- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 109
- 1/48двое суток
- 124
- 1/72трое суток
- 134
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ኢየሱስ ጌታ ነው(Jesus is Lord፤ Ἰησοῦς Κύριος - Isous Kyrios) ግሩም መድረክ ኢየሱስ ጌታ ነው !! ይህ የጥንታዊ እና የአሁኑ የክርስትና መታወቂያ ፣ በታሪክ፣ በሥነ-ልሳን፣ በሥነ-መለኮት እና በፖለቲካዊ-ማህበራዊ አውድ ውስጥ እጅግ ጥልቅ ትርጉም ያለው መሠረታዊ የእምነት መሰረት ነው። ይህንን መሰረት የሆነ አዋጅ የእምነታችን ዋልታና ማገር የሆነውን ቃል በተለያዩ መንገዶች እንመልከተው። 1ኛ. ቋንቋዊ ትንታኔ በአጭሩ ኩሪዮስ(Kyrios) እና የብሉይ ኪዳኑ ያህዌ (YHWH) በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰው ኩሪዮስ የሚለው የግሪክ ቃል ተራ የክብር ስም ሳይሆን፣ የብሉይ ኪዳኑን አምላክ ያህዌን የሚወክል ነው። ለእዚህ የሰብአ ሊቃናት (Septuagint/LXX) ማስረጃ መጠቀም እንችላለን ። ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዕብራይስጥ የነበረው ብሉይ ኪዳን ወደ ግሪክ ሲተርጎም (LXX ተብሎ ይጠራል)፣ የእስራኤል አምላክ የተቀደሰ ስም ያህዌ የሚለው ቃል ከ6,000 ጊዜ በላይ ኩሪዮስ ወይም Kyrios በሚለው ቃል ተተክቶ ነበር። የመጀመሪያዎቹ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ኢየሱስን ኩሪዮስ ብለው ሲጠሩት፣ በቀጥታ በብሉይ ኪዳን የተገለጠውን ብቸኛ አምላክ ያህዌን ማንነት እና ባህርይ ለኢየሱስ መስጠታቸው ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 10፡13 ላይ "የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" ብሎ ሲጽፍ፣ በቀጥታ በኢዩኤል 2፡32 ላይ "የያህዌን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" ተብሎ የተጻፈውን ትንቢት ለኢየሱስ በመተግበር ነው። ይህም ኢየሱስ እና ያህዌ በስልጣን፣ በክብር እና በድርጊት አንድ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ደግሞ እንደገና የፊልጵስዩስ 2፡9-11 ምስክርነት "በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ..."የሚለው ክፍል፣ በኢሳይያስ 45፡23 ላይ ያህዌ "ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል" ብሎ የተናገረውን ፍጹም መለኮታዊ ክብር ለኢየሱስ ይሰጣል። ስለሆነም ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ኢየሱስ ፍጹም አምላክና የሥነ-ፍጥረት ሁሉ ባለቤት ነው ማለት ነው። 👇 በእዚህ ርዕሰ ጉዳይ ተጨማሪ ንባብ ከፈለጋችሁ የ ፕሮፌሰር ጎርደን ፊ Pauline christology የሚለውን መጽሐፍ እና በአማርኛ በሰፊው የዳሰሰውን የወንድማችን ጳውሎስ ፍቃዱን የእግዚአብሔር ልጅ የተሰኘ መጽሐፍ ማንበብ እንደምትችሉ መጠቆም እወዳለሁ ። 2ኛ. ታሪክ እና ፖለቲካ በአንደኛው ክፍለ ዘመን በሮማ ኢምፓየር ግዛት ውስጥ ኩሪዮስ ወይም ጌታ የሚለው ማዕረግ ለሮም ቄሳር ብቻ የሚሰጥ የፖለቲካ እና የሃይማኖት ስም ነበር። የሮማ ሕዝቦች ቄሳር ጌታ ነው (Caesar is Lord) በማለት ለቄሳር ታማኝነታቸውን እና አምልኮታቸውን እንዲያቀርቡ በሕግ ይገደዱ ነበር።ክርስቲያኖች ኢየሱስ ጌታ ነው ሲሉ ቄሳር ጌታ አይደለም የመጨረሻውና የበላይ ስልጣን ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ማለታቸው ነበር። ይህም በወቅቱ እንደ ትልቅ የሀገር ማስደፈር እና የፖለቲካ ክደት ይቆጠር ነበር። በ2ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ገዥ የነበረው ፕሊኒ ታናሹ (Pliny the Younger) ለንጉሥ ትራጃን (Trajan) በጻፈው ታዋቂ ደብዳቤ ክርስቲያኖች የቄሳርን ምስል ለማምለክና ቄሳር ጌታ ነው ለማለት እንቢ እንደሚሉ እና በምትኩ ለክርስቶስ እንደ አምላኪ ሆነው መዝሙር እንደሚዘምሩ ገልጿል። የሰምርኔሱ ፖሊካርፕ (Polycarp of Smyrna) በ155 ዓ.ም በስቴዲየም ውስጥ ቄሳር ጌታ ነው በልና ይቅርታ ይደረግልህ ተብሎ ሲጠየቅ፣ "ለ86 ዓመታት አገልግለውታለሁ አንዳች አልበደለኝም፤ ታዲያ እንዴት አዳኜንና ንጉሤን እሳደባለሁ?" በማለት ለሞት ተዳርጓል ወይም ሰማዕት ሆኗል ።ስለሆነም ይህ የጌታ የኢየሱስ ጌታነት በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የደም ዋጋ የተከፈለበት እና የፍጹም ታማኝነት ቃል ኪዳን ነው። ኢየሱስ ጌታ ነው ይቀጥላል ....
ሙሉ ትምህርቱ!!🙏
без подписи
без подписи
без подписи
ይቀጥላል
без подписи
без подписи
без подписи
እግዚአብሔር የለም የሚሉ ወገኖቻችን ወይም አቴይስቶች ብለን የምንጠራቸው አካላት ለድምዳሜያቸው የሚጠቀሟቸው ምክንያቶች ፍልስፍናዊ፣ ሳይንሳዊ እና ሥነ-ልቦናዊ መነሻዎች ያሏቸው ቢሆንም በእነዚህ መከራከሪያዎች መሠረታዊ ድክመቶች አሉባቸው። ዋና ዋና ምክንያቶቻቸው ✅የመጀመሪያው የክፋትና የመከራ እንቆቅልሽ (Problem of Evil) ወይም አሌክስ ዘፀአት በመጽሐፉ የእከይ ጣጣ የሚለው ነጥብ ነው።በስነ መለኮቱ አለም ብዙ የተባለለት ፍልስፍናዊ ይዘት ያለው ርዕሰ ጉዳይም ነው ። ስለሆነም እነዚህ አምላክ አፍቃሪና ሁሉን ቻይ ከሆነ በዓለም ላይ መከራና ግፍ ለምን ይበዛል? የሚለው ጥያቄ ዋነኛው ፍልስፍናዊና ስሜታዊ መነሻቸው ነው። ✅ ሁለተኛው ነጥባቸው እውነታ ማለት በቤተ-ሙከራ የሚለካና በስሜት ሕዋሳት የሚዳሰስ ቁስ ብቻ ነው የሚል እምነት ሲሆን፣ መንፈሳዊውን ዓለም ሙሉ በሙሉ ይክዳል።እውነተኛው እግዚአብሔር የሚካደው በተመሳሳይ መንገድ አይደለም ።ለምሳሌ እግዚአብሔር መኖሩን አለመኖሩንም አናውቅም የሚለው የአግኖስቲሲዝም አቋም ያለ ጥርጥር እግዚአብሔር መካድ ነው ።ስለዚህም ካልተረጋገጠ አላምንም አንዱ የክህደት መንገድ ነው። ✅ሥስተኛው የአምላክ መሰወር ወይም Divine Hiddenness የሚባለው ነጥባቸው ነው ። እግዚአብሔር ቢኖር ኖሮ ለሰው ሁሉ በግልጽ ይታይ ነበር፤ ዝምታው ያለ መኖሩ ማረጋገጫ ነው የሚል ነው።የማታይ ነገር የለም ከተባለ በእውነት እግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ብዙ እውነታዎችን መካዳችን ነው። በኒቼና የመሰሎቹ ፍልስፍና ስንረዳው አምላክን መካድ የሰው ልጅ የራሱን ሥነ-ምግባር በነፃነት ለመደንገግና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ከሚያደርገው ፍላጎት ይመነጫል። አቴይዝም ልክ የማይሆንበት ፍልስፍናዊና ቴዎሎጂካዊ ምክንያቶች በአጭሩ ብናነሳ ✅አጽናፈ ዓለም መነሻ ያለው መሆኑ (Cosmological Argument) የመጀመሪያው ነጥባችን ነው።cosmological argument ሲነሳ በተለይም calm cosmological argument ሲነሳ የፕሮፌሰር William lane Craig ስራዎች የማይዘነጉ ናቸው ። reasonable faith የሚለውን የ YouTube ቻናል መመልከት ለእዚህ ጠቃሚ ነው። ዘመናዊ የኮስሞሎጂ ሳይንስ ዓለም መነሻ Big Bang እንዳለው ያረጋግጣል። ቁሳዊ ያልሆነ፣ ከጊዜና ከቦታ ውጭ የሆነ፣ እጅግ ኃያልና አሳቢ ሳይኖር ዓለም ከምንም ተነስታ ልትገኝ አትችልም።እንኳን ውስብስቡ ዩኒቨርስ ይቅርና ጥቃቅን የመጻፊያ መሳሪያዎች ማለትም ብዕር እንኳ አስቦ የሰራውን አካል የግድ መኖር አለበት ። ሰው ውስብስቡ ፍጥረት ድንገት ሊገኝ ይችላል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ይመስለኛል። ✅ሁለተኛው ነጥብ የክፋት ተቃርኖ ለራሳቸው መመለሱ ነው ይህ Moral Argument ውስጥ የሚተነተን ነው መከራና ክፋት አለ ብሎ ለመከራከር አስቀድሞ ትክክለኛና ስህተት የሆነ ተጨባጭ የሞራል ሕግ Objective Moral Law ያስፈልጋል። አምላክ ከሌለ ግን ክፋት/መልካም የሚባል ነገር የለም። የባዮሎጂካል እድገት ውጤት ብቻ ይሆናል። ስለዚህ የክፋት/መልካም መኖር በራሱ በሕገ ልቡና አምላክ እንዳለ ማረጋገጫ ነው። ✅የዓለም ጥብቅ ሥርዓት ይህ Teleological Argument በሚባለው ዘርፍ ውስጥ ይጀምራል ።የአጽናፈ ዓለም የፊዚክስ ሕጎች፣ የዲ.ኤን.ኤ (DNA) መረጃዎችና የስነ-ሕይወት ውስብስብነት በአጋጣሚ የመጡ ሳይሆኑ የላቀ ጥበብ ያለው ንድፍ አውጪ (Designer) እንዳለ ያሳያሉ።አላማ የሌለው መፈጠር የለበትም የሚባል ነገር በእዚህ ምድር ላይ የለም ። ሁሉ በአላማ ተፈጥራልና የእጅ የእግር ጥፍር ቅንድብና ሽፋሽፍት ሁሉ በአላማ ተፈጥረዋል ።የሰውን ልጅ ልብ ኩላሊት እጅግ ግዙፍ የሆኑ ፍጥረታት በጠቅላላ አላማ ባለው ባለ አላማ አምላክ ለአላማ የተፈጠሩ ፍጥረታ ናቸው። ስለዚህ ከፍጥረት በስተጀርባ ዲዛይነር አለ። ✅ የመጨረሻው ነጥቤ ይህ ነው ።የእግዚአብሔር ህልውና ባህርይ አለመረዳት የፈጠረባቸው ችግር ውጤት ነው። አቴይዝም እግዚአብሔርን በዓለም ውስጥ ያለ አንድ ቁሳዊ አካል አድርጎ ይስለዋል። ነገር ግን በስነ መለኮት አለም በቅዱሳት መጽሐፍት ምስክርነት እግዚአብሔር የቁስ አካል አካል ሳይሆን የህልውና ሁሉ ምንጭና መሠረት Ground of Being ነው። የእግዚአብሔርን ህልውና መካድ አብዛኛውን ጊዜ ከቁሳዊ እይታ አጥር አለመውጣትና የመንፈሳዊውን እውነታ ተፈጥሮ ካለመረዳት የሚመጣ እንጂ አምላክ ለመኖሩ የሚቀርቡት ድንቅ ፍልስፍናዊና ምክንያታዊ ማስረጃዎች እጥረት ኖሮባቸው አይደለም። እግዚአብሔር አለ !!
без подписи
ክፍሎቹ ምን ይላሉ ? ሁለተኛው ክፍል ይህንን ፅሁፍ የምፅፈው የሳተ እንዲመለስ ነገሩን በሰፊ ልብ ተመልክቶ ራሱን አይቶ እንዲመለስ ከሚሻ የፍቅር ልብ ነው። የእምነት ቃል ወይም Word of Faith ንቅናቄ ሥነ መለኮታዊ መሠረቱን የገነባው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶችን መነሻ በማድረግ እንደሆነ ቢናገርም፣ የትርጓሜ ሕግጋት ወይም Hermeneutics ሲመዘን ግን አፈታታቸው #አይሲጄሲስ ላይ የተመሰረተ ነው። #Eisegesis ማለት የራስን ፍልስፍና ወይም ሐሳብ ወደ ጽሑፉ ማስገባት ማለት ነው። (ይህንን ሐሳብ ከተወሰነ ጊዜ በፊት ሰፊተ ትንታኔ ሰጥቼበታለሁ ። ኮመንት ላይ ሊንክ አስቀምጣለሁ ።) ንቅናቄው በተለይ የታሪካዊ ሰዋሰዋዊ ተብሎ የሚጠራውን Historical Grammatical Context ደንቦችን በመጣስ፣ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን ወደ ሜታፊዚካዊ ሕግጋት በመቀየር እና የብሉይና አዲስ ኪዳን ስነ-ጽሑፋዊ ዘውጎችን በማደበዝዘዝ ይታወቃል።ለእዚህም ነው ትምህርታችንን ይደግፋል ብለው የሚያነሷቸው ጥቅሶች የማይሉትን የሚያስብሏቸው። ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ድረስ የዚህ አስተምህሮ መሠረት ተደርገው የሚወሰዱ ቁልፍ ጥቅሶች፣ የእነርሱ ትርጓሜ እና የመጽሐፍ ቅዱሳዊ አውዳዊ ትንተናቸው የሚከተለው ለማብራራት እንሞክራለን ። 1ኛ.ዘፍጥረት 1:26-28 "እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።"እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።" ይህ ክፍል የእንቅስቃሴው የሕልውና ጥቅስ ነው ።እዚህ ጥቅስ ላይ ነው የትምህርታቸው መሰረት የተገነባው ።እነዚህ ወንድሞቻችን የሳቱት ግን ክፍሉ እነሱ እንደሚሉት ባለማለቱ ነው። ዘፍጥረት 1:26-27 Imago Dei የእግዚአብሔር መልክ ወይስ ትንሽ አምላክ?የሚለውን እንመልከት እና ወደ ሌሎቹ እንዘልቃለን ። የእምነት ቃል ንቅናቄ አቀንቃኞች ይህንን ጥቅስ በመጠቀም፣ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ስለሆነ በእግዚአብሔር ምድብ ወይም God-class ውስጥ ያለ ፍጡር ነው ይላሉ። በሰማይ እግዚአብሔር እንዳለ ሁሉ፣ በምድር ላይ ደግሞ ሰው ትንሽ አምላክ ወይም Little god ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ። በጥንቱ ቅርብ ምስራቅ ባህል፣ አንድ ንጉሥ በራሱ ግዛት ስር ባሉና እርሱ በአካል በማይገኝባቸው ሩቅ አውራጃዎች ላይ የእራሱን ምስል ማለትም Statue ያቆም ነበር። ይህ ምስል የንጉሡን መገኘትና ስልጣን የሚወክል ነው። ሙሴ በዘፍጥረት ላይ Imago Dei በእግዚአብሔር መልክ መፈጠር የሚለውን ጽንሰ-ሀሳብ ሲጠቀም የወሰደው ከዚህ የታሪክ አውድ ነው። ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጠረ ማለት በምድር ላይ የእግዚአብሔር ሕያው ተወካይ ወይም Representative/Steward ሆኖ እንዲገዛ ተሾመ ማለት እንጂ፣ መለኮታዊ ባህርይን ተካፈለ ማለት አይደለም።በአዲስ ኪዳን የመለኮት ባህሪይ ተካፋይ የሚለው ቃል እራሱን የቻለ አውድ እንዳለው ልብ ይሏል። ማስተዋል ያለብን አንድ እውነታ በመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-መለኮት በፈጣሪና በፍጡር መካከል የማይታለፍ የባሕርይ ገደብ አለ። እግዚአብሔር ያልተፈጠረ ህልውና ወይም Uncreated Being ሲሆን፣ ሰው ግን የተፈጠረ ህልውና Created Being ነው። በዕብራይስጥ Tselem መልክ እና Demut ምሳሌ የሚሉት ቃላት የሚያሳዩት ረቂቅ መመሳሰልን ማለትም ማሰብ መቻልን፣ የሞራል ምርጫንና ግንኙነትን እንጂ የባሕርይ አንድነትን Identical Nature አይደለም። የእምነት ቃል አስተማሪዎች ሰው በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩን ከሥራና ከኃላፊነት አንጻር መረዳት ሲገባቸው፣ ወደ ምንነትና ባህርይ ማለትም Ontological በመቀየር ፍጡርን መለኮት የማድረግ ስህተት ነው። ዘፍ 1:28 ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ "እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙም፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዟትም..." (ዘፍጥረት 1:28) ይህ ጥቅስ ላይ ቆመው እግዚአብሔር ምድርን የመግዛትና የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን ለአዳም በህጋዊ ውል ሰጠው፤ አዳም ግን በውድቀቱ ምክንያት ይህንን ስልጣን ለሰይጣን አስተላለፈ ። ስለዚህ ሰይጣን የምድር ህጋዊ ገዥ ሆነ፣ እግዚአብሔርም ያለ ሰው ፍቃድ በምድር ላይ ጣልቃ መግባት የማይችልበት ህጋዊ እገዳ ተጣለበት ይላሉ። ( ለእዚህ ማስረጃ የምትፈልጉ ወዳጆች የ Abenezer Teklu Diyakon የእምነት ቃል እንቅስቃሴ የዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና የሚውን መፅሐፍ የጳውሎስ ፍቃዱ ሰው ማነው የሚለውን የ YouTube ትምህርት ክፍል አንድ እና ሁለት የዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ አባይ ነባይ እና እምነት ምንድነው የሚለውን አርቲክል እንድታነቡ መክራለሁ) ይህ አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ንግድ ሕግና ኮንትራት አድርጎ ከመመልከት የመነጨ ነው። ሆኖም በመጽሐፍ ቅዱስ አውድ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስተምረው በህግ እና በተግባር የምድር ባለቤትነት ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ነው። መዝሙር 24:1 “ምድርና በእርሷ የመላው ሁሉ ለእግዚአብሔር ናት” ይላል። እግዚአብሔር ሉዓላዊነቱን ለሰውም ሆነ ለሰይጣን በውል አሳልፎ አልሰጠም።አዳምም በምድር ላይ የተሾመው እንደ ታናሽ ንጉሥ ነው። አዳም ሲያምጽ መጋቢነቱን አጎደለ እንጂ ምድርን ለሰይጣን የማስተላለፍ የባለቤትነት መብት አልነበረውም። በዕብራይስጥ Kabash ወይም መግዛት/በቁጥጥር ስር ማዋል እና Radah ወይም መግዛት/መሪ መሆን የሚሉት ቃላት የእንክብካቤና የስምምነት አስተዳደርን የሚያመለክቱ እንጂ ሉዓላዊ የባለቤትነት መብትን የሚገልጹ አይደሉም። እግዚአብሔርን ከራሱ ሕግጋት በታች አድርጎ በመሳል፣ ሉዓላዊነቱን በሰዎች ውሳኔ ላይ ጥገኛ የማድረግና የፈጣሪን ሁሉን ቻይነት የመገደብ ስህተት ነው። ይቀጥላል ፀጋ ይብዛላችሁ 🙏
без подписи
ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ውስጥ ብዙ ተግዳሮቶች አልፋለች።አሁንም እያለፈች ትገኛለች ።ወደፊትም ይህ ተፈጥሯዊ ነውና ቅርፁን እየለዋወጠ ተግዳሮት መከሰቱ አይቀርም። በእዚህ ፅሁፍ ስለ የእምነት ቃል ወይም word of faith ስለሚባለው አስተምህሮ እናወራለን በጠንካራ ምንባብ ፍቺ መርህ መሰረት የሚነሱ ጥቅሶቻቸውን እንመለከታለን ። ይህ በፍቅር ለማቅናት የሚደረግ ወንድማዊ ፅሁፍ ነው።ከተቻለ ይህ አስተምህሮ ያለውን ችግር ተረድቶ ለመመለስ እንዲረዳቸው ብቻ ነው።በእዚህ አስተምህሮ ውስጥ ያለላችው ወንድም እህቶቼ ደግሞ ምን እንደሚያምኑ እንድታውቁ ነው ።በእዚህ አጋጣሚ በፀሎት እናስባቸው ዘንድ እንደሚገባ ለማሳሰብ እወዳለሁ ። የእምነት ቃል ወይም Word of Faith ንቅናቄ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰፊ ተፅዕኖ የፈጠረ ቢሆንም፣ ከዋናውና ከቀጥተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ-መለኮት ያፈነገጡ በርካታ ትምህርቶችን ያራምዳል። እነዚህ ትምህርቶች አብዛኛውን ጊዜ የሚመነጩት ጥቅሶችን ከታሪካዊና ሰዋሰዋዊ አውዳቸው ነጥሎ ከመተርጎም ነው። ዋና ዋና የስህተት ትምህርቶች 1ኛ . የሰው ትንሽ አምላክ መሆን ይህ በፈረንጆቹ አፍ The Little Gods Doctrine ይባላል ። ይህ አስተምህሮ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ምድብ/ክፍል ወይም God class ውስጥ ነው ይላል። አዳም በምድር ላይ አምላክ ነበረ ነገር ግን ውድቀቱ መለኮታዊ ስልጣኑን ለሰይጣን አሳልፎ እንዲሰጥ አድርጎታል። አማኞች ዳግም ሲወለዱ ግን ያንን የአምላክነት ተፈጥሮ መልሰው ያገኛሉ የሚል ይዘት አለው። ይህ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን መሠረታዊ ልዩነት ያደበዝዛል። ይህንን ንግግር በተደጋጋሚ ሁኔታ በአደባባይ ሲናገሩ የነበሩ ሰዎችን መስማት የተለመደ ነገር ነበር። በቅርቡ ትንንሽ አምላክ ሳይሆን ትልቅ አምላክ ነን ወደ ማለት ተደርሶ ነበር። ለእዚህ እንደማሳያ ኃይሉ ዮሃንስን ማንሳት እንችላለን ። 2ኛ . እምነት እንደ መንፈሳዊ ኃይል ወይም ሕግ በእምነት ቃል አስተምህሮ እምነት በእግዚአብሔር ላይ የሚጣል ሙሉ እምነትና መታመን ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ራሱ ዓለምን ለመፍጠር የተጠቀመበትና ማንም ሰው ሊጠቀምበት የሚችል የማይታይ መንፈሳዊ ሕግ ወይም ኃይል ተደርጎ ይወሰዳል። በዚህ እይታ እግዚአብሔር የሉዓላዊ ውሳኔ ባለቤት ከመሆን ይልቅ፣ አማኙ በእምነት ሕግ ተጠቅሞ ለሚያስተላልፈው ትዕዛዝ ምላሽ ለመስጠት የሚገደድ ይመስላል።አንዳንድ ከሃገራችን ውጪ ያሉ ሰዎች እግዚአብሔር ጣላቃ እንዲገባ እኛ ፍቃድ ልንሰጠው ይገባል እስከ ማለት ደርሰዋል ።እውነት ለመናገር እግዚአብሔር ፍቃዳችንን ያከብራል ።ሰውም ፍቃድ አለው ።ነገር ግን እግዚአብሔር የምድር አስተዳዳሪ ነው።ሕያዋን ሆነን የምንቀሳቀሰው በእርሱ በእግዚአብሔር ነው። ፍጥረት አለሙ በጠቅላላ የእርሱ ተዳዳሪ ነው ።በእዚህ ምድር ላይ እግዚአብሔር ለመስራት ፍቃድ የሚጠይቅ ሳይሆን የእርሱ ንብረት እና እርሱ የምድር አስተዳዳሪዋ እርሱ ስለሆነ ፍቃድ ያለብን ይልቁኑ ፍቃድ መጠየቅ ያለብን እኛ ነን። 3ኛ. የአዎንታዊ ኑዛዜ ኃይል ወይም Positive Confession የምትናገረውን ታገኛለህ What you say is what you get) የሚለው መርህ የዚህ አስተምህሮ ማዕከል ነው። የሰው ቃላት የራሳቸው የሆነ የመፍጠር ወይም የማጥፋት መለኮታዊ ኃይል አላቸው ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ ስለ በሽታ፣ ድህነት ወይም ድካም መናገር እነዚያን ነገሮች በሕይወት ውስጥ እንዲገለጡ ይጋብዛል፤ በተቃራኒው ጤናንና ሀብትን ማወጅ Confess ማድረግ ነገሮቹን ወደ መኖር ያመጣቸዋል ይላሉ።ይህ ሃሳብ እነርሱ በሚሉበት አውድ ውስጥ ልክ አይደለም። 4ኛ.የክርስቶስ በመንፈስ መሞትና በገሃነም መሠቃየት አንዳንድ የንቅናቄው ቁልፍ መጋቢዎች እንደሚያስተምሩት፣ የክርስቶስ የቤዛነት ሥራ የተጠናቀቀው በመስቀል ላይ ሳይሆን በገሃነም ውስጥ ነው። ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰይጣንን ጠባይ መንፈሳዊ ሞት ተካፈለ፣ ወደ ገሃነም ወርዶ በሰይጣንና በአጋንንት ተቀጠቀጠ፣ ከዚያም በገሃነም ውስጥ የመጀመሪያው ዳግም የተወለደ ሰው ሆኖ ተነሳ የሚል እጅግ አደገኛ የሆነ የክርስቶስ ስነ-መለኮት ስህተት ያራምዳሉ። 5ኛ ቁሳዊ ብልጽግና እና ፍጹም ጤንነት የቤዛነት መብት ናቸው ። ማንኛውም አማኝ በዚህ ምድር ላይ ፍጹም ባለጠጋና ከበሽታ ነፃ መሆን አለበት የሚል ድምዳሜ አላቸው። ማጣት ወይም መታመም የእምነት ጉድለት፣ የአዎንታዊ ኑዛዜ እጥረት ወይም የሰይጣን ጥቃት ተደርጎ እንጂ እግዚአብሔር ለአማኙ እድገት የሚጠቀምበት የባሕርይ መቅረጫ መንገድ ለምሳሌ በኢዮብ ወይም በጳውሎስ ሕይወት እንደታየው ተደርጎ አይወሰድም።ወይም በሕይወት ስርዓት ውስጥ የሚከሰቱ መሆናቸውን በወደቀ አለም ውስጥ በመኖራችንን የሚከሰቱ መሆናቸውን ባለማስተዋል በተለያዩ ሕመም ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዲሸመመቀቁ እና ካልተሻላቸው ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ጥርጣሬ እንዲኖራቸው ያደርጋል ። ይቀጥላል .... ፀጋ ይብዛላችሁ
без подписи
በወቅቱ የነበረው የአይሁድ ባህል የሴቶችን ምስክርነትና ትምህርት በሕግ ፊት እንኳ ተቀባይነት እንደሌለው አድርጎ ይቆጥር ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ባህል በመስበር፣ ሴትን የትንሣኤው የመጀመሪያዋ መምህርና ሐዋርያ አደረጋት #Apostle to the Apostles። በተመሳሳይ መንገድ፣ ሳምራዊቷ ሴት ከክርስቶስ ጋር ከተገናኘች በኋላ፣ ወደ ከተማዋ ሄዳ ለወንዶቹም ጭምር መሲሑን በማስተማር መላው ከተማ ወደ ክርስቶስ እንዲመጣ አድርጋለች (ዮሐ 4፥28-30)። የኢየሱስና የጳውሎስ ድጋፍ ለሴቶች አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ወጥ መንገድ ስንመለከተው፣ ኢየሱስም ሆነ ጳውሎስ ሴቶችን ከአገልጋይነት መስመር የሚያገሉ ሳይሆኑ፣ በተቃራኒው በወቅቱ የነበረውን የሴቶች ጭቆና ሰብረው ወደ መድረክ ያወጧቸው መሪዎች መሆናቸውን እንረዳለን። በቀጣይ ይህን ርዕስ በሰፊው እና የመድረክ አገልግሎትን ብሎም ሲያገለግሉ እንዴት ያገልግሉ ? የሚለውን ነጥብ እንመለከታለን ። ሴቶች አያስተምሩ ወይስ በመድረክ አያስተምሩ?ሴቶች አይምሩ ወይስ ቤተ ክርስቲያንን አይምሩ ?ሴቶች አያገልግሉ ወይስ በስብከት አያገልግሉ ወይስ ....ወይስ ...? 🔴✅ መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ? ይቀጥላል ፀጋ ይብዛላችሁ
ክፍል ሁለት ሴት እንዳታስተምር አለማቀፋዊ እና ዘላለማዊ እገዳ ተጥሎባታልን? የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ምን ያስተምሩናል ? ጠንካራ ምንባባት ግሩም መድረክ 1ኛ ጢሞ 2:11-12 "ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።" ባለፈው ክፍል የእዚህ ጥቅስ ትንታኔ ማየት ጀምረናል ።አሁን እርሱን እቀጥልና ሰፋ ወዳለው አጠቃላይ ትንታኔ እናልፋለን ። 🔴✅በዝግታ ትማር በዝግታ ወይም በጸጥታ ተብሎ የተረጎመው የግሪክ ቃል ሄሱኪያ Hesychia ይባላል። ይህ ቃል ፍጹም ድምፅ አለማውጣትን አያሳይም። ይልቁኑ የሰላም፣ የረጋ፣ የማይከራከርና ለመማር የተዘጋጀ መንፈስ ማለት ነው። ጳውሎስ በ2ኛ ተሰ 3፥12 ላይ ወንዶችም ጭምር በዝግታ/በፀጥታ #Hesychia እየሰሩ እንጀራቸውን ይብሉይላል። "እንደነዚህ ያሉትንም #በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን።" ስለዚህ ዝግታ የሴት ብቻ ሳይሆን፣ የአማኝ ሁሉ ጸባይ ነው። ሴቶች መጀመሪያ ያልተበላሸውን እውነት በጸጥታና በትሕትና ተምረው ማደግ እንዳለባቸው የሚገልጽ እንጂ አፋቸውን ለመስፋት የተሰጠ ትእዛዝ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ከብሉይ እና ከአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስን ስንተረጉም ግልጽ ያልሆኑና ለአንድ የተወሰነ አካባቢ የተጻፉ ጥቅሶችን፣ ግልጽና ሁለንተናዊ በሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችና እውነታዎች መነጽር ልንመረምራቸው ይገባል። ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጣን መያዝ እንደሚችሉ የተወሰኑ ማስረጃዎችን እንመልከት 🔴✅የጵርስቅላ አገልግሎት እና ታዋቂውን መምህር አጵሎስን ማስተማሯ በሐዋርያት ሥራ 18፥26 ላይ እጅግ አስደናቂ ታሪክ እናገኛለን። አጵሎስ የተባለ በቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀቱ የተመሰከረለት፣ የተማረና የነገረ-መለኮት ምሁር የነበረ ሰው ወደ ኤፌሶን መጣ።ይህ ሰውን ያጠጣ ነበር ተብሎ በጳውሎስ የተመሰከረለት ወይም በጥልቀት ያስተምር ነበር የተባለለት ሲሆን ነገር ግን በዕውቀቱ ላይ የተወሰነ ጉድለት ነበረበት።በሁሉ ነገር ሁል ጊዜ መሉ መሆን አይቻለም ።ሁሌ ሌሎች የሚያስፈልጉን ለእዛ ነው።ሕብረት መውደድ ያለብን በእዚህ መሰረት ላይ ነው። "እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፥ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት።" (አስተማሩት)(ሐዋ. 18፥26) እዚህ ጋ ጵርስቅላ የተባለችው ሴት ከባሏ ከአቂላ ጋር ሆና፣ ይህንን ታላቅ ወንድ መምህር የነገረ-መለኮት ትምህርት አስተምራዋለች፣ አስተካክላዋለችም። መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ታሪክ ላይ የጵርስቅላን ስም ከአቂላ አስቀድሞ መጻፉ ፣ እሷ በማስተማሩ ረገድ ይበልጥ ጎልታ የምትታወቅ ዋና መምህር እንደነበረች ሊያሳይ ይችላል ። ጳውሎስ ሴት ወንድን እንዳታስተምር ፍጹም ሕግ ቢኖረው ኖሮ፣ የእርሱ የቅርብ አጋር የሆነችው ጵርስቅላ አጵሎስን ስታስተምር በኮነናት ነበር፤ ነገር ግን ጳውሎስ በሮሜ 16፥3 ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ እያለ ያደንቃታልም 🔴✅ የዲቦራ (Deborah) መሪነት፣ ነቢይነትና ፍራጅነት በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ እስራኤል በከባድ የኃጢአትና የባርነት ጨለማ ውስጥ በነበረችበት ወቅት፣ እግዚአብሔር መላውን የእስራኤልን ሕዝብ ወንዶችንም ጭምር እንድትመራና እንድታስተምር ያስነሳት ሴት ዲቦራ ትባላለች። በዚያም ዘመን የልፊዶት ሚስት ነቢይቱ ዲቦራ በእስራኤል ላይ ትፈርድ ነበር... የእስራኤልም ልጆች ለፍርድ ወደ እርስዋ ይወጡ ነበር። (መሳ 4፥4-5) ዲቦራ ነቢይት ብቻ ሳትሆን፣ ከፍተኛው የፖለቲካ፣ የወታደራዊና የሃይማኖት ሥልጣን ባለቤት ነበረች። ወንዶች መሪዎችና የጦር አዛዦች ማለትም እንደ ባርቅ ያሉ በእሷ መመሪያ ሥር ይንቀሳቀሱ ነበር። እግዚአብሔር ሴት ወንድን እንድታስተምር ፈጽሞ እንዳትመራም የማይፈቅድ ቢሆን ኖሮ፣ ዲቦራን መላውን እስራኤል እንድትመራና የእግዚአብሔርን ሕግ እንድታስተምር ባላስነሳትም ነበር። የእሷ ታሪክ የሚያሳየው እግዚአብሔር ሰዎችን የሚመርጠው በጾታ ሳይሆን በጸጋ መሆኑን ነው።ይሄ በብሉይ ኪዳን ጭራሽ ዝግ ነበር ለሚሉ ሰዎች አይን ከፋች የሙግት ነጥብ ነው። 🔴✅ የነቢይቱ ኬልዳ ነገረ-መለኮታዊ ሥልጣን በነገሥታት ታሪክ ውስጥ ንጉሥ ኢዮስያስ በቤተ መቅደስ ውስጥ የጠፋውን የሕግ መጽሐፍ የሙሴን መጽሐፍ ባገኘ ጊዜ፣ የቃሉን ትክክለኛ ትርጉምና መለኮታዊ መልእክት ለማወቅ ወደ ማን መሄድ እንዳለበት ማሰስ ጀመረ። በወቅቱ እንደ ኤርምያስና ሰፎንያስ ያሉ ታላላቅ ወንዶች ነቢያት በሀገሪቱ ነበሩ። ነገር ግን ንጉሡ፣ ሊቀ ካህናቱና የሀገሪቱ ታላላቅ ባለሥልጣናት የእግዚአብሔርን ቃል ለመጠየቅ የሄዱት ወደ አንዲት ሴት ነበር፦ መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 22:14-15 "እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቲቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢያቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ከእርስዋም ጋር ተነጋገሩ።እርስዋም አለቻቸው። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት።" ኬልዳ ለንጉሡ፣ ለካህናቱና ለሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል በተደራጀና ባለሥልጣን በሆነ መንገድ አስተምራለች፣ ትንቢትም ተናግራለች። የእግዚአብሔርን ሕግ የመተርጎምና የማስተማር ሥልጣን በሴትነቷ ምክንያት አልተከለከለም። 🔴✅የሎይድ፣ የኤውንቄ እና በቲቶ መጽሐፍ ውስጥ የተሰጠው የማስተማር ትእዛዝ ሴቶች የማስተማር አገልግሎት እንዳላቸው ጳውሎስ ራሱ በሌሎች ክፍሎች በግልጽ አስቀምጧል። ጢሞቴዎስ ራሱ ለደረሰበት ታላቅ መንፈሳዊ ዕውቀትና እምነት መሠረቱ እናቱና አያቱ እንደሆኑ ጳውሎስ ይመሰክራል ። በአያትህ በሎይድና በእናትህ በኤውንቄ አስቀድሞ የነበረውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ (2 ጢሞ. 1፥5)። እነዚህ ሴቶች ጢሞቴዎስን ከሕፃንነቱ ጀምረው ቅዱሳት መጻሕፍትን አስተምረውታል። በተጨማሪም ጳውሎስ በቲቶ 2፥3-4 ላይ ለሽማግሌዎች ሴቶች ግልጽ ትእዛዝ ይሰጣል እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች... በጎውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ። ሴቶች የማስተማር ጸጋና ኃላፊነት እንዳላቸው ጳውሎስ ራሱ ያረጋገጠበት ሥነ-መለኮታዊ ማስረጃ ነው። "እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤" 🔴✅ የማርያም መግደላዊትና የሳምራዊቷ ሴት የመጀመሪያዎቹ መልእክተኝነት በአዲስ ኪዳን ወንጌል ታሪክ ውስጥ፣ ታላቁንና መሠረታዊውን የክርስትና ዶክትሪን የክርስቶስን ትንሣኤ ለሐዋርያት (ለወንዶች) እንድታበስርና እንድታስተምር የተላከችው የመጀመሪያዋ ሰው ማርያም መግደላዊት ናት። ኢየሱስም፦ ... ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው አላት። ማርያም መግደላዊት መጥታ ጌታን እንዳየች ይህንንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ አወራች።ዮሐ 20፥17-18
без подписи
ጳውሎስ የከለከለው ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጤናማ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጣን እንዲኖራቸው ሳይሆን፣ በኤፌሶን ይኖሩ እንደነበሩት የአርጤምስ ካህናት ወንዶችን እየጨቆኑ፣ ሥልጣንን በጉልበት እየነጠቁና የሐሰት ትምህርታቸውን በኃይል እየጫኑ የሚያደርጉትን ፈላጭ ቆራጭነት ነው። 🔴✅ በዝግታ ትማር ... ይቀጥላል ፀጋ ይብዛላችሁ !!