tgindex
Adoni Gospel channel

Adoni Gospel channel

Статистика

ኢየሱስ፦ የዘላለም መድኃኒት፤ የመጨረሻ መፍትሄ ነው።        Telegram- @adonigospel       Whatsapp 👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 732
−8 за 3 дн.
Сутки
−7
−0,15%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
899
23 постов
Вовлечённость
19,0%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
310
1/48двое суток
355
1/72трое суток
383

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ያለ ክርስቶስ ወደ መቃብር መውረድ ማለት ያለ መርከብ ውቅያኖስ ማቋረጥ እንደማለት ነው። ክርስቶስን መያዝ እጅግ ማትረፊያ ነው ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • አይዟችሁ የደከማችሁ እግዚአብሔር ኃይላችሁ ነው "ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።” — ዕንባቆም 3፥19          ✨ወዳጆቼ ኃይላችሁ ያላችሁ ስልጣንና ሀብት፣ ዝናና እውቀት ላይ አይደለም ኃይላችሁ እግዚአብሔር ነው። የመኪና ጎማ ንፋስ ካልተሞላ መኪናውን ተሸክሞ መሮጥ አይችልም ንፋስ ሲሞላ ጉልበቱ ኃያል ነው መኪናውን በጀርባው አዝሎ ይጓዛል። ልክ እንደዚሁ ሁሉ ክርስቲያን ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ኃይል መሞላት አለበት። ያለ እግዚአብሔር ኃይል የምጀምረው ጉዞ መዳረሻ የለውም፣ የምንወስነው ውሳኔ ፀፀት የተሞላ ነው። በራሳችን ለመቆም ስንሞክር ይበልጥ እንወድቃለን ስለዚህ እግዚአብሔርን ኃይላችሁ አድርጉ።      ✨እግዚአብሔር ኃይል የሚሆናችሁ በራሳችሁ መቆምን ስታቆሙ ነው። ድጋፌ አንተ ነህ፣ ምርኩዜ አንተ ነህ፣ እኔን የተሸከምከኝ አንተ ነህ በነገር ሁሉ ኃይል ሁነኝ ስትሉት ነው። እኔ በራሴ አቅም የለኝም ሙከራዬ ሁሉ ከሽፏል ስትሉ ያን ጊዜ የማያልቀው የእግዚአብሔር ኃይል እጃችሁን ይዞ መስራት ይጀምራል።         ✨ ዋላ ኑሮዋ ተራራ ላይ ነው። ዋላ በአስቸጋሪ ተራራ ላይ በቀላሉ ትጓዛለች። የሚያስፈራ ቁልቁለት ቢኖርም እግሯ ይጸናል። እኛም ሕይወታችን እንደተራራ የገዘፈ ችግር ባለበት፣ እንደሸለቆ በሰመጠ መከራ በበዛበት ዓለም ውስጥ ነው። አንዳንዴ መንገዱ የማይገፋ አቀበት ይሆናል። እግዚአብሔር ዋላን ተራራውን ሜዳ አድርጎ አይደለም የሚረዳት በተራራው ላይ የምትፀናበትን አቅም ይሰጣታል። እኛንም በሰላም የሚያኖረን የዓለምን ችግር አስወግዶ አይደለም፣ የዓለምን መከራ ከእኛ አርቆ አይደለም በመከራውና በችግሩ መሀል ኃይል ሰጥቶን፣ በአስቸጋሪው መንገድ ላይ በጸጋው ደግፎ አቁሞን ነው።           ✨የአንተ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ የአንቺ እግዚአብሔር በከፍታዎች ላይ የሚያስኬድ ነው። ዛሬ ችግርህ፣ የዛሬው መከራህ፣ ዛሬ የምታየው ዝቅታ ነገ ወደምትወጣው ከፍታ የሚያደርስህ መንገድ ነው። ችግርህ ያልፋል፣ ችግርህ ይለወጣል። የማይለወጠው የማያልፈው ጌታ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። በቸር ዋሉ!! ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • የሰው ፊት አያሳያችሁ      ✨አንድ መምህሬ "የማይለምን ሀብታም፤ የማይሰጥም ደሀ የለም" ይላል። ሁሉም ሰው በሙላት አልተፈጠረም። ጣቶቻችን መሀል ያለው ክፍተት በሌላ ሰው እንዲሞላ የተተወ ነው። ሁሉም የሰውነታችን አካል ሁለት ሁለት ሆነው ልባችን ግን አንድ ናት ሌላ ልብ ከሌላ ሰው እንድንጋራ ነው። ስለዚህ እኔ ምንም አይጎድለኝም ከሰው አንዳች አያስፈልገኝም ማለት የለብንም። የእኛ ጉድለት የሚሞላው በሌሎች ሙላት ነው የሌሎቹም ክፍተት የሚሞላው በእኛ ሙላት ነው። አንዱ ገንዘብ አለው እውቀት አይኖረውም፤ አንዱ እውቀት አለው ገንዘብ ይቸግረዋል፤ አንዱ ገንዘብም እውቀትም ይኖረዋል ጥበብ ይጎድለዋል። አንዱ ለአንዱ ተመጋጋቢ ሲሆን ሕይወት ይሰምራል።       ✨እናቴ ስትመርቀኝ " የሰው ፊት አያሳይህ" ትለኝ ነበር። የሰው ፊት ከእሳት በላይ የሚያቃጥል፣ አንገትን የሚሰብር፣ አኮማትሮ ትንሽ የሚያደርግ ነው። እኔም ዛሬ እመርቃችኋለሁ የሰው ፊት አያሳያችሁ የእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ይብራላችሁ። ሰው እንዲረዳችሁ እጃችሁን ዘርግታችሁ እንዳትኖሩ እግዚአብሔር የሚያስፈልጋችሁን ይስጣችሁ።            ረድኤቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ነው።” — መዝሙር 120/121፥1-2 ✨ረድዔታችሁ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። በሰው በኩል የሚረዳ የሚያግዝ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ቀኝ እጅ አድርጎ ከተጠቀመባቸው አልታዘዝም ማለት አይችሉም ስለዚህ ሰዎቹን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፊት ተመልከቱ። እርሱ ብሩህ ገፅ ነው። ✨ሰውን ሳይሆን መድኃኔዓለምን አስቸግራችሁ መኖርን ልመዱ። ሰው ይሰለቻል፤ ይማረራል... ሳይሰለች የሚቸር፣ ፊቱን ሳያጠቁር በፍቅር የሚሰጣችሁ፣ ያንቺስ ነገር ታከተኝ ሳይል እያለው የማይነፍግሽ እግዚአብሔር አለልሽ።        ✨እግዚአብሔር የመጀመሪያም የመጨረሻም ምርጫችሁ አድርጉት። ተስፋችሁን ከተሰባሪ ሰው ላይ አንሱና በክርስቶስ ላይ አድርጉት። ቢያኖራችሁም ቢገላችሁም እግዚአብሔርን ብቻ ሙጥኝ በሉ። መርዶክዮስ ተስፋውን ከአስቴር ላይ አንስቶ እግዚአብሔር ላይ አደረገ። እግዚአብሔር ንጉሱን እንቅልፍ ነስቶ ነገሩን ገለበጠለት። እግዚአብሔር የአንተን የአንቺን ችግር ለመፍታት ንጉስን የሚያህል ሰው እንቅልፍ ነስቶ ጉዳይሽን ጉዳይህን ይፈፅምልሃል።           🙏 ረድዔቴ እግዚአብሔር የሰው ፊት እየተመለከታችሁ እንዳትኖሩ ዓይናችሁን ወደ እርሱ ማንሳትን ያስተምራችሁ። ማንም በር ቢዘጋባችሁ የማይዘጋ በር ይክፈትላችሁ፣ መንገዳችሁን በቀና ጎዳናው ይምራላችሁ፣ የለመናችሁትን በእጥፍ ይስጣችሁ፣ ቤታችሁን ስራችሁን ጤናችሁን ይባርክላችሁ። ማንም ቢክዳችሁ ጀርባ ቢሰጣችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊቱን ያብራላችሁ፣ በችግር ጊዜ ረዳታችሁ፣ በጭንቀት ጊዜ መጽናኛችሁ ይሁናችሁ።     ከሰው ፊት ይልቅ የአንተን ፊት፤     ከሰው እርዳታ ይልቅ የአንተን ረድዔት፤     ከሰው ሞገስ ይልቅ የአንተን ሞገስ ስጠን። ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • በመከራ ውስጥ ለምታልፉ ሁሉ        እንዲህም አለ፡— ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን። (መጽ. ኢዮብ 1:21)       ✨አንዲት በሙያ የተካነች ሴት በኩሽናዋ ስጋ ለመጥበስ አሰበች። ማንም ሰው የሰራው ምግብ ተወዶ እንዲበላለት፣ ጣፍጦ እንዲመገቡለት ይፈልጋል። ይህችም እህት ጣፋጭ ስጋ ጥብስ ለመስራት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ አሟልታ ጉድ ጉድ ትላለች። ስጋውን የምትጠብስበትን መጥበሻ በደንብ አድርጋ እሳት ላይ ታግለዋለች። ይህ መጥበሻ በደንብ ከጋለላት በኋላ ስጋውን በመጥበሻው ላይ ትጥደዋለች።  እሳት ያልነካውን የስጋውን ክፍል በሙሉ እያገላበጠች በእሳት ትጠብሰዋለች ትለበልበዋለች። መብሰሉንም ለማየት ስትፈልግ በሹካ ወጋ ወጋ አድርጋ ታየዋለች። ይህን ሁሉ የምታደርገው በስጋው ላይ ቂም ኖሯት ሳይሆን በስሎ እንዲጣፍጥላት ነው። እሳት አብዝታ አታሳርረውም፤ አሳንሳም ጥሬ አታደርገውም። ልከኛውን እሳት በእጇ እየተቆጣጠረች ጣፋጭ አድርጋ ታበስለዋለች። የበሰለውንም ስጋ በንፁህና ባማረ ሰሀን አሸብርቃ ታቀርበዋለች። እኛ ሰሐኑ ላይ ስናየው ሽታው ሆድ ያላውሳል፣ ለዓይን ብሉኝ ብሉኝ ብሎ ያማልላል፣ ስንበላው ውስጣችንን ያስደስታል። ይህ ስጋ ምን አይነት መከራ አልፎ እንደመጣ ይቺ ባለሙያዋ ሴት ታውቃለች።       ✨ወዳጆቼ ይቺ ምድር መጥበሻ ናት። በሕይወት እስካለን ድረስ መከራ ይገጥመናል። እንደ ስጋው እያገላበጠ የሚጠብሰን መከራ ከወዲህም ከወዲያም ይገጥመናል። እግዚአብሔር ለህይወታችን እውቀት ይሰጡናል፣ ያበስሉናል ብሎ ባሰባቸው የተለያዩ ነገሮች ላይ ይጥደናል። ስራ ማጣት ሊሆን ይችላል፣ በወዳጅ መከዳት ሊሆን ይችላል፣ ገንዘብ ማጣት ሊሆን ይችላል፣ ስደት ሊሆን ይችላል። ይህ ብቻ አይደለም በሹካው ወጋ ወጋ እያደረገ መብሰላችንን ለማረጋገጥ አጠገባችን ያሉ ሰዎች እንደ እሾህ ሊወጉን ፍቅራችንን በአመድ ለውሠው ጦር ሊሰብቁብን ይችላሉ። በዚህ ሁሉ ውስጥ ስናልፍ ሁሉ ደህና ነው ማለት ከቻልን፣ ተመስገን እግዚአብሔር አንተ ሰጠኸኝ አንተ ነሳኸኝ ማለት ከቻልን በስለናል ማለት ነው።        ✨እግዚአብሔር እንዴት እኔ እንዲሰቃይ ይፈቅዳል? ለእኔ መልካም እንጂ ፈተናን እንዴት ያመጣብኛል? ልትሉ ትችላላችሁ። እግዚአብሔር አስተማሪ ነው ለዘመናት በሰላሙ መስክ፣ በእረፍቱ ጎዳና እየመራ ያስተማራችሁን ትምህርት የሚፈትንበት መፈተኛ ጣቢያው መከራ ነው። አንድ ወታደር በበረሃ ውስጥ ከባድ ልምምዶችን የሚያካሂደው የአገሩ መንግስት ስለጠላው ሳይሆን ብቁ እንዲሆን በማሰቡ ነው። እግዚአብሄርም እኛን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያስገባ ነው ህይወታችንን ሚያስተካክለው። መከራ እኛን ወደሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው። ገጣሚው "ደስታንም ሆነ መከራን ብትሰጠው፤ ከኔ ይልቅ ለኔ አንተ ነህ ምትቀርበው።" እግዚአብሔር በሕይወታችን ላይ ደስታንም ያምጣ መከራ እርሱ የወደደው ይሁንብን።        ✨ባለሙያዋ ሴት እሳቱን አብዝታ እንደማታሳርረው አሳንሳም ጥሬ እንደማታደርገው ሁሉ እግዚአብሔርም የመከራውን መቆጣጠሪያ በእጁ አድርጎታል። ከእግዚአብሔር የሆነው መከራ አያሳርራችሁም ያበስላችኋል። በመከራ ውስጥ የምታሳልፉት ስቃይ ቀላል አይደለም እጅግ መራራ ነው ግን ለመብሰል ነውና እግዚአብሔር ይመስገን። ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 10 авг.6981310

    እግዚአብሔርን እየመረጥን ነው የምንሰማው?      2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ። 3 አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል። . . . . 7 ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብፅ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። 8 የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። 9 ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት። (1ኛ ሳሙ 15)           ✨እግዚአብሔር ሳዖልን ከአማሌቅ ጋር እንዲዋጋ አዘዘው። አማሌቅ የኤሳው የልጅ ልጅ ሲሆን የአማሌቅ ዘሮች ደግሞ አማሌቃውያን ይባላሉ። አማሌቅ በሳዖል ጦር እንዲመታ እግዚአብሔር ያዘዘው የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲጓዙ ያለ አንዳች ምክንያት በረሃ ላይ የተዋጋቸው ታላቅ የእስራኤል ጠላት አማሌቅ ስለሆነ ነው።          ✨ሳዖልም የእስራኤል ንጉስ እንደመሆኑ መጠን የእስራኤልን ታሪካዊ ጠላት ለመዋጋት ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ተልዕኮ ተቀብሎ ወጣ። እግዚአብሔርም ለሳዖል ከሰጠው ትዕዛዝ አንዱ ከአማሌቃውያን አንዳችም እንዳያስተርፍ ንጉሱንም፣ ህዝቡንም፣ ንብረቱንም፣ እንስሶቹንም እንዲያጠፋ ነው። ሳዖል ግን በከፊል የሚሰማ ነውና ንጉሱን ከመግደል መማረክ፣ ከብቶቹን ከማጥፋት የሰባውን መርጦ መውሰድን ምርጫው አደረገ።          ✨ሳዖል እግዚአብሔርን በከፊል የሚሰማ ሰው ነበር። ከዚያም ሲያልፍ ስህተቱን የማያምን የራሱን ጥፋት በሌሎች ላይ የሚያላክክ ሰው ነበር። ለከብቶቹ የራራላቸውና ሳይገድል ይዞ ያመጣቸው ራሱ ሆኖ ሳለ ህዝቡ ለእግዚአብሔር ሊሰዋቸው ስለፈለጉ ይዘዋቸው መጡ ብሎ ህዝቡን ተጠያቂ ያደርጋል።         ✨ሳዖል ልክ በሁለት ቢለዋ እንደሚበላ ሰው ነው። እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ይሞክራል ደግሞም የራሱን ስሜትና ፍላጎትም ለማርካት ይፈልጋል። እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ካሰብን ከቃሉ ያፈነገጠ ማንነታችንን፣ የዓይን አምሮት የልብ መሻታችንን ልንገድል ይገባል። እግዚአብሔር ሲልከን አንጀቱን አርሰን መመለስ ይገባናል እንጂ የራሳችንን ነገር ይዘን እንድንመለስ አላከንም።         ✨የሳዖል ችግር ጆሮው ላይ ሳይሆን ልቡ ላይ ነው። ሳዖል ትእዛዙን ሰምቷል። ትዕዛዙን መፈፀም ላይ ግን እንከን ነበረበት። እኛም በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን፣ እንሰበካለን ነገር ግን የሰማነውን ለመፈፀም ታዛዥ አንሆንም። እመኑ ስንባል ራሳችንን እናምናለን፣ ዲያብሎስን ተቃወሙ ስንባል በአፋችን እየረገምነው በተግባር ግን ስራውን እንከተላለን። የእግዚአብሔር ቃል የምንሰማው ብቻ ሳይሆን የምንታዘዘው ነው። መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል እንደሚል ቃሉ እግዚአብሔርን መታዘዝ ቅድሚያ የሌለው ተግባር ነው። እግዚአብሔር ይህንን ግንኙነት ተው ሲለን እምቢ፣ ይሄንን ስራ አቁም ሲለን እምቢ፣ ይህንን ልማድ ተው ሲለን ለምን ማለት የለብንም።         ✨እኛ ለእግዚአብሔር ገንዘብ መስጠት እንፈልጋለን፣ እኛ ለእግዚአብሔር ጊዜ መስጠት እንፈልጋለን። ይህን መስጠት ጥሩ ነው ግን እግዚአብሔር ቅድሚያ ልባችንን እንድንሰጠው ይፈልጋል። ልባችንን ለዓለም ሰጥተን ገንዘባችንን ለእርሱ ብንሰጠው ከንቱ ልፋት ነው። እግዚአብሔር እንድንሰጠው ያልጠየቀንን ነገር ከመስጠት ይልቅ የጠየቀንን ነገር መፈጸም ይሻላል።        ✨ይህ ምድር የሚታይና የማይታይ ጦርነት የሚስተናገድበት ዓለም ነው። ሳዖል የሚታየውን ከአማሌቅ ጋር የሚደረገውን ጦርነት ድል ነሳ። ነገር ግን ልቡ ውስጥ የሚንቀለቀለውን ምኞት፣ ከራሱ ጋር ያለውን ግብግብ ማሸነፍ አልቻለም። ውጫዊውን ጦርነት በእግዚአብሔር እርዳታ አሸንፎ ውስጣዊውን ጦርነት ለብቻው ዘምቶ ተሸነፈ። ከእግዚአብሔር ይልቅ የራስን ደስታ ማስቀደም፣ ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ ለዓይን አምሮት ቦታ መስጠት በቁም መዘረር ነው።        ✨የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። የጥበብ መጨረሻም እግዚአብሔርን መታዘዝ ነው። ዛሬም እግዚአብሔር አጥፉ ያለንን ነገር አግበስብሰን ከያዝን፣ እግዚአብሔር ግደሉ ያለንን ኃጢአት እየመገብን ካቆየነው፣ እግዚአብሔር ሽሹ ያለንን ነገር ከተከተልነው.......በሕይወታችን ውስጥ ትልቁን እግዚአብሔርን እየከሰርን እያጣነው ነው።         ✨ሳዖል በውጊያው ድል ነስቶ፣ ህዝብ አጅቦት፣ አገር ተገዝቶለት የሚኖር ሰው ነበር። እግዚአብሔር አማሌቅን ሲያስገዛለት ልቡን ግን ለእግዚአብሄር ማስገዛት አልቻለም። ዛሬም ብዙዎቻችን በአገልግሎት ተሳክቶልን አቤቱ እርሱማ አቤት እርሷማ ተብለን ይሆናል፣ በገንዘብ በርትተን ባለጠጋ ሆነን ይሆናል፣ በእውቀትም ብዙ ዲግሪዎችን አካብተን ይሆናል፣ በስራችንም እጅግ ትርፋማ ልንሆን እንችላለን ግን በልባችንስ ስኬትን ተጎናፅፈን ይሆን? በሰው ፊት ያለን ድል በእግዚአብሔር ፊት ያለንን ሁኔታ አይወስንም። ልባችን ለእግዚአብሔር ልትማረክ ይገባል።         ✨አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እንድንሰማህ እርዳን፣ እንድንታዘዝህ እርዳን፣ ሰውን ሳይሆን አንተን እንድናስደስት እርዳን፣ ከዓይናችን አምሮት ከልባችን ምኞት ጠብቀህ ለቃልህ እንድንገዛ እርዳን፣ አንተን የማያከብር አንዳች ነገር በሕይወታችን ቢኖር ቆርጠህ ጣልልን። አሜን ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 5 авг.9193411

    ይህንን ሳታደርጉ ወደ መኝታችሁ እንዳትሄዱ       " በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።" መዝ 4:8           ✨ወዳጆቼ እንዴት አመሻችሁ? ዛሬ ቀኑን ከነበጀቱ ሰጥቶን ውለንበት አልፏል። ለአንዳንዶቻችን የደስታ ቀን፣ ለአንዳንዶችም የሀዘን፣ ለአንዳንዱ የውድቀት፣ ለአንዳንዱም የስኬት ቀን ሆኖ አልፎ ይሆናል ነገር ግን የሁላችንንም የቀን ውሎ እግዚአብሔር አይቷል። አሁን ውድቀታችን ከጠለቀችው ፀሐይ ጋር አብሮ አልፏል አሁን ለሊቱ ሊመጣ ነው። ስለዚህ ሁሉን ለእግዚአብሔር አስረክባችሁታል?            ✨ አንዳንዶቻችን አልጋ ላይ ሰውነታችን ያርፋል እንጂ አዕምሯችን ግን ቢዚ ይሆናል የሃሳብ ትርምስ ውስጥ ይገባል። ነገ እንዲህ ቢሆንስ? ይሄን እንዲህ ባደርገው ያ እንዲህ ቢሆን...እያልን ማረፍ ሲገባን እንባትታለን። እግዚአብሔር ግን ምን ይላል መሰላችሁ መብራት ያጠፋሁት እንድታርፉ ነው፣ ፀሀይን ያጨለምኩት እንድትተኙ ነው።  ስለዚህ እናንተ ተኙ እኔ እጠብቃለሁ፤ እናንተ እረፉ እኔ ሁሉንም ነገራችሁን እረከባችኋለሁ፣ እናንተ ጸልያችሁ ጋደም በሉ እኔ ስራችሁን እሰራለሁ ይላል።        ✨ቀን ቀን የምንሰራው ማታ የምናርፈው እኛ ነን። እግዚአብሔር ግን ቀን ብቻ ሳይሆን ለሊትም ይሰራል። እኛ የማናየውን እርሱ እያየ ነው። እኛ የማናውቀውን እርሱ እያወቀ ነው። እኛ የማንደርስበትን እርሱ ይደርስበታል። እኛ የማንፈታውን እርሱ ይፈታዋል። ስለዚህ ወዳጆቼ ዛሬ ለሊት ችግራችንን አጠገባችን አናስተኛው፤ አብሮን አልጋ ላይ እንዲወጣ አትፍቀዱለት በጸሎት ለእግዚአብሔር አስረክቡት። ✨በአንድ መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ሃሳብ አንብቢያለሁ " የቤታችን ድመት እኛን አምና አልጋችንን ተደግፋ ያለ ሃሳብ ትተኛለች እኛስ እግዚአብሔርን ተደግፈን ሁሉን ለእርሱ ሰጥተን ለምን አንተኛም? " እርሱን አምኖ ማረፍ ይሁንላችሁ።       ጸሎት “አቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፦ ዛሬ ስላሳለፍክልን ደግሞም ስላለፈንም ነገር እናመሰግንሃለን።  የሰራነውን በደል ኃጢአት ሁለ ይቅር በለን። የማንችለውን ነገር ከእጃችን ወስደህ በእጅህ ያዝልን። በመንታ መንገድ ላይ የቆመው ልባችንን አቅጣጫ ስጠው። በዚህ ለሊት ቤተሰቦቻችንን፣ ቤታችንን፣ በዙሪያችን ያሉ የምንወዳቸውን ሁሉ ጠብቅልን። ልባችንን ከነገ ፍርሃት አሳርፈው። አዕምሯችንን ከጭንቀት ገላግለው። ነገ የሚጠብቀንን ነገር ሁሉ አስቀድመህ ተረከበው። በሰላም ታሳድረን ዘንድ፣ በምህረትህ ክንፍ ትጋርደን ዘንድ፣ በይቅርታህ እቅፍ ውስጥ ታሳድረን ዘንድ ለመንህ በሰላም ታነቃን ዘንድ ለሊታችንን ላንተ ለታመንከው ጌታ አደራ ሰጠንህ። አሜንን ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 3 авг.935243

    ሲመሽ ይመጣል ሲመሽ ወዳጄ ያልከው ሲሸሽ" ዘ.ትዝታው ቀን ሳለ የጨለመባቸው፣ በቀትር የመሸባቸው፣ የሚወዱትን ከዓይናቸውም ከልባቸውም የሸኙ፣ ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ሆኖ የራቃቸው፣ በዝግ ቤትና በዝግ ልብ መኖር የከበዳቸው፣ በአዕምሯቸው አደባባይ የወጡ፣ በብቸኝነት ብርድ የሚገረፉ ብዙ ናቸው። 🙏አቤቱ ኢየሱስ ሆይ በዝግ ቤት ሁሉን አልፈህ ገብተሃል። ይሄን ሁሉ ችግራችንን ጥሰህ ናልን። የመሸበትን ወዳጅ ነህና ዛሬ ናልን፤ ከፍቶናል የተከፉትን የምትፈልግ አንተ ነህና ዛሬ ናልን! በሀዘን ያዘቀዘቁ ብዙ አንገቶች አሉ ኢየሱስ ና ቀና አድርገን። የዓይናችንን ሳይሆን የልባችንን እንባ ጥረግልን። እንደ ራሔል የእንባን ጎርፍ ወዳንተ እናፈሳለን ፈጥነህ ድረስልን። ነፍሳችንን የምታነብ የልብ አውቃ አንተ ነህና እባክህ ዛሬ ናልን። በአንተ ደስ ይበለን። ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 2 авг.962225

    ኢየሱስን ለምንድነው የምትወዱት?            ✨አንተ ያለ ምክንያት ወደድከኝ እኔ ግን በብዙ ምክንያት እወድኃለው።       ✨ሳልወድህ ስለወደድከኝ፣ ሙት ሳለሁ ስላልረሳኸኝ፣ ፅድቄ እንኳን የመርገም ጨርቅ ሳለ ከእኔ ስላልራቅ፣ ፍቅርህ በሁኔታዬ ስለማይለወጥ፣ በድክመቴም ስለማይቀንስ፣ በስኬቴም ስለማይጨምር እወድሃለው።      ✨ማንም ያላንከባለለው ሸክሜን ስለወሰድክልኝ፣ ኃጢአቴን ይቅር ስላልከኝ፣ ተስፋ በሌለኝ ጊዜ እንኳን ተስፋ ስለሆንከኝ፣ በጨለማው መንገዴ ብርሃን ስለሆንከኝ እወድሃለው።        ✨ማቄን ቀደድ ደስታን ስላስታጠከኝ፣ ፈጥረህ ስላልተውከኝ፣ ሰልችቼህ ጀርባ ስላልሰጠኸኝ፣ በደስታዬ ብቻ ሳይሆን በሀዘኔም ከእኔ ጋር ስለምትሆን፣ በመስቀልላይ እርቃንህን ተሰቅለህ ከእፍረት ስላዳንከኝ፣ ሞቴን ወስደህ ሕይወት ስለሰጠኸኝ፣ መንገድ እውነትና ሕይወት ስለሆንከኝ እወድሃለው።        ✨እንባዬን ስለምታብስልኝ፣ ስብራቴን ስለምትጠግን፣ ልቤን ስለምታጽናና፣ በትንሳኤህ ለዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ስለሰጠኸኝ ከሁሉ በላይ እወድሃለው። ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 31 июл.1 071162

    ኢየሱስ ክርስቶስ        ✨በቃላት ብቻ የማይገለጽ የክብር ጌታ ነው።      ✨ እርሱ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ ሰውን በማዳን ፍቅሩን የገለጠ፣ የትሕትና አርአያ፣ የሰላም አለቃ እና የዘላለም ሕይወት ምንጭ ነው።       ✨እርሱ የሚጮኸውን ይሰማል፣       ✨ የሚያለቅሰውን ያጽናናል፣       ✨የወደቀውን ያነሣል፣       ✨የተጎዳውን ይፈውሳል፣       ✨የጠፋውን ይፈልጋል። ✨ፍቅሩ ወሰን የለውም፣ ምሕረቱ መጨረሻ የለውም፣ ታማኝነቱም ለዘላለም ይኖራል። አሜን ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 30 июл.1 1199

    ❌ማስጠንቀቂያ ይህ ከላይ የምታዩት ስክሪን ሹት ቻናሉ ላይ ያሉ ወዳጆች የላኩልኝ ሲሆን ለእኔ ምንም አይነት ማስታወቂያ መለቀቁን አያሳየኝም። ይህ ሊንክ ከኔ ፍቃድና ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ የተለጠፈ ነውና በማን? እንዴት? እንደተለቀቀም የማላውቅ መሆኑን እንድትገነዘቡና ሊንኩን ባለመክፈት ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስል የጥንቃቄ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ። መልዕክቱ ከእኔ መስሏቸው ሰዎች እንዳይታለሉ በዚህ ዙሪያ ላይ መፍትሄውን ልትሰጡኝ የምትችሉ ባለሙያዎች ካላችሁ ትብብራችሁን የምሻ መሆኑን በፍቅር እጠይቃለሁ። ከታላቅ ፍቅር ጋር አዶኒ

  • በሕይወታችሁ ማንንም አታቃሉ             ዘፍ 16:4          ✨ የሰው ልጅ በየጊዜው የተለያዩ ጠባዮችን ያበቅላል። አወቅነው ስትሉ ጭራሽ አለማወቃችሁ ይገባችኋል። ወደ ልቡ የአመታት ጉዞ ብታደርጉ ጫፉን የማትደርሱበት ስምጥ ሸለቆ ማለት የሰው ልጅ ነው። አውቃችሁ አትጨርሱትም። ሰው ለሰው ብቻ ሳይሆን ለአምላኩም አስቸጋሪ የማይያዝ የማይጨበጥ ፍጡር ነው።        ✨አጋር የሳራ ባርያ ናት። የአጋር ሀላፊነት ቤት ውስጥ የሚያስፈልገውን የጉልበት ስራ መስራት እንጂ የመውለድ የማግባት ሀላፊነት የለባትም። ድንገት ግን ከሀላፊነቷ ውጪ ሌላ ነገር ገጠማት ጌታዋ አብርሃም   ወደ እርሷ ገብቶ ልጅ ፀነሰች። ይህ ለአጋር ድንገተኛ ነገር ነው። ይህች አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷ ሳራን በዓይንዋ አቃለለቻት።        ✨አጋር ድንገት ባገኘችው ነገር ሳራን በአይኗ ገፈተረቻት። ራሷን ከፍ ከፍ አድርጋ ማየት ጀመረች። የፀነሰችው የተባረከ ይሁን ያልተባረከ ሳታውቅ ሰውን ለማቃለል ተነሳች። ወዳጆቼ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው ድንገት በለስ ቀንቷቸው ገንዘብ ሲያገኙ ትላንት አብሯቸው የነበረውን ይንቃሉ፤ አሳንሰው መመልከት ይጀምራሉ። ✨አንዳንዶች ድንገት ባገኙት ነገር የትላንት ትዝታቸውን ጥለው እናንተ ላይ የንቀት ጅራፍ ያሳርፉባችኋል። ነገር ግን አይዟችሁ የናንተ ተራ ይመጣል። እንደ እንግጫ አይተው ሊረግጧችሁ እግራቸውን ቢያነሱባችሁም አይዟችሁ ለናንተም ቀን አለ።      ✨ሰውን በስድብ ብቻ ሳይሆን የምናቃልለው በአይናችንም በጠረባ ልንጥለው፣ ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ በንቀት እይታ እንደ ሽንኩርት ልንልጠው እንችላለን። አጋር በሆኑ ሰዎች ብንናቅም ዛሬ ያለንበት ሁኔታ የመጨረሻችን አይደለም።         ✨እግዚአብሔር በአጋር የተናቀችውን ሳራንም አሰባት። ሳራ ዛሬ አልወለደችም ማለት ነገ አትወልድም ማለት አይደለም። አጋሮች ጊዜ እንደሚለወጥ ትዕቢተኞችን የሚያዋርድ፣ ትሁታንን ከፍ የሚያደርግ ጌታ በዙፋኑ እንዳለ ይዘነጋሉ። ዛሬ በነገ ይቀየራል መሀኗ ልጅ ትታቀፋለች። ሳራ ትላንት ሞክራ አልሆን ብሏት ይሆናል ቀኗ ሲመጣ ድካሟ ፍሬ ያፈራል።          ✨ዛሬም ድንገት ባገኙት ብር ኑሯቸውን በለወጡ በአብሮ አደግ፣ ወንድም፣ ዘመድ፣ ጎረቤት ተንቆ ልቡ የተሰበረ ብዙ ሰው አለ። ሳራ በአጋር ተቃላ አልቀረችም እግዚአብሔር የባረከውን ይስሀቅን ሰቷታል። ዛሬም እግዚአብሔር ይስሀቅ የሆነ በረከትን በናቋችሁ ሰዎች ፊት ይሰጣችኋል። የሚንቅ ሰው ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ነው ነገ በሰውም በእግዚአብሔር ይናቃልና። እንኳን ትልቅ ሰው ዛሬ የተወለደ ህፃን ልጅ አይናቅም ምክንያቱም ይህ ህፃን ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅምና ማንንም አትናቁ። 🙏 አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ሳራን ቤቷን በሳቅ እንደጎበኘህ፣ ሳራን ከአንድ ቤተሰብ አልፎ ለትውልድ የሚተርፍ በረከት እንዳስታቀፍካት፣ ሳራን የመናቅ ዘመኗን አሳልፈህ የተከበረች ሴት እንዳደረካት የብዙዎችን የንቀት ዘመን አሳልፈህ ክብራቸውን አፍጥንላቸው፣ የተራቡትን በረከት አቅርብላቸው።                    ✍በአዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8

  • 🙏 ባለፉት አምስትና ስድስት ወራቶች ውስጥ እንደተለመደው በተለያየ ችግር ውስጥ ሆናችሁ በጸሎትም፣ በሃሳብም እንድረዳችሁ በውስጥ መስመር የተለያዩ መልዕክቶችን ልካችሁልኝ ምላሽ ያልሰጠኋችሁ ሁላችሁም ከልብ የሆነ ይቅርታን እጠይቃችኋለሁ። ከነበርኩበት ጥልቅ ኃዘን የተነሳ ዝም ማለትን ስለመረጥኩ እኔም ከነበርኩበት ስሜት እስከወጣ ነውና በዚህ መሃል ተቀይማችሁ ብሎክም ያደረጋችሁኝ ሁላችሁን ከልብ ይቅርታ እላችኋለሁ። እግዚአብሔር ባስለመደን ጸጋ እድሜ ጨምሮ ብዙ ለመማማር ያብቃን። በጸሎታችሁ አስቡኝ እወዳችኋለሁ። የክርስቶስ ፍቅር ይብዛላችሁ።❤️ አዶኒ

  • 27 июл.1 1911310

    ክርስቶስን የመምሰል ህይወት ✨ክርስትና እድገት ያለው ሕይወት ነው። ክርስቲያን የሚያድገው ወደጎን አይደለም፣ በቁመትም አይደለም! እድገቱ ክርስቶስን ወደ መምሰል ነው። የተጠራነው እገሌንና እገሊትን መስለን እንድንኖር ሳይሆን ክርስቶስን መስለን እንድንኖር ነው። የክርስቲያን የሕይወት ግብ ሰማይ መድረስ ብቻ ሳይሆን በምድርም ሳለን የክርስቶስን መልክ ተላብሰን መኖር ነው። ብዙዎች ክርስትናን በስም፣ በስርዓት ወይም በውጫዊ ምልክት ለመለካት ይፈልጋሉ።  ይህ የፈሪሳውያን ጠባይ እንጂ የክርስትና ሕይወት ገጽታ አይደለም። ጌታ ኢየሱስ የሚፈልገው የተለወጠ ልብን እንጂ አስመሳይን አይደለም። "ክርስቶስን መከተል በቃል ብቻ አይደለም። ሕይወታችንም የእርሱን ባሕርይ ሊያንጸባርቅ ይገባዋል።"                 ✨መምሰል ድካም አለው። አንድ ተዋናይ የተሰጠውን ገጸ ባህሪ መስሎ ወይም ሆኖ ለመተወን ትጋትን፣ ድካምን፣ ራስን መስጠትን ይጠይቃል። ክርስቲያንም ክርስቶስን ለመምሰል ሜካፕ መሰራት ሳይሆን በጸሎት፣ ቃሉን በማጥናት፣ ህብረት በማድረግ፣ በመንፈሳዊ አገልግሎቶች በመትጋት አልፎም በፀጋውና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው።  እኔ ክርስቲያን ነኝ ካልን አንዳንድ ቀን ሳይሆን ክርስቶስን የምንመስለው ሁልጊዜ ክርስቶስን በሐሳብ፣ በቃልና በሥራ መምሰል አለብን።       ✨ክርስቶስን መምሰል ማለት እንደ እርሱ መውደድ፣ እንደ እርሱ ማገልገል፣ እንደ እርሱ ይቅር ማለት፣ እንደ እርሱ ለአብ መታዘዝ ነው። የጌታ ትሕትና የሕይወቱ ጌጥ ነበር፤ እርሱ ጌታ ሆኖ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ። ይህም ታላቅነት በአገልግሎት እንጂ በሥልጣን እንዳልሆነ ያስተምረናል። ✨ክርስቶስን መምሰል መከራንም ይጠይቃል። ጌታችን እንዲህ አለ፦ "ማንም ሊከተለኝ ቢወድ፥ ራሱን ይካድ፥ መስቀሉንም በየቀኑ ተሸክሞ ይከተለኝ።" እርሱን መከተል ምቾትን ከመፈለግ ይልቅ ለእውነት መቆምን ይጠይቃል።         ✨  ክርስትናችን መምሰልን እየተወ ማስመሰልን መልመድ የለበትም። ንግግራችን እንደ ክርስቶስ፣ ተግባራችን እንደ ክርስቶስ፣ ሕይወታችን እንደ ክርስቶስ መሆን አለበት። ለታይታ የምናደርገው ነገር ሁሉ መቅረት አለበት። ሰው የምንረዳው ችግሩን መነገጃ አድርገን ካሜራ ደቅነን መሆን የለበትም። እግዚአብሔር ሸሽጎ በጓዳ እንደሰጠን እኛም የሰዎችን ችግር ሸፍነን በጓዳ ልንቸራቸው ይገባል። ክርስቶስን መምሰል የራስን ዝቅ ማድረግ ጌታን ማጉላት ነው።        ጸሎት           ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፦ ከማስመሰል ህይወት፣ ራስን ከማምለክ ህይወት ነጥቀህ አንተን በቃል ብቻ ሳይሆን በሕይወታችን እንድናሳይህ እርዳን። ሰዎች ርኛን ሲመለከቱ ክርስቶስን ማየት ይሁንላቸው። የአንተን ፈለግ መከተል፣ የአንተን ዱካ እየረገጥን መሄድ ይሁንልን። ትህትናህን አልብሰን፣ ፍቅርህን በልባችን ሙላ። መንፈስ ቅዱስ በነገር ሁሉ እርዳን። የምንሠራው ሁሉ ለክብርህ ይሁን። አሜን። ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 25 июл.1 025164

    ኢየሱስ ለእኔ ያላረክልኝ ምን አለ                     ከማህፀን ያየኸኝ፤ በዓላማህ ያኖርከኝ፤ እንደ ዳዊት ከተረሳሁበት ያነሳኸኝ፤ ጸጋህን እንደ ልብስ አለበስኽኝ ጌታ ኢየሱስ ተመስገንልኝ።         እጆቼን ባዶ አልተውከኝም፣ ልቤን ተስፋ አልነሳኸውም፣ ከቀን ወደ ቀን ታማኝነትህን አሳየኸኝ፣ አዕምሮዬን ጠበከው፣ ከብዙ ጉድ አወጣኸኝ ጌታ ኢየሱስ ተመስገንልኝ።         ያልታየኝን አንተ አየኸው፣ ያልቻልኩትን አንተ ሰራኸው፣ የተሰበረውን ልቤን አከምከው፣ የተዘጉ ደጆችን ከፈትክልኝ፣ ያልጠየኩትን ሰጠኸኝ፣ ያላሰብኩትን ጨመርክልኝ፣ በረከትህ ቀድሞ ደረሰልኝ፣ ምህረትህም በፊቴ ሄደ ጌታ ኢየሱስ ተመስገንልኝ።                   የሰጠኸኝን ስቆጥር መጨረሻው አይታወቅም፣ ምህረትህ ከባህር ይሰፋል ታማኝነትህ ከዘላለም ያልፋል። አልተራብኩም ከስጋህ አብልተኸኝ፣ አልተጠማሁም ደምህን አስጎንጭተኸኝ፣ አልተረሳሁም መቃብር ድረስ መጥተህ ፈልገኽኝ ጌታ ኢየሱስ ለኔ ያላደረክልኝ ምን አለ?          ስለዚህ አመሰግንሃለው ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን!! ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 24 июл.1 005124

    ኢየሱስ           ✨የታረድከው ጌታ፤ በክብር በምስጋና፣ በይባቤ ያረከው ጌታ ታማኝነትህ ያልጎደለብን፣ ሁኔታዎች ሲገለባበጡ ፀንተህ የቆምክልን፣ ድል መንሻችን ኢየሱስ ሆይ ተመስገን።     ✨ኢየሱስ ሆይ እንወድሃለን፤ ኢየሱስ ሆይ እናከብርሃለን፤    ኢየሱስ ሆይ እንሰግድልሃለን፤ ኢየሱስ ሆይ ከፍ ከፍ እናደርግሃለን።  ለማንነትህ እንጂ ለስጦታህ አንዘምርም፤ ለፍቅርህ እንጂ ለበረከትህ ብቻ አንሰግድም።  አንተ ወድቀህ ያነሳኸን ጀግና፤ ሞተህ ያኖርከን ወዳጅ፤  ከናንተ በፊት እኔን ያስቀድመኝ ብለህ የሞት ፅዋ የጠጣህልን ኢየሱስ ሆይ እንወድሃለን።       ✨አንተ በረሃችንን የምታረካ፤ ጥማችን የምትቆርጥ ውሃችን፤ ለሊቱን ስንጓዝ የእሳት አምድ ሆነህ የምትመራን፥ በረሃውን ስንጓዝ ደመና ሆነህ የምትጋርደን፤ በጨለማችን ብርሃን፣ በእንባችን መጽናናት፣ በጦርነታችን ድል የሆንክ፣ በድካማችን ኃይል ነህ። ለአንተ አንደበታችን ከዝማሬ አይታክትም፣ ስምህን ከማመስገን ልባችን አይሰንፍም ኢየሱስ ሆይ ተመስገን።      ✨አለን ብለን የምንቆጥርህ ብቸኛና ውድ ሀብታችን፣ ዘመን ቢለወጥ የማትለወጥ አባታችን፣ የማትዋሽ አምላካችን፣ የማትተወን መድኃኒታችን፣ የማትደክም ረዳታችን፣ እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ ስራችን አልኖርንም። ኢየሱስ ሆይ ለዘለዓለም ተመስገን። ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 22 июл.1 184296

    እግዚአብሔር ሁን ያለውን ጉም አይጋርደውም፤ ድምጽን በድምጽ የሚሽር የበላይ ዳኛ ነው። እርሱ ያለው ከአድማስ እስከ አድማስ ያለከልካይ ይሆናል። ተመስገን Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 21 июл.1 373207

    በክርስቶስ ኑሩ        "በእኔ ኑሩ፥ እኔም በእናንተ እኖራለሁ፤ ቅርንጫፉ በወይኑ ግንድ ካልኖረ ፍሬ ሊያፈራ እንደማይችል፥ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ እንዲሁ ናችሁ።" — ዮሐንስ 15፥4          ✨ክርስትና የራሳችንን ኃይል፣ እውቀት፣ ሀብት፣ ዝና፣ ስልጣን ተማምነን የምንኖረው ሕይወት አይደለም። ክርስቶስን አምነን የምንኖረው ጣፋጭ ሕይወት ነው። ክርስቶስ የምንኖርበት ከተማችን ስለሆነ በእኔ ኑሩ አለን።  ቅርንጫፍ ከወይኑ ግንድ ከተለየ እንደሚደርቅ ሁሉ እኛም ከክርስቶስ ተለይተን መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራት፣ ስኬታማ ሕይወትም ሊኖረን አንችልም። ስለዚህ ግንዳችን ከሆነው ከክርስቶስ ጋር በየቀኑ መጣበቅ፣ ልብን በፊቱ በማፍሰስ፣ የክርስቶስን ፍቅር በመቀበልና ለሌሎች በማሳየት፣ በእምነት በመታዘዝ፣ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የራሳችንን ፍቃድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፍቃድ በመመላለስ በክርስቶስ ውስጥ መኖር እንችላለን።                    ✨ይህን ማድረግ የልባችንን በር ለክርስቶስ እየከፈትን እርሱ በልባችን ተንሰራፍቶ እንዲኖርበት ያደርገዋል። ክርስቶስ በእኛ ውስጥ በመንፈሱ ይኖራል። እርሱ በእኛ ውስጥ ሲኖር ሕይወታችን ይለወጣል፤ ቁጣችን በትዕግስት፤ ጥላቻችን በፍቅር፤ ፍርሃታችን በእምነት ይለወጣል። ይህ የክርስቶስ ሕይወት በእኛ መገለጡ ማሳያ ነው።            ✨ቅርንጫፍ ከግንዱ እስከተጣበቀ ድረስ ብቻ ነው ፍሬ ማፍራት የሚችለው። ቅርንጫፉ ከግንዱ ጭማቂ እንደሚቀበል እኛም ከክርስቶስ ጸጋ፣ ኃይል እንቀበላለን። ብሎም ከክርስቶስ ጋር ስንኖር የመንፈስ ፍሬ እናፈራለን።       ✨ወዳጆቼ ዛሬ ከክርስቶስ ሊለዩን የሚሞክሩ ብዙ ነገሮች አሉ። የዓለም ፍቅር፣ የገንዘብ ፍላጎት፣ ኃጢአት፣ መንፈሳዊ ስንፍና፣ ምቾቶቻችን ሊላለዩን ይችላሉ። ጌታ ግን በእኔ ኑሩ ብሎ ይጠራናል። በእርሱ የሚኖር ሰው ከፈተና ንፁህ ይሆናል ማለት ሳይሆን ፈተናን ድል የሚነሳበት ጥበብ፣ ኃይል ይቀበላል ፈተናውንም ድል ይነሳል ማለት ነው። ✨ከእኛ የሚፈለገው ብዙ ድካም አይደለም። ከእርሱ ጋር የማያቋርጥ ሕብረት፣ ጸሎት፣ ንስሐ፣ ቅዱስ ቁርባን ነው። ልባችንን ለእርሱ መክፈት ራሳችንንም በእርሱ ላይ መጣል ነው። ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 19 июл.1 135212

    "ክርስቶስን ከልብህ አትለይ፤ እርሱ ከአንተ አይለይም።" የልባችን ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በልባችን ለአንድ ፍቅረኛችን ከምንሰጠውን ስፍራ በታች ለክርስቶስ አንስጠው። እርሱ ብቸኛ የልባችን ዙፋን የሚገባው ንጉሳችን ነው። ኢየሱስ ቀዳሚም ተከታይም የሌለው መውደዳችን ነው። ከልባችንም ከአንደበታችንም የማይለይ ውዳችን ነው። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፦ ልቤ ለአንተ ይሁን። ሐሳቤ ወደ አንተ ይመለስ። እግሬ በመንገድህ ይራመድ። ሕይወቴም ለክብርህ ይሁን። አሜን ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 18 июл.1 052161

    እግዚአብሔር የገለጠውን በእምነት ተቀበል፤ ያልገለጠውን በትሕትና ተወው። john Chrysostom እግዚአብሔር ራሱን በገለጠበት መጠን ማወቅ ግዴታ ነው። ራሱን ከገለጠበት በላይ ለማወቅ መጣር በተሸከምናት አዕምሮ የሚሆን አይደለም። ይህ የተሸከምነው ስጋ ደስታንም ሀዘንንም በሙሉነት መሸከም አይችልም። እግዚአብሔርን አቅም ኖሮን በሙሉነት ልንረዳው ይቅርና አንዳንድ የደስታ ሰርፕራይዞችና ሀዘኖችን እንኳ መቆጣጠር አቅቶን ራሳችንን እንስታለን። እግዚአብሔር ለእኛ አዕምሮ በሚበቃ መልኩ ራሱን ገልጧል። የገለጠው ብቻውን በቂ ነው። የተገለጠውን ተረድተን ሳንጨርስ ስላልተገለጠው ማንነቱ ለማወቅ አንቆፍር። እግዚአብሔር ማለት የተረዳነውም ያልተረዳነውም፣ ያወቅነውም ደግሞም ያላወቅነውም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን እንዳናውቀው አይከለክልም፤ በተቃራኒው እርሱን እንድናውቀው ይጋብዘናል። ነገር ግን ከገለጠው በላይ በግምት ወይም በሰው ፍልስፍና ለመድረስ መሞከር ተገቢ አይደለም። እኛ የምናውቀው እርሱ በቃሉና በክርስቶስ የገለጠልንን መጠን ነው። እግዚአብሔርን እንደቃሉ እንድናውቀው ይርዳን፤ መንፈስ ቅዱስ ይግለጥልን። አሜን! ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

  • 18 июл.1 123183

    ጸሎት " ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።" ሰቆ 3:23         አቤቱ የልቤ አምላክ እግዚአብሔር አመሰግንሃለሁ። ማደሪያህ የተባረከ ይሁን። ዓይኖቻችንን ከፍተህ ብሩኹን ቀን እንድንመለከት ስለረዳኸን ተመስገን። ምህረትህ የመቆማችን ምስጢር ነውና ምህረትህ ምርኩዝና እድል ስለሆነን እናመሰግንሃለን።       አቤቱ ልዑል ሆይ እርጅና የማያውቅህ የትላንቱን ጭንቀት፣ ያለፈውን ሃዘን፣ የከረመውን ስህተት፣ የተጫነንን ሸክም አራግፈህ የፍቅር ጸዳል ስላበራህልን እናመሰግንሃለን።         አባት እግዚአብሔር ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰዎች ሲለዋወጡብን፣ ሁኔታዎች ሲቀየሩብን፣ ዓለም ስትናወጥብን አንተ ግን አልተለወጥህም፤ ሳትንሸራተት በብዙ ታማኝነት ደግፈኸናል። ዛሬም በአንተ ላይ ልባችን ይወድቃል።          አንተ ከክፉ ወጥመድ፣ ከማንኛውም ስውር ፈተና፣ ከራሳችንም ጭምር ጠብቀን። ቃልህን ቃላችን አድርግልን ለሰው ጠገን አድርገን። በሄድንበት የአንተን መዓዛ የምንነሰንስ ባሪያዎችህ አድርገን። ለደከሙት ብርታት፣ ለታመሙት ፈውስ፣ ለተጨነቁ እውነተኛ መጽናናት፣ ለታወኩ የአዕምሮ ሰላም ነህና ይህን ለሚሹ ሁሉ ዛሬ ችግራቸው ሁሉ በኃይልህ ይተካላቸው።         አሜን ላሉት ሁሉ ይደረግላቸው። በምትወደው ልጅህ በኢየሱስ ስም። ✍አዶኒ              Telegram👉 t.me/adonigospel    Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X