ሀምዛ መስጂድ እና መድረሳ
Статистикаበአላህ ፍቃድ የሀምዛ መስጂድ ኹጥባዎች ደርሶች ሙሀደራዎች እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ቻናል ነው። العلم قبل القول والعمل <<እውቀት ከንግግርም ከተግባርም ይቀድማል>>። ኢማሙ አል ቡኻሪ
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 117
- 1/48двое суток
- 134
- 1/72трое суток
- 144
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
የብዕር ድልድይ (የልጅ እያሱ ታሪክ በትርጉም ጥበብ ሲቃኝ) ☆☆☆☆☆ ታሪክና ስነ-ጽሑፍ ሲገናኙ የቀደሙ ዘመናት ሁነቶች በወረቀት ላይ ሕይወት ይዘራሉ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የእውቀትና የስሜት ድልድይም ይሆናሉ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እጅግ አከራካሪ ከሆኑት ንጉሣውያን ገጸ-ባህሪያት አንዱ የልጅ እያሱ (ንጉሠ ነገሥት እያሱ) ታሪክ ነው። ይህንን ታሪክ ከደረቅ ሰነድነት አውጥቶ በስነ-ጽሑፍ ውበትና በታሪካዊ እውነታዎች መካከል አጣጥሞ ለተደራሲ ማቅረብ ደግሞ የዳበረ የብዕር ክህሎትን ይጠይቃል። ግብጻዊው ታዋቂ ደራሲ ነጂብ አል-ኪላኒ «ጥቁሩ ጥላ» (الظل الأسود) በተሰኘው ታዋቂ የስነ-ጽሑፍ ስራው የልጅ እያሱን ታሪክ፣ የፍትሕና የእኩልነት ራእይ፣ እንዲሁም በወቅቱ የነበረውን የፖለቲካና የማኀበራዊ መስተጋብር በልቦለድ መልክ ስሎታል። ይህንን ድንቅ ስራ ተርጎሚው መሐመድ ጀማል ሙኽታር ባለው የካበተ የስነ-ጽሑፍ ልምድና የትርጉም ጥበብ ብቃት «የንጉሠ ነገሥት እያሱ የፍትህ የእኩልነት እና የመቻቻል ራእይ እና የኢትዮጵያ ዐጼዎች ሙስሊሞችን የመጨቆን እና የማግለል ቋሚ ፖሊሲ፡ ታሪክ በትረካ» በሚል ርእስ ወደ አማርኛ መልሶታል። ተርጎሚው መሐመድ ጀማል ባለው የካበተ የስነ-ጽሑፍ ልምድ፣ ትርጉሙ ጥሬ ቃላትን ከመቀየር አልፎ የደራሲውን ዋና መንፈስና የስነ-ጽሑፍ ውበት ላለመቀነስ ጥረት አድርጓል:: ነጂብ አል-ኪላኒ (1931- 1995 እ.አ.አ) የግብጽ ዘመናዊ የስነ-ጽሑፍ ጉዞ ካፈራቸው ድንቅ ደራሲያን መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ፣ የኢስላማዊ ስነ-ጽሑፍና ፈር ቀዳጅ ደራሲ ነው። በብዕር ጉዞው ሁሉ ኢስላማዊ እሴቶችንና መመሪያዎችን ከመንፈሳዊ ውበት ጋር በማዋሃድ፣ የአንባቢን ልብ በሚማርክ የትረካ ጥበብ ለማቅረብ ታላቅ ጥረት አድርጓል። አል-ኪላኒ በቃላት ስዕሉ ለነባራዊው እውነታ ታማኝ የመሆንና ወደ ታሪካዊ እውነታዎች የመጠጋት አብይ ትኩረት ነበረው። ይህ የአል-ኪላኒ ስራ ማዕከላዊ ጭብጥና ህያው ገጸ-ባህሪያት ቀጥታ ከተጨባጩ የታሪክ ማህደር የተቀዱ በመሆናቸው፣ የታሪክ እውነትና የፈጠራ ጥበብ በተዋበ መልኩ የተጋመዱበት ድንቅ የብዕር ውጤት ሆኖ ይገኛል። የመጽሀፉ ተርጎሚ መሐመድ ጀማል ሙኽታር በበኩሉ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ከውጭ ደራሲያን እይታ አንጻር፣ በተለይም በኢስላማዊ ስነ-ጽሑፍ መነጽር እንዴት እንደተቃኘ ለአማርኛ አንባቢ በግልጽ እንዲደርስ አድርጓል። ደረቅ የታሪክ መረጃዎችን በስነ-ጽሁፋዊ ውበት አሽቶ በማቅረቡ፣ አንባቢው የልጅ እያሱን ፍላጎት፣ የገጠማቸውን ፈተና እና የሕሊና ሙግት በቅርበት እንዲረዳ ያግዛል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ልጅ እያሱ ከአጼ ምኒልክ በኋላ ወደ ሥልጣን መጥተው ያሳዩት ልዩ የፖለቲካና ማኀበራዊ አቋም በጎላ መንገድ ተስሏል:: ልጅ እያሱ በወቅቱ የነበረውን የሙስሊሞች መገለልና ጫና ለማስቀረት፣ የሃይማኖት እኩልነትን ለማስፈን፣ መስጂዶች እንዲገነቡ ለመፍቀድና የዜጎችን እኩልነት ለማረጋገጥ ያደረጉት ጥረት በስፋት ይዳሰሳል። አል-ኪላኒ እውነተኛውን የታሪክ መረጃ ችላ ሳይል፣ በፈጠራ ጥበቡ የልጅ እያሱን ውስጣዊ ስሜት፣ እምነትና የፍትሕ ተጋድሎ ቁልጭ አድርጎ አሳይቷል። የልጅ እያሱ የፍትሕና የእኩልነት እርምጃዎች በወቅቱ በነበሩት የፖለቲካና የሃይማኖት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም። በስራው ላይ እንደተብራራው፣ እነዚህን ተራማጅ አስተሳሰቦች በመቃወም በነበሩ ሴራዎች ምክንያት ልጅ እያሱ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱና እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ድረስ እንዲታሰሩ ሆኗል። በአጠቃላይ ይህ ስራ የልጅ እያሱን ታሪካዊ ቦታ ለመረዳት ብቻ ሳይሆን፣ በሁለት ባህሎችና ቋንቋዎች መካከል የተሰራ ድንቅ የስነ-ጽሑፍ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል። ✍ ነስሩ ኸድር እንደፃፈው
видео или голосовое, без подписи
🔴 የጁምዓ ኹጥባ 🎙 خطبة الجمعة أحوال يوم القيامة (الشفاعة) ✨ የቂያማ ቀን ክስተቶች 2 ሸፋዐ (ምልጃ) ⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️ 🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ 🗓 ሶፈር 25/1448 አ/ሂ http://t.me/kalityhamzamesjid
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የቡሉጒል መራም ኪታብ ባሳለፍነው ሳምንት ጁምዓ በአሏህ ፍቃድ ለመጨረስ ችለናል አልሐምዱሊላህ አሏህ ባወቁት ከሚሠሩ ያድርገን ኡስታዛችንንም አሏህ ረጅም እድሜን ከመልካም ስራ እንዲወፍቃቸው እንማፀነዋለን አሚን! በመቀጠል በተጠበቀው ቀን እና ሰአት አዲስ ኪታብ የምንጀምር ይሆናል ። 📚مختصر صحيح البخاري (التجريد الصريح لأحاديث…
ሓጃዎቻችን እንዲሳኩ... ነቢያችን ላይ ሰለዋት ማብዛት ሓጃን (ጉዳይን) እንደሚያሳካ፣ ወንጀልን እንደሚያራግፍ ቲርሚዚይ በዘገቡት ሐዲሥ ተነግሯል። ጊዜው የግልም የጋራም (የዲንም የዱኒያም) ሓጃ የበዛባት ሆኗልና ለሱናውም ለጉዳዩም ስንል ነቢያችን ላይ ሰለዋት ማውረድ እናብዛ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ. ዛዱል-መዓድ https://telegram.me/ahmedadem
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የቡሉጒል መራም ኪታብ ባሳለፍነው ሳምንት ጁምዓ በአሏህ ፍቃድ ለመጨረስ ችለናል አልሐምዱሊላህ አሏህ ባወቁት ከሚሠሩ ያድርገን ኡስታዛችንንም አሏህ ረጅም እድሜን ከመልካም ስራ እንዲወፍቃቸው እንማፀነዋለን አሚን! በመቀጠል በተጠበቀው ቀን እና ሰአት አዲስ ኪታብ የምንጀምር ይሆናል ። 📚مختصر صحيح البخاري (التجريد الصريح لأحاديث الجامع الصحيح ) 📚ሙኽተሰር ሶሒሑ አል ቡኻሪ (ተጅሪድ) ⚠️ ኪታቡን የምትፈልጉ አንድ ላይ ስለሚገዛ በዚህ ስልክ ቁጥር ስማችሁን ላኩልን 0921298515
🔴 የጁምዓ ኹጥባ 🎙 خطبة الجمعة أحوال يوم القيامة (الميزان) ✨ የቂያማ ቀን ክስተቶች ሚዛን ⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️ 🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ 🗓 ሶፈር 11/1448 አ/ሂ http://t.me/kalityhamzamesjid
⏱ ጊዜዬን በአግባቡ እንዴት ልጠቀም? ------------------------------------------------- 🎙ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ (حفظه الله)
የቃላት ቁጥጥር እና የትርጉም ፖለቲካ! ቋንቋ የቃላት ስብስብ ብቻ አይደለም፤ የአንድ ማህበረሰብ የማሰብ አድማስ፣ ዓለምን የሚያይበት እይታው የሚገለጽበት የስነ-ልቦናው ውቅር ነው። አንድን ህዝብ በወታደር ወርሮ ከመግዛት ይልቅ፣ የሚያስብበትን ቋንቋና የሚጠቀምባቸውን ቃላት ትርጉም መቆጣጠር የረጅም ጊዜ የአእምሮ የበላይነትን ያጎናጽፋል። የ1911ዱ የላክኖው ኮንፈረንስ እና ተከታታይ የሚሽነሪ የቋንቋ ጥናቶች ያረጋገጡት አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ “የክርስትናን ዶክትሪን በምዕራባዊ የቃላት ቆዳ ከሸፈንነው ሙስሊሙ እንደ ባዕድ ነቀርሳ ይተፋዋል፤ በገዛ ቋንቋውና በለመደው የቃላት ቃና ከቀመመነው ግን እንደ ማእድ ይመገበዋል።” ይህ ንጹህ የቋንቋ ጥናት የሚመስለው፣ በውስጡ ግን ከባድ የርዕዮተ-ዓለም ዘረፋ የያዘው ስልት በምሁራዊ አጠራሩ "ስነ-ልሳናዊ ጠለፋ" (Linguistic Hijacking) ይባላል። ይህ ስልት መሬት ላይ ሲተገበር እጅግ አስገራሚ የሆነ የቃላት ስርቆት ይፈጽማል። ሚሽነሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ወይም ስነ-ጽሑፎቻቸውን ወደ አረብኛ ወይም ኦሮምኛ ሲተረጉሙ አዳዲስ ቃላትን አይፈጥሩም፤ ይልቁንም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ የክብር፣ የፍርሃትና የልቅና ስሜት ያላቸውን ነባር ኢስላማዊ ቃላት ይወስዳሉ። ለምሳሌ 'እግዚአብሔር' ለማለት 'አላህ' ወይም 'ረቢ'፣ 'ኢየሱስ' ለማለት 'ዒሳ'፣ 'ምዕራፍ' ለማለት 'ሱራ'፣ እንዲሁም 'ወንጌል' ለማለት 'ኢንጂል' የሚሉትን ቃላት ይጠቀማሉ። እዚህ ጋ የተፈጸመው የስነ-ልቦና ማጭበርበር ምንድነው? ቃሉ የሙስሊሙ ነው (ለምሳሌ 'አላህ')፣ በዚያ ቃል ውስጥ የተሞላው ትርጉም ግን የሥላሴ ዶክትሪን ነው። ሙስሊሙ አንባቢ ጽሁፉን ሲያነብ የራሱን ቃል ስላገኘ ንቃተ-ህሊናው የጥርጣሬ በሩን ዝግ ያደርጋል፤ በገዛ የቃላት ቋቱ ውስጥ የተሸሸገውን ባዕድ ጽንሰ-ሀሳብም ያለምንም ተቃውሞ ወደ አእምሮው ያስገባል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ዩጂን ኒዳ የተባለ የቋንቋ ምሁር ያመጣው "Dynamic Equivalence" (ተለዋዋጭ አቻ ትርጉም) የተሰኘው መርህ ይህንን ስልት ወደ ላቀ የሳይንስ ደረጃ አድርሶታል። በዚህ መርህ መሠረት፣ ዋናው ቁምነገር የጥንታዊውን ጽሑፍ ቃል በቃል መተርጎም ሳይሆን፣ 'አንባቢው ጽሑፉን ሲያነብ ልክ ኦሪጂናል ጸሐፊው በሱ ቋንቋ እንደጻፈው አድርጎ እንዲሰማው ማድረግ' ነው። ለዚህም ሲባል በሚሽነሪዎች የሚዘጋጁ የአረብኛ በራሪ ጽሑፎችና ትራክቶች የሚጀምሩት በምዕራባዊ ሰላምታ ሳይሆን፣ "አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ... የተወደዳችሁ ወገኖቼ" በሚል ጥልቅ ኢስላማዊ የቃላት ዜማ ነው። የቁርዓንን የአጻጻፍ ሪትምና ሰዋሰዋዊ ውበት ኮፒ በማድረግ፣ የክርስትናን መልእክት በኢስላማዊ የስነ-ጽሑፍ ሻንጣ ውስጥ አሽገው ያቀርቡታል። አንባቢው 'ይህ መጽሐፍ ከቫቲካን ወይም ከለንደን የመጣ ነው' ብሎ ማሰብ አቁሞ፣ የሰፈሩ ሰው የጻፈው እስኪመስለው ድረስ በቃላት ወጥመድ ይያዛል። ይህ የቋንቋ ጦርነት በአፍሪካ ቀንድና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የነበረው ሚና እጅግ ሰፊ ነው። ላሚን ሳኔህ የተባለው ታዋቂው የታሪክ ምሁር "Translating the Message" በተሰኘው መጽሐፉ ላይ እንዳብራራው፣ ሚሽነሪዎች የአካባቢውን ቋንቋዎች በላቲን ወይም በራሳቸው ፊደል መዝገበ-ቃላት ሲያዘጋጁላቸው ዋነኛ አላማቸው ንባብ ማስተማር ብቻ አልነበረም። ህዝቡ ወደ አረብኛ ቋንቋና ወደ ኢስላማዊ ስነ-ጽሑፍ ከመሳቡ በፊት፣ የቋንቋውን 'የሃይማኖት መዝገበ-ቃላት' (Theological Vocabulary) በክርስትና መነጽር ቀድመው ለመቆለፍ የተደረገ የጊዜ ሩጫ ነበር። ቃላትን የፈጠረ ወይም መዝገበ-ቃላትን ያጠናቀረ አካል፣ ያ ህዝብ በሚቀጥሉት መቶ ዓመታት ስለ 'ኃጢአት'፣ ስለ 'ጽድቅ' እና ስለ 'አምላክ' የሚያስብበትን የአእምሮ ድንበር ይወስናልና። የብዕርን ጦርነት በቋንቋ ሰዋሰው ውስጥ የመሸሸግ ይህ ጥበብ፣ ያለምንም የጦር ሜዳ የህዝብን የማሰብ አቅም በቅኝ ግዛት ስር የማዋረድ የረቀቀ ፖለቲካ ነው። በቀጣዩ ክፍል የምንዳስሰው አጀንዳ፡ ድብቁ መረብ - "የቤት ውስጥ አብያተ ክርስቲያናት" እና ማህበረሰብን ከጓዳ ጀምሮ የመሸርሸር ስልትን በቀጣይ ክፍል - 15 በአላህ ፍቃድ እንመለከተዋለን። የመረጃ ምንጮች፦ • Lamin Sanneh, "Translating the Message: The Missionary Impact on Culture". • Eugene A. Nida, "Toward a Science of Translating" (Dynamic Equivalence Principles). • Papers and Discussions of Lucknow Missionary Conference, 1911 (Literature & Language Section). የሕያ ኢብኑ ኑህ https://t.me/Yahyanuhe
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ከህመም ጀርባ ያለ ስብከት! የሰው ልጅ ስነ-ልቦናዊ የመከላከያ ግንብ እጅግ የሚዳከመውና ለውጫዊ ተጽዕኖ ክፍት የሚሆነው አካሉ በህመም ሲመታ ነው። ይህንን ጥልቅ ተፈጥሯዊ እውነታ በሚገባ ያጠኑት ሚሽነሪዎች፣ የህክምና ማዕከላትን እንደ ተራ የጤና ተቋም ሳይሆን፣ "መንፈሳዊ ማደንዘዣ (አንስቴዥያ)" መስጫ ቁልፍ መሣሪያ አድርገው ቀርጸዋቸዋል። በ1911ዱ የላክኖው ኮንፈረንስ ስልታዊ ሰነዶች ላይ "Medical Missions as Pre-Evangelism" (ህክምና የወንጌል መንገድ መጥረጊያ ነው) የሚል መርህ በግልጽ ተቀምጧል። አንድ በጠና የታመመ ወይም በወረርሽኝ የተያዘ ሰው በዚያ የጭንቀት ሰዓት የሚፈልገው የሃይማኖት ክርክርን ሳይሆን ማስታገሻን ነው፤ በዚህ ሞትና ህይወት በሚፋጠጡበት ቅጽበት በነጭ ጋውን ተጠቅልሎ የሚቀርብለት ዶክተር በታካሚው ንቃተ-ህሊና ውስጥ 'አዳኝ መልአክ' ሆኖ ይሳላል። ይህ ስልት መሬት ላይ እንዴት እንደተተገበረ የሚያሳይ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ምሳሌ እንመልከት፦ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በግብጽ፣ በፋርስ (ኢራን) እና በኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍሎች የተቋቋሙት "የዓይን ህክምና እና የለምጽ ማዕከላት" ናቸው። በወቅቱ በነበረው የንጽህና ጉድለት ምክንያት የዓይን ትራኮማና ለምጽ የተለመዱ ነበሩ። ሚሽነሪዎቹ እነዚህን ማዕከላት ሲከፍቱ አንድ ጥብቅ ህግ አወጡ፦ ማንኛውም ታካሚ ሀኪም ቤት እንደገባ መጀመሪያ ጠዋት በጋራ በሚደረገው የ30 ደቂቃ 'የጸሎትና የወንጌል ንባብ' ፕሮግራም ላይ መገኘት አለበት። የዓይኑን ጠብታ ለማግኘት የሚጠብቀው ታካሚ፣ ጠብታው በዓይኑ ውስጥ ከመግባቱ በፊት የሰባኪው ቃል በጆሮው ውስጥ ይንጠባጠባል። ሳሙኤል ዝዌመር "Islam a Challenge to Faith" በተሰኘው መጽሐፉ ላይ፣ "አንድ ሙስሊም በጤንነቱ ጊዜ አንገቱን መዝዞ የሚከራከረንን ያህል፣ የሆድ ቁርጠት ወይም የዓይን ህመም ይዞት ጠረጴዛችን ላይ ሲተኛ እንደ ህጻን ታዛዥ ይሆናል" ሲል ይህንን የህመም ብዝበዛ በኩራት ዘግቦታል። ሁለተኛውና በዘመናችን የረቀቀው ምሳሌ ደግሞ "ተንቀሳቃሽ የገጠር ክሊኒኮች" ናቸው። ይህ ስልት በተለይ መንግስታዊ የመሰረተ ልማት ባልደረሰባቸው ራቅ ያሉ የሙስሊም መንደሮች ውስጥ ይተገበራል። አንድ የህክምና ቡድን መኪናውን ይዞ መንደሩ አደባባይ ላይ ይቆማል። ለህጻናት ነጻ የትላትል መድሃኒት፣ ለነፍሰጡሮች ደግሞ የአይረን ፎሊክ አሲድ ይታደላል። በህክምናው ሂደት ውስጥ ነርሷ ወይም ዶክተሩ የታካሚውን እጅ ይዞ፣ "መድሃኒቱን የምሰጥህ እኔ ነኝ፣ ፈውሱን ግን የሚሰጥህ ጌታ ዒሳ (ኢየሱስ) ነው፤ እስኪ ልጸልይልህ" ይለዋል። እዚህ ጋ የተፈጠረው ስነ-ልቦናዊ አጣብቂኝ እጅግ አደገኛ ነው፦ ታካሚው 'አሜን' እንዳይል እምነቱ ይከለክለዋል፣ 'አልፈልግም' ብሎ እጁን እንዳይሰበስብ ደግሞ የተዘረጋለት የህይወት አድን መድሃኒት ያዝዘዋል። በዚህ ስልታዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ የህልውና መውደድ (Survival instinct) በመጥለፍ ዶክትሪን ማጋት ይከናወናል። የዚህ 'የህክምና ስልት' የመጨረሻው ምሁራዊ ስሌት "የውለታ እዳ መፍጠር" ነው። አንድ ሰው በገንዘብ የተደረገላትን ውለታ መልሶ ሊከፍል ይችላል፤ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ የተደረገለት የህይወት አድን ህክምና ውለታ ግን 'በሞራል እዳነት' ህሊናውን ጠርንፎ ይይዘዋል። ማህበረሰቡ እነዚህን የህክምና ተቋማት ሲመለከት የሚያየው የተገነባውን ቆንጆ ቪላ እና የተደረገለትን ነጻ ህክምና ነው፤ ከነጭ ጋውኑ ጀርባ ያለውን የነፍስ ወለድ ስሌት ግን ማየት አይችልም። ዶክተር ኬኔዝ ኦስተር "Evangelism Among Muslims" በተሰኘው የዶክትሬት ጥናቱ ላይ እንዳስቀመጠው፣ "የህክምና ሚሽነሪነት ትልቁ ስኬቱ ስንት ሰው አዳነ የሚለው ሳይሆን፣ በፈወሰው ስጋ ቁጥር ልክ ስንት የተዘጋ አእምሮን ሰበረ የሚለው ነው" ይላል። ይህ ሰብዓዊነትን እንደ ርዕዮተ-ዓለማዊ ትሮጃን ፈረስ የተጠቀመበት የክፍለ ዘመናት ስውር ጥቃት ነው። በቀጣዩ ክፍል የምንዳስሰው አጀንዳ፡ ቋንቋን መቆጣጠር - የትርጉም ፖለቲካ እና መጽሐፍ ቅዱስን በሀገር በቀል ቋንቋዎች፣ ስሞችና የባህል ቃላት ውስጥ ሸሽጎ የማቅረብ ስልትን በቀጣይ ክፍል - 14 በአላህ ፍቃድ እንመለከተዋለን። የመረጃ ምንጮች፦ • Lucknow, 1911: Papers and Discussions of Lucknow Missionary Conference (Section on Medical Missions), pp. 46-59. • Kenneth S. Oster, "Evangelism Among Muslims", D.Min Dissertation, Andrews University, 1975. • Samuel Zwemer, "Islam a Challenge to Faith", p. 161. የሕያ ኢብኑ ኑህ https://t.me/Yahyanuhe
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ዛሬ እና ነገ ደርስ አይኖርም!
ነገ ረቡዕ የሙሐረም 9ኛ ቀን ነው። ትክክለኛ የሚፈለገው ጾም የሐሙሱ 10ኛውን ቀን ነው። ግን ከአይሁዶች ለመለየት ቀጣዩን አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውን እጾማለሁ ብለው ስለነበር ውዱ ነቢያችን ⏩️፣ ከነገ ጀምሩና እንጹም። ነገ ያለፈው ሰው ሐሙስንና ጁሙዓን ይጾማል። ያለፈ ወንጀልህን ማስማር ከፈለግክ አትዘናጋ። አላህ ያግራልን።
видео или голосовое, без подписи
ዱንያ ላይ ምን ደስ እንደሚል ታውቃለህ…? አላህ ሷሊሕ ልጆችን ሰጥቶህ፣ የፈጅር አዛን ሲል ትልልቆቹን ቀስ ብለህ ቀስቅሰህ፣ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ወደ መስጂድ ስታቀኑ… ከሶላት በኋላ አብራችሁ የጠዋት ደርስ ቀርታችሁ፣ ወደ ቤት ስትመለሱ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር የተዘጋጀውን ቁርስ በልታችሁ፣ ልጆችህን መርቀህ ወደ ትምህርት ቤት ስትሸኛቸው… ቀኑን ሙሉ ስትለፋ ውለህ ማታ ወደ ቤትህ ስትመለስ፤ ገና በር ሊከፈት ሲል ድምፅህን ሰምተው "አቢ መጣ! ባባ መጣ!" እያሉ እየተሻሙ ሲሮጡ… አንዱ በቀኝህ፣ ሌላኛው በግራህ ሲንጠለጠል፣ ትንሹ ደግሞ እግርህ ላይ ሲጠመጠም… ጠዋት ለስራ ስትወጣ "አቢ ሄደብን" ብለው ሲያለቅሱና ሲያኮርፉ ስታይ… ያኔ ነው ዱንያ እውነተኛ ጣዕሟ የሚገባህ! ያኔ ነው ጠዋት ስትወጣ ለምንና ለነማን ብለህ እንደምትወጣ፣ ምን ዓይነት ትልቅ ዓላማ እንዳለህ የሚሰማህ። ውዷን ሚስትህንና እነዚህን የአላህ ስጦታዎች አንደላቅቀህ ለማኖር ስትለፋ ድካምህ ሁሉ ወደ ደስታ ይቀየራል፤ ማታ ስትመለስም ቤትህ ከምንም በላይ ይናፍቅሃል። ቤታችሁ ራሱን የቻለ የዒባዳህ፣ የቁርኣን ቂርኣት፣ የዚክር፣ የመዝናኛ፣ የጥናትና የጨዋታ ጊዜ አለው። ሚስትህም የቤቱ ብርሃን ሆና፣ የልጆቹ መምህርና ሙረቢ፣ ያንተ የልብ እረፍት ትሆናለች። ላጤ ከሆንክ ግን ስትወጣም ስትገባም ማንም አይጠብቅህም፤ የለፋህበትም ድካም የዚህን ያህል ጥልቅ ትርጉም አይሰጥህም! ስለዚህ… አግባ ሐቢቢ! ዲን ያላትን ምረጥ፤ አላህ የዚህች ዱንያ ጀነት የሆነውን ያማረ ትዳርና ሷሊሕ የሆኑ ልጆችን ይወፍቅህ! Copy
## ተውሂድ እና ስለ ወደፊት እጣ ፈንታ አለመጨናነቅ ወንድሞቼ ሆይ! ሸይጣን በአማኝ ልብ ውስጥ ፍርሃትን ለመዝራት ትልቅ ዓላማ እና ከፍተኛ ጥረት አለው። ከፈጣሪ (ከአላህ) ውጭ ያለን ነገር የስጋት ስሜትን በአማኝ ልብ ውስጥ ለመትከል ይተጋል። ምክንያቱም አንድ ሰው ከአላህ ውጭ ያለን አካል ወይም ነገር በፈራ ቁጥር እምነቱ (ኢማኑ) እና ተውሂዱ እየደከመ ይሄዳል። አንድ አማኝ ከአላህ ውጭ ያለን ነገር መፍራት ከጀመረ፣ ያ (ለሸይጣን) መግቢያ በር ይሆንለታል። ልክ እንደ ሀዘን ሁሉ፤ ሸይጣን የአማኝን ልብ ለማሳዘን ከፍተኛ ፍላጎት አለው። አላህ በቁርአኑ እንደሚለው፦ > *"የሚስጥር ውይይት (የነጃዋ) ከሸይጣን ብቻ ነው፤ እነዚያን ያመኑትን ሊያሳዝን።"* > ስለዚህ ሸይጣን አማኞችን ለማሳዘን ይጓጓል። ### የሀዘንና የስጋት ተጽእኖ ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ‘መዳሪጁ አስ–ሳሊኪን በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ > *"አላህ ሀዘንን አይወድም። ሀዘን እምነትን ያደክማል። ሸይጣን ግን ሀዘንን ይወዳል። ለምን ቢሉ? ባሪያውን አላህን ከመታዘዝ ስራ ስለሚያስረው፣ ስለሚያዳክመውና ልቡን ስለሚሰብረው ነው። ፍርሃትም ልክ እንደዚሁ ነው።"* > ስለዚህ እናንተ ሙእሚኖች ሆይ! ከአላህ ውጭ ያለን ነገር ከመፍራት ተጠንቀቁ። ዛሬ ላይ ሰዎች በጭንቀት፣ በድንጋጤ እና ስለ መጪው እጣፈንታ በመጨነቅ እንዲሁም በሌሉና በማይጨበጡ ምኞቶች/ቅዠቶች ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ። ሊሆኑ ስለሚችሉ ነገሮች ከሚጨነቁት ቅዠቶች በተጨማሪ ማለት ነው። ነገር ግን እምነት በልብ ውስጥ ሲጠነክር እና ተውሂድ ሲጎለብት፣ ሰው ከአላህ በቀር ማንንም አይፈራም። ### የሕይወት ፈተናዎችን በአዎንታዊ እይታ መመልከት * በስራ ወይም በንግድ አጋርነት፦ አንድ ሰው ከባልደረባው ወይም ከንግድ አጋሩ ጋር በስራ ጉዳይ ቢኳረፍ፣ ሪዝቁ እንዳበቃለት አድርጎ ማሰብ የለበትም። በአጋሩ ጉዳይ አላህን ይፍራ፤ ነገሩ ቢሳካ አልሐምዱሊላህ፣ ባይሳካ ደግሞ ምናልባትም አላህ ከክፉ ነገር አርቆት ሊሆን ይችላል። * በትዳር ሕይወት፦ ከባለቤቱ ጋር ቢጣላና ዱንያ የጠበበችበት ቢመስለው፣ ምናልባትም አላህ በእነሱ መለያየት ውስጥ መልካም ነገርን አስቦ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ከመለያየቱ በኋላ የተሻለና የላቀ መስተካከልን ሊያመጣ ፈልጎ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሰው በጭንቀት ውስጥ ራሱን ሊያጋንን አይገባም። * በበሽታና በፈተና፦ ልጁ ቢታመም ወይም እሱ ራሱ በካንሰርና በመሰሉ ከባድ በሽታዎች ቢያዝ፣ ነገሩ ሁሉ አበቃለት ማለት ነው? አይደለም! አንተ ሙእመን ነህ። የዚህች ዓለም (የዱንያ) ሕይወት የፈተና እና የመሻገሪያ ቤት እንጂ ሌላ አይደለችም። ### በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ መኖር በአላህ እምላለሁ! በካንሰር እና በመሰሉ በሽታዎች የሚሞት ሰው፣ በድንገተኛ ሞት ከሚሞት ሰው በተወሰነ መልኩ የተሻለ እድል አለው። ምክንያቱም ይህኛው በበሽታው ምክንያት ወንጀሉ ይሰረዝለታል፣ ለእሱ ማስጠንቀቂያ ይሆነዋል፣ ራሱንም እንዲመረምር እድል ይሰጠዋል። በድንገተኛ ሞት የሚሞተው ግን ይህንን የመሰለ እድል አያገኝም። አላህ እጅግ በጣም አራህማን እና ለባሮቹ ሩህሩህ ነው። ስለዚህ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑራችሁ። > *"ከነሱም አንዲት ጭፍራ በእርግጥ ነፍሶቻቸው አሳሰቧቸው። በአላህ ላይ ያለ ሀቅ የጃሂሊያን (የመሃይማንን) ጥርጣሬ ይጠረጥራሉ።"* > ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! ከአላህ በቀር ሌላን አትፍሩ። መጪውን ጊዜ አትፍሩ፣ ድህነትን አትፍሩ፣ በሽታን አትፍሩ፣ በነፍሳችሁም ሆነ በልጆቻችሁ ላይ አትስጉ። ነገሩ ሁሉ በአላህ እጅ ነው። ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሕይወታችሁን ብትመረምሩ፣ በአንድ ወቅት ስላመለጣችሁ አዝናችሁበት የነበረ ነገር፣ በኋላ ላይ በእሱ ውስጥ ፈጽሞ ያላሰባችሁት መልካም ነገር እንደነበረበት ትገነዘባላችሁ። በሰዎች ታሪክና ሕይወት ውስጥም ይህንን እናያለን፤ ከስራው የተባረረ ሰው ስራዬ አለቀብኝ ብሎ ሲያስብ፣ አላህ ግን ሰፊና ታላቅ የሲሳይ በር ይከፍትለታል። ሰጪው አላህ ነው፤ ለአንተ የተጻፈልህ ነገር ሳይመጣልህ አይቀርም። ኢብኑል ቀይም እንዳሉት እወቅ፦ > *"ድህነት ከተጻፈብህ እሱ ላንተ መልካም ነው። ምክንያቱም አንተ ለዱንያ ሳይሆን ለአኼራ የተፈለግክ ልትሆን ትችላለህ። በሽታ ከተጻፈብህም ላንተ መልካም ነው፤ ምክንያቱም አላህ ለአኼራ ፈልጎሃል።"* > አላህ በራህመቱ ይሸፍነን፣ እርግጠኝነትን (የቂንን) ይስጠን። ከአላህ ውጭ ሌላን አንፍራ። ይህ ማለት ግን ሰበብ ማድረስን (መጣርን) መተው ማለት ነውን? ፈጽሞ አይደለም! ዛሬ ላይ እኛ የምንኖረው ሰበብን በማጋነን ቀውስ ውስጥ ነው..ያለነው። .