ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع
Статистикаበኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ የሚተላለፉ የተለያዩ ዲናዊ መልእክቶችን የሚያገኙበት ቻናል ነው። @Menhajadama_bot 👈 ለአስተያየት ይጠቀሙ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 14
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 411
- 1/48двое суток
- 471
- 1/72трое суток
- 507
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🕌 || የጁሙዓ ኹጥባ 🏷 የቀጣዩ አለም (አኼራ) አስፈሪነት እና አሳሳቢነት 🗓 || ጁሙዓ ዐ8/12/2018 ▸ አማርኛውን ለማድመጥ -> 7:10 ---------------------------------- ▸ በኡስታዝ ዐብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ 📍በአነስ ኢብኑ ማሊክ መስጂድ https://t.me/anesibnumalikislamiccenter
ዛሬ የባለፈው የሉጋ ኪታብ በደንብ ሙራጀኣ ይደረግ
🕌 የጁሙዓ ኹጥባ 🎙 በኡስታዝ አቡ የህያ አብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ 📆 ነገ አርብ ነሐሴ 8/2018 አ.ል 📍ገንደሃራ፤ አነስ ኢብኑ ማሊክ መስጂድ https://t.me/anesibnumalikislamiccenter
ፀጥተኛው መስዋዕትነት፡ ሌሎችን ለማስደሰት ስትል በዝምታ መቅለጥ ስኳር ራስን ለሌሎች ስለመሰዋት ጥልቅ የሆነ ትምህርት ታስተምረናለች፤ ጠዐሟን በሙሉ ለሻዩ ሰጥታ በዝምታ ትጠፋለች፤ በዚህም መልካሙ አሻራ እና ጣፋጩ ቃና በቋሚነት ይኖራል፤ሰዎችም ስኳሯን ረስተው ሻይዋን ያመሰግናሉ ፤ያደንቃሉ ፤ስኳራ ግን በዝምታ ተሰውራለች። ሁሉም በጎ ሥራ የሰዎችን ጭብጨባ አይፈልግም። ባለታላላቅ አእምሮዎችና ቅን ልቦች ምስጋናን ወይም ሙገሳን ሳይጠብቁ በሌሎች ሕይወት ውስጥ አዎንታዊ አሻራቸውን ማሳረፍን ይመርጣሉ።እስኪ እራሳችንን ብቻ አንውደድ፤ለሌሎችም መኖር እንልመድ፤በሀዲስ ውስጥ "የሰው መልካሙ ሰዎችን የጠቀመ ነው" ይላል። በጎ ሥራን ሥራ፣ መልካም አሻራንም አሳርፍ፤ የተከበረው ሥራህ ራሱ ስለ አንተ ይናገር።
ከአዲስአበባ መስጂዶች በአንድ ትልቅ መስጂድ ውስጥ ኹጥባ ነበረኝ፤ሆኖም የአዳማ ጀማኣ ቀድሞ ስለጠራኝ እና እኔም ጀማኣውን ከወንድሜ አንዋር በኋላ ስላልዘየርኩት በፍጹም አልቀርም ብዬ ሌላ ሰው ሰጥቻቸዋለሁ፤ሌላው አንዳንድ ታእዚያዎችም አሉ አቅም በፈቀደ ለመድረስ እሞክራለሁ ፤አላህ ዱንያ ኣኺራችንን ያሳምርልን፤ በዱኣ በርቱ፤ ጁምኣን ኢንሻአላህ አዳማ እንገናኝ
በአሁን ጊዜ በተለያየ መስጂድ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች እየታዘብኩ ነው፤አሁን ዙህር ሰግጄ የወጣሁበት መስጂድም ስለተመለከትኩ ነው ይህን የፃፍኩት ፤ እንደ ሚንበር ቲቪ አይነት የኡማውን ደም መጣጮችን ትቶ ኡማው እንዲህ አይነት ልጆቹን መሰብሰብ አለበት፤ ባለፈው አንድ ልጅ መስማት ስለ ተሳናቸው ልጆች ነግሮኝ እጅግ አዝኛለሁ ፤እንደ ሀገር ብዙዎች ያሉን ቢሆንም አንድ እስላማዊ ተቋም የላቸውምና ለኩፍር ተጋላጭ ሆነዋል ፤ እኔ ደግሞ ከላይ እንዳለፈው የእድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች በተለያዩ መስጂዶች እየተመለከትኩ ነው ፤እነርሱም አንድ ተቋምኳ ሳይኖራቸው ትምህርት ቤት መዋል ሲገባቸው፤ የዚህ ሰነፍ ህዝብ ልጅ በመሆናቸው እድላቸው እየተበላሸ ይገኛል ፤ ሰነፉ ህዝብ መስጂድ ላይ ቦታ ካገኘ እንዲህ ያሉ ወገኖችን አስተማሪ ፈልጎ ከማሰልጠን ይልቅ እርግብ ማርባትና ኳስ ማሰልጠን ይቀለዋል ፤ መቼ ነው ግን ለህዝብ ማሰብ የምንጀምረው?!
የሰላም ነገር እጅግ ያሳስበናል አዲስ አበባ ማለት ከኦሮሚያ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ አካላት ቤታቸው ና ሱቆቻቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ሸሽተው የተቀመጡባት፤ በአማራ ክልል በተለይ አነስተኛ ሙስሊም ያለበት አከባቢ ያሉ ሙስሊሞች ቤታቸው ሲዘረፍ በግፍ በሀይማኖታቸው ምክንያት ሲጠቁ የሸሹባት ፤ በሀዋሳ ሳይቀር ወደ ሲዳማነት ትግባ ተብሎ በነበረው ግጭት ሰዎች የሸሹት ወደ አ/አበባ ነው፤ ስለዚህ እቺን ከተማ ከህብረ ብሄራዊነት ማውጣት ማለት ምንም መሸሻ አልባ አድርጎ ህዝቡን ማስወቀጥ ማለት ነው፤ ሀገሪቱ ሰላም ብትሆንኳ ምንም አልነበረም ፤በዚህ ሰአት ግን በእንቅርት ላይ ጆሮደግፍ ነው፤ ሰላም ያሳስበናል ፤ በሰላም እንጂ ሰው መኖር አይችልም ።
እንዲሁም ያልቻልነው ዘረኝነት ና የሰላም መናጋት ሁሉንም የጋራ አድርገን መፍታት ሲገባን ፤ጭራሽ የጋራ የነበሩትን ከተሞች ወደ አንድ አከባቢ በመውሰድ የባሰ መከራ ውስጥ እንዳንገባ አሏህ ይጠብቀን
ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበል (አላህ ይውደድላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡ «ለሻፊዒይ ዱዓ ሳላደርግላቸው ያለፈች አንዲትም ሶላት ከሰላሳ ዓመታት ወዲህ የለችም...» ለእርሳቸው የሚያደርጉት ዱዓ የበዛ በመሆኑ፣ ልጃቸው «ኢማም ሻፊዒይ ይህን ሁሉ ዱዓ የምታደርግላቸው ምን ዓይነት ሰው ነበሩ?» ብሎ ጠየቃቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉት፡ «ልጄ ሆይ! ሻፊዒይ ለዚህ ዓለም እንደ ፀሐይ፣ ለሰዎች ደግሞ እንደ ጤና ነበሩ።» የጠቀመንን ሰው በተለይ ያስተማረንን አንዘንጋ ፤ከሁሉ በላይ በዱኣ
እኔ ላይ ሰዎች የሆነ ነገር ስላረጉ ደእዋም ሆነ ኹጥባ ማድረግ አልወድም ፤በሰዎች ላይ በሚደርሱ ነገሮች ግን ምናልባት የመፍትሔው አካል ከሆንኩ ብዬ አደርጋለሁ ፤ሚንበሩ የሙስሊሞች መድረክ እንጂ የግሌ እንዳልሆነም ጠንቅቄ ስለምረዳም ነው፤ በተቃራኒው ሁሉንም የኹጥባ ርእሶች የራሳቸውን ችግር መፍቻ ያደረጉ ሰዎች በተደጋጋሚ ይገጥመኛል ፤በልጅነቴ ሰዎች ለኔ ዘካ እንዲሰጡኝ ስለዘካ ደእዋ አድርግልኝ ያለኝ ሰው አሁን ትዝ አለኝ፤ እንዲህ ያሉት ሰዎች ሊያገቡ ሲሉ ስለትዳር ሊወልዱ ሲሉ ስለ አቂቃ ፤ ልጃቸው መንቧረቅ ስትጀምር ስለ እቃቃ፤ ከሚስታቸው ከተለዩ ስለ እቃ ፤ከሚስታቸው ጋር ሲጣሉ የባል ሀቅ ፤ እነሱ የማይመቹት ሰው እንዳለ ካወቁ ስለ ኒፋቅ ፤ጀመኣው እንደሚጠላቸው ካወቁ ሁሌ ስለ ወሬ መጥፎነት፤ወንድ ልጃቸውን ሊድሩ ሲሉ ስለ መህር መወደድ፤ሴት ልጃቸውን ሊድሩ ሲሉ ስለ ሴት ልጅ ክብር፤ቤት ሊከራዩ ከሆነ ስለ ኑሮ ውድነት፤ቤት ወይ ሱቅ ሊያከራዩ ከሆነ በአግባቡ ወሩን ጠብቆ ስለመክፈልና የሰውን ንብረት በጥንቃቄ ስለመያዝ ... አያችሁ ሁሌም ከራሳቸው ጋር ናቸው፤ ኤርፎን ያደረገ ሰው ድምፁን መመጠን እንደማችል ሁሉ ሁሉንም ነገር በራሳቸው ጥቅም ላይ ብቻ መስርተው ማንንም አይሰሙም ፤ አንድ ኮሌጅ እያለሁ በጣም ጎበዝ የሻሸመኔ ልጅ ነበር ፤አንድ ቀን ስለ ኢማሞች እያወራኝ ምን አለኝ መሰላችሁ "ወሬ ይቅርብን ..."ምናምን እያለ መስጂድ ላይ አንድ ኢማም ደጋግሞ በየጊዜው ካነሳ ጀመኣው ይጠላዋል ማለት ነው አለኝ ትከበሩ ዘንዳ መስጂዶችን አክብሩ ፤መብራት ስላልጠፋ ብቻ ማይክ አንስታችሁ አታውሩ ፤ሰው ሲከበር ካያችሁ ስለሚያወራ ብቻ አይምሰላችሁ ፤አስፈላጊ ቦታ ላይ ዝምም ስለሚል ጭምር ነው። በመጨረሻም ይህ ፁሁፍ ሰበበ ፁሁፍ ይኖረው ይሁን ? ብላችህ እራሳችሁን አታሳምሙ ፤የለውም ግን የሚገርመው ሰዎቹ በየመስጂዶቻችሁ እንዳሉ ፀሀፊው ይገምታል ሳይሆን ያውቃል
በአሁኑ ጊዜ አንድ ሰው መስጂድ ስላየሀው ብቻ ኢማሙ አህመድ እንዳይመስልህ ፤በዱንያ ጉዳይ ልብነ ድንግል ሊሆን ይችላል ፤ የሰው ሀቅ መጠንቀቅ ዲን እንደሆነ ብዙ ሰው ይዘነጋል
የአሁኑን ጁምኣ አዳማ ኹጥባ ይኖረናል የዛ ሰው ይበለን ኢንሻአላህ
የዉዱ ወንድማችን ኡስታዝ አቡ ዑወይስ ናፍያድ ቃሲም እህት ወደ አኼራ ስለሄደች ዛሬ ዙሑር ሰላት ላይ አዳማ ከተማ በሚገኘው 105 ዳሩል አርቀም መስጂድ ጀናዛ ተሰግዶ እዛው የሙስሊሞች መቃብር ቀብር ይፈፀማል። ወንድሞች እናስቀብር! إنا لله وإنا إليه راجعون! أعظم الله أجرك وأحسن عزاءك وغفر لميتك
ይህንን መልእክት አሁን አየሁና በጣም አዘንኩ ወንድማችን በቅርቡ ነበር አባቱን ወደ ኣኺራ የሸኘው አሏህ ሰብሩን ላንተና ለቤተሰባችሁ ይስጥ፤አጅራችሁን ያብዛላችሁ፤ሞት ለማንም አይቀርም ተመካሪም ያድርገን
🕌 || የጁሙዓ ኹጥባ 🏷 በደል! ከትልቅ እስከ ትንሹ 🗓 || ጁሙዓ ዐ1/12/2018 ▸ አማርኛውን ለማድመጥ -> 2:46 ---------------------------------- ▸ በኡስታዝ ዐብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ ---------------------------------- ▸ @assualihin ▸ @menhajadama
видео или голосовое, без подписи
ኡፍፍ.. መጽሐፍትን ከመገልበጥ (ከመጻፍ) እረፍት አገኘሁ! አቡ በክር አል-ደቃቅ (በኢብን አል-ኻዲበህ የሚታወቀው) ታላቅ ዓሊምና /ከአል-ኸጢብ አል-በግዳዲ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ። ስለ ራሳቸው ሲተርኩ እንዲህ ብለዋል፦ «በጎርፉ ዓመት — እርሱም በ446 ዓ.ሂ (በሂጅራ) — ቤቴ ፈረሰ። ለእኔም ቤተሰብ ነበረኝ፤ እናቴ፣ ባለቤቴና ሴት ልጄ ነበሩ። ለቤተሰቦቼ የምሰጠውን ቀለብ ለመሸፈን ስል የወረቀት ሥራ ጀመርኩ — ማለትም በወረቀት ማዘጋጀትና መጻሕፍትን በመገልበጥ ሥራ ላይ ተሰማርቼ ነበር። እንዲያውም በዚያች ዓመት ብቻ «ሶሒሕ ሙስሊምን» ሰባት ጊዜ ገልብጬ ጽፌዋለሁ! በአንዲት ሌሊትም በሕልሜ ልክ ቂያማ (የቂያም ቀን) እንደቆመ አየሁ። ጥሪ አድራጊም፦ "ኢብን አል-ኻዲበህ ወዴት አለ?" ብሎ ሲጠራ ተሰማ። እኔንም አቀረቡኝ፤ "ወደ ጀነት ግባ" ተባልኩ። በሩን አልፌ ወደ ጀነት ውስጥ በገባሁ ጊዜ፣ በጀርባዬ ተንጋለልኩ፤ አንዱን እግሬንም በሌላኛው እግሬ ላይ አጣመርኩና፦ "ኡፍፍ.. በአላህ ይሁንብኝ መጽሐፍትን ከመገልበጥ እረፍት አገኘሁ!" አልኩ።» አሏህ ሁላችንንም ጀነት ውስጥ ኡፍፍ.. ተገላላገልኩ የምንል ያድርገን
ሒጅሪ ፣ አማርኛና እንግሊዘኛ ካላንደርን ባንድ ላይ የያዘ App
የተቸገርንበት ነገር
በተደጋጋሚ ካስጠነቀቅኩት ነገር አንዱ ጊዚያዊ ፖለቲካን ከመንሀጅ ጋር አለመደባለቅ ነው፤ ዛሬ ሰኡዲያ ፖኪስታንና ቱርክ በአንድነት የጦር አንድነት ውል አድርገው አንዳችን ላይ ከተተኮሰ ሁላችንም ወደ ጦርነት እንገባለን ተባብለዋል፤ አሁን እንግዲህ ከዚህ በፊት በጭፍን እርስ በርስ ስትጣሉ የነበራችሁ ጠብ አደሮች ምን ይውጣችሁ?! ሁሌም እንደ ሙስሊም ሙስሊሞች በቁርኣንና ሀዲስ ተሳስረው አንድ ሆነው እንዲኖሩ ነው መመኘት ያለብን፤ጃሂሎች ብሎም ፍረሽ ሰለፍዮች ደግሞ ሁሉን ነገር የመንሀጅ እያደረጋችሁ በዚህ ኑሮ ኑሯችሁንም እኛንም አትበጥብጡን። ሁሌም የሙስሊሞችን ትብብር አላህ ያሳየን፤ፍሬያማም አላህ ያድርገው ፤ሁሉንም ሙስሊም ሀገራት እንወዳቸዋለን በተለይ የነቢያችንን ሀገር ከነመሪዎቹ አላህ ይጠብቅልን ፤ባጠፉበት ነገርም አላህ ያብጃቸው።