Ethiopia - ኢትዮጵያ 🇪🇹
Статистикаውስጥ አስታወቂያ ማስተባበር https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=d_5454205860
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 286
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 31
- 1/48двое суток
- 35
- 1/72трое суток
- 38
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
❤️ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ባለቤቶችን ወደ Inside Ad እጋብዛለሁ፡፡ ለእድገትና ለገንዘብ ማግኘት ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሉ ስልት! https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=r_5454205860
https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=r_5454205860 I invite you to Inside Ad: Smart tool for channel growth
" አባቴን ፖሊስና ሚሊሾች ከቤት መጥተው የወሰዱት ' ለተማሪዎች የተገዛው እህል ተጭኖ መወሰዱን ለምን ለሚዲያ ተናገርክ ? ' ብለው ነው " - የታሳሪ ቤተሰብ‼️ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ድጉና ፋንጎ ወረዳ፣ አንካ ድጉና ቀበሌ በሚገኘው አንካ ብሳሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የተዘጋጁ ልዩ ልዩ የምግብ ግብዓቶች ከትምህርት ቤቱ ተጭነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ማህበረሰብ ገለፁ። አካባቢው በድርቅ መመታቱን ተከተሎ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ከቀረበው ድጋፍ ውስጥ ፦ - ሩዝ፣ - ዘይት፣ - ቦለቄ፣ - ቂንጬ፣ - ስንዴና ጨው ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ገደማ በሞተር ሳይክሎች ተጭኖ መወሰዱ ይታወቃል። የድጉና ፋንጎ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወርቁ ባዛ በተገኙበት " ለሚዲያ መረጃ ለምን ሰጣችሁ ? በሰዓቱ ለማንም እንዳትናገሩ ብለናችሁስ አልነበረም ወይ ? " በማለት ፦ - የአንካ ድጉና ቀበሌ ሥራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ኮይሻ - አቶ ሳሙኤል አልጋ (የቀበሌው ሽማግሌ)፣ - አቶ ሹሚ ኢላሆ እና - አቶ አሊዬ ቢቢሶ በዛሬው እለት ከቀኑ 8:00 ሰዓት መታሰራቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እና በሰዓቱ ሲታሰሩ ያዩ የአይን እማኞች ገልጸዋል። እማኞቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ በቀበሌው ሊቀመንበር አስተባባሪነት ለተማሪዎች የምግባ ፕሮግራም የተገዛው እህል ሲጫን በዕለቱ ያዩትን እና ትክክለኛ መረጃዎችን " ለሚዲያ ሰጥታችኋል " በማለት ከቀበሌው ስራ አስኪያጅ ውጭ ያሉትን በአንካ ድጉና ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ አስረዋቸዋል። " ቀበሌው ሥራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ኮይሻን ወደ ወረዳ ከመሸ ወስደዋቸዋል " ሲሉ አክለዋል። ቃላቸውን የሰጡ የአይን እማኞች የሚከተለው ተናግረዋል ። " ' እናንተ ናችሁ ለሚዲያ መረጃ የሰጣችሁት፣ ንብረቱ ቢበላ እናንተ ምን አገባችሁ፣ ንብረትነቱ የመንግስት ነው፣ ይህ እህል ከእናንተ ማሳ አልሰጣችሁን፣ ምን ያገባችኋል ? በሰዓቱ አልነገርናችሁም ወይ ከወረዳ መንግስት ጋር ተነጋግረን ነው የምንጭነው ብለን ? እኛ ተናበን ነው የምንሰራው፣ እናንተ ምንም አታመጡም፣ በማያዋጣችሁ ነገር ውስጥ ነው የገባችሁት፣ የእጃችሁን ታገኛላችሁ ' እያሉ አስረው ሲወስዷቸው አይቻለሁ። ' ለሚዲያ ማን መረጃ ስጡ አላችሁ ? ' በማለት ነው ያሰሯቸው። የቀበሌው ስራ አስኪያጅ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አናውቅም። የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ነው በመኪና ይዟቸው የሔደው። ሌሎቹ እዚሁ ቀበሌ ነው የታሰሩት። የቀበሌው ሚኒሾች ግለሰቦቹ በታሰሩበት እየደበደቧቸውና እያስፈራሯቸው ነው " ብለዋል። ለደህንነቱ ሲባል ስሙ ያልተጠቀሰ አንድ የታሳሪ ቤተሰብ፥ " አባቴን ፖሊስና ሚሊሾች ከቤት መጥተው የወሰዱት ' ለሚዲያ ለምን ጥቆማ ሰጠህ ? 'ብለው ነው። ለተማሪዎች የተገዛው እህል ተጭኖ መወሰዱን ' ለምን ተናገርክ ? ' " ብለው ነው ያሰሩት " ሲል ተናግሯል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንድሰጡን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወርቁ ባዛ የጠየቅን ሲሆን ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ የስልክ ጥሪያችንን አቋርጠዋል። ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም Ethiopia - ኢትዮጵያ 🇪🇹 https://t.me/goodethionews
без подписи
без подписи
የገንባቢ ትምህርት ሥርዓት እና ብድርድ ዕቅፎች እንዳይተወዋሌ ተልባን ልኝ በዚህ እንዲህ ይህ ሁሉ የተዘጋጅበት ዝግጅት እንደ ዚህ ቁርጷ ይደርሳሉ ፡ እንደ አፋላሊያ ይይዙ፣ ቢንዋኑ ዋኗ ደብዳቤ ይረጉግ! የእኔ ዝግጅት ይረጉግ! እባኮት ይናገሩ፤ አስተማሪኒ ይናዳ ወይቀዘ ወይደቆ ውሳኤ ወይደማር ወይደማር ይሉት! #ትንቢት #ዝግጅት 📢 በኢንሳይድ የተሰራ
без подписи
የኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ ኃይል ማስገቢያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ በሙሉ ተነሳ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስገቢያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጠየቅ የነበረውን ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ። ቀደም ሲል የዱቤ ክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ወለድ ይጣል ነበር። አሁን ወለዱ መነሳቱ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ዜጎች የምስራች መሆኑንና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተጀመረው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር በሁለት ሳምንታት ብቻ 19,231 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል። ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664,505 አዳዲስ ደንበኞችን ያገናኘ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም. ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ለማገናኘት አቅዷል። ኢንጅነር ጌቱ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ በ70 ዓመታት ታሪኩ 5.88 ሚሊዮን ደንበኞችን ማገናኘት ችሏል፤ አሁን ግን በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል። ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም ምንጭ : tikvahethiopia https://t.me/goodethionews
በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውንና አካባቢው በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች 11 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ ‼️ ሰኞ፣ ነሐሴ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን እና አካባቢዋ በተለያዩ ሦስት ሥፍራዎች በተፈጸሙ የተኩስ ጥቃቶች ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በጥቃቶቹ ሌሎች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውንም አክሎ የገለፀው የሀገሪቱ ፖሊስ፤ በሳፕስ፣ ካይሌትሻ፣ ላንጋ እና በጉጉሌቱ አካባቢዎች በተፈጸሙት ጥቃቶች ላይ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል። የመጀመሪያው ጥቃት በኬፕ ታውን ካይሌትሻ አካባቢ በሚገኘው ሊንጌሌቱ ዌስት የተፈፀመ ሲሆን በዚህ ጥቃት የ25፣ 31 እና የ35 ዓመት ሦስት ወንዶች በጥይት ተመትተው በቦታው መሞታቸውን ፖሊስ ገልጿል። የጥቃቱ መንስኤና አጥቂዎቹ ማን እንደሆኑ ግን እስካሁን አልታወቀም። ሁለተኛው የተኩስ ጥቃት በላንጋ በሚገኘው ክዋላንጋ አካባቢ፣ በዊኒ ማንዴላ ጎዳና ላይ የተፈፀመ ሲሆን በዚህ ጥቃት አራት ወንዶችና አንዲት ሴት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሦስተኛው ጥቃት ደግሞ በጉጉሌቱ አካባቢ በሚገኘው ባርሴሎና ጊዜያዊ መኖሪያ መንደር የተከሰተ ሲሆን በዚህ ጥቃት ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት ሲገደሉ፣ ሌሎች ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን ፖሊስን እማኝ አደርጎ አናዶሉ ዘግቧል፡፡ በአጠቃላይ በሦስቱ የተለያዩ ጥቃቶች 11 ሰዎች ሲገደሉ፣ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል። ፖሊስ የጥቃቶቹ ትክክለኛ ዓላማ እና ተጠርጣሪዎቹ ማን እንደሆኑ ለማወቅ ምርመራውን እያጠናከረ መሆኑም ተመላክቷል። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ጥቃቶቹ ከተከሰቱባቸው አካባቢዎች በተጨማሪ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት እንዳለባቸው በተለዩ ሌሎች ሥፍራዎች ተጨማሪ የፖሊስ ኃይሎችን ማሰማራቱን አስታውቋል። የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢዎቹ የሚካሄዱ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከልና ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ተጨማሪ ክትትል እያደረጉ ነው። የዌስት ኬፕ ግዛት የፖሊስ ኮሚሽነር ሌተናል ጄኔራል ሲዛክሌ ድያንቲ የተኩስ ጥቃቶቹ መንስኤ እስካሁን በምርመራ ላይ መሆኑን እና የጥቃቶቹ ዓላማ እንዳልተረጋገጠ ገልጸው ኮሚሽነሩ ለጥቃቶቹ ምርመራ ጠቃሚ ሊሆን የሚችል መረጃ ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ መረጃውን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል። የጥቃቶቹ ፈጻሚዎችን ለማስያዝ የሚያግዝ መረጃ ለሚያቀርብ ሰውም 100 ሺህ የደቡብ አፍሪካ ራንድ ሽልማት እንደሚሰጥም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። ይህም 6,185 የአሜሪካ ዶላር ይሆናል፡፡ በደቡብ አፍሪካ በተለይም በዌስት ኬፕ ግዛት የወንበዴ ቡድኖች ጥቃትና ሕገወጥ የጦር መሣሪያ መጠቀም ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ሆነው መቀጠላቸውን የፖሊስ ኃላፊው ገልጸዋል። ምንጭ : አዲስ ማለዳ https://t.me/goodethionews
https://static-cdn.tellowebs.com/web/h5/#/share_livePage?uid=1314621&hostId=1314621&roomId=168109
без подписи
የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ! (ሀምሌ 24/2018 ዓ.ም) መመዝገቢያ ሊንክ፡- https://lyuhub.com/jobs ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
без подписи
без подписи
#ማስታወቂያ! #ለተማሪዎች_ብቻ 👏 (ነሀሴ1/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠዉን ትምህርት ጥራት ለማላቅ ሞዴል አለም አቀፍ የሳይንስ ልህቀት ማዕከል በመፍጠር በትኩረት በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2019 የትምህርት ዘመን በምስራቅ ጎህ የሳይንስ ልህቀት ማዕከል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ9ኛ እስክ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የቅድመ ዝግጅት ስራዉን ያጠናቀቀ በመሆኑ በትምህርት ቤቱ ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች በትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ላይ በተገለጸው የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት በተጠቀሰው የመመዝገቢያ ሊንክ እስከ 8/12/2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መመዝገቢያ ሊንክ፡- https://bs.ministry.et የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ https://t.me/goodethionews
በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱ፣ ሌላ ግጭት ይከሰታል የሚል ስጋት ውስጥ እንደገባ የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ !! ረቡዕ ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በቅርቡ እየጨመረ የመጣው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ውጥረት ተባብሶ ሌላ ግጭት ይከሰታል የሚል ስጋት እንዳለው በመግለጽ ውጥረቱን በማርገብ በሰላም መፈታት እንዳለበት አሳሰበ። ድርጅቱ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው ከሆነ ከአካባቢው እና ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የተገኙ ዘገባዎች በአዲስ አበባ እና በመቀሌ መካከል ያለው ግንኙነት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ እየተበላሸ መምጣቱን ያሳያሉ። ይህ ሁኔታም በኢትዮጵያ እና ሱዳን አቅራቢያ ባሉ የድንበር አካባቢዎች አዲስ የትጥቅ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩን ጠቁሟል። የፕሪቶሪያው ስምምነት አስከፊውን ጦርነት በማቆም ብሔራዊ እርቅ እና ዘላቂ ሰላምን እና እምነትንን ለመገንባት መንገድ የከፈተ ታሪካዊ እድል ነው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በትግበራው ላይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች በተለይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በህወሓት መካከል ያሉ ውጥረቶች እንዲያይሉ በማድረግ እንዲሁም በመቀሌ እና በአዲስ አበባ መካከል እያደገ የመጣው አለመተማመን እስካሁን የተመዘገቡ አዎንታዊ እርምጃዎችን አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን አስታውቋል። ለፖለቲካዊ አለመግባባቶች ወታደራዊ መፍትሔ ሊኖር እንደማይችል የጠቆመው ፋውንዴሽኑ፣ ወደ ግጭት መመለስ በከባድ ጥረት የተገኘውን ሰላም ወደኋላ የሚመልስ እና ሰብአዊ መከራን የሚያበዛ ነው ሲል አስጠንቅቋል። የሰላም ፋውንደሽኑ አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት በከፍተኛ ሁኔታ ትዕግስታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ያለ ሲሆን ውጥረቱን ከሚያባብሱ እርምጃዎች እንዲቆጠቡ እና የፕሪቶሪያን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ዳግም ቁርጠኛነታቸውን ማሳየት አለባቸው ሲል ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም እ.አ.አ. በ2030 ዓለም አቀፍ የሰላም ተነሳሽነት መሰረት ሁለቱም ወገኖች የሕዝብን ደህንነት እና ጥቅምን ከማንኛውም ፖለቲካዊና ወታደራዊ ፍላጎት አስቀድመው በመስጠት ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊና አካታች በሆነ ውይይት ሊፈቱ እንደሚገባ እናምናለን ሲል አሳስቧል። Via : አዲስ ማለዳ https://t.me/goodethionews
без подписи
❤️ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ባለቤቶችን ወደ Inside Ad እጋብዛለሁ፡፡ ለእድገትና ለገንዘብ ማግኘት ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሉ ስልት! https://t.me/InsideAds_bot/open?startapp=r_5454205860
በዘይሴ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት 10 ሰዎች መሞታቸውን ኢሰመጉ ገለጸ ሐሙስ፣ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ዘይሴ ወረዳ በመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)፤ ድርጊቱን በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ። ኢሰመጉ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በዘይሴ ወረዳ በሚገኙ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከሰኔ 11 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመንግሥት የታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በተጨማሪም በ3 ግለሰቦች ላይ የአካል ጉዳት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት እንዲሁም የጅምላ እስር መፈጸሙን ድርጅቱ ከአካባቢው ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ መቻሉን ገልጿል። ከአካባቢው በተነሱና ምላሽ ባላገኙ የማኅበረሰብ ጥያቄዎች ሳቢያ እየተባባሰ በመጣው በዚህ ጥቃት ምክንያት፣ በርካታ ነዋሪዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን መግለጫው ያስረዳል። ኢሰመጉ ቀደም ሲል በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ጥሪ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል። ጉዳዩን አስመልክቶ ከአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት እስካሁን ባይሳካም፣ ወደፊት ተጨማሪ ምርመራዎችን በማድረግና የወረዳውን ምላሽ በማካተት ዝርዝር መረጃዎችን ይፋ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የተለያዩ ጥሪዎችን አስተላልፏል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና የጋሞ ዞን የጸጥታ አካላት የንጹኃንን ደህንነት የመጠበቅና የሰብዓዊ መብቶችን የማክበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ የጸጥታ አካላት በወንጀል የሚፈልጓቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውለው ፍትህ የማግኘት መብታቸውን እንዲያከብሩ፣ በክልሉ የሚነሱ ጥያቄዎች ሕግን በተከተለና ማኅበረሰቡን ባሳተፈ ሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ፣ በዘይሴ ማኅበረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲቆም ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ፣ በአካባቢው በደረሱት ጥሰቶች ላይ አፋጣኝ ማጣራት ተደርጎ ጥፋተኞች ለሕግ እንዲቀረቡ አበክሮ ጠይቋል። Via : Addis Maleda https://t.me/goodethionews
без подписи