tgindex
Abu Ruhama

➧«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ»፡፡ (ማኢዳ፥3)

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
26
Всего постов
33
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
978
−2 за 3 дн.
Сутки
−2
−0,20%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
13
32 постов
Вовлечённость
1,3%
к подписчикам
Постов в день
3,7
всего 33
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
11
1/48двое суток
12
1/72трое суток
13

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.7из Yahyanuhe

    የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስሜታዊ ፍጡር ነው። በዘመናዊው የሥነ-ልቦና እና የፊዚዮሎጂ ሳይንስ እንደተረጋገጠው፣ በአካል መነካካት በሰውነታችን ውስጥ እንደ "ኦክሲቶሲን" እና "ዶፓሚን" ያሉ የቅርበት እና የስሜት መነሳሳትን የሚፈጥሩ ሆርሞኖች እንዲመረቱ ያደርጋል። ንክኪ በሁለት ሰዎች መካከል ያለውን ሥነ-ልቦናዊ የርቀት ግድግዳ የማፍረስ ከፍተኛ ኃይል አለው። ​እስልምና ይህንን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ (ፍትወተ-ሥጋ) በሚገባ ያውቃል። በመሆኑም ሎጂኩ እጅግ ግልጽ ነው፦ "አንድን አደጋ ለመከላከል፣ ወደ አደጋው የሚያደርሱትን መንገዶች በሙሉ መዝጋት ያስፈልጋል።" አንድ ሰው በሚያዳልጥ ጭቃ ላይ እየተንሸራተተ "አልወድቅም" ብሎ ማሰብ እንደማይችለው ሁሉ፣ የሰውን ልጅ ከተፈጥሯዊ ስሜቱ ጋር እያጋጩ "በንጹህ ልብ ከተደረገ ችግር የለውም" ማለት ምክንያታዊነት የጎደለው የዋህነት ነው። ለዚህም ነው እስልምና መጨባበጥን እንደ አንድ የዝሙት መግቢያ በመቁጠር አስቀድሞ በር የሚዘጋው። መጽሀፍ ቅዱስ በማቴዎስ ወንጌል፣ ምዕራፍ 5፣ ቁጥር 28 ፦ "ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል"። ይላል። ​እዚህ ላይ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ እናንሳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ "ማየት" ብቻውን የልብን ንጽህና አጉድፎ ወደ "ልብ ዝሙት" ያደርሳል ብሎ ካመነ፣ ከእይታ በበለጠ እጅግ ጠንካራ ስሜትን የሚቀሰቅሰው "አካላዊ ንክኪ (መጨባበጥ)" እንዴት "በንጹህ ልብ" በሚል ሰበብ ችላ ሊባል ይችላል? እይታ ኃጢአት ከሆነ፣ መነካካት በሎጂክ ደረጃ የከፋ ነው። አላህ የሰው ልጅን የፈጠረ ጌታ እንደመሆኑ፣ ለሰው ልጅ የቱ እንደሚበጀው አስቀድሞ በማወቅ መከላከያ አጥርን አበጅቶለታል። እስልምና እጅግ ተግባራዊ (Practical) የሆነ ዲን ነው። በሽታው ከመጣ በኋላ መድኃኒት ከመፈለግ፣ በሽታው የሚመጣበትን መንገድ አስቀድሞ ማድረቅን የሚመርጥ መለኮታዊ ሀይማኖት ነው። ፌስቡክ | ዋትስአፕ

  • 14 авг.10из Seidsocial

    ኔታኒያሁ እንግሊዝ በቅርቡ ኢስላማዊት ሪፐብሊክ መሆኗን መግለፁ በአለምአቀፍ ሚዲያዎች ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። የወራሪዋ እና ህገወጥ ሰፋሪዋ ሀገር መሪ እንግሊዝን ኢስላማዊት ሪፐብሊክ ብሪታኒያ ሲል ጠርቷታል። ናታኒያሁ አክሎም እንግሊዝ የኑክሌያር መሳሪያ የታጠቀች ሙስሊም ሀገር ናት ብሏታል። ኔታኒያሁ ይህን ያለው የእንግሊዝ ፖለቲካ በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩን ተከትሎ ነው። በእንግሊዝ ውስጥ በርካታ ሙስሊም ባለስልጣናት ወደ ፊት እየመጡና የሙስሊሞች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ከመሆኑም ሌላ እንግሊዝ የቀድሞ ድጋፏን ለእስራኤል መቀነሷን ተከትሎ ኔታኒያሁ በኢስላማዊነት ፈርጇታል። አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርን በእስራኤል አመራሮች ፣ ተቋማትና ሰፋሪዎች ላይ ማእቀብ እንደሚጥሉ መናገራቸውን ተከትሎ እስራኤል ቁጣዋን ገልፃለች። የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊስተን ቸርች ልጆች ከእስራኤል ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት የተጓዙበትን ታሪክ አስተዋሶ እንግሊዝ ምን ያክል የእስራኤል ጠበቃ እንደነበረች የገለፀው ናታኒያሁ አሁን ላይ ያንን ማሰብ እንኳ አይቻልም አሁን ያለቺው ኢስላማዊቷ ሀገር እንግሊዝ ነች ብሏል። የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስም በሰጠው መግለጫ እንግሊዝ በኢስላሞች ትዋጣለች አሜሪካም ቀጣይ ፕሬዚዳንቷ ሙስሊም ሊሆን ይችላል በማለት የተሰማውን ስጋት ተናግሯል። ቴሌግራም 👉 t.me/Seidsocial

  • ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በእኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።" አሏሁመ ሶሊወሰሊም ወባሪክ ዐላነቢይና ሙሀመድ                   صَلَّى اللّٰهُ عَلَيهِ وَاٰلِهٖ وَسَلِِّم ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢠⣶⣦⣀ ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⣾⣿⣿⣿⣷⡄ .  .  የጁሙዓ ስጦታ🎁⢀⢀⢀⢻⣿⣿⣿⡿ ⢀⢀⢀⢀  ⢀ ይጫኑ        ⣠⡶⠿⠛⠛⠉⠁ ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢸⡆⢀⢀⢀⡴⠚⠉ ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⠈⡇⢠⣿⣿⣷⣶⣶⣶⣶⣶⣶⣤⣤⣤⣤⡄ ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⣷⢀⠉⠉⠉⠙⠛⠛⠛⠛⢛⣿⣿⣿⣿⣿ ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⣿⡀⢀⢀⢀⢀⣀⣴⠶⠟⠋⠉ ⢸⣆⣀⣀⣀⣤⣶⡞⠈⣇⢀⢀⡴⠟⠉ ⠸⠿⠿⠿⠿⠟⠛⠁⢀⢻⣆⣾⡀ ⢀⢀⢀ﷺ⢀⢀⢀⢀⢀⠻⣿⣿⣦⡀ ⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⢀⠙⠿⣿⣿   🕌ሶሉ ዓላ ረሱሊላህ‼️   🛰𝐀𝐝𝐝 ሱና 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥         ✉️⇊⇊⇊⇊📨 © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@HikmaWave_bot

  • እንደነዚህ ሰዎች የክፋት ስብከት ግን ሙስሊሞች ላይ የደረሱ ጉዳቶች በጣም ትንሽ ናቸው ማለት ይቻላል። እንደነሱ ሴራና ክፋት ቢሆን እልቂቱም ጉዳቱም ከደረሰው በላይ ይሆን ነበር። እንደነሱ የክፋት ስብከት ሀገሪቷ እስካሁን መዝለቋም ተአምር ነው። ነጋ ጠባ በዚህ ልክ መር ^ዝ የሚጋት ህዝብ እንደነሱ ቅስቀሳ አለመሆኑም በአንፃራዊነት በጣም ከነሱ የተሻለ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 🌱⓶) በታጋሽነቱ የሚታወቀው ነቢይ ማን ይባላል⁉️       ተሳተፉ ቀላል ጥያቄ ነው! ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@HikmaWave_bot

  • 🌱መላእክት ሲያዩት የሚፈሩት ሶሓቢ ማን ነው⁉️ © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@HikmaWave_bot

  • 📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰#አልዓርቢዓዐ 2⃣9⃣  #ሰፈር 1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ

  • የማለዳ መልእክት (44) ~ ስለ ሌሎች ጥፋት መናገር የሚፈልግ ሰው የመጀመሪያው የሚጠበቅበት ነጥብ ማስረገጥ ነው። የተነገረን ነገር የእውነት በተወራው መልኩ ነው ወይ? ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ማስረገጥ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፣ ዋጂብ። አሉባልታ ላይ ተመስርቶ ማማት፣ ፍረጃ ውስጥ መግባት፣ ነገር ማራገብ፣ ለመልስ መቸኮል፣ ... አንደኛ ከተቅዋ ጋር የሚሄድ አይደለም። ሁለተኛ ከማንም በላይ የሚጎዳው እኛኑ ነው። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ كَفى بالمَرءِ كَذِبًا أن يُحَدِّثَ بكُلِّ ما سَمِعَ "አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ከውሸት በኩል (ውሸታም ለመባል) በቂው ነው።" [ሙስሊም፡ 5] ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “በሰው ላይ መዋሸት ሰውየው ሙስሊምም ሆነ ካ^ፊር፣ መልካምም ሆነ አመፀኛ ሙሉ ለሙሉ ክልክል ነው። በሙእሚን ላይ መቅጠፍ ግን የከፋ ነው፡፡” [መጀመዑል ፈታዋ፡ 28/ 223] ውሸቱ ሰላም የሚያደፈርስ፣ ሰዎችን የሚያቆራርጥ፣ ደዕዋን የሚያሰናክል ከሆነ ደግሞ በሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂነት ስለሚኖር በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 29 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • #NationalDialogue🇪🇹 በ4 የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ላይ መግባባት ተደረሰ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር፣ 4 የሥራ ቡድኖች በተመካከሩባቸው ምክረ ሃሳቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አሳውቋል። እነዚህም አጀንዳዎች፦ • የሃይማኖት ጉዳዮች • የሰላም ግንባታ • የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርዓት • ሙስናና መልካም አስተዳደር .... ጉዳዮች ናቸው። እያንዳንዱ አጀንዳ 500 ተሳታፊዎች ባሉት የሥራ ቡድን ሲመከር ቆይቷል። ቡድኖቹ በተጠናቀሩ የጋራ ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ ተስማምተው በቃለ ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈራረም መግባባቱን አረጋግጠዋል። በቀሪዎቹ አጀንዳዎችም በቀጣይ ቀናት ተመሳሳይ ምክክርና የመግባባት ሂደት እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ ገልጿል። (ዝርዝር መረጃዎችን የምናቀርብ ይሆናል) ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 7 ሚሊዮን ኮደርስ በዚህ ክረምት ethiocoders.et ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ " ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል " ሲሉ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ጥሪ አቅርበዋል። የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ እንደሚገኙ ገልጸው የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልጸዋል። " 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል፣ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው " ብለዋል። እስከ ሰኔ 2018 ዓ/ም ድረስ የሰልጣኞች ቁጥር 5,005,146 ሲሆን እስከ ነሃሴ 2018 ዓ/ም ይህን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ ግብ ተቀምጧል፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት በኢኒሼቲቩ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሂዷል። መድረኩ የዘርፉን መሪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች፣ የምስክር ወረቀት ያላቸው የኢኒሼቲቩን ምሩቃን እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድ ላይ አገናኝቷል። ተሳታፊዎች ተሞክሯቸውንና እይታቸውን በመድረኩ እንዲያካፍሉ መደላድልን የፈጠረ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ በተግባራዊ ዲጂታል ክህሎት ልማት አማካኝነት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አጀንዳ ዕድገት የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱ ተገልጿል። ‎ ‎መርሃ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም ንግግር አድርገዋል። የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ፤ የወጣቶች የቴክኒክና ዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው፣ የኮደሮችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊዮን ለማድረስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል። በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ (gheero) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤተልሔም ደሴ፣ የኢኒሼቲቩ ምሩቃን አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም በፓናል ውይይት ላይ ተሳትፈዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ወጣቶች  ፦ - ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ፣ - በተግባር ላይ ያተኮሩ መፍትሔዎችን እንዲያበለጽጉ፣ - በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገትና ፈጠራ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ አበረታተዋል። ወጣት ተሳታፊዎች የዲጂታል ክህሎትን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለፓናሊስቶች አቅርበው ምላሽ ያገኙበት ሲሆን አጠቃላይ መርሃ ግብሩ ግልጽ ውይይትና የልምድ ልውውጥ የተስተናገደበት ነው። ይህ የልምድ ልውውጥ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ እና ሀገራዊ ለውጥን ለማፋጠን ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል። የልምድ ልውውጥ መድረኩን በዚህ ይከታተሉ ፦ https://youtu.be/7zQ0gY90XLA?si=pTAgMXGz0VBoHV4u እንዴት ልመዝገብ ? ከ5 ሚሊዮን ለተሻገረው ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ለመመዝገብ 👉 ethiocoders.et ይጫኑ። የምስክር ወረቀቱ ዓለም አቀፍ እውቅና አለው። ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • #ኢራን የመካ ስምምነት የቀጣናውን ከ #አሜሪካ መራቅ የሚያሳይ ነው አለች፤ “ሰምምነቱ የሚያሳስብ ነገር አይደለም” ስትልም ገለጸች ኢራን በ #ሳዑዲ_ዓረብያ፣ በ #ፓኪስታን እና በ #ቱርክ መካከል የተፈረመው የሶስትዮሽ የመከላከያ ስምምነት አገራት ስለ አሜሪካ ያላቸውን አመለካከት መለወጡንና በራሳቸው የደኅንነት መዋቅር ላይ መተማመናቸውን የሚያሳይ ነው ስትል ገልጻለች። ቴህራን አክላም ስምምነቱን እንደ ስጋት ለመመልከት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለ አስታውቃለች። ቱርኪ ቱደይ እንደዘገበው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ ይህንን አስተያየት የሰጡት ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ቃል አቀባዩ አሜሪካን በማመላከት “ደኅንነት ከሐሰተኛ ደላሎች የሚገዛ ሸቀጥ አለመሆኑን” የቀጣናው ሀገራት ተገንዝበዋል ብለዋል። እስማኤል አክለውም ኢራን ከሳዑዲ ዓረብያ፣ ከፓኪስታን እና ከቱርክ ጋር ያላትን “ጥልቅ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እና የሥልጣኔ ቁርኝት” በመጥቀስ ስምምነቱ በቴህራን ላይ ያነጣጠረ ነው ብሎ ለማሰብ “ምንም ምክንያት የለም” ብለዋል። https://www.facebook.com/share/p/1PHrdA3a66/

  • በነገራችን ላይ ዐረብኛ ቋንቋ የዐረቦች ብቻ አይደለም፣ የመላው ዓለም ሙስሊሞችም ጭምር እንጂ። 0ረብኛ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ የኢስላም ቋንቋ ነው። ዐረብኛ የሶላት፣ የዚክር ቋንቋ ነው። ስለዚህ ኢስላም ማንነታችን እስከሆነ ድረስ ዐረብኛ ቋንቋ የማንነታችን አካል ነው። ስለሆነም የማንችለው ለመቻል፣ የምንችለው ለማሻሻል ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። በአራቱም የቋንቋ ክህሎቶች (መናገር፤ ማዳመጥ፣ መፃፍ እና ማንበብ) ላይ አቅማችንን ለማዳበር ብንጥር እንጠቀማለን። አላህ አግርቶለት ቋንቋውን የቻለ ደግሞ በሂደት እንዳይረሳው የሚችሉ ሰዎች ጋር ሲገናኝ ቢጠቀምበት መልካም ነው። ዛሬ ደግሞ ዐረብኛ ለሚሊዮኖች የእንጀራ ሰበብም ሆኗል። ስለዚህ ከራሳችን አልፎ ልጆቻችንም እንዲማሩት ትኩረት ብንሰጥ መልካም ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 ጀምሮ የሚተገበሩ 11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶችን ይፋ አደረገ ነጃሺ ቲቪ || ነሐሴ 5/2018 የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር ተግባራዊ የሚደረጉ 11 ተጨማሪ የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶችን ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ እንዳመለከተው፣ በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሠረት የሙያና ቴክኒክ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከተማሪዎች የእድሜ ደረጃ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲካተት ተደርጓል። በዚህም መሠረት በ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን የሙያ መስክ እንዲመርጡ አቅጣጫ የሚሰጥ ትምህርት እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ደግሞ በተለዩ የሙያ ዓይነቶች ከተለመደው ትምህርታቸው ጎን ለጎን ሰፊ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ12ኛ ክፍል 12 የሙያ ዓይነቶች እየተሰጡ እንደሚገኙ የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የሚሆኑ ተጨማሪ 11 የሙያ ዓይነቶች ይፋ ሆነው የትምህርት መመሪያዎች (Syllabus) ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቋል። በመሆኑም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ከወዲሁ ዝርዝር ዕቅድ በማዘጋጀትና አስፈላጊውን በጀት በመመደብ፣ ትምህርት ቤቶችን እና የተማሪዎችን ቁጥር በመለየት፣ ለአዲሶቹ የሙያ ዓይነቶች መምህራንን በመመደብ፣ የማስተማሪያ ግብዓቶችን በማሟላት እንዲሁም የመምህራንና የትምህርት አመራሮችን አቅም በመገንባት፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። በ ሐቢብ በሽር

  • ሶፍትዌር ደቨሎፕመንት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ ከሚሰጡ ሙያዎች መካከል ተካቷል።

  • ከታላቅ ቅናሽ ጋር‼️ 🛍ማስተዋወቅ የሚፈልጉት ነገር አለ ? 🪬 መልሶት አዎ ከሆነ ከእኛ ጋር በመስራት የፈለጉትን ማስታወቂያ አሪፍ ባላቸው ቻናሎችና ባሉን የዌቭ ፎልደሮች በማስተዋወቅ ስኬታማነትዎን እና ተደራሽነትዎን ያስፉ። ★የቁርአን ማስታወቂያ ★የቻናል  ማስታወቂያ ★የድርጅት ማስታወቂያ ★የተለያዮ አልባሳት ★የ መድሀኒቶችን ማስታወቂያ ★የክፍት ስራ ቦታ ማስታወቂያ ★የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ★የስልክ እና የlaptop ★ የዑምራ ፓኬጅ ማስታወቂያ ★ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ★የትምህርት ተቋማት…... ★ የህክምና ማዕከላት  ★የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች…… ★ ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች...... ህጋዊነት ያለውንና ሐላል የሆነ ማንኛውም ማስታወቂያ ቻናላችን ላይ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ! ✉️ Đм нєяє  @HikmaWave_bot

  • እውነት ነው ኣ ፌሚኒስቶች¿

  • እናንተም ተሳተፉና ተበሉ! አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት ሽመልስ እና ቤተሰቦቻቸው፣ በዘመናዊ የዲጂታል ቀማኞች ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ ተዘርፈዋል። ጉዳዩ የተጀመረው «ቤት ቁጭ ብሎ በወር ከ70 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር መሥራት ይቻላል» በሚል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚወጣ አታላይ ማስታወቂያ ነው። የቤት እመቤት የሆነችው ባለቤታቸው ነገሩን አምና አፕሊኬሽኑን ስትሞክረው፤ ወደ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ግሩፖች በመግባት «አሊባባ ኦንላይን ንግድ» በሚባል አደገኛ መዋቅር ውስጥ ትገባለች። አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን ለማጥመድ የተካኑ ስለሆኑ፣ እምነት ለማግኘት ሲሉ በመጀመሪያ 800 ብር ልከው 1,500 ብር ይመልሱላቸዋል። ቤተሰቡም «ነገሩ እውነት ነው» ብሎ እንዲያምን ያደርጉታል።ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ትክክለኛው ሰቆቃ የሚጀምረው። የገንዘቡ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲመጣ፣ የራሳቸውን ቁጠባ ጨምሮ ከውጭ ሀገር ከምትኖር የባለቤታቸው እህት ጭምር 600,000 ብር ተበድረው ገቢ ያደርጋሉ። አጭበርባሪዎቹ ጨካኝነታቸውን አሳይተው «አንደኛ ደረጃ ነጋዴ ስለሆናችሁ ከፍተኛ ግብር መክፈል አለባችሁ» በማለት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስገቡ አድርገው በድምሩ 1.3 ሚሊየን ብር እንዲዘረፉ አድርገዋቸዋል። በሐሰተኛው መተግበሪያ ላይ 3 ሚሊየን ብር አትርፈዋል ተብሎ ይታይባቸውም ነበር፤ ነገር ግን ገንዘቡን ማውጣት ሳይችሉ ቀርተው አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! ይህ ሁሉ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት በሥራ ስምሪት (ፊልድ) ላይ ነበሩ። የገንዘቡን መበላት ስትሰማ የባለቤታቸው ልብ ድንጋጤን መቋቋም አቅቶት ዛሬ ላይ በጽኑ ታማ በጸበል ቦታ መንፈሳዊ ሕክምና እየተደረገላት ይገኛል። የዕድሜ ልክ ድካማቸው በአንድ ቀን ባዕድ ኃይል መናጋቱ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከቷቸዋል። የማለዳ ቤተሰቦች ሆይ! ዛሬ ሶሻል ሚዲያ ላይ «ቀላል ገንዘብ፣ ያለ ሥራ ብዙሀብት» የሚሉ ማስታወቂያዎች በዝተዋል። ከዚህ በፊት ብዙዎችን አጥምደዋል፤ አሁንም እየጨረሱ ነው። እባካችሁ ይህንን መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት (በማካፈል) ሕብረተሰቡ ከዚህ መሰል የዲጂታል ቀማኞች ራሱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ እንፍጠር። የተሰበረውን ቤተሰብ ፈጣሪ ያጽናናቸው! ማለዳ

  • 9 авг.13из ..

    ልብህን ለማን እንደምትሰጥ እወቅ! የዱኑያ ምሽት ላይ እንደመሆናችንና የመሲሐድ'ደጃል መምጫም እንደመቃረቡ ዲኑ ላይ የሚጫወቱና እራሳቸው ተደናብረው ኡማውን የሚያደናብሩ ሰዎች በዝተዋል። ማህበራዊ ሚዲያውም የራሱ ጥሩ ጎን እንዳለው ሁሉ ሰዎችን ማሳሳትና ግራ ማጋባት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ  ይገኛል። መችና ከማን የሸሪዓህ እውቀት እንደተማሩ የማይታወቅ ሰዎች በካሜራ (በስልክና ኮምፒዩተር) መስኮት ብቅ እያሉ የፈለጉትን ሐላል፣ የፈለጉትን ሐራም ብለው ያለ በቂ እውቀት በስሜትና በግምት በመናገር ብዙ አላዋቂዎችን ያሳስታሉ። ከዚህም አልፎ ገና አዲስ ወደ ኢስላም የገቡ ወንድምና እህቶች እራሳቸው እንኳ ዲኑን በትክክልና በጥልቀት ሳይረዱ መደበኛ አስተማሪ ሆነው ቀርበው ኢስላምና ሙስሊሞችን ወክለው ሲናገሩና ሲከራከሩም ይታያል !! ይህ በጣም ይገርማል፤ ያሳዝናልም! ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እንደ ትልቅ አዋቂ ቆጥረው የሚከተሏቸውና ልባቸውን የሚሰጧቸው ሰዎች ሁኔታ ነው!! ኢስላማዊ እውቀት የዲኑ/የእምነቱ አንድ አካል ነው፤ ከኔ ይሻላል ከሚሉት ሁሉ (ከየትም፣ ከማንም) እውቀትን ዝም ብሎ መቀበል እምነትን ሊያበላሽ፣ ማንነትና አስተሳሰብን ሊቀይር ይችላልና ምላስና ድፍረት ስላለው ብቻ ራሱን በራሱ ጊዜ አስተማሪ አድርጎ የቀረበን ሁሉ ከመስማትና ከመከተል እንጠንቀቅ!! ለአካላዊ ጤናችን ሃኪም ከምንመርጠው በላይ ለልብና ለእምነታችን መሪና መካሪ እንምረጥ። ትልቁ መሲሐድ'ደጃል ከመምጣቱ በፊት ለሱ መንገድ የሚያመቻቹ ብዙ ትናንሽ ደጃሎች እንዳሉ ተነግሯል። ቂያማ ሲቃረብ ሸይጣን በሰው ተመስሎ አስተማሪ ሆኖ እንደሚቀርብም ተገልጿልና ልብህን ለማን እንዳምትሰጥ/ጪ፣ የሸሪዓህ እውቀትን ከማን እንደምትቀስም/ሚ ጠንቅቀህ/ሽ እወቅ/ቂ። የሸሪዓህ እውቀትን ከምንጩ ያልወሰደና በዑለሞች ያልተመሰከረለት የዩቱበር፣ የቲክቶከርና ፌስቡከር ...  መጫወቻ እንዳትሆን/ኚ!! ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

Abu Ruhama — tgindex