Kingdom Youths Mission Ministry
СтатистикаThis channel is including a all of kindness and charity action, menatal, self coaching, spiritual teaching & worship...
- Последний пост
- 17:13
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 16
- Всего постов
- 47
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 43
- 1/48двое суток
- 49
- 1/72трое суток
- 53
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#የብቻዎች (Sola) መርሕ #ለኦርቶዶክስ "ብቻ" የሚለው ቃል፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አስተምህሮ ቅቡል (Acceptable) አይደለም። ቃሉን ባንወደውም፣ ግዴታ፣ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ አለ። በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለበትን ሁኔታዎች እንመልከት፦ 1) የእግዚአብሔርን አምላክነት ለመግለጽ “አሁንም እኔ ብቻዬን* እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር* አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ ከእጄም የሚያድን የለም።” — ዘዳግም 32፥39 “ብቻውን* አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 “አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ*፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።” — ነሀምያ 9፥6 እነዚህ ክፍሎች፣ የእግዚአብሔርን ብቻነት [ርሱ ብቻ አምላክ እንደ ሆነ] ያመለክታሉ። 2) የእግዚአብሔርን መፍጠርና ማዳን በሚመለከት “እርሱ ብቻውን* ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤” — መዝሙር 136፥4 “ብቻውን* ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤” — መዝሙር 136፥7 “እግዚአብሔር ብቻውን* መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።” — ዘዳግም 32፥12 እነዚህ ቁጥሮች ደግሞ፣ እግዚአብሔር ያለ ማንም ድጋፍ ብቻውን ስላደረጋቸው ነገሮች [መፍጠር፣ መጠበቅ፣ ማዳን] ይናገራሉ። ብቻ (Only, Alone) የሚለው ቃል፣ የግድ ጥቅም ላይ እንደሚውል መስማማት ይጠበቅብናል! ኦርቶዶክስ ወደ #መሠረቷ እንድትመለስ እና የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲከናወንባት፣ የግድ አንዳንድ ብቻዎችን [ሶላዎችን] መቀበል ይኖርባታል። ለምሳሌ፦ _ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ (sola scriptura) _ ክርስቶስ ብቻ (solus Christus)፣ _ ጸጋ ብቻ (sola gratia)፣ _ እምነት ብቻ (sola fide) እና _ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ (soli Deo gloria) እነዚህ ብቻዎች (only, alone) የሉተር ተሐድሶ ምሰሶዎች መሆናቸው ይታወቃል። በወቅቱ የነበረውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የአስተምህሮ ችግሮች፣ ለመፍታት የቀረቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመፍትሔ ሐሳቦች ነበሩ። እነዚህ ብቻዎች፣ በእኛ ሁኔታና #ዐውድ (context) አሁንም መደገም እንዳለባቸው አምናለሁ። ጥቂት ትንታኔ፦ 1_ "የእግዚአብሔር ቃል ብቻ" (sola scriptura)፦ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሲባል፣ አዋልድ መጻሕፍት ነፍሳችን ውስጥ ይጋፋሉ። በዚህ ጉዳይ ሁለት ነገሮች ልጠቁም፦ የመጀመሪያው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማለት፦ የእግዚአብሔርን ሙሉ ምክር ለመረዳት፣ [የመዳንን እውቀት ለማግኘት፣ ለትምህርት፣ ለተግሳጽ ወዘተ.] መጽሐፍ ቅዱስ በቂ እና ብቁ ነው ማለት ነው። በሌላ አገላለጽ፣ ስልጣን (Authority) ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው ማለት ነው። ሌሎች አዋልድ መጻሕፍት፣ ባለሥልጣናት አይደሉም። ሌላው አንድ ኦርቶዶክስ የሆነ ሰው ማድረግ ያለበት፣ አዋልድ መጻሕፍት የምር የመጽሐፍ ቅዱሱ ልጆች መሆናቸው አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ነው። ይህን ሲያደርግ፣ መጽሐፍ ቅዱሱን የትምህርት መመዘኛ እና የቀኖና መስፈሪያ ማድረግ ይኖርበታል። 2_ "ክርስቶስ ብቻ" (solus Christus)፦ ይህን ሐሳብ ከመዳን አንጻር መመልከት ተገቢ ነው። የሰው ልጆች መዳን፣ የሥላሴ ምክርና ፈቃድ ቢሆንም፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሱታፌ ቢኖራቸውም፤ የተሰቀለው፣ የሞተው እና የተነሣው አዳኙ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። በዚህ ምክንያት፣ መዳን በርሱ ብቻ መሆኑ በቃሉ ውስጥ ተገልጿል፦ “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” — ሐዋርያት 4፥12 “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ሲባል፣ ወደ አእምሯችን የሚመጡ ሌሎች አዳኞች መኖር የለባቸውም። አዳኙ አንድ ነው፤ አንድየ እንደምንለው። 3_ "ጸጋ ብቻ" (sola gratia)፦ "ጸጋ ብቻ" ማለት የመዳናችን ጉዳይ ከክርስቶስ ሥራ ጋራ ብቻ የተገናኘ መሆኑን ያሳያል! "ጸጋ ብቻ" ማለት፣ መዳን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ያሳያል። መዳን ሠርተን የምናገኘው አይደለም! መዳን ሠርተን ወደ ፊት የምንሸለመው አይደለም! (ሮሜ፣ ኤፌሶን እና ገላትያ ይነበቡ) 4_ "እምነት ብቻ" (sola fide)፦ ይህ የሚያሳየው መዳንን ለመቀበል መሥራት እንደማይጠበቅብን ነው። ማመን፣ አዳኙን የእግዚአብሔር ጸጋ፣ መቀበል ማለት ነው። (ገላትያ 2፥16 ኤፌሶን 1፥13) ለመዳን ምንም ዐይነት ሥራ መሥራት፣ ምንም ዐይነት ምስጢራት መፈጸም አያስፈልግም! ጸጋና እምነት፣ እንዴት አብረው እንደሚሠሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ያስረዳል፦ "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።" (ኤፌሶን 2፥8_9) የመልካም ሥራ ጉዳይ፣ ኤፌሶን 2፥10 ላይ ተገልጿል። ለመዳን ሳይሆን ስለዳንን የምናደርገው ነው! ውጤቱ ደግሞ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥10 ላይ ይታያል! 5_ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ (soli Deo gloria)፦ ክብር በዚህ ዐውድ አምልኮን ገላጭ ነው። ለአምላክ የሚገባውን ክብር፣ ውዳሴ፣ ዝማሬ፣ ምስጋና፣ አምልኮ እና ቅኔ፣ ለሌሎች መስጠት የለብንም! ብዙ ኦርቶዶክሳውያን፣ እግዚአብሔርን ብቻ እናመልካለን ብለው ያምናሉ። አንዱን እና እውነተኛውን አምላክ የምናመልክ ከሆነ፣ የሚዘመርለት መልአክ፣ ጻድቅ፣ ቅዱስ፣ ሰማዕት ሊኖር አይችልም! #ብቻዎችን (Sola) #ለኦርቶዶክስ እንደ መፍትሔ ማሰብ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የተሐድሶ መንገድ መከተል ነው! #በርናባስ #ዘመነ
ወገን ከዚህ ቤት መውጣት አቃተን እኮ...!! ሆሆሆ🤔 ምን ዓይነት መንፈስ ነው ያገኘን? ኧረ ተባርካችሁ ቅሩ! መልካም ሳምንት! መልካም ምሽት!
አጉ ጌታ ይባርክህ ድንቅ ነው። ሙሉውን እንጠብቃለን! ከስር ያለው ፅሁፍ እኔ ከወራት በፊት የፃፍኩት ነው። የመልዕክቱ መመሳሰል ስለገረመኝ ይህን ላካፍላችሁ ወደድኩ ተባረኩ! ቤተሰብ 😊 22/09/18 E.C ጨምሩ! ተወልጄ ያደግኩት በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ በመሆኑ የልጅነት ጊዜዬ በብዛት በቤተክርስቲያን አከባቢ ነበር። ሆኖም ግን ምን አልባት ዛሬ ላይ ቆም ብዬ ሳየው ከመኖር ይልቅ የተወረሰ ክርስትና የኑሮዬ መሰረት ስለነበረ ክርስቲያናዊ ባህሪዬን ቅርፅ ሳያሳጣው አልቀረም። ስላመንኩበት ሳይሆን እንዲህና እንዲያ መሆን አለብሽ ተብሎ ስለተነገረኝ እሆን የነበረው ብዙ ነው። ብዙ ነገሮች መለዋወጥ የጀመሩት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስገባ ነበር። በርግጥ አስር አመት ከተማርኩበት የልጅነት ትምህርት ቤት መውጣቴ ተፅዕኖ ሳያሳድርብኝ አልቀረም። ያለወትሮዬ ዝምተኛ ከመናገር መስማት የምመርጥ እየሆንኩ መጣው። ጉርምስናውም ይሆን እንደዛ የለወጠኝ? እርግጠኛ አይደለሁም። ይልቁንም በክርስትያን ተማሪዎች ህብረት አደርግ የነበረው ተሳትፎ ቆም ብዬ ራሴን በደንብ እንዳይ አድርጎኛል። ከእለታት በአንደኛው እሁድ አንድ ጓደኛዬ እርሱ ያመልክበት ወደ ነበረው ቤተክርስትያን ጉባኤ እንድካፈል ጋብዞኝ የሆነ ጥግ ላይ ተቀመጥኩ አጠገቤ ክፍት ቦታም ስለነበረ የያዝኩትን መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ደብተር እዚያ አስቀምጬ ፀሎቱን ተቀላቀልኩ። ከጥቂት ደቂቃም በኋላ አንድ ሱፍ የለበሰ ሰው ከወንበሩ ላይ የእኔን እቃዎች አስነስቶ አጠገቤ በመቀመጥ ይፀልይ ነበር። የፀሎት ሰዐት ባለቀም ጊዜ አንድ አስተናጋጅ ወደ እርሱ በመምጣት አገልጋዮች ይቀመጡበት ወደነበረው ለየት ያለ ወንበር ይወስደዋል።ተጋባዥ ቃል አቅራቢ እርሱ እንደሆነ ያወቅኩት መድረክ ላይ ሳየው ነበር። ከሌላ አከባቢ የመጣ ተከታታይ ሳምንታትን እያስተማራቸው የነበረ አገልጋይ ነው። በርግጥ ለእርሱ የተዘጋጀ ስፍራ ጠፍቶት አይመሰለኝም ይልቁኑ እኔ ትህትናን እማር ዘንድ አጠገቤ መጥቶ የተቀመጠ እንጂ። ከዚያ ወዲህ በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን እያየው በየእለቱ ወደ ራሴ በመመልከት እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል እገዛ ብዙ የባህሪይ ለውጥ ለማድረግ እጣጣራለሁ። አንዴ ስላሳየነው አንድ ጥሩ ባህሪይ የእኛ ማንነት መገለጫ ላይሆን ይችላል። ለዚያም ይመስለኛል መፅሐፍ ቅዱሳችን "ጨምሩ" የሚልን ማሳሰቢያ የሚሰጠን 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:5-7 •••••••••• ⁵ ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ ⁶ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ ⁷ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። አዎ! ምንም እንኳን ሌሎች የእኛን ባህሪይ የሚያጎድፉ እልፍ መጥፎ ምግባር ቢያሳዩን እንኳን እኛ ግን የእነርሱን የሚያስንቅ ድንቅ ባህሪይ በማሳየት ትምህርት ልንሆናቸው ይገባል። ምክንያቱም እኛ ክርስትያን ነንና።
https://t.me/hisonworshiping?videochat=f33c7aab770edd6055
ርዕስ ጨምሩ 1የተሰጠንን መለኮታዊ ሀይል ማወቅ እግዚአብሔር ለህይወትና ለበጎ ስራ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ አስቀድሞ ሰጥቶናል ፦በክርስቶስ በኩል ከዓለም ጥፋት አምልጠን የመለኮቱ ባሕርይ ተካፋዮች እንድንሆን ታላቅና የተከበረ ተስፋ ተስጥቶናል 2 በእምነታችን ላይ የምንጨምራቸው 7 ነገሮች በእምነታቹ በጎነትን በበጎነትም እውቀትን በእውቀትም ራስን መግዛት ራስን በመግዛት መፅናትን በመፅናትም እግዚአብሔርን መምሰል እግዚአብሔርን በመምሰል የወንድመማች መዋደድ በወንድማማች መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ 3 የእድገትና የትጋት ፍሬ 2ኛ ጴጥሮስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ ⁹ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ¹⁰ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። ¹¹ እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።
2ኛ ጴጥሮስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤ ²-³ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ⁴ ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። ⁵ ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ ⁶ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ ⁷ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። ⁸ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤
ቃለ እግዚአብሔር ጊዜ!
መዝሙር
https://vt.tiktok.com/ZSV28CAE1/
ሳምንቱን ለባላሳምንቱ ዛሬ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ በKyMM Worship Zone እንገናኝ! https://t.me/goandserveall https://t.me/hisonworshiping
Kingdom Youth Mission Ministry አንድ ተማሪ ዓመቱን ሙሉ የሚማርበትን አንድ ደርዘን ደብተር እንድትገዙ እገዛችሁን ሽቷል!! የKYMM Coordinater's Contact አድርጉአቸው። ለሾኔ Stuff= +251961825892 = +251948231273 ለቆርጋ Stuff= +251926252772 = +251919218972 = +251926217424 ለሀዋሳ Stuff = +251916916126 = +251919762696 = +251946701904 USA = https://t.me/mesfinabaro UAE Dubai = @m_ite ለሌንዳ Stuff= +251920988086 = +251919593944 = +251911927673 ለሆሳዕና Stuff= +251924664646 = +251916748292 = +251919273585 https://t.me/goandserveall https://t.me/hisonworshiping
#ጥቁር_ጠባሳዎች! "..ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በዚ ጭለማ ምንድን ነው የምትፈልገው ብዬ ጠየኩት "እሱም ቁራሽ ዳቦ ባገኝ ብዬ ነው ብሎ መለሰልኝ፡፡ አንጀቴን በላው ድፍን 10 ብር አውጥቼ ሰጠውት እሱም ተቀብሎ ወደ ሱቅ ሄዶ ባትሪ ገዝቶ ተመልሶ ፍለጋውን ቀጠለ፡፡"😍 በእውቀቱ ስዩም! ' የነገ ተስፋ ተብሎ የሚታመነው፣ ዛሬ የሚማሩ ተማሪዎች ናቸው፤ የዛሬ ምሁራንም ትላንት ተማሪ የነበሩ ናቸው። ታዲያስ:- ትላንት የተማሩት ዛሬ ከተኩ፣ ለነገ ደግሞ ዛሬ ማስተማር አይጠበቅብንም ን? መማር እያማራቸው ሳይማሩ፣ ከሰፈር እንዳይቀሩ፣ ዛሬ ደጋግ ልቦች እስኪ የበኩላችንን አሻራ አስሸምጡ። #KYMM የ2019 ዓ.ም የትምህርት መርኻ ግብርን ተማሪዎችን ሊያስጀምር የእናንተን እገዛ ይጠብቃል። እንደ በእውቀቱ ስዩም ወግ #10ብር በመለገስ ሳይሆን ከ100 (ከአንድ መቶ ብር) ጀምረን ነጌውን እንዲያበራ #ባትሪ እናስገዛቸው!! ሮሜ 12፤9፦ "... ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤" #1ደብተር_አግዙን_ለማለት_ያህል_ነው!! 1000462398062 Christian Hulentenawi Bego Hebert Kingdom Youth Mission Ministry
ሰላም ተወዳጆች ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ጠብቆን ለዓመት በቅተናል፤ ዘንድሮም አምና በተለያዩ አከባቢዎች ያስተማርናቸው ተማሪዎች ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ = በቆርጋ እና ሌንዳ አከባቢ ፦በሲዳማ ክልል = በሐዋሳ ከተማና ከከተማው ውጪ ፦በኦሮሚያ ክልል = በሮጲ ከተማ በቁጥር በዛ ያሉ ተማሪዎቻችን የእኛን እገዛ እየጠበቁ ስለሆነ ላለፉት አራት ዓመታት ለአሥር አንድ (10/1) ተማሪውን እናስተምር ቻሌንጅ ነበር አሁን ግን ለአምስት አንድ (5/1) ተማሪ እንድናስተምር እንላለን። ድጋፋችሁ አይለየን! የKYMM Coordinater's Contact አድርጉአቸው። ለሾኔ Stuff= +251961825892 = +251948231273 ለቆርጋ Stuff= +251926252772 = +251919218972 = +251926217424 ለሀዋሳ Stuff = +251916916126 = +251919762696 = +251946701904 USA = https://t.me/mesfinabaro UAE Dubai = @m_ite ለሌንዳ Stuff= +251920988086 = +251919593944 = +251911927673 ለሆሳዕና Stuff= +251924664646 = +251916748292 = +251919273585 https://t.me/goandserveall https://t.me/hisonworshiping
“ድነትን በሂደት እንፈጽማለን” ብሎ ማስተማር ምን ችግሮች አሉት? 1. “ሰው በሥራው ድነቱን እየጨረሰ ነው” ማለት የክርስቶስን የተፈጸመ ሥራ ያሳንሳል። “ድነት በሰው ሥራ ይፈጸማል” ማለት የክርስቶስን የመስቀል ሥራ ሙሉነትና በቂነት ያሳንሳል። ክርስቶስ በመስቀል ላይ “ተፈጸመ” ሲል የማዳን ሥራው ለመዳን የሚያስፈልገውን ሥራ ሙሉ በሙሉ እንደፈጸመ የሚያበስር ነው። የሰው ሥራ የክርስቶስን የጎደለ ነገር ለመሙላት የሚጨመር አይደለም። የዕብራውያን መልዕክት ጸሐፊ ስለ ክርስቶስ መሥዋዕት ምሉዕነትና በቂነት ሲናገር:- “አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።” (ዕብ. 10:14) ብሏል። ሰው “ክርስቶስ ያደረገው በቂ አይደለም እኔም በሥራዬ የቀረውን መዳን መፈጸም አለብኝ” ቢል የክርስቶስን ሙሉ ሥራ ያሳንሳል። መልካም ሥራ የክርስቶስ ሥራ በእኛ ውስጥ መሥራቱን የሚያሳይ ፍሬ ነው እንጂ የክርስቶስን ሥራ የሚያጠናቅቅ ማሟያ አይደለም። አንድ ሰው “ዳነ” ማለት “ልቡ ተለውጧል” ማለት ነው። ከመንግሥተ ሰማይ የሚያስቀረው ልብ ከርሱ ጋር የለም። የክርስቶስን ልብ ተቀብሏል። ሠርቶ ሊድን የሚችል ስለጠፋ አምኖ መዳን መጥቷል። ላመነ ሰው የራሱን ጽድቅ ሰጥቶ ጻድቅ ያደረገው ክርስቶስ ነው። አንዴ የዳነ በቃ ድኗል። ያልዳነ ሰው አልዳነም በቃ። ድኗል ግን አልዳነም የሚባል ሰው የለም። 2. “ሰው በሥራው ድነቱን እየጨረሰ ነው” ማለት የጸጋን ተፈጥሮ ያዛባል። “ሰው በሥራው ድነቱን እየፈጸመ ነው” የሚለው አባባል የጸጋ ቴዎሎጂ አንጻር ትልቅ የሥነ-መለኮት ችግር ይይዛል። ይህንን ትምህርት ከምንም በላይ ክፉ የሚያደርገው ጸጋን ከስጦታነት ወደ ደመወዝ የሚቀይር መኾኑ ነው። ጸጋ ማለት ሰው በሥራው ያላገኘውን እግዚአብሔር በነጻ መስጠት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ይህ ትምህርት የክርስቶስን ሥራ ከሰው ሥራ ጋር ይደባልቃል። መጽሐፍ በግልጽ እንደሚያስተምረው ሰው ድነቱን በሥራው አይጨርስም። ዳሩ ግን እግዚአብሔር ራሱ በጸጋው የጀመረውን የመዳን ሥራ ራሱ ይፈጽማል። ለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ:- “በእናንተ መልካሙን ሥራ የጀመረው እስከ ክርስቶስ ቀን ራሱ እንዲፈጽመው ተረድቻለሁ” ያለው። የጸጋው ባለቤት እግዚአብሔር ነው ብቻውን ያድናል። ጸጋው ያለ ሰው መዋጮ ያድናል። 3. “ሰው በሥራው ድነቱን እየጨረሰ ነው” ማለት መጽደቅን ከሥራ ጋር ያቆራኛል። መጽደቅን (justification) ከሰው ሥራ ጋር የማያያዝ አደጋ አለው። በእምነት የምንቀበለውን ጽድቅ በሥራ የምንቀበለው ያደርጋል። መጽደቅ በሰው መልካም ሥራ የሚገኝ አይደለም በክርስቶስ ጽድቅ ላይ ተመስርቶ በእምነት የሚቀበለው የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው:: ሰው የሚጸድቀው የራሱን የጽድቅ መጠን ስለጨመረ ሳይኾን የክርስቶስ ጽድቅ በእምነት ስለተቆጠረለት ነው። ሰው በመልካም ሥራው “የቀረውን መጽደቅ እየጨረሰ” አይደለም። “ሰው በሥራው ድነቱን እየጨረሰ ነው” ስንል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ገና ያልተሟላ ነው ሰው በራሱ ሥራ የቀረውን እየሞላ ነው የሚል ሀሳብ ይፈጥራል። የአማኙ ተስፋ “እኔ ምን ያህል ሠራሁ?” በሚለው ላይ ሳይሆን “ክርስቶስ ምን አደረገ?” በሚለው ላይ ይመሠረታል። ቃሉ በግልጽ:- “በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” (ሮሜ 3:24) ይላል። መጽደቅ በሰው ሥራ የሚጨምር ወይም የሚጠናቀቅ ነገር አይደለም። የቅድስና ሕይወት ለጸደቁ ሰዎች እንደ መንፈሳዊ ፍሬ የሚታይ እንጂ የድነት ማሟያ ሥራ አይደለም። 4. “መዳን በሂደት ነው” ብቻ ካልን ሰው ገና የዳነ አይደለም በመልካም ሥራው ድነቱን እያጠናቀቀ ነው ወደሚል ስህተት ሊወስድ ይችላል። “ሰው የመዳን ሙሉነትን በራሱ ሥራ እየጨረሰ ነው” ወደሚል አሳብ ማዘንበል ሰውን ወደ ኃይማኖታዊ ወግ አጥባቂነት የሚመራ አካሄድ ነው። “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” (1ቆሮ. 1:18) ይላል። ይህንን ቃል አንዳንድ ሰዎች “ለእኛ ለምንድን” የሚለው ቃል በሂደት መዳናችንን ያሳየናል በሚል ያልተጠናቀቀ መዳን የተቀበልን ያስመስላሉ። ይህ በሕይወት ውስጥ የሚቀጥለውን የመቀደስ ሥራ ያመለክታል እንጂ ያልተጨረሰ በእኛ የሚቀጥል የድነት ሥራ መኖሩን አያመለክትም። ይህ ክፍል በምንም ምክንያት ሰው የመዳንን ዋጋ በሥራው እየከፈለ ነው ወደሚል ትርጉም ሊወስደን አይችልም። መቀደስ በሂደት ይከናወናል ማለት መጽደቅ በሂደት እየጨመረ የሚሄድ ነው ማለት አይደለም። ሰው በክርስቶስ ሲጸድቅ በአንድ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ተብሎ ይቆጠራል እንጂ በከፊል ጻድቅ ኾኖ በሥራው እየጸደቀ አይድንም። ሰው ተኮር ከኾነው አዲሱ ጴንጤቆስጤያዊ እምነት ራሳችሁን ጠብቁ። እንዲህ ብዬ ላጠቃልል። አንድ ኃጢአተኛ ሰው ዳነ ስንል ያለ ምንም ሥራ በጸጋው ብቻ በክርስቶስ አማካይነት በእምነት ጸድቋል ማለታችን ነው። ይህ ሰው በመንፈስ ቅዱስ አሠራር አዲስ ልደት አግኝቶና አዲስ ፍጥረት ኾኖ ክርስቶስን በመምሰል ሕይወት በአካሉ ያድጋል። ክርስቶስ የራሱን ጽድቅ አልብሶ በአብ ፊት ከፍርድና ከኩነኔ ነጻ አውጥቶ በጽድቅ ያቆመውን ሰው “በሥራህ ትድናለህ” ማለት በሌላ አነጋገር “ክርስቶስ የመዋጀት ተልእኮውን የሠራ ቢኾንም ሙሉ በሙሉ አልተሳካለትም” እንደ ማለት ነው። እውነቱ ግን የመስቀሉ መሥዋዕት የተሟላና በቂ ነው። ስለዚህ የመዳን መሠረት የሰው ሥራ ሳይሆን የክርስቶስ ሥራ ነው። ክርስቶስ የመዋጀትን ሥራ ፈጽሟል መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ያንን የመዋጀት ሥራ በተመረጠው ሰው ሕይወት ይተገብራል እንጂ ሰውዬው በራሱ አቅም የሚፈጽመው የመዳን ተግባር የለም። አማኙ በክርስቶስ ሲያምን፣ በክርስቶስ ያለው ጽድቅ ለእርሱ ይቆጠራል። በቂ መልካም ስለሆንኩ አልጸደቅሁም፤ ክርስቶስ ፍጹም ስለሆነ እና በእርሱ ስለታመንኩ ጸደቅሁ። መጽደቅ progressive justification አይደለም። በመልካም ሥራ ስንቀጥል ድነታችንን እንፈጽማለን ከማለት ይልቅ እውነተኛ እምነት ፍሬ ያፈራል ማለት የተሻለ ትርጉም ይሰጣል።
እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው
ሰላም ተወዳጆች ከዚህ በፊት እንደምናደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ጠብቆን ለዓመት በቅተናል፤ ዘንድሮም አምና በተለያዩ አከባቢዎች ያስተማርናቸው ተማሪዎች ፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ = በቆርጋ እና ሌንዳ አከባቢ ፦በሲዳማ ክልል = በሐዋሳ ከተማና ከከተማው ውጪ ፦በኦሮሚያ ክልል = በሮጲ ከተማ በቁጥር በዛ ያሉ ተማሪዎቻችን የእኛን እገዛ እየጠበቁ ስለሆነ ላለፉት አራት ዓመታት ለአሥር አንድ (10/1) ተማሪውን እናስተምር ቻሌንጅ ነበር አሁን ግን ለአምስት አንድ (5/1) ተማሪ እንድናስተምር እንላለን። ድጋፋችሁ አይለየን! የKYMM Coordinater's Contact አድርጉአቸው። ለሾኔ Stuff= +251961825892 = +251948231273 ለቆርጋ Stuff= +251926252772 = +251919218972 = +251926217424 ለሀዋሳ Stuff = +251916916126 = +251919762696 = +251946701904 USA = https://t.me/mesfinabaro UAE Dubai = @m_ite ለሌንዳ Stuff= +251920988086 = +251919593944 = +251911927673 ለሆሳዕና Stuff= +251924664646 = +251916748292 = +251919273585 https://t.me/goandserveall https://t.me/hisonworshiping
без подписи
без подписи
Shalom tewedajoch🙏🤗
без подписи