ግጥም
описание
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
5 226
подписчиков
Охват к подписчикам
38,8%
ERR
Реакции к просмотрам
1,05%
424 на 20 постов
Пересылки к просмотрам
0,46%
186
Постов в день
0,4
всего 21
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 10 авг.#ያኔ_እንዳደረግነው!!! እንታረቅ ውዴ በትንሽ ጣታችን በለመድነው ኩርፊያ በልጅነታችን ቂም በማይቋጥረው በለጋነት ውበት ያኔ እንዳደረግነው ጥልቅ የፍቅር ስሜት ዛሬም እንድገመው ጣልቃ ሳናስገባ በትንሽ ጣታችን እኛው እንግባባ ኩርፊያችን የፍቅር ይቅርታችን ከምር የልጅነታችን በትንሽ ጣታችን ዛሬም እንታረቅ እሽ በይኝ ውዴ ቂም መያዝሽን ተይ ይቅር መናደዴ መጣላታችንን ማንም ሰው ሳይሰማ እንደጥንቱ ዛሬም እኛው እንስማማ ጣትሽን ሳሚልኝ ጣቴን እስማለሁ ፈገግ በይልኝ እኔም እስቃለሁ አድገን እንድገመው ያለሽማግሌ ስሜትሽ ስሜቴ አካልሽ አካሌ! የውሸት ተጣልተን የምር እንታረቅ በንጹህ ፈገግታ ጥርሳችን ይፍለቅለቅ አምላክም ብሎናል ህፃናት ምሰሉ መጽደቅን ብትሹ ቂም አታንከባሉ ልባችን የልጆች እድሚያችን የትልቅ እንታረቅና እኛው ለኛ እንሳቅ!! አምጭ ትንሿን ጣት እኔም ልጎትታት ፍቅር ማለት ለካስ ያኔ ነበር የእውነት በከንፈር ተኳርፎ በጣት ለመግባባት ያኮረፈን ከንፈር ፈልቅቆ ማላቀቅ ያለሽማግሌ ተግባብቶ መታረቅ!!! @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ2,49%
- 29 июл.#ልብ_ነው_ዘመኑ!! ጥርሴን አትመኑት ቢስቅ ውሸቱን ነው የልቤን ውስጥ እሳት እያዳፈነ ነው አልፋችሁ ከልቤ ግቡና መርምሩት ከደጅ ቆማችሁ ሳቄን አትመኑት ባለቅስም አትስሙኝ እንባን አትመኑ የሰው ልጅ ከተማ ልብ ነው ዘመኑ ምላሴንም ተውት ይወትውት ይናገር የሁሉም ከተማ ልብ እኮ ነው ሐገር ብደሰት ብከፋ ምንጩ ከልቤ ነው የሚታየው አካል እያስመሰለ ነው ልብን ተረዱና ልትረዱት ሞክሩ ከውስጥ ይነሳል ሰው የመሆን ክብሩ ይስቃል አትበሉ ጥርስማ ያገጣል አዘነም አትበሉ ፊት ድንገት ይጠቁራል የሰው ልጅን ማወቅ ከልብ ይጀምራል ገፅታ ከንቱ ነው ይገለባበጣል!!! @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ2,05%
- 12 авг.#ያማል ራሴን ልሰጥክ ወስኛለሁ ብላ፤ ማታ ቀጠረችኝ ከለመድናት ቦታ። ሰአቴን ጠብቄ ከቦታው ተገኘሁ፤ ቃሏን እያሰብኩኝ ትእዛዝ እየሰጠሁ፤ ጥቂት እንደቆየሁ እሷ መጣችና፤ በምግብ በመጠጥ ትንሽ ጠገብንና፤ ወደክፍሉ አመራን ወደያዝነው አልጋ፤ በፍቅር ቀለጥን ለሊቱ እስኪነጋ። ይሄ ውብ ቃላችን እራስን የመስጠት፤ ችግር መሃል ገብቶ ቃልን በቃል ሲያስት፤ በቃ አልፈልግህም ሂድልኝ አለችኝ፤ ለካስ የዛን ምሽት፤ አካሏን ነው እንጂ መች ልቧን ሰጠችኝ። የስሜቱን ነገር እንደውለታ ቆጥራ፤ ችግሩ ሲፈጠር ቀረች ተሰውራ። ችግሩ ምንድነው መባል ስለማይቀር፤ ልናገር (HIV)፤ positive ነኝ እኔ በውልደቴ ጀንበር፤ በእኔ ጥንቃቄ፤ ጤነኛ መሆኗን እርግጠኛ ስትሆን፤ እራሷን ልሰጠኝ ቃሏን እንዳልሰጠች፤ ህመምህ ህመሜ ብላ እንዳላለች፤ የፍቅርን ትርጉም እሷ መች አወቀች፤ ለወደዱት መሞት እሷ ስላልቻለች፤ መልካም ናት አውቃለሁ እርቃኝ ሄዳለች፤ ሌላ አፍቃሪ እንዲሞት እድሉን ሰጥታለች፤ ፍቅርን ለሞት ጥላ ሸሽታ ኮብልላለች፤ ቀድማኝ እንደማትሞት ግምቷን ሰጥታለች። አንድ ቀን ሲገባት፤ የማይገኝ ፍቅርን መሞት እንደቀማት፤ ሞት ግን ስለማይቀር ያማል ፍቅር ማጣት። @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ1,68%
- 27 июл.የልቤ ባልኩሽ ሰው በድንገት ብከዳ ብዙም እንዳላዝን ብዙ እንዳልጎዳ… አንቺም ድንገት ነገ ፤ “የልቤ” ባልሽኝ ሰው በኔ ብትከጂ ብዙ እንዳተክዢ ብዙ እንዳትጎጂ። አየሽ… ከ እልፍኝ ያልዘለቀ ቀርቶ ከ በረንዳ ደፍሮ አይጎዳም ባዳ። ይልቅ… ከ በረንዳ አልፎ ከ እልፍኝ የዘለቀው ሽራፊ ሳትቀር ገመናን ያወቀው የልብ ያሉት ሰው ነው… በክህደት መዶሻ ልብን የሚያደቀው። @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ እዮብ ዘ ማርያም1,55%
- 2 авг.#ጎዳናው_ይገርማል?! ይገርማል መንገዱ እግረኛው ይገርማል ሸራ ጫማ ባ'ይነት በነጫጭ ካልሲ በሲኪኒ ሱሪ ከመምህሩ ጋራ አይስክሬም ሚልስ የሀይስኩል ተማሪ ፀባይኛ ወጣት ጃንቦ ተከልሎ በምርቃና ሆኖ ሀሳብ የሚፈትል አንዲት ሙ......ደኛ እናት በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል ፒዛውን የሚገምጥ ጭማቂ የሚመጥ አራዳ አባወራ በሚስቱ ትከሻ በልጆቹ ምላስ ቅምጥ የሚጣራ አንድ ፍሬ ሴቶች በተገዛ ቅንድብ በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ ማኪያቶ ከበው ለውስኪ ሚንጫጩ ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ.... ድንቡሽቡሽ ህፃናት በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ ቀልባቸው የከሳ በአይፎኑ አጮልቆ ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ ቀውጢ ዳያስፖራ የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው ነቄ ብላቴና ከዮፍታዬ ቀዬ ካ'ዲስ አለማየሁ ከመዝገቡ መንደር የአዲስ አ'ባ ጥሪ በቁምጣ ያበረረው ከቅኔ ተጣልቶ ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው ፀዴ ብላቴና ከባላገር ዘመን ከጨለማ ዘመን ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ ነብሱ እየሰለለች በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ ሲያዘግም የሚውል ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ ፎቆቹ በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው ሁሉም ...... ሁሉም ከዘለለት ጥድፊያ ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው የ'ድሜ ክቡር ጀንበር በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው ቆጥራለው.....ቆጥራለው ቆጥራለው አዛውንት በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ ቆጥራለው በ'ያደባባዩ የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል ጥያቄ የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ ባጣበበው መንገድ እንደምን ይቻላል ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ? ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ በተሰራ መንገድ እውነት ቀላል ነው ወይ ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ? ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ በተሰራ መንገድ እንደምን ይቻላል ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ? አያት....አያት...አያትነት ማለት በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት .....................................የሚታደስ እውነት አያት ሆኑ ማለት ድርብ አባትነት ድርብ እናትነት በተለይ እዚህማ....... በዚህች አይነት ሀገር ጎጆዋን ላቆመች በተጋድሎ ካስማ ባርበኝነት ማገር በዚህች አይነት ሀገር ጥያቄና መልሷን ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር በዱአ በፀሎት በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር! ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው እላለው... እላለው.... የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና መንገዱ አይልቅም ጎዳናው አያልቅም ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል እግረኛው ሞኝ ነው ሳንቲሙን ዘርዝሮ ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል መንገዱ ያስፈራል መንገዱ ይጨንቃል ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው አያት እምባ ይጨምቃል መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ? እላለው........እላለው ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው ጥያቄ እጥላለው እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ? በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን ከሆነ እጣችን ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን ግድ የለም እንመን እንመን በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ በልጅ ልጆች ዓለም እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን አባት ሆይ ለልጆችህ ርዕዮት ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት ከልጅህ አንደበት ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም ከልጆችህ ባህር አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ እፅዋት ተክሎች እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ ግድ የለም እንመን........እንመን የስኬት ክብደቱ የምቾት አይነቱ የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር ጀግና ልጅ አትወልድም አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር ከፎቆቹ ጥላ.... ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ ይኸው አነበብኩት አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ በመኪና ብዛት በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ በግንብ አጥር መአት በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ ይኸው ይታየኛል አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ ...................ተስሏል ሽንፈቴ! @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ በረከት በላይነህ1,46%
- 6 авг.ተጋፈጥኩ መከራዬን ተፋላምኩ ፈተናዬን ኃይሌን ጨረስኩ እንጂ መች አገኙሁ ውጤት እኔ አለቅኩ እንጂ መች በቃሁ ለስኬት ሩጫዬን ገታሁ አቆምኩ ትግሌን ላፍታ ቃኘሁት ድክመቴን የሽንፈቴን ቃታ ለካ ብቻዬን ነው ምጓዝ እርቃኔን ወጥቼ መከታ ጋሻዬን ረዳቴን ትቼ ለካ ውልክፍክፍ ስንኩልኩል ነበር አሯሯጤ እውር ድንብር ነበር ሚወነጨፍ ውስጤ ለካ በዜሮ ተባዝቷል ሙከራ ጥረቴ አንቺን ሳልይዝ ሂጄ ድንግል እመቤቴ አፈገፈግኩ ወደ ኋላ ተመለስኩ ወደ ቀልቤ ሰአሊ ለነ እያልኩ ታጠቅኩሽ በልቤ ይኸው ነጻ ጥርጊያው ይኸው ቀና መንገዱ ገና ሳልጠጋው ሲያዘቀዝቅ አየሁ የመከራ ቀንዱ @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ኤልዳን1,46%
- 11 июл.#ትቀሪያለሽ_ብየ... ግድየለሽምና ፥ ከልብ ላፈቀረሽ ሶስቴ ተቀጣጥረን፥ አራት ጊዜ ቀረሽ። ዛሬም እንደ ወትሮው፥ ትቀሪያለሽ ብየ እድል የላከውን፥ እጣ የሚመስል፤ እጦት ተቀብየ፥ አበባ ሳልቀጥፍ አልጋ ሳላነጥፍ ሙታንታየን ሳልጥፍ በትራስጌየ ላይ ፎቶሽን ሳለጥፍ፥ ትቀሪያለሽ ብየ፥ በመስታውቴ ፊት ከልብ አስቀይሜ አንድ እፍኝ ነጭ ሽንኩርት እንደ ተልባ ቅሜ አየሩን መርዤ፥ ህዋሴን አክሜ፤ ትቀሪያለሽ ብየ፥ ጥፍሬን ሳልከረክም በመቀስ ሳልንደው፥ የጉያየን ሸክም ትቀሪያለሽ ብየ ጀንበርን ቀድሜ፤ ቤቴ ተከትቼ ግቤን ያለ ረዳት፥ በጊዜ መትቼ የከሸፈ ትውልድ አንሶላ ላይ ትቼ ልተኛ ስዘጋጅ፥ እፎይ ብየ አርፌ ከወደ በራፌ “ውዴ! ደርሻለሁ፥ የሚል ድምጽሽ መጣ” ከመግባትሽ በፊት፥ እኔ በየት ልውጣ? @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍በእውቀቱ ስዩም1,27%
- 8 авг.እኔ እወድሻለሁ ብዙ ሺህ ዘመናት እልፍ አዕላፍ ሌሊት ሚሊዮን መሰለኝ ፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ። እኔ እወድሻለሁ የሰማይ መሬቱን የባህር ስፋቱን የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል እንደ ፅጌ-ረዳ እንደ አደይ አበባ እንደሎሚ ሽታ። እንደእጣን ጢስ እንጨት፥ እንደከርቤ ብርጉድ፥ እኔ እወድሻለሁ፥ አበባ እንዳየ ንብ። እንደቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋር አማርኛ አይበቃ፤ ወይጉድ! ባለም ቁዋንቁዋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፥ እኔ እወድሻለሁ እንደማታ ጀንበር። እንደ ጨረቃ ጌጥ፥ እንደንጋት ኮከብ፥ እኔ እማልጠግብሽ ስወድሽ፥ ስወድሽ፥ ስወድሽ፥ ስወድሽ። ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ሀይወቴ ነው። ጣይ እንዳየ ቅቤ ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፥ አፈር መሬት ትቢያ ወሃ እንደሚበላው፤ ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ብዙ ሺህ ዘመናት እልፍ አዕላፍ ሌሊት እኔ እወድሻለሁ፤ አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ ስወድሽ ስወድሽ እኔ እወድሻለሁ። @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ1,15%
- 4 авг.#ለምስኪን_ገጣሚ! የእርሱን ብሶት ችሎ አዳፍኖ በልቡ፣ የሌላውን ስቃይ በብዕር ማጀቡ፣ ቃላት እያማጠ ስንኝን መውለዱ፣ ሌላውን አግባብቶ እርሱ ግን ማበዱ፣ በምቾት አይደለም በስቃይ አልጋ ነው በእህ! እህ መከራ ግጥምን የሚጽፈው ! የሌሎችን ስቃይ ከፊት በማስቀደም ከእርሱ ሸክም በላይ ቀድሞ በመሸከም እህ! እህ ለሚሉ ዓለም ለናቃቸው ጥበብን አምጦ ድምጽ ሊሆናቸው ቃል ስለገባ ነው የጥበብ አደራ እርሱ ከሰል መስሎ ለሌሎች ሊያበራ እንጂማ ገጣሚው ስቃዩ ቢዳሰስ!!! የእርሱ ታሪክ ነበር የእውነት የሚያስለቅስ! በሌሎች እንባ ጎርፍ የእራሱን ደብቆ፣ ደስተኛ መስሎ በተስፋ ቃል ስቆ! ጥቅስ እያጣቀሰ ሌሎችን ሲያጀግን፣ ለምስኪን ገጣሚስ ማን ይሆን የሚያዝን? መገለልን ችለው ጥበብ ለሚያምጡ እስኪ እንባ ማበሻ መጽናኛ ቃል አምጡ። @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ1,05%
- 25 июл.#ኑ_አብረን_ሞኝ_እንሁን በሚያስለቅስ እንሳቅ በሚያስቅ እናልቅስ ኑ አብረን ሞኝ እንሁን በተቃርኖ ድግስ ሲርበን እንጥገብ ስንጠግብ ይራበን ሲጠማን እንርካ ስንረካ ይጥማን በለቅሶ ላይ ዘፈን በሰርግ ላይ ሙሾ አብረን እንጃጃል በመዘመን እርሾ እንሰልጥን በጋራ በቂልነት እውቀት ዘር ዘር ይሻለናል ይቅርብን ሰውነት ። ከክብር ዝቅ እንበል አንድ ላይ ተባብረን በሞኝ ስልጣኔ እንጓዝ ቸኩለን!!! ዓለም ይሳቅብን ስራችን ይቃረን በደንብ አሳስቆ ውሃው እንዲበላን። @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ1,04%
- 17 июл.#ፈርመሐል_በቃ ብጥልህ ባነሳህ ብስምህ ብነክስህ እንደኳስ አጉኘ መልሸ ብቀልብህ እሹሩሩ እያልኩኝ ስፈልግ ባልልህ ፈርመሐል በቃ በ80 ገመድ በውል ሽማግሌ እንደፈለኩ ላድርግህ ነህና የግሌ ስፈልግ ልፈታህ ስፈልግም ላስርህ ቅር ባለኝ ጊዜ ንብረት ልካፈልህ መች ይሆናል ትዳር በዚህ አይነት ሒሳብ ባሰርኩት ጠፈርኩት የንቧይ ጫወታ ካብ በፍቅር አስረሽው ልቡን ካልገዛሽው በ10 ሽማግሌ በ80 ጣጣ ዘወትር ብጠፍሪው መች እሱስ እሽ ሊል ልቡ እየሸፈተ ከውጭ ባየው ዳሌ ዘሎ እየዘመተ አስሪያለሁ ስትይ ታስረሽ እንዳትቀሪ ከ80 በላይ ቤት በፍቅር ስሪ። @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ1,02%
- 9 июл.#በማይከፈት_ቤት! ተሻለህ አትበሉኝ ዛሬም ብሶብኛል ወይ አልሞት አልድንም ስቃይ ያኖረኛል በሰቀቀን እንባ በሐዘን ዜማ ስልት ግራ በተጋባ ትርጉም አልባ ቅኝት ክራሬን ስገርፈው ብሶት እያዜመ የአምናው በሽታየ ዘንድሮም ከረመ ግርፉ ሲሰለቸኝ ብደረድረውም ቅኝቱን ቀይሬ ከተለከፈበት የሗሊት አዙሪት ቆሞ ቀርቷል እግሬ እንኳንስ መራመድ መንፏቀቅ ብርቁ ነው በትዝታ አለንጋ በመለየት ጅራፍ የተገረፈ ሰው ዳዴ ማለት አይችል ግፋ ቢል መንፏቀቅ በታመነ ልቡ የናፍቆት ከበሮ ቀን በቀን መደለቅ ክራሬን ስበሩት ድንገት ከተሻለኝ ዋሽንቱን ሰንጥቁት ሳጣው ከቀለለኝ በገና ማሲንቆ አደራ እንዳተሰብሩ ካምላክ እንድታረቅ ይልቅስ ደርድሩ አምና ዝናብ ጥሎ እህል በቅሎ ነበር የኔ ልብ ግን ዘርቶ ድርቅ ያጠቃው ፍቅር ከውስጥ በተዘጋ በማይከፈት ቤት ለብቻው ነው ዛሬም በስቃይ አዙሪት ይኸ ሰው ምን ነካው ሲሉ እየሰማሁኝ ከንፈር እያስመጠጥኩ በህይወት አለሁኝ @gitm_post ♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ0,94%