Abu hasenet
Статистика((በአንደበትህ መጣራት ባትችል በሰው አንደበት ተጣራ)) እንዳያመልጥዎ የተለያዩኢስላማዊ 📌ዳእዋቶች 📌ንጽጽሮች 📌 አስፈላጊ ዜናዋች እምንለቅበት ቻናል ነው ለሁሉ ተደራሽ እንዲሆን ሼር በማድረግ በአቅምዎ ዳዕዋ ውን ያስፋፉ🙏 ለትብብሮ እናመሰግናለን ✔️
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Криптовалюты (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7
- 1/48двое суток
- 8
- 1/72трое суток
- 8
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://vt.tiktok.com/ZSVd32vWf/
https://vt.tiktok.com/ZSVd32vWf/
"ፊርዐውኖቹ" እና "ሉሲዎቹ" ~ ብሄርተኝነት በጠባቡም ይሁን በሰፊው ትርጓሜውም የጃሂሊያ ስርአት አካል ነው። ሰሞኑን አንድ ስሙንም፣ የስራ ድርሻውንም የማላውቀው 0ረብ በሚገረም ሁኔታ ግብፆች ላይ ሲወርድባቸው አየሁ። ኮመንት ሳጥን ውስጥ ገባሁ። በዚህ መጠን ነው ዐረቦች ግብፆችን የሚጠሏቸው? ይሄ እግር ኳስ ህዝብና ህዝብን ያስተሳስራል የሚለውን ሞቶ ባዶ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ከመራራቅም በላይ በጣም ይጠላላሉ። ግብፆቹም "ነሕኑ ፈራዒና" / "እኛ ፊርዐውኆች ነን" / ይላሉ። ምላሳቸው እንዴት ችሎ አወጣላቸው ግን? ጃሂሊያ ነገሮችን 'ኖርማል' ስለሚያስመስል እንጂ አሁን ይሄ ሙስሊም በሆነ አካል የሚቻል ነው ወይ? በሃገራችንም ካልተሳሳትኩ "ሉሲዎች" ሲሉ ሰምቻለሁ። "ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ናት" ፣ Land of origin፣ እያለ ሰው በፈጣሪ የተፈጠረ ሳይሆን የዝግመተ ለውጥ ውጤት ነው በሚለው የዝግመቴዎች ሲምቦል የሚጎረር ስንት "ሃይማኖተኛ" አለ? ኧረ እንዲያውም የሆነ ጊዜ "የሃይማኖት ሰዎች" ሉሲን ሲያጅቡ ነበር። እንዲህ ነው ከረከሱ አይቀር! ሌሎችም ኢሬቻን ሲደግፉ ነበር። ይሄ የጃሂሊያ ውጤት ነው። በዘር ተለውሶ ለሚቀርብ የኩ F ር ነፀብራቅ እንድትወግን ያደርግሃል። ከእምነት ጋር የሚጋጭን ነገር በኢትዮጵያ ስም፣ በአማራ ስም፣ በኦሮሞ ስም፣ በትግራይ ስም፣ በአፋር ስም፣ ... እያቀረቡ በጭፍን እንድትወግን ካደረጉህ የጭንቅላትህ ሪሞት በነሱ እጅ ነው ያለው ማለት ነው። እዚህ ደረጃ ከደረስክ ከሰው ተራ የወረድክ፣ በራስህ መወሰን የማትችል በቀደዱልህ የምትፈስ የቦይ ውሃ ነህ ማለት ነው። ብሄርተኝነት ከአስካሪ መጠጥ፣ ከአደንዛዥ እፅ የከፋ ተፅእኖ ቶሎ የማይለቅ መጥፎ ልክፍት ነው። = ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
⚠️ ለ"online ኡስታዝ" ተብዬዎች የተላለፈ ከባድ ማስጠንቀቂያ! ይህ በዲን ስም ለሚነግዱ፣ አደራ ለሚበሉና እህቶችን ለሚያውኩ "በሚዲያ ቁረአን እናቀራለን ለሚሉ ኡስታዞች" የተሰጠ ጠንካራ ማሳሰቢያ! —** ቁርአን የልባችን ብርሃን፣ የነፍሳችን ምግብ እና የቂያማ ቀን አማላጃችን ነው። ይህንን ታላቅ የአላህ ቃል ማስተማር የነቢያት ቅርስ እንጂ የገንዘብ ማጋቢያ ወጥመድ አይደለም። ሆኖም ግን በቅርብ ጊዜ በሚዲያ ላይ "ኡስታዝ" የሚለውን ክቡር ስም ተገን አድርገው፣ የእህቶቻችንን አደራ የሚበሉና የዲን ንግድ ውስጥ የገቡ ጥቂት ግለሰቦች የብዙ እህቶቻችንን ህይወት እያመሰቃቀሉ ይገኛሉ። ዛሬ የምናነሳው ጉዳይ የብዙ እህቶቻችንን ልብ የሰበረ፣ የእምነት ጥንካሬያቸውን የፈተነና በዝምታ የታለፈ ትልቅ ጠባሳ ነው። ቁርአን መቅራትና ማቅራት የነቢያት ታላቅ ቅርስ እንጂ፣ የሰው ኪስ ማድረቂያ ወይም የሴቶች መጀንጀኛ ድልድይ አይደለም። ሆኖም ግን፣ "ኡስታዝ" የሚለውን ክቡር ስም ተገን አድርገው፣ በአላህ ቃል ስም የሚነግዱ ጥቂት ግለሰቦች የኡማውን ክብር እያቆሸሹ ይገኛሉ። 📍 ለእነዚህ "ኡስታዞች" የቀረበ ግልጽ መልፅክት! 1. "ታማኝነት" (አማና) የት ሄደ? አንዲት እህታችን ቁርአን ልቅራ ብላ ከፊታችሁ ስትቀመጥ፣ እናንተ በስልካችሁ ቻት የምታደርጉ፣ የት ላይ እንደደረሰች የማታውቁ፣ ስህተቷን ሳታርሙ "ማሻአላህ" እያላችሁ የምታሳልፉ ሰዎች ሆይ— አላህን አትፈሩም? ይህቺ እህት ቁርአን መማር የፈለገችው ከአላህ ጋር ለመገናኘት ነው፤ እናንተ ግን በዝንታችሁና በቸልተኝነታችሁ በአላህና በእሷ መካከል ግርዶሽ ሆናችኋል። 2. የድሆችን እና የቤተሰብን ሀቅ አትብሉ! ብዙዎቹ እህቶቻችን ቤተሰቦቻቸው በረሃብ እየተሰቃዩ፣ ካለቻቸው ጥቂት የቀን ገቢ ላይ ቀንሰው ነው ለእናንተ ክፍያ የሚከፍሉት። የአራት እና የአምስት ወር ክፍያ ቀድማችሁ ተቀብላችሁ፣ ግማሽ ሱራ ሳታቀሩ "በቃሽ" ብላችሁ የምታባርሩ ሰዎች— ይህ የምትበሉት ብር ለእናንተም ሆነ ለቤተሰባችሁ "ሀራም" (የእሳት ሲሳይ) እንጂ በረካ አይሆንም። ስራውን በአግባቡ ሳትሰሩ የምትቀበሉት እያንዳንዱ ሳንቲም በቂያማ ቀን ይጠየቅባችኋል። 3. "ኡስታዝነት" የሴቶች መጀንጀኛ ዘዴ አይደለም! በዲን ስም ተሸሽጋችሁ፣ በውስጥ መስመር (Inbox) እየገባችሁ የተማሪዎቻችሁን ስነ-ልቦና የምትሰርቁ፣ ከአላማቸው የምታዘናጉና ክብራቸውን የምትነኩ ግለሰቦች ሆይ— የቁርአን መምህርነት ስም አይገባችሁም! እናንተ የዲን ተኩላዎች እንጂ መሪዎች አይደላችሁም። የሙስሊም ሴቶች ክብር የአላህ አደራ መሆኑን አትርሱ። 💡 ተማሪ እህቶቻችን ምን ማድረግ አለባቸው? እህቴ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደርስብሽ መከራ ሁሉ ምንዳ አለው። ነገር ግን አትታለዪ፦ ይህ በደል የብዙዎች መሆኑን እንረዳለን፤ ነገር ግን ዝምታው ሊበቃ ይገባል። ብራችሁንም ጊዜያችሁንም እንዳትበዘበዙ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች አድርጉ፦ * 🚩 ሴት መምህራንን (ኡስታዛቶችን) ፈልጉ፦ ከወንድ ጋር ከመቀራት ይልቅ እውቀቱና ተቅዋው ያላቸውን ሴት መምህራን መፈለግ ለዲናችሁም ለክብራችሁም አስተማማኝ ነው። * 🚩 ለክፍያ አትቸኩሉ፦ ምንም አይነት አስተማማኝ ማስረጃ ሳይኖራችሁ የብዙ ወር ክፍያ በአንዴ አትክፈሉ። ጥራቱን እያያችሁ በየወሩ ክፈሉ። * 🚩 ድምፃችሁን አውጡ፦ በደል ሲደርስባችሁ ዝም አትበሉ። ለሌሎች እህቶች ንገሩ፣ አጋልጡ። ዝምታችሁ ሌላ እህት ለተመሳሳይ በደል እንድትዳረግ በር ይከፍታል። * 🚩 የታወቁ መርከዞችን ምረጡ፦ በግለሰብ ደረጃ "አቀራለሁ" ከሚሉ ይልቅ ተጠያቂነትና ክትትል ባለባቸው ታዋቂ የኦንላይን መርከዞች መመዝገብ ብክነትን ይቀንሳል። #### ⚠️ ከጉዳዩ በስተጀርባ ያሉ ተጨማሪ አደጋዎች ይህ ችግር ከገንዘብ ብክነት ባለፈ የሚከተሉትን አደጋዎች ይዞ መጥቷል፦ * የእምነት መላላት፦ እህቶች በእነዚህ ሰዎች ምክንያት መላውን የሃይማኖት መምህራን በጥርጣሬ እንዲያዩና ከዲን ትምህርት እንዲርቁ ያደርጋል። * የቁርአን ስርአት መበላሸት፦ ስህተት ሳይታረም "ማሻአላህ" እየተባለ የሚታለፍ ከሆነ፣ ትውልዱ ቁርአንን በተሳሳተ መረጃና አቀራር እንዲይዝ ያደርጋል። * የዳዕዋው ዘርፍ መርከስ፦ በዲን ስም የሚነግዱ ሰዎች በበዙ ቁጥር፣ እውነተኛዎቹና አላህን የሚፈሩ ኡስታዞች ስማቸው አብሮ እንዲጠፋ ያደርጋል። 📢 የመጨረሻ መልዕክት! እውነተኛ አላህን የሚፈሩ፣ ሌት ተቀን የሚያቀሩ፣ የሰውን ገንዘብ የማይመኙ ምርጥ ኡስታዞች አሉን፤ አላህ ያብዛቸው፣ ይጠብቃቸውም። ነገር ግን እነዚህን ጥቂት በዝባዦች ማጋለጥና መገሰጽ የሁላችንም ግዴታ ነው። አንቺ የተበደልሽ እህቴ ሆይ! አላህ ላወጣሽው ወጪና ለደከምሽው ድካም ምንዳሽን ይክፈልሽ። በእነዚህ መጥፎ ሰዎች ምክንያት የቁርአንን መንገድ እንዳትተዪው፤ አላህ የተሻለ መምህር ይወፍቅሻል። "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ሁኑ።" (አል-ተውባህ፡ 119) t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
без подписи
ኢሥላም የተስፋፋው በሰይፍ ነው እያላችሁ ስትቀጥፉ አልነበረም እንዴ? ታዲያ ኢሥላም ወደ ኢትዮጵያ የገባው ለምን በነጋዴዎች አማካኝነት ሆነ? ለምን በሰይፍ አልሆነም? እንደው እውነታው ሌላ የእናንተ ቅጥፈት ሌላ😁 ✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ https://t.me/mukamil12
በነገራችን ላይ ክርስትያኖች ሙሥሊሞችን ለማጥቃትና ለማጥፋት ከየትኛውም ሐገር ሆነ ሐይማኖት ጋር ትብብር ያደርጋሉ! ለዚህ ሁነኛ ምሳሌ በኢማሙ አህመድ(አህመድ ግራኝ) ጊዜ የተደረገውን ማየት በቂ ነው! ክርስትያኖች ኢማሙ አህመድን ለመዋጋትና ሙሥሊሞችን ለማጥፋት ከ ፖርቹጋል ጋር አንድ ሆነው ነበር። በዛን ጊዜ ፖርቹጋላዊያን የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነበሩ ዛሬ በኢትዮጵያ የተስፋፋው የካቶሊክ እምነት ዋና መሰረቱም ያ ጦርነት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሙሥሊሞችን ለማጥፋት ከማንም ሐገር ከየትኛውም ሐይማኖት ጋር ትተባበራለች። ዛሬ ላይ እንኳን ልብ ብላችሁ ከተመለከታችሁ እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ የምታደርገውን ጭፍጨፋ በግልጽ ድል ለእስራኤል እያሉ ሲደግፉ ትመለከታላችሁ። ✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ https://t.me/mukamil12
??
ያለቀሰ ሁሉ ተበዳይ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል! የዩሱፍን ወንድሞች ተመልከት በዳዮቹ እነርሱ ሆነው ሲያበቁ ወደ አባታቸው ሲመለሱ ግን ተበዳይ ለመምሰል እያለቀሱ ነበር የመጡት። እናም ያለቀሰ ሁሉ ተበዳይ አይደለም።😊 وَجَاءُوا أَبَاهُمْ عِشَاءً يَبْكُونَ (📗ሱረቱ ዩሱፍ - 16) አባታቸውንም በምሽት እያለቀሱ መጡት፡፡ ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ https://t.me/mukamil12
✨መካ ግርማ ሞገስ ያላት ውብ ከተማ ስትሆን መዲና ደግሞ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት ምድር ናት። 🌹 አንደኛዋ በፍርሀትና በናፍቆት ስታንቀጠቅጥ፣ ሌላኛዋ ደግሞ በደስታና በሰላም ታክማለች። 👉መካ የጉዞው መጀመሪያ ስትሆን መዲና ደግሞ የነፍስ ማረፊያ መጠጊያ ናት። የመካና የመዲና ለሊቶች ልዩ ውበት አላቸው። ለሊቱ ሲገሰግስና የሰማዩ ድምቀት ሲጨምር የመስጂዱ ነጫጭ እምነበረድ ወለሎች በብርሀን ይንፀባረቃሉ? በ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በዝምታና በተመሰጥኦ ዱዐ ሲያደርጉ ከተሞቹ በሰላም እቅፍ ውስጥ ይረጋሉ። 👉ወደነዚህ ከተሞች የተጓዘና የአየሩን ጠረን ያሸተተ ሰው አካሉ ይመለስ ይሆናል እንጂ ልቡ ግን እዚያው ለዘላለም ቀርቶ ይኖራል። 🤲🤲አላህዋ! ዳር ቆመን ታዛቢ ብቻ አታድርገን። ሩህ ጀሰዳችን ለትዕዛዝህ የሰላ ባሮችህ አድርገኸን እኛንም ከቤትህ ከደጃፍህ አመላልሰን። "ኑ" የምትለንን ቀን ቅርብ አድርገውና ሀጅ ዑምራውን፣ መካ መዲናውን፣ሚና ሙዝደሊፋውን ወፍቀን ያረብ....... አሰላሙ አለይኩም መሰዓል ኸይር ወዳጆቼ?
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ! / ሰላም ጤና ይስጥልኝ! 🌸 የቤተሰብ፣ የጋብቻ እና የውርስ ጉዳዮች በማንኛውም ጊዜ ሊያጋጥሙን የሚችሉ የዕለት ተዕለት የሕይወታችን አካል ናቸው። ታዲያ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መብትና ግዴታዎን በምን ያህል ደረጃ ያውቃሉ? 🤔 ይህን ክፍተት የሚሞላ እና ራስዎን ከተጠያቂነት እንዲጠብቁ የሚረዳ ወሳኝ የሕግ መጽሐፍ እነሆ ተዘጋጅቶሎታል! 📚✨ 📩 መጽሐፉን ለማዘዝ ወይም ለማማከር በዚህ የቴሌግራም አድራሻዬ ያግኙኝ👇 👉 @Hikmetulahbedredin
አንድ ጀግና ላስተዋዉቃችሁ! በየጦር ሜዳው የጣዖት አምላኪዎችን አንገት ቀንጥሶ ከአፈር ጋር በመቀላቀል ረገድ አቻ ያልተገኘለት ጀግና ተዋጊ ነው። የአሏህንና የነቢዩን 🤍 ጠላቶች በማሸበር ወደር ያልተገኘለትም ጀግና ነዉ። ወደ ጦር ሜዳ ሲገባ ጭንቅላቱ ላይ የሚጠመጥማትን ቀይ አማይማ የተመለከተ ከሀዲ በሙሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር። ግና አንድ መሰረታዊ የሆነ ትልቅ ችግር ነበረበት፤ ሁልጊዜም የአልኮል መጠጥ ይጠጣል፣ ጭንብስ ብሎም ይሰክራል። የአሏህን ሕግ በተደጋጋሚ እየጣሰ ስለሚያስቸግር በአደባባይ ብዙ ጊዜ ተገርፏል። ከዚህ አስከፊ ድርጊቱና ሱሱ ባለመላቀቁ ምክንያት በመጨረሻ በእግረ ሙቅ ተጠፍሮ በግዞት ወደ እስር ቤት ተወርውሮ ነበር። ዕለቱ የቃዲሲያ ዘመቻ እየተካሄደ የነበረበት ወቅት ነበር። አቡ ሚህጀን የታሰረው ጦርነቱ ከሚካሄድበት ሜዳ እጅግ ሳይርቅ በቅርብ ርቀት ላይ ነበር። ከታሰረበት ሆኖ የፈረሶችን ማሽካካት እና የሰይፎች ግጭት ሲሰማ መታሰሩንና ከትግሉ መራቁን አምርሮ ጠላው። ከተጋጋለው ጦር መሀል ገብቶ የአሏህን ጠላቶች አንገት በሰይፍ መሸልቀቅን እና ለአሏህ ዲን መዋጋትን በእጅጉ ናፈቀ። ከአይኖቹ እምባን እያረገፈ ውስጡ ክፉኛ ተረበሸ፤ የጂሃድ ፍቅር እንደ ነበልባል እያንገበገበ አላስችል ቢለው የታሰረበትን ክፍል በር በሀይል ደብድቦ ለጦር አዛዡ ለሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ 🤎 ባለቤት መልዕክት ላከ። እንዲህም አላት በአሏህ ይሁንብሽ! ካቴናዬን ፈተሽ የጦር መሳሪያና የሰዕድን ፈረስ አዘጋጅተሽ የናፈቅኩትን ጂሃድ እንድካፈል አድርጊኝ። ወደ ካፊሮች መሃል ገብቼ እፋለም ዘንድ እርጂኝ፤ በሕይወት ከተረፍኩ ራሴ መጥቼ የእስር ቤቱን በር በላዬ ላይ እከረችማለሁ፤ እግሬንም መልሼ እታሰራለሁ ሲል ተማፀናት። የጦር መሪው ሚስት የአቡ ሚህጂን እውነተኛ የጂሃድ ቁርጠኝነት ተመልከታ ፈረስና ሰይፍ ሰጥታ ለቀቀችው። አቡ ሚህጀንም ማንነቱን ለመሸፈን ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ልክ እንደ መብረቅ ወደ ጦር ሜዳው መሃል ሰፈረ። በዚያን ወቅት ካፊሮች የበላይነትን ለመቆጣጠር ቀርበዋል። የሙስሊሙም ጦር ተዳክሞ ነበር። በዚህ አስጨናቂ ቅጽበት አቡ ሚህጀን ከመሃላቸው ተከሰተ፤ ጠላትን እየበተነ አንዱን በአንዱ ላይ አነባበረው። ድል ወዲያውኑ ወደ ሙስሊሞች ማዘንበል ጀመረ። የካፊርን ደም የተጠማው አቡ ሚህጀን የአሏህንና የሙስሊሙን ጠላቶች እንደ ቅጠል አረገፋቸው፤ ከፊቱ የቀረበውን የጠላት ጦር አንገት እየቀነጠሰ ወደ መሃል ገሰገሰ። የሙስሊሙ ጦር አዛዥ ሰዕድ 🤎 የዚህን ተዋጊ ጀግንነት እየተመለከተ እንዲህ በፅናት የአሏህን ጠላቶች አመድ የሚያደርገው ይህ ፈረስና ተዋጊ ማን ነው? ሲል ጠየቀ። የሚያውቀው ሰው ግን ጠፋ፤ ሰዕድም በመገረም ፈረሱ የኔን ፈረስ በልቃዕን ይመስላል። የአጠቃቁ ስልቱ ደግሞ የአቡ ሚህጀንን ይመስላል። ነገር ግን አቡ ሚህጀን የታሰረ በመሆኑ እርሱ ሊሆን አይችልም አለ። ጦርነቱ በሙስሊሞች ድል አድራጊነት መጠናቀቁን የተመለከተው አቡ ሚህጀን በገባው ቃል መሰረት ሳይዘገይ ተመልሶ ወደ እስር ቤቱ ገባና በጦርነት የደከሙ እግሮቹንና እጆቹን በካቴና ጠፍሮ አሰራቸው። ሰዕድ 🤎 ከጦር ሜዳ ወደ ቤቱ ሲመለስ ሚስቱ ዛሬ ውጊያው እንዴት ነበር? በማለት ጠየቀችው። ሰዕድም መጀመሪያ ላይ የሽንፈት ማቅ ልንከናነብ ቀርበን ነበር፤ አሏህ ግን ሳናስበው አንድ ጀግና የጦር ተዋጊ ላከልንና ያ የመነመነ የድል ተስፋችን ወደ እኛ ተቀልብሶ ለማሸነፍ ቻልን። አቡ ሚህጀንን አስሬው ባልሄድ ኖሮ ያ ጀግና ተፋላሚ እርሱ ነው ብዬ እጠረጥር ነበር በማለት ተናገረ። ሚስቱም በአሏህ ይሁንብኝ ያ ተዋጊ ራሱ አቡ ሚህጀን ነው ብላ የተከሰተውን በሙሉ አስረዳችው። በሁኔታው በእጅጉ የተደሰተው ሰዕድ ወዲያውኑ አቡ ሚህጀንን አስጠርቶ ካቴናውን እየፈታ በአሏህ ይሁንብኝ ከአሁኗ ሰዓት ጀምሬ አላስርህም፣ አልገርፍህም፤ በነፃ ለቅቄሃለሁ አለው። አቡ ሚህጀንም ቀጠል በማድረግ በአሏህ ይሁንብኝ እኔም ከዛሬ ጀምሬ አልኮል አልቀምስም፣ አልሰክርም በማለት መለሰ። ከዛች ቀን ጀምሮ አቡ ሚህጀን መጠጥን ፈፅሞ በመተው አሏህን ከሚፈሩ ታላላቅ ሙጃሂዶች አንዱ ሆኖ ዘለቀ። t.me/IbnuHashm
የአቡ ጃዕፈር አል ወራክ የልጅ ልጅና የኢስላማዊቷ አንደሉስ የፅናት ተምሳሌት የሆነች ትጉህ ሙጃሂድ ነበረች። ከአባቷ የወረሰችው ጥልቅ ንባብና የዕውቀት ፍቅር ከነቤተመፅሕፍቱ የተሰጣት ትልቅ አደራ ነበር። ገና በልጅነቷ የካቶሊክ መስቀላውያን ወታደሮች የእስልምናን መብራት ለማጥፋት ቁርዓንን፣ ኢስላማዊ የታሪክ መጻሕፍትን እና በሙስሊም ሳይንቲስቶች የተቀመሩ የምርምር ውጤቶችን በግራናዳ የረምላ አደባባይ ላይ በግፍ ሲያቃጥሉ በዓይኗ ተመልክታ በቁጭት አድጋለች። ሰሊማ በአንደሉስ ከነበሩት ጥቂት የበሰሉ ሴት ምሁራን መካከል አንዷ ናት። በተለይም በሕክምናው ዘርፍ የላቀ ብቃት የነበራት ሊቅ ነበረች። በገዛ ቤቷ ውስጥ ለሕሙማን የሚሆኑ መድሃኒቶችን የምታመርትበት የራሷ የሆነ የላቦራቶሪ ክፍል ሳይቀር ነበራት። የክርስትና እምነት በአንደሉስ ምድር ላይ በሀይል እንዲሰፍን ተደርጎ ሙስሊሞችን በግድ የማክፈር የኢንክዊዚሽን ዘመቻ ሲጀመር ባለቤቷ ሰዐድ አል ማሊቂ አቋሙን ያልሸጠ ሙጃሂድ በመሆኑ ከመስቀላውያኑ አደን በመሸሽ ቀን ቀን በምስጢር ይሸሸግ ነበር። ሌሊት ሌሊት በድብቅ ወደ ቤቱ በመምጣት ከባለቤቱ ከሰሊማ ጋር ይገናኛል። ጥንቆላና ድግምት ትሰራለች፤ ሌሊት ሌሊት በአየር ላይ እየበረረች ከሰይጣን ጋር ዝሙት ትፈፅማለች፤ ከእርሱም አርግዛለች በሚል ክስ በቁጥጥር ሥር አዋሏት። በመቀጠልም አሰቃቂ ውሳኔዎችን በሚያስተላልፈውና የጭካኔ ማዕከል በነበረው መሐኪመ ተፍቲሽ በአንደሉስ ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ፊት ለፊት አቆሟት። በችሎቱም ላይ በነቢዩ 🤍 የእስራእ ወል ሚዕራጅ ጉዞ አምናለች፤ ከሰይጣንም አርግዛለች በሚል ከንቱ ሰበብ የስቅላትና የሞት ፍርድ ተወሰነባት። ከታሰረችበት እስር ቤት ውስጥ በህይወትና በሞት መካከል ሆና ታጣጥራለች። እርግጫውና ዱላው ከመደፈሯ ጋር ተደማምሮ የመጨረሻ እስትንፋሷ ላይ ተቃርባለች። ጌታዬ አሏህ ነው በማለቷ ብቻ በመስቀላዊያን ወታደሮች ተደፍራለች። በሆዷ ውስጥ ከሐላል ባለቤቷ ያገኘችውን ፅንስ ተሸክማ ሳለች በጀርባዋ አስተኝተው ሆዷን በስለታማ ከስክስና በደንዳና ዱላ ይመቷት ያዙ። ከዓይኗ ኩልል ብሎ የሚወርደው የሕመም ዕንባ ከአፏ ከሚፈሰው የደም ጎርፍ ጋር ተቀላቅሎ ከንፈሯን አርሶታል። ከማህፀኗ ውስጥ ፅንሱ እየተቆራረጠ ሲወጣ አቅሟን ሙሉ በሙሉ አሳጣት። ወታደሮች ግን በዚህ አላበቁም፤ በትከሻቸው ተሸክመው የሽንት ቤት መቀመጫ ቀዳዳ ላይ በአፏ አስተኟት። በእጃቸው በያዙት ስለታማ ቢላ እጅግ በሚዘግን ሁኔታ ጡቷን ቆረጧት። በዚህ ሁሉ የስቃይ ጣር ውስጥ ሆና እስትንፋሷ ሊቋረጥ አፋፍ ላይ በደረሰበት ጊዜ አንገቷን ወደ ላይ አቅንታ በደካማ ድምፅ ''ጌታዬ ሆይ! በዚህች ምድር ላይ በሕይወት የመቆየቴ ብቸኛ ምክንያት አንተን ማምለክና መገዛት ነበር፤ ግና የሚገባህን ያህል ሳልገዛህ ቀረሁ በማለት ተናገረች። ስለ አሏህ ብቸኛ ተመላኪነትና ረሱልም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መስክራ ሩኋ ከጀሰዷ ተላቀቀ። የአንደሉሷን ሸሂድ ሰሊማ ቢንት ጃዕፈርን አሏህ ጀነተል ፍርደውስ ወራሽ ያድርጋት! t.me/IbnuHashm
без подписи
https://vt.tiktok.com/ZSXKrK4bx/
https://vt.tiktok.com/ZSXKMqfMJ/
https://vt.tiktok.com/ZSXK6tNSW/
በሐራም ግንኙነት ውስጥ ብዙ ነገሮችን ታጣለህ። ገንዘብህን፣ ግዜህን ከዛም ወንጀል ላይ ትወድቃለህ። አላህ ይጠብቀን🤲
https://vt.tiktok.com/ZSX35gR3V/
https://vt.tiktok.com/ZSX3UNVYM/