tgindex
የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

Статистика
Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
8
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 123
+4 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
466
21 постов
Вовлечённость
22,0%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
329
1/48двое суток
377
1/72трое суток
406

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።" (ኤፌ.2፥10)

  • 'ጉድ አያልቅበት' ዳዊት ፋሲል፣ "መጥምቁ ዮሐንስ የማያገባው[ፖለቲካ] ውስጥ ገብቶ ነው የሞተው።" (ዳዊት ፋሲል) ጌታችን ኢየሱስ ግን ስለ አጥማቂው ዮሐንስ ሲናገር፣ "... እናንተ ወደ ዮሐንስ ልካችኋል እርሱም ለእውነት መስክሮአል። እኔ ግን ከሰው ምስክር አልቀበልም፥ እናንተ እንድትድኑ ይህን እላለሁ እንጂ። እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ፥" (ዮሐ. 5፥33-35) ጌታችን ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ይህን ሲናገር፣ ዮሐንስ በሥጋው ዐርፎ ነበር። "የሚነድና የሚያበራ" ነበረ አለ እንጂ፣ "በማያገባው ገብቶ ሞተ" አላለም። ጥቂት የማይባሉ አገልጋዮች መጥምቁ ዮሐንስን የአመንዝራነት ጉዳይ ፊት ለፊት በመቃወሙና ኀጢአትን በመኮነኑ እምብዛም ደስ አይሰኙበትም። ምናልባት ሰዎች በዚህ መንገድ ወድቀው ቢገኙ "በምን አገባኝ" አልፈው የሚሄዱ አልያም እንደ መጥምቁ በጽድቅ ኀጢአትን እንደ ኮነነው ጳውሎስ፣ ዝሙትን ፊት ለፊት በተቃወመበት በዚያው መንገድ ለመቃወም ድፍረት የሌላቸው "ፈሪዎች" ናቸው። እነዳዊት "የጸጋ ወንጌል" እናቀነቅናለን ይበሉ እንጂ ጸጋን በትክክል አያውቁትም። በተለይም  "የእውነት ቃል አገልግሎት አገልጋዮች" ኀጢአት እንዲኮነን፤ ኀጢአተኝነት እንዲካድ ብዙም የሚሹ አይደሉም። እኛ ግን እንላለን፣ በክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጸጋ ከኀጢአት ያዳነን ደግሞም ከኀጢአት ጋር ስንጋደል የሚያግዘን ነው። ዝሙትን መቃወምና መኮነን ፖለቲካ አይደለም፤ ዛሬ ላይ ጥቂት ያይደሉ በምድሪቱ ያሉ የሃይማኖትም ኾነ የአገር መሪዎች "በዝሙት የነደዱትና ዝሙት ጌጥ እየኾነ የመጣው" እንዲህ ያሉ ዋዘኛ 'አገልጋዮች' በመብዛታቸው ነው። እናም ለክርስቶስ ወንጌል ታመኑ እንጂ፣ በልፍለፋ ብዛት የሚስቱ መምህራንን በመከተል "የሰው ደቀ መዛሙርት" አትኹኑ!

  • “አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር።” (ቲቶ 2፥1)

  • “እግሬ አዳለጠኝ” ባልሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ።" (መዝ. 94፥18)

  • ዳዊት ፋሲል የተባለ "የእውነት ቃል አገልግሎት አጋፋሪ" እና "በጸጋ ስጦታ ተሳላቂ" ሰውን ከሙት ስለ ማስነሣት ሲናገር፣  "... ኑሮ ተወዶ ሰውየውን ባስነሣ ሰውየው ራሱ ይለቀኛል ወይ? ... የሞተውን ሰው እኔ ባስነሳ፣ የተነሳው ሰውዬ፣ እኔን ያስነሳኝ ጠላቴ ማነው ቢለኝስ?!" እያለ ይሳለቃል። ኹሉን በራስ ልክ ለመስፋት ማሰብ እንዴት ያለ ሞ'ኝነት ነው?! በዚህ ንግግሩ፣ 1. ዳዊት ከግብዝነቱ ብዛት ከሞት አንሺ ርሱ ራሱ ይመስላል! 2. ዳዊት ለሌላው ቤተ እምነት (በተለይ በምሳሌ እንደ ጠቀሰው ለወንጌላውያኑ) ያለው ንቀት እጅግ ይደንቃል! 3. ዳዊት፣ የጸጋ ስጦታ "የኢትዮጵያ ኑሮ" ያህል የሚጠላው ከኾነ፣ ምናለ "የጸጋ ወንጌሌ የሚለውን ልፍለፋውን" ብቻ ቢለፍፍ?! እግዚአብሔርና ስጦታዎቹ አይዘበትባቸውም!

  • የክርስቶስን ጌትነት በመስበክ ዘወትር ለምትተጉ ኹሉ ጸጋና ሰላም ይብዛላችኹ፤ አሜን።

  • "... ጥበብ ግን መድኃኒታችን ነው፤ በስጋው መቆረስ የተቤዠን፤ በደሙ መፍሰስ የዋጀን ፤ ለመንግስቱም የመረጠን ለዘለዓለሙ ...አሜን።" (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)

  • 9 авг.502111

    ይህ አጭር ቪዲዮ "ሰዶ"ማዊነት አንድን ገዳም መውረሱን ይናገራል። ከአሥር ዓመታት በፊት "ገዳማት" የሰዶ'ማውያን "መፈልፈያ" ይኾናሉ ብዬ ስጽፍ ብዙ ወዳጆች ኮንነውኛል። በጊዜውም እኛ "መካከል" የነበረ አንድ 'የታወቀ' አገልጋይ በዚህ ነውር መያዙን በብዙ መክረነው አልመለስ ብሎ ሌሎችን ሲተናኮል በአደባባይ በመናገሬ፣ ከግራና ቀኝ ብዙ ወከባ ነበረብኝ። ብቻ ግን እኒህ "ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞች" ይህን ታላቅ ነውር ወደ አደባባይ አምጥተው መናገራቸው ይበል ያሰኛል። የንስሐ አንዱ መንገድ ነውን በአደባባይ መናዘዝና መግለጥ ነውና። ከዚያ በዘለለ ዐመጻ በስሙ ሲጠራ የሚቁነጠነጥ፣ የዐመጻው ደጋፊና አጋፋሪ ብቻ ነው። ዛሬም ግን አልረፈደም፤ ከዐመጻ ለመመለስና ንስሐ ገብቶ መንገድን ለማስተካከል መቼም አይረፍድም። ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም ኾነ፣ ሰዶ'ማዊነትን በእጀ አዙር ለሚደግፉ ሌሎች "አብያተ ክርስቲያናት"፣ ቀኑ ሳይባጅባቸው ቢመለሱ ይበጃቸዋል። እግዚአብሔር አምላክ ለአብያተ ክርስቲያናት ሰዶ'ማዊነትን በግልጥ የሚጠየፉበትን ጸጋ ያብዛላቸው፤ አሜን። የቴሌግራም አድራሻ - https://t.me/ebenezertek

  • 9 авг.451132

    "... ሊቀ ካህናት ዘይቀዉም ሎሙ ለቅዱሳን በደብተራ ስምዕ እንተ እግዚአብሔር ተከላ ዉእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ..." "... እግዚአብሔር በተከላት የምስክርነት ድንኳን ለቅዱሳን የሚቆምላቸው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ..." ሰዓታት ዘሌሊት ❤

  • “ስለእኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹህ የሚሆን የመሢህም ደም እነሆ ስለእኔ ይጮኻል፡፡” (የሐዋርያት ቅዳሴ) (መጽሐፈ ቅዳሴ ጕልህ፡፡ 1994 ዓ.ም፡፡ አዲስ አበባ፣ ትንሳኤ ማተሚያ ድርጅት፡፡ ገጽ 107)

  • ጸጋ ያለምንም ብቁነት የሚሰጥ የእግዚአብሔር ያልተገባ ምሕረትና ሞገስ ነው።

  • 7 авг.542101

    ክርስቶስ እኛን ከኃጢአት በማዳኑ፥ ለንጹሕ ሕይወትና ለመልካም ሥራም አድኖናል።

  • “ከመስቀል ሌላ የመዳን አማራጭ አለ ብሎ ማሰብ ከእውነትና ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ መሆንን ያመለክታል፡፡ መስቀል አያስፈልገንም ከነኃጢአታችን ወደእግዚአብሔር ለመቅረብ እንችላለን ማለት ዘበት ነው፤ ሐሰት ነው፤ ከእግዚአብሔር ተለይቶ መቅረት ካልሆነ በስተቀር የእግዚአብሔር የቅድስና መለኮታዊ ባህርዩ የሚያቃጥል እሳት ስለሆነ በክርስቶስ መስቀል በኩል ካልሆነ ማንም ሊድንና ወደእግዚአብሔር ሊቀርብ አይችልም፡፡ (አበራ በቀለ(ሊቀ ጉባኤ) ፤ 1996 ዓ.ም፤ ትምህርተ ሃይማኖት እና ክርስቲያናዊ ህይወት፡፡ አዲስአበባ ፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት(ማህበረቅዱሳን)፡፡ ገጽ.116)

  • 6 авг.629143

    ፍልሰታን ለጌታ እንዋጅ!   ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ጌታችን ኢየሱስን በመውለዷ ቅድስትና ብጽዕት ናት። የጌታ መልአክ መልአኩ ገብርኤል መጥቶ እግዚአብሔር ሊሠራ የወደደውን ጅማሮ በርሷ መሥራት እንደሚጀምር ሲያበስራትም በመረዳት መታዘዝዋ ስለተጻፈልን፣ ለአዲስ ኪዳን አማኞችም ለጌታ ቃል ጥንቅቅ ባለ መንገድ መታዘዝና በትክክል መረዳትም እዳለብን ከሕይወትዋ እንማራለን። ይህ ብቻ ሳይኾን፣ በዕብ. 11 ላይ እንደ ተጠቀሱት የእምነት አርበኞች፣ የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀትዋ በጸሎትዋ፤  ልምምድና ሥራዋ ደግሞ በተጋድሎዋ ፍንትው ብሎ ይታያል። ስለ እርስዋ የተነገረው ይህና ይህን የሚመስል ኾኖ ሳለ፣ ዳሩ ግን እርስዋን ታክኮ የሚነገረው፣ “በብልሃት የተፈጠረው ተረት” እጅግ አሳዛኝና ብዙዎችን በማሳት የታወቀ ነው። ከነዚህም ውስጥ ግንባር ቀደሙን የሚይይዘው “ሞትሽ በጥር፤ በነሐሴ መቃብር” የሚለው አንዱ ተረት ነው። የቅድስት ማርያምን ሞት ብዙ ኦርቶዶክሳውያንና ካቶሊካውያን “ከመ ምስለ ፍቁር ወልዳ - ልክ እንደ ተወደደ ልጅዋ” ለማድረግ ያላደረጉት ጥረት የለም። በልጅዋና በርሷ መካከል የፍጡርና የፈጣሪ ያህል ግልጥ ልዩነት መኖሩን ያልተረዱ እስኪመስል “ትንሳኤዋን ከልጅዋ ትንሣኤ” ጋር ሲያነጻጽሩ ይስተዋላል። ዛሬም፣ “ትንሳኤዋን እንዳዩት ሰዎች እኛም የርሷን ትንሳኤ እንመለከታለን” በማለት፣ “የፍልሰታ ጾምን” ሲያውጁ እንመለከታለን። የፍልሰታ ጾም ቀዳሚ ዓላማው “ሌሎች የርሷን ትንሳኤ እንዳዩ ለእኛም ትታይልን ዘንድ እንጹም” የሚል ነው። ግን አንድ እውነት አስረግጠን መናገር ይገባል፤ ከክርስቶስ መካከል ሞትን ድል ነሥቶ ከሙታን መካከል የተነሣ ሌላ በፍጹም የለም። ከርሱ በቀር ያሉት ኹሉም፣ በርሱ ኹለተኛ መምጣት መነሣትን ይህን እውነት እንኳንና ቅዱሳት መጻሕፍት የአባቶች ትምህርትም እንዲህ ይላል፣ “ስለዚህም ጌታ … በፈቃዱ ሞተ፤ ከተነሣም በኋላ ዳግመኛ አይሞትም፤ ከትንሣኤው በኋላ ግን ጌታ ይህን አልተናገረም፤ ከሰውም ወገን ማንንም ተነሥ፤ ከመቃብር ውጣ አላለም፤ ዳግመኛ እስከሚመጣባት ቀን ድረስ ለሰዎች ኹሉ አንድ ኾነው በሚነሡበት ቀን ሙታን ይነሣሉ አላቸው።”[1]  “ … ከሙታን ተለይቶ እርሱ ብቻ ስለ ተነሣ ነው እንጂ ሥጋውን ብቻ ሕያው አድርጎ ከኹሉ አስቀድሞ በአስነሣ ጊዜ፤ በተዋሐደው ሥጋ በሞተው ሞትም የሞትን ሥልጣን በአጠፋ ጊዜ ለባሕርያችን ወደ ትንሣኤ የሚያደርስ መንገድ እንደ ኾነ ነገሩ የተገለጠ ነው፤ …”[2] መጽሐፍ ቅዱስ “ዘመኑን ዋጁ” ወይም “ይህ ዘመን ክፉ ስለ ሆነ በማናቸውም አጋጣሚ ጊዜ ተጠቀሙ።” ይላል፤ ለኢየሱስ ክብር ጊዜ ካገኘን (ገላ. 6፥10) የትኛውንም ዕድል መጠቀም ይገባልና። ይም ትክክለኛውን ጊዜ በአግባቡና በትክክል። ቢቻል ደግሞ ከኢየሱስ “ተነጥቆ” ለሰው ወይም ለፍጡር የተሰጠውን “ጊዜና ክብር” ለኢየሱስ ማስመለስ ወይም እንዲመለስ ማድረግ። ከዚህ የተነሳ የፍልሰታ ቀናት ለማርያም ሳይኾን ለኢየሱስ ክብር አምልኮ እንዲቀርብ ሊመለሱለት ይገባቸዋል። የትንሣኤው በኵር፣ ጌታና ንጉሥ ርሱ ብቻ ነውና። ለሙታን ኹሉ ተስፋና ፋና ወጊ ኾኖ በኋለኛው ዘመን በቃሉ ሥልጣን ሊያስነሣቸው የሚመጣው፣ በሞትና በሲዖል፤ በገሃነምና በዲያብሎስ ላይ ሥልጣን ያለው ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ብሉያት፤ ሐዲሳት ብሎም መላው ኦሪትና መዝሙራት፤ ነቢያትም ጭምር ከሙታን መካከል የተነሣውና በመምጣቱ ደግሞ ሥጋ ለባሽን ኹሉ ማስነሣት የሚቻለው መሲሑ ብቻ እንደ ኾነ በአንድነት ይመሰክራሉ፤ አሜን። መንፈስ ቅዱስ በነገር ኹሉ ማስተዋልን ያብዛልን፤ አሜን።     [1] ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፤ 1988 ዓ.ም፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ ምዕ. 59 ክፍል 13 ቊ. 49 ገጽ 209 [2] ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ፤  1988 ዓ.ም፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤  ምዕ. 79 ክፍል 50 ቊ. 51 ገጽ 326 Blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2026/08/blog-post.html?m=1

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የመንግሥቱን ምሥራች የምትናገረው የክርስቶስ መንግሥት ወንጌል፣ ደግሞም ማኅበራዊ ወንጌልም አላት። የወንጌል ሕይወት የሚቆረስ፤ በርኅራኄ የሚሰጥ በጎ ነገር አለ። ከጥልቅ ድህነት ውስጥ የሚቆረስ፤ ስስት የሌለበት ስጦታ። እግዚአብሔር የወንጌል ብርሃን ብቻ ሳይኾን፣ ፊደል ያልቆጠሩ ፊደል ቆጥረው ቅዱሳት መጻሕፍት በቋንቋቸው እንዲያነቡ ማገዝ ታላቅ ሥራ ነው። በዚህ ሥራ እየተጋችሁ ላላችሁ ጸጋና ሠላም ይብዛላችሁ። ፎቶ - ማኅበረ አኅው ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ።

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ — tgindex