tgindex
Nolawi ኖላዊ

Nolawi ኖላዊ

Статистика

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ! 0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

Последний пост
16:31
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
16
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
9 184
+27 за 2 дн.
Сутки
+7
+0,08%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
956
26 постов
Вовлечённость
10,4%
к подписчикам
Постов в день
2,3
всего 29
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
810
1/48двое суток
928
1/72трое суток
1 001

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 16:311672

    видео или голосовое, без подписи

  • Live stream finished (1 hour)

  • እግዚአብሔር ትልቅ ነው 3 የመጨረሻው ክፍል ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

  • 2:00 ይጀምራል

  • Live stream started

  • ዛሬ ዓርብ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት  ላይ ትምህርታችን ይጀምራል :: የትምህርታችን ርእስ " እግዚአብሔር ትልቅ ነው 3 መዝ 144 ፥ 3 ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል። ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ https://t.me/Nolawii

  • ቅድስት ማርያም/4   ናዝሬት   “በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ ።” ሉቃ. 1 ፡ 26-27 ።   መልአኩ ገብርኤል የተላከው ናዝሬት ወደምትባል የገሊላ ከተማ ነው ። ገሊላ ሰሜናዊ የእስራኤል ግዛት ነው ። እስራኤል ሦስት ታላላቅ ግዛቶች ነበሩአት ። ደቡቡ ይሁዳ ፣ ማዕከሉ ሰማርያ ፣ ሰሜኑ ገሊላ ይባላል ። በገሊላ ከሚገኙ አነስተኛ ከተሞች አንድዋ ናዝሬት ናት ። ናዝሬት በብሉይ ኪዳን ስምዋ አልተጠራም ። ታዋቂ የሆኑ ድርጊቶች ያልተከናወኑባት ፣ ስመ ጥር ሰዎች ያልወጡባት ፣ የጦርነትም የዕድገትም መዝገበ ቃላት ያላወቃት አነስተኛ መንደር ነበረች ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱን ብሥራት የላከው ወደዚህች ወደ ናዝሬት መንደር ነው ። የናዝሬት መንደር የተናቀች ነበረች ። ወደ ተናቀችው መንደር ታላቅ የምሥራች መጣ ። ጌታችን ለልደቱ ቤተ ልሔምን እንደ መረጠ ፣ ለፅንሰቱ ናዝሬትን መረጠ ። እርሱ ከሚጠራበት ስም ገናናው “የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚለው ነው ። የተናቁት ወዳጅ ፣ የምስኪኖች አለኝታ መሆኑን የሚያሳይ ስም ነው ። ናዝሬት በቅርብ ከተሞች እንኳ የተናቀች ለመኖሪያነት የማትመረጥ አነስተኛ መንደር ነበረች ። ማንም የማያውቃት ያቺ ናዝሬት መላው ዓለም ያውቃታል ። የተናቁትን ማክበር እግዚአብሔር ያውቃል ። ትላንት የተናቁ አገራትና ከተሞች ዛሬ እየተወደዱ መጥተዋል ። በተቃራኒው የተከበሩ አገሮችና መንደሮች ተንቀዋል ። በዓለም ላይ በጣም ደምቀው የደበዘዙ ከተሞች ብዙ ናቸው ። ሮም ፣ ባቢሎን ፣ እስክንድሪያ ፣ አንጾኪያ ፣ ቍስጥንጥንያ/ኢስታንቡል ፣ አኵሱም በጣም ስመ ጥር የነበሩ የዓለማችን ከተሞች ናቸው ። ዛሬ ግን ደብዝዘዋል ። ናዝሬት ግን በትንሽ ጀምራ በመላው ዓለም ትታወቃለች ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ በሚለው መጠሪያ ከአምላክ ጋር ስትነሣ ትኖራለች ።   እግዚአብሔር የተናቁ አገሮችን ያከብራል ። ዛሬ አገራችን ከዓለም መጨረሻ ሁና ብትታይ እንኳ እግዚአብሔር ቀኝ ኋላ ዙር ያለ ቀን አንደኛ ትሆናለች ። ይህ እንዲሆን የምሥራቹን መቀበል ያስፈልጋል ። ወንጌል በራሱ በእግዚአብሔር ፣ በአበው ፣ በነቢያት ፣ በካህናት ፣ በመልአክ ፣ በድንግል ማርያም ፣ በሐዋርያት የተሰበከ ትውልደ ሐረግ ያለው መልእክት ነው ። ይህን ወንጌል አምኖ መኖር ክብርን ያሰጣል ። እግዚአብሔር ናዝሬትን ብቻ ሳይሆን ታናሽ ብላቴና የምትሆነውንም ድንግል ማርያምንም አከበረ ። እርስዋ ራስዋ አክባሪነቱን ስትገልጥ፡- “እነሆም ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤” አለች ።(ሉቃ. 1 ፡ 48) ። ከዛሬ ጀምሮ የሚለውን እናስተውል ። ከዚህ ቀን በፊት ማንም የተዘጋጀላትን ክብር አላወቀም ነበር ። እርስዋም አላወቀችም ነበር ። አሁን ግን የአምላክ እናት ሁናለችና ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እንደሚሏት ተናገረች ። እግዚአብሔር የተናቁ መንደሮችን ፣ የተናቁ ሰዎችን ያከብራል ። እመቤታችን አሁንም በተደነቀው ጸሎትዋ፡- “የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና” ብላለች ። እግዚአብሔር ያያል ። የተናቁትን ለክብር ቀን ያስባል ። ሔዋን ተዋርዳ ነበር ፣ አሁን አያት ። በልጅ ልጅዋ በድንግል ማርያም በኩል የሔዋን ውርደት ተካሰ ። ሔዋን ካመጣችው ውርደት ለድንግል ማርያም የሆነው ክብር በለጠ ። በዚህም የሴት ዓለም ከበረ ።   በኮልታፋ ምላሳችን ሰዎች ይንቁን ይሆን ? እስራኤልን እየመራ ያወጣው ሙሴ ኮልታፋ ነበር ። እግዚአብሔር ከአፌ ቅቤው ከአሮን ይልቅ ሙሴን መረጠ ። እንደ ሰው ቢሆን ቃላተኛው አሮን የሕዝብ መሪ ፣ ሙሴ ደግሞ ካህንና ጸሎት አሳራጊ በሆኑ ነበር ። እንደ ሰው ቢሆን ብሉያትን ያጠና ጳውሎስ መምህረ አይሁድ ፣ ጴጥሮስ መምህረ አሕዛብ ተደርገው በተደለደሉ ነበር ። ኃይላችን የማያግዘው ፣ ድካማችን የማይመልሰው እግዚአብሔር በእውነት ድንቅ ነው ። እኔም በልቡናዬ ጉልበት ተንበርክኬ አመሰግነዋለሁ ። ደካማ የሆነ የአካል ክፍል ስላለን ፣ ቁመናችን ስለማይማርክ ሰዎች እንደ ናቁን እናስብ ይሆን ? እነ ኤልያብን ትቶ አጭሩን ዳዊትን ፣ እነ ቀያፋን ጥሎ ቁመተ ትንሽ ዘኬዎስን የመረጠ አምላክ ዛሬም አሠራሩ አልተለወጠም ። ከተናቀች አገር በመምጣታችን እየተጨነቅን ይሆን ? እግዚአብሔር ከፍታን ሲያወርሰን ማንም አያግዘውም።   ይቀጥላል ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም.

  • 13 авг.1 183182

    видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.1 193454

    ገለል በል ከፊቴ አገርህ ከድታህ፣ ወገንህ ለግድያው ስም ሰጥቶ መሣሪያ የወደረብህ ፣ ጥፋትህ ጠፍቶህ ፣ ያልበደልከውን ካስ ስትባል ግራ የገባህ ፣ ጥፋትህንም ገዳይህንም ዛሬ ስታያቸው ሕልም ዓለም ውስጥ የገባህ ፣ እመጣለሁ ብለህ ደውለህ ሳትደርስ የቀረኸው አንተ ብላሽ ገለል በል ከፊቴ ። ግንድ ተማፅኖ በሚዳንበት አገር የአምላክህን ስም ጠርተህም የሚራራ ያጣኸው አንተ ጀምር ገለል በል ከፊቴ። ምድር የጌታ ነው ብለህ ተቀምጠህ የሰው ሲሆንብህ ፣ መንገድ የእግዜር ነው ተብለህ አድገህ ሰው አምላክ ካልሆንሁ ሲልህ ጭልም ያለብህ አንተ እሸት ገለል በል ከፊቴ ። ከመቼው አድገህ ለሞት በቃህ፣ ለማታውቀው አያትህ ዕዳ ከፋይ ለመሆን በቃህ። አንተ ሠርክ በጅምር ገለል በል ከፊቴ ። እንዳላለቅስልህ ለማልቀስም ቀን ይፈልጋል ፣ የማልቀሻዋ ቤትም ቤተ ፈያት /የወንበዴ ዋሻ/ ሆናለች። ወንድ በጠላው ዘመን ተወልደህ ፣ ወጣትነትህ እንደ ዕዳ በሚቆጠርበት ምድር ተገኝተህ ፣ በቅጡ መኖር በቅጡ መሞት አቅቶህ የተሰቃየኸው አንተ ጎበዝ ገለል በል ከፊቴ። ስለ ወንድ ልጅ አምላክ ብለህ ስትለምን የተጨከነብህ ፣ እናትህን ልጅህን እያሰብህ በሜዳ የቀረኸው ፣ ገዳይህ በደሉ እንዳይጠፋ ፎቶ አንሥቶ የሚገድልህ ፣ ቪድዮ ቀርፆ ላይበላህ የሚያርድህ አንተ ወጣት ገለል በል ከፊቴ ። የወጣት ሞት ፣ የወንድ ልጅ አበሳ ሃምሳ ዓመት ሞላው ፣ በነጻ ኖረህ በዋጋ ትሞታለህ። ለመብል የረሳህ ለጥይት ያስታውስሃል ። አንተ በሥጋ ሞትህ፣ እኛ ግን በሕሊና እንሞታለን ። አንተ አንድ ጊዜ ሞትህ ቋሚው ደጋግሞ ይሞታል። የሰው አንገት አንድ ነውና ሰው የሆነ ሁሉ ያዝናል። አንተ ስቃይህ ለአንድ ሰዓት ነው፣ ገዳዮችህ ግን ዘመናቸው ሁሉ የስቃይ ነው። ደምህን ደመ ኢየሱስ ይዋቀሰዋል ! አልተሸካከፈም ያገሬ አዝመራው ፣ ዛላው ዛላው ወድቋል በየጎዳናው ። የሚፈሰው ደም ይብቃ!!!

  • 11 авг.914213из Nolawii

    የመጽሐፍ ስጦታ ተማሪዎች የሆናችሁ ና መጽሐፍ መግዛት የማትችሉ ከዲያቆን አሸናፊ መኰንን መጻሕፍት በስጦታ ታገኛላችሁ። 0911699907 በቴሌግራም አሳውቁን! እነዚህ መጻሕፍት በስጦታ እንዲተላለፉ የገንዘብ ስጦታ ያደረጋችሁ ወዳጆች እግዚአብሔር በሰማያዊና በምድራዊ በረከት ይባርካችሁ!

  • 11 авг.9078из Nolawii

    የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! በዚህ ክረምት ከዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሥራዎች የመጻሕፍት ስጦታ ለተማሪዎች፣ ለእስረኞች፣ መግዛት ለማይችሉ ፣ ለቤተ መጻሕፍት ለመስጠት አስበናል። ይህን በረከት ለመሳተፍ የምትፈልጉ ቀጥሎ ባለው አካውንት የፈቀዳችሁትን መስጠት ትችላላችሁ ። ያስገባችሁበትን በቴሌግራም 0911699907 ላኩልን ! የእግዚአብሔር በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሸናፊ መኰንን ወርቁ Ashenafi Mekonnen worku  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000165078482

  • 11 авг.1 599397

    ቅድስት ማርያም/2 የሰው ልጆች በያዙት ነገር የማይረኩት ሁልጊዜም የሚመጣውን የሚናፍቁት መንግሥተ ሰማያት ሲደርሱ እንዲያርፉ ሁነው ስለ ተሠሩ ነው ። ሰይጣን ሰዎችን በሽንገላ ከጣለበት ነገር አንዱ ገንዘብና ሥልጣን ቢኖራችሁ እርካታን ታገኛላችሁ ብሎ በማታለል ነው ። ሰዎች ገንዘብና ሥልጣንን ሲይዙ የሚገጥማቸው ባዶነትና እዚያ ለመድረስ የከፈሉትን ተጋድሎ ማስታረቅ አቅቷቸው ራሳቸውን በተስፋ ማጣት ይጎዱታል ። የሰው ልጆችን በእቅፉ ሊያስጠጋና ዘላለማዊ መልስ ሊሆናቸው አምላክ ወደ ምድር መምጣት ፈለገ ። የአምላክ ጉብኝት ዕለታዊና ያልተቋረጠ ቢሆንም ይህ መምጣት ግን በሥጋ መገለጥ ነው ። በክርስቶስ መምጣት ዓለም መልካም አልተደረገለትም ፣ መልካም ሆነለት ። የማያቋርጥ ደግነት ፈሰሰ ። ሁለት መልእክተኞች ከንጉሡ ፊት ፊት ይሄዳሉ ። አንደኛው ሰማያዊ ፣ አንደኛው ምድራዊ ነው ። ምድራዊ ጥሪት ሁለቱም አልነበራቸውም ። በሰማያዊ ጸጋ አሸብርቀዋል ። እነርሱም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና መጥምቁ ዮሐንስ ናቸው ። ለአምላክ መወለድ ፣ ለሰው ዘር መዳን የምሥራች እንዲነግር የተላከ መልአኩ ገብርኤል ነው ። መልአክ በወደቀ ጊዜ አምላክ መልአክ ሁኖ ለምን አላዳነም  ሰው በወደቀ ጊዜ እንዴት ሰው ሆነ አላለም ። መልአኩ በሰው መዳን ደስተኛ ነበረ ። የአምላክ ሰው መሆን ሂደት በሰማይ በተሰማ ጊዜ ታላቅ ደስታ ነበረ ። ዓለም በተፈጠረበት ቀን ዓለም እንዲድን ፣ ብሥራት እንዲነገር መልአኩ ተጠራ ። ባለቤቱ ሰማይን ሳይሰናበት በምድር ይገኛል ። ምድርን እንግዳ ሳይሆንባት በሥጋ እንግድነት ይገለጥባታል ። የእግዚአብሔር ልጅነቱን ሳይለቅ የሰው ልጅ ይባላል ። ለአምላክ ልጅ የሰው ልጅ መባል እንግዳ ነው ። ካለንበት የመጣው ካለበት ሊያደርሰን ነው ። ሕዝብና አሕዛብ ሁሉ በዘመናት የናፈቁት ክርስቶስ በሥጋ እየመጣ ነው ። እንግዳን ቤተ ዘመድ ይቀበለዋል ፣ እልልታ ይሰማል ። አንዲት ድንግል ግን በቤትዋ ሳይሆን በማኅፀንዋ ተቀበለችው ። ጉዳዩ እስከ ጊዜው ምሥጢር ነበርና የምሥጢር መዝገብ የሆነችው ማርያም ሰወረችው ። እርስዋ ከሴቶች የተለየች ናት ። ሔዋን ምሥጢር አውጥታ ሞትን ጋበዘች ፣ ምሥጢር ጠባቂዋ የሕይወትን ፍሬ አስገኘች ። የመምጣቱን ዜና የሚናገሩ የተቀደሱ ትንቢቶች በእኔ ይፈጸማል ብላ አንድም ቀን አስባ አታውቅም ። ከሥጋዋ ሥጋ ፣ ከነፍስዋ ነፍስ ነሥቶ ፣ አገሯን አገሩ አድርጎ ሊወለድ መጣ ። አስደናቂው ነገር ከአባቱ የተወለደው መለኮታዊው ልደት የዘመን መቀዳደም የለውም ። እናቱ በሥጋ ልደት እየቀደመችው ቢሆንም የፈጠራት ግን እርሱ ነው ። እናቱን የጦረ ልጅ እናውቃለን ፣ እናቱን የፈጠረ ልጅ ግን ታይቶ ተሰምቶ አያውቅም ። አባቱም በዘመን ያልቀደመው ፣ በክብር ያልበለጠው ይህ ሕፃን እንደምን ያለ ነው !! ዘመን የሌለው ሁኖ ሲኖር ሳለ በዘመን ቋጠሮ ውስጥ የገባው ፣ እርሱ ዘመን የለሽ እርሱ ዘመነኛ ነው ። ዘመናችንን ሊቀድስ ፣ ዓመተ ፍዳን ወደ ዓመተ ምሕረት ፣ ዓመተ ኵነኔን ወደ ዓመተ ጽድቅ ሊለውጥ መጣ ። የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ ። ለአባቱ የበኵር ልጅ የነበረው ለእናቱም የበኵር ልጅ ሆነ ። ሁለት አባት የለውምና ያለ ወንድ ዘር ተወለደ ። በቀዳማዊ ልደቱ እናት ፣ በደኃራዊ ልደቱ አባት የለውም ። በቀዳማዊ ልደቱ ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው ፣ በደኃራዊ ልደቱ ፍጹም ሰው ነው ። አምላክነቱ ሰውነቱን ሳያጠፋ ፣ ሰውነቱም አምላክነቱን ሳይሰበስብ አንዱ ክርስቶስ በተዋሕዶ ይኖራል ። እግዚአብሔር አንድነት መገለጫው ነው ። ሦስት አካል አንድ አምላክ ነው ፤ አሁንም ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሁኖ በአንድነት ይኖራል ። አንድ ስንሆን እግዚአብሔርን እንመስላለን ። የእግዚአብሔርን የፍቅሩን ውበት ፣ ድሀና ባለጠጋ ፣ ጥቁርና ነጭ ሳይለይ ሁሉም ይናፍቀው ነበር ። ይህን የውበት ፀሐይ ቀና ብሎ ለማየት ሰው በኃጢአት ጎበጠ ፤ ዝቅ ብሎ ያየው ዘንድ በበረት ተወለደ ። ሕፃናትን ለማስተማር በእነርሱ መጠን ዝቅ ብሎ በቁመታቸው ልክ ተንበርክኮ መናገር ውጤታማ ያደርጋል ። እውነተኛው የሕይወት መምህር በእኛ ሥጋ ተገለጠ ። ጣዖትን ከሚሻ ሕፃንነት አዳነን ። ስምዖን የቀሬናው በድንገት መስቀል ተሸከመ ። ድንግል ማርያም ግን በድንገት የአምላክ እናት አልሆነችም ። መሢሑን እጅግ የምትናፍቅ ፣ የብሉይ ኪዳም ትንቢቶችን የምታጠና ፣ በእግዚአብሔር ቤት እግዚአብሔርን የምትጠባበቅ ነበረች ። እግዚአብሔር ንጉሥ ነውና ከለመኑት በላይ ይሰጣል ሲባል ይሰማ ነበር ። ያለመኑትንም እንደሚሰጥ በድንግል ማርያም ታየ ። እርሱም ወላዲተ አምላክ መባል ነው ። ነቢይነትም ፣ ሐዋርያነትም ፣ ሰማዕትነትም ለብዙዎች ይሰጣል ። ለድንግል ማርያም የተሰጠው ግን የማይደገም ጸጋ ነው ። በአምላክ ሰው መሆን ኃይሉ ፣ ዳኝነቱ ፣ ፍርዱ ፣ ችሎታው ሳይሆን ፍቅሩ ተገለጠ ። የሰው ልጅ እግዚአብሔር ነፍጎኛል ብሎ ከሰይጣን ጋር አምላኩን አምቶ ነበር ። ስለዚህ በፍቅሩ ተገለጠ ። እኛ የአባትነት ፍቅር የሚያድርብን ልጅ ስንወልድ ነው ፣ እግዚአብሔር ግን የዘላለም አባት ነው ። ፍቅርንም በእኛ አልተለማመደም ፣ የዘላለም ፍቅር ነው ። መለኮት እኔ ልሙት ብሎ የመጨረሻውን መሐላ ለወዳጆቹ ምሎ ነበር ። በባሕርዩ አይሞትምና መሐላው ተንጠለጠለ ። የሚሞትበትን ሥጋ ለብሶ በመስቀል ላይ ዋለ ። የመጨረሻውን መሐላና ፍቅር በተግባር ገለጠ ። እኔ ልሙት ያሉን ብዙዎች ናቸው ፣ ሞተው ግን አላሳዩንም ። ሩቅ ሁኖ ማዘዝ ቀላል ነው እያሉ ሰዎች አጉረምርመው ነበርና በቅርብ ተገኝቶ ታዘዘ ፣ የሰጠውንም ሕግ ፈጸመ ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የሌለበት የዘላለም አባት ፣ የሚመጣው ንጉሥ ፣ የሚያሳርፈው የሰላም አለቃ ፣ የሚራራው ሊቀ ካህን ፣ ልቅደምልህ የሚል መሥዋዕት ፣ እጅግ ልበ ሰፊ ፣ ዝንጉዎችን የሚታገሥ ፣ የኃጢአተኞች ወዳጅ ፣ ሸፍኖ የሚሠራ ፣ አጋልጦ የማያዋርድ ፣ የሕመምተኞች ጤና ፣ የጥያቄዎች ሁሉ መልስ ፣ በለጋስነት ሁሉን የሚሰጥ ፣ የቆሰለ ልብን በደሙ የሚፈውስ ፣ ነፍስን የሚገዛ የሰማይ ልዑል ፣ አገር ለሌላቸው አገራቸው ፣ በግፍ ለሚገደሉት ተበቃያቸው ፣ የወደቁትን በተስፋ ቃል የሚያናግር ፣ አገሩ እዚህ ነው የማይባል ፣ ሁሉም መልኬ የሚለው ፣ የዘር ልዩነትን ያጠፋ ፣ የድሆችን ንቀት ያስወገደ ነው ። የዚህ ታላቅ ጌታ እናት ነሽና ማርያም ሆይ ደስታ ይገባሻል ! ክርስቶስ ሆይ የታመመው አልድን ፣ የወጣው አልገባ ያለበትን ይህን ዘመን ስለ እናት ስለ ማርያም ብለህ ለውጠው ! ይቀጥላል ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም.

  • 10 авг.1 745634

    видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг.1 6993611

    ቅድስት ማርያም   “በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ ።” ሉቃ. 1 ፡ 26-27 ።   ዓለም ሁሉ በታላቅ ኀዘን ፣ ለሞትም በተሸነፈ ልብ ይኖር ነበር ። መዳን በሰዎች ፣ ሰዎችም በሚያደርጉት ጥረት የማይገኝ መሆኑ ታወቀ ። የእንስሳት መሥዋዕትም ሥጋዊና መንፈሳዊ ሞትን ማስቀረት አልቻለም ። መሥዋዕተ እንስሳ ለጊዜው ቍጣን ቢያበርድም የገነትን በር ከፍቶ ጽኑ ይቅርታን ማምጣት አልቻለም ። የአበው ተስፋ ፣ የነቢያት ትንቢት ፣ የአዋቂዎች ሱባዔ ዘገየ እየተባለ ይታሰብ ነበር ። ፈሪሳውያን በታላቅ ቁጭት ሕዝቡን ለመሢሑ መምጣት ያነሣሡ ነበር ። ከእነርሱ የተከፈሉ ኤሤናውያንም በሙት ባሕር ዳርቻ በኩምራን ገዳም ተወስነው ፣ በጾምና በጸሎት ጸንተው ፣ መጻሕፍትን እየጻፉ መሢሑን ቶሎ ና እያሉ ይናፍቁት ነበር ። የእግዚአብሔር ጠባዩ ይህ ነው ። እያለ ና ይባላል ። በልብ ተቀምጦ ይናፍቃል ። የእግዚአብሔር የፍቅር ልብ በሰው ላይ አዝኖ ነበር ። ካሣ ሊከፈል ፣ መዳን ሊፈጸም ፣ ሰውም ወደ ቤቱ ሊመለስ ፣ የዳግም ልደት ምሥጢር ሊጀመር የግድ ያስፈልጋል ። ሰው እንደ ወጣ እንዲቀር የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አሳብና ጽኑ ፍቅሩ አላስቻለውም ። እንደ ራሱ የጠፋው ሰው እንደ እግዚአብሔር መዳን አለበት ። ሰው እግዚአብሔርን መምሰል አለበት ተብሎ ስለ ቅድስና ሲነገረው ነበር ። ሰውም በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠረ እየተባለ ዘወትር ይዘመራል ። አሁን ግን እግዚአብሔር ሰውን ሊመስል ፣ የሰውንም ሥጋ ሊለብስ ዘመን ደረሰ ።   ይህ ሥጋ በፈላስፎች እንደ ርኵስ ተቆጥሮ ነበር ። ሥጋንም በማጎሳቆል አምላክን ደስ ማሰኘት የሚል የግሪካውያን ፍልስፍና ተስፋፍቶ ነበር ። ሥጋን በመልበሱ ሥጋን ሊያከብረው ፈለገ ።   በቀጠሮው ማርፈድ የማያውቅ በሰዓቱ ፣ በቦታው የሚገኝ እግዚአብሔር በስድስተኛው ወር በናዝሬት ገሊላ ተገኘ ። እግዚአብሔር የዘገየ የሚመስለን በእኛ ሰዓት ስለምንጠብቀው ነው ። የእግዚአብሔር ተስፋ በእኛ ጊዜ ቢፈጸም ይጎዳናል ፤ ተስፋው በራሱ ጊዜ ሲፈጸም ይጠቅመናል ። እስራኤልን በምድረ በዳ እየመገበና ዐርባ ዓመት እያስጠበቀ በከነዓን ደግሞ አሞራውያንን ለንስሐ ጊዜ እየሰጠ ነበር ። እኛን እዚህ ሲያቆየን እነዚያን ለንስሐ እየጠበቀ ነው ። እኛ በትዕግሥት ስንጠብቅ እግዚአብሔር ደግሞ የታገሣቸው ሰዎች አሉ ። የእኛ ተስፋ በእኛ ጊዜ ሲፈጸም የእነርሱ ንስሐ ይቀራል ። የእኛ በረከት የዘገየ የመሰለን የሌሎች ሕይወት እየዳነ ስለ ነበር ነው ። ሐኪሙ በቀዶ ጥገና ክፍል ቢዘገይ የእኛ ኪኒን ግን በደቂቃ የሚታዘዝ ፣ ዓመታዊ ምርመራችን ጊዜ የሚሰጥ ነው ። ዓመታዊ ምርመራችን ዘገየ ስንለው እዚያ ጋ ዛሬ ካልሠራላቸው የሚሞቱ ወገኖች ገጥመውት ነው ። እግዚአብሔር የዘገየ ሲመስለን እየፈጠነ ፣ የረሳን ሲመስለን ታላቅ ፍቅርን እየገለጠ ነው ።   በራሱ ጊዜ የሚሠራው አምላክ መልአኩ ገብርኤልን ሊልክ ወደ ታላቁ ዙፋን ጠራው ። ከብዙ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል የተመረጠው ለምን ይሆን ? ብለን መጠየቃችን አይቀርም ። ከ600 ዓመታት በፊት መሢሑ የሚወለድበትና የሚሰቀልበት የተሰፈረ የሱባዔ ቍጥር ለነቢዩ ዳንኤል የተገለጠው በቅዱስ ገብርኤል በኩል ነው (ዳን. 9 ፡ 24-27) ። አሁን የሱባዔው ፍጻሜ መሆኑን ለመግለጥ ወደ ድንግል ማርያም ተላከ ። በስድስተኛው ወር ሲል በስድስት መቶኛው ዓመት ማለትም ነው ። ለዳንኤል በተገለጠ በስድስት መቶኛው ዓመት መልአኩ ገብርኤል ለድንግል ማርያም ተገለጠ ።   በባቢሎን ግዞት የነበሩት በዚህ የሱባዔ ምሥጢር ደስ አላቸው ። መሢሑ መምጣቱን መስማት የልብ ድጋፍ ሆናቸው ። እግዚአብሔር ታዳጊ ነው ብለው ዘመሩ ። ቀጥሎ የሚታያቸው የፈረሰው መቅደስ መሠራት ፣ ማኅበረ እስራኤል እንደገና ለዝማሬ መቆም ነው ። እስራኤል በባርነት እንደ ተጋዙ ዓለም በሙሉ ወደ ሲኦል ተግዞ ነበር ። እስራኤልን ወክሎ የምሥራቹን ዳንኤል እንደ ሰማ የሰውን ዘር ወክላ ድኅነተ ዓለምን የሰማች ድንግል ማርያም ናት ። ድንግል ማርያም የሰማችው ለመላው የሰው ዘር የሚሆነውን የምሥራች ነው ። ነቢዩ ዳንኤል ግን የሰማው ለእስራኤል ብቻ የሆነውን የምሥራች ነው ። የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸው ነቢያት ይባላሉ ፣ ድንግል ማርያምም የእግዚአብሔር ቃል መጥቶላታልና ነቢይት ትባላለች ። ለእስራኤል ብሔራዊ ጥያቄና ለሰው ዘር ዓለም አቀፋዊ እንቆቅልሽ መልሱ አንድ ነበረ ። እርሱም የመሢሑ መምጣት ነው ።   ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ሱባዔ ሳለ የመሢሑ መምጣት በተሰፈረ ዘመን ተገለጠለት ። ድንግል ማርያም በታላቅ ዝግጅት ላይ ሳለች ፣ በጸሎትና ቃሉን በማንበብ ስትተጋ የምሥራች መጣላት ። እንደ ንጉሥ ሳኦል በመንገድ የምሥራች የመጣላት ሳትሆን ለቃሉ ፍቅር ሕይወትዋን ሰጥታ ሳለች የምሥራቹ መጣ ። ቃሉን ስታፈቅር ቃለ አብ ኢየሱስ ከእርስዋ ሰው ሊሆን መጣ ። ቃልን ሰምታ ቃልን ፀነሰች ። የአምላክ አገልጋይ መሆን ስትሻ ወላዲተ አምላክ ለመሆን በቃች !   ይቀጥላል   ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.

  • 10 авг.56091из Nolawii

    የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! በዚህ ክረምት ከዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሥራዎች የመጻሕፍት ስጦታ ለተማሪዎች፣ ለእስረኞች፣ መግዛት ለማይችሉ ፣ ለቤተ መጻሕፍት ለመስጠት አስበናል። ይህን በረከት ለመሳተፍ የምትፈልጉ ቀጥሎ ባለው አካውንት የፈቀዳችሁትን መስጠት ትችላላችሁ ። ያስገባችሁበትን በቴሌግራም 0911699907 ላኩልን ! የእግዚአብሔር በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሸናፊ መኰንን ወርቁ Ashenafi Mekonnen worku  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000165078482

  • 10 авг.93471из Nolawii

    የመጽሐፍ ስጦታ ተማሪዎች የሆናችሁ ና መጽሐፍ መግዛት የማትችሉ ከዲያቆን አሸናፊ መኰንን መጻሕፍት በስጦታ ታገኛላችሁ። 0911699907 በቴሌግራም አሳውቁን! እነዚህ መጻሕፍት በስጦታ እንዲተላለፉ የገንዘብ ስጦታ ያደረጋችሁ ወዳጆች እግዚአብሔር በሰማያዊና በምድራዊ በረከት ይባርካችሁ!

  • 9 авг.1 878196

    እግዚአብሔር ትልቅ ነው 2 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

  • Live stream finished (1 hour)

  • 9 авг.1 818

    4:00 ትምህርት ይጀምራል

  • Live stream started

Nolawi ኖላዊ — tgindex