Agizachew Tefera
Статистика"አምላኬ ሆይ፥ በፊትህ የምንለምን ስለ ብዙ ምሕረትህ ነው እንጂ ስለ ጽድቃችን አይደለምና ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ ጥፋታችን... ተመልከት።" (ዳን. 9፥18)
- Последний пост
- 6 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 461
- 1/48двое суток
- 528
- 1/72трое суток
- 569
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://www.facebook.com/reel/1024927656808740/ መጽሐፍ ቅዱስ፥ “ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው።” ይላል (ምሳሌ 12፥10)። አራዊት ግን እንዲህ ዐይነት ዕውቀት ማስተዋል ስለ ሌላቸው፥ አንዱ አውሬ ሌላውን የዱር እንስሳ እየበላ መኖሩ ሕገ ተፈጥሮ ነው። ሰው ደግሞ በሰው ላይ ልዩ ልዩ የጭካኔ ተግባራትን ሲፈጽም ከጥንት እስከ ዘመናችን አይተናል። ልጆች እያለቀሱ ወላጆችን በልጆቻቸው ፊት የቀጠፉ ወይም ለልጆቻቸው ሳያስቡና ሳይራሩ ወላጆችን በልጆቻቸው ፊት ያጠፉ ሰዎች የጭካኔ ድርጊት፥ ለሚሰማውና ለሚያየው ሰው ሰቅጣጭ ነው። ከዚህ አንጻር ከታየ፥ ይህ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲመላለስ አግኝቼ፥ ከታች የለጠፍኹት የቪዲዮ ትዕይንት፥ አውሬ ከሰው ተሽሎ የተገኘበት ነው ማለት ይቻላል። እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ኾኖ ኢዮብን፥ “እንግዲህ እንደ ሰው ወገብኽን ታጠቅ እጠይቅኻለኹ፥ አንተም ተናገረኝ።” (ኢዮ. 38፥3) ብሎ ከዘረዘራቸው የፍጥረት ጕዳዮች አንዱ፥ አንስት አንበሳን ያጣቅሳል፤ “በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው፥ በጫካም ውስጥ አድብተው ሳሉ፥ ለአንበሳይቱ ዐደን ታድናለኽን? የልጆችዋንስ ነፍስ ታጠግብ ዘንድ ትችላለኽን?” (ኢዮ. 38፥39-40) የሚለው ይገኝበታል። አንበሳይቱ የያዘቻትን የዱር እንስሳ እናትና በርሷው ቍጥጥር ሥር ያለችውን ግልገሏን እንደ ለመደችው ተራ በተራ መዘነጣጠልና መብላት ትችላለች። ነገር ግን የከለከላት ምን ይኾን? ሮጣ ለማምለጥ ዐቅም የሌላት ግልገሊቱ፥ እናቷን ከአንበሳይቱ አፍ ለማስጣል ያደረገችው የመውጋት ሙከራ፣ የአንበሳይቱን ፊት አንዳች ያልጐዳው ቢኾንም፥ በድርጊቷ ግን ልቧ በጣም እንደ ተነካና ርኅራኄ እንደ ተሰማት እንመለከታለን። ምናልባት አንበሳይቱ እንስት ስለ ኾነችም አንዳች የእናትነት ስሜት ተሰምቷት ይኾናል። ስለዚህ ባልተጠበቀና የሚመለከታትን ሰው አጀብ በሚያሠኝ አኳኋን፣ ከአፏ የገባውን የእናቲቱን ዐንገት ለቅቃ ኹለቱንም ትታቸው ኼደች። እንዲህ ያለ የርኅራኄ ልብ ያጣ ሰው፥ ከዚህ የአውሬ ርኅራኄ አንዳች ትምህርት ያገኛል ብዬ ለጠፍኹት።
https://www.facebook.com/share/p/1JR7jm7PQS/ ለኅትመት የተዘጋጀውን "ጥላ እና አካል" የተሠኘውን ፪ኛውን መጽሐፌን መሠረት በማድረግ፥ ከ"ድንቅ ፍጻሜ" የቴሌቪዥንና ዩቲዩብ ቻናል ጋራ የተደረገው ውይይት ፪ኛ ክፍል ዕንኾ። "ጥላ እና አካል" የተሠኘውንና ለማኅበረ በኵር የወንጌል አገልግሎት የሚውለውን ይህን ዕትም ለማሳተም ዐብራችኹን እንድትቆሙ በሥራው ባለቤት በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጋብዛለን። Mahbere Bekur CBE 1000002276848
https://youtu.be/h-v1CziFJ_U?si=pWSH_37leMKtLvbg ለኅትመት የተዘጋጀውን "ጥላ እና አካል" የተሠኘውን ፪ኛውን መጽሐፌን መሠረት በማድረግ፥ ከ"ድንቅ ፍጻሜ" የቴሌቪዥንና ዩቲዩብ ቻናል ጋራ የተደረገውን ውይይት የመጀመሪያ ክፍል ታደምጡ ዘንድ ዕንኾ።
видео или голосовое, без подписи
https://www.facebook.com/share/p/18KmZdo7db/
share share share
https://vt.tiktok.com/ZSXpHE8pG/ መሬት ላይ ያለው አጿጿም እንዲህም ነው።
"በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ" (ሐ.ሥ. 3፥6) ላለማለት "በናዝሬቱ በእግዚአብሔር ስም ተነሣና ተመላለስ" ይላል ያለው "ሰባኪ" ማን ነበር?
видео или голосовое, без подписи
ዘሚካኤላውያን በዚህ [በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ] ዘመን ለውዝግብ ምክንያት የኾነው ሌላው ሃይማኖታዊ ጕዳይ የእነ አባ ዘሚካኤል የእምነት አቋም ነው። ከአባ ዘሚካኤል ጋራ ስማቸው ዐብሮ የሚነሣው ዋናዎቹ ሊቃውንት አባ ገማልያልና አባ ዐፅቃ ሲኾኑ፥ የተጕለት ሰዎች እንደ ኾኑ ይገመታል። እነዚህ አበው በትምህርት የበሰሉና በሚያራምዱት የእምነት አቋም ላይ አስተያየታቸው የላቀ ኾኖ ይታያል። ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋራ ያጋጫቸው የእምነት አቋም የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔር እንደ ሰው መልክ ያለ መልክ የለውም፤ እግዚአብሔር የአዳምን የሚዳሰሰውንና የሚታየውን የሥጋውን መልክ በራሱ አርኣያና በአምሳሉ አልፈጠረውም። የእግዚአብሔር አርኣያና አምሳል የማይታየው በአዳም ገጽ ላይ የነፋው (እፍ ያለው) መንፈስ ነው። ዮሐንስ በወንጌሉ እንዳለው፥ እግዚአብሔርን ያየው ፈጽሞ የለም። (ያየው ፈጽሞ ከሌለ እዛዲያ (ታዲያ) ማንን ይመስላል እንበል?) እግዚአብሔር አይታይም፤ ሰው የሚያውቀው መልክም የለውም፤ መልኩን ራሱ ነው የሚያውቀው። [እንደዚሁ] ነፍስም ሰው የሚያውቀው መልክ የላትም፤ የእግዚአብሔር አምሳል ስለ ኾነች አትታይም። (ጌታቸው፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ 65።) ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ይህን ትምህርት በተመለከተ ትልቅ ጉባኤ አድርጎ ከእነዚህ ሊቃውንት ጋራ እንደ ተከራከረና “እግዚአብሔር የሰውን መልክ የሚመስል መልክ እንዳለው [በማስረዳት]” የረታው ርሱ እንደ ኾነ ተነግሯል (ጌታቸው፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ 65)። መቼም ይህ ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ በጕልበትና በኀይል የረታበት ካልኾነ በቀር፥ በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ያገኘው ድል እንዳልኾነ ይታወቃል። ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯል ሲባል፥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እንዳለው እግዚአብሔር እንደ ሰው ያለ የሚታይና የሚዳሰስ ግዙፍ አካል አለው ማለት አይደለም። ኾኖም መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ አንዳንድ ክፍሎች እግዚአብሔር የአካል ክፍሎች እንዳሉት የሚናገሩበት ኹኔታ አለና፥ እንደ እኛ ዐይነት ግዙፍ የሰውነት ክፍሎች ያሉት ሊመስለን ይችላል፤ ለምሳሌ በሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እግዚአብሔር፦ · ዐይኖች (ዘዳ. 1፥12፤ መዝ. 32/33፥18፤ 33/34፥15፤ ምሳ. 15፥3፤ 22፥12፤ ሕዝ. 8፥18፤ 20፥17፤ አሞ. 9፥8፤ ዘካ. 4፥10፤ 9፥1፤ 1ጴጥ. 3፥12)፤ · ጆሮዎች (መዝ. 33/34፥15፤ ኢሳ. 59፥1፤ ሕዝ. 8፥18፤ 1ጴጥ. 3፥12)፥ · እጅ (ዘፀ. 9፥3፤ ዘኍ. 11፥23፤ ዘዳ. 2፥15፤ ኢያ. 4፥24፤ ኢሳ. 4፥19፤ 59፥1፤)፤ · እግር (ኢሳ. 66፥1፤ ሕዝ. 43፥7፤ ናሆ. 1፥3፤ ማቴ. 5፥35፤ ሐ.ሥ. 7፥48-50፤ ዕብ. 10፥13) ወዘተ. እንዳሉት ተጽፎ እናነብባለን። ነገር ግን እንደ እኛ ያሉ፥ የሚታዩና የሚዳሰሱ፦ የሥጋ የኾኑ ግዙፍ ዐይኖች፣ ጆሮዎች፣ እጆችና እግሮች አሉት ማለት አይደለም። መንፈስ የኾነውን ትልቁን ጌታ እግዚአብሔርን፥ ኢምንት ለኾነው ሰው በሚገባው መንገድ ለመግለጥ መጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀመበት ቋንቋ እንደ ኾነ የታመነ እውነት ነው። “እግዚአብሔር አያይም” ላሉት ኀጢአተኞች ዘማሪው ምላሽ የሰጠው፥ “ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዐይንን የሠራው አያይምን?” በማለት ነው (መዝ. 93/94፥7፡9)። ስለዚህ እግዚአብሔር ዐይኖች አሉት ማለት ያያል፥ ያስተውላል፥ ይመለከታል፤ ጆሮዎች አሉት ማለት ደግሞ ይሰማል፥ ያደምጣል ማለት ነው እንጂ፥ እንደ እኛ ዐይነት ግዙፍ ዐይኖችና ጆሮዎች አሉት ማለት አይደለም። በመጽሐፈ ኢዮብ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዲህ ይለዋል፥ “በውኑ የሥጋ ዐይን አለኽን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለኽን?” (10፥4)። በርግጥም እግዚአብሔር የሥጋ ዐይን የለውም፤ ሰው እንደሚያይም አያይም። የእይታውን መጠን ስፋቱንና ጥልቀቱን መናገር ያስቸግራል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን፥ “እኛን በሚቈጣጠር በርሱ ዐይኖቹ ፊት ኹሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም” በማለት ገልጦታል (ዕብ. 4፥13)። በውጭ ያለውና የሥጋ ዐይን የሚያየውን ብቻ ሳይኾን፥ እጅግ የጠለቀውንና የረቀቀውን በሰው ውስጥ ያለውን ኹሉ ያያል። “አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም ዕወቅ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ” (መዝ. 139/140፥23-24)። ገና ሳይኾን ወደ ፊት የሚኾነውንም ቀድሞ ያያል። “እኔ በስውር በተሠራኹ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። ያልተሠራ አካሌን ዐይኖችኽ አዩኝ” (ቍ. 16፡17)። እጆችና እግሮች አሉት ማለትም በተመሳሳይ መንገድ የሚተረጐም እንጂ፥ መንፈስ ለኾነው እግዚአብሔር ግዙፍ አካልን የሚያጐናጽፍ ቃል አይደለም። ይህን ዐሎ ብሎ (ክዶ) እንደ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በማሰብ፥ መንፈስ የኾነውን ጌታ እግዚአብሔርን ግዙፍ አካል ያለው አስመስሎ መናገር ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው። ሰው እግዚአብሔርን የመሰለበት መልኩ ሥጋዊ ወይም ግዙፍ ሳይኾን፥ መንፈሳዊ መኾኑን የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስም እንዲህ በማለት አስረድቷል። “በኦሪት የተጻፈውን ቃል ምክንያት አድርገው ለእግዚአብሔር ቀድሞ ሥጋ እንደ ነበረው የሚናገሩ፥ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰውን በእኛ አምሳል እንፍጠር አለ፤ በእኛ አምሳል ያለውም ስለ ሰው ሥጋ ነው የሚሉ አሉ (ዘፍ. ፩፥፳፯)። ነገር ግን እንዲህ አይደለም፤ ርሱ ስለ ውስጣዊ ሰውነታችን (ነፍስ) ተናገረ እንጂ፤ ርሱ ኹልጊዜ በመታደስ ጸንቶ ይኖራልና፤ አፍኣዊ ሰውነታችን (ሥጋ) ይሞት ዘንድ፥ እስኪነሣ ድረስም ይፈርስ፥ ይበሰብስ ዘንድ እንዳለው ነገሩ የታወቀ ነው፤ ውስጣዊ ግን አይሞትም፤ አይፈርስም፤ አይበሰብስም (፪ ቆሮ. ፬፥፲፮)።” (ሃይማኖተ አበው፣ ገጽ 263)። (ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና አባ እስጢፋኖስ ገጽ 232 የተወሰደ)
"ኢትእመኑ ሰብአ እንበለ ዋሕድ ሥላሴ በሳምናዊት ዘመን አምጣነ አልቦ መነኩሴ" የምትልና ከአበው የሰማኋት ጉባኤ ቃና ትዝ ብትለኝ ለጠፍኋት።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ዕድሜ ጠግብ የኾኑትን፣ በሌላቸውና ባልተጻፈላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ እየተቀባቡ፥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ ዘመን ዘለቅ የኾኑትን፥ ያለፈው ሳያንስ፥ አኹን ያለው ትውልድም ወደ ወንጌል እውነት እንዳይደርስ ለማድረግ ዐልመው፥ በየጊዜው የሚነዙትን የስሕተት ትምህርቶች፥ እግር በእግር እየተከታተለ፥ ስሕተታቸውን ለማጋለጥ፥ የወንጌልን እውነት ደግሞ ለመግለጥ፥ እግዚአብሔር በሰጠው ሸክም ተግቶ በመሥራት በርካታ መጻሕፍትን ያበረከተልን ወንድማችን ቴዎድሮስ ደመላሽ፥ አኹንም፦ 1. ሃይማኖታዊ እንክርዳድ ቅጽ 2 2. ለሥዕሏ መስገድ ይገባልን? የተሠኙ ኹለት መጻሕፍትን አሳትሞ፥ መጻሕፍቱ በማተሚያ ቤት ይገኛሉ። “ዝናም የሌላት ደመና” በሚል ርእስ በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ዶ/ር መስከረም ሌቺሳ ለጻፈችው ማስረጃ አልባ መጽሐፍም ያዘጋጀውን ምላሽ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። የታተሙት ኹለቱ መጻሕፍት ከማተሚያ ቤት እንዲወጡና ወደ ተዘጋጀላቸው አንባቢ እንዲደርሱ፥ በቀጣይ ለሚያሳትመውም መጽሐፍ ከወንድማችን ጐን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንድናደርግና ዐብረነው እንድናገለግል እጋብዛለኹ። https://t.me/tewoderosdemelash
“በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፥ እንደ መንፈስ ቅዱስ ችላ የተባለ ወይም ያልታወቀ ከሦስቱ አካላት የለም። ለምሳሌ በአኹኑ ጊዜ (መጽሐፉ የታተመው በ1987 ዓ.ም. ነው)፥ በዐዲስ አበባ 56 አብያተ ክርስቲያናት አሉ። በመንፈስ ቅዱስ ስም የታነጸ ግን አንድም የለም። የሥላሴ 2፥ የእግዚአብሔር አብ 3፥ የመድኀኔ ዓለም 7፥ ይህም ከማርያም ስለ ተወለደ እንጂ ማን ዙሮ አይቶት አያ፥ በጠቅላላ በአስማተ ሠለስቱ ሥላሴ አሐዱ አምላክ 10 አብያተ ክርስቲያናት አሉ። የተቀረው ግን በማርያም፣ በመላእክት፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታት ስም ነው። ምስኪን የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ መንፈስ ቅዱስ ግን፥ አንድም እንኳ የለውም። ያመት እንጂ የወር በዓልም የለውም። ሰዎች ሲደነግጡ፥ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሲሉ በቀር፥ ስሙን ማን አንሥቶት አያ! ከእነዚሁም በጣም ካልደነገጡ በስመ አብ ብቻ ብለው ዝም የሚሉ አሉ።” (ዓለማየኹ ሞገስ፣ ኹሉም ኹሉን ይወቅ፣ ገጽ 140)።
የቀናችው (ኦርቶዶክሳዊት) እምነት ይህች ናት “ዳግመኛም በውነት በመለኮት አንድ የሚኾኑ ሦስቱ አካላት፥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው። በቃልና በሥራ እናመሰግናቸዋለን፤ እንሰግድላቸዋለን። ከዚህ እምነት የተለየ፣ ሌላ ያሰበ፣ ከእሊህ ከሦስቱ አካላት በቀር ሌላ ያመሰገነ የተወገዘ ይኹን።” (ምንጭ፦ ሃይማኖተ አበው ዘቆዝሞስ ምዕራፍ 97 ክፍል 1 ቍጥር 9 ገጽ 433)
ተኣምረ ማርያምና የተሰጠው ቦታ (ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና አባ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ) ካለፈው የቀጠለ በዋናነት በመቅድሙ ላይ ማርያምን በመጽሐፍ ቅዱስ ከምናውቃት የተለየችና አለቅጥ ከፍ ከፍ ያለች፥ ወይም ከአምላክ ጋራ የተካከለች አድርጎ የሚያቀርብበት ኹኔታ ብዙ ነው። ለአብነት ያኽል የሚከተሉትን የመቅድሙን ክፍሎች[1] በዐጭር በዐጪሩ እንመልከት፦ · ተኣምረ ማርያም፥ “ፍጥረት ኹሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ” ይላል፤ F መጽሐፍ ቅዱስ ግን፥ “እግዚአብሔር ኹሉን ለርሱ ለራሱ ፈጠረ” ነው የሚለው (ምሳ. 16፥4)። ሌላውም ከዚህ በታች የተዘረዘረው ኹሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት አይደለም፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋራ የሚጣላ የስሕተት ትምህርት ነው እንጂ። · “አዳምና ሔዋን የተፈጠሩት እመቤታችን ከእነርሱ እንድትወለድ ነው” ይላል፤ F እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን የፈጠረው ማርያም ከእነርሱ እንድትወለድ ብሎ ነው የሚል ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ከቶ አናገኝም። ከላይ እንዳየነው ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሔር ክብር ነው። · “የእመቤታችን ክብሯም ምስጋናዋም ተጽፎ ቢኾን ምን ብራና በቻለው ነበር” ይላል። F ይህ በወንጌለ ዮሐንስ ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ያደረገው ሌላ ብዙ ነገር እንዳለና እያንዳንዱ ቢጻፍ መጻሕፍት ቀርቶ ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል (ዮሐ. 21፥25) ተብሎ ከተነገረው የተኰረጀና ማርያምን አለቅጥ ከፍ ያደረገ አገላለጥ ነው። · “እመቤታችን ማርያም ከአዳም ጀምሮ እስከ አብርሃም፥ ከአብርሃም እስከ ሙሴ፥ ከሙሴ እስከ ዳዊት ድረስ በብዙ ምሳሌ እየታየች ትነገር ነበር … እመቤታችን በነቢያት ትነገር ነበር፤ በሐዋርያትም ትነገር ነበር” ይላል። F ከአዳም ጀምሮ ሴቲቱ ዐልፎ ዐልፎ ብትጠቀስም፥ በዋናነት በመጽሐፍ ቅዱስ ሲነገር የነበረው ግን ስለ ሴቲቱ ዘር እንጂ ስለ ሴቲቱ አይደለም። ከአዳም እስከ አብርሃም ከአብርሃም እስከ ሙሴ፥ ከሙሴ እስከ ዳዊት ሲነገር የነበረው ስለ ርሷ ሳይኾን፥ ከርሷ ሰው ኾኖ ስለሚወለደው መሲሕ ነው። ራሱ ባለቤቱ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው በማለት የተናገረው ለዚህ በቂ ምስክር ነው (ዮሐ. 5፥39፤ እንዲሁም ሐ.ሥ. 3፥21-26)። እውነታው ይህ ኾኖ ሳለ ታዲያ፥ ስለ ክርስቶስ የተነገረውን ለማርያም መስጠት ለምን አስፈለገ? ርሷን ከፈጣሪ ጋራ ለማስተካከል አይደለምን? ነቢያትና ሐዋርያት የተናገሩትም ስለ መሲሑ እንጂ ስለ እናቱ አይደለም። እናቱን ከርሱ ጋራ በተያያዘ ሲናገሩ ከመጥቀስ ባለፈ ርሷን ዋናና ማእከል አድርገው የተናገሩት ነገር የለም። ለምሳሌ ከነቢያት ኢሳይያስ፥ “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” (ኢሳ. 7፥14) ሲል፥ ሐዋርያው ጳውሎስ ደግሞ፥ “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ. 4፥4) ብሏል። በእነዚህ ውስጥ እናቱ፥ “ድንግል” እና “ሴት” ተብላ ብትጠቀስም፥ የትንቢቱም ኾነ የፍጻሜው ማእከል ዐማኑኤል፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነው እንጂ እናቱ አይደለችም። · “ሥጋዊ ነገርን ከማሰብ መጠበቅ ከአዳም ልጆች ለማን ተሰጠ፤ ኀጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ለመላእክት እንኳ አልተሰጣቸውም [ለማርያም ነው እንጂ]፤ ከእመቤታችን በቀር ኀጢአትን ያልሠራ የለም” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከማርያም በቀር ሳይል፥ ሰው ኾኖ ኀጢአት ያልሠራ ማንም እንደሌለ በግልጥ ይናገራል (1ነገ. 8፥46፤ ኢዮ. 4፥17-19፤ መዝ. 142/143፥2፤ ምሳ. 20፥9፤ መክ. 7፥20፤ ሮሜ 3፥9-11፡23፤ ገላ. 3፥22)። ስለ ክርስቶስ ሲናገር ብቻ ግን፥ “ከኀጢአት በቀር በነገር ኹሉ እንደኛ የተፈተነ” መኾኑን፥ ኀጢአት የሌለበት መኾኑንም በግልጥ ይናገራል (ዕብ. 4፥15፤ ዮሐ. 8፥46፤ 1ጴጥ. 2፥22)። ማርያምን ለርሷ በተገባ ክብር ማክበር ሲገባ፥ ባልተነገረላት ክብር ለማክበር መሞከር፥ የክርስቶስን ማንነት ለርሷ ለመስጠትና ርሷን በርሱ ስፍራ አስገብቶ ለማምለክ እንጂ ሌላ ዐላማ የለውም። ይቀጥላል [1]ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ ተኣምረ ማርያም፣ ገጽ 3-4፡15፡16።
ተኣምረ ማርያምና የተሰጠው ቦታ (ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና አባ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ) ዶ/ር አምሳሉ አክሊሉ ተኣምረ ማርያምንና ተኣምረ ኢየሱስን ጠቅሰው፥ “በኢትዮጵያ ውስጥ ቅድስት ማርያምን የአምላክ ያኽል ማክበር የተመሠረተው በነዚህ መጻሕፍት መስፋፋት የተነሣ ሳይኾን አይቀርም”[1] ብለዋል። በዋናነት ደግሞ በተኣምረ ማርያም ላይ እንደ ኾነ ለማንም ግልጥ ነው። ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ማርያምን አስመልክቶ ለመሠረታቸው ትምህርቶችና ለሠራቸው ሥርዐቶች ዋና መሠረቱ ይኸው ተኣምረ ማርያም ነው። የዚህ መጽሐፍ ተጽዕኖ ምን ያኽል እንደ ኾነ፥ ቀጥሎ የቀረበው የፕ/ር ጌታቸው ኀይሌ ምስክርነት ይገልጣል፤ “በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን (ኢኦተቤ) ምእመናን ላይ ከማንኛውም መንፈሳዊ ድርሰት (ከመጽሐፍ ቅዱሱም ጭምር) የበለጠ ተጽዕኖ” ያደረገው ተኣምረ ማርያም[2] ነው። ተኣምረ ማርያም በመጀመሪያ የተጻፈው በአውሮፓ ሲኾን፥ ከዚያ ወደ ሶርያና ኢየሩሳሌም ዘልቆ፥ እንደ ገና ወደ ምድረ ግብጽ ደርሶ፥ ወደ ዐረብኛ ተተርጕሟል።[3] “የማርያምን ተኣምራት መሰብሰብ የጀመረው ሂልደፎንስ የሚባል እስፓኝ ውስጥ ቶሌዶ የምትባል ከተማ ጳጳስ ነበር።”[4] በኢትዮጵያ ወደ ግእዝ መተርጐም የጀመረው ደግሞ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ነው። ርሱ “በፈረንሳይ፣ በእስፓኝ፣ በግብጽ፣ በፍልስጥኤም የተሠሩትን ተኣምሮቿን ወደ ግእዝ መተርጐም በሰፊው ቀጠለበት።”[5] ይህም የተኣምረ ማርያም መነሻ በአብዛኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደ ኾነች ፍንጭ ይሰጠናል። የትርጕሙ ሥራ የተስፋፋውና በከፍተኛ ኹኔታ በሥራ ላይ የዋለው ግን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ነው። ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት (በ1433 ዓ.ም.)፥ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደ ተተረጐመ የተኣምረ ማርያም መቅድም ይናገራል። ከዐረብኛ ተተረጐመ ቢባልም፥ በውስጡ የያዘው፥ “ኢትዮጵያ ውስጥ በርሱ ዘመን (በተለይም ርሱን በመደገፍና ተቃዋሚዎቹን በመኰነን)” ማርያም ሠራች ያለውን ዐዳዲስ ተኣምራትም ጭምር ነው።[6] ራሱ ተኣምረ ማርያም ስለ ራሱ እንደሚመሰክረው ደግሞ፥ “ይህ የሥርዐት መጽሐፍ የምስር ዕፃ (ክፍል) ከሚኾን ከመዓልቃ ቦታ ከሐዋርያው ከማርቆስ መንበር ተገኝቶ የወጣ ነው”[7] ይላል። ነገር ግን “በቅብጥ (ኮፕቲክ) ወይም በዐረብኛ የዚህ መጽሐፈ ሥርዐት አቻው አልተገኘም። ስለዚህ የተኣምረ ማርያም መቅድም ደራሲ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እንደ ነበር መገመት አያዳግትም።”[8] ተኣምረ ማርያም በራሱ መቅድም ላይ “የሥርዐት መጽሐፍ” ነኝ ይበል እንጂ፥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የሥርዐት መጻሕፍት ብላ ከቈጠረቻቸው መጻሕፍት መካከል የለም። መጽሐፉ እንደ ሥርዐት መጽሐፍ ባይወሰድም፥ በውስጡ ያስተላለፋቸው ትምህርቶችና የሠራቸው ሥርዐቶች ግን ቀስ በቀስ ተቀባይነት አግኝተው እስካኹን ሕዝቡ እያመናቸውና እየፈጸማቸው ይገኛሉ። ዐፄው ተኣምረ ማርያምን “የሥርዐት መጽሐፍ” ያለው ማርያምን አስመልክቶ ሊያስተዋውቃቸው ለፈለጋቸው እንግዳ ትምህርቶችና ሥርዐቶች፥ እንደ ዋና ምንጭና መሠረት እንዲቈጠር ፈልጎ በዐላማ ያደረገው እንደ ኾነ ግን ከማመን አናመልጥም። ተኣምረ ማርያም የማርያምን አምልኮ መሠረት ለማስያዝ ስልታዊ በኾነ መንገድ የተደረሰ ሥራ መኾኑንም መጽሐፉ በውስጡ የያዛቸውና ወደ ፊት የምናየቸው ዋና ዋና ርእሰ ጕዳዮች ያስረዳሉ። ይቀጥላል [1]አምሳሉ፣ ዐጭር የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ፣ ገጽ 50። [2] ጌታቸው፣ከግእዝ ሥነ ጽሑፍ ጋራ ብዙ አፍታ ቈይታ፣ ገጽ 132። [3]ሥርግው (ዶ/ር)፣ዐማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት (ቍ. 4)፣ ገጽ 97። [4]ጌታቸው፣ ከግእዝ ሥነ ጽሑፍ ጋራ ብዙ አፍታ ቈይታ፣ ገጽ 365። [5]ጌታቸው (ተርጓሚ)፣ ደቂቀ እስጢፋኖስ፣ ገጽ 25። [6]ጌታቸው፣ ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች፣ ገጽ 61። [7]ተስፋ፣ ስድሳ አራቱ ተኣምረ ማርያም፣ ገጽ 11። [8]መብራቱ ኪሮስ (ቀሲስ፣ ዶ/ር)፣ አኰቴተ ቍርባን፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐተ ቅዳሴ መሠረት፣ ታሪካዊ እድገትና ይዘት (2ኛ ዕትም) (ዐዲስ አበባ፦ ጃጃው ዐታሚዎችና ዴቨሎፐርስ ኀላ.የተ.የግ.ማኅበር፤ 2012 ዓ.ም.)፣ ገጽ 198።
видео или голосовое, без подписи
በምድራችን የስሕተት ትምህርቶችን ከማ*ጋ*ለ*ጥ በሻገር፥ እውነተኛውን የመዳን መንገድ መግለጥ ያስፈልጋል። በዚህ አቅጣጫ የሚጻፉ መጻሕፍት በሚገባ መሠራጨትና ወደ ተጻፈላቸው ወገኖች መድረስ አለባቸው። “ሓጢኣተኛ ዘፅድቕ ፀጋ እግዚኣብሄር” በሚል ርእስ፥ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ በትግሪኛ የተዘጋጀውን የወንድማችንን የኀይሉ ጫቕሉን በነገረ ድኅነት ላይ የተጻፈውን መጽሐፍ በማሠራጨት የወንጌል እውነት ለወገኖች እንዲደርስ፥ ሸክም ያላችኹ ወገኖች ከወንድማችን ጐን እንድትቆሙ በእግዚአብሔር ፍቅር እንጋብዛለን። (0931112108) መጽሐፉ ወደ ዐማርኛ ተተርጕሞ የአርትዖቱ ሥራ እየተሠራ መኾኑንና ወደፊት በዐማርኛም ታትሞ ለንባብ እንደሚበቃ ይጠበቃል።