የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
Статистикаይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 044
- 1/48двое суток
- 1 196
- 1/72трое суток
- 1 290
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አንድ ወጣት እንዲህ ይላል፦ "አንድ ቀን እኔና ጓደኛዬ የገንዘብ ቦርሳችንን (ዋሌታችንን) ተለዋወጥን። እኔ የእሱን ቦርሳ ስፈትሽ፣ እሱ ደግሞ የእኔን ቦርሳ ይፈትሽ ነበር። ቦርሳው ውስጥ የነበሩትን በርካታ የወረቀት ቁርጥራጮች እያነበብኩ ነበር። በአንዱ ወረቀት ላይ የተጻፈውን አነበብኩ ፊቴ በደስታና በግርምት ተሞላ። 'ይህ ምንድን ነው?' ብዬ ጠየቅኩት፤ – በስሜ የተቆረጠ የበጎ አድራጎት ድርጅት ደረሰኝ ነበር – እሱም፡ 'የአንድ አባት የሌለው ልጅ (የየቲም) እርዳታ/ድጋፍ ነው' አለኝ። እኔም፡ 'ግን ለምን በኔ ስም ሆነ!?' አልኩት። እሱም፡ 'በአንተ ስም ነው የቲሙን የደገፍኩት' አለኝ። እኔም፡ 'ከመቼ ጀምሮ ነው?' አልኩት። እሱም፡ 'ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ' አለኝ። እኔም፡ 'ለምን ይህንን አደረግክ!' ብዬ ጠየቅኩት። እሱም፡ 'እሳት (ጀሃነም) እንዳይነካህ ስለፈራሁልህ ነው' ሲል መለሰልኝ።” አላህ ሆይ! መልካም እና ደግ ጓደኛን ወፍቀን! 🥺
اللهم مع شروق هذا اليوم، نسألك خيراً في كل أمر، ونوراً في كل درب، وراحة في البال، وتوفيقاً يرافق خطواتنا.
اللهم ارزقنا عمرة و عودةً اليها لا تنقطع، ولقاءً يطمئن به القلب. 🕋✨ آمين آمين آمين
ነገሮች ሲዘበራረቁ ቦታቸውን እያየዙ ሊሆን ይችላል፤ ተስፋ አትቁረጥ! በአንድ ጉዳይ ላይ ወደ አላህ አብዝተህና አጥብቀህ ዱዓ አድርገህ ... ከዚያ በኋላ ግን ሁሉም ነገር ወደ ተቃራኒው ሲቀየር ብታይ፣ ዱአዬ አልተቀበለኝም ብለህ እንዳታስብ! አላህ መልካሙን ነገር አንተ ልትረዳው በማትችለው መንገድ እየመራው ይሆናል፤ በክስተቶችም የምስክርነትህንና የእምነትህን ጥንካሬ ይፈትናል። የእምነትህ ፅናት ሳይናወጥ የጸና ሆኖ ካገኘው ደግሞ ባልጠበቅኸው ስጦታ ያስገርምሃል.. አላህ በእርሱ በሚተማመኑት ባሮቹ ጥርጣሬና ግምት ልክ ነው!♥️
በአቅራቢያዋ ሰላምና ስክነት አለ…🕊️ በአላህ መልእክተኛ ﷺ መስጂድ ቅጽር ግቢ ውስጥ ደግሞ ከምንም ነገር ጋር የማይመሳሰል የልብ እርጋታና እረፍት ይገኛል። 💚
«ደካማ የሆነ ምላሽ(ረድ) ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ የሚያደርሰው ጉዳት ያመዝናል! ጠንካራ ያልሆነ ምላሽ ሊመልሱ ወይም ማስረጃ የማይሆንን ነገር እንደ ማስረጃ ሊያቀርቡ ይችላሉ፤ ከዚያም በህዝቡ መካከል ሲበተኑት፣ በዚህ ጥርጣሬ (ሹብሃ) የተበከለው ሰው ምላሽህ ደካማ መሆኑን ሲያውቅ ያኔ ጥርጣሬው በልቡ ውስጥ የበለጠ ይስፋፋል። አንተ የአህሉሱና ተወካይ ነህ፤ በዚህ ጃህል እይታ ውስጥ የአንተ ድክመት ማለት የሱና መንገድ (መዝሀብ) ድክመት ተደርጎ ይወሰዳል—ይህ ደግሞ ትልቅ ችግር ነው። አንዳንዶች ምላሽ ለመስጠት በቅድመ-ግንባር ይሰለፋሉ፤ ነገር ግን ምላሾቻቸው ደካማና ተሰባሪ ናቸው፤ አስፈላጊው ዕውቀት፣ ጥንካሬና ጥልቀት የላቸውም። በራስህ ውስጥ የዚህ መስክ ባለቤት አለመሆንህን ካወቅህ፣ አላህ ከአቅምህ በላይ አልጫነብህምና ጉዳዩን ለሌሎች ተወው። በህዝቡ መካከል 'ይህ የአህሉሱና መንገድ ነው' ብለህ እያሰራጨህ ምላሽህ ግን ያን ያህል ጠንካራ ካልሆነ፣በጣም አደገኛ ጉዳይ ነው። ይህም ወደ ሌላ ነባራዊ ሁኔታ ትኩረት እንድስብ ያደርገኛል፤ እርሱም፦ ዛሬ ያሉ ወጣቶች በልቦቻቸው ውስጥ ጥርጣሬዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ጥርጣሬዎቹ ከቀደር ጋር የተያያዙ፣ ከአንዳንድ ሕግጋት ጋር የተያያዙ፣ ወይም ደግሞ ከፈጣሪ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ማንነት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያና የኢንተርኔት መረቦች በዚህ ግልጽ በሆነ የጥመቶች ስብስብ የተሞሉ ናቸው፤ ስለዚህ ከእነዚህ ጥርጣሬዎች መካከል የሆነ ነገር በዚያ ወጣት ልብ ውስጥ ሊያድር ይችላል። እናም አንተ በትምህርት ቤት ውስጥ ያለህ አስተማሪ፣ በ መስጂድ ውስጥ ያለህ ኢማም፣ ወይም ደግሞ እርሱ እንደ ሸይኽና እንደ ዓሊም (ዕውቀት ያለው ሰው) አድርጎ የሚያይህ ሰው ወደ አንተ መጥቶ ጥያቄውን ሲያቀርብልህ፤ እንዴት ምላሽ መስጠት አለብህ? በአላህ መልካም ፈቃድ ጥርጣሬውን ከልቡ የሚያስወግድ፣ አጥጋቢና ትክክለኛ የሆነ ምላሽ ካልሰጠኸው፣ ማድረግ የሚገባህን አልሰራህም። በዚያ ደካማ ምላሽ ምክንያት እርሱ ዝም ሊል ወይም በፊቱ አንገቱን ሊነቀንቅ ይችላል፤ ነገር ግን በእውነቱ በልቡ ውስጥ 'ጉዳዩ በእርግጥም አጠራጣሪ ነው፣ እረ እናንተ ሸይኾች ዘንድ ምንም ምላሽ የላችሁም' ብሎ ያምናል። ይህንንም ከአንዳንዶቹ ሰምቼዋለሁ፤ ከእነዚህ ወጣቶች አንዱ ስላጋጠመው ጥርጣሬ ሲጠይቅ የተሰጠው ምላሽ፦ 'ይህን ንግግር ተወው!' የሚል ነበር። 'ይህን ንግግር ተወው' የሚለው ምላሽ በልቡ ውስጥ ያለውን ጥርጣሬ ያስወግደዋልን? አያስወግደውም! በተለይም የዛሬ ወጣቶች አሳማኝ ማስረጃ ያስፈልጋቸዋል፤ ልስላሴ ልታሳያቸው፣ በሚረዱትና በሚገባቸው ቋንቋ ልታበራራላቸው ይገባል። ስለዚህ አንተ በቁጣ፣ ወይም 'ዝም በል' በማለት፣ ወይም ደግሞ በደካማ ምላሽ ካሰናበትከው፣ ጥርጣሬውን በልቡ ውስጥ የበለጠ ታጠናክራለህ። ስለሆነም፦ ወይም አጥጋቢ ምላሽ ስጠው፣ ወይም ደግሞ መልካም ምላሽ መስጠት ወደሚችልና ወደሚያውቅ ሰው እጁን ይዘህ ውሰደው።" ፕሮፌሰር ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሲንዲ
🔴 የጁምዓ ኹጥባ 🎙 خطبة الجمعة سلسلة أحداث يوم القيامة (الشفاعة) ✨ የቂያማ ቀን ክስተቶች (3) ሸፈዓ (ምልጃ) ⚠️ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ❗️ 🎙በኡስታዝ ሱልጧን ኸድር 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ 🗓 ሶፈር 25/1448 አ/ሂ http://t.me/kalityhamzamesjid
«በጀመዓ (በአንድነት) ውስጥ ያለ ችግር፣ በመለያየት ከሚገኝ ምቾት ይበልጣል።» ሸይኽ ሷሊሕ ኢቢኑ አብደልዐዚዝ ኢቢን ዑሥማን አስ-ሲንዲ (በመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የዐቂዳ ፕሮፌሰር)
በሰላቱ ላይ የዘወተረ ሰው፣ በሁለት ሰላቶች መካከል ይሞታል፡ በሰገዳት እና በሚጠብቃት ሰላት መካከል፤ 🥹🌻🌸 አላህ ሆይ! ያማረ መጨረሻንና ከፍተኛዋን ጀነት (ፊርደውስን) እንለምንሃለን።
በሁሉም ነገር ውስጥ የአላህን ቸርነት እና ደግነት መፈለግን ለራሳችሁ ልማድ አድርጉ፤ ግራ በሚያጋቡ አጋጣሚዎች እና በጭንቀት/በመከራ ወቅትም እንኳ ቢሆን። ሁልጊዜም፦ «ምናልባት መልካም ይሆናል፤ ምናልባት አላህ የማላውቀውን ክፉ ነገር ከእኔ አርቆልኝ ይሆናል፤ ምናልባት ከዚህ በኋላ መላቀቅ፣ እረፍት እና ማቃለል ይመጣል» ማለትን ልማድ አድርጉ። ሁልጊዜም በአላህ ውሳኔ የመርካት (ቀደርን የመቀበል) መንፈስ ይኑራችሁ... ከዚያም በኋላ አላህ እንዴት እንደሚያስደስታችሁ እና እንዴት እንደሚበቃችሁ ታያላችሁ።
እውነተኛ ጓደኝነት ለአላህ ብሎ ሲሆን… ✨ በዚህች ምድር ላይ ለአንድ አማኝ ከተሰጡት ትላልቅ ጸጋዎች አንዱ "መልካም ጓደኛ" ነው። ይህ ጓደኛ በገንዘብ፣ በዝና ወይም በጊዜያዊ ጥቅም ሳይሆን፣ ንጹህ በሆነው የአላህ ፍቅር ብቻ የተሳሰራችሁት ነው። አብዛኛው የሰው ልጅ ግንኙነት በግላዊ ጥቅም ላይ በተመሰረተበት በዚህ ጊዜ፣ ለአላህ ተብሎ የሚመሰረት ውዴታ እጅግ ውድ ነው። ነቢዩ ሰለሏሁ አይሂ ወሰለም አላህ ዘንድ በልዩ ሁኔታ ስለሚጠለሉት ሰዎች ሲናገሩ፦ "ስለ አላህ ብለው የተዋደዱ፣ በእርሱ ላይ የተሰበሰቡና በእርሱ ላይ የተለያዩ..." ብለዋል። ይህ ማለት ለአላህ ተብሎ የተገነባ የወንድማማችነት ፍቅር በሞት አያበቃም፤ ጠቀሜታውም ሆነ አማላጅነቱ ጀነት ድረስ የሚዘልቅ ዘላለማዊ ትስስር ነው! 🤲 ኢላሂ! ወደ አንተ የሚመሩንን፣ ስንዘናጋ የሚያስታውሱንን እና ትዕዛዝህን በመፈጸም ላይ የሚያግዙንን መልካም ጓደኞች ወፍቀን። ውዴታችንን ላንተ ብሎ ብቻ አድርግልን፤ በቂያማ ቀንም ምንም ጥላ በሌለበት ጊዜ በአርሽህ ጥላ ስር ከሚሰበሰቡት ባሮችህ አድርገን። አሚን! 🤍
የመልካም ጓደኝነት ውብ ከሆኑ ነገሮች አንዱ፡ በዚህች ዱንያ መጠናቀቅ የማይበቃ መሆኑ ነው፤ ይልቁንም እስከ ቂያማ የሚዘልቅ ሲሆን፣ ከአላህ ጥላ ውጭ ምንም ጥላ በሌለበት ቀን በአላህ ጥላ ስር አብረው ይጠለላሉ። ورجلان تحابا في الله اجتمعا عليه وتفرقا عليه.
ሰላም! ለዚያች በፍቅሯ ልባችንን ላሸነፈችው ከተማ ..🤍💔 ሰላም! እሷን ላበሯት ነቢያችን ﷺ፣ ሰላም! በየቀኑ እሷን ለሚናፍቅ ልብ ። 💔🕊...
ወርቃማ ምክር ከሸይኽ ሙሐመድ ረምዛን ሃጅሪይ ሀፊዘሁላህ «ከአላህ ጋር ያለህን ምስጢር አድስ» «ሰዎች ቢያወድሱህም፣ ቢያስታውሱህም፣ ላደረግከው መልካም ነገር ቢያመሰግኑህም... አንተ ከማንም በላይ የራስህን ሰወር ጥፋቶች ታውቃለህ። የራስህን ምስጢር ታውቃለህ፣ ሌሊትህን ታውቃለህ፣ ቀንህን ታውቃለህ... ስልክህንና በእርሱ ውስጥ ያሉትን መልእክቶች፣ ያየሃቸውንና የሰማሃቸውን ነገሮች ሁሉ ታውቃለህ። የሰዎችን ሙገሳና አድናቆት ተወው፤ አንተ ከአላህ ጋር ያለህን ምስጢር ከማንም በላይ አዋቂ ነህ። ራስህን አስተካክል... ራስህን አክም! በውስጥህ ግድፈትና ጉድለት ካየህ፣ ያንነ አውቀህ አስተካክለው። የሰዎች ወሬና የአሞጋሾች ማወደስ አይሸንግልህ፤ አንተ ራስህን ከማንም በላይ ታውቃለህና ራስህን አርም! ጥፋትህን ➔ አስተካክለው! የልሳን ስህተት ➔ በዚክር (አላህን በማስታወስ) ለውጠው! ሐሜት ➔ በመልካም ወሬ ለውጠው! እግርህ ወደ ወንጀል አመራች? ➔ ወደ መስጂድ አቅናት! ምላስህ ተንሸራተተች? ➔ ቁርዓን ወደ ማንበብ ቀይረው! ዓይንህ? ➔ የአላህን መጽሐፍ ክፈት! ጆሮህ? ➔ ቁርኣንን፣ ዚክርንና መልካም ነገርን ስማ! ዝምድና መቁረጥ? ➔ ሂድና ያቋረጥከውን ሰው ቀጥል... አባትህ፣ እናትህ፣ አክስትህ፣ አጎትህ... እከሌ ቢሆን እንኳን ሂድና ይቅርታ ጠይቅ! ወለድ? ➔ ተወው! ወንጀል? የሙዚቃ/እያዩ የመስማት ነገሮች? ➔ ተጠንቀቅ፣ አስተካክለው! «በእርግጥ መልካም ሥራዎች መጥፎ ሥራዎችን ያስወግዳሉ!»»
ይህንን ፔጅ ለሚከታተል እያንዳንዱ ሰው ልብ የተላከ መልእክት🤍.. ለእኛ የተጻፈልን ነገር የእኛ እንደሚሆን ጥልቅ እምነትና የቂን ሊኖረን ይገባል.. ስለዚህም ምስጋና ለአላህ ይሁንና.. አንድ ቀን እንረዘቃለን፣ እንደሰታለን፣ መከራን ሁሉ እናልፈዋለን፣ እንዲሁም በሚያምር ነገር ሁሉ እንካሳለን.. («እኔ ባሪያዬ እኔ ባሰበኝ(በጠረጠረኛ)ዘንድ ነኝ») ብሏልና። አላህ እንደሚሰማህና የልብህን ሰወር ቦታዎች እንደሚያውቅ ስታስታውስ የሚሰማህ ስሜት እጅግ ያረጋጋል.. ለማንም ያልተናገርካቸው ቃላትህ፣ ያላሳየኸው ሀዘንህ፣ እናም እርሱ በተባረከ እዝነቱ ከመጠየቅህ በፊት እንኳ የሚያቃልልልህ መሆኑ.. በአላህ መተማመን ምን ያህል ያምራል! አላህ እኛን ከነፈገን የሚበልጥ መልካም ስጦታዎች አሉት፤ ከመሆኑም ጋር ብዙ ለመስጠት ሲል ጥቂት ነገርን ይወስዳል.. መልካም ትዕግስት ይኑርህ፤ ሕይወት ያለ ትዕግስት ልናልፋቸው የማንችላቸው ፈተናዎች አሏትና..
የዓለማቱ ጌታ (ረበል ዓለሚን) አልረሳህም፤ በደከምክበትና በሰብር ባሳለፍከው በእያንዳንዱ ቅጽበት ምትክ ይክስሃል። ተረጋጋ፣ እረፍት ይሰማህ፣ በዓለማቱም ጌታ ተማመን! ምክንያቱም የእሱ ካሣ እንደ ሰብርህ መጠን ነውና። የጠፋ ድካምም ሆነ መና ሆኖ የሚቀር ትዕግሥት የለም፤ ሁሉም የጊዜ ጉዳይ ነው፤ ደስ ይልሃል፣ ልብህንም ደስ ያሰኘዋል። ፈጽሞ ተስፋ እንዳትቆርጥ፤ ምክንያቱም ቀኑ ቀርቧል... ቀርቧል! የአላህም ካሣ ይመጣል።
አላህ ሆይ! በልብ ውስጥ ትርታ እስከ አለ፣ ነፍስም መናፈቋን እስከቀጠለች ድረስ መዲናን እንድንጎበኛት አድርገን፤ በነቢይህ ﷺ መስጂድ ውስጥ ሶላትን ስጠን፤ በውስጧም የማይጠፋ እፎይታንና በህይወትም ሆነ በሞት አጠገቧ መሆንን ለግሰን። 🤍🌿.. #የነቢዩ_መስጂድ (#المسجد_النبوي)
يارب 🕋🤲 « ኢላሂ! የማይዘጋ የኡምራ በር እና የማይመለስ (ተቀባይነት ያለው) ዱዓ ስጠን፤ አሚን ያ ረብ!» «ኢላሂ! ይህ አካል ሩህ እስካለው ድረስ መካን ደጋግሞ መዘየር ወፍቀን..» «ኢላሂ! በየትኛውም ጊዜና ወቅት መካን ለመዘየር አብቃን!
ኢላሂ! ወደ መካ የሚያደርሰንን መንገድ የማይቋረጥ አድርግልን፤ ዱንያ ምንም ያህል ብትጠብብን በእሷ ውስጥ ሰፊ እፎይታ የሚያገኝ ልብንም ስጠን። ❤️ ኢላሂ! ደጋግሜ እንድጎበኛት የሚረዳኝን ሲሳይ (ሪዝቅ) ለግሰኝ... አሚን አሚን አሚን #ያ_ረብ 🤍🤲🕊🕋❤️"
ዑምራ፡ የመንፈስ ጉዞ ወይስ የዱንያ መዝናኛ? ዑምራ—የእስልምናን ቅዱሳት ስፍራዎች የመጎብኘት፣ ወንጀልን የማሰሪያ፣ ቀልብን ከዓለማዊ እና ቁሳዊ ሸክም አጥቦ ወደ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የመመለሻ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የሚስተዋሉ አንዳንድ ልማዶችና የቱር አዘጋጆች ዘይቤ፣ የዚህን ታላቅ ዒባዳ ዋና ዓላማ እያሳቱት ይሆን? የሚል እውነተኛ ስጋት እያስነሳ ይገኛል። 1. የዓለማዊ ነገሮች መጎላትና የመንፈሳዊነቱ መቀጨጭ በዑምራ ጉዞዎች ላይ አሁን አሁን ዋና ትኩረቱ ከዒባዳ ወደ መዝናናት ሲያደላ ይስተዋላል። ፈረስ ግልቢያ፣ የቀስት ውርወራ፣ የባህር ላይ የጀልባ ሽርሽር እና መሰል መዝናኛዎች የጉዞው ዋና ማእከል እየሆኑ መጥተዋል። ከሁሉም በላይ ግን አሳዛኙ ነገር፡ በአል-ሐረመይን (በመካው መስጂደል ሐራም እና በነቢያችን መስጂድ) አንድ ሰላት መስገድ እስከ 100,000 ሰላት እጥፍ በነቢዩ መስጂድ ደግሞ አንድ ሺህ የሚደርስ ታላቅ ምንዳ (አጅር) እንዳለው እየታወቀ፣ ያንን ሁሉ እድል አግኝቶ በጨዋታና በመዝናናት ጊዜን በማሳለፍ በጀማዓ መስገድን ማስመለጥ ትልቅ ሂርማን (የአጅር ኪሳራ) ነው። መዝናናት በራሱ የተከለከለ ባይሆንም፣ ቅዱስ ስፍራ ላይ ቆሞ ጊዜን በእንዲህ አይነት ነገሮች ማሳለፍ ግን የዑምራን ዋና መንፈሳዊ ጥቅም እና የልብ መረጋጋት እያመናመነው ይገኛል። 2. የሱህባ እና የሳሊሆች ሚና መዛባት አንድ ሰው ለዑምራ ሲነሳ ከጎኑ የሚፈልገው አላህን የሚያስታውሱት፣ አምልኮቱን የሚያስተካክሉለት እና ወደ አኼራ የሚጠቁሙትን "ሩፍቀት አስ-ሳሊሃ" (መልካም ጓደኞችን) ነው። አሳዛኙ ነገር ግን፣ የቱር ኤጀንሲዎች ማስታወቂያዎቻቸው ላይ ሸሪዓዊ እውቀት ያላቸውን ረባኒይ መሻይኾች እና ዓሊሞችን መሪ ከማድረግ ይልቅ፣ የቲክቶክ እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን (Activists) እንደ ዋና ሳቢ ማስታወቂያ ማቅረባቸው ነው። መንፈሳዊ መሪዎችን በቲክቶክ አክቲቪስቶች መተካት የጉዞውን ሚዛን ያሳስታል። የዑምራ ጉዞ በቪዲዮ እይታና በፎቶ ብዛት ሳይሆን በዕንባ፣ በዱዓ እና በኢኽላስ የሚለካ ተግባር ነው። የዑምራ አዘጋጆችም ሆኑ ተጓዦች ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይገባል። ዑምራ የልብ ህክምና እንጂ የካሜራ ትርኢት ወይም የቱሪዝም ሽርሽር አይደለም። የዑምራ ጉዞ እውነተኛ ዓላማውን ሳይስት፣ የአላህን ፍራቻ እና የመንፈስ እድሳትን ማዕከል ያደረገ ይሆን ዘንድ አቀራረባችንን እና አስተሳሰባችንን ልንፈትሽ ይገባል።