Ibnu Hashim(أمير هاشم)
Статистика"ألا لستُ للفردوسِ أهلا ولا أقوى على نار الجحيم فهبْ لي توبة واغفر ذنوبي فإنك غافر الذنب الأغامي"!!
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 232
- 1/48двое суток
- 1 411
- 1/72трое суток
- 1 522
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ምንድን ነው የሚባለው?! በእውነት ፍትህስ የሚጠየቀው ከማን ነው?! እንደወጡ ከመቅረት፣ ንፁሀን ዜጎችን በማንነታቸው እየለዩ በየመንገዱ እየተጎተቱ ፎቶ እያነሱ መረሸንና መጨፍጨፍ የዚህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ይሁን?! ወሏሂ ይሄንን ፎቶ አይቶ አለመረበሽ፣ አለመታመም፣ አለማልቀስ አይቻልም። ህመማቸው፣ ስቃያቸዉን፣ ፍርሃታቸዉ፣ ተስፋ መቁረጣቸው በሙሉ ይጋባል። ድንጋጤያቸውና ተስፋ ማጣታቸዉ በፊታቸው ላይ ይናገራል። የሚያዝኑላቸዉ እና የሚራሩላቸው ሰዎች ላይ እንዳልወደቁ ታውቋቸዋል፤ ከሰው ልጅ ጋር ሳይሆን ከአረመኔ ጋር እንደተፋጠጡ አይናቸው ድብን አድርጎ ይናገራል። ከቤታቸው ሲወጡ ይሄ መከራ እንደሚጠብቃቸው አላሰቡም። ወደተሻለ ህይወትና የስራ ዕድል እየመጡ እንደሆነ፣ ለቤተሰቦቻቸው ተስፋ ሊሆኑ እንደሆነ ተሰምቷቸው ይሆናል። ልክ እንደ እኛ እየሳቁ፣ ልክ እንደ እኛ እየተጨዋወቱ፣ ስለ ነገው የተሻለ ህይወት እያቀዱና እየተመኙ ይጓዙ እንደነበር አልጠራጠርም። ትልቅ ተስፋ ነበራቸው፣ ህይወታቸዉን የሚያሻሽሉበት በርካታ ምኞት ነበራቸው፣ ከጀርባቸው የሚረዱት ደካማ እናት፣ የሚጦሩት አባት፣ የሚያሳድጉትና የሚያስተምሩት ልጅ ይኖራቸዋል። ከተሳፈሩበት መኪና ውስጥ መታወቂያቸውን ብቻ አይተው በግፍ ሲያስወርዷቸው፣ ከሌሎች አብረዋቸው ከተሳፈሩ መንገደኞች ለይተው ሲነጥሏቸው፣ ደም በደም እስኪሆኑ ሲደበድቧቸው፣ ለቀጣይ የፕሮፓጋንዳ ማሸበሪያነት አስቀምጠው ፎቶ ሲያነሷቸው ምን ይሰማቸዉ ይሆን?! ምንስ እያሰቡ ይሆን? ይሄንን የልጇን ፎቶ የምታይ እናትስ በምን ቃል ትፅናናለች?! ምንስ አበርትቷት በዚህች በግፍ በተሞላች ምድር ላይ ትኖራለች?! በእውነት የዚህ ሁሉ ንጹህ ደም ግፍና መከራ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው?! t.me/IbnuHashm
አዲስ አበባ የማን ናት? Well እንግድክ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ስለተከከበች የኦሮሚያ ናት የሚሉ አሉ። የማይሉም አሉ። በከበበ እንሂድ ችግር የለም። በኦሮሚያ ስለተከበበች የኦሮሚያ ከሆነች ኦሮሚያም የከበቧት ክልሎች ሀብት ነች። ኢትዮጵያም የከበቧት ጎረቤት ሀገራት ሀብት ልትሆንም አይደል። አፍሪካስ የውቅያኖስና የሌሎች አሕጉሮች ሀብት ነች ማለት ነው። ታዲያ ምድርስ የማን ነች? የከበቧት ፕላኔቶች፣ ከዋክብት፣ ጨረቃና ፀሐይ ነች:: ስለዚህ ሲጠቃለል አዲስ አበባ የአሏህ ነች። © Hasen Injamo t.me/IbnuHashm
እንደነዚህ ዓይነት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጥምረቶች ከወረቀት በዘለለ መሬት የረገጠ አንዳችም ተግባራዊ ፋይዳ የላቸውም። መጀመሪያ ላይ ይህ ስምምነት በሳዑዲ ዓረቢያና በፓኪስታን መካከል ነበር የተደረገዉ። በስምምነቱ ላይ አንዱ ሀገር በውጭ አካል ከተጠቃ ሌላኛው ሀገር ልክ በራሱ ህልውና ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ አድርጎ ቆጥሮ ወዲያውኑ ጦርነቱን ይቀላቀላል የሚል የኔቶን አንቀፅ 5 የሚያስታውስ የጋራ መከላከል ጥምረት ነበር በሳዑዲና በፓኪስታን ተቀምሮ የነበረዉ። ነገር ግን መሬት ላይ እንደምናየዉ ሳዑዲ ዓረቢያ ቀደም ሲል በኢራን በቀጥታም ሆነ በአሁኑ ወቅት በየመኑ ሁቲዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈፅሙባትና የነዳጅ ማጣሪያዎቿ ሲመቱ ይህ የታወጀው ጥምረት ተንቀሳቅሶ መሬት ሲወርድና ወታደራዊ እርምጃ ሲወስድ አልተመለከትንም። አሁን ላይ የቱርክ ወደዚህ ጥምረት መጨመርም ቢሆን ከወረቀት በዘለለ መሬት ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ የሚያመጣ አይሆንም። ለምሳሌ በዚህ በተፈራረሙት ስምምነት ላይ የጥምረቱ አባል ሀገር በሌላ አካል ከተጠቃ ፈራሚዎቹ ሀገሮች ጥቃቱ በራሳቸው ላይ እንደተቃጣ ቆጥረው በይፋ ጦርነቱን ይቀላቀላሉ ይላል። ይኸው ስምምነት መሬት ላይ ይወርዳል ከተባለ አንድ ቀን ፓኪስታን ከህንድ ጋር ጦርነት ብትጀምር ሳዑዲ ዓረቢያ ጦሯን አዝምታ ህንድን ታጠቃታለች ማለት ነውን😁 ሳዑዲ ይህንን ካደረገች ደግሞ ከዋና አጋሯ ከአሜሪካ ጋር ተጋጨች ማለት ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሁቲዎች ሳዑዲ ላይ ጥቃት ቢፈፅሙ ሁቲ የመንግስትነት ወይም የሀገርነት ዕውቅና ስለሌለዉ የጥምረቱ አባል ሀገራት እዚህ ጥቃት ላይ እጃቸዉን አያስገቡም ማለት ነዉ። ስለዚህ ይህ አይነቱ ጥምረት የሁቲን ዓይነት ተፎካካሪዎችን ለማስፈራራት ካልሆነ በስተቀር ከወረቀት በላይ የማይሻገር አቅመ ቢስ ጥምረት ነው። t.me/IbnuHashm
አንተ ወጣት ሆይ! ያንን ሁሉ ተተኪ ትውልድ ለጦርነት ገብሮ፣ ትናንት ከወደቀበት ስህተት ሳይማር ዛሬም የዕልቂት ከበሮ መደስኮር ድንቁርና ነው። የሞት ወጥመድን እንደ አዲስ ማደስ ደግሞ የድንቁርና ድንቁርና ነዉ። የአበባ ያህል የሚፈኩ ወጣቶችን ከመቅሰፍ፣ እናቶችን በሐዘን ከማኮማተር፣ አዛዉንቶችን ያለ ጧሪ በባዶ ሜዳ ከማስቀረት በላይ ዉስጥን የሚያደማ ከቶ ምን አለ?! እንዲህ ላለው አሰቃቂ ሀቅ ጆሮ ሰጥቶ የማይደነግጥ ህሊና ከማንኛውም ጠላት በላይ አደገኛ ነው። አስተዋይ ማህበረሰብ በሌሎች ውድቀት ተምሮ መንገዱን ያቀናል፤ በገዛ አካሉና በትውልዱ ላይ ከደረሰው መሪር ስቃይ መማር ያቀተው ህሊና ግን በራሱ ላይ የቀጣይ ጥፋት ፈራጅ ነው። አንተ ወጣት ሆይ አርቀህ ማሰብና የራስን መንገድ መምረጥ አለብህ። በስምህ እየማለ የስሜት መጋረጃ የሚጋርድልህ ሁሉ በእውነት ለአንተ አስቦ እንዳይመስልህ፤ ጀግና እያለ የሚያቆላምጥህ ጥንካሬህን አክብሮ ሳይሆን በስሜት አደንዝዞ ለገዛ ዓላማው ሲል አሳልፎ ሊገብርህ ስለፈለገ ነው። የገዛ ልጆቻቸዉን ከሀገር አስወጥተዉ ከጦርነቱ ሲያርቁ አንተን ግን የመከራው እሳት መጀመሪያ ላይ ያስቀምጡሃል። ነገ አንተ በሞት ከተለየህ በኋላ የእናትህን ዕንባ የሚጠርግ፣ የልጆችህን ረሃብ የሚጋራ አልያም የቤተሰብህን ደጅ የሚያጠና አንዳችም ሰው አታገኝም። ምን አልባት ግፋ ቢል ከሞትክ በኋላ የመታሰቢያ ሀውልት ብለዉ ድንጋይ ይተክሉልህ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ለአንተም ሆነ ለወላጆችህ ምንም ጥቅም የለዉም። አትጠራጠር የአንተን መስዋዕትነት ለህዝብ ስሜት ማደንዘዣና ለቀጣዩ እልቂት ማቀጣጠያ ማገዶ ያደርጉታል። ከዚህ ባለፈ ምንም ጥቅም የለዉም። ለእውነተኛ ሕይወትህ የሚበጅ አንዳችም ፋይዳም የለው። ስለዚህ አንተ ወጣት ሆይ ለገዛ ህልውና ስትል አስተዋይ ልትሆን ይገባል። t.me/IbnuHashm
ይህ የምታዩት ምስል ጋዛውያን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ የተገደሉ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን በጋራ አሰባስበው የጀናዛ ሶላት ሰግደው የሸኙበት እና በጅምላ የቀበሩበት ልብ ሰባሪ ክስተት ነው። ከዚህም በላይ በቃላት ሊገለፁ የማይችሉ ሰቅጣጭ እውነታዎች በየቀኑ ይከሰታሉ። ትናንት'ኳ አንድ በፍርስራሽ ህንፃ ውስጥ የተቀበረን ህፃን ሲያወጡት አስክሬኑ ከነበረበት አካል በስብሶ የወላለቁ አጥንቶቹ ብቻ ነበሩ የቀሩት። ህፃኑ ወንድ ይሁን ሴት^ኳን ለይቶ ማወቅ በማይቻልበት ደረጃ ነበር አካሉን ሙሉ በሙሉ ያወደሙት። ዛሬ በጋዛ ምድር ላይ እያንዳንዷ ድንጋይ የንፁሐን አስክሬን ደብቃለች፤ እያንዳንዷም አፈር የንፁሐንን ጀሰድ አልብሳ ይዛለች። በጋዛ ምድር የሰው ልጅ ክብር እጅግ ረክሷል። ጋዛ ላይ በአሜሪካ ስፖንሰር አድራጊነትና በፅዮናውያኑ መንግሥት ቀጥተኛ ፈፃሚነት ንፁሐን ይህንን አሰቃቂ የግፍ ፅዋ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ እየተጎነጯት ይገኛሉ። t.me/IbnuHashm
ግማሽ አካሉን አጥቶ ደም እየፈሰሰው የሚፋለመውን ወደር የለሽ ጀግናን ላስተዋዉቃችሁ! የቅርብ ጓደኞቹ በጀግንነቱ ከታላቁ ሶሃባ ከጃዕፈር 🤎 ጋር በማመሳሰል ጦያር የሚል ቅፅል ስም ሰጥተውታል። ጀግንነቱ ሁልጊዜም በትውልድ ዘንድ የሚወሳ፣ የሸሂድነት ጉጉቱ እስከ ዛሬ ድረስ የሚዘከር የሻሚል ባየሲቭ ቅርብ ወንድምና ጓደኛ ነው። ስሙም ባይሳንጉር ቤኖኤቭስኪ ይሰኛል። ባይሳንጉር ገና በወጣትነቱ 218 ሙጃሂዶችን ብቻ ይዞ ከ13,000 በላይ የሚሆኑ የሩሲያ ተዋጊዎችን ለማንበርከክ በጌርጌቢል ተራራ ላይ ጦሩን በግርማ ሞገስ አንቀሳቀሰ። ሩሲያውያን በሺዎች የሚቆጠሩ የቼቸንያ ሙጃሂዶችን እየገጠሙ እስኪመስላቸው ድረስ ጦርነቱ በተራሮቹ መካከል ተቀጣጠለ። በዚያ ፍልሚያ ከ3,000 በላይ የሩሲያ ወታደሮች ተገደሉ። በርካታ የጦር ተሽከርካሪዎቻቸውም ወደሙ። ባይሳንጉር ግን ግማሽ አካሉን አጥቶ'ኳ ከጂሃድ አልተለየም። በውጊያው ወቅት ግራ ክንዱ ቢቆስልም መዋጋቱን አላቆመም። ልብሱን ቀዶ እጁን በጨርቅ በማሰር ውጊያውን ቀጠለ። በሂደት ግራ እግሩ፣ ግራ እጁ እና የግራ ዓይኑ ሙሉ በሙሉ ጠፉ። ግና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሶት ራሱን ስቶ እስኪወድቅ ድረስ በፅናት ተፋለመ፤ እጣፈንታው ሆኖም በሩሲያውያን እጅ ምርኮኛ ሆነ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን በእስረኞች ልውውጥ ወቅት ከግዞት ወጥቶ ወደ ሙስሊሞች ካምፕ ዳግም ተቀላቀለ። በሻዕባን ሶስተኛው ቀን 1277 ሂጅሪያ(እ.አ.አ. 1861) ሙስሊሞች ለሳልቶ ዘመቻ እየተዘጋጁ ነበር። አንዳንድ ተዋጊዎች ከጠላት ቁጥር ማደግ የተነሳ ወደ ኋላ መሸሽና ማፈግፈግን ባሰቡበት ሰዓት ግማሽ ሰውነቱን ያጣው ባይሳንጉር ከጦሩ መሃል ተነስቶ እንዲህ ሲል በወኔ ተናገረ። ''ገንዘቤን፣ ንብረቴን፣ አካሌን በማጣቴ አላዝንም... በሩሲያውያን የመስቀል ጦረኞች የባርነት ቀንበር ስር ለመኖር ያሰቡ ዕድለ ቢስ ሰዎች ግን ያሳዝኑኛል'' በማለት ተናገረ። በአንድ እጅ፣ በአንድ እግር፣ በአንድ ዓይን ብቻ ይህንን ጂሃድ ለማድረግ ወደ ጦር ሜዳ አመራ፤ በፅናት ለመፋለም ይረዳው ዘንድም ራሱን ከፈረሱ ጋር አስሮ ወደ ጦር ሜዳው መሃል እንደ መብረቅ ገሰገሰ። ጦርነቱ ተጀመረ፤ ውጊያው በከፍተኛ ሁኔታ ተጧጧፈ። የጥይትና የሰይፍ ድምፅ አድማሱን ሰንጥቆ በካውካሰስ ተራራዎች መካከል ተስተጋባ። ከ40 ሺህ በላይ የሩሲያ ወታደሮች ኢማም ሻሚልንና 400 ሙጃሂዶችን በያዘው ስብስብ ላይ ከበባ አደረጉ። ባይሳንጉር ከነዚያ ሙጃሂዶች መካከል አንዱ ነበር። በአሏህ መንገድ ለመሰዋትና ለዲኑ በጀግንነት ለመፋለም በልቡ ቆርጧል። የግራ አካሉን ከፈረሱ ጋር አስሮ የጥይቱን ቃታ እየሳበ በጀግንነት ይዋጋ ጀመር። ኢማም ሻሚልና ጥቂት ሙጃሂዶች ከከበባው ያመልጡ ዘንድ ራሱን ፊዳ ለማድረግ ለአሏህ ቃል ገባ። ያሰበውና የተመኘውም ተሳካለት፤ እነ ኢማም ሻሚል ከወጥመዱ አመለጡ። ከእልህ አስጨራሽና ረጅም ፍልሚያ በኋላ ባይሳንጉር ተማረከና በሩሲያ የመስቀል ጦረኞች እጅ ላይ ዳግም ወደቀ። የሞት ውሳኔ ተፈረደበት፤ ግማሽ አካሉ አገልግሎት ስለማይሰጥ ራሱን ከፈረስ ጋር አስሮ ይፋለም ነበርና በፈረሱ ላይ ታስሮ እንዲገደል ተወሰነ። በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ከፈረሱ ልጓም ጋር ታሰረ። በዚህን ጊዜ የሩሲያ አዛዦች በሙስሊሞች መካከል ጥላቻን ለመዝራትና የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማሰብ አንድ ዳግስታኒ ሙስሊም ቼቸንያዊውን ባይሳንጉርን እንዲገድለውና ፈረሱን እንዲመታ አዘዙ። ባይሳንጉር ይህንን ተንኮላቸውንና ሴራቸውን ወዲያውኑ ተረዳ፤ በወንድሞቹ መካከል ጥላቻ እንዳይፈጠር ሲል ያንን ዳግስታኒ ወንድሙን ከመታዘዝ ለማዳን ሲል የነበረችውን አንዲት እግሩን አምበልብሎ ፈረሱን በሀይል ረገጠው። ፈረሱም ደንግጦ እየፈረጠጠ በመሄድ ባይሳንጉርን ይዞ ከገደል አፋፍ ላይ ፈጠፈጠዉ። ወዲያዉ ነፍሱ ከጀሰዱ ተለያየች። ይህ ታላቅ ጀግና በሰባ ዓመት ዕድሜው የአሏህን ዲን ከፍ ለማድረግና የሙስሊሞችን አንድነት ላለማፍረስ ሲል ህይወቱን መሰዋዕትነት አደረገ። አሏህ ከታላላቅ ሸሂዶች ይመድበው! t.me/IbnuHashm
የሙሽሪትና የሙሽራው አጎቶች እንዲሁም የቁረይሽ መሪዎች ተሰባስበው ወጉን ሊጀምሩ እርስ በርስ በደስታ እየተያዩ ነው። በዚያ ምሽት የሙሽራው አጎት የሆነው አቡ ጧሊብ ከመሃላቸው ብድግ ብሎ ቆመ፤ ስፍራው ላይ የታደሙት የቁረይሽ ታላላቆች አቡ ጧሊብ ለመናገር እንደቆመ በተረዱ ጊዜ በቦታው ላይ ፅሞናን አሰፈሩ። አቡ ጧሊብም የቃላት ውበት የተሞላበትን ንግግር እንዲህ ሲል ጀመረ የኢብራሂም ዝርያዎች እና የኢስማዒል ፍሬዎች ያደረገን ጌታ፣ የክብርነት ቤቱ ጠባቂያዎች እና የጎብኚዎቹም ተቀባይ ስላደረገን ጌታችንን እናመሰግናለን። በመቀጠልም ይህ የወንድሜ ልጅ ሙሐመድ ምንም እንኳን በቁሳቁስና በሀብት ደረጃ ደሃ ቢሆንም ከመካ ቁረይሽ ወጣቶች በሙሉ ጋር ብታነፃፅሩት አቻና ብጤ የሌለው ታላቅ ሰው ነው። በልግስና፣ በትህትና፣ በሞራል፣ በታማኝነትና በክብር ማንም ቢሆን ከእርሱ ጋር አይስተካከለውም። ባለፀጋነት እንደሆን የቀን ጥላ ነው፤ የቀን ጥላ ደግሞ ማታ ጠፊ ነዉ። ልጃችን ልጃችሁን የከጀለ ሲሆን ልጃችሁም ልጃችንን ከጅላለች፤ ስለዚህ ያሻችሁን የመህር ተመን ወስኑ ከፋዩ እኔ ነኝ! ብሎ የሽምግልና ሂደቱን አስጀመረ። በመቀጠል የሙሽሪት አጎት እሷን ወክሎ ሊድራት ከተሰየመበት የክብር መንበር ተቀምጦ ንግግሩን እንዲህ ሲል ቀጠለ ''በአወሳሃቸው ታላላቅ ፀጋዎች በሙሉ ለጌታችን ምስጋና ይገባዉ። እኛን የመላው ዐረብ በላጮች እና መሪዎች ስላደረገን ጌታችንን እያመሰገንን እናንተም በኑ ሀሺሞች የዐረብ በሙሉ ቁንጮና መሪዎቻችን መሆናችሁን በደስታ እንመሰክራለን። እኛም ከእናንተ ጋር በሚያስተሳስረን የዝምድና ገመድ ይበልጥ ለመተሳሰርና ለመዛመድ ከጅለናል'' ብሎ ሽምግልናውን ተቀበለ። ንግግሩን በመቀጠል በስፍራው ወደታደሙት የቁረይሽ ነገዶች በሙሉ ፊቱን አዙሮ እናንተ የቁረይሽ ነገዶች ሆይ! እኔ ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድን ለሙሐመድ ኢብን ዐብዱሏህ የዳርኩ ስሆን እናንተም በዚሁ ጋብቻ ላይ ምስክር ሁኑ ብሎ ለዓለማቱ እዝነት ለረሱል 🤍 አስረከበ። ይሄኛው የረሱል 🤍 ሰርግ ቢያመልጠንም ነገ በአኼራ በጀነት እልፍኞች ውስጥ የሚደገሰውን ሰርጋቸውን በክብር እንድናጅባቸው አሏህ ይወፍቀን። ላጤዎችም እያገባችሁ! t.me/IbnuHashm
አንድ ጀግና ላስተዋዉቃችሁ! በየጦር ሜዳው የጣዖት አምላኪዎችን አንገት ቀንጥሶ ከአፈር ጋር በመቀላቀል ረገድ አቻ ያልተገኘለት ጀግና ተዋጊ ነው። የአሏህንና የነቢዩን 🤍 ጠላቶች በማሸበር ወደር ያልተገኘለትም ጀግና ነዉ። ወደ ጦር ሜዳ ሲገባ ጭንቅላቱ ላይ የሚጠመጥማትን ቀይ አማይማ የተመለከተ ከሀዲ በሙሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር። ግና አንድ መሰረታዊ የሆነ ትልቅ ችግር ነበረበት፤ ሁልጊዜም የአልኮል መጠጥ ይጠጣል፣ ጭንብስ ብሎም ይሰክራል። የአሏህን ሕግ በተደጋጋሚ እየጣሰ ስለሚያስቸግር በአደባባይ ብዙ ጊዜ ተገርፏል። ከዚህ አስከፊ ድርጊቱና ሱሱ ባለመላቀቁ ምክንያት በመጨረሻ በእግረ ሙቅ ተጠፍሮ በግዞት ወደ እስር ቤት ተወርውሮ ነበር። ዕለቱ የቃዲሲያ ዘመቻ እየተካሄደ የነበረበት ወቅት ነበር። አቡ ሚህጀን የታሰረው ጦርነቱ ከሚካሄድበት ሜዳ እጅግ ሳይርቅ በቅርብ ርቀት ላይ ነበር። ከታሰረበት ሆኖ የፈረሶችን ማሽካካት እና የሰይፎች ግጭት ሲሰማ መታሰሩንና ከትግሉ መራቁን አምርሮ ጠላው። ከተጋጋለው ጦር መሀል ገብቶ የአሏህን ጠላቶች አንገት በሰይፍ መሸልቀቅን እና ለአሏህ ዲን መዋጋትን በእጅጉ ናፈቀ። ከአይኖቹ እምባን እያረገፈ ውስጡ ክፉኛ ተረበሸ፤ የጂሃድ ፍቅር እንደ ነበልባል እያንገበገበ አላስችል ቢለው የታሰረበትን ክፍል በር በሀይል ደብድቦ ለጦር አዛዡ ለሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ 🤎 ባለቤት መልዕክት ላከ። እንዲህም አላት በአሏህ ይሁንብሽ! ካቴናዬን ፈተሽ የጦር መሳሪያና የሰዕድን ፈረስ አዘጋጅተሽ የናፈቅኩትን ጂሃድ እንድካፈል አድርጊኝ። ወደ ካፊሮች መሃል ገብቼ እፋለም ዘንድ እርጂኝ፤ በሕይወት ከተረፍኩ ራሴ መጥቼ የእስር ቤቱን በር በላዬ ላይ እከረችማለሁ፤ እግሬንም መልሼ እታሰራለሁ ሲል ተማፀናት። የጦር መሪው ሚስት የአቡ ሚህጂን እውነተኛ የጂሃድ ቁርጠኝነት ተመልከታ ፈረስና ሰይፍ ሰጥታ ለቀቀችው። አቡ ሚህጀንም ማንነቱን ለመሸፈን ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ልክ እንደ መብረቅ ወደ ጦር ሜዳው መሃል ሰፈረ። በዚያን ወቅት ካፊሮች የበላይነትን ለመቆጣጠር ቀርበዋል። የሙስሊሙም ጦር ተዳክሞ ነበር። በዚህ አስጨናቂ ቅጽበት አቡ ሚህጀን ከመሃላቸው ተከሰተ፤ ጠላትን እየበተነ አንዱን በአንዱ ላይ አነባበረው። ድል ወዲያውኑ ወደ ሙስሊሞች ማዘንበል ጀመረ። የካፊርን ደም የተጠማው አቡ ሚህጀን የአሏህንና የሙስሊሙን ጠላቶች እንደ ቅጠል አረገፋቸው፤ ከፊቱ የቀረበውን የጠላት ጦር አንገት እየቀነጠሰ ወደ መሃል ገሰገሰ። የሙስሊሙ ጦር አዛዥ ሰዕድ 🤎 የዚህን ተዋጊ ጀግንነት እየተመለከተ እንዲህ በፅናት የአሏህን ጠላቶች አመድ የሚያደርገው ይህ ፈረስና ተዋጊ ማን ነው? ሲል ጠየቀ። የሚያውቀው ሰው ግን ጠፋ፤ ሰዕድም በመገረም ፈረሱ የኔን ፈረስ በልቃዕን ይመስላል። የአጠቃቁ ስልቱ ደግሞ የአቡ ሚህጀንን ይመስላል። ነገር ግን አቡ ሚህጀን የታሰረ በመሆኑ እርሱ ሊሆን አይችልም አለ። ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል አድራጊነት መጠናቀቁን የተመለከተው አቡ ሚህጀን በገባው ቃል መሰረት ሳይዘገይ ተመልሶ ወደ እስር ቤቱ ገባና በጦርነት የደከሙ እግሮቹንና እጆቹን በካቴና ጠፍሮ አሰራቸው። ሰዕድ 🤎 ከጦር ሜዳ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱ ዛሬ ውጊያው እንዴት ነበር? በማለት ጠየቀችው። ሰዕድም መጀመሪያ ላይ የሽንፈት ማቅ ልንከናነብ ቀርበን ነበር፤ አሏህ ግን ሳናስበው አንድ ጀግና የጦር ተዋጊ ላከልንና ያ የመነመነ የድል ተስፋችን ወደ እኛ ተቀልብሶ ለማሸነፍ ቻልን። አቡ ሚህጀንን አስሬው ባልሄድ ኖሮ ያ ጀግና ተፋላሚ እርሱ ነው ብዬ እጠረጥር ነበር በማለት ተናገረ። ሚስቱም በአሏህ ይሁንብኝ ያ ተዋጊ ራሱ አቡ ሚህጀን ነው ብላ የተከሰተውን በሙሉ አስረዳችው። በሁኔታው በእጅጉ የተደሰተው ሰዕድ ወዲያውኑ አቡ ሚህጀንን አስጠርቶ ካቴናውን እየፈታ በአሏህ ይሁንብኝ ከአሁኗ ሰዓት ጀምሬ አላስርህም፣ አልገርፍህም፤ በነፃ ለቅቄሃለሁ አለው። አቡ ሚህጀንም ቀጠል በማድረግ በአሏህ ይሁንብኝ እኔም ከዛሬ ጀምሬ አልኮል አልቀምስም፣ አልሰክርም በማለት መለሰ። ከዛች ቀን ጀምሮ አቡ ሚህጀን መጠጥን ፈፅሞ በመተው አሏህን ከሚፈሩ ታላላቅ ሙጃሂዶች አንዱ ሆኖ ዘለቀ። t.me/IbnuHashm
የአቡ ጃዕፈር አል ወራክ የልጅ ልጅና የኢስላማዊቷ አንደሉስ የፅናት ተምሳሌት የሆነች ትጉህ ሙጃሂድ ነበረች። ከአባቷ የወረሰችው ጥልቅ ንባብና የዕውቀት ፍቅር ከነቤተመፅሕፍቱ የተሰጣት ትልቅ አደራ ነበር። ገና በልጅነቷ የካቶሊክ መስቀላውያን ወታደሮች የእስልምናን መብራት ለማጥፋት ቁርዓንን፣ ኢስላማዊ የታሪክ መጻሕፍትን እና በሙስሊም ሳይንቲስቶች የተቀመሩ የምርምር ውጤቶችን በግራናዳ የረምላ አደባባይ ላይ በግፍ ሲያቃጥሉ በዓይኗ ተመልክታ በቁጭት አድጋለች። ሰሊማ በአንደሉስ ከነበሩት ጥቂት የበሰሉ ሴት ምሁራን መካከል አንዷ ናት። በተለይም በሕክምናው ዘርፍ የላቀ ብቃት የነበራት ሊቅ ነበረች። በገዛ ቤቷ ውስጥ ለሕሙማን የሚሆኑ መድሃኒቶችን የምታመርትበት የራሷ የሆነ የላቦራቶሪ ክፍል ሳይቀር ነበራት። የክርስትና እምነት በአንደሉስ ምድር ላይ በሀይል እንዲሰፍን ተደርጎ ሙስሊሞችን በግድ የማክፈር የኢንክዊዚሽን ዘመቻ ሲጀመር ባለቤቷ ሰዐድ አል ማሊቂ አቋሙን ያልሸጠ ሙጃሂድ በመሆኑ ከመስቀላውያኑ አደን በመሸሽ ቀን ቀን በምስጢር ይሸሸግ ነበር። ሌሊት ሌሊት በድብቅ ወደ ቤቱ በመምጣት ከባለቤቱ ከሰሊማ ጋር ይገናኛል። ጥንቆላና ድግምት ትሰራለች፤ ሌሊት ሌሊት በአየር ላይ እየበረረች ከሰይጣን ጋር ዝሙት ትፈፅማለች፤ ከእርሱም አርግዛለች በሚል ክስ በቁጥጥር ሥር አዋሏት። በመቀጠልም አሰቃቂ ውሳኔዎችን በሚያስተላልፈውና የጭካኔ ማዕከል በነበረው መሐኪመ ተፍቲሽ በአንደሉስ ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ፊት ለፊት አቆሟት። በችሎቱም ላይ በነቢዩ 🤍 የእስራእ ወል ሚዕራጅ ጉዞ አምናለች፤ ከሰይጣንም አርግዛለች በሚል ከንቱ ሰበብ የስቅላትና የሞት ፍርድ ተወሰነባት። ከታሰረችበት እስር ቤት ውስጥ በህይወትና በሞት መካከል ሆና ታጣጥራለች። እርግጫውና ዱላው ከመደፈሯ ጋር ተደማምሮ የመጨረሻ እስትንፋሷ ላይ ተቃርባለች። ጌታዬ አሏህ ነው በማለቷ ብቻ በመስቀላዊያን ወታደሮች ተደፍራለች። በሆዷ ውስጥ ከሐላል ባለቤቷ ያገኘችውን ፅንስ ተሸክማ ሳለች በጀርባዋ አስተኝተው ሆዷን በስለታማ ከስክስና በደንዳና ዱላ ይመቷት ያዙ። ከዓይኗ ኩልል ብሎ የሚወርደው የሕመም ዕንባ ከአፏ ከሚፈሰው የደም ጎርፍ ጋር ተቀላቅሎ ከንፈሯን አርሶታል። ከማህፀኗ ውስጥ ፅንሱ እየተቆራረጠ ሲወጣ አቅሟን ሙሉ በሙሉ አሳጣት። ወታደሮች ግን በዚህ አላበቁም፤ በትከሻቸው ተሸክመው የሽንት ቤት መቀመጫ ቀዳዳ ላይ በአፏ አስተኟት። በእጃቸው በያዙት ስለታማ ቢላ እጅግ በሚዘግን ሁኔታ ጡቷን ቆረጧት። በዚህ ሁሉ የስቃይ ጣር ውስጥ ሆና እስትንፋሷ ሊቋረጥ አፋፍ ላይ በደረሰበት ጊዜ አንገቷን ወደ ላይ አቅንታ በደካማ ድምፅ ''ጌታዬ ሆይ! በዚህች ምድር ላይ በሕይወት የመቆየቴ ብቸኛ ምክንያት አንተን ማምለክና መገዛት ነበር፤ ግና የሚገባህን ያህል ሳልገዛህ ቀረሁ በማለት ተናገረች። ስለ አሏህ ብቸኛ ተመላኪነትና ረሱልም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መስክራ ሩኋ ከጀሰዷ ተላቀቀ። የአንደሉሷን ሸሂድ ሰሊማ ቢንት ጃዕፈርን አሏህ ጀነተል ፍርደውስ ወራሽ ያድርጋት! t.me/IbnuHashm
ሳዑዲ እንዲህ ነበረች! ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት በሂጅራ አቆጣጠር ረመዷን 28/1415 ዓ.ሂ (ከሰላሳ ዓመታት ገደማ በፊት) በሳዑዲ ዓረቢያ ታትሞ የወጣ ጋዜጣ ነው። በዚያ ወርቃማ ዘመን በመልካም ማዘዝ እና ከመጥፎ መከልከል (هيئة أمر بالمعروف والنهي عن المنكر) በመባል የሚታወቀው አንጋፋ ተቋም በሃገሪቱ ግዛት ዉስጥ በሙሉ ስልጣን ይንቀሳቀስ ነበር። የዚህ ጋዜጣ የፊት ገፅ ላይ እንደምናነበዉ ተቋሙ በዋና ከተማዋ ሪያድ ውስጥ በፈጅር ሶላት ላይ ከመስጂድ የሚቀሩ ሰዎችን በቅርብ ተከታትሎ የመለየት፣ ያጋጠማቸውን ችግር በየአራት ወሩ በሚያደርገው ህዝባዊ ውይይትና ምክር ላይ ለመቅረፍ እንደ ወጠነ ያሳያል። የዚያ ዘመን አቀራረብ ህዝቡን ወደ አሏህ ቤት በመሳብ እና ዲኑን በመጠበቅ ላይ ያተኮረ ነበር። ይሁን እንጂ በሸሪዓው ጥበቃ ላይ ቆሞ የነበረው ይህ ባለሙሉ ስልጣን ተቋም ዛሬ ላይ ክንፉ ተቆርጦ እና ፈርሶ እንጦሮጦስ ወርዷል። ተቋሙ መፍረሱ ብቻ ሳይሆን ሙሐመድ ቢን ሰልማን ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በተለይም በሪያድና በጅዳ ከተሞች ውስጥ የሚፈፅማቸውን ስር ነቀል ፀረ ዲን እንቅስቃሴዎች በአደባባይ የሚቃወም ካለ ከመሬት በታች ባለ እስር ቤት ዉስጥ ያጉራቸዋል። ተቃውሞ ለማድረግ የተንደረደሩትን አልያም ከእኔ የለወጥ አካሄድ በተፃራሪ ይንቀሳቀሳሉ ብሎ ያሰባቸውን የሀገሪቱን ዑለሞችን፣ ጥበበኞችን፣ ፀሐፊዎችን፣ ገጣሚዎችን፣ ኢማሞችን፣ መሻይኾች ወ.ዘ.ተ በሙሉ ቢን ሰልማን ያለ ምንም ርህራሄ በእስር ቤት መቀመቅ ውስጥ ከቶዓቸዋል። አነስ ቢን ማሊክ 🤎 ባስተላለፉት ሀዲስ የአሏህ መልእክተኛ 🤍 ''ጌታችሁን እስክታገኙ ድረስ ከየትኛውም ሸረኛ ዘመን ቀጥሎ የሚመጣው ዘመን የባሰ እንጂ የተሻለ አይሆንም'' በማለት የተናገሩትን ትንቢታዊ እውነታ በጥልቀት ልብ ማለት ያስፈልጋል። ሳዑዲ የአሏህ ቤት የሆኑት መስጂዶች ባዶዓቸውን የሚቀሩባት እና በምትኩ የዘፈን አደባባዮች የሚጨናነቁባት አስከፊ ዘመን ላይ ደርሳለች። t.me/IbnuHashm
ክብር ከአረብ መሪዎች ተሽሎ ሰብዓዊነትን ላነገበው ፔድሮ ሳንቺዝና ለሚመራው ህዝብ እና ቡድን ይሁን🫡 t.me/IbnuHashm
ይህ እግር ኳስ ብቻ አይደለም፤ ሰብዓዊነትም ጭምር ነዉ! ስፔን በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ላይ እንደ ሌሎች ምዕራባውያን ሃገራት ለአሜሪካና ለፅዮናዊው አምባገነናዊ ፍላጎት ሳትገዛ የራሷን የሞራል እና የፍትህ መርህ አፅንታ በመያዟ ምክንያት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እና የኤኮኖሚ ጫና እንዲሁም የጎላ ተቃውሞ ሲደርስባት የቆየች ሃገር ናት። የስፔን መንግስት እና ህዝቧ በእስራኤል የጋዛ ወረራና የንፁሐን ጭፍጨፋ ላይ ያሳዩት የማያወላውል ተቃውሞ በፅዮናውያን አመራሮች እና በአጋሮቻቸው ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ከዚህም በላይ ስፔን ራሷን የቻለች ሉዓላዊ ሃገር መሆኗን በማስመስከር የአየር ግዛቷ በኢራን ላይ ለሚፈፀም ማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ጥቃት ማካሄጃነት እንዳይውል በማገዷ የዓለም ትኩረት ሆናለች። ይህ የስፔን መርሀዊ አቋም በርካታ የአረብና የሙስሊም ሃገራት'ኳ የገዛ ህልውናቸውን ፈርተው መፈፀም ያልቻሉት አቋም ነበር። በዚሁ ሰብዓዊ አቋሟ የተነሳ ስፔን የዶናልድ ትራምፕ የትችት፣ የዛቻ ከዚህም አልፎ የንቀት ዋነኛ ኢላማ ሆና ቆይታለች። በተለይም በቅርቡ በተካሄደው የኔቶ ጉባኤ ላይ ትራምፕ ከስፔን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አንፈልግም፤ ንግድንና የቱሪዝም ጉብኝትን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ ማቋረጥ አለብን፤ ይህንን የጠነከረ እርምጃ ስንወስድ ደግሞ ተንበርክከውና ተለማምጠው ይመጣሉ... ሲል በከፍተኛ ንቀት እና ትዕቢት ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጂ ታሪኩ እጅግ አስገራሚ መልክ ይዞ ብቅ ብሏል። ትራምፕ ስፔንን በጠላትነት ፈርጀው በንቀት ከተናገሩ 2 ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስፔን በአሜሪካ ምድር በተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ላይ ሁሉንም ተፎካካሪዎቿን አሸንፋ የዓለም ሻምፒዮን በመሆን ድልን ተቀዳጅታለች። ከሁሉም በላይ ግን የፍፃሜውን የድል ዋንጫ ከራሱ ከትራምፕ እጅ በኩራት መረከቧ ድግምቱ በደጋሚው ላይ ዞረ😁 የሚያስብል ትዕቢተኞችን በገዛ ምድራቸው ላይ ያናወጠ ትልቅ ትርጉም ያለው እና ታሪካዊ ክስተት ሆኖ አልፏል። t.me/IbnuHashm
በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ዳግም አገርሽቶ ወደ ከፋ ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያሳዩ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። ኢራን ምሽቱን ጆርዳን ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ በፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው እየተነገረ ነው። ጥቃቱን ተከትሎ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከላዊ እዝ ባወጣው መግለጫ መጀመሪያ ላይ 3 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውን በይፋ ያረጋገጠ ሲሆን የሌሎቹ ወታደሮች አድራሻ እስከ አሁን እንደጠፋና የት እንዳሉ እንደማይታወቅ አስታውቋል። በተጨማሪ በጥቃቱ ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ጆርዳን ከፍተኛ ወታደራዊና ሲቪል ሆስፒታሎች ተወስደው ከፍተኛ ክትትል ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። ኢራን ይህንን ጥቃት የፈፀመችዉ ቀደም ሲል ለተሰነዘሩባት ጥቃቶች የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መሆኑን የገለፀች ሲሆን ክስተቱ ወደለየለት ጦርነት እንደሚያመራ ተጠቁሟል። ይህንን ተከትሎ በዋሽንግተን በኩል የአሜሪካ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ሲቪል ዜጎቹ በሙሉ ቀጠናውን በአስቸኳይ ለመልቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አስቸኳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል። t.me/IbnuHashm
በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች የአንድን ሰው ፅሑፍ ስክሪንሹት ለማንሳት የሚያደርጉት ፍጥነት አንዳንዴ ሳይ ይገርመኛል። አንድ ሰዉ የፃፈዉ ሃሳብ ገና ራሱ መለስ ብሎ ሳያነበዉ እና ሳያርመው፤ እነሱ ልክ እንደ ፎቶ አንሺ ቀጭ ቀጭ አድርገው ፋይል ውስጥ ለማስቀመጠት የሚያደርጉት ፍጥነተ ዐጂብ ያስብላል። አንዳንዶቹ'ማ ተሳስተን የሆነ ነገር ለጥፈን ትንሽ ቆይተን ታርመናል ብለን ፅሑፉን ብናጠፋ እንኳን በፊት ስክሪንሹት ያደረጉትን እያመጡ ይኸው የፃፍከው እያሉ በድሮው አቋማችን ይገመግሙናል። ቆይ በእናንተ ቤት አንድ ሰዉ መታረም፣ ስህተቱን አምኖ ተውበት ማድረግ አይችልም ማለት ነዉ? የታረመውን እና ኢዲት የተደረገውን በሳል ሃሳብ ትታችሁ የቀደመዉን አልያም የተሰረዘውን ፅሑፍ እርስ በርሳችሁ እየተቀባበላችሁ ስም ለማጥፋት መሞከር ድንቁርና ነዉ። ይሄንን ዕውር አካሄድ ትታችሁ ወደ እውነተኛው የሃገራችን ፖለቲካዊ እውነታ ስንመጣ ደግሞ የሸሪዓ መንግስት ኢትዮጵያ ዉስጥ በምንም ሂሳብ ሊመሰረት አይችልም(ሐቁ ይህ ነዉ ቢመራችሁም ዋጡት)። ይህንን የማይሆን እና ከእውነታው የራቀ ከንቱ ምኞት መሆኑን ልትረዱት ይገባል። እንኳን ኢትዮጵያ ቀርታ የሕዝባቸው ቁጥር ከ90% በላይ ሙስሊም የሆኑት እና የሸሪዓ መንግስት መመስረት ቢፈልጉ'ኳ ያን ያክል እንቅፋት የማይገጥማቸዉ እንደ ግብፅ እና ቱርክ ያሉ ትልልቅ ሃገራት'ኳ ዛሬ ላይ በሸሪዓ ሕግ እንደማይተዳደሩ እያየን ነዉ። ታዲያ ኢትዮጵያ ግማሹ ሙስሊም ግማሹ ክርስቲያን በሆነባት እኩል ሃይማኖታዊ ስብጥር ባላት ሃገር ውስጥ በምን ዓይነት ፖለቲካዊ ሂሳብ እና ቀመር ነው የሸሪዓ መንግስት ሊመሰረት የሚችለው? ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ ጠፍተው ከሆነ ምናልባት ይህ ሃሳብ ሊሰራ እና ሊያስማማን ይችላል። ከዛ ውጪ ግን በጭራሽ አይሆንም። እኛ እንደ ሙስሊም የምንታገለው በዚች በጋራ ሃገራችን ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ መሰረታዊ መብቱ እና ክብሩ ተከብሮለት ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመተሳሰብ እና በመከባበር እንዲኖር እንጂ የሸሪዓ መንግስት ለመመስረት አይደለም። ብንፈልገው እንኳን ከነባራዊው የሃገራችን የፖለቲካ እና የህዝብ ስብጥር አንፃር ፈፅሞ ሊሳካ የማይችል ተጨባጭ የሌለው ሃሳብ ነው። ስለዚህ ከህልም ዓለም ወጥተን እውነታውን እንጋፈጠው። በሓሳብ የሚሞግተኝ ካለ እቀበላለሁ፤ የሚሳደብ በblock ይሸኛል! t.me/IbnuHashm
ክብር ለሚገባዉ ክብር፤ ቦታ ለሚሰጠው ሰው ቦታ መስጠት የሚጠበቅ እና ትክክለኛ ባህሪ ነው። የሚገባዉ ሰዉ ሁኖ ደግሞ እንዲህ ሲከበር ያምራል። አንዳንድ መገፋቶች ለኸይር ናቸዉ። t.me/IbnuHashm
ጋዛ ሙሉ በሙሉ በኑክሌር መሣሪያ ካልተደበደበች እያለ ሲፎክር የነበረው እንዲሁም ኢራን ካልወደመችና ካልጠፋች እያለ የጥፋት ነጋሪት ሲጎስም የነበረው ፅንፈኛው የአሜሪካ ሴናተር ሊንድሴይ ግራሃም በድንገት መሞቱ ተሰምቷል። አል-ሐምዱ-ሊላህ! አሏህ የስራዉን ይስጠዉ። t.me/IbnuHashm
ዘመናትን ተሻግረው የሰውን ልጅ በእንባ ካራጩ ታሪኾች መካከል የሰዕለባ ታሪክ አንዱ ነው። ሰዕለባ የአሏህን መልዕክተኛ 🤍 አብዝተው ከሚያገለግሉ የመዲና ታዳጊ ወጣቶች መካከል አንዱ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ነቢ ሰዕለባን ለሆነ ጉዳይ ወደ ውጪ ይልኩታል። እርሱም የታዘዘበትን መልዕክት ይዞ በመንገድ ላይ ሳለ ከአንሷሮች መኖሪያ ቤቶች መካከል በሩ ገርበብ ብሎ የተከፈተን አንድ ቤት በአጋጣሚ አስተዋለ። ልክ በዚያው ቅፅበት በቤቱ ውስጥ ያለውን መጋረጃ ሀይለኛ ንፋስ ገልጦት ገላዋን እየታጠበች ባለች አንዲት እንስት ላይ በአጋጣሚ ዓይኑ አረፈ። ሰዕለባ በዚህ ሁኔታ እጅግ ደነግጦ መላ አካላቱ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ። በፍጥነትም አካባቢውን ለቆ ወጣ። ነገር ግን ውስጡ ሰላም ሊያገኝ አልቻለም። በፅፅት እየተቃጠለ እንዴት እይታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም? ረሱልን ባየሁበት ዓይኔ ጭራሽ የሳቸውን መልዕክት ይዤ እየተጓዝኩ እንዴት ዓይኔ ሐራም ነገር ላይ ያርፋል? ምን አልባትም እኔ መናፍቅ ሆኜ ይሆን? እያለ ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ ጀመር። ሐራም ባየሁበት አይኔ በድጋሚ ረሱልን ማየት አይገባኝም አሏህ ይቅር እስኪለኝ አልያም መለከል መውት መጥቶ ሩሄን እስኪያወጣው በዚህ ኮረብታ ማሳለፍ ይኖርብኛል። በማለት ከመዲና ተራሮች ወደ አንዱ በመሸሽ ራሱን አገለለ። የአሏህ መልዕክተኛ 🤍 ለጉዳይ ልከውት ስለቆየባቸው ልጅ ማጠያየቅ ጀመሩ። ቀናቶች ተቆጠሩ ሳምንታትም አለፉ። ነገር ግን ስለ ሰዕለባ የተጠየቁ የመዲና ሰዎችን ሁሉ አናውቅም የሚል ምላሽ ብቻ ነበር የሚሰጡት። የሰዕለባ መጥፋት ያሳሰባቸው ነቢ ዑመር ኢብኑል ኸጣብን እና ሰልማን አል ፋርሲን ከተወሰኑ ሶሀቦች ጋር አብረው እንዲፈልጉት ላኳቸው። ዑመር እና ባልደረቦቻቸውም በእግር በፈረስ በየቦታው ሲፈልጉት ቆይተው በስተመጨረሻ በመካና በመዲና መካከል ባለ አንድ ገለልተኛ ኮረብታ ላይ ደረሱ። በዚያም እረኞችን ተመልክተው ስለ ሰዕለባ አንዳንድ የአካል እና የሁኔታ ምልክቶችን በመንገር አይተውት እንደሆነ ጠየቋቸው። እረኞቹም ከዚያ ኮረብታ ስር እኛ ወተት እያለብን በነፃ የምንሰጠው አንድ ወጣት አለ፤ እዚህ ከመጣ እነሆ 40 ቀናትን አስቆጥሯል። ሌሊትም ቀንም ሳያቋርጥ በልቅሶ ያነባል፤ የዚህን ልቅሶውን ምክንያት ግን ሊነግረን ፈፅሞ አልፈቀደም አሏቸው። ዑመር እና ባልደረቦቻቸው ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ በአቅራቢያው ተደብቀው የልጁን መውጣት ይጠባበቁ ጀመር። ፀሐይ ስታዘነብል ሰዕለባ ከተደበቀበት ተራራ ወጣ። እረኞቹም ምንም ሳይሉ ወተቱን አልበው ሰጡት። ነገር ግን ያ የተጠማ ወጣት ሁለት ጉንጭ እንደተጎነጨ አይኖቹ በእንባ ዘለላዎች ተሞሉ። ከውስጥ ቃጠሎው የተነሳ ወተቱን ጨርሶ መጠጣት አልቻለም። ኩባያውን መሬት ላይ ቁጭ አድርጎ ወደ ኋላው ሲዞር ዑመር እና አብረውት ያሉት ሶሃቦች ከተደበቁበት ወጥተው ያዙት። ሰዕለባም በድንጋጤ ምን ነካችሁ? ለመሆኑ የአሏህ መልዕክተኛ እኔ መናፍቅ መሆኔን የሚገልጽ ወሕይ ወረደላቸው? ለዚህ ነው ልትፈልጉኝ የመጣችሁት? ሲል ጠየቃቸው። ዑመርም በጭራሽ እንዲህ አይደለም! በማለት መለሱለት። ሶሃቦቹ በልጁ ላይ በደረሰው ነገር ተጨንቀው በለቅሶ እና በረሃብ ተጎሳቁሎ የነበረውን ሰዕለባን ይዘውት ወደ መዲና ተመለሱ። ረሱል ሰዕለባ ወዳለበት ቤት አቀኑ፤ አስፈቅደውም በሩን ከፍተው ገቡ። ሰዕለባ ግን ከነበረው ሃፍረት የተነሳ የነቢዩን ፊት ላለማየት ሲል ፊቱን ወደ መሬት ደፍቶ አቀረቀረ። በዚህ ጊዜ ነቢ ጭንቅላቱን ቀና አድርገው በገዛ ታፋቸው ላይ አስደገፉት። ሰዕለባ ግን ያ ነቢየሏህ ይህንን በወንጀል የተጨማለቀን ራስ ከሰውነትዎ ላይ ያንሱልኝ አላቸው። እሳቸውም ለመሆኑ ምን ሆንክ? ምንስ ያሰጋሃል? ሲሉ ጠየቁት። እርሱም የአሏህ ከባድ ቅጣት ያሰጋኛል ሲል መለሰ። ታዲያ ምንስ ትፈልጋለህ? አሉት፤ እርሱም የጌታዬን ሰፊ እዝነት እና ምህረት ብቻ ሲል መለሰላቸው። አዛኙ ነቢም የምትፈልገውን እዝነት እንድታገኝና ከምትፈራው ቅጣት እንድትጠበቅ እኔ ራሴ ዋስ እሆንሃለሁ ሲሉ አረጋገጡለት። በዚያው ቅፅበት ሰዕለባ ያ ነቢየሏህ የጉንዳን መንጋ በደም ስሬ ውስጥ እየተግተለተለ እንደሚሄድ ዓይነት ከባድ ስሜት ይሰማኛል አላቸው። እሳቸውም ይህማ የሞት መምጣት ምልክት ነው፤ እነሆ አሁን ጌታህን ልትገናኝ ነው በማለት የሸሃዳ ቃል አስታወሱት። እርሱም ሸሃዳውን ይዞ ወደማይቀረው ዓለም ተጓዘ። የአላህ መልዕክተኛ 🤍 በጀናዛው ላይ ሰግደውበት ወደ ቀብር ቦታ በሚወስዱት ጊዜ አካሄዳቸው ልክ በጠባብ መንገድ ላይ እንደሚጓዝ ሰው በጣቶቻቸው ጫፍ ብቻ እየተራመዱ ነበር። ይህንን ያስተዋለው ዑመር መንገዱ ምንም ዓይነት ጭንቅንቅ በሌለበት ሁኔታ ለምን እንዲህ እንደሚራመዱ ጠየቃቸው። እሳቸውም ወሏሂ ያ ዑመር የሰዎች ጭንቅንቅ ሳይሆን እጅግ በጣም ብዙ መላዒኮች የሰዕለባንን ጀናዛ ለመሸኘት መንገዱን አጨናንቀውታል። እኔም ከእነርሱ ጋር እየተጋፋሁ እንዳረግጣቸው በጥንቃቄ ተጠንቅቄ ነው እንዲህ በጣቶቼ ጫፍ የምራመደው በማለት መለሱለት። ለመሆኑ እኛስ? አንዴ ሳይሆን በቁጥር ልናስበው በማንችለው አያሌ ጊዜያት አሏህን አላመፅንም? እይታችንን፣ ልባችንን፣ ሕይወታችንን በሀራም ድንበር ጥሰቶች አላቆሸሽንም? ታዲያ እንደዚህ ወጣት አልቅሰን ወደ አሏህ መመለስ አይጠበቅብንምን? ጌታችን አሏህ በተከበረዉ ቃሉ እንዳለው ''ለነዚያ ላመኑ ሰዎች ልቦናቸው ለአሏህ ግሳፄ የሚፈራበት ጊዜ አልደረሰምን?[ሱረቱል አል ሐዲድ 65] t.me/IbnuHashm
በምድር ላይ እንደ እርሷ አይነት ሰው ታውቃላችሁ? እርሷ በአንድ ትንሽዬ መንደር ውስጥ ተራ መምህርት ሆና በቅንነት ትሰራ የነበረች ሴት ነበረች። ለተማሪዎቿ ከጀርባዋ ያለውን የክብር ገመና ፈፅሞ አታሳይም። አባቷ የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ አባል የነበሩ ሲሆን ባለቤቷ ደግሞ የኢራን ከፍተኛ መሪ ሰይድ ሞጅተባ ኻሚኔ ናቸዉ። በከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ የድህረ ምረቃ ዲግሪ አላት። በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተደላድላ የመስራት አቅሙ ነበራት። ነገር ግን እርሷ የመረጠችው መንገድ ሌላ ነበር። የገዛ ማንነቷን፣ የባለቤቷን እና የአባቷን የስልጣን ክብር በመደበቅ ካኖም ሆሴኒ(ወይዘሮ ሆሴኒ) በሚል የውሸት ስም በደቡብ ቴህራን ሰፈሮች ውስጥ ተደብቃ በመምህርት ማገልገልን መረጠች። አንድ ጊዜ የቅርብ ጓደኛዋ ማጄደህ መሐመዲ ወደ ቤቷ ልትጎበኛት በሄደች ጊዜ የምትኖርበት ቤት ተራ ምንጣፍ በተነጠፈበት፣ ጥቂት የሱፍ ትራሶች በተቀመጡበት፣ ከመግቢያው አጠገብ ባለ ጠባብ ኩሽና እና ሁለት ትናንሽ ክፍሎች ብቻ ባሉት በአጠቃላይ 80 ካሬ ሜትር በሆነ ቤት ውስጥ እንደሆነ ተናግራ ነበር። እናቷ፣ አባቷና ሌሎች የቅርብ ቤተሰቦቿም ቢሆኑ ይህንን የእርሷን ትህትና እና ከማንኛውም የዓለም ክብር የራቀ የአኗኗር ዘይቤ በተደጋጋሚ አረጋግጠው ተናግረዋል። በእርሷ ህይወት ውስጥ የቅንጦት ዲዛይነር ልብሶች፣ ባለ 4,000 ዳላር የቻኔል ቦርሳዎች፣ በአልማዝ የተለበጡ ውድ ሰዓቶች አልያም የደህንነት ጠባቂ አጃቢዎች ፈፅሞ አይታወቁም። እያወራን ያለነው የኑክሌር መሳሪያ አቅም ያላት፣ መላው ምዕራባውያን የሚንቀጠቀጡላት የታላቋ ሀገር መሪ ልጅ እና ባለቤት ስለነበረችዉ ሴት ነው። እርሷ ማንነቷን ሳታሳውቅ ለህዝቧ ስትል ራሷን አሳልፋ የሰጠች የዘመናችን ጀግና ሴት ነበረች። ይህቺ ሴት ዘህራ ሃዳድ አደል ትባላላች። አሏህ ጀነተል ፊርደዉስ ይወፍቃት። ለመሆኑ በዚህ የጥቅም እና የስልጣን ጥማት በናወዘበት ዓለም ውስጥ እንደ እርሷ ዓይነት ሰው ከየት ይገኛል? t.me/IbnuHashm
የኢማም ዒሊ ኻሚና ፍፃሜ ለዓለም ሀያላን ትልቅ ትምህርት ነዉ። እንደ ተሸነፉ መንግሳታቶች ከጉድጓድ ውስጥ ተጎትተው አልወጡም፤ እጃቸው ላይ የውርደት ካቴና ገብቶ ጠላቶቻቸውን አላስደሰቱም ወይም ደግሞ ተማርከው አልያም አንገት ደፍተው የተከታዮቻቸውን ኩራት አላረከሱም። በእስልምናቸው እንደኮሩ ለዘመኑ የዚዳዊያን እጅ እንደማይሰጡ በተግባር አሳይተው በኩራት ያለፉ የዘመናችን ጀግና መሪ ናቸዉ። የጀግና መሪ አሻራው ለሞት ና ብሎ መጥራት እንጂ ሞት እስኪመጣ መደበቅ አይደለም። ያንን ኩሩ የፐርሺያ ህዝብንም ለባዕድ ሀይሎች አላዋረዱትም፤ የኢስላማዊ ታሪኩን ገፅታ በክህደት እና በሽንፈት አላቆሸሹትም። "ሁሉም ሙስሊም ተንበርክኳል" የሚለው የታሪክ ጠባሳ እንዳይኖር እርሳቸው ህያው ፋና ሆነው አልፈዋል። አዎን! ዛሬ ላይ ፅዮናዊያን እርሳቸዉ በመሞታቸዉ በድል ስሜት ሊደሰቱ ይችላሉ። በየቦታው ያሉ የእነርሱ አገልጋዮችም በደስታ ሊቦርቁ ይችላሉ። ነገር ግን እነርሱ ያልተረዱት ሐቅ ይህ የሽንፈት ሳይሆን የልቅና ጉዞ መሆኑን ነው። ልቅና ማለት ላመኑበት እውነት መኖር ብቻ ሳይሆን ለገቡለት ቃል ታምኖ የመጨረሻዋን የጀግንነት ዋጋ ከፍሎ ማለፍ ነው። ይህ አሟሟት ለጠላቶቻቸው ድል ቢመስላቸውም ለባለ አዕምሮዎች ግን የሰው ልጅ የሞራል ልዕልና የመጨረሻው ጥግ ነው። አሏህ ከሹሀዳኦች እና ከሷሊሆች ያድርጋቸው። ድል አልያም ሸሂድነት ማለት ይህ ነዉ። t.me/IbnuHashm
የፐርሺያ ህዝብ ማለት ዝም ብለዉ የሚኖሩ ህዝቦች ሳይሆኑ የሚወራ ታሪክ፣ የሚኖሩለትም ሆነ የሚሞቱለት ዓላማ ያላቸዉ ድንቅ ህዝቦች ናቸዉ። በዓለም የኢምፓየሮች ታሪክ ውስጥ ማንኛውም ራሱን ልዕለ ሀያል አድርጎ የፈረጀ ወራሪ ሀይል ሁሉ የራሱን መቃብር የሚምሰው ፐርሺያ ምድር ላይ ሲደርስ ነው። የትኞቹም ክንዳቸው የጠነከረ ኢምፓየሮች ሁሉ ወደ ፐርሺያ ሲጠጉ ሳይዋረዱ እና እጅ ሳይሰጡ አይመለሱም። በአብዛኛው የዓለም ክፍል ጦርነት እና መከራ ሲከሰት አብዘሀኛዉ ህዝብ ሀገሩን ጥሎ መኮብለልን እንደ አማራጭ ይወስዳል። ፐርሺያውያን ግን ጦርነት ሲመጣባቸዉ ወደ ዉጭ ሊሰደዱ ቀርቶ ሀገራቸው ስትደፈር በውጭ ሀገር የሚኖሩት ጭምር ጥሪያቸውን አክብረው ወደ እናት ሀገራቸው ይተማሉ። ለዚህም አንዱ ማረጋገጫ በአውስትራሊያ ላይ ግጥሚያ የነበራቸው የሴት እግር ኳስ ቡድን አባላት ናቸው። ከአሜሪካ ጀምሮ ያሉ በርካታ የምዕራባውያን ሀገራት ዜግነት እንስጣችሁ እያሉ ቢለማመጧቸው፣ በግልም ሆነ በቡድን በጥቅማጥቅሞች ሊደልሏቸው ቢሞክሩም ዞር ብለው ምላሽ'ኳ ሳይሰጧቸው ጦር ሜዳ ወደሆነችው እናት ሀገራቸው ተመዉ ገብተዋል። ይህ ተግባር ብቻ የዚህ ህዝብ የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው። ለሀገራቸዉ እና ለመሪያቸዉ ያላቸዉ ፍቅር ልዩ ነዉ። የዚህ ህዝብ መሪ የነበሩት ኢማም ዓሊ ኻሚኔም ቢሆኑ በወጣትነት ዘመናቸው በትግል ሜዳ ላይ ቀኝ እጃቸውን አጥተው በግራ እጃቸው ብቻ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በፅናት የተፋለሙ እና እስከ መጨረሻው የሕይወት እስትንፋሳቸው ድረስ በጦር ግንባር የቆዩ መሪ ነበሩ። በርግጥ የሞቱት ለራሳቸው ሳይሆን ለክብር ነው፤ የወደቁት ለሽንፈት ሳይሆን ትውልድን ቀና አድርጎ ለማሳለፍ ነው። ዓለም የሚያስታውሰው በባርነት የከበሩትን ሳይሆን በነፃነት የሞቱትን ነው። በወርቅ ሀልጋ ላይ ተኝተው የሞቱት ነገሥታት ይረሳሉ፤ በእውነት አደባባይ ላይ የተሰውት ጀግኖች ግን ለዘላለም ህያው ሆነው ይኖራሉ። እርሳቸውም የክብርን ዋጋ ውድ አድርገው እና የነፃነትን ችቦ ለቀጣዩ ትውልድ አቀብለው አልፈዋል። ይህ ገድል ለዘመናት ሲነገር ይኖራል ኢራን አልተንበረከከችም መሪዋም አልተዋረደም። አሏህ ይርሃማቸው ምህረቱንም ይለግሳቸው። በርግጥ ዓለም እንደርሳቸዉ ያለ መሪ ዳግም ትናፍቃለች። t.me/IbnuHashm