tgindex
Jesus is the only way!!

Jesus is the only way!!

Статистика

መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። ሐዋ 4:12 ለአስተያየትዎ https://t.me/Danicheru

Последний пост
16 мар. 2025 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
228
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 210
19 постов
Вовлечённость
530,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ከክርስቶስ ጋር ተሰቅለናል ገላ ፡ 2፥20 ከዛሬ ሁለት ሺ አመት በፊት ክርስቶስ ሲሰቀል ጳውሎስ አብሮ ተሰቅሎ ነበር እንዴ? አልተሰቀለም!! ከክርስቶስ ጋር ተሰቅለው የነበሩት ሁለት ወንበዴዎች ነበሩ። ታዲያ ለምንድነው ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ያለው?? ✍ሰው በእግዚአብሄር ፊት ሲታይ አዳማዊ ማንነት የተላበሰ፣ በሁሉም ነገር የተበላሸ፣ በሀጥያት የጨቀየ እና ምንም ፅድቅ የሌለው ምስኪን ፍጥረት ሆነ። ታዲያ እግዚአብሄር ሰውን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከመሞት ውጪ ምንም ጥቅም የለሌው ፍጥረት ስለሆነ እንዲሞት ፈረደበት። ስለዚህ ራሳችንን ስናስብ በመስቀል ሞት ተሰቅዬ ከመሞት በቀር ለምንም የማልጠቅም ተራ ፍጥረት ሆኜ ተገኘሁ ማለት መቻል አለብን። እግዚአብሄር ግን እኔ መሰቀል ሲገባኝ ልጁን እኔን ተክቶ እንዲሰቀል አደረገው።ስለዚህ ክርስቶስ ሲሰቀል እግዚአብሄር ከመስቀል ሞት ውጪ ለምንም አይጠቅምም ያለው እኔ ዳንኤልን ይዞኝ ተሰቅሏል። እኔ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ይዞ ተሰቅሏል። ከክርስቶስ ጋር ተሰቅለናል!!!! ✍ታዲያ በመስቀል የሞተው አዳማዊ ማንነት ዛሬም ከሞት ተነስቶ እያስቸገረን ይሆን?  ከሆነ ሁለት ነገር እናድርግ፦ 1/እያስቸገረን ላለው አዳማዊ ማንነታችን ደጋግመን እንንገረው። ሞተሀል ክርስቶስ ሲሰቀል በመስቀል ላይ ገሎሀል ብለን ደጋግመን እንንገረው። የዛኔ ይሸነፋል 2/ ጌታ ከተቀበልን ዕለት ጀምሮ ክርስቶስ በውስጣችን እንዳለ በእምነት እርግጠኛ እንሁን። ስለዚህ በውስጣችን ያለው ክርስቶስ ስራውን (ቅድስና፣ በጎነት፣ የዋህነት፣ ቸርነት ፣ አለማዊ ምኞትን መጥላት እና ወዘተ…)  በየእለቱ እንዲያከናውን እንፍቀድለት። እኛ በሰው ፊት ጻዲቅ ለመምሰል ምናደርገውን ጥረት አቁመን እንደተሸነፈ አቅም እንደሌለው በራሱ ጥረት ምንም ማድረግ እንደማይችል ሰው ሆነን በውስጣችን ላለው ለክርስቶስ እንንገረው። ጳውሎስ እኔ አልኖርም ክርስቶስ ነው በእኔ ሚኖረው ብሏል።አንተ እንድትኖርብኝ ፈቅጃለሁ እንበለው። በጣም ትሁት ሆነን በሞኝነት ያስቸገሩን ሀጥያቶች ፅፈን እነዚህ ሀጥያቶች ውሰድልኝ እንበለው። ክርስቶስ ሙሉ ማንነታችን ተረክቦ ሊኖርብን ይፈልጋል። እንፍቀድለት!!!! ከፈቀድንለት አዳማዊ ማንነት አሸንፎን በውስጣችን አይኖርብንም።  አሜን✋🤚 ወንድማቹ ዳንኤል ቸሩ ነኝ። ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በውስጥ መስመር አውሩኝ እንዲሁም አዳማዊ ማንነት የሚያስቸግራቹ ካላችሁ አውሩኝ ጌታ ኢየሱስ ይባርካቹ✋✋✋

  • ከሁሉ የመብለጫ ጥበብ          ማቴ 18 ÷1~4 በደቀመዛሙርት መካከል አንድ ትልቅ ክርክር ነበር። በመንግስተ ሰማይ ትልቅ እኔ ነኝ የማለት ክርክርና ፉክክር ብዙ ጊዜ ይደጋገም ነበር። አንድ ቀን ኢየሱስን ጠየቁት። ኢየሱስ ግን ህፃን በመካከላቸው በማቆም ሁሉት ነገሮች ተናገራቸው። 1/ ካልተለወጣቹና እንደ ህፃን ካልሆናችሁ መንግስተ ሰማይ አትገቡም አላቸው። ምን ማለቱ ነው? ✍ህፃናት በራሳቸው አቅም እንደሌላቸው እና ሁሉም ነገር በወላጆቻቸው በኩል እንደሚሆንላቸው ያውቃሉ። ስለዚህ ሰው መንግስተ ሰማይ ለመግባት በራሱ ምንም አቅም እንደሌለውና ፈጣሪ ሊያደርግለት የሚችለው ነገር ብቻ እንደሆነ ማወቅ አለበት። መንግስተ ሰማይ በሰው ፅድቅና በጎ ስራ ሚሆን ነገር አይደለም። ልክ ህፃን በራሱ ምንም እንደሆነ አውቆ የወላጁን አቅም እንደሚተማመን ሰው ስለመንግስተ ሰማይ ሲያስብ በራሱ የማያደርገው በፈጣሪ ፈቃድና እርዳታ የሚያገኘው ነገር መሆኑን ማወቅ አለበት። ይሄ አስተሳሰብ ከሌላቹ አትገቡም እያላቸው ነው። 2/ በመንግስተ ሰማይ ትልቅ ለመሆን የሚፈልግ ከሁሉ ራሱን ዝቅ ያደርግ ልክ እንደ ህፃን አላቸው። ✍ዘንድሮ ያልሆነውን ሆነን በመታየት ትልቅ እንድንባል እንፈልጋለን ። ትልቅ እንዲሉን የሀሰት ትንቢት ከመናገር ጀምረን ማንፈነቅለው ድንጋይ የለም። ሌላም ብዙ ነገር እናደርጋለን። የሌሎች ጥሩ ስብከትና ዝማሬ ሁላ ማየት አንፈልግም ያናድደናል።  ስለዚህ ሳናውቀው በመንግስተ ሰማይ ትንሽ እየሆንን ነው። ህፃናት ትሁት ናቸው። እበልጣለሁ የሚል ሀሳብ በፍፁም የላቸውም። ስለዚህ ይሄ የህፃናት አስተሳሰብ በመንግስተ ሰማይ ትልቅ የመሆኛ ጥበብ ነው ። ይሄ የተናገረው ትልቅ ሆኖ ሳለ ትሁት ሆኖ፤ ባዶ ሆኖ ፤ ተሸንፈፎ እኛን ያዳነን ክርስቶስ ነው። እራሱን ያለ ልክ ዝቅ ስላደርገ አብ ከሁሉ በላይ አከበረው። ዛሬም ዝቅ የማለትና ትሁት የመሆን መንፈስ ይኑረን። በብዙ ተባረኩ✋🤚  ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ አብረን እናገልግል 🙏🙏

  • በዚህ በመጨረሻ ዘመን እንዴት እንመላለስ?             2ኛ ጢሞ 3፥1~17 ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ጢሞቴዎስ በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ እወቅ እያለው ነው።  ታዲያ አሁን ያለንበት ጊዜ የመጨረሻ ዘመን ነው?? አዎ ጳውሎስ እንደምልክት የዘረዘራቸው ሀሳቦች ካየናቸው ሁሉም አሁን እየሆኑ ያሉና እኛም እየተሳተፍንባቸው ያሉ ነገሮች ናቸው። ከቁጥር 2 እስከ 5 ያሉት ቃላቶች እያንዳንዳቸው አሁን በስፋት እየሆኑ ያሉ ነገሮች ናቸው። አንዳንዶቹን ለማየት ያክል፦      1/ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ ይላል ይሄ የሁሉም ሰው መለያ ሆኗል። ከእኔ ይልቅ ለወንድሜ የሚል ማግኘት ብርቅ ነው። ሁሉም ራስ ወዳድ ሆኗል። 2/ ገንዘብን የሚወዱ ይሆናሉ ይሄ ደግሞ ግልፅ ሀሳብ ነው። ሰው በትክክል ገንዘብን መውደድ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ጭምር ያስበለጥንበት ዘመን ነው። ሁሉንም መዘርዘር ይቻላል ግን ለማሳጠር ያክል ቀሪዎቹን አንቧቸው። ስለዚህ እነዚህ ሀሳቦች አንድ በአንድ ካየን በዚህ ዘመን እየሆኑ ያሉ ነገሮች ናቸው። በትክክል ጳውሎስ ያለው የሚያስጨንቅ ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ታዲያ እንዴት ነው በዚህ ጊዜ መሻገር ያለብን? በዚሁ ክፍል  ጳውሎስ በቁጥር 10 እና 14 ያሉ መሰረታዊ ሀሳቦች ማየት ያስፈልጋል 1/ አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዐላማዬን ወዘተ… ታውቃለህ እያለው ነው። ይሄ ማለት ከእኔ የክርስትናና የአገልግሎት ሂወት ተማር እያለው ነው። ✍ዛሬም በዚህ ዘመን ከታላላቆቻችን መማርና ምክር መጠየቅ እጅግ አስፈላጊ ነው። ጥቂት ነገር ካወቅን ብዙ ያወቅን እየመሰለን እንታበያለን። ሚያቃኑን አካሄድን ሊያሳዩን የሚችሉ አባቶችን እንንቃለን። ዘመኑ ለመሻገር ከቀደሙ አባቶች ተሞክሮ እንውሰድ ህይወታቸውን ያለፉበት ህይወት ማወቅና አካሄዳቸውን መከተል አስፈላጊ ነው። ጌታ ይርዳን!! 2/ በቁጥር 14 በተማርከውና በተረዳኸው ፅና እያለው ነው። ✍ይሄ እጅግ መሰረታዊ ነገር ነው። የእግዚአብሄር ቃል ማወቅ እና ባወቁት እውነት መኖር መሻገሪያ ቁልፍ ነው። መፅሀፍ ቅዱስ ማጥናት፤ መንፈሳዊ ትምርቶች መማር ብቻ ባገኘነው አጋጣሚ የእግዚአብሄር ቃል ለማወቅ መትጋት ከዛም በተማርነውና በተረዳነው እውነት ፀንተን መቆም ያስፈልጋል። ይሄንን የማድረግ ህይወት ካለን በዚህ በሚያስጨንቅ ዘመድ በድል እንኖራለን። ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ 🙏 ተባረኩ!!!

  • без подписи

  • የተወደዳችሁ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ይሄ የድምፅ መልእክት ያዘጋጀሁት ለአንድ ናሆም ለተባለ ኦርቶዶክስ ወንድም ነው። ይሄ ወንድም አንድ ቀን ወንጌል እየሰራሁ አግኝቼው ወንጌል ነግሬው ስልክ ተለዋወጥን ከዛም የእነሱ አስተማሪ ያስተማረው ሰማዕታት ያማልዳሉ የሚለው የተሳሳተ ትምርት የያዘ ቪዲዮ ላከልኝ። እና እኔም ይሄንን የመልስ ትምርት አዘጋጅቼ ላኩለት። በእርግጥ በእኛ የመዳን ስራ ላይ የሚጨምረውም የሚቀንሰው ነገር ባይኖርም ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ከስህተት የሚመልስ ትምርት ስለሆነ ለምታውቋቸው ላኩላቸው። እንዲሁም ወንጌል ስትሰሩ ጥያቄ ቢነሳባቸ እውቀት ይሆናችኋል ተባረኩ።

  • እንኳን አደረሰን! የገናን በአል ስናስብ በመጀመሪያ የነበረው ወልድ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን( አምላክ ፅንስ የሆነበትን፤ ዘጠኝ ወር በማህፀን የተቀመጠበትን፤ በመጨረሻም በግርግም ተወለደበትን) ትልቁን መለኮታዊ ሚስጥር እናስብ። ታዲያ ገና ወይም የክርስቶስ የልደት በአል አምላክ ሰው የሆነበትን ጥበብ ማስታወሻ ነው። አምላክ ሰው የሆነው ደግሞ እኛን ከዘላለም ፍርድ ለማዳን የግድ ሰው ሆኖ ተወልዶ የሀጥያተኛ ሞት የሚባለውን የመስቀል ሞት መሞት ስለነበረበት ነው።ስለዚህ ኢየሱስ የተወለደው ለአንተ ለአንቺ ነው። ክብር ከዘለአለም እስከዘላዘም ለኢየሱስ ይሁን። መልካም በአል በድጋሚ!

  • ጎበዝ ተወዳዳሪ ወይም ስፖርተኛ 2ኛ ጢሞ 2፥5 ከላይ በተመለከትነው ፅሁፍ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንደ በጎ ወታደር ሆኖ መከራ እንዲቀበል ነግሮታል። በዚህ ክፍል ደግሞ በውድድር እንደሚሳተፍ ስፖርተኛ ሆነህ ተከተል እያለው ነው። ✍በውድድር የሚሳተፍ ስፖርተኛ ምን አይነት መሆን አለበት? 1 / የሚወዳደርበት ስፖርት ህጎች ጠንቅቆ ማወቅ አለበት። እያንዳንዱ ውድድር የራሱ ህግ አለው። እነዚህ ህጎች ካልተጠበቁ ከውድድር ያስወጣሉ። 2/ በየቀኑ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ልምምድ ማድረግ አለበት። ልምምድ ማያደርግ እስፖርተኛ የመጨረስ አቅም አይኖረውም። 3/ ያገኘው ነገር አግበስብሶ አይበላም። አግበስብሶ ከበላ ክብደቱ ይጨምርና እንኳን አሸናፊ ሊሆን ውድድሩን የመጨረስ አቅም እንኳን አይኖረውም። ✍ስለዚህ የክርስትና ህይወት ከስፖርተኛ ህይወት ጋር እንዴት ተመሳሰለ? 1/ ጳውሎስ ክርስትናን ከእስፖርተኛ ያገናኘበት ሀሳብ ክርስትና የራሱ የሆነ የአኗኗር ስርአት ስላለው ነው። ክርስትና እንደፈለጉ ሆነው የሚኖሩበት ህይወት አይደለም። እንዴት መኖር እንዳለብን በቅዱስ ቃሉ በደንብ ተዘርዝሯል። ስለዚህ እነዚህን ክርስቶስ ያዘዘንን ጠንቅቀን በመተግበር የምንጓዝበት ህይወት ነው። 2/ ክርስቲያን በየቀኑ በፀሎትና የእግዚአብሄር ቃል በማንበብ መትጋት አለበት። ትጉ ያልሆነ አማኝ በህይወቱ ጠንካራ አይደለም ። ማለትም ልክ ቶሎ እንደሚደክም እስፖርተኛ ልፍስፍስ ነው።መንፈሳዊ ጥንካሬ(እድገት) የሚመጣው በብዙ ፀሎትና ብዙ የእግዚአብሄር ቃል በመመገብ ነው። 3/ እስፖርተኛ አግበስብሶ እንደማይመገብ ሁሉ አማኝም አያግበሰብስም። ዝሙት አያግበሰብስም። ፈጣሪ በማይከብርበት መንገድ ብር አያከማችም። ፈጣሪ የማይከብርበት ሀብት አያግበሰብስም።ፈጣሪ በማይከብርበት መንገድ ታዋቂነትንና ዝናን አያግበሰብስም ወዘተ… የሚያግበሰብስ አማኝ እንኳን አክሊል ሊሸለም ክርስትናን ለመጨረስ ይቸገራል። ጌታ ማስተዋሉን ይስጠን!!!

  • በጎ ወታደር 2ኛጢሞ 2፥3_4 ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ጢሞቴዎስ እንደ በጎ ወታደር ሆነህ አብረኸኝ መከራ ተቀበል እያለው ነው። በጎ ወታደር ምን አይነት ነው። 1/ የመጀመሪያው አዛዡን ለማስደሰት ይጥራል ደግሞም ያደርገዋል 2/ በብዙ ስራዎች መጠላለፍ አይችልም። ቅድሚያ ሚሰጠው ለተሰማራበት የውትድርና ስራ ነው 3/ ጠላቶቹን በጀግንነት ተዋግቶ ማሸነፍ አለበት ✍እኛም ዛሬ በዚህ ዘመን ስንኖር በጎ ወታደር ሆነን ክርስቶስን መከተል አለብን። የአማኝ ህይወት ከወታደር ህይወት ጋር ተመሳስሏል። 1/ አንደኛ አዛዥ አለው የክርስትና ህይወት ክርስቶስ የሚባል አዛዥ አለው። ስለዚህ ወታደር የበላይ አዛዡን መስማትና ትእዛዙን የመፈፀም ግዴታ እንዳለበት ሁሉ እኛም አማኞች የበላይ አዛዣችን የሆነውን ክርስቶስ የመስማትና ትእዛዙን የመፈፀም ግዴታ አለብን። 2/ ወታደር በብዙ ስራዎች መጠላለፍ እንደማይችል እኛም አማኞች እግዚአብሄር በማይከብርበት ስራዎች ውስጥ መጠላለፍ እንደሌለብን ነው ሚያሳየው። ወታደር በብዙ ስራዎች ማይጠላለፈው አላማው ስለሚያስቱት ነው። ዛሬም ስራ አንስራ ሳይሆን ከክርስትና ጉዞ የሚያወጣን ስራ መስራት እንደሌለብን ለማሳየት ነው። 3/ ወታደር ጠላቶቹን ተዋግቶ ማሸነፍ እንዳለበት ሁሉ አማኝ ሁል ጊዜ ጠላቶቹን ተዋግቶ ማሸነፍ አለበት።የአማኝ ጠላቶች ሰይጣን እና ሀጥያት ናቸው። ስለዚህ አማኝ ሰይጣንና ሀጥያትን በጀግንነት ተዋግቶ ማሸነፍ አለበት። ክርስቶስ  የውጊያ ስልቱን አሳይቶናል። ሙሉ ትጥቅ ታጥቀን እነዚህን ሁለቱን ጠላቶቻችን ማሸነፍ አለብን። ጌታ ይርዳን!

  • Channel photo updated

  • ትልቁ ታምራት ምንድነው( The biggest miracle ever in our life) ሉቃ 10፥ 17_20 በዚህ ክፍል ኢየሱስ ሰባ ሁለት ሰዎችን መርጦ ስለእግዚአብሄር መንግስት እንዲሰብኩ ላካቸው። እንደነገራቸውም አደረጉ። በስሙም አጋንንት አስወጡ ምናባትም ብዙ ታምራት አርገው ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ተደስተው ሲያያቸው በዚህ ደስ አይበላችሁ ይልቅስ ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ወይም ስለዳናችሁ ደስ ይበላችሁ አላቸው። 1/ ሰዎቹ የተደሰቱት አጋንንት ስለታዘዘላቸው እና ምናልባትም በሽተኞችን ስለፈወሱ ሊሆን ይችላል። ይሄ ተአምር ነው ምንም ጥያቄ የለውም። ዛሬም በእኛ ዘመን አብዛኛው ጊዜ የውጤታማ አገልግሎት መስፈርት ተደርጎ ይወሰዳል። አንድ አገልጋይ አጋንንት ከታዘዘለት፣ በሽተኛ ከተፈወሰለት፣ ስማችን ካወቅ፣ የአንድ ዘመዳችን ስም ከጠራ፣ ስልክ ቁጥራችን ካወቀ ወዘተ በራሱ ያደረገው ይመስል ገድል እንደሰራ ጀግና አድርገን ከማየት አልፈን ልንሰግድለት እንደርሳለን። የምንሰግድ ሰዎችም አንጠፋም። ነገር ግን የእነዚህ ታምራቶች ባለቤት ጌታ ራሱ መሆኑን ማመን አለብን። 2/ እውነት እነዚህ ታምራቶች ብናደርግም ሆነ በሕይወትችን ቢደረግ እጅግ የአስደናቂ ነገር እንዳደረግን ወይም እንደተደረገልን እጅግ ልንደነቅ አይገባም። ምክንያቱም እነዚህ ተአምራቶች ምንም እንዳልሆኑ ሚያሳይ ትልቅ ተአምር በሕይወታችን ቀድሞ ሆኗል። ከመዳናችን በላይ የሚሆን ተአምር ሆኖ አያውቅምም ወደፊትም አይሆንም። በአንድ አማኝ ሕይወት ውስጥ ትልቁ ተአምር መዳኑ ነው። ብዙ ገዜ ስለመዳናችን ሲሰበክ እንቅልፋችን ይመጣል ወይም እንደ ተራ ስብከት ቆጥረን ምንም ሳያስደስተን ሰባኪው ከመድረክ ይወርዳል ። ነገር ግን ድንገት በጉባኤ መካከል አስቁሞን ስማችን ወይም የዘመዳችን ስም ከጠራ በጩኸት ቸርች ድብልቅልቅ እናረጋለን። ይሄ ሚያሳየው መዳናችን እንደ ተአምር አንቆጥረውም። አሁንም መረዳት ያለብን ነገር መዳናችን ነው ከሁሉ የሚበልጠው ተአምር። እጅግ አብዝተን መደሰት ያለብን ስለመዳናችን ሲነገረን መሆን አለበት። ጌታ ኢየሱስ ይባልካችሁ!!!!

  • ከእግዚያብሄር የሆነ ነገር በማንም እና በምንም ሊቆም አይችልም። ሐዋ 5፥ 33_39 ይሄ ክፍል ሙሉውን ስናነበው እግዚአብሄር በሐዋርያቶች እጅ ብዙ ታምራት ሲያደርግ እና ብዙ ሰው ጌታን እያገኘ ከሐዋርያቶች ጋር ሲጨመር የህግ መምህራን እና ሰዶቃውያን ሐዋርያቶን በማሰር በማንገላታት ብሎም በመግደል ወንጌል ለመግታት ሲሞክሩ እንመለከታለን። ነገር ግን የህግ መምህር የነበረው ገማልያ አስደናቂ ንግግር ተናገረ። ምን አለ? ከዛ በፊት ቴዎዳስና ይሁዳ የተባሉ ለራሳቸው ብዙ ተከታይ የነበራቸው ሰዎች እንዴት እንደጠፉ በመናገር የሐዋርያቶች ድርጊትና እየተስፋፋ የነበረው ወንጌል ከእግዚአብሄር ካልሆነ በራሱ ጊዜ ይጠፋል። ነገር ግን ከእግዚአብሄር ከሆነ ማስቆም አትችሉም እያላቸው ነበር። እውነትም ከእግዚአብሄር የነበረው ወንጌል ከ12 ሰዎች ተነስቶ ዛሬ ላይ ደረሰ። ✍ዛሬም በህወታችን እግዚአብሄር ያስጀመራችሁ አገልግሎት ካለ፣ ራዕይ ካላችሁ፣ ህልም ካላችሁ በማንምና በምንም አይቆምም። ችግር አያስቆማቹም። የክፉ ሰዎች ምክር አያስቆማቹም። ምንም ነገር ቢሆን አያስቆማቹም። ምክንያቱም ከእግዚአብሄር የሆነ ነገር በምንም አይቆምም ይፈፀማል እንጂ። ከፈተና ብዛት አገልግሎታችሁ ፣ ራዕያቹ የጣላቹ መልሳችሁ አንሱት። ባለቤቱ እግዚአብሄር የሆነ ነገር አይቆምም። ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ያለብን ከእግዚአብሄር ነው ወይ የተቀበልነው ሚለው ነገር ነው። ሼር በማድረግ ለሌሎች እንዲደርስ አድርጉ🙏 ጌታ ኢየሱስ ይባርካቹ

  • በዚህ ክፋት በሞላበት ዘመን የእግዚአብሄር የልብ ሰው መሆን ይቻላል!    ዘፍ 6: 1~22 ይሄ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ ተፀፅቶ የፈጠረውን ሰው መልሶ ለማጥፋት ሲወስን እናያለን። እግዚያብሄር ሲፀፀት!!!!🤔🤔🤔🤔 ለምንድነው እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ የተፀፀተው? 1/ የፈጠራቸው ሰዎች አመፀኞች ሆኑ። እግዚአብሄር የማይሰሙ ሆኑ። በአጠቃላይ በእግዚአብሄር ላይ አመፁ። ይሄ ድርጊታቸው በጣም አስቆጣው። 2/ የእግዚአብሄር ልጆች ከሰው ልጆች ጋር ተጋቡ። የእግዚአብሄር ልጆች ከማይገባቸው ጋር ተጋቡ ። ከማይገባቸው ጋር ተዳሩ። በወቅቱ ዝሙት ልቅ ሆነ። ከእግዚአብሄር ሀሳብ ውጪ ማግባት መብላት መጠጣት መስከር መዳራት ብዙ አይነት እግዚአብሄርን ሚያስቆጡ ነገርች በምድር ላይ በዙ። ታዲያ እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ ተፀፀተ!! ዛሬም የእኛ ዘመን ኖህ ከኖረበት ዘመን ጋር በብዙ ይመሳሰላል። 1/ በዚህ ዘመን ያለ ሰው እጅግ ክፉና አመፀኛ ነው። በአለማችን ብሎም በሀገራችን ክፋትና አመፅ እጅግ በዝቷል። ሰውን መግደል፤ ማሰቃየት ፤ ከልክ ያለፈ ጭካኔ፤ በሰው ላይ ክፋትን ማሰብ ሌሎችም የክፋት አይነቶች በዝተው ይታያሉ። 2/የዝሙት ርኩሰት ኖህ ከኖረበትም ዘመን ምናልባት እጅግ በዝቶ በዚ ዘመን ይታያል።ወሲብ ልቅ ሆኗል። የስራ ዘርፍ እስከሚመስል አብዛኛው ወጣት በዝሙት ስራ ተሰማርቷል። የዝሙት ቪዲዎች እና ምስሎች በአብዛኛው ሰው እጅ ላይ ይገኛሉ። ዝሙት መስመሩን አልፎ በጣም አስነዋሪ በሆነ መንገድ እየተደረገ ነው። ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ጭምር ተስፋፍቷል። ታዲያ ይሄ ዘመን ከኖህ ዘመን ቢብስ እንጂ አያንስም። 3/ በኖህ ዘመን እግዚአብሄር ያስቆጣው ነገር የእግዚአብሄር ልጆች ከማይገባቸው ጋር በትዳር መጣመራቸው ነበር። ዛሬም ብዙ ክርስቲያን በጌታ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ይጣመራል። ክርስቲያኖች የሌሉ ይመስል በአለም ካሉት ጋር በትዳርና በዝሙት ለመጣመር እጅግ እንፈጥናለን። ከትዳር አጋራችን ውጪ ዝሙት ካደረግን በኖህ ዘመን የነበረው ሀጥያት እየደገምን ነው። በሌሎችም የክፋት ስራዎች ላይ ከአለም ጋር እየተጣመርን ነው። ሳናውቀው አለም እየሆንን ነው ✍ያለንበት ዘመን የኖህን ዘመን ከመሰለ እኛም ኖህ መምሰል አለብን።በዛ አስቸጋሪ ዘመን ኖህ በእግዚአብሄር ፊት ሞገስ አገኘ። እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ በተፀፀተበት ዘመን ኖህ ግን ሞገስ ያገኘ ብቸኛ ሰው ነበር። ምን ነበር ሞገስ የማግኘቱ ሚስጥር??? 1/ አካሄዱ ከእግዚአብሄር ጋር ያደረገ ሰው ነበር። ኖህ የሚሰሩት ክፋቶት ያያል ግን አይከተላቸውም። የሚከተለው እግዚአብሄርን ብቻ ነበር። 2/ ጻድቅ ሰው ነበር። አካሄዱ ከእግዚአብሄር ጋር አድርጎ  ስለነበር እግዚአብሄር ሚወደውን ብቻ ያደርጋል። እግዚያብሄር ስለተከተለ ሀጥያት አይሰራም ነበር። ሰው ሁሉ በአንድ አቅጣጫ(በሀጥያት) ሲሄድ ኖህ ብቻው እግዚአብሄርን በፅድቅ ይከተል ነበር። ✍ዛሬም የዘመኑ ኖህ እንሁን። በእግዚአብሄር ፊት በፅድቅ በመመላለስ፤አካሄዳችን ከእርሱ ጋር በማድረግ እንመላለስ። አካሄዳችን አኗኗራችን በፊቱ ሞገስ ሚያገኝ ሰዎች እንሁን። ሚስጥሩ አንድ ነው በቃሉ የሚወዳቸውና የሚጠላቸው ነገሮች ለይቶ ማወቅ እና ያወቅነውን መተግበር። ጌታ ይባርካችሁ ዳንኤል ቸሩ

  • ከተራ ልፍለፋ እንራቅ!!! 2ኛ ጤሞ 2፥16 ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በዚህ ክፍል እግዚአብሄርን ከማያስከብር ከንቱ ልፍለፋ ራቅ እያለው።ስራቸው እግዚያብሄርን የማያስከብር ከንቱ ልፍለፋ የሆነ ሰዎች ስላሉ ከእነሱ ራቅ እያለው ነው። በዚያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች የራሳቸው መገለጫ ነበራቸው። ከትምህርታቸውም ውስጥ ትንሳኤ ከሙታን በፊት ሆኗል የሚል የተሳሳተ አስተምሮ አንዱ ነበር። እና ጳውሎስ ከእነዚህ ሰዎች ራቅ እያለው ነው።እነዚህ ሰዎች ክርስቲያን ናቸው ግን ውስጣቸው ሞልቶ የነበረው እግዚአብሄርን የማያስከብር ልፍለፋ ነበር። በቤት ውስጥ ከወርቅና ከብር የሚሰራ የክብር እቃ አለ ደግሞም ከእንጨት እና ከሸክላ የሚሰራ የክብር ያልሆነ እቃ አለ።እነዚህ ለክብር የማይሆኑ ከእንጨት የተሰሩ እቃዎች ናቸው። ምሳሌው ግልፅ ነው በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ እግዚአብሄር ሚከብርባቸው አገልጋዮች፣ ዘማሪዎች ፣ምእመናን እና ሌሎችም አሉ። ደግሞ እግዚአብሄር ማይከብርባቸው በተራ ልፍለፋ ሰውን ወደ ገሀነም እያንደረደሩ ያሉ ብዙዎች አሉ። እኛ ከየትኛው ነን??? ምንስ አይነት ትምርት እና ስብከት እየሰማን ነው???ከምን አይነት ክርስቲያኖች ጋር እየዋልን ነው??? የምንሰማቸው ስብከቶችና ትምርቶች፦ 1/ የክርስቶስን መለኮታዊ ማንነት ሚያጎሉ ናቸው ? ወይስ ሰውን ያለቅጥ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው? 2/ ስለመንግስተ ሰማይ እንድናስብና ለዛ የሚበቃ ህይወት እንድንኖር የሚያደርጉን ናቸው ወይስ ምድራዊ ነገር ላይ ብቻ አይምሮአችን እንዲያዝ የሚያደርጉ ናቸው???? ታዲያ ለማወቅ ቀላል ነው። እንንቃ!!! ነቅተን ደግሞ እንሽሽ!!!እንራቅ!!!! ከተራ ልፍለፋ እንራቅ!!!!ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ ራቅ እያለው ነው። ዛሬም የእግዚአብሄር መንፈስ እኛንም ራቁ እያለን ነው።

  • አይነ ስውራኖችን ወደ ኢየሱስ እንድናመጣቸው ታዘናል ሉቃ 18፣40 በዚህ ክፍል በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይነ ስውር ኢየሱስ እያለፈ መሆኑ ሲሰማ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ ብሎ የጮኸበት ታሪክ እናገኛለን። ታዲያ ከአይነስውሩ ብዙ ጩኸት የተነሳ ኢየሱስ ከመንገዱ በመቆም ወደ እርሱ እንዲያመጡት ለተከታዮቹ ሲያዛቸው እናያለን። ይሄንን ክፍል በደንብ ሳጠናው ኢየሱስ አምጡት ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ እንድንማርበት ልቤን ሞላው። ዛሬም በዚህ ዘመን ኢየሱስ አይነስውራኖችን ወደ እኔ አምጧቸው!! ወደ እኔ አስጠጓቸው!! እያለን ነው። ታዲያ አይነ ስውር ማን ነው??? ዮሐ 9፥40~41 በዚህ ክፍል ኢየሱስ የእርሱን መለኮታዊ ማንነት ያልተረዱ ሰዎች አይነስውር እንደሆኑ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ ሲናገራቸው እንመለከታለን። ዛሬም በዚህ ዘመን የክርስቶስን መለኮታዊ ማንነት የማይቀበሉ ሰዎች አይነ ስውር ናቸው። የታወረው ውጫዊ አይናቸው ሳይሆን የክርስቶስ መለኮታዊ ስራ ሊያሳያቸው የሚችለው መንፈሳዊ አይናቸው ነው። ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር እናገናቸው። ወደ እርሱ እናምጣቸው። አይነስውሩ ኢየሱስ ይጠራሀል ሲሉት ልብሱን ጥሎ ተነሳ። ዛሬም አሮጌ ማንነታቸው ጥለው እንዲነሱ እንርዳቸው። ክርስቶስ ወደ እኔ አምጧቸው ብሏል። እርሱ ዛሬም እኛ እንድናመጣቸው እነርሱም እንዲመጡ እየጠበቀ ነው። አዳኙ ከዘላለም ሞት ሊያድናችሁ እየጠራችሁ ነው እንበላቸው። ጌታ ይርዳን።

  • የሕይወት ቃል የሆነው ኢየሱስ ተገለጠ!!!! 1ኛ ዮሐ 1፥1~2 በዚህ ክፍል ዮሐንስ በመጀመሪያ የነበረና ብዙ የሰማነውን የሕይወት ቃል ተገለጠ እያለ ነው። ሶስት ነገሮች እንመልከት፦ 1/ የሕይወት ቃል ብሎታል፦የሕይወት ቃል ማለት የሕይወት ተቃራኒ የሆነው ሞትን አሸንፎ በሕይወት የሚያኖር ማለት ነው። 2/ በመጀመሪያ የነበረ ብሎታል ፦ ዮሐንስ የሕይወት ቃል ከፍጥረት ጅማሬ ጀምሮ (ለዘላለም) የነበረ መሆኑን ለማሳየት ነው። 3/ ብዙ የሰማነውን፦ ዮሐንስ ስለ ሕይውት ቃል በብሉይ ኪዳን ሲነገር ያውቃል እና ብዙ ሰምቷል። ይሄማለት በብሉይ ኪዳን ስለሕይወት ቃል በነቢያት እግዚአብሄር በልዩ ልዩ መንገድ ተናግሯል። ስለዚህ ስለሕይወት ቃል ከመጀመሪያ የነበረውንና የሰማነውን ሲል እነዚህ ሶስት እውነታዎች ለማመልከት ነው። ቀጥሎ ዮሐንስ ይሄ የሕይወት ቃል አይተነዋል ተመልክተነዋል ዳሰነዋል እያለ ነው። 👉ታዲያ ቃል ይታያል? ቃል ይዳሰሳል?? ✍ዮሐንስ ኢየሱስን ነው የሕይወት ቃል ብሎ የገለፀው።በነቢያቶች ብዙ የተነገረለት፤ በአብ ዘንድ ከዘላለም ጀምሮ የነበረው ፤ ብቸኛ የሕይወት ምንጭ የሆነው ኢየሱስ ተገለጠ!!!!! ስለዚህ ዮሐንስ አይቼዋለሁ ዳስሼዋለሁ ብሎ የተናገረለት ኢየሱስ እውነት ነው። ዛሬ በአካል ስለማናየው ውሸት አይደለም ተገልጧል። ዛሬ የሚታየው በአይን አይደለም በእምነት ነው። ስለዚህ በእምነት ሕይወት ከሆነው እርሱ ሕይወትን እንቀበል። ዛሬም እኔ ወንድማችሁ እርግጠኛ ሆኜ ምነግራችሁ ነገር ቢኖር ሕይወት የሆነው ኢየሱስ ተገልጧል። አሜን!!!!!!! ምትጠራጠሩ ሰዎች አትጠራጠሩ ኢየሱስ እውነት ነው። ደግሞ ሕይወት ነው። አሜን!!!!!

  • без подписи

  • የቤተክርስቲያን መሰረት ማቴ16፥14_18 አንድ ቀን ኢየሱስ ሰዎች ስለእሱ ምን እንደሚሉ ለመስማት ፈልጎ ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል ብሎ ደቀመ ዛሙርቱን ጠየቃቸው።እነሱም ከሰው የሰሙትን ሁሉ ነገሩት። ለእናንተስ እኔ ማን ነኝ ብሎ ጠየቃቸው?ጴጥሮስ አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ነህ ብሎ መለሰ። በርግጥ ይሄ መልስ ከጴጥሮስ የተገኘ አነበረም ከአብ ዘንድ የመጣ መገለጥ እንጂ። ታዲያ ኢየሱስ አንድ ንግግር ተናገረ፦ ማቴ16፥18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። ከዚህ ንግግር በመነሳት ሶስት ነገሮች ማየት አለብን 1/ በዚህች አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሰራለሁ አለ። ብዙዎች አለት የተባለው ጴጥሮስን ነው ይላሉ። ኢየሱስ ግን አለት ያለው በጴጥሮስ በኩል አብ የገለጠው አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ነህ የሚለው መገለጥን ነበር።የቤተክርስቲያን መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው የሚለው ዘላለማዊ እውነት ላይ ነው።ዛሬም ቤተክርስቲያን መስበክ፤አብዝታ ማስተጋባት ያለባት ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ነው የሚለው መሰረቷ የሆነው እውነትን ነው። በርግጥ በዚህ ዘመን ይሄንን እውነት ወደ ጎን ብላ ሌላ ነገር እያስተጋባች ነው 2/በዚሁ ጥቅስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኔን ነው ያለው ይሄ ማለት የእርሱ መሆኗን ያሳያል። የቤተክርስቲያን ባለቤት ክርስቶስ ነው። ምናልባት ዘንድሮ ንብረትነታቸው የሰው የሆኑ ብዙ ቤተክርስቲያኖች በሀገራችን ይገኛሉ ግን ትልቅ ስህተት ነው። ሰው የራሱ የግሉ አርጎ እየተጠቀማቸው ያሉ ብዙ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ከክርስቶስ ተወስደው በፓስተሮች እጅ ያሉ ማለቴ ነው። እንንቃ!!! 3/የገሀነም ደጆች አይችሏትም የገሀነም ደጆች የማይችሏት ቤተ ክርስቲያን ነው ክርስቶስ የተከለው። የገነም ደጆችን ሁሉ አሸንፋ ትውልድን ለእግዚአብሄር መንግስት እንድትማርክ ነው ክርስቶስ የተከላት። ዛሬ ግን ብዙ ቤተ ክርስቲያን ከፍተናል የሚሉ የዘመናችን አገልጋዮች ትውልድን ለገሀነም እያመቻቹት ነው። ✍ይሄንን ፅሁፍ የምታነቡ እናንተ ቤተክርስቲያናቹሁ ምን ትመስላለች? ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑን በደንብ ይስተጋባል?የቤቱ ባለቤት ክርስቶስ ነው ወይስ ሰው?ትውልድን ከገሀነም እየተናጠቀ ነው ወይስ ተረት ተረት የሚመስል ምድራዊ ስብከት እየተሰበከለት ወደ ሲዖል እየተነዳ ነው። እንንቃ!!!! ጌታ ማስተዋሉን ይስጠን!!!

  • ሰላም የተወደዳቹ ዛሬም ከባለፈው በመቀጠል እንደ እግዚአብሄር አብ ሁሉ ለክርስቶስ የተሰጡት የማእረግና የክብር ስሞች ቀጥለን እናያለን። 2/ አዳኝ እግዚአብሄር አዳኝ እንደሆነ በብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ተገልጿል። አዳኝነት የመለኮት ስራ ነው ። ሰው ማዳን አይችልም፤ መላአክት ማዳን አይችሉም ፤ ማንም ሰው የሆነ ሁሉ ማዳን አይችልም። የሚያድነው እግዚአብሄር መለኮት ብቻ ነው።የሚከተሉት ክፍሎች እንመልከት 👉ኢሳ 43፥11 /ኢሳ 45፥21_22/1ጢሞ 4፥10 ✍እነዚህ ጥቅሶች ሁሉ እግዚአብሄር አዳኝ እንደሆነ ያስረዳሉ። የሚከተሉት ጥቅሶች ደግሞ እንመልከት 👉ማቴ1፥21/ 1ኛዮሐ4፥14/ ዕብ 5፥9 ✍እነዚህ ክፍሎች ደግሞ በስጋ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ መሆኑን ያስረዳሉ።እንድታነቡ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ። እያንዳንዱ ጥቅስ ካብራራሁኝ እንዳላሰለቻችሁ ብዬ ነው። 3/እረኛ እግዚአብሄር መልካም እረኛ ነው። እረኛ የሚለው ስም ለእግዚአብሄር መጠሪያነት የዋለ ስም ነው። 👉መዝ 23፥1 / ኢሳ 40፥11 ✍እነዚህ ክፍሎች እግዚአብሄር እረኛ እንደሆነ ይናገራሉ። የሚከተሉት ክፍሎች ደግሞ እንመልከት። 👉ዮሐ 10፥11 / ዕብ 13፥20 ✍በእነዚህ ጥቅሶች ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ እረኛ መሆኑን ተገልጿል 4/ አለት እግዚአብሄር ብቻ አለት እንደሆነ በመፅሀፍ ቅዱስ ተጠቅሷል 👉ኢሳ 44 ፥8 ✍ይሄ ክፍል ብቸኛ አለት እግዚአብሄር እንደሆነ ይናገራል። በሌላ ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ አለት እንደሆነ በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልጿል። 👉1ኛ ቆሮ10፥4 ✍ልክ እንደ አብ ሁሉ በዚህ ክፍል ደግሞ ክርስቶስ አለት እንደሆነ ተገልጿል። የተወደዳችው የዚህ ቻናል ቤተሰቦች የዛሬ ፅሁፍ ስለረዘም ሊያሰለቻችሁ ይችላል። ለዛም ነው ብዙ ሳላብራራ የፃፍኩት። ጥቅሶቹን እየመረመራቹ ክርስቶስ ከአብ ጋር እኩል እንደሆነ እንድትረዱ ያግዙአችኋል ብዬ አስባለሁ። የሚፈጠርባችሁ ጥያቄ ካለ መንፈስ ቅዱስ ይፈዳኛል አብራራለሁ ስለዚህ እንድትጠይቁኝ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለብን። ካልሆነ መዳናችን ጥያቄ ውስጥ ነው።ላሳያቹ የሞከርኩት ሰው ሆኖ የመጣው ኢየሱስ እግዚአብሄር አብ በተጠራባቸው የማዕረግና የክብር ስሞች መጠራቱን እንድናውቅ ነው። ይሄ ሚያሳየው ከአብ ጋር እኩል መሆኑን ነው። አው በገሊላ ምድር የተወለደው የተናቀው የተሰቀለው የሞተው እጅግ ብዙ ስቃይ ያየው የማርያም ልጅ ኢየሱስ እርሱ መለኮት ነው። አይቅለልብን!!!! በብዙ ተባረኩ!!!!

  • ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር ነው? በዚህ ዘመን ክርስቶስን የሚያሳንሱ ብዙ ትምህርቶች እየተደጋገሙ ነው። አውቀናል የሚሉ የዘመኑ አስተማሪዎች የክርስቶስን መለኮታዊ ማንነት ለመደበቅ ይሞክራሉ። ሲፈልጉ ከሰው እኩል ያደርጉታል።ሲፈልጉ ከአብ በታች ያደርጉታል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እኔና አብ አንድ ነን ብሏል ዮሐ10፥30 በተጨማሪም ኢየሱስ ራሱ እኔን ያየ አብን አይቷል ብላል ዮሐ14፥9። ስለዚህ ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል መሆኑ በደንብ መረዳት አለብን።ለዚህም እንዲረዳን ለአብ የተሰጡ የአምላክነት ስሞችና ባህሪያቶች ለወልድም እንዴት እንደተሰጡ አንድ በአንድ እናያለን። ዛሬ የመጀመሪያውን እናያለን። 1/ዘላለማዊነት (አልፋና ኦሜጋ) ✍ይሄ ስም ለአምላክ ብቻ የተሰጠ ስም ነው። እግዚአብሄር ብቻ ነው ዘላለማዊ። ማለትም ፊተኛና ኋለኛ(አልፋና ኦሜጋ) የሚለው ስም ለእግዚአብሄር ብቻ የተሰጠ ስም ነው። 👉ኢሳ 44፥6 ራሱ እግዚአብሄር ፊተኛና ኋለኛ እኔ ነኝ ብሎ የተናገረበት ክፍል ነው። ይሄ ማለት እግዚአብሄር አልፋና ኦሜጋ ነው። ታዲያ በተመሳሳይ ይሄ አልፋና ኦሜጋ የሚለው ስም ወልድም ተጠቅሞታል። 👉ራዕ 1፥17 በዚህ ክፍል ኢየሱስ ራሱ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም (አልፋ እና ኦሜጋ) እኔ ነኝ ብሏል 👉ራዕ22፥13 በተጨማሪም በዚህኛውም ክፍልም ኢየሱስ በተመሳሳይ አልፋ ኦሜጋ እኔ ነኝ ብሎ ተናግሯል። ስለዚህ ኢየሱስ እንደ አብ ሁሉ አልፋ እና ኦሜጋ ነው።  ስለዚህ ኢየሱስ እግዚአብሄር ነው። በብዙ ተባሩኩ ቀጣይ ከአብ ጋር አንድ የሚያደርገው ሌላ ባህሪው እናያለን። ዳንኤል ቸሩ

  • 2/አለማዊ ምኞትን እና ሀጥያትን ሙሉ በሙሉ የማስካድ አቅም አለው በተገለጠው ጸጋ ስናምን አለም የሚከተለውን የጨለማ ወይም የሀጥያት መንገድ ክደናል ተለይተናል። ታዲያ የለበስነው ስጋ ሁል ጊዜ በጽድቅ ከምንኖር ይልቅ በሀጥያት ወይም በአለም አሰራር አልፈን እንድንረክስ ይፈልጋል። ስጋችን እና መንፈሳችን ሁሌም ተቃራኒ ናቸው 👉ገላ 5፥17 ይሄ ክፍል በስጋችንና በመንፈሳችን መካከል ያለው የእርስ በርስ ተቃውሞ ያሳያል። ታዲያ እያሸነፈና ሂወታችን እየመራው ያለው ማን ነው??ስጋችን ወይስ መንፈሳችን? ✍በዘመናችን ብዙ ክርስቲያን በአንድ እግሩ መንፈሳዊነት ይጫወታል በሌላ እግሩ አለማዊነትን ይጫወታል። ወይም አንዴ መንፈሳዊ ደሞም አለማዊ እየሆነ ህይወቱን ይገፋል። አለማዊ ምኞቶችን ሙሉ በሙሉ ክዶ በፅድቅ የሚኖር አማኝ ማግኘት ከባድ ሆኗል። እየዋሸን ፣እያጭበረበርን ፣እየዘሞትን ፣እየሴሰንን ወዘተ ከሆነ ገና አለማዊነትን አልካድንም!!!!!! የተቀበልነው ፀጋ ግን አለማዊነትን የማስካድ እና የማስተው ሙሉ አቅም አለው!!!!! 👉ቲቶ 2፥12 ጳውሎስ በዚህ ክፍል የተገለጠው ፀጋ አለማዊ ምኞትንና ሀጥያትን ያስክዳል ይላል። ✍ታዲያ ዛሬም አለማዊ ምኞት መካድ ካቃተን ወደ ፀጋው ዙፏን በእምነት እንቅረብ። ፀጋው አቅም ይሰጠናል። ምክንያቱም አለማዊ ምኞትንና ሀጥያተኝነትን የማስተው ሙሉ አቅም አለው።