የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Статистика﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | ለንግድ፣ ለህክምና ወይም ለጉብኝት ወደ ቱርክ፣ ዱባይ እና የተለያዩ ሀገራት ለመጓዝ ካሰባችሁ ፈሲሩ ትራቭል የትኬት ጉዳያችሁን በኃላፊነት ያጠናቅቃል። እንግልት የሌለበት ጉዞ ለማድረግ ስትፈልጉ በዋትስአፕ አግኙን፦ https://wa.me/qr/5CWCIMYBZLCJB1
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 006
- 1/48двое суток
- 1 152
- 1/72трое суток
- 1 243
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
በአሜሪካ ሚቺጋን ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ የፕራይመሪ ምርጫ ላይ የተከሰተው ታሪክ፣ ማንነቱን ለሚክድና ሃይማኖቱን ለዱንያ ጥቅም ለሚሸጥ ሁሉ ትልቅ ማስተማሪያ ነው። አሚር ሀሰን የተባለው ግለሰብ፣ ቀድሞ ሙስሊም የነበረና በኋላ ግን ሃይማኖቱን ቀይሮ ክርስቲያን መሆኑን ያወጀ ሰው ነው። ይህ ሰው በጽንፈኛ ፖለቲከኞች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲል፣ እጅግ አክራሪ፣ ፀረ-ሙስሊምና ፀረ-ስደተኛ አቋሞችን ማንጸባረቅ ጀመረ። በዚህ የክህደት መንገዱም ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከኮንግረስ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን እና ከሴናተር ቲም ስኮት ሳይቀር ሙሉ ድጋፍን (Endorsement) አገኘ። በገንዘብም በኩል ከፍተኛ ዶላር በማሰባሰብ፣ "አሁንማ ማንም አያቆመኝም" ብሎ የተመካበት ጊዜ ነበር። ነገር ግን የአላህ (ሱ.ወ) ጥበብና ፍትህ አስገራሚ ነው። የቱንም ያህል ማንነትህን ብትክድና ሙስሊሞችን ብትጠላም፣ ፀረ-ሙስሊም የሆኑ ዘረኞች መቼም ቢሆን በሙሉ ልብ አይቀበሉህም። አሚር ክርስቲያን ነኝ ብሎ ቢምልም፣ ዘረኞቹ መራጮች ስሙ "አረብኛ/ሙስሊም" ስለሚመስል ብቻ አላመኑትም፤ ድምፃቸውንም ነፈጉት። ከዚህም በላይ አላህ ይህንን ግለሰብ ያዋረደውና መሳለቂያ ያደረገው በጠንካራ ተፎካካሪ እጅ አይደለም! አሚር የተሸነፈው ቶም ስሚዝ ለተባለ ግለሰብ ሲሆን፣ ይህ አሸናፊ ሰው፦ ⛳️ በፌስቡክ ገጹ 95 ብቻ ተከታዮች ፎሎወሮች ያሉት፣ ⛳️ ለምርጫው ከ2,000 ዶላር በታች ያወጣ፣ ⛳️ እና ከሁሉ በላይ ደግሞ "ከምርጫው ራሴን አግልያለሁ" ብሎ ላሳወቀና "ለሌላ እጩ ድምፃችሁን ስጡ" በማለት ቅስቀሳውን ላቆመ ሰው ነበር! ከምርጫው ራሱን ባገለለና ምንም ዓይነት የፖለቲካ ክብደት በሌለው ሰው መሸነፍ፣ ተራ ሽንፈት ሳይሆን ታሪክ የማይረሳው መለኮታዊ ውርደት ነው። እምነትን ሸጦ ክብርን ከሰው ልጆች መፈለግ መጨረሻው ኪሳራ ነው። ታላቁ ጌታችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ላይ፣ እውነተኛ ክብር ከማን ዘንድ እንደሚገኝ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል፡- “እነዚያ ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ እነሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን ልቅናውም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው፡፡” — አን-ኒሳዕ (4:139) የሰዎችን ውዴታ ለማግኘት ሲባል የአላህን መንገድ መተው የሚያስከትለውን አሳፋሪ ውድቀት፣ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሚከተለው ሐዲሳቸው እንደሚከተለው ገልጸውታል፡- "አላህን በማስቆጣት የሰዎችን ውዴታ የፈለገ ሰው፣ አላህም በእርሱ ላይ ይቆጣል፤ ሰዎችንም በእርሱ ላይ ያስቆጣበታል።" (ሱነን አል-ቲርሚዚ 2414) ሃይማኖቱን ሸጦ ዱንያን ለማግኘት የሞከረ፣ አላህ በዱንያም እንዲህ መሳለቂያ ያደርገዋል፤ የአኼራውም ዕጣ ፈንታ የከፋ ይሆናል። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን፤ ማንነታችንንና እምነታችንን ጠብቀን፣ ለፈጣሪያችን ብቻ አድረን በክብር የምንኖር ያድርገን! ፌስቡክ | ዋትስአፕ
без подписи
ክርስትናን በርግጥ የመሰረተው ማነው? ዛሬ በስፋት የሚታወቀው የክርስትና ሃይማኖት ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት በቀጥታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተ ሳይሆን፣ በጠርሴሱ ጳውሎስ የተቀረጸ መሆኑን የሚከራከሩ የታሪክና የነገረ-መለኮት ምሁራን አሉ። ጳውሎስ በሥጋ አይቶትም ሆነ አግኝቶት የማያውቀውን የኢየሱስን ታሪካዊ ህይወት ወስዶ፣ ኢየሱስም ሆነ የመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት ወደማያውቁት አዲስ የድነት ርዕዮተ-ዓለም ቀይሮታል። ከእርሱ በፊት ከነበሩት የኢየሱስ የቅርብ ተከታዮች ትምህርት የተለየ እና የሙሴን ህግጋት የሚሽር አዲስ ወንጌል ይዞ ብቅ ማለቱ፣ ከመጀመሪያዋ የኢየሩሳሌም አማኝ አባላት እና ከኢየሱስ ተከታዮች ጋር ከፍተኛ የሥነ-መለኮትና የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ከትቶት ነበር። ይህንን ሃሳብ ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሃያም ማኮቢ በመጽሐፋቸው በሰፊው ዳስሰውታል። ማኮቢ እንዳብራሩት፣ የጳውሎስ ትምህርት ከንጹሑ የኢየሱስ አስተምህሮ የተገኘ ሳይሆን፣ በዘመኑ ከነበሩት የግሪክ ጣዖት አምልኮዎች የተቀዳና የኢየሱስን ትክክለኛ መሲህነት ያዛባ አዲስ ሃይማኖት ነው። በመሆኑም ዛሬ የምናየው ክርስትና የኢየሱስን ቀጥተኛ አስተምህሮ ሳይሆን፣ ጳውሎስ የራሱን ራእዮች እና አመለካከቶች ተጠቅሞ የፈጠረውን እምነት መሆኑን መገንዘብ እንችላለን። • Hyam Maccoby, The Mythmaker: Paul and The Invention of Christianity, Chapter 1: The Problem of Paul. . . ⛳️ በዚህ ጉዳይ እንቀጥላለን! ፌስቡክ | ዋትስአፕ
በአሜሪካ ሚቺጋን ግዛት የተመዘገበው የአብዱልረህማን አል-ሰይድ አስደናቂ ድል፣ በዲሞክራቶችም ሆነ በሪፐብሊካኖች ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ከመፍጠሩም በላይ፣ የአሜሪካን የፖለቲካ ታሪክ አቅጣጫ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረ ይገኛል። በአሜሪካ የጽዮናውያን ዋነኛ የፖለቲካ ደጋፊ እና ሎቢስት የሆነው "አይፓክ" እና አጋሮቹ፣ የአብዱልረህማንን ተቀናቃኝ ለማሳለፍ ብቻ 65 ሚሊዮን ዶላር አፍስሰው ነበር። ይህን ያህል የገንዘብ ጎርፍ ለምን አስፈለገ? ከተባለ መልሱ ግልጽ ነው፤ የአሜሪካን ግብር ከፋይ ገንዘብ፣ የጦር መሳሪያ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የ"ድምጽን በድምጽ የመሻር" መብት በመጠቀም በፍልስጤም ህዝብ ላይ እየፈጸሙ ያለውን የዘር ማጥፋት ያለከልካይ ለማስቀጠል ስለፈለጉ ነው። በደንብ አስቡት፣ አይፓክ በአንድ የሴኔት ወንበር ምርጫ ላይ የራሱን ተላላኪ ዕጩ ለማሳለፍ ብቻ 65 ሚሊዮን ዶላር አፈሰሰ። በመጨረሻ ግን... በሕዝብ ድምጽ ተሸነፈ! ይህ የምርጫ ውጤት ከአንድ ግለሰብ ማሸነፍ ባለፈ እጅግ ትልቅ ትርጉም አለው። ላለፉት ዓመታት የተፈጸመውን ጭ*ፍጨ*ፋ በቅርበት የተከታተለው ተራው አሜሪካዊ መራጭ፤ የሀገሩ ፖለቲካ በገንዘብ በሚገዙ የውጭ ሎቢስቶች ሳይሆን፣ በሕዝቡ ፍላጎት፣ እሴትና ህሊና እንዲመራ ያለውን ጽኑ አቋም አሳይቷል። ቀድሞ በጽዮናውያን ሎቢ (አይፓክ) መደገፍ ለአንድ ፖለቲከኛ ትልቅ የድል ካርድ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ዛሬ ግን በአብዛኛው የአሜሪካ ክፍል የነሱ ድጋፍ ማግኘት እንደ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራና ውርደት መቆጠር ጀምሯል። የትኛውም የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ የሎቢስቶች ጥረት ከተራው ዜጋ ድምጽ ሊበልጥ አይችልም። የሕዝብ ገንዘብም ንጹሃንን ለመጨፍጨፍ መዋል የለበትም። የአሜሪካ ሕዝብ ግብሩ እና ሀብቱ የውጭ ሀገር ጦርነቶችንና ጭፍጨፋዎችን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ሳይሆን፣ ለፍትህ እና ለራሱ ሕዝብ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲውል አጥብቆ እየጠየቀ መሆኑን የሚቺጋኑ ድል በግልጽ አሳይቷል። ገንዘብ የሕዝብን ድምጽ መግዛት ያቃተው ታሪካዊ አጋጣሚ! ፌስቡክ | ዋትስአፕ
без подписи
በቁም እስር ላይ ያሉን የሰው ልጆች በአውሬዎች አስከብቦ ማስፈራራትና ማሰቃየት... ይህ በዚህ ዘመን የምንሰማው ሳይሆን በጨለማው ዘመን የነበሩ ጨካኝ ነገሥታት እንኳ ለማድረግ የሚከብዳቸው ተግባር ነው። ነገር ግን፣ ይሄ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በእስራኤል ምድር ሊተገበር የታሰበ እውነታ ነበር። የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር የሆነው ኢታማር ቤን-ግቪር፣ ፍልስጤማውያን የፖለቲካ እስረኞች በሚገኙበት የኬትዚኦት እስር ቤት ዙሪያ፣ "አዞዎችን" በማስቀመጥ እስረኞቹን በከፍተኛ ፍርሃትና ሥነ-ልቦናዊ ስቃይ ውስጥ ለማኖር አውዛጋቢ እቅድ አውጥቶ ነበር። ታዲያ እቅዱ ለምን ተገታ? የእስራኤል ፍርድ ቤት እቅዱን በጊዜያዊነት ያገደው ግን፣ የታሳሪዎቹ መብት ተገፎ፣ የሰው ልጅ በአውሬ ሊበላ ይችላል በሚል ስጋት ወይንም "ሰብዓዊ መብት" ተሟጋቾች በፈጠሩት ጫና አይደለም። ይልቁንም፣ 'ሌት ዘ ኤኒማልስ ሊቭ' የተሰኘ የእንስሳት መብት ተሟጋች ቡድን ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ነው። ፍርድ ቤቱ እግዱን የጣለው፦ "ይህ አሰራር በአዞዎቹ (በእንስሳቱ) ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል" በሚል ስጋት ነው። ልብ የሚሰብረው እውነታ እዚህ ላይ ነው! ዓለም ለሰዎች ሰብዓዊ መብት መቆሙ ቀርቶ፣ ለእስራኤል ፍርድ ቤትም ሆነ ለመብት ተሟጋቾች፣ ከፍልስጤማውያን እስረኞች ሕይወትና ሥነ-ልቦናዊ ደህንነት ይልቅ፣ የአዞዎቹ ደህንነት በለጠባቸው! ሰውየው በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰው ልጆችን ከቀን በቀን በአዞዎች አፍ ፊት ለማኖር ሲያቅድ፣ የዓለም ፍርድ ቤቶች የሚያስቡት ስለ እንስሳቱ እንጂ ስለ ፍልስጤማውያኑ አይደለም። ይህ በእውነት የእስራኤላውያንን ጭካኔ ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፍልስጤማውያን ያለውን ግድየለሽነትና ደብል ስታንዳርድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይህ ግፍ ግን እንዲህ አይቀጥልም፣ በአላህ ፍቃድ ፍልስጤማውያን ይህንን ሰው* በ*ላ ስርኣት ገርስሰው በነጻነት የሚኖሩበት ቀን ሩቅ አይደለም! ፌስቡክ | ዋትስአፕ
без подписи
የዘመኑ ምርጥ የዲፕሎማሲ ቀልድ! 🤣 የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳዓር ሰሞኑን ቀልድ አምሮታል መሰል ለሚዲያ ቀርቦ እንዲህ ይላል፦ "ሰዎች እስራኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተገልላለች ይላሉ... ይሄ እኮ ፈጽሞ የማይረባ ውሸት ነው! ብዙ ሀገራት ወደ እኛ እየመጡ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንደሚፈልጉ እየነገሩን ነው። ለማስረጃ ያህል... ልብ በሉ... በዚህ ሳምንት የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እኛ ጋር መጥቶ ነበር!" እውነትም ታላቅ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ድል! 👏😂 አይ የዓለም ልዕለ ኃያልነት! የዓለም መንግሥታት ሁሉ በተግባራቸው አፍረውና ህዝባቸውን ሰግተው ጀርባቸውን ቢሰጡም፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ውግዘት ቢያዘንቡም፣ አውሮፓውያን ቢሸሹም... ዋናው ነገር ኮንጎ ከእስራኤል ጎን ናት! ከ190 በላይ የዓለም ሀገራት ቢያገሉን ምን ይገርማል? ኮንጎ መጥታ ከጎበኘችንማ እንዴት "ተገልለናል" እንላለን? የእስራኤል መንግሥት የደረሰበትን የዲፕሎማሲ ኪሳራና የብቸኝነት ጥግ ከዚህ በላይ የሚያስረዳ ፖለቲካዊ ኮሜዲ ከየትም አይገኝም! እስኪ ኮንጎን አምጡልን! 🇨🇩🤝🇮🇱 😅 ቪዲዮው ፌስቡክ ኮሜንት ላይ አለ።
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe pinned a photo
ለሚቀጥለው ወር በተዘጋጀው የኡምራ ፓኬጅ በሸይኽ አብዱልዋሲዕ አህመድ መሪነትና በጋዜጠኛ አብዱረሕማን አሚን አስተባባሪበት በአላህ ፍቃድ አብረን እንጓዛለን። በነዚህ ቀናት ኡምራ ለማድረግ የነያችሁ ጉዟችሁን ከከውከብ ትራቭል ጋር ማድረግ ትችላላችሁ። የጉዟችን ዝርዝር መረጃዎች፦ • የጉዞ ጊዜ፡ ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 03 • የቆይታ ጊዜ፡ 7 ቀናት በመካ እና 3 ቀናት በመዲና በከውከብ ትራቭል ልዩ የጉዞ ጥቅል ውስጥ የተካተቱት፦ • የአየር ትኬት • የዑምራ ቪዛ • ምቹ የውስጥ ትራንስፖርት • ደረጃውን የጠበቀ የሆቴል ማረፊያ • የሁለቱንም ከተሞች ታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ለበለጠ መረጃ እና ምዝገባ፦ 📞 09 46 28 55 55 📞 09 11 27 40 33 📍 አድራሻ፡ ጀሞ 1፣ ሳባ ሕንፃ ከውከብ ትራቭል - ታማኝ የጉዞ አጋርዎ!
አንዳንድ ጉዞዎች ከእይታ ባለፈ ነፍስን ያነጋግራሉ፤ ታሪክን ህያው አድርገው ልብን በጥልቅ ስሜት ይነካሉ። ወንድማችን ጀማሉዲን ወደ ቦስኒያ ካደረገው ጉዞ በኋላ በእንግሊዝኛ ያካፈለን ይህ ማስታወሻ፣ የአንድን ህዝብ ፅናት፣ እምነት እና ስነ-ልቦና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። እጅግ ስሜትን በሚሰረስር እና በርካታ ቁምነገሮችን ባዘለ መልኩ ወንድሜ ጀማል ኡዲን የገጠመውን ገጠመኝ እና አስተንትኖ እነሆ ከዚህ በታች በመጠኑ አቅርቤላችኋለው። አንብቡት፣ ነፍስን ያድሳል! "ከቦስኒያ ስመለስ ልቤ በእጅጉ ተነክቷል። በአንድ በኩል አይንን በሚማርክ የተፈጥሮ ውበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላም ገና ባላባራ እና ትውልድ በተሻገረ ጥልቅ ሀዘንና ስነ-ልቦናዊ ስብራት የተገነባችን ምድር በአዲስ እይታ እንድመለከት አድርጎኛል። አላህ (ሱ.ወ) ይህችን ምድር በተፈጥሮም ሆነ በመንፈሳዊ ግርማ ሞገስ አድሎታል። ለምለም አረንጓዴ ተራሮች፣ ንጹህ ወንዞች እና እንደ ምሰሶ ቆመው የሚታዩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሚናራዎች... እነዚህ ሁሉ እስልምናን እና ሙስሊሞችን ከአውሮፓ እምብርት ላይ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የተቃጣባቸውን ጭካኔ የተሞላበት ዘመቻ በፅናት የተቋቋመና የተረፈ ህዝብ ህያው ምስክሮች ናቸው። ፀጉረ-ወርቅ እና ሰማያዊ አይን ያላቸውን ኢማሞች፣ የትራንስፖርት አሽከርካሪዎችን እና ሂጃብ የለበሱ እህቶችን እዛው ማግኘት አንድ ትልቅ እውነታን ያስታውሰናል። ምንም እንኳን አውሮፓዊ እና ስላቪክ (Slavic) ማንነት ቢኖራቸውም፣ እነዚህ ሰዎች በቅርቡ የሰለሙ ህዝቦች አይደሉም። ከገዛ ወገኖቻቸው እንደ ከሀዲ እና እምነት አፍራሽ ቢቆጠሩም፣ አላህን በጌትነቱ፣ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) በመልዕክተኛነታቸው በሙሉ ልብ የተቀበሉ የ15ኛ እና የ16ኛ ትውልድ ሙስሊሞች ናቸው። ዛሬ በጋዛ እና በሶሪያ የምናየውን አሳዛኝ እና ዘግናኝ እልቂት የሚያስታውስ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምባቸው እንኳን ወደ ኋላ አላሉም። ከሶሻሊዝም ስርዓት አስገዳጅ ሴኩላሪዝም በኋላም፣ ፊታቸውን በቀጥታ ወደ አላህ ነው የመለሱት። የዘር ማጥፋት ሰለባ የነበሩ ህዝቦች በመሆናቸው፣ ለጋዛ ያላቸውን ጥልቅ ስሜት እና አጋርነት በግልጽ ማየት ይቻላል። በተደጋጋሚ የቦስኒያን ባንዲራ እና የ'ስሬብሬኒካ' አበባን ከፍልስጤም ባንዲራ ጎን በክብር ተውለብልበው አይቻለሁ። ብዙዎቹ የቦስኒያ ሙስሊሞች ሰፊው የሙስሊሙ ኡማ እንደረሳቸው ይሰማቸዋል። ነገር ግን በራሳቸው የሚተማመኑ እና ለራሳቸው ትልቅ ክብር ያላቸው በመሆናቸው፣ ለይስሙላ የሚደረግ እርዳታን ወይም ባዶ ርህራሄን አይፈልጉም። እነሱ የሚፈልጉት እውነተኛ ወንድማማችነትን እና ትስስርን ነው። ብዙ ጊዜ እድለኝነትን የምንለካው በቁሳቁስ ምቾት ነው። ነገር ግን መከራን መቋቋም፣ ገንዘብ ሊገዛው የማይችለውን መንፈሳዊ ጥንካሬን እና ተወኩልን ያጎናጽፋል። ዛሬም ድረስ በዘመናችን እንዳሉት 'አስሀቡል ኡኽዱድ'፣ ከባድ ግፍ እና ሰቆቃ ሲደርስባቸው ፅናታቸውን ላላጡ ወንድም እና እህቶቻችን በቻልነውና አቅማችን በፈቀደው ልክ ከጎናቸው እንቁምላቸው። አላህ የቦስኒያን ህዝብ በረካ ያድርገው፤ አሁንም ድረስ ከእስልምና ጠላቶች ከሚሰነዘርባቸው ተከታታይ ዛቻ እና አደጋም ይጠብቃቸው። አሚን! | ፌስቡክ | ዋትስአፕ |
без подписи
ኡስታዝ ጀማል በሽር እና የታቦተ ጽዮን ትርክት! ከአመት በፊት ገደማ ኡስታዝ ጀማል በሽር አንድ አረብኛ ተናጋሪ ግለሰብ "የሙሴ የቃል ኪዳን ታቦት (ታቦተ ጽዮን) ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል" በሚል ስሜት የተናገረውን ቪዲዮ ወደ አማርኛ ተርጉሞና የራሱን አገላለጾች በመጨመር ሲያጋራ ተመልክተናል። ይህ ድርጊት በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ እንደ በጎ አቀራረብ ቢታይም፣ ከታሪክ፣ ከሥነ-መለኮት እና ከእውነተኛ ማስረጃዎች…
ኡስታዝ ጀማል በሽር እና የታቦተ ጽዮን ትርክት! ከአመት በፊት ገደማ ኡስታዝ ጀማል በሽር አንድ አረብኛ ተናጋሪ ግለሰብ "የሙሴ የቃል ኪዳን ታቦት (ታቦተ ጽዮን) ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል" በሚል ስሜት የተናገረውን ቪዲዮ ወደ አማርኛ ተርጉሞና የራሱን አገላለጾች በመጨመር ሲያጋራ ተመልክተናል። ይህ ድርጊት በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ እንደ በጎ አቀራረብ ቢታይም፣ ከታሪክ፣ ከሥነ-መለኮት እና ከእውነተኛ ማስረጃዎች አንጻር ሲመዘን ግን ትልቅ ስህተትና ሚዛኑን የሳተ አካሄድ ነው። እንደ ኡስታዝ ጀማል ያለ በእስልምናውም ሆነ በሌሎች እውቀቶች ግንዛቤ አለው ተብሎ የሚታሰብ ሰው፣ የክርስትናውን አማኝ ስሜት ለማስደሰት (crowd-pleasing) ብቻ ሲል፣ በራሱ በክርስትናው መሠረታዊ መጽሐፍት ጭምር ውድቅ የተደረገን "ትውፊታዊ ተረት" አጉልቶ ማቅረቡ በእጅጉ ያሳዝናል። እውነታው ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ታቦተ ጽዮን ምን ይላል? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታቦቱ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በንጉሥ ሰሎሞን ጊዜ (በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት) ነው ብላ ታስተምራለች። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ትርክት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ያደርገዋል። እንዴት ካሉ ከዚህ በታች በዝርዝር እንመልከተው፦ • ከሰሎሞን በኋላ ከ300 ዓመታት በላይ ታቦቱ እስራኤል ነበር። ከሰሎሞን በኋላ 16ኛ ንጉሥ በሆነው በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ እዛው እስራኤል ውስጥ መኖሩን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይዘግባል፦ "እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት... እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም" (ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3)። • ለምን በትከሻቸው ይሸከሙት ነበር? ከኢዮስያስ በፊት ምናሴ በነገሰበት ዘመን ቤተ መቅደሱ ውስጥ ጣዖት አስገብቶ ስለነበር (ዜና መዋዕል ካልዕ 33፥7-8) ካህናቱ ታቦቱን ላለማስነካት ተሸክመውት ይዞሩ ነበር። ኢዮስያስ ይህን አስቁሞ ታቦቱን ወደ መቅደሱ መለሰው። እንግዲህ ታቦቱ በኢዮስያስ ዘመን (ከሰሎሞን ሞት 300 ዓመት በኋላ) በእስራኤል ከነበረ፣ "በሰሎሞን ጊዜ ኢትዮጵያ ገባ" የሚለው ትርክት መሠረተ ቢስ መሆኑን መጽሐፉ ራሱ ያረጋግጣል። የታቦቱ የመጨረሻ እጣ ፈንታ (በባቢሎን ምርኮ) በመጨረሻም እስራኤላውያን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር ሲወረሩ ቤተ መቅደሱ ፈረሰ፤ ንዋየ ቅዱሳቱም ተዘረፉ። • "የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ... እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ... የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ" (ዜና መዋዕል ካልዕ 36፥17-20)። በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ብቻ ተቀባይነት ያለው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በሆነው "መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል" ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ በግልጽ ሰፍሯል፦ • "...የእግዚአብሔርንም ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግስት ቤትም ያለውን ሳጥኑን ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ" (ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ 1፥54)። • "...የህጋችን ማደሪያ ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች፣ ንዋየ ቅዱሳት እንዳደፉ... ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮን እንደጠፋች ቀረች፤ ከሷም ንዋየ ቅዱሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን" (ዕዝራ ሱቱኤል 9፥21-23)። የአክሱሙ ታቦትና የፓትርያርኩ ምላሽ ከጥቂት ዓመታት በፊት የአሁኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ጋዜጠኛዋ ታቦቱ በአክሱም ስለመገኘቱ አንስታ "እንደ ፓትርያርክ እርስዎ አይተውታል ወይ?" ብላ ለጠየቀቻቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ "አባቶቻችን አይተውታል፣ በእርግጥ እኔ እስካሁን አላየሁትም" ማለታቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። መስቀልም ሲመጣ "እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው" የሚባለውን ትውፊት ስንሰማ ይህ የፓትርያርኩ ንግግር እውነታውን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። ታሪካዊና ምሁራዊ ጥናቶችም "ክብረ ነገሥት" በተሰኘው የ14ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ድርሳን ላይ ከተጻፈው ትውፊት ባለፈ፣ በአክሱም የሙሴ ጽላት መኖሩን የሚያረጋግጥ አንዳችም ታሪካዊም ሆነ አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃ አላገኙም። ለኡስታዝ ጀማል በሽር እና ለመሰል ወንድሞች የሚሰጥ ምክር ኡስታዝ ጀማል በሽር እንደ አንድ ሙስሊም ምሁር፣ እስልምና ስለ ታሪካዊ እውነታዎች የሚያስተምረውንና በተጨባጭ የታሪክ መዛግብት የተረጋገጠውን እውነት መከተል እንጂ፣ የሰዎችን ስሜት ለማስደሰት ሲባል የስህተት ትርክቶችን ማራገብ አልነበረበትም። በእስልምናም ቢሆን ቁርኣን ስለ "ታቡት" (የቃል ኪዳኑ ታቦት) ሲያወራ፣ ታቦቱ በእስራኤላውያን (በጧሉት/ሳኦል ዘመን) እጅ እንደነበር እና መላእክት ተሸክመውት እንደመጡ (ሱረቱል በቀራህ 2፡248) ይገልጻል እንጂ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመኖሩ የሚጠቁም ምንም አይነት ኢስላማዊ መሠረት የለም። የሌላውን እምነት ተከታይ ማክበርና አብሮ መኖር ማለት፣ የማናምንባቸውን መሠረተ-ቢስ የሆኑ ትውፊቶቻቸውን እንደ እውነት እያጋነኑ ማቅረብ ማለት አይደለም። ሃይማኖታዊ መቻቻል የሚገነባው እርስ በርስ መብትን በማክበር እንጂ፣ በነገረ-መለኮት እና በታሪክ ተቀባይነት የሌላቸውን ትርክቶችን በማዳነቅ አይደለም። ኡስታዝ ጀማልም ሆነ ሌሎች የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች ቪዲዮዎችን ሲተረጉሙ ታሪካዊ እውነታን፣ የነገረ-መለኮት ሚዛንን እና የምክንያታዊነትን መነጽር ሊጠቀሙ ይገባል። ከምንም በላይ ሙስሊምነት ደግሞ ለነዚህ ስራዎች ሁሉ ሚዛን መሆኑን አለመዘንጋት ተገቢ ነው። | ፌስቡክ | ዋትስአፕ |
без подписи
ከ 'ABC News' ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሚቀርብበትን የዘር ማጥፋት ክስ "ፈጽሞ የማይረባ ነው" በማለት ሊያጣጥለው ሞክሯል። መከራከሪያው ደግሞ ምን ቢሆን ጥሩ ነው? "እስራኤል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የጽሑፍ መልእክቶችን እና የስልክ ጥሪዎችን ለንጹሃን ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች፤ ስለዚህ የዘር ማጥፋት እቅድ የላትም" የሚል አባባል ነው። ምናልባት የኔታንያሁ አማካሪዎች አንድ የረሱት ነገር ይኖር ይሆን? እስራኤል የጋዛን የቴሌኮም መሰረተ-ልማቶች ደጋግማ በቦምብ በማጋየት የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ እንዳቋረጠች ማን በነገራቸው! ኔትዎርክ በሌለበት የቁም እስር ቤት ውስጥ፣ ንጹሃኑ ፈልገው እንኳ ቢሆን እነዚህን "የማስጠንቀቂያ" መልእክቶች ሊቀበሉ እንደማይችሉ ጠፍቶት ነው? ይባስ ብሎ፣ ይህ በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖረው የዘመናችን አውሬ የሆነው ግለሰብ፣ የንጹሃን እልቂት "በሂደት እየቀነሰ መምጣቱን" እንደ እስራኤል በጎ ፈቃድና ርህራሄ ማረጋገጫ አድርጎ ሊያቀርበው ሞክሯል። ሌላው አስገራሚው ንግግሩ ደግሞ፣ "ማንኛውም ሰው 'Google Maps'ን ተጠቅሞ መሬት ላይ ምን እየተፈጠረ እንዳለ ማረጋገጥ ይችላል" ማለቱ ነው። ምናልባት በዚህ ንግግሩ፣ ጋዛ ላይ የደረሰው ዘግናኝ ውድመት ኢንተርኔት ላለው ማንኛውም የዓለም ዜጋ ከጠፈር ጭምር በግልጽ ይታያል ማለቱ ይሆን? መቼም ከእግር ጥፍሩ እስከራስ ጸጉሩ በንጹሀን ደም የጨቀየ ግለሰብ ኃፍረተ ቢስነቱ አያስደንቀንም! | ፌስቡክ | ዋትስአፕ |