tgindex
Event Addis Media

Event Addis Media

Статистика

Connect with Addis artistic community! Contact: @Tmanaye

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
10
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
9 428
+3 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 578
21 постов
Вовлечённость
27,3%
к подписчикам
Постов в день
1,4
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 564
1/48двое суток
1 792
1/72трое суток
1 933

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.1 3677из kelematadshub

    . የቻናል ጥቆማ የህይወት እይታዎን ማሻሻል ከፈለጉ ይህ ቦታ ለእርስዎ ነዉ፤ ይቀላቀሉ ! @Seidendre የሚያጋጥሙንን ክስተቶች መወሰን እና መቆጣጠር ባንችልም ስሜታችንን እና አፀፋችንን መቆጣጠር ግን በእጃችን ነዉ። Rise Daily — Where great minds are built through daily discipline ! 📌 Join: @SeidEndre 🚀Share: @SeidEndre

  • 12 авг.1 64687

    🔶ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን በድምቀት ተከበረ ​"የወጣቶች ቀን፣ የበጎ ፈቃደኝነት እና የተለያዩ  እድሎች” በሚል መሪ ቃል በብሪቲሽ ካውንስል አዳራሽ የተዘጋጀው የ2026 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። ​በ'ስዊት ላይፍ ፎር ኦል' (Sweet Life For All) ዋና አዘጋጅነት፣ ከብሪቲሽ ካውንስል፣ ከኢትዮጵያ የብሪታንያ ኤምባሲ እና ከቲኤች group (TH Group) ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ታዳጊ ተማሪዎች  ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል። መድረኩ ወጣቶች የሚማሩበት፣ የሚወያዩበት፣ ትስስር የሚፈጥሩበት እና ተስፋ የሚያንፁበት አጋጣሚን ፈጥሯል። ​በበዓሉ አከባበር ላይ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ፣ ከብሪቲሽ ካውንስል እንዲሁም ከብሪቲሽ ኤምባሲ የተወከሉ እንግዶች እንዲሁም የሲቪል ማህበራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ የወጣቶች ድምፅ የፕሮግራሙ ዋና ማዕከል ሆኖ ውሏል። ​በወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረ አሳታፊ እና አበረታች ውይይት ተካሂዷል።በስደት እና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ተደርጓል። ​በወጣቶች የተዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች የቀረቡ ሲሆን፣ አወንታዊ የሥራ ትስስሮችም ተፈጥረዋል።​ይህ መድረክ ወጣቶች ማህበረሰባቸውን የማገልገል እና ለማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ የማፍለቅ ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው በተግባር ያሳየ እንደነበር ተገልጿል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 12 авг.1 7721511

    🔶ሀሰተኛው ሞትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት በቻይና ሁናን ግዛት ሰክሮ በማሽከርከሩ የሚጠብቀውን የሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ የሐሰት ሞትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ያዘጋጀው ወጣት በቁጥጥር ሥር ዋለ። ሲ የተባለው ግለሰብ የሕግ ተጠያቂነትን ለማምለጥ ሲል ከቤተሰቡ ጋር በመተባበር የሐሰት የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸሙን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ግለሰቡ ቀደም ሲል ያለ መንጃ ፈቃድ በስካር በማሽከርከር ሁለት ጊዜ የተያዘ ሲሆን፣ ለሦስተኛ ጊዜ በተመሳሳይ ጥፋት በመያዙ ምክንያት የሚጠብቀውን የእስራት ቅጣት በመፍራት በዋስ ከተለቀቀ በኋላ ከሀገር ለማምለጥ አቅዷል። በመቀጠልም  ሲ እና ቤተሰቦቹ አስቀድመው የሬሳ ሣጥን በመግዛት ዕቅዳቸውን መተግበር ጀምረዋል። ፖሊስ እንዳወጣው መረጃ፤ አቶ ሲ በመድኃኒት መጠን ማለፍ ምክንያት እንደሞተ ለማስመሰል ባዶ የመድኃኒት ብልቃጦችን በቤቱ በመበተን፣ እስትንፋስን የመያዝ ልምምድ በማድረግና የሰውነት ሙቀትን የሚቀንሱ መሣሪያዎችን በመጠቀም የሐሰት ሞቱን አስመስሏል። የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በተካሄደበት ዕለትም እናቱና አያቱ የሲ ፊት በመድኃኒቱ ምክንያት ተበላሽቷል የሚል ምክንያት በመስጠት ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ቀብሩን ፈጽመዋል። የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት በሚከናወንበት ወቅት ግን ግለሰቡ ወደ ሌላ ግዛት በማምለጥ ላይ ነበር። የፖሊስ አባላት ድራማውን በቀላሉ ሊደርሱበት የቻሉት የሬሳ ሣጥኑ ግለሰቡ ከመሞቱ በፊት በመገዛቱ፣ የሕክምና እርዳታ ወይም ፖሊስ ባለመጠራቱ፣ የሞት ምስክር ወረቀት ባለመኖሩና የክትትል ካሜራዎች እንዲሁም የባንክ እንቅስቃሴዎች ግለሰቡ በሕይወት መኖሩን በማረጋገጣቸው ነበር። በክትትሉም ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ የ5 ወራት የእስራት ቅጣትና የ20 ሺህ ዩዋን የገንዘብ መቀጮ ተጥሉበታል። ©️ቻናል ዋን ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 11 авг.1 9861361

    🔶3ኛው ‘አዲስ ኬክ እና ቤክ ኤክስፖ’ ይካሄዳል በኤክስፖው ላይ ታዋቂ ካፌዎች፣ ዳቦ ቤት እና ኬክ ቤቶች እንዲሁም የኬክ ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ይሳተፋሉ። በተጨማሪም የተለያየ ባለሙያ ሼፎች ስለ ኬክ አሰራር እና የዘርፉን አዳዲስ ነገሮች ትምህርት እና ልምድ ይሰጣሉ። እንዲሁም የተለያዩ ጌሞች፣ የሼፎች ውድድሮች እና ለታዳሚዎች የተለያዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ውድድሮች መዘጋጀታቸውን አዘጋጆቹ ለአራዳ አስታውቀዋል። 3ኛው ‘አዲስ ኬክ እና ቤክ ኤክስፖ’ addis cake and bake expo ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ይካሄዳል። መግቢያው በነፃ በመሆኑ ታዳሚዎች ይህን ልዩ ኩነት እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል ሲል አራዳ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 11 авг.1 751155

    🔶የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት 1 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ መሆኑን ዐቢይ አህመድ ጠቅሰዋል። ‎ ‎ፓርኩ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ መሆኑን በመጥቀስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል ሲሉም አስፍረዋል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 11 авг.1 6921411

    🔶"ለድምጽ ብክለት የሚጣለው ቅጣት ትንሹ 5 ሺህ ብር፤ ትልቁ ደግሞ 25 ሺህ ብር ነው" አዲስ አበባ የድምጽ ብክለት በሚፈጥሩ ተቋማት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት ልትጥል ነው አዲሱ መመሪያ የበለጠ አስተማሪ እና አጥፊዎችን ቆንጠጥ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለድምጽ ብክለት የሚጣለው ቅጣት ትንሹ 5 ሺህ ብር፤ ትልቁ ደግሞ 25 ሺህ ብር ነው፡፡ በ2018 በጀት ዓመት 12,376 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የድምጽ ብክለት ቁጥጥር ተደርጓል፦ 3,116 አገልግሎት ሰጪዎች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፣ 28 ታሽገዋል፣ ከተላለፈ የገንዘብ ቅጣት 140,000 ብር ተሰብስቧል፡፡ የቅጣት እርከኑን በአዲስ አበባ ለመተግበር የሚያስችለው አዲስ ረቂቅ መመሪያ ለከተማ አስተዳደሩ ፍትሕ ቢሮ መላኩን የሀገር ውስጥ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 11 авг.1 75557из yimaru

    እንግሊዝኛን መናገር በመቻልህ ብቻ ብዙ የውጪ ዕድሎች እያመለጡህ ነው! በየቀኑ 10 ደቂቃ ብቻ ተለማመድ፣ የመናገር ችሎታህን አሻሽል እና በራስ መተማመን ጨምር። ዛሬ ጀምር። ነገ በልበ ሙሉነት ተናገር! ✅ Free Video Lessons ✅ Free Conversation Practice ✅ Expert Guidance & Practice Materials To download our app: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.yimaru.lms.app For any help and enquiries: Call: 0946396655 Telegram: @yimarusup Telegram channel: https://t.me/yimaru

  • 10 авг.2 2243524

    🔶 ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ ነው ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንደሆነ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው በአሁኑ ወቅት ከሆቴሉ ጀርባ የሚገኙት ቦታዎችና ግንባታዎች በመፍረስ ላይ ሲሆኑ ሆቴሉ እስከሚቀጥለው ጥቅምት ፈርሶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ተብሏል። ይህ ሆቴል የሚፈርሰው በምትኩ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ሊሰራበት ነው፡፡ የሆቴሉ ባለቤት የሆነው ቢኬ ግሩፕ ከመንግስት ከገዛው በኋላ የማስፋፊያ ስራ ወዲያውኑ የጀመረ ሲሆን ከይዞታው 4000 ካሬ ሜትር በተጨማሪ በ5500 ካሬ ሜትር ላይ ትልቅ ህንፃ የመገንባት እቅድ እንዳለው አስታውቆ ነበር፡፡ ከመነሻው እቅዱ ባለ63 ፎቅ ህንፃ የመገንባት ቢሆንም ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/309 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 10 авг.2 04588

    🔶የዕድሜ ደመራ መጽሐፍ ተመረቀ የደራሲት፣ መምህርትና ጋዜጠኛ ውድአላት ገዳሙ ተሻለ የዕድሜ ደመራ መጽሐፍ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በድምቀት ተመርቋል። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደራሲቷ የቅርብ ዘመዶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በርካታ የጥበብ ወዳጆች ተገኝተዋል። ይህ መጽሐፍ የውድአላት ገዳሙ ተሻለን የሕይወት ትውስታዎችንና የልጅነት ጉዞዎችን የሚዳስስ ነው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 10 авг.2 043212из kelematadshub

    የቴሌግራም ቻናል ባለቤት ከሆኑ እና ከ850 በላይ ሰብስክራበር ካለዎት ማስታወቂያዎችን በቻናሎ ላይ በመልቀቅ በቀላሉ ገንዘብ ያግኙ። ከ 120+ በላይ ቻናሎች አብረውን እየሰሩ ነው፡፡ only for Ethiopian Based Telegram Channels. Payment With Telebirr Register on kelemat Ads & Start immediately Interested? 👉 Contact us for registration @temaripath

  • 8 авг.2 342102

    🔸 ጣፋጭ ሕይወት በአራዳ 95.1 ከወራት እረፍት በኋላ ዛሬ ወደ አየር ይመለሳል። ከ8ዓመታት በላይ የአድማጮችን ልብ ያሸነፈው ፕሮግራም በአራዳ FM 95.1 ዛሬ ይጀምራል! ከ8ዓመታት በላይ የአድማጮችን ልብ በሀሳብ፣ በተስፋ እና በአዎንታዊ እይታ ያጣፈጠው "ጣፋጭ ሕይወት" የሬዲዮ ፕሮግራም... አሁን ትልቅ የሆነ አዲስ ምዕራፍ ይጀምራል! ከነሐሴ 2 ጀምሮ በአራዳ FM 95.1 በአዲስ አቀራረብ፣ በአዲስ ጉልበት እና በተሻሻለ ይዘት ዛሬ ወደ አየር ይመለሳል። "አመለካከት ሲቀየር ሕይወት ይጣፍጣል!" የቅዳሜ ምሽቶቻችሁ... ከእንግዲህ የተለየ ጣዕም ይኖራቸዋል። ዛሬ ምሽት ነሐሴ 2 በ12:00-2:00

  • 5 авг.3 1972736

    🔶የጠላ፣ጠጅና አረቄ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጨመረ በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡ በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡ ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ። ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ። በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው አጥናፉ የጥናቱን ውጤት ጠቅሰው ነግረውናል፡፡ በሌላ በኩል መንግስት የሚያገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉንም በጥናቱ አረጋግጠናል ይላሉ። የፍኖት አሶሼት መስራች አባል እና የፍኖት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶ/ር ፅኑኤል ግርማ በበኩላቸው እንደ ትንባሆ እና ሲጋራ ምርቶች በህገወጥ መንገድ አሁንም እየገቡ መሆኑን ነግረውናል። በፍኖት አሶሼት የፋይናንሲንግ ም/ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ደዬ በፋብሪካዎች የማይመረቱ፣ የአልኮል መጠናቸውም በማይታወቁ እንደ ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄ ያሉ መጠጦች በሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያመጡ ነው ብለዋል ። በሌላ በኩል በህገወጥ የሚገቡ ምርቶችን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል። ©️ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ======== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1

  • 5 авг.2 910818

    🔶"በመሃል" ቅዳሜ ይመረቃል በእመቤት አብዲሳ የተፃፈው  "በመሃል" የተሰኘው  የፈጠራ ሥራ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ኧርባን ሴንተር(የከተማ ማዕከል) ይመረቃል። በምረቃ መርሀ -ግብሩ ላይ የደራሲዋ እንግዶች፣ ወዳጆች የሚታደሙ ሲሆን የመፅሐፍ ዳሰሳን ጨምሮ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችም እንደሚኖሩ ይጠበቃል። የመፅሐፉ ደራሲ እመቤት አብዲሳ ጅግሳ፣ ከተማሪነት ዕድሜዋ ጀምሮ ለቃላትና ለሃሳብ ፍቅር በማሳደሯ ገና በልጅነቷ ወደ ጽሑፍ ዓለም የገባች ጋዜጠኛ ነች። የኮሙኒኬሽን ባለሙያ እና አሁን ደግሞ ደራሲ የሆነችው እመቤት በጋዜጠኝነት ሙያዋ በታወቁ ጋዜጦች ላይ በርካታ ማኅበራዊና ባህላዊ አጀንዳዎችን ያነሱ ጽሑፎችን ስታቀርብ ቆይታለች። የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሳለችም  የተለያየ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎች፣ ቃለ- መጠይቆችና ፕሮግራሞችን በመሥራት ሰፊ ልምድ አካብታለች። በተጨማሪም በኮሙኒኬሽን ባለሙያነት የተለያዩ ማህበረሰባዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በመሥራት ላይ ትገኛለች። እመቤት ባለፉት ዓመታት ያከማቸቻቸውን የሕይወት ምልከታዎች፣ ስሜቶችና ልምዶች በማጣመር «በመሃል» የተሰኘውን የፈጠራ ሥራዋን ለአንባቢዎች አበርክታለች። በ195 ገጾች የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ፣ በስፋት የተቃኙ 14 አጫጭር ታሪኮችን እና 43 ግጥሞችን በውስጡ  ይዟል። 450 ብርም እንደሚሸጥ ከደራሲዋ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። በቅርቡ በ «ንባብ ለሕይወት» ኤግዚቢሽን ላይ ከአንባቢያን ጋር የተዋወቀው «በመሐል» መጽሀፍ የደራሲዋ የፅሑፍ ክህሎት የታየበት ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ነው ሲሉ ያነበቡት ሀሣብ ሰንዝረዋል። ©️ተወዳጅ ሚዲያ ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 5 авг.2 7801139

    🔶ቅዳሜ ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም 192 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተመልካቾች ባሉት አማዞን ፕራይም አማካኝነት የሚተላለፈው እና የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ፣ የባህልና የቅርስ ሀብቶች እንዲሁም የከተማችንን አዲስ ገጽታን የሚያስቃኘው “Why Are You Not Here?” የተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ሲሪየስ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በይፋ ለዕይታ ይበቃል። ይህ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተው ሲሪየስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቶ በሃገሪቷ ፍቅር፣ በባህሏ፣ በቅርሶቿና በህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት ስለተማረከ አፍሪካዊ-አሜሪካዊ ገጣሚ የሚተርክ ልዩ ሥራ ነው። በምርቃቱ ላይ በመገኘትዎ: • ሁነቱን በነፃ የመታደም እድል ያገኛሉ። • የዓድዋ ድል መታሰቢያን ይጎበኛሉ። • ከአለም አቀፍ እንግዶች ጋር የመገናኘትና የመተዋወቅ አጋጣሚ ይኖርዎታል። ቦታ: ዓድዋ ድል መታሰቢያ ቀን: ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት: ከቀኑ 9:00 ሰዓት መግቢያ: በነፃ ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ: EthiopianRSVP.com ቀድመው ይመዝገቡ፣ ፖስቱንም ለወዳጅዎ ያጋሩ ያድርጉ! http://www.ethiopiarsvp.com/ ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 2 авг.3 0101518

    🔶“የቃል ሊቀ መኳስ” አዲስ መጽሐፍ በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፍ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጌራወርቅ ጥላዬ “የቃል ሊቀ መኳስ” በሚል ዐዲስ መጽሐፍ መጥቷል። ኤቨንት አዲስ ቀድማ እንደሰማሁ ከሆነ መጽሐፉ አንድ ሺህ ኮፒ ብዛት፣ በ128 ገጽ ታትሞ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ በዚህ ሳምንት ከሕትመት ቤት የወጣ ሲሆን ለአንበባቢ ይፋ የሚሆንበት ቀን ግን ገና እንዳልተወሰነ ነው። ጌራወርቅ ከዚህ ቀደም በነበረው በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፍ በ2016ዓ.ም በተካሄደው የክብር አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ” በሚል ዘርፍ አሸናፊ ነበር። ከመጽሐፍ ባለፈ የሙዚቃ ግጥም ደራሲ ሲሆን የሃሌሉያ ተ/ጻዲቅ “የልቤ ቁምነገር” የሚለው ተወዳጅ ሥራዋ የጌራ ድርሰት ነው። ይህም ሙዚቃ በአፍሪማ አዋርድ እጩ የነበረና በዩጋንዳ በተካሄደው አይኮኒክ አዋርድ ደግሞ “የዓመቱ ምርጥ ዘፈን” በሚል ተሸላሚ ነበር። ከዓመታት በፊት “ሙሉ አካል ትዝታ” በሚል ልቦለድ እንደሚመጣ ተናግሮ እንደነበር አይዘነጋም። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 30 июл.6 3851240

    🔶 “ንባብ ለሕይወት” ዐውደ ርዕይ ተከፈተ “ንባብ ለሕይወት”የመጽሐፍት ዐውደ ርዕይ በኤግዚቪሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል። ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ ደራሲያንና አንባቢያንን እያገናኘ ያለው “ንባብለሕይወት” የመጽሐፍት ዐውደ ርዕይ ከዛሬ ሐምሌ 24 ቀን ጀምሮ እስከ እሑድ ሐምሌ 27 ቀን ድረስ ይቆያል ተብሏል። የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ እና ሌሎች ተቋማትም የንባብ ለህይወት አካል ናቸው። በዐውደ ርዕዩ ላይ የልጆች መጽሐፍት፣የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የቢዝነስ (ኢኮኖሚ)፣ ልብወለድ፣ ግጥም፣ የጠፉና አዳዲስ መጽሐፍቶች ጨምሮ በየዘውጉ ይገኛሉ። ደራሲያንን ማስፈረምና የጋራ ፎቶዎችን መነሳት፣ ከማተሚያ የወጡ አዳዲስ መፅሐፍቶችን በአንባቢያን ማስመረቅ የዐውደ ርዕዩ አካል ናቸው። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 29 июл.3 9951419

    🔶የዓለም ደራሲያን ድርጅት በኢትዮጵያ የዓለም ደራሲያን ድርጅት በኢትዮጵያ ዛሬ ስብሰባውን እንደሚያደርግ ተገለፀ። ኢትዮጵያዊያን ደራሲያን ተሳታፊ የሚሆኑበትና አለም አቀፍ እንደሆነ የተነገረለት ጉባኤ ዛሬ ሐምሌ 22 2018 ከ 10 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ሆቴል እንደሚደረግ ታውቋል። በሥነ-ፅሑፍ ሙያ ላይ የተሰማሩ፣ በአርትዖት የተለየ አሻራ ያኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሚሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትና በአፍሪካ ሥነ ፅሑፍ ላይ ያጠኑት ዶክተር አቢይ ዳንኤል ወረቀት ያቀርባሉ። እንዲሁም ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ከፅሑፍ አቅራቢዎቹ መካከል ናቸው። የአለም የደራሲያን ማህበር ፕሬዘዳንት ማርጋሬት ኤ አይ ለዚሁ ስብሰባ ሲሉ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን የጉባኤው ቅድመ ዝግጅትም እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል። Africa in shaping a common future በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ከአፍሪካ ሥነ ፅሑፍ ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደሚቀርቡም ታውቋል። ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሲደረግ የኢትዮጵያ ደራሲያንን በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ግንኙነት በማሳደግ የራሱ ሚና እንደሚኖረው ይታወቃል። ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽንም በመፅሐፍ ዝግጅቴ ሥራ ላይ የተሠማራ በመሆኑ መሥራቹ እዝራ እጅጉን ጨምሮ የዝግጅት ክፍሉ አባላት በኢሊሊው ጉባኤ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ©️ተወዳጅ ሚዲያ ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 29 июл.3 131612

    🔶በቆሎና ንባብ በክረምት በልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ የተዘጋጀው "በቆሎና ንባብ በክረምት" መሰናዶ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 25 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጎተራ ማሳለጫ ይካሄዳል።በዕለቱም የተለያዩ እንግዶች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 28 июл.3 166158

    🔶የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ አዲስ መጽሐፍ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ "አደይ እና ጥቀርሻ" የተሰኘ የግጥም መፅሐፉን በቅርቡ ለንባብ ያበቃል። ይህ መጽሐፍ የበድሉ ዋቅጅራ ስድስተኛ የሥነግጥም መጸሐፉ ነው። አስቀድሞ የፍካት ናፋቂዎች፣እውነት ማለት የእኔ ልጅ፣የተስፋ ክትባት፣የወይራ ስር ፀሎት፣የራስ ምስል የተሰኙ አምስት የግጥም መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

  • 28 июл.2 353611

    🔶 "የፒያሣ ድምፆች" ዐውደርዕይ መንገዶቹ  ቢቀየሩም ድምጻቸው አሁንም ይኖራሉ በሚል ሀሳብ የተዘጋጀው "የፒያሣ ድምፆች" የተሰኘ የዲጂታል አርት ዐውደርዕይ ነገ ይከፈታል። በዳዊት ክፍሌ የተዘጋጀው ይህ አውደርዕይ ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 18 2018 ዓ.ም በፈንድቃ የባሕል ማዕከል በዕይታ ይቆያል ተብሏል። ይህ ዲጂታል የሥነጥበብ ዐውደርዕይ ድሮዋን ፒያሣ ያስታውሳል ተብሏል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1