Telkhis (هذه عقيدتنا)
Статистикаይህ እኔ ወንድማችሁ "አህመድ ሲራጅ ሙሐመድ" ከተለያዩ ምንጮች ያገኘኋቸውን ቁም ነገር አዘል መልእክቶች የማጋራበት ቻናል ነው። ስለተወዳጁኝ አመሰግናለሁ። ጌታዬ ሆይ!! ወንጀሌን ሁሉ ይቅር በለኝ። አባቴንም ከፍ ካለችዋ ጀነት ኗሪ አድርግልኝ። እናቴንም በጤና ጠብቅልኝ። ሁሉንም ሙእሚን እና ሙእሚናትን ማራቸው፣ ይቅር በላቸው። رب اغفر لي ولوالدي وللمؤمنين والمؤمنات
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 177
- 1/48двое суток
- 202
- 1/72трое суток
- 218
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🎉✨ ታላቅ የምርቃትና የዳዕዋ ፕሮግራም✨ 🎓 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ወሎ ቅርንጫፍ፣ደሴ ላለፉት 2 አመታት በዲፕሎማና በሰርተፍኬት መርኋግብር ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን ለማስመረቅ የፊታችን ቅዳሜ ነሀሴ 2/2018 በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል። 🌹የፕሮግራሙ ተጋባዥ እንግዶቻችን ✅ ሸይኽ ኢልያስ አህመድ ✅ ሸይኽ ሙሀመድ ኢድሪስ ✅ ኡስታዝ አዩብ ደርባቸው እና ሌሎችም ታላላቅ መሻይኾችና ኡስታዞች ተጋብዘዋል። በዕለቱ በተመራቂ ተማሪዎች የሚቀርቡ አስደማሚና ምርጥ ምርጥ ፕሮግራሞች ተሰናድተዋል። 🌸 ለሴቶች በቂ ቦታ አለ! 📌 አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል‼️ 🕌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ወሎ ቅንርጫፍ፣ ደሴ ☘️ https://t.me/merkezunadessie
ገንዘቡን ሊያጠፋበት ቃል ገብቷል። ማን? አላህ የማንን? ላለመክፈል አቅዶ የተበደረን ሰው!!
ሰዎች በንግድ ስራ ላይ እየተጣደፉ ባሉባቸው ገበያዎችና የንግድ ማእከላት ቁርአንን መክፈት አይቻልም። ሙንተሓ አል ኢራዳት
ልጄ ሸይኽ ናሲሩዲን አህመድ ሲራጅ ነው። حفظه الله وبارك عليه
ሐነፊዮች ዘንድ የዊትር ዱዓእ ከሩኩዕ በፊት መሆኑ ነው ትክክለኛው አፈጻጸም። ለዚህም ዐብዱላህ ቢን መስዑድ እና አበስ ቢን ማሊክ رضي الله عنهما ያስተላለፏቸውን ትክክለኛ ሐዱሶችን ለመረጃነት ያቀርባሉ። عن عَلقمةَ: (أنَّ ابنَ مسعودٍ وأصحابَ النبيِّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم كانوا يَقنُتونَ في الوترِ قبلَ الركوع) رواه ابن ابي شيبة ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي
ሐነፊያ የሐገራችን አንዱ ወሳኝ መዝሀብ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ መሻይኾች ወይ ሻፍዒያ ወይም ሐነፊያ ናቸው። ሸይኼ ሸይኽ ዘያድ ሙሀመድም የሐነፊያን መዝሀብ በመማር ነው እድሜያቸውን ያሳለፉት። የምኖርባት ሀገር (ደቡብ አፍሪካም) የሐነፊዮች ሀገር ነች። በደቡባችን የሶማሊ ማህበረሰብ በርካታ ቁጥር ስላለው የሻፍዒዮችን መዝሀብም ያስተምራሉ። በሁሉም መዝሀብ ላይ ያሉ ምሁራኖች እንደሚመክሩት: ሰዎች መማር ያለባቸውም የሚኖሩበትን ሐገር መዝሀብ ነው። ኢትዮጵያውያንም ይሁን ደቡብ አፍሪካውያን የሐነፊያን ወይም የሻፍዒያን መዝሀብ መማራቸው ስርአት ያለው የትምህርት ካሪኩለም ተደርጎ ይወሰድላቸዋል። ከዚያ ውጭ የማሊኪያን ወይም የሀንበሊያን መዝሀብ ቢማሩ ወረቀት ላይ ብቻ የሚቀርን ትምህርት ነው የቀሰሙት።
ነጃሳን መምጠት የማይችሉ ለስላሳ ነገራቶች (مصقل) ነጃሳ ቢነካቸው ማጠብ አያስፈልጋቸውም። ማበስ በቂያቸው ነው። የዚህ ምሳሌው ማእድናት፣ የመስተዋት ምርቶች፣ ዘመናዊ የሽንትቤት መቀመጫዎች፣ የሴራሚክ ምርቶች ናቸው። እነዚህ ምርቶች ነጃሳው ሰርጎ የማይገባባቸው አይነት ምርቶች ስለሆኑ ዉሃ በነካው ስፖንጅ በሶፍት ወይም በፎጣ ጠረግ ቢደረጉ በቂ ነው። ለዚህም መረጃችን ሶሃባዎች ሰይፎቻቸውንም ይሁን ስለት መሳሪያዎቻቸውን ያብሱ እንደነበረ እንጅ ያጥቡ እንደነበረ አለመገለጹ ነው። ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي
ዉዱእ ላይ መጉመጥመጥና በአፍንጫ ዉሃን መሳብ ሱንና እንጅ ግዴታ አይደለም። ሱንና ነው እንድንል ያስገደደን ደግሞ አላህ በቁርአኑ ውስጥ ስለዉዱእ አፈጻጸም ሲገልጽ ሁለቱን አለመጥቀሱ አንዱ ምክንያት ነው። በተጨማሪም ትክክለኛነቱ በተረጋገጠ ሐዲስ አንድ ገጠሬ ሰው ነብዩ صلى الله عليه وسلم ጋር መጥቶ ስለዉዱእ አደራረግ ጠይቋቸው አላህ እንዳዘዘህ ዉዱእ አድርግ ብለው መልሰውለታል። ያ ገጠሬ ይህችን የነብዩን ምላሽ ፍጹም የሚረዳት ቁርአኑ ላይ በግልጽ በተቀመጠው መልኩ ነው። እንዳውም በአንዳንድ ዘገባዎች ፊትህን እጠብ፣ እጆችህን እጠብ፣ ጭንቅላትህን አብስ፣ እግሮችህን እጠብ ብለው በዝርዝር አስረድተውታልም ይባላል። ስለዚህ የዚያ ሶሃባቸው ዉዱእ አደራረግ ፍጹም የተሟላ ነው ማለት ነው። በተጨማሪም በተለያዩ ገላ አሳጣቢ ምክንያቶች (ሐይድ፣ጁኑብ እና ኒፋስ) ሙሉ አካሉን በዉሃ ያዳረሰ ሰው ምንም አይነት ውዱእ ሳይጨምር በትጥበቱ ብቻ ሶላትን መስገድ ይችላል። ለትጥበት ደግሞ መጉመጥመጡም ይሁን በአፍንጫ ዉሃ መሳቡ ግዴታ አለመሆኑ በጣም ግልጽ በሆኑ ሐዲሶች ተረጋግጧል። ስለመጉመጥመጥና በአፍንጫ ስለመሳብ የተጠቀሱ ሀዲሶች በበርካታ የሀዲስ ምሁራኖች ዘንድ ደካማ ናቸው። ትክክለኛ ናቸው ቢባልም እንኳ ከላይ የቀረቡትን አሳማኝ መረጃዎች በመርታት ግዴታነትን አያስይዙም። ሱንናነትን እንጅ። ይህ ምርጫ የሐነፊዮች ብቻ አቋም አይደለም። የአብዛኛዎቹ ሊቃውንቶችም ጭምር ነው። ፊቅሑን ሐነፊይ #فقه_حنفي
የዐሊም አለባበስ በአላህ ችሮታ የተንበሻበሸ፣ በራሱ የተብቃቃ አይነት አለባበስ መሆኑ ተገቢ ነው። ዐሊሞች ውዳቂ፣ ድሪቶና ቡቲቶ አይነት አለባበስን ሊርቁ ይገባቸዋል። ምክንያቱም አይረቤ ልብስ መልበሳቸው እርዱኝ፣ አግዙኝ፣ ተቸግሬያለሁና እጃችሁን ዘርጉልኝ እንደማለት ይወሰድና የሚያስተላልፉት የሸሪዓ ትምህርት ተሰሚነቱ ያነሰ ይሆናል። ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي
ሁሉም መዝሀቦች መሰረታቸው ቁርአን እና ሀዲስ ነው። ሁሉም መዝሀቦች ውስጥ ደካማ የሚባልም፣ ወጣ ያሉ የሚባሉም እይታዎች አሉ። ሁሉም መዝሀቦች ውስጥ ከሌሎቹ መዝሀቦች የተሻለ የሚባል አቋምና እይታ አለ። ሁሉም መዝሀቦች ውስጥ ብልሹ ዐቂዳ ያላቸው ምሁራኖች ብዙ ናቸው።
ሲዋክ የጽዳት ጉዳይ ነው። ይህም ማለት ሲዋክ ከዉዱእ ጋር የሚስማማ ነው። በዚህም መሰረት ውዱእ ላይ ሲዋክን መጠቀም የሚወደድ ተግባር ነው። ለሶላት ሲቆሙ ጥርስን መጎርጎርም ይሁን አፍን ማጽዳቱ ግን አደብ ስላልሆነ ሲዋክን መጠቀሙ ሱንና አይሆንም። ለሶላት ሲዘጋጁ የሲዋኩን ስብርባሪም ይሁን ከአፍ ውስጥ የሚገጸዱን ቆሻሻዎች መትፋቱም ይሁን መዋጡ አደበቢስነት ነውና። ይህ የማሊኪያዎችም እይታ ነው። ወቅታዊዉ እውነታም ይሄንኑ እይታ ይደግፈዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሱት "ለእያንዳንዱ ሶላት" በሚል የተዘገቡ ሀዲሶች በሙሉ ለእያንዳንዱ ዉዱእ በሚል ይገደባሉ/ይተረጎማሉ። ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي
አቡ ሐኒፋም ሆነ ሌሎች አኢማዎች ቂያስን በማስቀደም ወይም በሌሎች ምክንያቶች ትክክለኛነታቸው የተረጋገጡን ሐዲሶች ሆን ብለው ወደ ጎን ይጥላሉ ብሎ ያመነ ሰው በርግጥ እሱ ወይም በስሜት ወይም በስህተት ጥፋትን ተናግሯል። ኢብኑ ተይሚያህ ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي
ሚስት በግል ገንዘቧ አጠቃቀም ዙሪያ ማንንም የማስፈቀድ ግዴታ የለባትም። ይጠቅመኛል ላለችው ጉዳይ ማውጣት ፍጹም መብቷ ነው። ባል በሚስት የግል ገንዘብ ላይ ፈላጭ ቆራጭ፣ ፈቃጅና ከልካይ እንድሆን ፍጹም አይፈቀድለትም። ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي
ወተትን ሀላል ለማድረግ እንስሳዋ መታረድ አለባት እንደማይባለው ሁሉ ወተት አይበክትም። ይህም ማለት እንስሳዋ ከሞተች በኋላ ከጋቷ ውስጥ ያለው ወተት ሀላል ነው። አይነጀስም። ከሞተች ዶሮ ውስጥ የተገኘ እንቁላልም ቢሆን ተመሳሳይ ብይን አለው። ፊቅሁን ሐነፊይ #فقه_حنفي ============================= ይህ እይታ የዟሂሪያዎች ምርጫ ነው። ኢብኑ ተይሚያህም ይሄንኑ ይደግፉታል። ኢብኑ ዑሰይሚኒም መራቁ በላጭ መሆኑን ከመግለጽ ጋር ቢጠጣው ግን ሀራም አይሆንበትም ይላሉ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи