ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Статистикаዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 6 283
- 1/48двое суток
- 7 200
- 1/72трое суток
- 7 765
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
የአምልኮ መገዛት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ "የባሕርይ መገዛዛት"Ontological subordination" ማለት በባሕርይ የማይመሳሰሉ ሆነው ነገር ግን በባሕርይ አንዱ ከሌላው ስለሚበልጥ በመካከላቸው ገዥ እና ተገዥ አለ። ለምሳሌ፦ ሰው እና እንስሳ በምንነት የተለያዩ "ባሕርይ"Essence" ስላላቸው ሰው ገዥ እንስሳ ተገዥ ነው፦ መዝሙር 8፥6 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት። πάντα ὑπέταξας ὑποκάτω τῶν ποδῶν αὐτοῦ, እዚህ አንቀጽ ላይ ለመገዛት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ሲሆን ገዥው ሰው ተገዥው በጎችን፣ ላሞችን፣ ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርን ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ ነው፦ ዘፍጥረት 1፥28 የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ "ግዙአቸው"። መዝሙር 8፥8 በጎችን፣ ላሞችን፣ ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርን ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ። እንስሳ ሰውን የሚገዛው የባሕርይ ቢሆንም የአክብሮት መገዛት እንጂ የአምልኮ መገዛት አይደለም። ነገር ግን ኢየሱስ ፍጡር ስለሆነ ለአምላክ የሚገዛበትን ለማሳየት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ነው፦ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን "አምላክ" ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት "ይገዛል"። ὅταν δὲ ὑποταγῇ αὐτῷ τὰ πάντα, τότε καὶ αὐτὸς ὁ Υἱὸς ὑποταγήσεται τῷ ὑποτάξαντι αὐτῷ τὰ πάντα, ἵνα ᾖ ὁ Θεὸς πάντα ἐν πᾶσιν. "ሆ ቴዎስ" ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ ሁሉን ላስገዛለት አምላክ ይገዛል፥ ለአምላክ የሚደረግ መገዛት የባሕርይ መገዛት ሲሆን የአምልኮ መገዛት ነው፦ ያዕቆብ 4፥7 እንግዲህ ለአምላክ "ተገዙ"! ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል። ὑποτάγητε οὖν τῷ Θεῷ· ἀντίστητε δὲ τῷ διαβόλῳ, καὶ φεύξεται ἀφ’ ὑμῶν· እዚህ አንቀጽ ላይ "ተገዙ" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ነው፥ ስለዚህ ኢየሱስ በምንነት ሰው፣ የሰው ልጅ፣ ፍጡር በማንነቱ ነቢይ፣ መልእክተኛ እና መሢሕ ስለሆነ ለአምላኩ የሚገዛው መገዛት የአምልኮ መገዛት ነው። ኢየሱስ በምድራዊ ቆይታው አምላኩን ሲለምን፣ ሲጸልይ፣ ሲሰግድለት፣ ሲጦም እና ሲፈራው ከማየት ባሻገር አሁን ላይ ሰማይ የአምላኩ አገልጋይ ነው፦ ዕብራውያን 8፥2 እርሱ በመቅደስ "አገልጋይ" ነው። τῶν ἁγίων λειτουργὸς እዚህ አንቀጽ ላይ "ሌይቶሬዎርጎስ" λειτουργός ሲሆን የግሥ መደቡ "ላትሬኦ" λατρεύω ነው፥ "ላትሬያ" λατρεία ማለት "አምልኮ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ በሰማይ ባለው መቅደስ "አምላኪ"(አገልጋይ) ሰለሆነ ሰማይ ላይ "አምላካችን" እያለ የሚናገርለት አምላክ አለው፦ ራእይ 19፥5 ድምፅም እንዲህ ሲል ከዙፋኑ ወጣ፦ “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! "አምላካችንን" አመስግኑ”። καὶ φωνὴ ἀπὸ τοῦ θρόνου ἐξῆλθεν λέγουσα Αἰνεῖτε τῷ Θεῷ ἡμῶν, πάντες οἱ δοῦλοι αὐτοῦ, οἱ φοβούμενοι αὐτόν, οἱ μικροὶ καὶ οἱ μεγάλοι. "አምላካችን" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ከዙፋኑ የወጣው "አምላካችን" የሚል ድምፅ በዙፋኑ መካከል ካለው ከኢየሱስ የወጣ ድምፅ ነው፥ "በዚያን ጊዜ" ማለት በሚመጣበት ጊዜ ንግሥና እና መገዛት ለሰው መሆኑ ቀርቶ አምላኩ ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ ኢየሱስ ለአምላኩ የአምልኮ መገዛት በግልጽ እና በይፋ ይገዛል። የእርሱ አስተምህሮት «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» የሚል ነው፦ 3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ ክርስቲያኖች ሆይ! ኢየሱስ ያመለከውን አምላክ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
በባይብል የገደለ ብቻ ሳይሆን አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደላል፦ ዘሌዋውያን 27፥17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል። ዘጸአት 21፥17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል። ኢየሱስ ሲመጣ ደግሞ ሕጉ ጠብቆ እና አጥብቆ የሞት ፍርድ የሚገባው የገደለ ብቻ ሳይሆን በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ የሞት ፍርድ እንደሚገባው አበክሮ እና አዘክሮ ተናግሯል፦ ማቴዎስ 5፥21-22 ለቀደሙት፦ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። "የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት በዘሌዋውያን 27፥17 "ፈጽሞ ይገደል" የሚለው ከሆነ "በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት "ፈጽሞ ይገደላል" ማለት ነው። እንደውም ኢየሱስ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ፦ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" ብሏል፦ ራእይ 13፥10 "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"። በተጨማሪ ሬካብ እና ወንድሙ በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ገብተው ኢያቡስቴን ገድለዉት እራሱን ቆረጡት፥ ዳዊትም ሬካብን እና ወንድሙ በዓናን አስገድሎ እጃቸውን እና እግራቸውን እንዲቆረጥ አድርጓል፦ 2 ሳሙኤል 4፥7 ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ እርሱ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት። ሳሙኤል 4፥12 ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፤ እጃቸውን እና እግራቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። ኢዮአብ እና ሠራዊቱ በአሞን ከከተማ ይኖሩ የነበሩትን የአሞን ልጆች አውጥተው በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው። ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ፦ 1ኛ ዜና መዋዕል 20፥3 በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥተው በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው። ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። καὶ τὸν λαὸν τὸν ἐν αὐτῇ ἐξήγαγε καὶ διέπρισε πρίοσι καὶ ἐν σκεπάρνοις σιδηροῖς καὶ ἐν διασχίζουσι· καὶ οὕτως ἐποίησε Δαυὶδ τοῖς πᾶσιν υἱοῖς ᾿Αμμών. καὶ ἀνέστρεψε Δαυὶδ καὶ πᾶς ὁ λαὸς αὐτοῦ εἰς ῾Ιερουσαλήμ. "ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ" በማለት ዳዊት ልክ እንደ ኢዮአብ የአሞን ልጆችን በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው፥ ግሪክ ሰፕቱአጀንት በዚህ ልክ ያስቀመጡት ሲሆን የ 2 ሺህ የኦርቶዶክስ ባይብል እና King James Version በዚህ አግባብ ተርጉመውታል፦ 1 Chronicles 20፥3 KJV And he brought out the people that were in it, and cut them with saws, and with harrows of iron, and with axes. Even so dealt David with all the cities of the children of Ammon. And David and all the people returned to Jerusalem. ነቢያችን"ﷺ" በቂሷስ ፍርድ እና ቅጣት ማድረጋቸው ነቢይ ላለመሆናቸው መስፈርት ከሆነ እንግዲያውስ በነካ አፋችሁን "ሙሴ፣ ኢየሱስ፣ ዳዊት የፈጣሪ ነቢይ አይደሉም" በሉና! ምን ይሻላችኃል ግን? ባይብል ሲጠቀስ እንቡር እና ፒርር እንዲሁ ቡፍ እና ኩፍ ከምትሉ ቁርኣንን እና ሐዲስን ለማሳጣት፣ ለማጭሸማቀቅ እና ለማሳቀቅ ፊጥ እና ቁጢጥ የምትሉትን ተዉ! አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
የነቢያችን"ﷺ" ቅጣት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا "ቂሷስ" قِصَاص የሚለው ቃል "ቋሶ" قَاصَّ ማለትም "አመሳሰለ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ማመሳሰል" ማለት ነው፦ 2፥179 ባለ አእምሮዎች ሆይ! ለእናንተም በማመሳሰል ሕግ ውስጥ ሕይወት አለላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ፡፡ وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ እዚህ አንቀጽ ላይ "ማመሳሰል" ለሚለው ቃል የገባው "ቂሷስ" قِصَاص መሆኑ ልብ አድርግ! ሰው ጤናማ ሕይወት ይኖር ዘንድ አምላካችን አሏህ ቂሷስን ደንግጓል፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጠፋል፣ አፍንጫም ያጠፋ አፍንጫው ይጠፋል፣ ጆሮም ያጠፋ ጆሮው ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል። እነዚህ ቁስሎችን በቂሷስ ይፈታሉ፦ 5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፥ ቁስሎችንም "ማመሳሰል" አለባቸው» ማለትን ጻፍን፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ማመሳሰል" ለሚለው ቃል የገባው "ቂሷስ" قِصَاص መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። መጥፎ ለሠሩ ሠዎች መጥፎ ቅጣት መቅጣት ቂሷስ ነው፥ የአሏህ መጽሐፍ ጭብጡ ቂሷስ ነው፦ 42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 26 አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአሏህ መጽሐፍ ቂሷስ ነው"። أَنَّ أَنَسًا، حَدَّثَهُمْ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ كِتَابُ اللَّهِ الْقِصَاصُ ”. የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ስለሆነ በአንድ ወቅት ነቢያችን"ﷺ" እረኛቸውን ለዑረይናህ ሰዎች እንዲንከባከባቸው ሰተዋቸው ሳሉ የዑረይናህ ሰዎች ግን በተቃራኒው የነቢያችንን"ﷺ" እረኛ እጅና እግር ቆርጠው እና ዓይን አጥፍተው በመግደላቸው ቂሷስ ተደርጎ እጃቸውንና እግራቸውንም እንዲቆረጥ እና ዓይኖቻቸውም እንዲጠፋ ተደርጓል፦ ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 62 አነሥ እንደተረከው፦ "ሰዎች ከዑክል ወይም ከዑረይናህ ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጡ፥ የመዲናህ አየር ንብረት ተጨናንቋል። ነቢዩም"ﷺ" ለእነርሱ፦ "ወደ ግመሎች ሂዱና ወተታቸውን ጠጡ እንዲሁ ሽንታቸውን ለመድኃኒት ተጠቀሙ" ብለው አዘዟቸው፥ እነርሱ ግን እረኛውን ገድለው ግመሎቹን ሰረቁ። ነቢዩም"ﷺ" ከኃላቸው ሰው ልከው እጃቸውን እና እግራቸውንም ቈረጡ፥ ዓይኖቻቸውም አጠፉ"። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم نَفَرٌ مِنْ عُكْلٍ أَوْ عُرَيْنَةَ فَأَمَرَ لَهُمْ - وَاجْتَوَوُا الْمَدِينَةَ - بِذَوْدٍ أَوْ لِقَاحٍ يَشْرَبُونَ أَلْبَانَهَا وَأَبْوَالَهَا فَقَتَلُوا الرَّاعِيَ وَاسْتَاقُوا الإِبِلَ فَبَعَثَ فِي طَلَبِهِمْ فَقَطَّعَ أَيْدِيَهُمْ وَأَرْجُلَهُمْ وَسَمَلَ أَعْيُنَهُمْ . "ሠመለ" سَمَلَ ማለት "አጠፋ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ፦ "ዓይንም በዓይን ይያዛል፥ ቁስሎችንም "ማመሳሰል" አለባቸው" ስላለ እነዚህ ሰዎች የእረኛውን ዓይን ስላጠፉ ዓይናቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፦ ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 78 አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" የእረኛውን ዓይኖች በማጥፋታቸው ምክንያት የእነዚያን ሰዎች ዓይኖች ብቻ አጥፍተው ነበር"። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ إِنَّمَا سَمَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَعْيُنَ أُولَئِكَ لأَنَّهُمْ سَمَلُوا أَعْيُنَ الرُّعَاةِ . በኪታቡ አት-ተሕሪሙ አድ-ደም ዐውድ ውስጥ "እነዚያ" የተባሉት የዑረይናህ ሰዎች እንደሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በባይብልም ቢሆን ዓይን ያጠፋ ዓይኑ እንዲጠፋ ትእዛዝ አለ፦ ዘጸአት 21፥23-25 ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፣ ዓይን በዓይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር፣ መቃጠል በመቃጠል፣ ቍስል በቍስል፣ ግርፋት በግርፋት ይከፈል።
ገድል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 2፥193 ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ "ተጋደሉዋቸው"። وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ "ገድል" የሚለው የግዕዝ ቃል "ተጋደለ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ውጊያ" "ትግል" "ፍልሚያ" "መዋጋት" "መጋደል" "ጦርነት" ማለት ነው፦ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥18 በእርሱ መልካም "ጦርነት" ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ። እዚህ አንቀጽ ላይ "ጦርነት"War" ለሚለው በግዕዙ የገባው ቃል "ገድል" ሲሆን የግዕዙ መጽሐፍ "በከመ ተነብዮ ዘላዕሌከ ከመ ትጽናዕ በኵሉ "ገድል" ሠናይ" ይለዋል። ለቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ከጥንት ጀምሮ የተሰጠ ሃይማኖት አንድ ሃይማኖት ሲሆን ለቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ስለ ተሰጠ ሃይማኖት መጋደል ይገባል፦ ይሁዳ 1፥3 ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት "እንድትጋደሉ" እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። ከጥንት የነበሩት ነቢያት በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ፦ ዕብራውያን 11፥34 በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። "ኢትዮጽያዊ ቄርሎስ" በሚል ማዕረግ የሚጠራው የሥነ መለኮት ምሁር አቦ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሃይማኖትን በካዱት ሰዎች ላይ ያለው ብይን በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን የሞት ፍርድ እንደሆነ ተናግሯል፦ መጽሐፈ ምሥጢር 2፥28 "እነሆ ሃይማኖትን በካዱት ላይ በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን የሞት ትእዛዝ ወጣ"። መጽሐፈ ምሥጢር 2፥29 "የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌሜንጦስን፦ "ፍጽምት ስለምትሆን ሃይማኖት "ሰይፈህን መዘህ በኢየሱስ ክርስቶስ የማያምኑትን ከሀዲዎች እና ጨካኞች በብረት ሰይፍ ተዋጋ" አለው"። መጽሐፈ ምሥጢር 2፥35 "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንን እንድናነሳት እና እንድናጸናት ሥልጣንን አገኘን፥ ይህንንም የተላለፈ ሰይፍ ይለፍበት ብለው አሜን ወአሜን"። ፍጽምት ስለምትሆን ሃይማኖት የብረት ሰይፍን መዞ መጋደል በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን የታዘዘ መሆኑን አበክሮ ይገልጻል። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ዓለም እስኪሰማና እስኪስማማ ድረስ ጂሃድ በሐቅ እና በባጢል መካከል ያለ ትግል ነው፥ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እውነት ለማንገሥ ሐሠትን ለማርከሥ መጋደል ግዴታ ነው፦ 2፥193 ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ "ተጋደሉዋቸው"። وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ አንቀጹን ልብ ብለነው ከሆነ "ተጋደሉ" እንጂ "ግደሉ" አይልም። ልዩነቱን እስቲ እንመልከት፦ 2፥244 በአሏህ መንገድ "ተጋደሉ"፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ እነዚህ አንቀጽ ላይ ተጋደሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ቃቲሉ" قَاتِلُوا ሲሆን "ግደሉ" ለማለት ቢፈልግ "ኡቅቱሉ" اقْتُلُوا ይሆን ነበር፦ 2፥191 ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ "ግደሉ"-ዋቸው፡፡ وَاقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ እነዚህ አንቀጽ ላይ ግደሉ" ለሚለው "ኡቅቱሉ" اقْتُلُوا ሲሆን መከላከል"Defensive" ሳይሆን "ማጥቃት"Offensive" ነው። ተጨማሪ አንድ አንቀጽ እንመልከት፦ 9፥111 በአሏህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፣ ይገድላሉ፣ ይገደላሉ"፡፡ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَيَقْتُلُونَ وَيُقْتَلُونَ አያችሁ? "ይጋደላሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩቃቲሉነ" يُقَاتِلُونَ ሲሆን፣ "ይገድላሉ" ለሚለው ግን "የቅቱሉነ" يَقْتُلُونَ ነው። "ቀትል" قَتْل ማለት እና "ቂታል" قِتَال ማለት ሁለት ለየቅል ቃላት እና ትርጉም አላቸው፥ "ቂታል" قِتَال ማለት በግዕዝ "ገድል"Fight" ማለት ነው። "ተጋደሉ" የግሥ መደብ ሲሆን "ገድል" የስመ መደብ ነው፥ ስለዚህ "ገድል" ማለት ጂሃዱል ቀልቢያህ፣ ጂሃዱል ቀውሊያህ እና ጂሃዱል ዐመሊያህ ተጠቅሞ የአሏህን ንግግር የበላይ ማድረግ ነው። ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአሏህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ከኩፋሮች ጋር እንጋደላለን፥ ዓለም በአሏህ ሸሪዓህ እስክትደዳደር ድረስ መጋደሉ ይቀጥላል። ተወዳጁ ነቢያች"ﷺ" የታዘዙበት መርሕ ይህ ነው፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3 ሐዲስ 18 ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሰዎችን "ከአሏህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድም የአሏህ መልእክተኛ ነው" ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን እስኪቆሙ እና ዘካህን እስኪያወጡ ድረስ "እንድጋደላቸው" ታዝዣለሁ"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " أُمِرْتُ أَنْ أُقَاتِلَ النَّاسَ حَتَّى يَشْهَدُوا أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَيُقِيمُوا الصَّلاَةَ، وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ እዚህም ሐዲስ ላይ "አን ኡቃቲለ" أَنْ أُقَاتِلَ ማለት "እንድጋደል" ማለት ሲሆን "እንድገድል" ለማለት ቢሆን ኖሮ "አን አቅቱለ" أَنْ أَقْتُلَ ይሆን ነበር፥ "እንድገድል" ቢል ኖሮ "በሃይማኖት መስገደድ የለም" ከሚል መርሕ ጋር ይጋጭ ነበር። ገድል አጠቃላይ ሦስቱንም የጂሃድ ክፍል የሚይዝ ቃል ነው፦ ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184 አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ “ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: “من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان በእጅ፣ በምላስ እና በልቡ ያልታገለ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለውም። ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአሏህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፦ 49፥15 ምእምናን እነዚያ በአሏህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአሏህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ አምላካችን አሏህ በእርሱ መንገድ ከሚጋደሉ ባሮቹ ያርገን! ለነፍሲያ ተብሎ ከሚደረግ የዘር፣ የብሔር፣ የዘውግ ገድል ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ምሥጢረ ትዳር ይህ ወንድ ልጅ አንድ ሚስት አለው፥ ያቺ ሚስቱ በአካል አራት ናቸው። አራቱ ሴቶች በአካል፣ በስም እና በግብር አራት ሲሆኑ በሚስትነት ግን አንድ ናቸው፥ አራቱም ሴቶች ሚስት የሚለውን ቃል ይጋራሉ። ኸዲጃ ሚስት ናት፣ ዘይነብ ሚስት ናት፣ ሰሚራህ ሚስት ናት፣ አሚራህ ሚስት ናት። ነገር ግን አራቱ አካላት አንድን ሚስትነት ስለሚጋሩ ለወንድ አንድ ሚስት ናቸው። ስለዚህ አንድ ወንድ አራት ሴቶች ሲያገባ ሚስቱ ግን አንዲት ናት። ይህ "ምሥጢረ ትዳር" ካልተገለጸልህ አይገባህም።
ኢሳይያስ 7፥14 ላይ በግሪክ ሰፕቱአጀንት"LXX" ላይ "ወጣት ሴት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓርቴኖስ" παρθένος ሲሆን በትርጉም ደረጃ "ድንግል" ብቻ ሳይሆን "ወጣት ሴት" ማለትም ነው፦ ዘፍጥረት 24፥43 "እነሆ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፥ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም "ቆንጆ"፦ "ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ" ስላት። ἰδοὺ ἐγὼ ἐφέστηκα ἐπὶ τῆς πηγῆς τοῦ ὕδατος, καὶ αἱ θυγατέρες τῶν ἀνθρώπων τῆς πόλεως ἐκπορεύονται ἀντλῆσαι ὕδωρ, καὶ ἔσται ἡ παρθένος, ᾗ ἂν ἐγὼ εἴπω, πότισόν με ἐκ τῆς ὑδρίας σου μικρὸν ὕδωρ, ዘፍጥረት 34፥3 ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፥ "ብላቴናይቱንም" ወደዳት፥ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት። καὶ προσέσχε τῇ ψυχῇ Δείνας τῆς θυγατρὸς ᾿Ιακὼβ καὶ ἠγάπησε τὴν παρθένον καὶ ἐλάλησε κατὰ τὴν διάνοιαν τῆς παρθένου αὐτῇ. እነዚህ አናቅጽ ላይ "ቆንጆ" "ብላቴናይት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓርቴኖስ" παρθένος ሲሆን ሰባው ሊቃናት "ወጣት ሴት" የሚለውን አስበው እንጂ "ድንግል" የሚለው አስበው ስላልሆነ አኪላስ፣ ቴዎቶዶስ እና ሲማቲከስ የተባሉ ጥንታዊ የግሪክ መተርጉማን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ የኢሳይያስ 7፥14 ላይ ያለውን አንቀጽ ሲተረጉሙ "ኔአኒደስ" νεάνιδες ማለትም "ኮረዳ" ብለው ግልጽ እና የማያሻማ ቃል አስቀምጠውታል። ግሪክ ሰፕቱአጀንት የትርጉም ሥራ"Translation" እንጂ ሥረ መሠረታዊ ጽሑፍ"Orginal Text" ካለመሆንም ባሻገር ከዕብራይስጡ የተለየ አሳብ ያቀርባል፦ ኢሳይያስ 7፥14 "ስሙንም አማኑኤል "ትለዋለህ"። καὶ καλέσεις τὸ ὄνομα αὐτοῦ ᾿Εμμανουήλ· "ትለዋለህ" ለወንድ ነጠላ ሲሆን "ትለዋለች" ለሴት ነጠላ ነው፥ የቱን ነው ኢሳይያስ በትክክል ያለው? ትርጉም ሊሳሳት እንደሚችል ተረድተን የማቴዎስ ጸሐፊ ደግሞ ከዕብራይስጡ እና ከግሪክ ሰፕቱአጀንቱ በተለየ መልኩ አስቀምጦታል፦ ማቴዎስ 1፥23 እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል "ይሉታል"። Ἰδοὺ ἡ παρθένος ἐν γαστρὶ ἕξει καὶ τέξεται υἱόν, καὶ καλέσουσιν τὸ ὄνομα αὐτοῦ Ἐμμανουήλ, "ይሉታል" በብዙ ቁጥር ሲሆን "ትለዋለህ" "ትለዋለች" ከሚለው ቃል እጅጉን ይለያል፥ የቱን ነው ኢሳይያስ በትክክል ያለው? ምነው የማቴዎስ ጸሐፊ ሲኮርጅ በትትክክል ከመኮረጅ ይልቅ ስርዋፅ ያስገባልን? ለሌላ ሴት የተነገረ ጥቅስ ለማርያም ሰቶ ከመሰቃየት ይልቅ በትክክሉ "ማርያም ያለ ወንድ ዘር በድንግልና ፀንሳለች" ብሎ ማስቀመጥ በቂ ነበር። ማርያም ልጇን "ኢየሱስ" እንጂ "አማኑኤል" ብላ መቼ ጠራችው? መርየም አሏህን፦ "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፦ 3፥47 "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ" ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ አሏህም በመልአኩ፦ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦ 3፥47 ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ አሏህ ያለ ወንድ እና ያለ ሴት ዘር አደምን ከአፈር ከፈጠረ እና ሐዋን ያለ ሴት ዘር ከአደም አጥንት ከፈጠረ ዒሣን ካለ ወንድ ዘር ከመርየም ብቻ መፍጠር ይችላል፥ ዒሣ በድንግልና መፀነሱ እና እናቱ መርየም በድንግልና መውለዷ በእርግጥ ተአምር ናቸው፦ 23፥50 የመርየምን ልጅ እና እናቱን ተአምር አደረግናቸው፡፡ وَجَعَلْنَا ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ آيَةً 21፥91 እርሷን እና ልጅዋን ለዓለማት ተአምር ያደረግናትን አስታውስ፡፡ وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ ይህ በድንግል መፅነስ"Partheno genesis" ተአምር ሲሆን አሏህ በመርየም ብቻ ሳይሆን በተለያየ ፍጡር ያደርጋል፥ "ፓርቴኖ ጌኔሲስ" παρθένο γένεσις የሚለው ቃል "የድንግል ልደት" ማለት ሲሆን ያለ ወንድ በድንግልና ከሚፀንሱ ፍጡራን መካከል "ኮሞዶ ድራጎን"Komodo Dragon" ተጠቃሽ ናት። በአዞ፣ በወፍ፣ በአሳ፣ በቀንድ አውጣ፣ በሸረሪት ዝርያዎች ውስጥ ያለ ወንድ በድንግና ፀንሰው የሚወልዱ እንስት ፍጡራን ስላሉ አሏህ መርየምን ያለ ወንድ እንድትፀንስ ማድረጉ የእርሱ ተአምር ነው፦ 19፥21 አላት «ነገሩ እንደዚህሽ ነው» ጌታሽ፦ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፥ ለሰዎች ተአምር እና ከእኛም ችሮታ ልናደርገው ይህንን ሠራን የተፈረደም ነገር ነው» አለ፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ ۖ وَلِنَجْعَلَهُ آيَةً لِّلنَّاسِ وَرَحْمَةً مِّنَّا ۚ وَكَانَ أَمْرًا مَّقْضِيًّا የእይሁዳውያንን እና የክርስቲያኖችን ውዝግብ አሏህ በዚህ መልኩ ይፈታልናል። አምላካችን አሏህ ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ድንግል ማርያም በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥47 "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ" ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ በዕብራይስጥ "በቱላህ" בְּתוּלָה ማለት "ድንግል" ማለት ነው፥ በታናኽ "በቱላህ" בְּתוּלָה በነጠላ 32 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ወንድ የማያውቃት ድንግል ሴት ናት፦ ዘፍጥረት 24፥16 ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት "ድንግል" ነበረች። וְהַנַּעֲרָ֗ טֹבַ֤ת מַרְאֶה֙ מְאֹ֔ד בְּתוּלָ֕ה וְאִ֖ישׁ לֹ֣א יְדָעָ֑הּ እዚህ አንቀጽ ላይ "ድንግል" ለሚለው የገባው ቃል "በቱላህ" בְּתוּלָה ነው፥ ይህቺ ሴት ርብቃ ስትሆን እርሷ ድንግል ብቻ ሳትሆን ቆንጆ ወጣት ሴት ነበረች፦ ዘፍጥረት 24፥43 ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም "ቆንጆ" ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ። וְהָיָ֤ה הָֽעַלְמָה֙ הַיֹּצֵ֣את לִשְׁאֹ֔ב וְאָמַרְתִּ֣י אֵלֶ֔יהָ הַשְׁקִֽינִי־נָ֥א מְעַט־מַ֖יִם מִכַּדֵּֽךְ׃ እዚህ አንቀጽ ላይ "ቆንጆ" ለሚለው የገባው ቃል "አልማህ" עַלְמָה ሲሆን "ኮረዳ" "ወጣት ሴት" "ብላቴናይት" ማለት ነው፦ ዘጸአት 2፥8 "ብላቴናይቱ" ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች። הָֽעַלְמָ֔ה וַתִּקְרָ֖א אֶת־אֵ֥ם הַיָּֽלֶד׃ ምሳሌ 30፥19 የሰው መንገድ ከ-"ቆንጆ" ጋር ነው። וְדֶרֶךְ גֶּבֶר בְּעַלְמָה በታናኽ "አልማህ" עַלְמָה የሚለው ቃል 7 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን "ብላቴናይት" "ቆንጆ" "ኮረዳ" "ወጣት ሴት" ማለት ነው፥ "ኤሌም" עֶלֶם ማለት "ብላቴና" "ቆንጆ" "ጎረምሳ" "ወጣት ወንድ" ማለት ነው፦ 1ኛ ሳሙኤል 17፥56 ንጉሡም፦ "ይህ "ብላቴና" የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይቅ" አለ። נו וַיֹּאמֶר, הַמֶּלֶךְ: שְׁאַל אַתָּה, בֶּן-מִי-זֶה הָעָלֶם. 1ኛ ሳሙኤል 20፥22 "ብላቴናውን" ግን፦ "እነሆ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው" ያልሁት እንደ ሆነ ያህዌህ አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። כב וְאִם-כֹּה אֹמַר לָעֶלֶם, הִנֵּה הַחִצִּים מִמְּךָ וָהָלְאָה--לֵךְ, כִּי שִׁלַּחֲךָ יְהוָה. እነዚህ አናቅጽ ላይ "ብላቴና" ወይም "ወጣት ወንድ" ለሚለው የገባው ተዕባታይ ቃል "ኤሌም" עֶלֶם ነው፥ ስለዚህ "ኤሌም" עֶלֶם የሚለው ተባዕታይ መደብ ሆነ "አልማህ" עַלְמָה የሚለው አንስታይ መደብ "ድንግል" ማለት በፍጹም አይደለም። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች የሚራኮቱበትን ጥቅስ በቅጡ እና በአግባብ መመልከት ይቻላል፦ ኢሳይያስ 7፥14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ "ወጣት ሴት" ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች።לָכֵן יִתֵּן אֲדֹנָי הוּא, לָכֶם–אוֹת: הִנֵּה הָעַלְמָה, הָרָה וְיֹלֶדֶת בֵּן, וְקָרָאת שְׁמוֹ, עִמָּנוּ אֵל. የክርስቲያን መተርጉማን፦ 1. NET Bible 2. New American Bible 3. Good News Translation 4. New Revised Standard Version "ወጣት ልጅ"a young woman" ብለው በትክክሉ ተርጉመውታል። በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን እና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ሲሉ አካዝ የተሰጠው ምልክት ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ መሆን ነው፦ ኢሳይያስ 7፥16 ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው "የሁለቱ ነገሥታት" አገር ባድማ ትሆናለች። ቢኢሳይያስ ዘመን የነበረችው ያቺ ወጣት ሴት ነቢይቱን ሕፃኑን ወለደችው፥ ኢሳይያስም ያ ከወጣቲቱ ሴት የተወለደውን ሕፃን በወቅቱ በሁለተኛ መደብ "አማኑኤል ሆይ" እያለ ያናግረው ነበር፦ ኢሳይያስ 8፥3 ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች። ኢሳይያስ 8፥8 አማኑኤል ሆይ! የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች። ይህ አማኑኤል የተባለው ሕፃን አባት እና እናት ያለው ሕፃን ሲሆን ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብት እና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት በመወሰድ ትንቢቱ ተፈጽሟል፦ ኢሳይያስ 8፥4 "ሕፃኑ "አባቱን" እና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብት እና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና" አለኝ።
የሐሰት ትርክት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 22፥30 ከጣዖታት እርኩሰት ተጠንቀቁ! የሐሰትን ቃል ራቁ፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ "ኢትዮጵያ" የምትባል አገር ከሦስት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያላት አገር መሆኗን በታሪክ ምሁራን ዘንድ ይተረካል፥ ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ የራሷ ቋንቋ፣ ፊደል፣ ሥነ ጽሑፍ ያላት አገር ናት። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለ ኦርቶዶክስ ደሴታውያን፦ "ኦርቶዶክስ ፊደል ቀርጻ፣ ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣ አገር ገንብታለች" በማለት የሐሰት ትርክት ይተርካሉ፥ እውን ኦርቶዶክስ አገር በቀል እሳቤ ነው ወይስ ከሌላ አገር የመጣ እሳቤ ነው? እንደ ጎርጎሮሳውያን በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ከኢትዮጵያ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ወንጌል ሰምቶ እና አምኖ ወደ አገሩ ተመለሰ፥ ያ ሰው ከእርሱ አልፎ ለኢትዮጵያውያን ያስተላለፈው እና ያስፋፋው ነገር እንደሌለ እሙን እና ቅቡል ነው። በአራተኛው ክፍለ ዘመን ሊባኖሳዊ ፍሬምናጥስ በማዕረግ ስሙ "አባ ሰላማ" በንጉሥ ዒዛና ዘመነ መንግሥት ክርስትናን በይፋ አስገብቷል፥ በመቀጠል በ 480 ድኅረ ልደት ተስዓቱ(ዘጠኙ) ቅዱሳን ክርስትናን በጽብሓውያን የአስተሳሰብ ውቅር ወደ ኢትዮጵያ አስገብተዋል። ሙግቱ እስቲ ጠበብ እናርገውና "ክርስትና የገባው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ነው" እንበል "ኢትዮጵያን የሚባሉ ሕዝቦች ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የሉም" እያላችሁን ነው? ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ፊደል፣ ቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ የለምን? ስለዚህ "ኦርቶዶክስ ፊደል ቀርጻ፣ ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣ አገር ገንብታለች" የሚለው ትርክት የሐሰት ትርክት ነው። ሌላው ደሴታውያን "ኦርቶዶክስ አገር ናት" የሚል የሐሰት ትርክት አላቸው፥ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድ የክርስትና አንጃ"Sect" እና የክርስትና ሃይማኖት ምድብ እንጂ አገር በፍጹም አይደለችም። አገር ኢትዮጵያ እንደመሆኗ መጠን ኢትዮጵያ ዋቄፈታውን፣ አይሁዳውያንን፣ ሙሥሊሙን፣ እንዲሁ የተለያየ የክርስትና አንጃ እና ጎጥ"Denomination" ያካተተች አገር እንጂ ለኦርቶዶክስ እውነተኛ እናት ለተቀረው የእንጀራ እናት አይደለችም። ዋቄፈታውን፣ አይሁዳውያንን፣ ሙሥሊሙን፣ እንዲሁ የተለያየ የክርስትና አንጃ እና ጎጥ ከጨዋታ ውጪ በማድረግ "ኦርቶዶክስ የአገር ባለቤት ናት" የሚል ትርክርት አሁንም የሐሰት ትርክት ነው፥ አገሪቱ ከሃይማኖት በገለልተኛ አስተሳሰብ"Secularism" መንግሥት እስከተመራች ድረስ አንድ ሰው የአገር ባለቤት ለመሆን ሃይማኖት መስፈርት አይሆንበትም። "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" የሚል የሐሰት ትርክት የተቀበረ እና ደሴታውያን ይህንን የሐሰት ትርክት ሊያንሰራሩ ቢሞክሩም በአገር ግንባታ እና በብሔራዊ መግባባት ትርክቱ እየተደቆሰ ነው። ለማንኛውም እንደ አንድ ሙሥሊም የሐሰት ትርክትን አጋልጠን ትክክለኛውን ንግግር መናገር ይገባናል፦ 33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛውን ንግግር ተናገሩ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا የሐሰት ትርክት ሲተረክ የሐሰትን ቃል ራቁ! እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ከእውነተኞቹ ጋር ኹኑ፦ 22፥30 ከጣዖታት እርኩሰት ተጠንቀቁ! የሐሰትን ቃል ራቁ፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ 9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ከእውነተኞቹ ጋር ኹኑ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ ከላይ የቀረበው መጣጥፍ "ትክክል አይደለም" የሚል ካለ በማስረጃ መሞገት ይቻላል፥ እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ እና በዕውቀት ንገሩኝ፦ 2፥111 እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ" በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ 6፥143 እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ" በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ማየት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 57፥4 እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አሏህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ የሰው ምንነት እና ማንነት የዓይን፣ የጆሮ፣ የእግር፣ የእጅ ወዘተ ቅንብር"Complex" ነው፥ ለምሳሌ፦ እኔ በምንነት እና በማንነት አንድ ብሆንም የእኔ አንድነት የቅንብር አንድነት ነው። "ዑድው" عُضْو ማለት "ብልት"Organ" ወይም "ክፍል"Part" ማለት ሲሆን የሰው ዓይን፣ ጆሮ፣ እግር፣ እጅ ወዘተ የምንነቱ ክፍል ሲሆን ሕዋስ ነው፥ "ሓሣህ" حَاسَّة ማለት "ሕዋስ"Sense" ማለት ሲሆን ዓይን፣ ጆሮ፣ እግር፣ እጅ ወዘተ የሰው ሕዋስ ነው። አምላካችን አሏህ ሰውን ሰሚ ተመልካችም አድርጎ ፈጥሮታል፦ 76፥2 እኛ ሰውን የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا "በሲር" بَصِير ማለት "ተመልካች" ማለት ሲሆን የሰው ተመልካችነት በጊዜ እና በቦታ የተወሰነ ሲሆን የሚመለከትበት መመልከቻ ዓይን እራሱ ግዙፍ እና ስሉጥ ነው፥ የሰው ዓይን ያለ ብርሃን በጨለማ የማያይ እና ብርሃን የሚቀበልበት ውኃ"lens" ያለው ነው። "መሕዱድ" مَحْدُود ማለት "ውስን"Limited" ማለት ሲሆን "መሕዱዲያህ" مَحْدُودِيَّة ማለት "ውስንነት"Limitedness" ነው፥ የፍጡራን ዓይን ውስን ነው። አምላካችን አሏህ ግን ከማንም ፍጡር ጋር የማይመሳሰል ሲሆን እርሱ ተመልካች ነው፦ 42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ እዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስል" مِثْل በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው "ከ" كَ የሚል መስተዋድድ "በጭራሽ" "በፍጹም" ማለት ነው፥ "ሸይእ" شَيْء በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉም ምንነት የሚካተቱ ሲሆኑ ከፍጡራን መካከል እርሱን የሚመስል ብጤ በጭራሽ የለም። አሏህ ከፍጡራን ጋር በጭራሽ እና በፍጹም የማይመሳሰል የማየት ባሕሪ አለው፥ የእርሱ ማየት ከፍጡራን ማየት ጋር አይመሳሰልም። "ተሽቢህ" تَشْبِيه ማለት "ማመሳሰል" ማለት ሲሆን የአሏህን ማየት ከፍጡራን ማየት ጋር ማመሳሰል እና አሏህን በፍጡር ቂያሥ ማድረግ "ተሽቢህ" تَشْبِيه ነው፥ አሏህ እንደ ፍጡራን ዓይነት ዓይን በጭራሽ የለውም። የአሏህ ዓይን መለኮታዊ እና አምላካዊ ዓይን እንጂ ሰዋዊ እና ፍጥረታዊ አይደለም፦ 52፥48 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ! አንተ በ-"ዓይናችን" ሥር ነህና፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡ وَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعْيُنِنَا ۖ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ "በሶር" بَصَر ማለት "መመልከቻ" ማለት ሲሆን መመልከቻ በሉገቲል ዐረቢይ "ዐይን" عَيْن ነው፥ አሏህ የራሱ ዓይን እንዳለው ከላይ ያለው ጥቅስ ያሳያል። የተሽቢህ ተቃራኒ "ተንዚህ" تَنْزِيه ሲሆን የአሏህን ባሕሪይ ከፍጡራን ጋር አለማመሳሰል "ተንዚህ" تَنْزِيه ነው፥ የእርሱ ዓይን ረቂቅ እንጂ ግዙፍ ስላልሆነ ከፍጡራን እርሱን ማንጻት "ተንዚህ" تَنْزِيه ነው። "ሙጥለቅ" مُطْلَق ማለት "ያልተወሰነ"Unlimited" ማለት ሲሆን "ሙጥለቃህ" مُطْلَقَة ማለት "ኢ ውስንንነት"Unlimitedness" ማለት ነው፥ የአሏህ ዓይን ምሉዕ ነው፦ 57፥4 እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አሏህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ የትም ብንሆን አሏህ ሁሉን ነገር ስለሚመለከት የእርሱ ማየት ያልተወሰነ ምሉዕ ነው፥ "ወዚፋህ" وَظِيفَة ማለት "ግብር"Function" ማለት ሲሆን ዓይን ለአሏህ ሲወሶፍ ግብር እንጂ እንደ ሰው የሕዋስ ክፍል አይደለም። ወደ ባይብል ስንገባ ኢዮብ በአንድ ወቅት፦ "በውኑ የሥጋ ዓይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? በማለት በአጠይቆት አምላክ የሥጋ ዓይን እንደሌለው እና ሰው እንደሚያይ ዓይነት አስተያየት እንደሌለው ጠቁሞ ነበር፦ ኢዮብ 10፥4 በውኑ የሥጋ ዓይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? הַעֵינֵי בָשָׂר לָךְ אִם־כִּרְאוֹת אֱנוֹשׁ תִּרְאֶה የሰው ማየት ውስንነት ያለው፣ ያለ ብርሃን ማየት የማይችል፣ በጨለማ ማየት የማይችል ሲሆን ዓይኑ የሥጋ ዓይን ነው፥ የአምላክ ማየት ግን ያለ ብርሃን ማየት የሚችል፣ በጨለማ ማየት የሚችል፣ እይታው ያልተወሰነ የመለኮት ዓይን ነው፦ ምሳሌ 15፥3 የያህዌህ ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችን እና ደጎችን ይመለከታሉ። בְּכָל־מָקוֹם עֵינֵי יְהוָה צֹפוֹת רָעִים וְטוֹבִים የአምላክ ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ክፉዎችን እና ደጎችን ይመለከታሉ፥ የመለኮት ዓይን ረቂቅ፣ ምጡቅ፣ ምሉዕ ነው። ማንም ሰው ባይብል ላይ "የአምላክ ዓይን" ማለት "ይህ ማለት ነው" ብሎ ተርጉሞ ማስረጃ ማምጣት አይችልም፥ ከዚያ ይልቅ ሠለስቱ ምዕት ወጥ በሆነ ስምምነት ለእግዚአብሔር ምሳሌአዊ ሳይሆን አማናዊ ዓይን እንዳለው ተናግረዋል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 19 ቁጥር 33 “ለእግዚአብሔር ዓይኖች እና ጆሮዎች እንዳሉት መጽሐፍት የተናገሩት እና የቀሩት እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር የተነገረው ሁሉ የታመነ እና እውነተኛ እንደሆነ እናምናለን፥ ነገር ግን አይመረመርም አይታሰብም”። "ሠለስቱ ምዕት" ማለት በ 325 ድኅረ ልደት በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት ናቸው፥ ይህ የኒቂያ ጉባኤ ወጥ የአበው ስምምነት"Consensus Patrum" ነው። በኒቅያ ጉባኤ ከነበሩት አበው አንዱ አትናቴዎስ ዘእስክንድሪያ ለእግዚአብሔር ምሳሌአዊ ሳይሆን አማናዊ ዓይን እንዳለው ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 30 “ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በከበሩ መጻሕፍት የተጻፈ ሁሉ የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም”። ዓይኑ ምን ዓይነት እንደሆነ "አይመረመርም አይታወቅም" ካለ ይህ በኢሥላም ሥነ መለኮት "ተፍዊድ" ይባላል፥ "ተፍዊድ" تَفْوِيض ማለት "ማስጠጋት"Delegation" ማለት ነው። "ተክዪፍ" تَكْيِيف ማለት "እንዴትነት"Howness" ማለት ሲሆን የአሏህን ባሕርዮት ያለ እንዴትነት "ቢላ ከይፈ" بِلَا كَيْفَ እንዴትነቱን ወደ አሏህ አስጠግቶ መቀበል "ተፍዊድ" تَفْوِيض ይባላል። በኃላ ላይ ግን ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እና አውግስጢንዮስ ዘሂፓ የኡሲያ ኢኔርጌያ የተባሉትን ዓይን፣ ጆሮ፣ እግር፣ እጅ ከአማናዊ ወደ ምሳሌአዊ ትርጉም በመስጠት ተሕሪፍ አረጉት፥ "ተሕሪፍ" تَحْرِيف ማለት "ትርጉሙን ማዛባት" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ የእርሱን ባሕሪይ ያለ ተሕሪፍ፣ ያለ ተዕጢል፣ ያለ ተሽቢህ፣ ያለ ተክዪፍ የምንቀበል ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢየሱስ ፆታ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ እዚህ ዐውድ ላይ "ፆታ" ማለት ኃፍረተ ሥጋ ልዩነት ያለው ወንድ እና ሴትን ያቀፈ "የመራቢያ አካል"Sexual Organ" ማለት ነው፥ "ፅንስ" ማለት ደግሞ "በማኅፀን ውስጥ የተለያየ ሂደት"Process" ያደረገ ፍጡር" ማለት ነው። ድንግል ማርያም በማኅፀኗ ውስጥ የተፀነሰችው ፅንስ እና የወለደችው ልጇ ፆታው "ወንድ" ነው፦ ሉቃስ 1፥31 እነሆም ትፀንሻለሽ "ወንድ ልጅም" ትወልጃለሽ፥ ስሙንም "ኤሱስ" ትዪዋለሽ። καὶ ἰδοὺ συλλήμψῃ ἐν γαστρὶ καὶ τέξῃ υἱόν, καὶ καλέσεις τὸ ὄνομα αὐτοῦ Ἰησοῦν. "ወንድ" የሚለው የሥጋ መደብ እና የሥጋ አንቀጽ ሲሆን ይህም እልም አርጎ ፍጡርን ያሳያል፥ የወንዱ ልጅ ስሙ በዕብራይስጥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ በግሪክ ኮይኔ ደግሞ "ኤሱስ" Ἰησοῦς ሲባል ይህ ስም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከመወለዱ እና ከመፈጠሩ በፊት ለፍጡር ሰው የሚውል ስም ነው፦ ሉቃስ 2፥21 ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ በማኅፀን ሳይረገዝ(ሳይፀነስ) በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ "ኤሱስ" ተብሎ ተጠራ። Καὶ ὅτε ἐπλήσθησαν ἡμέραι ὀκτὼ τοῦ περιτεμεῖν αὐτόν, καὶ ἐκλήθη τὸ ὄνομα αὐτοῦ Ἰησοῦς, τὸ κληθὲν ὑπὸ τοῦ ἀγγέλου πρὸ τοῦ συλλημφθῆναι αὐτὸν ἐν τῇ κοιλίᾳ. "ሊገርዙት" የሚለው ይሰመርበት! የሚገርዙት የመራቢያ አካሉን ሲሆን ተገርዞ የሚጣለው ሸለፈቱ ነው፥ አምላክ ጅማሮ እና መነሻ የሌለው ሲሆን ይህ ወንድ ልጅ ግን ስምንተኛ ቀን ሆኖት ጅማሮ እና መነሻ አለው። በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ጥር 1 ቀን በአገራችን ደግሞ ጥር 6 ቀን በዓመት አንዴ "ግዝረተ ኢየሱስ"The Circumcision of Christ" ተብሎ ይህንን ወንድ ልጅ የተገዘረበትን ዓመታዊ ክብረ በዓል ይዘከራሉ፥ "ግዝረት” ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን “ግርዘት”Circumcision” ማለት ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 70 ቁጥር 24 "ሰውም እንደ መሆኑ ለሥጋ እንደሚገባ ተገዘረ"። ድርሳነ መስቀል ምዕራፍ 3 ቁጥር 26 "የኦሪትን ሕግ ይፈጽም ዘንድ በስምንተኛው ቀን እንደ ሕፃናት ተገረዘ"። ኢየሱስ በስምንተኛው ቀን የተገረዘ ወንድ ልጅ ነው፥ ከተገረዘ እና ወንድ ልጅ ከሆነ ፆታ አለው። መለኮት ግን መንፈስ ነው፥ መንፈስ ደግሞ ሥጋ እና አጥንት ስለሌለው ፆታ የለውም፦ ዮሐንስ 4፥24 አምላክ መንፈስ ነው። Πνεῦμα ὁ Θεός, ሉቃስ 24፥39 መንፈስ ሥጋ እና አጥንት የለውምና። ὅτι πνεῦμα σάρκα καὶ ὀστέα οὐκ. "መንፈስ" ማለት "ረቂቅ" "ምጡቅ" ማለት ሲሆን የግዙፍ እና የስሉጥ ተቃራኒ ነው። እንደ ተዋሕዶ አስተምህሮት መለኮት የትስብእትን ርስት እና ገንዘብ የራሱ ርስት እና ገንዘብ ካደረገ መለኮት የትስብእትን የመራቢያ ፆታን ገንዘቡ አድርጓልን? "አይ" ካላችሁ እንግዲያውስ የተዋሕዶ ተስተምህሮት ዶግ አመድ ይሆናል፥ "አዎ" ካላችሁ እንግዲያውስ "መለኮት የመራቢያ ፆታ አለው" ማለት ነው። ይህ የተሠግዎት አጣብቂኝ"Incarnation Dilemma" ሲሆን "አዎ" ከተባለ ቀጣይ ይዞ የሚመጣው መዘዝ የመራቢያ ፆታ ያለው የማን መለኮት ነው? የወልድ መለኮት ወይስ የሦስቱም መለኮት? "የወልድ መለኮት" ከተባለ የመራቢያ ፆታ የሌለው የአብ እና የመንፈስ ቅዱስ መለኮት አለን? "የሦስቱም መለኮት" ከተባለ አብ እና መንፈስ ቅዱስ የመራቢያ ፆታ አላቸውን? አምላክ እና ሰውን እንደ መርፌ እና ቁልፍ፣ እንደ ጭድ እና ጭቃ፣ እንደ መርፍ እና ሞፈር አንድ ለማድረግ በተለያየ የጊዜ ሱባኤ በተለያየ የቦታ ጉባኤ መዳከሩ ምን ይፈይዳል? "መለኮት ነጠላ አንድ ነው"Divine is Simple" ተብሎ ከፍጡር ሰው ጋር ውቅር"Composition" ሆነ ማለትስ "መለኮት ውቅር ነው"Divine is Complex" ማለት አይሆንምን? ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰው ውስን፣ ግዙፍ እና ስሉጥ ሲሆን መለኮት ደግሞ በተቃራኒው ምሉዕ፣ ረቂቅ እና ምጡቅ ነው፦ ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና። διότι Θεὸς ἐγώ εἰμι καὶ οὐκ ἄνθρωπος· ያ ከፍጥረት ውጪ ያለው አምላክ ፍጡራንን ያካበበ እና በፍጥረት ውስጥ የተወሰነ ስላልሆነ ሰው አይደለም፥ ሰው ግን በአጭር ቁመት እና በጠባብ ደረት ውስን የሆነ ፍጡር ነው። ኢየሱስ ግን በምንነቱ ከአምላክ እየሰማ ሲናገር የነበረ ሰው ብቻ እና ብቻ ነው፦ ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከ-"አምላክ" የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን "ሰው" ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። νῦν δὲ ζητεῖτέ με ἀποκτεῖναι, ἄνθρωπον ὃς τὴν ἀλήθειαν ὑμῖν λελάληκα, ἣν ἤκουσα παρὰ τοῦ Θεοῦ· እዚህ አንቀጽ ላይ "ቴዎስ" Θεὸς እና "አንትሮፓስ" ἄνθρωπος በሰዋስው አወቃቀር ሁለት የተለያዩ ምንነት"Ontology" ሆነው ተቀምጠዋል፥ "ቴዎስ" Θεὸς ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "አንትሮፓስ" ἄνθρωπος ማለት "ሰው" ማለት ነው። "አምላክ" አሰሚ ባለቤት"Subject" ሲሆን "ሰው" ሰሚ ተሳቢ"Object" ነው፥ በአምላክ እና በሰው መካከል "የሰማሁት" የሚል አጫፋሪ ግሥ"Transitive Verb" ስላለ አሰሚው አምላክ እና ሰሚው ሰው ሁለት የተለያዩ ማንነት"Metaphysics" እንደሆኑ ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። ፍጹሙ ሰው ኢየሱስ ከፍጹሙ አምላክ እየሰማ ከተናገረ የተገረዘው እና ወንድ ልጅ የሆነው ፍጹሙ ሰው ከመለኮት በሰዋስው አደረጃጀት ተለይቶ ተቀምጧል፥ ከአምላክ ሰምቶ የሚናገር ሰው ደግሞ በማንነት ነቢይ እና መልእክተኛ ነው። የማርያም ልጅ ኢየሱስ በምንነት ሰው በማንነት መሢሕ ሆኖ ሳለ "አምላክ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦ 5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ይህ በሰው የተፈጠረው ውርክብ ለመግታት ምንም ዓይነት የሥነ መለኮት ዕውቀት፣ የሥነ አመክንዮ ሙግት፣ የሥነ ልቡና ዘይቤ ቢቀርብ እንኳን ከአንጀት ጠብ የሚል መልስ ሊገኝ አልተቻለም። መፍትሔው ሴት ማኅፀን ውስጥ የተፀነሰ እና የተወለደ፣ የተገረዘ፣ የመራቢያ ፆታ ያለው ወንድ ልጅ ከማምለክ ይልቅ ያንን ወንድ ልጅ በማርያም ማኅፀን የፈጠረውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። በአምላክነቱ ሰውነት የሌለበት አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! ለእኛም ኢሥቲቃማህ ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ "መድሎተ አሚን" በሚል መጽሐፋቸው ለዶክተር አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት ለተባሉ ካቶሊካዊ መነኩሴ መልስ ሲሰጡ እንዲህ አስቀምጠዋል፦ "(ልዮን)፦ አካላዊ ተዋሕዶ የሚለውን አነጋገር "አካል ለመለኮት እንጂ ለትስብእት የለውም፥ ለትስብእት ያለው ባሕርይ ብቻ ነው" በማለቱ አፍርሶታል"። መድሎተ አሚን(አድማሱ ጀንበሬ) ገጽ 108 ከላይ ያለውን የተናገረው በ 451 ድኅረ ልደት ልዮን ዘሮም ለዲስቆርዮስ ዘእስክንድርያ ነው፥ "ወልድ አካለ መለኮት እንጂ አካለ ትስብእት የለውም" የሚለው ትምህርት በልዮን መስመር የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ትምህርት እንጂ በዲስቆርዮስ መስመር የጽብሓውያን ኦርቶዶክስ ትምህርት አይደለም። "አካል" ማን? ብለን የምንጠይቅበት ባለቤት"Subsistence" ሲሆን "ባሕርይ" ደግሞ ምን? ብለን የምንጠይቅበት ሥር"Substance" ነው፥ ኢየሱስ "ከ-እኔ አብ ይበልጣል" ብሎአል፦ ዮሐንስ 14፥28 "ከ"እኔ" አብ ይበልጣልና። ὁ Πατὴρ μείζων μού ἐστιν. ኢየሱስ "እኔ" የሚል የሰው ማንነት ከሌለው "ከእኔ አብ ይበልጣል" ሲል "እኔ" ከሚለው የመለኮት ማንነት አብ ይበጣል እያላችሁ ነው? አንዱ የመለኮት ማንነት ከሌላው የመለኮት ማንነት ይበላለጣልን? "የግብር መበላለጥ ኑፋቄአዊ የአርጌንስ ትምህርት ነው" ትሉ የለምን? አምላካችን አሏህ " "እኛ "ነሷራ" ነን" ካሉት ከሐዋርያት ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳንን ይዟል፦ 5፥14 ከእነዚያም "እኛ "ነሷራ" ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ ከሐዋርያት ሕልፈት በኃላ ግን በእነርሱ እግር ሥር ተተካን የሚሉት ነሷራ ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፥ በተውሒድ ላይ ተሥሊሥ በመጨመር እንዲሁ ተሠግዎት የሚባል የፓጋን ትምህርት በመጨመር ወሰን አለፉ፦ 4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ 4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቅጣት ነው፦ 5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብን እና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አሏህ ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል። فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ "ስለዚህ" ማለት በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን በመተዋቸው ምክንያት እርስ በእርስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቁጣ ነው። አምላካችን አሏህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበረው ውዝግብ በመካከላችሁ በመፍረድ ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል። አምላካችን አሏህ በዒሣ ዙሪያ የምትወዛገቡትን ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
አብሲማዳኮስ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብን እና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ "አምላክ" ተብሎ "መለኮት" ሲባል "ሰብእ" ተብሎ "ትስብእት" ተብሎ ይባላል፥ "ሰብእ" ማለት "ሰው" ማለት ነው። "ቴሌኦስ" τέλειος ማለት "ፍጹም" "ሙሉ"Fully" ማለት ሲሆን አንድ ሰው ሙሉ ሰው የሚባለው የሰው ምንነት እና ማንነት ስላለው ነው፥ "ኢየሱስ ሙሉ ወይም ፍጹም ሰው ነው" ከተባለ ኢየሱስ የሰው ባሕርይ"Human Nature" ብቻ ሳይሆን የሰው አካል"human Hypostasis" አለው። ቄርሎስ ዘእስክንድርያ በ 431 በኤፌሶን ጉባኤ፦ "ሄኖሲስ ካት ሒፓስታሲን" ἕνωσις καθ᾽ ὑπόστασιν ሲል ትርጉሙ "አካላዊ ተዋሕዶ"Hypostatic Union" ማለት ነው፥ ንስጥሮስ ዘቁስጥንጥንያ፦ "ኢየሱስ የአብ ልጅ እና የማርያም ልጅ ሁለት አካል ናቸው" ሲል በኤፌሶን ጉባኤ ተወግዟል። ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ፦ "ዘውእቱ ብሂል አሐዱ እምክልኤቱ" ማለትም "ከሁለቱ አንድ የሆነ"From two made in to One" ብሎአል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 54 ቁጥር 21 "ስለዚህም "አብሲማዳኮስ" ተባለ ይኸውም "ከሁለት አንድ የሆነ" ማለት ነው። "አብሲማዳኮስ" ማለት "ከሁለት አንድ የሆነ" ማለት ነው፥ በኤፌሶን ጉባኤ የጸደቀው "ተዋሕዶ ሁለቱን አካላት አንድ አካል አደረጋቸው" የሚል ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 49 ቁጥር 28 "ተዋሕዶ ሁለቱን አካላት አንድ አካል አደረጋቸው"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 73 ቁጥር 3 "እርሱ ወልድ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆነ"። ነገር ግን የኬልቄዶን ጉባኤ ጉዳዩ ተቀይሮ "ወልድ አንድ የመለኮት አካል ነው፥ በአንድ የመለኮት አካል ሁለት የመለኮት ባሕርይ እና የሰው ባሕርይ አሉ" የሚል ውሳኔ ወሰኑ፥ ይህንን ውሳኔ ዲስቆርዮስ ዘእስክንድርያ ሳይቀበል በመቅረቱ ዛሬ ላይ ያሉት የጽብሓውያን ኦርቶዶክስ "ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆነ" የሚል አቋም ይዘዋል። ቀሲስ ዶክተር መብራቱ ኪሮስ ገብሩ "Miaphsite Chriatology" በሚል በነገረ ክርስቶስ ጥናታዊ ጽሑፍ"Thesis" ባዘጋጁት መጽሐፋቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፦ "የኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ምሁራን፦ "ክርስቶስ ከሁለት ባሕርይ እና ከሁለት አካል አንድ አካል እና አንድ ባሕርይ ነው" ብለው ያስተምራሉ" "Ethiopian theologians teach that Christ is one person(akal) and one nature(baharey) from two natures and two persons" Miaphsite Chriatology(Mebratu kiros Gebru) Page 13 "ኡሲያ" οὐσία ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል "ፊሲስ" φύσις ሲሆን "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ደግሞ "ሒፓስታቲስ" ὑπόστασις ነው፥ "አካል" የሚለው የግዕዝ ቃል "አካለ" ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ" "መያወቂያ" ማለት ነው። የአሌክሳንድሪያ ሥነ መለኮታዊን "አካል" ለማለት "ሒፓስታቲስ" ὑπόστασις ብለው ሲጠቀሙ የአንጾኪያ ሥነ መለኮታዊን "አካል" ለማለት "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ብለው ይጠቀማሉ፥ ለምሳሌ፦ አርጌንስ ዘእስክንድርያ እና ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ሦስት አካላት" ለማለት "three hypostases" በማለት ተጠቅመዋል፦ "We consider, therefore, that there are three hypostases, the Father and the Son and the Holy Spirit". Commentary on John (Origen) Book II(2) Number 6 "And when I speak of God you must be illumined at once by one flash of light and by three. Three in Individualities or Hypostases". Orations (Gregory Nazianzen) Oration 39 Number XI(11) "ሒፓስታቲስ" ὑπόστασις በዐረቢኛ "ኡቅኑም" أُقْنُوم ሲባል "ሸኽስ" شَخْص ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ነው፥ "አቃኒም" أَقَانِيم ደግሞ "ኡቅኑም" أُقْنُوم ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው። ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ "አቃኒም ማለት "አካላት" ማለት እንደሆነ ተናግሯል፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 13 ቁጥር 6 "የእግዚአብሔር አቃኒም ስሞች ናቸው፥ ስሞችም አቃኒም ናቸው። የአቃኒም ትርጓሜው በገጽ እና በመልክ ፍጹማን የሚሆኑ፤ ባለመለወጥ ጸንተው የሚኖሩ አካላት ማለት ነውና"። ስለዚህ "ሦስት ሒፓስታቲስ" ሲባል "ሦስት እኔ የሚሉ ማንነት" ከሆነ "ከሁለት ሒፓስታቲስ አንድ ሒፓስታቲስ" ማለት "ከሁለት እኔ ባይ ማንነት አንድ እኔ ባይ ማንነት ሆነ" ማለታቸው ነው፥ ጽብሓውያን "የኢየሱስ የሰው ማንነት ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረ እና ጅማሮ ያለው እንጂ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረ ሰው አይደለም" ብለው ያምናሉ።
ቲክቶዶክስ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ የመሬቷ ኦርቶዶክስ የጽብሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" ሲሆን ቲክ ቶክ ላይ ያለው ኦርቶዶክስ ደግሞ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ"Eastern Orthodox" ነው፥ ቲክ ቶክ ላይ ያለው ኦርቶዶክስ የሽሙጥ እና የለበጣ ስሙ "ቲክቶዶክስ" ሲሆን በጽብሓውያን ኦርቶዶክስ ማሊያ ለምሥራቅ ኦርቶዶክስ የሚጫወት ነው። ይህ ስውር አጀንዳ የምሥራቅ ኦርቶዶክስን ትምህርት በቅጡ እና በአግባብ ያልተረዳ ሰው አያውቀውም፥ ቲክቶዶክስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትውፊትን፣ አዋልድን፣ ሃይማኖተ አበውን እና ሊቃውንትን ጭምር ሳይቀር የማይቀበልበት እና የሚንቅበት ምክንያት ለዛ ነው። "ፊሲስ" φύσις ማለት "ባሕርይ" ማለት ሲሆን "ምንነት" ነው፥ "ሒፓስታቲስ" ὑπόστασις ማለት "አካል" ማለት ሲሆን "ማንነት" ማለት ነው። ፨ "ክርስቶስ ከማርያም የሰው ባሕርይ"Human Nature" እንጂ የሰው አካል"human Hypostasis" አልነሳም" የሚሉ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ በላቲን "አን ሒፓስታሲያ"An Hypostasia" ሲባሉ "አን ሒፓስታቲስ" ἀν ὑπόστασις ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ነው። "አን ሒፓስታቲስ" ἀν ὑπόστασις ማለት "ኢ አካል" ማለት ነው፥ አን" ἀν ማለት አፍራሽ ሲሆን ኢ"Not" ማለት ነው። "ኢየሱስ የመለኮት አካል እንጂ የሰው አካል የለውም" የሚለው የቲክቶዶክስ ትምህርት ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ የተቀዳ ነው፥ ይህንን ለማረጋገጥ ለቲክቶዶክስ "ኢየሱስ የሰው አካል አለው ወይስ የለውም" ብሎ መጠየቅ ብቻ በቂ ነው። ፨ "ክርስቶስ ከማርያም የሰው ባሕርይ"human nature" ብቻ ሳይሆን የሰው አካል"human Hypostasis" ነስቷል" የሚሉ የጽብሓውያን ኦርቶዶክስ በላቲን "ኤን ሒፓስታሲያ"En Hypostasia" ሲባሉ "ኤን ሒፓስታቲስ" ἐν ὑπόστασις ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ነው። "ኤን ሒፓስታቲስ" ἐν ὑπόστασις ማለት "በ አካል" ማለት ነው፥ ኤን" ἐν ማለት አውንታዊ ሲሆን በ"In" ማለት ነው። ይህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አቋም ነው፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 73 ቁጥር 3 "እርሱ ወልድ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆነ"። ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 94 ቁጥር 13 "ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ከሁለት አካል አንድ አካል እንደሆነ እርሱን እናውቃለን"። ሁለት ባሕርይ የአምላክ ባሕርይ እና የሰው ባሕርይ ሲሆኑ "ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ" ማለት "የአምላክ ባሕርይ እና የሰው ባሕርይ አንድ ሆነ" ማለታቸው ነው፥ እንዲሁ ሁለት አካል የአምላክ አካል እና የሰው አካል ሲሆኑ "ከሁለት አካል አንድ አካል" ማለት "የአምላክ አካል እና የሰው አካል አንድ ሆነ" ማለታቸው ነው። ከዚህ በተቃራኒው ቲክ ቶክ ላይ ያሉ የቲክቶኩ ኦርቶዶክስ "ወልድ የአምላክነት አካል እንጂ የሰውነት አካል የለውም" የሚለው ትምህርት የቃረሙት፣ የገበዩት እና የቀሰሙት ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ ነው፥ የሚያሳዝነው ቲክቶዶክስ በጉባኤ ቤት ወይም መጽሐፍ ቤት ሊገቡ ይቅርና ንባብ ቤት ገብተው ስለማያውቁ ግዕዝ እንኳን ለማንበብ አይሞክሩም። በኢሥላም ነገረ ክርስቶስ ኢየሱስ ምንነቱ የሰው ምንነት ሲሆን ማንነቱ የሰው ማንነት ነው፥ በምንነቱ የማርያም ልጅ ሲሆን በማንነቱ ነቢይ፣ መልእክተኛ እና መሢሕ ነው። እንግዲህ አምላካችን አሏህ ስለ ዒሣ ምንነት እና ማንነት በቁርኣን የነገረን ቃል እውነተኛ ቃል ነው፦ 19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ “የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለት “የሚከራከሩበት” ማለት ሲሆን በታሪክ ውስጥ ብዙ ሰዎች በዒሣ ምንነት እና ማንነት ቢከራከሩበትም አሏህ ስለ ዒሣ የነገረን ግን እውነተኛ ንግግር ነው፥ “ሂ” هِ ማለትም “እርሱ” የተባለው ዒሣ ሲሆን “እርሱ” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ፊ” فِي የሚል መስተዋድድ ሲኖር “ስለ”About” በሚል የመጣ ነው። አምላካችን አሏህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፦ 22፥69 አሏህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡ اللَّهُ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ አምላካችን አሏህ በዒሣ ዙሪያ የምትወዛገቡትን ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የትምህርት ገበታ ንባብ ቤት፣ ዜማ ቤት እና መጽሐፍ ቤት የሚባሉ ክፍሎች አሉ። ፨ ንባብ ቤት ግዕዝ ንባብ፣ ውርድ ንባብ እና ቁም ንባብ ሆነው የሚነበቡ መልእክተ ዮሐንስ፣ ወንጌለ ዮሐንስ፣ መዝሙረ ዳዊት፣ የዘውትር ጸሎት፣ ውዳሴ ማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ ይወድስዋ መላእክት፣ መልክአ ማርያም፣ መልክአ ኢየሱስ ተጠቃሽ ናቸው። ፨ ዜማ ቤት ውዳሴ ማርያም፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም፣ ሠልስት እና ቅዳሴ ወሰዓታት ወዘተ ናቸው። ፨ መጽሐፍ ቤት የጉባኤ ቤት ሲሆኑ መጽሐፈ ብሉይ፣ መጽሐፈ ሐዲስ፣ መጽሐፈ መነኮሳት እና መጽሐፈ ሊቃውንት ናቸው። 1.መጽሐፈ ብሉይ 46 የብሉይ መጻሕፍት የሥነ አፈታት ጥናት አንድምታ ነው፣ 2. መጽሐፈ ሐዲስ 35 የሐዲስ መጻሕፍት የሥነ አፈታት ጥናት አንድምታ ነው፣ 3. መጽሐፈ መነኮሳት የሚባሉት ማር ይስሐቅ፣ ፊልክስዩስ እና አረጋዊ መንፈሳዊ ናቸው። 4. መጽሐፈ ሊቃውንት የሚባሉት ሃይማኖተ አበው፣ ድርሳነ ቄርሎስ፣ ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ተግሣጸ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ፍትሐ ነገሥት፣ 14ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ እና አቡ ሻህር(ባሕረ አሳብ) ናቸው። ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ጌጡ በጉባኤ ቤት ያለፉ በብሉይ ኪዳን ያስመሰከሩ መጋቤ ብሉይ፣ በሐዲስ ኪዳን ያስመሰከሩ መጋቤ ሐዲስ፣ በመጽሐፈ መነኮሳት ያስመሰከሩ ቆሞስ፣ በመጽሐፈ ሊቃውንት ያስመሰከሩ ሊቀ ሊቃውንት ናቸው፥ በዚህም እርሳቸው አራቱንም ያስመሰከሩ አራት ዓይና ናቸው። "ፆታ" ማለት "ክፍል" "ወገን" "መደብ" "ተቃራኒ የመራቢያ አካል" "ተራ" ማለት ነው፦ ዘጸአት 39፥10 ዕንቍዎቹንም በአራት "ተራ" አደረጉበት። "ተራ" ለሚለው በግዕዙ የገባው ቃል "ፆታ" ነው፥ ስለዚህ "ፆታ" የሚለው ቃል እንደየ ዐውዱ ይለያያል። ለምሳሌ፦ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ላይ፦ ""ሠራዊተ መላእክት በበፆታሆሙ ይሴብሕዎ ለእግዚአብሔር" ይላል፥ ትርጉሙ፦ "የመላእክት ሠራዊት በየምድባቸው ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባሉ" ማለት ነው። "ፆታ" ለሁለት ይከፈላል፥ አንዱ የተፈጥሮ ፆታ ሲሆን ተቃራኒ የመራቢያ አካል ያለው ወንድ እና ሴት ነው፥ ሁለተኛው የሰዋስው ፆታ ሲሆን በወንድ አንቀጽ የሚቀመጥ የተባዕታይ መደብ እና በሴት አንቀጽ የሚቀመጥ የአንስታይ መደብ ነው። ነፍስ፣ መላእክት እና ፈጣሪ "እርሱ" ወይም "እርሷ" እያልን ስንጠቀም የሰዋስው መደብ እንጂ ወንድ ወይም ሴት አይደሉም። ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ይህ ነገር ጠፍቷቸው ሳይሆን አንድ ሁለት ፉት ብለው እንደሆነ ከራሳቸው አንደበት ተናግረዋል። ይህ ዳህጸ ልሳን ሳይሆን ዳህጸ ምሥጢር ነው። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
видео или голосовое, без подписи
"ለእግዚአብሔር እንደሰው የተወሰነ፣ የተከፋፈለ፣ ቅርጽ ያለው አካል የለውም አልን እንጂ አካል የለውም አላልንም። ያ አካሉ ደግሞ ድንቡልቡል ነው አንልም። ያ በምልአት ያለው አካል ወሰን የሌለበት ዓይን፣ እጅ፣ እግር አለው። ሃይማኖተ አበው የሚገልጽልን ይህንን ነው። ዐይኑ ከሆነ ቦታ፣ እጁ ከሆነ ቦታ፣ እግሩ ከሆነ ቦታ ተከፋፍሎ አለ ማለት ግን ክሕደት ይሆናል። ዐይኑ ካለበት ቦታ ሁሉ እጁ እግሩ አለ። አንዱ ኖሮ ሌላው የሌለበት ቦታ የለም። ይህንን ካልን መከፋፈል፣ ቅርጽ ማውጣት ውስጥ መግባት ነውና። ይህ ደግሞ አእምሯችን የፈጠረው እንጂ ለእግዚአብሔር አይነገርም። ዐይን፣ እጅ፣ እግር፣...ወዘተ እንዳለው እናምናለን። ዐይኑ፣ እጁ፣ እግሩ፣...ግን የተከፋፈለ፣ ቅርጽ ያለው፣ የተወሰነ ነው አንልም" መምህር በትረ ማርያም አበባው
ምልክቶቹ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 31፥37 ሌሊት እና ቀንም ፀሐይ እና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ አምላካችን አሏህ ከእርሱ በፊት ምንም ነገር ስለሌለ "አል አወል" الْأَوَّل ነው፥ ከእርሱ በኃላ ምንም ነገር ስለሌለ "አል አኺር" الْآخِر ነው። እርሱ በሲፋቱ ግልጽ ስለሆነ "አዝ ዛሂር" الظَّاهِر ነው፥ እርሱ በዛቱ ስውር ስለሆነ "አል ባጢን" الْبَاطِن ነው፦ 57፥3 እርሱ ፊትም ያለ እና ኋላም ቀሪ፥ ግልጽ እና ስውር ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ የአሏህ ዛት ከፍጡራን ውጪ እና ባሻገር ስላለ "መጅሁል" مَجْهُول ነው፥ "መጅሁል" مَجْهُول ማለት "የማይታወቅ"Unknowable" ማለት ሲሆን ይህ አፖፋቲኮስ ነው። "አፖፋቲኮስ" ἀποφατικός ማለት "አሉታዊ"Negation" ማለት ነው። ይህንን በቀላሉ እንድትረዱ ይህንን ጥቅስ ተመልከቱ፦ ኢዮብ 36፥26 እነሆ አምላክ ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም። הֶן־אֵל שַׂגִּיא וְלֹא נֵדָע מִסְפַּר שָׁנָיו וְלֹא־חֵקֶר "እኛም አናውቀውም" የሚለው ይሰመርበት! የአሏህ ሲፋህ ፍጡራንን ያካበበ ስለሆነ "መዕሉም" مَعْلُوم ነው፥ "መዕሉም" مَعْلُوم ማለት "የሚታወቅ"Knowable" ማለት ሲሆን ይህ ካታፋቲኮስ ነው። "ካታፋቲኮስ" καταφατικός ማለት "አውንታዊ"Affirmation" ማለት ሲሆን የአሏህን ሲፋት ማስበት ነው፥ የአሏህ ሲፋት በግልጠት የሚታወቅ ነው። "ወሕይ" وَحْى የሚለው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰ ማለትም "ገለጠ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ግልጠት"Revelation" ማለት ነው፥ "ወሕይ" وَحْى እራሱ "ወሕይ ዓም" وَحْى عَامّ እና "ወሕይ ኻሥ" وَحْى خَاصّ ተብሎ ለሁለት ይከፈላል። ፨ "ዓም" عَامّ ማለት "ጥቅል"General" ማለት ሲሆን "ወሕይ ዓም" وَحْى عَامّ ማለት "ጥቅላዊ ግልጠት"General Revelation" ማለት ነው፦ 99፥5 ጌታህ ለእርሷ "በማሳወቁ" ምክንያት፡፡ بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا 16፥68 ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል "አስታወቀ"፦ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አሳወቀ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰ ሲሆን አምላካችን አሏህ በፍጥረቱ እራሱ የገለጠበት ግልጠት ጥቅላዊ ግልጠት ነው፥ "አያቱል ከውኒያህ" آيَات الكَوْنِيَّة ማለት "ተፈጥሬአዊ ምልክት" ማለት ሲሆን አሏህ እራሱን የገለጠበት በተፈጥሮ ውስጥ ምልክቶች ነው፦ 31፥37 ሌሊት እና ቀንም ፀሐይ እና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ "ምልክቶቹ" ለሚለው የገባው ቃል "አያቲ-ሂ" آيَاتِهِ ሲሆን ይህ "አያቱል ከውኒያህ" آيَات الكَوْنِيَّة ነው፦ 45፥3 በሰማያት እና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርግጠኛ "ምልክቶች" አሉ፡፡ إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ 52፥36 ወይስ ሰማያትን እና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ أَمْ خَلَقُوا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ ፨ "ኻስ" خَاصّ ማለት "ተናጥል"Specifical" ማለት ሲሆን "ወሕይ ኻስ" وَحْى خَاصّ ማለት "ተናጥሎአዊ ግልጠት"Specifical Revelation" ማለት ነው፦ 4፥163 እኛ ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ "አወረድን" ለሚለው የገባው ቃል "አውሐይና" أَوْحَيْنَا ሲሆን አምላካችን አሏህ በነቢያቱ እራሱ የገለጠበት ግልጠት ተናጥሎአዊ ግልጠት ነው፥ "አያቱ አሽ ሸርዒያህ" آيَات الشَرْعِيَّة ማለት "ሸሪዓዊ ምልክት" ማለት ሲሆን አሏህ እራሱን የገለጠበት በአንቀጾቹ ነው፦ 7፥35 የአዳም ልጆች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ በእናንተ ላይ "አንቀጾቼን" የሚያነቡ መልእክተኞች ቢመጧችሁ ከእናንተ ክሕደትን የተጠነቀቁ እና መልካምንም የሠሩ በእነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነሱም አያዝኑም፡፡ يَا بَنِي آدَمَ إِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي ۙ فَمَنِ اتَّقَىٰ وَأَصْلَحَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ "አንቀጾቼ" ለሚለው የገባው ቃል "አያቲ" آيَاتِي ሲሆን ወደ መልእክተኞቹ የሚያወርደው ወሕይ የእርሱ ምልክቶቹ ሲሆን "አያቱ አሽ ሸርዒያህ" آيَات الشَرْعِيَّة ነው፦ 18፥106 ነገሩ ይህ ነው፡፡ በክህደታቸው "አንቀጾቼን" እና መልእክተኞቼን መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሃነም ነው፡፡ ذَٰلِكَ جَزَاؤُهُمْ جَهَنَّمُ بِمَا كَفَرُوا وَاتَّخَذُوا آيَاتِي وَرُسُلِي هُزُوًا አምላካችን አሏህ በምልክቶቹ ያመኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
видео или голосовое, без подписи
የምሥራቅ ሥነ መለኮት የኦርቶዶክስ ሥነ መለኮት ሲሆን ከ 1296 ድኅረ ልደት እስከ 1359 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ጎርጎርዮስ ፓላማስ"Gregory Palamas" ያፋፋው ፓላማዊ ሥነ መለኮት"Palamite Theology" የኦርቶዶክስ አንቀጸ እምነት ሆኗል፥ ፓላማዊ ሥነ መለኮት "በኡሲያህ እና በኢኔርጌያ መካከል የእውነት ልዩነት"Real distinction" አለ" የሚል ነው። በኦርቶዶክስ ሥነ መለኮት ውስጥ ያለው በኡሲያህ እና በኢኔርጌያ መካከል የእውነት ልዩነት በፓላማዊነት"Palamism" ይፋፋ እና ይዳብር እንጂ ከጥንትም በአበው ነበረ፥ ሦስቱ የቀጰዶቅያን አበው"Cappadocian Fathers" የሚባሉት ባስልዮስ ዘቂሳሪያ፣ የባስሊዮስ ወንድም ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እና ጓደኛው ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ናቸው። ባስልዮስ ዘቂሳሪያ "ታላቁ ባስልዮስ" በሚል የሚታወቅ ሲሆን ስለ ምንነት እና ስለ የምንነት ባሕሪዮት እንዲህ ይለናል፦ "እርሱ(ኢይኖመስ) እንዳለው አምላክ ነጠላ ነው፥ እናም የእርሱን ባሕሪ"Attribute" ማወቅ የምትችሉትን ማንኛውንም ባሕሪ ከምንነቱ"Essence" ነው"። Letters (St. Basil of Caesarea) Letter 234 Number 1 "የአምላክ ታላቅነት፣ ኃይሉን፣ ጥበቡን፣ መልካምነቱን፣ በእኛ ላይ ያለውን ሲሳዩን እና የፍርዱን ፍትሓዊነትነት እናውቃለን" እንላለን፥ ነገር ግን የእሱን እውነተኛ ምንነት"Essence" አይደለም"። Letters (St. Basil of Caesarea) Letter 234 Number 1 "በምንነቱ እና በእያንዳንዱ በተዘረዘሩት ባሕሪያት መካከል ልዩነት እንዳለ እራሳቸውን አምነዋልና፥ ባሕሪያት የተለያዩ ሲሆኑ ምንነቱ ነጠላ ነው። "አምላካችንን ከባሕሪያቱ እናውቀዋለን፥ ነገር ግን ወደ እርሱ ምንነት ለመቅረብ አንዳፈርም" እንላለን፥ የእሱ ባሕሪያት ወደ እኛ ሲወርዱ ነገር ግን የእርሱ ምንነት ከአጸዳችን ባሻገር ይቀራል"። Letters (St. Basil of Caesarea) Letter 234 Number 1 ባስልዮስ ዘቂሳሪያ በግልጽ በኡሲያ እና በኢኔርጌያ መካከል ያለውን ልዩነት ፍትንው እንዲህ ከላይ አርጎ ገልጿል። የባስሊዮስ ወንድም ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በኡሲያ እና በኢኔርጌያ መካከል ያለውን ልዩነት ቁልጭ አርጎ አስቀምጧል፦ "የምትጠቀሙበት እያንዳንዱ ስም የኑባሬ ባሕሪ ነው፥ ነገር ግን የኑባሬ አይደለም"። Against Eunomius (Gregory of Nyssa) Book VII(7) Number 5 "ምክንያቱም በተፈጥሮው ከዓይናችን በላይ የሆነው አምላክ በባሕሪያቱ ይገለጻል፥ ኑባሬው በአጸዱ ባሉት ባሕሪዮት ይገለጻል"። On the Beatitudes (Gregory of Nyssa) Homily 6 ከጥንትም ጀምሮ በነበሩት አበው ሆነ በኦርቶዶክስ ሥነ መለኮት "አምላክ በኢኔርጌያ እንጂ በኡሲያ አልተገለጸም አይገለጽም" ብለው ያምናሉ። ዮሐንስ ዘደማስቆ"John of Damascus" በኡሲያ እና በኢኔርጌያ መካከል ያለውን ልዩነት እንዲህ ሲል አስቀምጦአል፦ "አምላክ የአምላክን ምንነት እንደማያሳይ እና ነገር ግን የምንነቱን ባሕሪያት ብቻ እንደሚያሳይ ማረጋገጥ እንችላለን፥ ምክንያቱም ስለ እርሱ ቸር፣ ጻድቅ፣ ጥበበኛ እና የመሳሰሉትን ስትናገር የምትናገረው የአምላክን ምንነት ሳይሆን የምንነቱን ባሕርያት ብቻ ነው"። An Exposition of the Orthodox Faith (John of Damascus) Book I(1) Chapter 4 በነገራችን ላይ በኦርቶዶክስ ሥነ መለኮት ኢኔርጌያ ያልተፈጠረ፣ ዘላለማዊ እና ኡሲያ ያልሆነ ነው፥ ኢኔርጌያ የተባሉት ችሎታ፣ ኃይል፣ ንግሥና፣ ፍርድ፣ ቸርነት፣ ምሕረት፣ ጥበብ፣ ዕውቀት የአምላክ ናቸው እንጂ እያንዳቸው አምላክ አይደሉም። "አምላክ እነዚህ ባሕርዮት አሉት" እንጂ "አምላክ ናቸው" አይባልም፥ ለምሳሌ፦ የእኔ ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ የእኔ ባሕሪዮት እንጂ እኔ አይደለሁም። የእኔ ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ ወሒድ ሳይሆኑ የወሒድ ናቸው፥ ከወሒድ ውጪም አይደሉም። ስለዚህ እኛ ሙሥሊሞች በዛት እና በሲፋት መካከል ያለውን ልዩነት ስናስቀምጥ እና የአሏህ ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ ወዘተ "አሏህ ሳይሆኑ የአሏህ ባሕሪያት ናቸው" ስንል በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁ። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! ለእኛም ኢሥቲቃማህ ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም