Охват к подписчикам
36,7%
ERR
Реакции к просмотрам
2,02%
218 на 23 постов
Пересылки к просмотрам
0,59%
64
Постов в день
0,3
всего 23
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 1 авг. 2024 г.без подписи9,39%
- 11 авг.<<<<<<<100>>>>> ስጠን (keysopia) ክረምቱም ገባ በጋም ደና አደረ ዝናብ ደጄ ጥሎ ጎርፍ አወዳደረ። አሁን ምን ይዋጠን ቀኝ አርጎ ፈጥሮ ፡ ግራውን ካልሰጠን። በዘመድም ይሁን ፣ በባዳ ጥቆማ በጠለፋም ይሁን ፣ ከተገኘች ቆማ በድግስም ትምጣ ፣ ወይ በሀዘን ድንኳን ችለነው እንድንቀዝፍ ፣ ተለዋዋጭ መልኳን ዝናቡን ለማለፍ ፣ የምትሆን ጥላ ሙቅ እሳቷን ላግኝ ፣ ከሰማይ ተጥላ። @keysopia✍️ @getembate @getembate4,79%
- 14 авг.(ጥላዬ)@ከይሶፕያ እሳት ናት ነበልባል ንፋሱ ስር ስትሰርግ ፣ መንፈሷ ይስባል። ደመና ነው የጥጥ ክምር ዳብሰው ያላሻሹት ፣ የባዶነት ድምር። መልኳን እረሳሁት ፣ ጠፋኝ አቅጣጫዋ ጀንበር ምስራቅ ሆኖ ፣ መግቢያና መውጫዋ። ወዳጅ እንደከዳው ብርቱ ብላቴና፣ ይቅር አልኳት ዳግም በነፍሴ አንቴና። መዳፌን ዘረጋሁ አቅፌያት አለሜን ፣ በስስት ልቃኘው አዲስ ስም ሰጠሁት ፣ አምናዬን ላገኘው። ፡ እያሰብኳት ፀለመች : እያየኋት ታመመች : ፀደይ ወራቱ ላይ እንደ ጤዛ ማልዳ፣ አሸክማኝ ሄደች አዲስ ፍቅር ወልዳ። : ባለ ጥላው ኮፈን ሰውሮ ቢያስቀራት ፣ እንደ ጉም በትኖ ይኖራል ዘላለም በቃል የታሰረ ፣ የትም ሀገር ኳትኖ። ቲች😭 @getembate @getembate4,00%
- 12 авг.ለእህታችን ቻሌንጅ! 10 ብር ለአንድ ሰው ትንሽ ቢመስልም ስንበዛ ግን ከኛ የወጣው 10 ብር ለሌላ ሰው ህይወቱን ማትረፍ ሊሆን ይችላል ከ10 ብር ጀምረን መላክ የምንችለውን እንላክላት... ለእህታችን እንድረስ❤️ CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay በእኛው እድሜ ያለች ወጣት ነች እንርዳት 🥺 ይህ Post ከ24 ሰዓት በኋላ ይደለታል፡፡ እስከዛ እያስገባችሁ ለጓደኞቻችሁ Share አድርጉ፡፡ ያስገባችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን🙏 ይህቺን ተጫኗት 👉 ❤️ [ ያስገባችሁ ብቻ]3,01%
- 7 авг.ትንሣኤሽን ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። እንኳን አደረሳችሁ🙏 ✍ዔደን ታደሰ @getembate @getembate2,34%
- 22 июн.<<<<<<<<<96>>>>>>>> ለእናቴ! ፍጡር ብቻ አይደለሽ ፥ የሞት ሲሳይ ቀማሽ ህይወት ነሽ ፣ ለሰማሽ ብፁህ አንቺነትሽ ፥ ስጋ ለበስ ፍጡር ሰውነት ላይ ፀንቷል ፥ በኖርሽበት ቁጥር። ያለ ምስራቅ ጀንበር ፣ ያለ ሰማይ ኮከብ ማዕበል ላይ የሚጓዝ ፥ ታምረኛ መርከብ። ካማጥሽኝ አንስቶ ፥ እስከ ጡትሽ ወተት ድግምት የማይሰብረው ፥ ይዞኝ አንድ መተት። እንደ ዛፍ አደኩ ፥ እንደ አበባ ፈካሁ ከእቅፍሽ ስር ነቃሁ ፥ በሌላም ተተካሁ። ምስኪን ነበርሽ.... ከመከራሽ ጋራ የምትታገዪ አይኖቼ ስር ገብተሽ ብርሃን የምታዪ ምስኪንማ ነበርሽ.... ሁሉም የሚሰብርሽ ካንቺ ደስታ በላይ ፥ ስቃይ የሚቀርብሽ። ወድቄ እንዳልቀር ፥ መኖር ከኔ ገዝፋ ከህመም ባታስጥዪኝ ፥ ሰተሽኛል ተስፋ። እማዬ አለሜ ፥ እማ የልቤ ወዳጅ ጦር ሜዳ ዘምታለው ፥ አንቺን መውደድ ቢሆን ፥ የአላማዬ ግዳጅ። እናቴ ስለሆንሽ እኮራለሁ!!!! @ከkeysopia @getembate @getembate2,20%
- 28 янв. 2025 г.без подписи1,63%
- 9 июн.6ትናንሽ ታሪኮች ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 1 በአንድ ወቅት በአንድር መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ፀሎት ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ፀሎቱ በሚያደርጉበት ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዙ ተገኘ፡፡ (ይህ እምነት ይባላል፡፡) ፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 2 ህጻን ልጅህን ወደላይ እየወረወርህ ስታጫውታት በደስታ ትፍነከነካች እንጂ አታለቅስም ፡፡ምክንያቱም መልሰህ እንደምትቀልባት ታውቃለችና!! ይህም እርግጠኝንት ይባላል፡፡ ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 3 በእያንዳንዱ ምሽት ወደ አልጋችን ስንሄድ በነገው ማለዳ በህይወት እንደምንቆይ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባይኖረንም አላርም(የማንቂያ ደወል) ሞልተን እንተኛለን!! ይህም ተስፋ ይባላል፡፡ ፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 4 ወደ ፊት ምን እንደምንሆን (እንደሚሆን)እውቀት ሳይኖረን ታላላቅ እቅዶችን እንነድፋለን!!! ይህ ደሞ በራስ *,መተማማን ይባላል፡፡** ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 5 ዓለም ላይ የሚወርደውን መከራና ስቃይ እናያለን ይሁን እንጂ አሁንም እንጋባለን ይህም ፍቅር ይባላል፡፡ ፣፣፣፣፣፣ 6 አንድ ሽማግሌ በለመበሰው ቲሸርት ላይ እንዲህ የምትል አንዲት ጉሩም ዐረፍተ ነገር ተጽፋለች “እኔ የስድሳ ኣመት ሽማግሌ አይደለሁም ፣የአርባ አራት ኣመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የአስራ ስድሰት ኣመት ወጣት እንጂ” ይህ ለራሳቸእን ያለንን አመለካከት ያሳያል፡፡ ፣፣፣፣ መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!! እምንት ፣እርግጠኝነት ፣ተስፋ ፣በራስ መተማማን ፣ ፍቅርና ለራሳችሁ ጥሩ አመለካካት ሳይለያችሁ ኑሩ !!! @getembate @getembate1,44%
- 17 июн.<<<<<<<<<<94>>>>>>>> (የሸለቆ ውበት..) የሺህ ዘመን ተስፋ ፥ ባንድ ቃል ፈርሶ፣ ሁሉም ከጨከነ ፥ የደም በቀል ወርሶ። ከደናግል መሀል ፥ እርጉዝ ሴት ተነስታ፣ ለምድር ጭፍሮች ፥ የሞት አክሊል ነስታ። ጭጋጉ ስር ሸሽታ ፥ እንደምትኖር መንፈስ፣ ደስታ ሳትል ሀዘን ፥ እንደልቧ ስትፈስ። ጭንቅ ምጧ መቶ ፥ ጊዜ ወርቋን ንዶ፣ ጭኗን አስከፈተው ፥ ሰው መሳዩ ዘንዶ። ድምፅ አልባው ጅረት ፥ በንፋስ ዳንስ ስር፣ ሀሳብ ልቡን ቃኝቶ ፥ እልፍ አለሙን ሲያስር። የሸለቆ ታላቅ ውበት ፥ እንደመፍካት ባዲስ ፋና፣ አክ ተብሎ እንደምራቅ ፥ እመንገድ ላይ ተተፋና። ዳግም ክንፍ አብቅሎ ፥ ባይችል ጎጆ መስራት፣ ጎዳናው ላይ አንቀላፋ ፥ ህልሙ ውስጥ ሊኖራት። @keysopia @getembate @getembate 1,22%
- 5 авг.ውሰደን እንዳንል ቅጣትህ አስፈራን፥ አኑረን እንዳንል ኖረን ምን አፈራን፥ ፀሎቱ ጠፍቶናል በፈለከው ምራን። By andina @getembate @getembate1,18%
- 27 июл.<<<<<<<<<<99>>>>>>>> እንጃ... አሁን ነው በኋላ ጨለማ ነው ጥላ ክብር ወይስ ንቀት ዕድገት ወይስ ውድቀት እንጃ.... ማብቂያ ወዴት አለ..የታል አዲስ ጉዞ ይኬዳል ባዕድ አገር ..ሙት ገላ ተይዞ ዝምታ ውስጥ ታስራ..የተሰጠች ታጭታ ቅፅበት ነበር ሁሉም..የብርሀን ብልጭታ። @keysopia @getembate @getembate1,16%
- 6 июн.ሰበበኛ <<<<<<<<<<93>>>>>>>> ባይገባት - ወንድነት የከዳው ፥ ገላ ተሸክሜ፣ በኑሮ ውጣ ውረድ ፥ አናቴን ኮርክሜ። ክፉ አትዪ ብዬ ፥ ሀዘኔን ብደብቅ፣ ጠላኝ ብላ አሰበች ፥ እኔ እሷን ስጠብቅ። ከተሻለ ብዬ ፥ ሳደርግ ነገን ተስፋ፣ በማይሆን ኩነኔ ፥ ስሜን አስቀስፋ። እንደ ኮብላይ ሽፍታ ፥ አርጓት ሽብር ሽብር ቁጣ ቁጣ ሸቷት ፥ ስትሆን እንደነብር። ንፋስ እንዳመጣ ፥ እንደቆሼ ብናኝ በቅዠት ማዕበል ፥ ግራ ገብቶኝ ስናኝ። ንዴት ይሁን እብደት ፥ ውስጤን እያጋለው፣ መዳፌ ስር ፌቷን ፥ አሳልፎ ጣለው። ያልታሰበ ጥፊ ፥ ፊቶቿ ላይ አርፎ፣ ሌቱም ዳግም ነጋ ፥ ባንድነት ተኳርፎ። በንቅሳት ቀለም- ደረት ላይ ያተሟት ፥ የትዝታ ምስል፣ በቻሏት ቁጥር- ሳቆችን በርዛ ፥ ነፍሴን ስታቆስል። መንፈሴ በአንድ ቃል ፥ ከቋጠረው እሳት፣ እፍ አልኩባት- ከህመሜ ቁራሽ ፥ እሷም እንዲደርሳት። @keysopia @getembate @getembate 0,95%