንጠረጥረው ከነበረበት ሜዳ እንዳገኘነው ዕርግጠኛ ነን፡፡ ግን ደግሞ ለነማን እየሰራ ነው? የሚለውን ፍርድ ለሕሊናዎ በመተው ግለሰቡ በፍጹም እንደ ዋዛ የምናየው ሰው እንዳልኾነና እሱን በተለያዩ ሚዲያዎች የምትከታተሉ አድናቂዎቹ ሙስሊሞች ማንን እንደምትከታተሉ ልታውቁና ጥንቃቄም ልታደርጉ እንደሚገባ አምናለኹ፡፡ https://t.me/E_M_ahmoud

  • 30 июл.1 341125

    без подписи

  • 29 июл.1 60685

    سوء الظن بالناس-أربع قواعد في العلاج https://youtube.com/watch?v=oafV2JHN0bU&si=OmXlUWh0OykmImI8

  • 27 июл.2 276415

    ስም ... ሰዎች የሚሰጡን ስሞች ብዙውን ጊዜ በአወንታዊም በአሉታዊም ጎኑ ግነት ሊኖረው ይችላል። ችግሩ ሰዎች ለምን በዛ ልክ ለጥጠው ዐዩን ሳይኾን እኛ የተሰጠንን ስም እንዴት አሜን ብለን ተቀበልን ነው። ባልዋልንበት ያዋሉንና ማንነታችንን በእሪያ ስጋ ልኬት አርክሰው ከአደባባይ ያወጡንን ሰዎች ተከትለን መናገርና ስማችንን ለማስተካከል መሞከር ብዙውን ጊዜ ነጥብ ያስጥለናል እንጂ ስኬታማ አያደርገንም። በመጀመሪያ መታወቅ ያለበት ስማችንን እያጠፉ ያሉ አካላት ከዚህ ቀደም አላወቅናቸው ኾኖ ወይም ይሕ ክፉ ችሎታቸው የሚታይበት "መልካም" አጋጣሚ ሳይፈጠርላቸው ቀርቶ እንጂ በስም ማጨቅየት ከፍ ያለ ተመኩሮ ያላቸው ናቸው። ተመኩሮ እንኳ ባይኖራቸው ስም ማጠልሸት ተፈጥሮአዊ መክሊታቸው ናት። ከነዚህ ሰዎች ፊት ራስን ለመከላከል መቆም ከዕብድ ውሻ ፊት ከመቆም እኩል ነው። ስማችንን ላጠፉ ኹሉ ስራ ሰርተን እነርሱ እንዳሉት እንዳልኾን ማሳየት ከቃላት በላይ ፈጣንና መቅሰፍታዊ ምላሽ ይሰጥልናል። በተመሳሳይ መልኩ አጓጉል ስም ከሚያቀልሙ ሰዎችም መጠንቀቅ እጅግ ያስፈልጋል። ያልኾነውን ናችኹ እያሉ የሚያንቆለጳጵሱን ኹሉ በዱምዱም ሰንዳ እያረዱን እንደኾነ ልብ ይላል። አንድ ሰው ምንም ያህል የአንበሳ ልብ ቢኖረው እንኳ ዳኛ ፈራጅ ሳይኾን በአውጫጭኝ ፊት ስላስቀመጡት ብቻ በተካሳሾች መካከል ላሸማግል አይልም። በተመሳሳይ መልኩ የሌለውን ስም ሰዎች ሲሰጡት ዕያየ የሚቀበልም እንደዚያው ነው። ዛሬ ላይ ብዙዎቻችን ሰዎች እጅግ ባገነኗቸው "ስብዕናዎቻችን" በጣም ከፍ ብለን ዕየታየን ነው። በትክክል ኾኖ መገኘት እኛ ለመታየት እንኳ ባንፈቅድ ገዝፈን እንድይታይ ያደርጋል። ወትሮውንም በትክክል ትልቅ ማንነት ያላቸው መታየትንም መታወቅንም አይፈልጉትም። በአንጻሩ መታየትና መታወቅ ግቡ የኾነ ከድሬዳዋ ወደ አ.አበባ የሚጓዝ ባቡር በመጥለፍ አውስታራሊያ ልሂድ በሚል ከንቱ ምኞት ዕውቅናን ይፈልጋል። ሰው ዱንያ ላይ ጥሎት ለሚኼደው ስሙ በዚህ ልክ ከሚታትር ስራውን ከአላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) ፊት አሳምሮ መሻገርን ቢያስብ ዱንያዊ ስሙ አምሮ ሰዎች ልብ ውስጥም ቦታን ባገኘ ነበር። إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَيَجْعَلُ لَهُمُ الرَّحْمَٰنُ وُدًّا https://t.me/E_M_ahmoud

  • 24 июл.1 74138

    አንድ ሰው ከሚሰጥኽ ስጦታዎች ኹሉ በላጩ ከአላህ ቃል ከቁርአን በላይ ላይኖር ይችላል። ወዳጄ NB ለውድ ስጦታኽ አመስግኛለኹ

  • 24 июл.1 64915

    без подписи

  • 20 июл.2 106365

    ይሕ ከላይ የለጠፍኹት ጋዜጣ በሂጅራ አቆጣጠር ረመዷን 28/1415 በሳውዲ ዐረቢያ ታትሞ የወጣ ነው። ያኔ በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል (هيئة أمر بالمعروف والنهي عن المنكر) የሚሰኝ ተቋም በሐገሪቱ ላይ በሙሉ ስልጣን ይንቀሳቀስ ነበር። እዚህ ጋዜጣ ላይ እንደምናነበው ይሕ ተቋም ሪያድ ከተማ ላይ ከፈጅር ሰሏት መስጂድ የሚቀሩትን ሰዎች ተከታትሎ ችግራቸውን በየ አራት ወር በሚያደርገው ውይይት ለመቅረፍ እንደ ወጠነ ያሳያል። ይሕ ባለ ሙሉ ስልጣን ተቋም ዛሬ ላይ ሕልውና የለውም። ተቋሙ አይደለም ቢን ሰልማን በተለይ ሪያድና ጅዳ ላይ የሚሰራቸውን ስር ነቀል ጸረ_ዲን እንቅስቃሴዎችን በአደባባይ የሚቃወም ካለ እናቱ የወለደችው ጀግና መኾን አለበት። ለመቃወም የተንደረደሩትን ወይም ከኔ በተጻራሪ ይንቀሳቀሳሉ ብሎ ያሰባቸውን ኹሉ ቢን ሰልማን ያለ ምንም ርሕራሔ መቀመቅ ውስጥ ከቶአቸዋል። አነስ ቢን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሐዲስ መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲናገሩ ፦ "ጌታችኹን እስክታገኙ ድረስ ከየትኛውም ሸረኛ ዘመን ቀጥሎ የሚመጣው ዘመን የባሰ እንጂ የተሻለ አይኾንም" በማለት ማሳሰባቸውን ልብ ይሏል።

  • 20 июл.1 70393

    ما مِن عامٍ إلَّا والَّذي بعدَهُ شرٌّ منهُ حتَّى تلقَوا ربَّكم أنس بن مالك رضي الله عنه

  • 18 июл.2 130566

    ዛሬ ማለዳውን ከአዲስ አበባ የኾነ ቀበሌ ላይ ተከሰትኹ። ከቦታው እንደ ደረስኹ ተመሳሳይ ብዙ ሕንጻዎች ነበሩና ሕንጻውን መለየት አልቻልኹም ነበር። ስልክ ደወልኩ...በተነገረኝ ምልክት ተመላክቼ ሕንጻውን አገኘኹት። ዘልቄ ስገባ ዘበኛው ክረምት ባቀጨጨው ድምጽ "ምን ነበር? ማንን ፈለጉ? አለኝ" "እዚሕ .... " ብዬ የመጣኹበትን ጉዳይ ገለጽኹለት። ዘበኛውም ለምን እንደመጣኹ ሲገባው አክብሮት በታከለበት ድምጽ "እሺ ወደ ውስጥ ይግቡ...አራተኛ ፎቅ...". "ክረምቱ አስቸጋሪ ነው አይደል?..." የሚል ርዕስ ዘለል ሓሳብም አነሳልኝ። እጁ ላይ በያዘው በትር እየጠቆመ ሽቅብ ፎቁን እንደወጣ ነገረኝ። ወደ ላይ ፎቁን እያቀናኹ "ጉድ! እዚህ ቦታ ላይ በዕድሜ የገፋ ሽማግሌ፣ወይም ጉልበቱ ላይ ሕመም ብጤ ያለው ሰው ቢኾን ይሕንን ፎቅ እንዴት ሊቃና ነበር? ብዬ አሰብኹና ድንገት ኸሊል ጂብራን "Youth and Age" በሚለው የፍልስፍና ጽሑፉ ወጣትነትና እርጅናን የገለጸበት ድንቅ አባባል ትዝ አለኝ፦ "The difference between my youth which was my spring,and these forty years,and they are my autumn, is the very difference that exists between flower and fruit" "የጸደይ አበባ የነበረው የወጣትነት ዕድሜዬ እና የመኽር ወቅት የኾነው የዐርባዎቹ ዕድሜዬ በአበባና በፍሬ መካከል ያለ ልዩነት ብቻ ነው" በማለት ኹለቱንም ዘመኖቹን ሳያማር ወጣትነቱንም በከንቱ ሳይናፍቅ ኹለቱም የራሳቸው ውበት እንዳላቸው ይናገራል። ዕውነት ነው አበባ ሲያዩት ደስ የሚል ነው። መዓዛውም ያውዳል። ልክ እንደ ጽጌሬዳ እሾኽ ቢኖረውም አበባነቱን እንጂ ቆንጥርነቱን አስቦ ከጽጌሬዳ የሚሸሽ የለም። ፍሬ ደግሞ የሚበላውን ቁስ የሚይዝ፣ በአበባነት ዘመን ብትንትን ብለው የነበሩ ነገራት ሰብሰብ ብለው ጥበብ የሚኾኑበት ወቅት ነው። ኹለቱም ዘመናት ወጣትነትም ዕርጅናም የሕይወት ዑደቶች ናቸው። በሞናሊዛ ልኬት ሸይጣንን እንኳ የሚፈታተን ውበት ያላት እንስት ከኾነ ዘመን በኋላ ያላትን የዕርጅና ማንነት መቀበል ያቃታት እለት መሞት ትጀምራለች። የብዙ ሴቶች የሞትም ደረጃ የሚለካው ዕርጅናን ለመቀልበስ በሚኼዱበት ርቀት ነው። ፊታቸው ላይ የሚያፈሱት ዘመናዊው ጥቀርሻ (ሜካፕ)፦ ጸጉር ማቅለሚያና የሚጨምሩት የሚቀንሱት መብዛቱ ወጣትነትን በመፈለግ ውስጥ ያለ ሞት ነው። ራስ ዳሽንን እንደ ሜዳ እየሮጠ ይመላለስበት የነበረ የያኔው ወጣት ዛሬ ጉልበቱ ዝሎ ደረጃ እንኳ በግድፍ ሲወጣ እያየ በድሮ በሬዬ ለምን ማረስ ተሳነኝ ያለ ቀን መሞት ጀምሯል። የዛሬዎቹ ጎልማሶች ጡንቻቸውን እንደምንም አሳብጠው በንቅሳት ብራና ላይ የተሳለ የተፋሰስ ካርታ የሚመስል ነገር አስለው፣ "በምንሼ ነው" እጅግ አስቀያሚ ቋንቁኛ (ቋንቋ የሚመስል ቋንቋ ያልኾነ ) ጸጉራቸውን ቆነዳድረው ወጣትነትን ሊመሉስ ሲሰቃዩ ማየት ቻይንኛን በገጠሩ አማርኛ ቃና ከማውራት በላይ ዘገናኝ ነው። ወዳጄ ወደድንም ጠላንም ጊዜ ሲያልፍ አይደለም ጉልበትና ውበት ይቅርና የተማርነውም የሸመደድነውም ኹሉ ከመሰረታዊ ፍልስፍናው ውጪ ይረሳል። ምንም ጉልበቱ ቢበረታና ሌት ከመዐልት ዶፉን ቢያወርደው ክረምቱ እንደኹ ማለፉ አይቀርም፤እኛም የኾነ ቀን እናልፋለን። https://t.me/E_M_ahmoud

  • 13 июл.2 235364

    የሰሞኑ የኬጂ ግራጁዌሽን .. መቼም ቀን ሄዶ ቀን ሲተካ የማናየው የማንሰማው ጉድ የለም፡፡ ድሮ ድሮ አንድ ተማሪ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ሲጨርስ ቤተሰቦቹ ደስታቻውን አጋፋሪ ጠርተው ድግስ በማብላት ያከብሩ ነበር፡፡ የቀድሞው ግራጁዌሽን ድግስ በትክክልም የኾኑ ዕንቅልፍ የታጣባቸው አድካሚ የሕይወት ምዕራፎች ታልፈው፣ ከዩኒቨርሲቲ የካምፕ ሕይወት ወደ ቀጣይና እረፍትም ወዳለበት የተሻለ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ድልድይ ስለነበር፣በትክክለኛ ቦታው የሚደረግ ሷደቃ ነበር፡፡ ፊደል እየቆጠረና በመሐከልም እየተኛ ከኬጂ ወደ ግሬድ የተላለፈን አንድ ተማሪ ምናልባት የተሻለ ንቃት ኖሮት ትምሕርቱን እንዲቀጥል ለማድረግ መጠነኛ የቤት ውስጥ መሰናዶ ማድረጉና በተቀረው ገንዘብ ደግሞ በዙሪያችን ላሉ ድሆች ምጽዋት ማድረጉ ተመረቀ ላልነው ሕጻን ትልቅ ማስታወሻ አዘል ትምህርት ይኾን ነበር፡፡ በተቃራኒው ግን የመቶ ሺህ ብሮች ስጦታና ድንኳን ተጥሎ፣ አሞራ የሚያወርድ ድል ያለ ድግስ ተደግሶ፤ድግሱ አልበቃ ብሎ በሙሽራ ልኬት ከሽንጠ ረዥም ሊሞዚን ውስጥ ጨቅላው አንገቱን አውጥቶ ዕጁን እያወዛወዘ ከተማ ላይ ሽር ብትን ሲል ማየት፣ ጉዳዩ የጉራና የታይታ ጥግና ጠርዝ ካልተባለ በቀር ምንም ሊባል አይችልም፡፡ እንዲያው እንዴት እንዴት ብንለካካ ነው ጃል በዚህ ልክ ገንዘብ ሰበሰብኹ ያለ ኹሉ ነጋሪት እየጎሰመ “በሃይ ሎጋ ሆ”፣ በክላክስና “በዓልምሽ ዛሬ ነው ዛሬ” የልጁን ፊደል ቆጠራ እንደ ሰርጋና ምላሽ የሚያከብረው? እናንት ትምክህተኞች አይገባችኹ ኾነና ነው እንጂ እኛንም እኮ ከእንግዲህ ኒካሕ ሲታሰር እንኳ ብናይ ሰርግ ነው ወይስ ግራጁዌሽን? ብለን እንድንጠራጠር እያደረጋችኹን ነው። ገና ጎዞውን “ሀ” ብሎ ላልጀመረ ጨቅላ በዚሕ ልክ ያለንን ዕወቁልን በሚመስል መልኩ የሐብት ብክነት ሲፈጸም መንግስት ዝም ሊል አይገባውም ነበር፤ ይልቁንም ብዙኃኑን ከርቸሌ ለማስገባት አጓጉል ሕግ እንዳረቀቀ ኹሉ ለዚሕም ብልግና የኾነ ሕግ ሊያበጅለት ይገባ ነበር፡፡ በዚሕ የሚሊዮኖች በቀን አንዴ መቀመስ እንኳ ተረት በኾነበት ሐገር ውስጥ ነገ ለኛ ይኹን አይኹን ጨርሶ ዕርግጣኛ ሳንኾን በቀቢጸ ተስፋ ብቻ እየኖርን ባለንበት ግልጽ ተጨባጭ እነ አባ ጉርምርሜ ገንዘባቸውን ሰፍተው መልበስ ከጀመሩ፣እንግዲያውስ ሳናየው ቀርተን እንጂ ደጃል ከደጃፋችን ቆሟል!!! ወዳጄ ኹላችንም በዘጠኝ ወር ተወለድን፤ከኛ መካካል አንድስ እንኳ በዘጠኝ ዓመት የተወለደ የለም፡፡ ኹላችንም ሰብዓዊ ስጋ የለበስን በተፈጥሮ ሕግ የምንዳኝ፣ ጅማሮአችን ምንም የነበረ መጨረሻችንም ትቢያ ኾኖ እስከ ትንሳኤ የሚቆይ እንጂ ከኛ መካከል በሰው አምሳል የተከሰተ መስሎ የመጣ መልዓክ የለም፡፡ ታዲያ ወዳጄ ይሕ እጅግ ቅጥ ያጣ ጎፈሬ ማበጠርና አጓጉል ቀረርቶ በመካከላችን ሐብት በቅጡ እየተሸከረከረ እንዳልኾነ፣ኹላችንም እኩል ተጠቃሚዎች እንዳልኾንና ጥቂቶች በሚሊዮኖች ተሰፍረው በኛ ላብ እየወዙ ያሉበት ዕውነታ ላይ እንደ ደረስን ያሳያል፡፡ እነ አባጉርምርሜ ለሰከሩት ድሃው የሚንገዳገድበት ዕውነታ ላይ እንዳለን አኹን በደንብ የገባን ይመስለኛል፡፡ በቀጣይ ሌላ ሰማያዊ ተዓምር እስካልመጣ ድረስ የነርሱ ስካር ከፍ ባለ ቁጥር በየገደሉ እስከ ወዲያኛው ወድቆ የሚያሸልበው ድሃ የትየለሌ እንደሚኾን ግልጽ ነው፡፡ https://t.me/E_M_ahmoud

  • 11 июл.2 129318

    ከስነ ልቦና አስተምህሮዎች ... በጣም ከባድ ቁጣ እጅግ መልካም በኾኑ ሰዎች ላይ ሊታይ ይችላል። እነዚህ ሰዎች እስከ ጥግ ድረስ ሄደው ይታገሳሉ፤ያልፋሉም። ትዕግስታቸው የተንጠፋጠፈ ጊዜ ምንም ባያደርጉም ላይመለሱ ግን ጥለው ይሄዳሉ። ስለዚህ ወዳጄ ብዙ ስናጠፋ ዝም የሚሉን ሰዎች ሳይሰማቸው ቀርቶ ወይም ስላላወቁብን እንዳይመስለን። ይልቁንም ጊዜ ሰጥተው ኹኔታችንን በጥንቃቄ እያጠኑ እንደኾነ ልብ ይሏል። በዚህ ዝምታቸው ውስጥ እያሉ ከነርሱ በኩል ምንም የባሕሪ ለውጥ አናይም። እንደ ኹሌውም ሊያገኙን ይሞክራሉ። እንደ ኹሌውም ሰላማችንና ጤንነታችን ሊያሳስባቸው ይችላል። በስተመጨረሻ ግን "ኦሮማይ" ብለው ከኛ ጋር የከፈቱትን ዶሴ ለዝንተ_ዓለም ያቃጥሉታል። በነዚህ ሰዎች የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መፍረድ እጅግ ያስቸግራል። ምክንያቱም ኹላችንም ተራ ሰብዓዊ ባሕሪ እንጂ የመላዕክት ወይም የነብያት ማንነት የለንም። ታዲያ ወዳጄ የስጋ ዘመድም ቢኾን እኮ ዕድሜ ልክ ለኛ ምክንያት እየሰጠና ጥፋታችንን እያለፈ አይዘልቅም። የኾነ ቀን ይቆርጥለታል። የተቆረጠ ነገር ደግሞ ዳግም በኾነ ተዓምር እንኳ ቢቀጠል፣በጭራሽ እንደ ወትሮው አያምርም። ሊጤን የሚገባው ነገር ኹሌም ነገራት በኾነ አጋጣሚ መሰበራቸው ሳይኾን ዳግም መጠገን አለመቻላቸው ነው የመጨረሻ ሐዘን የሚኾነው። Thanks to Alan Paton in his novel "Cry, the Beloved Country" he said፦ "The tragedy is not that things are broken. The tragedy is that things are not mended again" ... https://t.me/E_M_ahmoud