Tiriyachen | ጥሪያችን
Статистика- Последний пост
- 2 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 517
- 1/48двое суток
- 592
- 1/72трое суток
- 639
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ጥያቄ ለክርስቲያኖች °°°°°°°°°°°°°°°°°°° ኢየሱስ በምድር ላይ ሙሉ ስልጣን ካለው ታዲያ ለምን ራሱን ማስነሳት አልቻለም? 📌 ማቴዎስ 28፡18 - ኢየሱስም «በሰማይና በምድር ስልጣን ሁሉ ተሰጥቶኛል» አለ! 📌 የሐዋርያት ሥራ 3፡26 - አገልጋዩን ኢየሱስን ያስነሳው እግዚአብሔር ነው! 🤲🏻አገልገይህን (ዒሳን) ወደ እርሱ ከፍ ላደረገው አላህ ምስጋና ይሁን!! ___ https://t.me/tiriyachen
መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ ይበልጣል °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° "በሰው ልጅ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ በደሉ ይቅር ይባልለታል። በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ሁሉ ግን በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም በደሉ ይቅር አይባልለትም።" 📜ማቴዎስ 12:32 ይህ የሥላሴን ጽንሰ-ሀሳብ ያፈርሳል ምክንያቱም ሁለቱ እኩል አይደሉም ----------------------------------------------- ጥያቄ ይቅርታ አለመደረጉ የባህርይ የበላይነትን ያሳያል ወይስ የመለኮታዊ ክብርን ልዩነትን? °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° የበለጠ ለማወቅ Facebook ፦ ጥሪያችን Tiriyachen
https://tiriyachen.org/ያልተወለደ-አምላክ/
ኢየሱስ ሙስሊም ነው! አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ Telegram ፦ https://t.me/tiriyachen
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « (አማልክት) ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ 📜ቁርአን [4፥171] የበለጠ ለማወቅ ጥሪያችን Tiriyachen
ኢየሱስ (ኢሳ) እንዲህ ብሏል:- -------------------------------------- (ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡» —📍 ቁርአን (19:30) ----------------------------- አየሱስ ነቢይ ነው! ------------------------ አየሱስ እራሱን ነበይ ብሎ ጠርቷል ። —📍 በማቴዎስ 13:57 ደቀ መዛሙርቱ አየሱስን ነቢይ ብለው ጠርተውታል :: —📍 ሉቃስ 24:19 የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እና ምስክሮቹ ኢየሱስን ነቢይ ብለው ጠርተውታል፡፡ —📍 ማቴዎስ 21:11 በየቀኑ የሚለቀቁ ትምህርቶች ለመከታተል https://t.me/tiriyachen
ጂብሪል መልእክተኛነቱ ለጌታ ከሆነ ልጅን የሚሰጥ አሏህ ስለሆነ ከጌታ ይዞት የመጣው መልእክት፦ "ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ" የሚል ነው፥ "መልአክ" مَلْأَك የሚለው ቃል "ለአከ" لَأَكَ ማለትም "ላከ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው። የጌታ መልአክ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" የሚል መልእክት ከጌታው ይዞ እንደመጣ የጌታ መልአክ ጂብሪልም "ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ" የሚለውን የጌታን መልእክት ከጌታ አሏህ ይዞ የመጣ ነው። ሊአሀበ" لِأَهَبَ የሚለው የግሥ መደብ "ፊዕሉል ሙዷሪዕ" فِعْل ٱلْمُضَارِع ሲሆን የሚጠጋው ወደ አሏህ ነው፦ 42፥49 የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ "ይሰጣል" ለሚለው የገባው ቃል "የሀቡ" يَهَبُ ሲሆን "ሊአሀበ" لِأَهَبَ ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። ተግባባን? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ Facebook ፦ ጥሪያችን Tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም
የጌታ መልአክ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 19፥19 «ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፥ እኔ የጌታሽ መልእክተኛ ብቻ ነኝ» አላት፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَنَا رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَامًا زَكِيًّا "ጌታ" በግሪክ ሰፕቱጀንት"LXX" ውስጥ "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን "ዮድ ሄ ቫቭ ሔ" יְהוָֹה የሚለውን ቴትራ ግራማቶን ተክቶ መጥቷል፥ ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ" በኢ-አመልካች ውስን መስተአምር "አንጌሎስ ኩርዩ" ἄγγελος Κυρίου በሚል አሊያም "በአመልካች ውስን መስተአምር "ሆ አንጌሎስ ኩርዩ" ὁ ἄγγελος Κυρίου በሚል መጥቷል። ለምሳሌ፦ "የያህዌህ መልአክ" የሚለው "የጌታ መልአክ" በሚል መጥቷል፦ ዘፍጥረት 16፥7 የጌታ መልአክ በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው። Εὗρε δὲ αὐτὴν ἄγγελος Κυρίου ἐπὶ τῆς πηγῆς τοῦ ὕδατος ἐν τῇ ἐρήμῳ, ἐπὶ τῆς πηγῆς ἐν τῇ ὁδῷ Σούρ. እዚህ አንቀጽ ላይ "ጌታ" ለሚለው የገባው ቃል "ኩሪዮስ" κύριος ሲሆን "ያህዌህ" יְהוָֹה የሚለውን ቴትራ ግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፥ "መልአክ" ለሚለው የገባው ቃል "አንጌሎስ" ἄγγελος ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው። መልአኩ ከጌታ ይዞት የመጣው መልእክት "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም" የሚል ነው፦ ዘፍጥረት 16፥10 የጌታ መልአክ፦ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም” አላት። καὶ εἶπεν αὐτῇ ὁ ἄγγελος Κυρίου· πληθύνων πληθυνῶ τὸ σπέρμα σου, καὶ οὐκ ἀριθμηθήσεται ὑπὸ τοῦ πλήθους. "የጌታ መልአክ" ማንኛውንም ከአንዱ ጌታ አምላክ የሚላክ ሰማያዊ እና መንፈሳዊ ፍጡር ሊያመለክት የሚችል ቃል ነው። አብርሃም ልጁን ሊሠዋ የነበረው ለጌታ አምላክ ሆኖ ሳለ መልአኩ መልእክተኛ ነውና የጌታን መልእክት፦ "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" በማለት ተናግሯል፦ ዘፍጥረት 22፥11 የጌታ መልአክ ከሰማይ ጠራና፦ “አብርሃም አብርሃም፡” አለው፤ እርሱም፦ “እነሆኝ፡” አለ። እርሱም፦ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" አምላክን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ፡” አለ። καὶ ἐκάλεσεν αὐτὸν ἄγγελος Κυρίου ἐκ τοῦ οὐρανοῦ καὶ εἶπεν· ῾Αβραάμ, ῾Αβραάμ. ὁ δὲ εἶπεν· ἰδοὺ ἐγώ. καὶ εἶπε· μὴ ἐπιβάλῃς τὴν χεῖρά σου ἐπὶ τὸ παιδάριον μηδὲ ποιήσῃς αὐτῷ μηδέν· νῦν γὰρ ἔγνων, ὅτι φοβῇ σὺ τὸν Θεὸν καὶ οὐκ ἐφείσω τοῦ υἱοῦ σου τοῦ ἀγαπητοῦ δι᾿ ἐμέ. "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" የሚለው መልእክት ከጌታ በመልአኩ የተላለፈ መልእክት መሆኑን የምንረዳው ይህ የጌታ መልአክ ለአብርሃም ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠርቶ “ጌታም፦ ‘በራሴ ማልሁ፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" ይላል" ማለቱ ነው፦ ዘፍጥረት 22፥15 የጌታ መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥ እንዲህም አለው፦ “ጌታም፦ ‘በራሴ ማልሁ፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" "ይላል"። καὶ ἐκάλεσεν ἄγγελος Κυρίου τὸν ῾Αβραὰμ δεύτερον ἐκ τοῦ οὐρανοῦ, λέγων· κατ᾿ ἐμαυτοῦ ὤμοσα, λέγει Κύριος, οὗ εἵνεκεν ἐποίησας τὸ ρῆμα τοῦτο, καὶ οὐκ ἐφείσω τοῦ υἱοῦ σου τοῦ ἀγαπητοῦ δι᾿ ἐμέ, "ይላል" የሚለው ይሰመርበት! መልአኩ "ይላል" ካለ "አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" ያለው ጌታ አምላክ ነው፥ አስተላላፊው ደግሞ የጌታ መልአክ ነው። "አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና" መልእክቱ የላኪው እንጂ የተላኪው አይደለም። አብርሃምን ከሰማይ "አብርሃም" ፍጡር መልአክ መሆኑን ኩፋሌ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦ ኩፋሌ 14፥13 በሰማይም ሆኜ “አብርሃም፥ አብርሃም” ብዬ ጠራሁት። እርሱም ደንግጦ፥ “እነሆ፥ እኔ አለሁ” አለኝ። ወደ አዲስ ኪዳን ስንማትር የጌታ መልአክ ወደ ዘካርያስ የተላከ መልአክ ነው፥ ይህም መልአክ "እኔ በአምላክ ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" ብሎአል፦ ሉቃስ 1፥11 የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው። ሉቃስ 1፥19 መልአኩም መልሶ፦ “እኔ በአምላክ ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር። ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ" የተባለውን ሁሉ ለኢየሱስ የሚሰጡ ሰዎች አዲስ ኪዳን ላይ ገብርኤል "የጌታ መልአክ" መባሉን ሲያውቁ ምን ይውጣቸው ይሆን? ይህ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም የታየው ነው፦ ማቴዎስ ፥1፥20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው። ይህ ጥቅስ የጌታ መልአክ ኢየሱስ ሳይሆን ሰማያዊ ፍጡር የሆነ መልአክ ነው፥ የጌታ መልአክ ኢየሱስ ሲወለድ ለማብሰር መጥቶ ነበረ፦ ሉቃስ 2፥9 እነሆም "የጌታ መልአክ" ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። የጌታ መልአክ ሰብአ ሰገል ከሄዱ በኋላ እና ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶታል፦ ማቴዎስ 2፥13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ማቴዎስ 2፥19 ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦ ኢየሱስ በሚያገለግልበት ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበር፦ ዮሐንስ 5፥4 አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና። የጌታ መልአክ በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ ሐዋርያትን አወጣቸው፣ የጌታም መልአክ ፊልጶስን አናገረው፣ የጌታ መልአክ ጴጥሮስን አናገረው፣ የጌታ መልአክ ሄሮድስን መታው በትልም ተበልቶ ሞተ፦ የሐዋርያት 5፥19 የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና። የሐዋርያት 8፥26 የጌታም መልአክ ፊልጶስን፦ "ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ፡፥" አለው። የሐዋርያት 12፥7 እነሆም የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፥ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና፦ "ፈጥነህ ተነሣ" አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። የሐዋርያት 12፥23 ለአምላክ ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ ኢየሱስ ነው" የሚል በቀጥታ ሆነ በተዛዋዋሪ ማስረጃ እና መረጃ የለም፥ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊያን "ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ" የተባለው ኢየሱስ ነው" ብለው በቀጥታ ሆነ በተዛዋዋሪ ስላልተናገሩ "የጌታ መልአክ ኢየሱስ ነው" የሚለው ንግግር ምናባዊ ቅዠት እንጂ ነባራዊ እውነታ አይደለም። በቁርኣን "የጌታ መልአክ" ጂብሪል ነው፦ 19፥19 «ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፥ እኔ የጌታሽ መልእክተኛ ብቻ ነኝ» አላት፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَنَا رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَامًا زَكِيًّا
без подписи
ክርስቲያኖች ሆይ! ኢየሱስ ያመለከው አምላክ አምልካችሁ ለመዳን ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
ያዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ ከኔ በኋላ ማንን ትገዛላችሁ ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? (እነርሱም) አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለርሱ ፍፁም ታዛዦች ኾነን እናመልካለን አሉ፡፡ ቁርአን (2፥133)
ጥያቄ ለክርስቲያኖች °°°°°°°°°°°°°°°°°°° ኢየሱስ በምድር ላይ ሙሉ ስልጣን ካለው ታዲያ ለምን ራሱን ማስነሳት አልቻለም? 📌 ማቴዎስ 28፡18 - ኢየሱስም «በሰማይና በምድር ስልጣን ሁሉ ተሰጥቶኛል» አለ! 📌 የሐዋርያት ሥራ 3፡26 - አገልጋዩን ኢየሱስን ያስነሳው እግዚአብሔር ነው! 🤲🏻አገልገይህን (ዒሳን) ወደ እርሱ ከፍ ላደረገው አላህ ምስጋና ይሁን!! ___ Facebook ፦ ጥሪያችን Tiriyachen
ታዲያ ለምን ይሆን ክርስቲያን ሴት ተገላልጣ በጎዳና ላይ የምትሄደው?
ዲኑል ኢሥላም በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ አምላካች አሏህ በተለያየ ዘመነ መግቦት"dispensation" መልእክተኛ ልኳል፥ ያ የሚላከው ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ አማኞች ሊታዘዙት እንጂ አልተላከም፦ 4፥64 ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ "ኢዝን" بِإِذْن ማለት "ፈቃድ" ማለት ሲሆን አንድ አማኝ የተላከው መልእክተኛ መታዘዝ የአሏህ ፈቃድ ነው፥ በዚህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ሉጥ፣ ሹዕይብ፣ ዒሣ ወዘተ "ታዘዙኝ" በማለት ይናገራሉ፦ 26፥108 26፥126 26፥144 26፥163 26፥169 3፥50 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዘዙኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑኒ" أَطِيعُونِ ነው፥ አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ እንዳለብን ሲናገር "መልእክተኛውን ታዘዙ" በማለት ነው፦ 24፥56 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልእክተኛውን ታዘዙ! ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑ" أَطِيعُوا እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰዎች ለአሏህ "ታዘዙ" የተባሉበት ትእዛዝ ግን ለእርሱ ብቻ አምልኮታዊ መታዘዝ ነው፦ 22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ! ለአሏህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ "አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" ካለ በኃላ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ" በማለት ያስቀምጣል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን ለእርሱ በብቸኝነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፦ 39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ!፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት እራሱ "መታዘዝ" ማለት ነው፦ 3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ለአሏህ ብቻ በውጥን የሚደረግ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፥ "ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው። "ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ" "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ነው። አንድ ማንነት ለአሏህ ብቻ በአምልኮ ሲታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይባላል፦ 3፥84 «እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ 2፥136 «እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ 29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው፥ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት በነጠላ "ታዛዥ" ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥሩ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው። ታዲያ ቀደምት ነቢያት ሙሥሊሞች አይደሉምን? ዲናቸውስ "ፈጣሪ አንድ አምላክ ነው" ተብሎ ፈጣሪን ብቻ በአምልኮ መታዘዝ አይደለምን? እንዴታ። ወደ እኛም የተወረደው እና ወደ መጽሐፉ ሰዎች የተወረደው ግልጠተ መለኮት ጭብጡ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፦ 21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ አሏህ ከጥንት ጀምሮ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሎ ለሚልከው ነቢይ የሚገልጠው ይህ ግልጠት ነው፥ "የምናወርድ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑሒ" نُوحِي ሲሆን የሚወርድለት "ወሕይ" وَحْي ነው። ስለዚህ የቀደሙት ነቢያት ሙሥሊም ነበሩ፦ 5፥44 እነዚያ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በእርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا በግሥ መደብ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን በስም መደብ "ሙሥሊም" مُسْلِم ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፦ 3፥64 በል፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ ይህቺ የጋራ ትክክለኛ ቃል አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው፦ 3፥64 እርሷም፦ "አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው"። أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ "ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር "አርባብ" أَرْبَابً ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። አሏህን በአምልኮቱ እና በጌትነቱ መታዘዝ ኢሥላም ሲሆን ይህንን ሐቅ ካስተባበሉ ሑጃህ እንዲቆምባቸው እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፦ 3፥64 ምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ" በሏቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! ሙሥሊም አድርጎ ወደ እርሱ ይውሰደን! አሚን። ✍ ከወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም ጥሪያችን Tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም
без подписи
https://tiriyachen.org/ሕይወትን-መስጠት/
ቪድዬ ተለቋል https://vt.tiktok.com/ZSQDvdwHD/
ተጸጸተ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦ 65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ አሏህ አንድ ነገር ከመከሰቱ፣ ከመሆኑ፣ ከመደረጉ፣ ከመከናወኑ በፊት ያለውን ሩቅ ነገር እና አንድ ነገር ከተከሰተ፣ ከሆነ፣ ከተደረገ፣ ከተከናወነ በኃላ ያለውን ግልጹን ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፦ 64፥18 ሩቁን ነገር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ "አማሬ ኲሉ" ማለት "ሁሉን ዐዋቂ" ማለት ነው፥ መለኮት "ሁሉን ዐዋቂ" ነው። በባይብል አንዱ አምላክ "ሁሉን ዐዋቂ" ነው፦ 1 ዮሐንስ 3፥20 አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና "ሁሉንም ያውቃል"። ὅτι μείζων ἐστὶν ὁ Θεὸς τῆς καρδίας ἡμῶν καὶ γινώσκει πάντα. ቅሉ ግን አንድ ማንነት በሠራው ሥራ ከተጸጸተ ያንን ሥራ ከመሥራቱ በፊት ስለማያውቅ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። ለምሳሌ፦ ሰው በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፦ ዘጸአት 13፥17 አምላክ፦ "ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው እና ወደ ግብፅ እንዳይመለስ" ብሎአልና። אָמַ֣ר אֱלֹהִ֗ים פֶּֽן־יִנָּחֵ֥ם הָעָ֛ם בִּרְאֹתָ֥ם מִלְחָמָ֖ה וְשָׁ֥בוּ מִצְרָֽיְמָה׃ እዚህ አንቀጽ ላይ "እንዳይጸጽተው" ለሚለው የገባው ግሥ " ፐን ዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው። የእስራኤል ሕዝብን የፈርዖንን ሠራዊት ሰልፍ ባየ ጊዜ ከግብፅ መውጣቱ ጸጽቶት ወደ ግብፅ መመለስ ከከጀለ በመውጣቱ ይጸጸት ነበር፥ የእስራኤል ሕዝብን ሰው ስለሆነ የወደፊቱን ሰማያውቅ በሠራው ሥራ ሊጸጸት ስለሚችል ፈጣሪ እንዳይጸጸቱ መክሯቸዋል። ሰው የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስላልሆነ በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፥ የሰው ተቃራኒ አምላክ ደግሞ የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስለሆነ በሚሠራው ሥራ አይጸጸትም፦ ዘኍልቍ 23፥19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ አምላክ ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። לֹ֣א אִ֥ישׁ אֵל֙ וִֽיכַזֵּ֔ב וּבֶן־אָדָ֖ם וְיִתְנֶחָ֑ם 1 ሳሙኤል 15፥29 የእስራኤል ኃይል አይዋሽም አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና። וְגַם֙ נֵ֣צַח יִשְׂרָאֵ֔ל לֹ֥א יְשַׁקֵּ֖ר וְלֹ֣א יִנָּחֵ֑ם כִּ֣י לֹ֥א אָדָ֛ם ה֖וּא לְהִנָּחֵֽם׃ ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መጸጸት" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ከዚያ በተቃራኒው ያህዌህ በሠራው ሥራ እንደተጸጸተ ባይብሉ ይናገራል፦ ዘፍጥረት 6፥6 ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም እጅግ አዘነ። וַיִּנָּ֣חֶם יְהוָ֔ה כִּֽי־עָשָׂ֥ה אֶת־הָֽאָדָ֖ם בָּאָ֑רֶץ וַיִּתְעַצֵּ֖ב אֶל־לִבֹּֽו׃ እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጸጸተ" ለሚለው የገባው ግሥ "ይዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው፥ ያህዌህ የተጸጸተ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ነው። የሠሩትን ወንጀል ዓይቶ "ከመነሻው ሰው መፍጠር አልነበረብኝም" ብሎ በሠራው ሥራ ተጸጸተ፥ መጸጸት ለሁሉን ዐዋቂ አምላክ የተገባ ባሕርይ አይደለም። በእርግጥ "ናኻም" נָחַם የሚለው ቃል "ተጸጸተ" ብቻ ሳይሆን "አዘነ" "ራራ" "አጽናና" "ረዳ" "ተቆጣ" የሚል ፍቺ ይኖረዋል፥ ይህንን ይዘን፦ ፨"ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አዘነ" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ራራ" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አጽናና" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ረዳ" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ተቆጣ" ትርጉም ይሰጣልን? እራሱ በሠራው ሥራ ማዘን፣ መራራት፣ መጽናናት፣ መርዳት፣ መቆጣት ትርጉም አይሰጥም፥ ነገር ግን እራሱ በሠራው ሥራ ተጸጽቷል። ይህ የፈጣሪ ባሕርይ በፍጹም አይደለም፥ "አምላክ ይጸጸት ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም" "እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም" ከሚሉት አናቅጽ ጋር ከመጋጨት አልፎ በመላተም ይፋጫል። የሚያሳዝነው "ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ" ብሎ የሚነግረው ያህዌህ ወይም ሙሴ ሳይሆን ማንነቱ በውል የማይታወቅ ሰው ነው፦ ዘፍጥረት 6፥7 ያህዌህ፦ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና” አለ። እሺ ሰውስ ስላጠፋ አምላክ ሰውን በመፍጠሩ ጸጸተ እንስሳ፣ ተንቀሳቃሽ እና የሰማይ ወፍ ምን አድርገው ነው እነርሱ ስለ መፍጠሩ የተጸጸተው? ይህ ውሉ የማይታወቅ ሰው ንግግር ይዘን እንደ አምላክ ቃል መሞገት አግባብ አይደም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ Facebook ፦ ጥሪያችን Tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም
без подписи
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”። 📜ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53