tgindex
Addis Standard Amharic

Addis Standard Amharic

Статистика

አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው። ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3 ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
31
Всего постов
1 015
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
20 035
+82 за 3 дн.
Сутки
+15
+0,07%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 934
40 постов
Вовлечённость
14,6%
к подписчикам
Постов в день
4,4
всего 1 015
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
по 4 постам
1/24сутки в ленте
2 644
1/48двое суток
3 015
1/72трое суток
3 251

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 15 авг.1 6053

    видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 15 авг.1 9151

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.2 7327

    ዜና: የመንግሥት «ሥልጣንን የማዕከላዊ ማድረግ» ጥረት በ2025 የ #ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ተቋማትና ሰብአዊ መብቶች አዳክሟል — የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔር ውጥረቶች እና በትጥቅ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ መካከል ሥልጣንን የማዕከላዊ ለማድረግ ያደረገው ጥረት በ2025 «ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን ይበልጥ ያዳከመ እና የሰብአዊ መብቶች መከበርን የሸረሸረ» እንደነበር የአውሮፓ ሕብረት የ2025 ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የዲሞክራሲ ሪፖርት ይፋ አደረገ። ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እና የዲሞክራሲ ሁኔታ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ለሁለት ዓመታት በተካሄደው አውዳሚ ጦርነት ያልተፈቱ መዘዞች፣ የትጥቅ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ተጽዕኖ ስር መቆየቱን ጠቁሟል። በአፋር እና በአማራ ክልሎች ሰፊ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችም የፀጥታ ችግር መቀጠሉን ገልጿል። በተጠቀሰው ዓመት ትጥቅ በመፍታት፣ በሽግግር ፍትሕ እና በተጠያቂነት እርምጃዎች ላይ የተፈጠሩ መዘገየቶች እንደነበሩና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ሰፊ ጥረቶችን ማስተጎጎላቸው በሪፖርቱ ተጠቅሷል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13768

  • 14 авг.2 9323

    ዜና: #ሲፒጄ አምስት #ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ በሽብርተኝነት ተግባር ላይ መሳተፋቸውን እንዲያምኑ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገለጸ   የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሲፒጄ ለሶስት ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙት አምስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ በሽብርተኝነት ተግባር ላይ መሳተፋቸውን እንዲያምኑ እና ይቅርታ እንዲጠይቁ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገለፀ፤ ድርጅቱ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋዜጠኞቹን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል። በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ማለትም ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ በ2015 ዓ.ም. በአማራ ክልል ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በሰሩት ዘገባ የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል። እንደ ሲፒጄ መግለጫ፣ የጋዜጠኞቹ ጠበቃ ስለሞን ገዛኸኝ አምስቱም ጋዜጠኞች የይቅርታ ደብዳቤውን ለመፈረም ወይም ለመጻፍ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። በተጨማሪም የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋዜጠኞቹን ከሌሎች እስረኞች በመለየት በመንግሥት የቀረበውን የይቅርታ ረቂቅ ሰነድ ተከትለው የራሳቸውን ደብዳቤ እንዲያዘጋጁ ለማስገደድ ማስፈራሪያ እነዳደረሱባቸው ጠበቃው ገልጸዋል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13765

  • 14 авг.2 8544

    ዜና: የ #ሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ኃይል በ #ኢትዮጵያ ደንበር አቅራቢያ የምትገኘውን ቁልፍ ከተማ መቆጣጠሩን አስታወቀ የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) እና አጋር ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ ጋር በሚዋስነው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን እና ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላትን አል ኩርሙክ ከተማን መቆጣጠራቸውን አልጃዚራ እና ዘ ናሽናል ዘገቡ። የወታደራዊ እና የመንግሥት ምንጮች ሐሙስ ዕለት ለአልጃዚራ እንደገለጹት፣ የሱዳን መከላከያ ሠራዊት (SAF) አባላት ለቀው በመውጣት በኩርሙክ ክወጭ መክተማቸውን ተከትሎ የአር ኤስ ኤፍ ታጣቂዎች እና የሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ-ሰሜን (SPLM-N) አባላት ወደ ከተማዋ ገብተዋል። ታጣቂ ቡድኑ በበኩሉ በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን እና በርካታ መሳሪያዎችንና ጥይቶችን መማረኩን ገልጿል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13761

  • 14 авг.2 9314

    #ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ ለሁለገብ ጫናዎችና ለሉዓላዊነት ሥጋት ተጋላጭ መሆኗን ሚኒስትሩ ገለፁ ​ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ በገንዘብ ሊገመቱ ለማይችሉ በርካታ ጫናዎች፣ ለከፍተኛ ወጪና ለሉዓላዊነት ሥጋት ተጋላጭ መሆኗን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለፁ። ሚኒስትሩ ከበሪሳ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀገሪቱ የባሕር በር በማጣቷ በግንባር ቀደምትነት ተጎጂ ከሚሆኑ ዘርፎች መካከል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል። ሚኒስተሩ የባሕር በር የሌላት ሀገር ምስጢር ሊኖራት ስለማይችል ለጠላት ተጋላጭ በማድረግ በሉዓላዊነቷ ላይ ጫና እንደሚፈጥር አስረድተዋል። የባሕር በር ያለአግባብ የሚወጣን ወጪ ለመቀነስ፣ ለአገልግሎት የሚከፈለውን ዋጋ ተመጣጣኝ ለማድረግና የምርት ስርጭትን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ጠቁመው ይህም ሀገር በራሷ የምትቆጣጠረው የባሕር በር ወይም ወደብ ሲኖራት ብቻ ሁኔታው የሚስተካከል መሆኑን አስረድተዋል። ይህ በለመሆኑም ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ ከሚወጣው ከፍተኛ ወጪ ባሻገር ለተለያዩ ጫናዎች እየተጋለጠች እንደሚገኝም አስታውቀዋል። አንድ ምርት ከውጭ ሀገር ተገዝቶ በፍጥነት መቅረብ አለበት ሲባል የባሕር በሩን የሚቆጣጠረው፣ ጫኝና አውራጅ ሠራተኞችን የሚያሰማራው፣ እንዲሁም መርከብ የት መቆም እንዳለባትና የትኛው ምርት መጀመሪያ መምጣት እንዳለበት የሚወስነው ኢትዮጵያ እንዳልሆነች ሚኒስትሩ አብራርተዋል። https://www.facebook.com/share/p/1CX6qxYSiq/

  • 13 авг.3 2033

    ዜና: በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶስት ሰዎች ከህግ አግባብ ወጭ መገደላቸው መዘገቡን ተከትሎ የክልሉ የፀጥታ ኃላፊ «በታጣቂዎች» ላይ እርምጃ መወሰዱን ገለጹ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአበሽጌ ወረዳ «የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ባለቀበሉ ታጣቂዎች» ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ገለጹ። ይህ መግለጫ የተሰጠው በአካባቢው ሶስት ሰዎች ከህግ አግባብ ወጭ መገደላቸውን የሚገልፁ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ከወጡ ከቀናት በኋላ ነው። የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማይ ስለተባሉት ግለሰቦች ግድያ የተሰራጩ ዘገባዎችን ጠቅሰው ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም። ሆኖም የኃላፊው መግለጫ የወጣው፣ ሶስቱ ግለሰቦች በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አገና አካባቢ «የፋኖ አባላት ናቸው» በሚል ከሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በኃይል እንዲወርዱ ተደርገው ከተወሰዱ በኋላ ተገድለዋል የሚሉ ዘገባዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13753

  • 13 авг.3 20411

    ትንታኔ: የ #ኢትዮጵያ የፀጥታ ችግሮች እየተባባሱ ባሉበት ወቅት በ #ኦሮሚያ ክልል የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ዳግም መጀመሩ ተገለጸ በ #አዲስ_አበባ ዙሪያ በሚገኙ የሸገር ከተማ አካባቢዎችን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ዳግም አየተካሄደ መሆንን ነዋሪዎች ገለጹ። ቤተሰቦች እንደተናገሩት ወጣቶች ያለ ፍላጎታቸው በኃይል ተወስደዋል፤ በአንዳንዶች ደግሞ ወጣቶቹን ለማስፈታት ገንዘብ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል። አዲስ ስታንዳርድ በ #ምስራቅ_ሐረርጌ እና በ #ምስራቅ_ባሌ ዞኖች ከሚገኙ ነዋሪዎች መረጃዎችን አሰባስቧል፤ ይህ የምልመላ ድርጊት የተከሰተው በሀገሪቱ የፀጥታ ውጥረቶች በተከሰቱበት ወቅት ነው። ከእነዚህም መካከል በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል እንደገና ያገረሸው ውጥረት፣ በ #አማራ ክልል በፌደራል ኃይሎች እና በ #ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ያለው ግጭት፣ እንዲሁም በ #ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል የሚታየው አለመረጋጋት ይገኙበታል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13745

  • 13 авг.3 1492

    በ #ናይሮቢ የሚገኘው የ #ደቡብ_ሱዳን ኤምባሲ ባልተከፈለ የቢሮ ኪራይ ዕዳ ምክንያት ተዘጋ በኬንያ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ባልተከፈለ የቤት ኪራይ ዕዳ ምክንያት መዘጋቱን የኤምባሲው ሠራተኞች እና ወደ ሥፍራው አገልግሎት ለማግኘት የሄዱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ገለጹ። በናይሮቢ ኪሊማኒ አቅራቢያ የሚገኘው ኤምባሲው የተዘጋው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. መሆኑን ከራዲዮ ታማዙጅ (Radio Tamazuj) ጋር ቆይታ ያደረጉ አንድ የኤምባሲው ሠራተኛ ተናግረዋል። ሠራተኛው መንግሥት የነሐሴ ወርን ጨምሮ የቪላውን የአራት ወራት ኪራይ መክፈል እንዳልቻለ ገልፀዋል። «ኤምባሲው በአሁኑ ወቅት ተዘግቷል። መንግሥት ጣልቃ ገብቶ መፍትሔ እስኪሰጥ ድረስ ኤምባሲው ተዘግቶ ይቆያል» ሲሉም አክለው ተናግረዋል። እራሱን ስቲፈን ብሎ ያስተዋወቀ አንድ የደቡብ ሱዳን ዜጋ የጉዞ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ወደ ኤምባሲው ሄዶ የነበረ ቢሆንም፣ በጥበቃዎች እንዲመለስ መደረጉን ገልጿል። https://www.facebook.com/share/p/1BpBqfmF3A/

  • 13 авг.3 0253

    በ #ሱዳኑ ታጠቂ ኃይል (RSF) የተሾሙት የኮርዶፋን ገዥ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውንና ከቡድኑ መውጣታቸውን አስታወቁ በሱዳን ፈጣን ድጋፍ ኃይል (RSF) የኮርዶፋን ክልል ገዥ ሆነው ተሾመው የነበሩት ሐማድ ሞሐመድ ሐማድ ኻሊፋ ከቡድኑ መውጣታቸውን እና ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ረቡዕ ዕለት አስታወቁ። ኻሊፋ ከኃላፊነታቸው መውጣታቸውን ይፋ ያደረጉት አል አረቢያ ለተሰኘው የ #ሳዑዲ_ዓረብያ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት የቀጥታ ቃለ-መጠይቅ ወቅት ነው። አር ኤስ ኤፍ (RSF) ባለፈው ዓመት ኻሊፋን የኮርዶፋን ገዥ እንዲሁም በታሲስ ጥምረት በተቋቋመው መንግሥት ስር የፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት አባል አድርጎ ሾሟቸው ነበር። ኻሊፋ በቃለ-መጠይቃቸው እንደተናገሩት፣ የሱዳን ሕዝብ «ሕግ-ወጥ ሚሊሻዎች» ካሏቸው አካላት ጋር ከመታገል ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም ያሉ ሲሆን፣ ታጣቂው ቡድን ጎሳን፣ ሰላማዊ ሰዎችን እና ብሔርን ያማከለ ግጭት እየቀሰቀሰ ነው ሲሉ ከሰዋል። አክለውም ሕጋዊ የሆኑ የመንግሥት ተቋማት ወደ ኮርዶፋን እና ዳርፉር ክልሎች እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። https://www.facebook.com/share/p/1BccuPG7tZ/

  • 13 авг.3 2274

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.3 3604

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.3 1094

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.2 7954

    የ #ኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና መከላከያ ሠራዊት በኤ.አይ በመታገዝ የሠራዊቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተደራጀ ዘመናዊ መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ። ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በሎጀስቲክስ፣ በስልጠና፣ በሳይበር ደህንነት፣ በመከላከያ ሰራዊት ጤና አጠባበቅ፣ እንዲሁም በአየር ኃይል እና በኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር ዘርፎች በኤ.አይ በመታገዝ የሠራዊቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ አበይት ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው፣ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በስምምነቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሀገር ሉዓላዊነትን እና ብሄራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ዘመናዊ ሰራዊት ለማደራጀት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። https://www.facebook.com/share/p/1EEau8ANfS/

  • 12 авг.3 2678

    #ደቡብ_አፍሪካ ሰነድ አልባ #ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመመለስ ያወጣችውን ወጪ #ኢትዮጵያ እንድትጋራ ጠየቀች ደቡብ አፍሪካ በተያዘው ዓመት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ካወጣችው ከ18 ሚሊዮን ዶላር (292 ሚሊዮን ራንድ) ውስጥ የተወሰነውን ወጪ እንዲሸፍኑ ለ #ኢትዮጵያ፣ ለ #ናይጄሪያ እና ለ #ሜላዊ ጥያቄ አቀረበች። የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥያቄው መቅረቡን ይፋ ያደረገው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፓርላማው የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ ወቅት ነው። የቋሚ ኮሚቴው ዋና ዳይሬክተር ቶሚ ማኮዴ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ ለዚህ ተግባር ቀደም ሲል የመደበው በጀት 60 ሚሊዮን ራንድ ብቻ ቢሆንም፣ እስካሁን 292 ሚሊዮን ራንድ ስደተኞችን ለመመለስ ወጪ አድርጓል። ማኮዴ ስደተኞችን የመመለስ መርሃ-ግብር «በጀት ያልተያዘለት ኃላፊነት» መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለዚህ ያህል ሰፊ እንቅስቃሴ በጀት እንዳልመደቡ ተናግረዋል። አክለውም የትራንስፖርት ክፍያው ወጪው ከፍተኛ እንዲሆን ዋና ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል። https://www.facebook.com/share/p/198ddEu7km/

  • 12 авг.3 2267

    ዜና: የ #ሱዳን ፈጣን ድጋፍ ኃይል በድንበር ከተማ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ጥቃቱ የተሰነዘረው 'ከ #ኢትዮጵያ ነው' ሲል የሱዳን ጦር ከሰሰ የሱዳን ፈጣን ደጋፍ ኃይል (RSF) ማክሰኞ ዕለት በብሉ ናይል ክልል በሚገኘው የጌሳን የድንበር ከተማ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ቡድኑ እና የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለፁ። የሱዳን ሰራዊት ምንጭ በበኩሉ ጥቃቱ የተሰነዘረው «ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ» ነው ሲል ለኤኤፍፒ (AFP) ከሷል። የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንደገለጸው፣ ይህ ግጭት አዲስ መፈናቀል ያስከተለ ሲሆን፣ በዚህም 2,500 ሰዎች ከጌሳን ተፈናቅለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲው የስደተኞች ሁኔታን የሚከታተለው ቡድኑ የደኅንነት ሁኔታው በማሽቆልቆሉ ምክንያት 500 አባወራዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በጌሳን አካባቢ ባሉ ሌሎች ቦታዎች የተጠለሉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አይ ኦ ኤም (IOM) ገልጿል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13738

  • 12 авг.3 3433

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.3 4803

    በ #ግብጽ የጭነት መርከብ ላይ ሁቲዎች በባብ ኤል-መንደብ በተፈጸሙት አዲስ ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አስር ቆሰሉ በ #ኢራን የሚደገፉት የመን የሁቲ ኃይሎች ባብ ኤል-መንደብን በማቋረጥ ላይ በነበረችውና «ቲሃማህ» በተሰኘችው የግብጽ የጭነት መርከብ ላይ በባሊስቲክ ሚሳኤሎች ባካሄዱት ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አስር መቆሰላቸውን የየመን መንግሥት አስታወቀ። ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በታንዛኒያን የተመዘገች መርከብ በሶስት ሚሳኤሎች ተመታለች። በጥቃቱ ሶስት ፓኪስታናውያን እና አንድ ኢንዶኔዥያዊ በአጠቃላይ አራት ሰራተኛች መግደላቸውን ተገልጿል። ጥቃቱ ከፍተኛ የእሳት አደጋ ማስከተሉም ተዘግቧል። በታጣቂዎቹ የተወነጨፈው ሁለተኛው ሚሳኤል የነፍስ አድን ሥራ እተከናወነ በነበረበት ወቅት መሆኑና፣ በጥቃቱም የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገልጿል። https://www.facebook.com/share/p/1Bj7dZnJZ3/

  • 12 авг.3 4173

    ዜና: የታጠቁ ቡድኖች #ግልገል በለስ ለመግባት ያደረጉት ሙከራ «መምከኑን» የዞኑ አስተዳደር ቢገልፅም ነዋሪዎች ታጣቂዎቹ ገብተው ከ10 በላይ ንፁሃንን መግደላቸውን ተናገሩ በ #ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የሚገኙ የጸጥታ ኃይሎች ማክሰኞ ማለዳ ላይ ታጣቂ ቡድኖች ወደ ግልገል በለስ ከተማ ለመግባት ያደረጉትን ሙከራ ማምከናቸውን የመተከል ዞን አስተዳደር አስታወቀ። የዞኑ አስተዳደር ማክሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በጫካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እና ራሳቸውን «የጉሙዝ ኃይል» ብለው የሚጠሩ፣ እንዲሁም «ከ #ፋኖ ጋር» አብረው ይሰራሉ የተባሉ ቡድኖች «በዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ» ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ከተማዋ ለመግባት ሙከራ ማድረጋቸውን ገልጻል። አስተዳደሩ ጥቃቱ መምከኑን ቢገልፅም ታጣቂዎቹ ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከ10 በላይ ሰዎችን ደመግደላቸውን ነዋሪዎችን ተናግረዋል። ጥቃቱ በመነሐሪያ እና አንድ ቤተክርስቲያን አካባቢ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የክልሉ ምክር ቤት አባል ተናግረዋል። https://addisstandard.com/Amharic/?p=13724

Addis Standard Amharic — tgindex