tgindex
𝙷𝙰𝙼𝙼𝙰𝙳✎𝚃𝚄𝙱𝙴

𝙷𝙰𝙼𝙼𝙰𝙳✎𝚃𝚄𝙱𝙴

Статистика
@hammad_tubeарабский

''وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِين''

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
арабский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
815
0 Са 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
38
25 постов
Вовлечённость
4,7%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всогО 25
УпОПинаниК
1
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
6
1/48двое суток
6
1/72трое суток
7

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.4иС IbnuMunewor

    አስቸኳይ የትብብር ጥያቄ ~ አንዲት እህታችን "ማህበረሰቤን ልጥቀም" ብላ አንድ ኸይር አሰበች። ወለኔ ውስጥ ቤደር የምትባል መንደር ላይ አንድ መርከዝ ማሰራት አስባ ሞከረች ሞከረች ሞከረች ግን ግቡን ሊመታ ቀርቶ ሩቡን ማሳካት አልቻለችም። ወላሂ የተፈለገው ገንዘብ ትንሽ ነው። ነገር ግን የረባ ትብብር ባለመኖሩ እዚህ ግባ የሚባል ድጋፍ አልተሰበሰበም። እውነት ብንረባረብ ሁለት ሚሊዮን ብር ብዙ ነው ወይ? ለዚሁ አላም ታስቦ ዛሬ ጁምዓ ማታ 3 ሰዓት ላይ የተወሰኑ ኡስታዞች የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይኖራልና በመገኘት የድርሻቸውን እንድትወጡ አደራ እላለሁ። የግሩፑ ሊንክ 👉 https://t.me/+h5YVkNAk55hkYWI8 ፕሮግራሙ ላይ መገኘት የማትችሉም ትንሽ ትልቅ ሳትሉ በዚህ አካውንት በማስገባት አግዙ። 1000675591664 ሱፍያን ሱልጣን እና ቀድሪያ ኸድር አላህ ይቀበላችሁ። ከተባበርን በጣም ትንሽ ነው። ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ደግሞ ጌጡ ነው።

  • 14 авг.5иС Sle_qelbachn1

    ● በተባረከው የጁሙዓ ቀን ውስጥ፣ ዱዓችን ያለ አንዳች ግርዶሽ ተቀባይነትን የምታገኝባት አንዲት የተለየች ሰዓት አለች። ብዙ ኡለማዎች ይህች ወርቃማ ጊዜ የምትገኘው «ከዐሱር በኋላ» እንደሆነች ይገልፃሉ። እጆቻችሁን ዘርግታችሁ ይህችን  ሰዓት ለመጠቀም ተዘጋጁ!

  • 🔖የጁምዓ ቀን ሱናዎች!.. ➊ الـغـسـل_ገላን መታጠብ ➋ الـتـطـيـب_ለወንዶች ሽቶ መቀባት ➌ الـسـواك_ሲዋክ መጠቀም ➍ لـبـس الـجـمـيـل _ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ الـتـبـكـيـࢪ لـصـلاة الـجـمـعـة በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➏ قـࢪاءة سـوࢪة الـكـهـف ሱረቱ ከህፍን መቅራት ➐ الإكــثـار مـن الدعاء وتحري سؚ؊ الإجابة ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰዐት መጠባበቅ ❽ الإكــثـار مـن الـصـلاة عـلـى الـنـبي() በነብዩ()ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት الـلَّـهُـمَّ صـَلِّ وَسَـلِّـمْ علـى نَـبِـيِّـنَـا مُـحـمَّـد() الـلَّـهُـمَّ صـَلِّ وَسَـلِّـمْ علـى نَـبِـيِّـنَـا مُـحـمَّـد () ďťż ➥https://t.me/sunah_channel

  • 13 авг.7иС IbnuMunewor

    السلام عليكم ورحمة الله وبركاتة ታላቅ የሙሀደራና የኒያ (የገቢ ማሰባሰቢያ) ፕሮግራም! ​እነሆ የፊታችን ጁመዓ ምሽት 3:00 በወለኔ ወረዳ ቤደር ከተማ ለሚገነባው የአል-ሂዳያ መርከዝ ደማቅ የሙሀደራ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። እርሶም ባሉበት ሆነው በኦንላይን በመከታተል የዚህ ታላቅ ኸይር ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል። ​🎤 የእለቱ ተጋባዥ ኡስታዞች፦ 🎙 ኡስታዝ አቡ ሱፍያን 🎙 ኡስታዝ አብድረዛቅ ባጂ 🎙 ኡስታዝ አብዱል መሊክ ​🎤 የፕሮግራሙ መሪዎች፦ 🎙 አቡ ሂበቲላህ እና አቡ ሁዘይፋ ​📌 ማሳሰቢያ፦ ፕሮግራሙ በቀጥታ በመርከዙ የቴሌግራም ቻናል የሚተላለፍ በመሆኑ፣ ከወዲሁ ቻናሉን በመቀላቀል ሰዓቱን አክብረው ይጠብቁን። ​📲 የቀጥታ ስርጭቱን ለመከታተል የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/+h5YVkNAk55hkYWI8 ​💳 የበኩሎን አስተዋፅኦ ለማድረግ (የባንክ ሒሳብ)፦ ​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000675591664 ​የሒሳብ ስም፦ ሱፉያን ሱልጣን እና ቀድሪያ ኸድር ​መልዕክቱን ላልሰሙ ወንድምና እህቶች በማጋራት (Share) የኸይሩ ተካፋይ እንሁን!

  • ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • 10 авг.14иС Sle_qelbachn1

    📌ለደረቀችው ልቤ! 🎙በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቀጥታ ስርጭት ተጀመረ! 👇👇 https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=4b7952a17ac57f8cf5

  • አንዲት መልዕክት የዕድሜ ልክ መገለጥን ትሠጠን ይሆናል፡፡ አንዲት ቃል የማይደረስበት የተስፋ አድማስ ታወርሰን ይሆናል፡፡ ቃል ያደክማል፣ ቃል ያበረታል፣ ቃል ይገድላል፣ ቃል ያነሳል። መልካም ንግግር ሶደቃ ነው። ሶድቃችሁ ዋሉ። በመልካም ነገር የሚያስታዉሱንን ቢያንስ ላይክ በመስጠት እናበረታለን። መሳአል ኸይር ❤

  • 10 авг.18иС IbnuMunewor

    መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ? ~ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ ቀደም ብየ ገልጬ ነበር። አሁን ደግሞ ለምን አላማ ጀመሩት የሚለውን ባጭሩ እዳስሳለሁ። በግብፅ የአስዩጥ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶክተር ሐሰን ኢብራሂም ሐሰን እና በሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትምህርቶች ገምጋሚ የነበሩት ጦሀ አሕመድ ሸረፍ በጋራ በመሆን “አልሙዒዝ ሊዲኒላህ” በሚል ርእስ ስለ“ፋጢሚያዎቹ” ንጉስ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አንድ መፅሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ “አውደ - አመታት እና በዓላት” በሚል ርእስ ስር ያሰፈሩት ሃሳብ “መውሊድ ለምን አላማ ታስቦ ነው የተጀመረው?” ለሚለው ጥያቄ ጥሩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡- “(ንጉሱ) አልሙዒዝ በሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ቀን፣ በነብዩ ﷺ መውሊድ ቀን፣ በረጀብ መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በሸዕባን መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በረመዷን መጀመሪያ ቀን ከሚያስተዳድራቸው ህዝቦች ጋር ይካፈል ነበር፡፡ ይህን የሚያደርገው * የሱኒ፞ዮቹን ልብ ለማረጋጋት፣ * እንዲሁም በሱኒ፞ዮች መርሆዎችና በሺዐዎች እምነቶች መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ በማሰብ ነው፡፡ * በተጨማሪም ይሄ አልሙኢዝ ሊዲኒላ፞ህ የንግስና ዘመኑን ያሸበረቀባቸውን እነዚህን በዓላት የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ እምነቶችን ለማሰራጨት ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሑሰይንን ዝክር ህያው ለማድረግ የዓሹራእ ቀንን ያከብር የነበረው፡፡ ልክ እንዲሁ የበርካታ አኢማዎችን መውሊድና ስልጣን ላይ ያለውን ገዢ መውሊድ በሚልም (የራሱን ልደት) ያከብር ነበር፡፡ * ልክ በዚህ መልኩ የህዝቦቹን ትኩረት ወደሱ ለመሳብና የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ መሰረታዊ እምነቶችን ለማሰራጨት እነዚህን በዓላት እንደ መዳረሻ ይጠቀምባቸው ነበር፡፡” [አልሙዒዝ ሊዲኒ'ላህ፡ 284] ስለዚህ መውሊድ የተጀመረው ለፖለቲካዊ ትርፍና የሺዐን እምነት ለማስፋፋት ዓላማ ነው ማለት ነው፡፡ የክርስቲያኖቹ ገና፞፣ ሁዳዴ፣ …፣ የሺዐዎቹ የዓሹራእ በዓል፣ ገዲር ኹም፣ …፣ የእሳት አምላኪ መጁሳዎቹ ነይሩዝ ይከበሩ ከነበሩት በዓላት ውስጥ ነበሩ፡፡ የህዝብን ትኩረት ለመሳብ፣ ቅሬታ ውስጥ ያሉ ሱኒ፞ዮችን ልብ ለማረጋጋት በሂደትም ወደራሱ የሺዐ እምነት ሰዎችን ለማስገባት በማለም ነው፡፡ ቀስ እያለ በጉልበት ወደ ሺዐ እምነት መጣራት እንደተጀመረ ይታወስ፡፡ ስለዚህ አላማቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡትን የህዝብ ግፊቶች በማርገብ ይከተሉት የነበሩትን የኢስማዒሊያ ሺዐ እምነት ማስፋፋት ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ ዛሬ ሱፍዮች እንደሚያስቡት “የወሃብዮች” ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ከላይ እንዳየነው የታሪክ አጥኚዎች ድምዳሜ ነው፡፡ የመውሊድ ስርኣቱ ለእኩይ አላማ የታለመ ስለነበርም ነው ሶላሑዲን አልአዩቢይ ሺ0ዎችን አስወግዶ ግብፅን ሲቆጣጠር አስቁሞት የነበረው፡፡ መቼም እሱንም “ወሃቢ ነው” እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ዳግም የተጀመረው ኋላ በመምሉካውያን ጊዜ ነው፡፡ የመውሊድ ተግባር እንደገና ሲመለስ ሌሎቹ በአላት የሌላ እምነት መሰረት ያላቸው ወይም ሺዐ-ዘመም ስለነበሩ በሱኒ፞ው አለም ገበያ አላገኙም፡፡ ዛሬም የሙስሊሞችን መብት የሚጨፈልቁ የፖለቲካ ኃይሎች አጉል ተቆርቋሪ ሊመስሉ ለመውሊድ የተለየ ሸፋንና ድጋፍ ሲሰጡ ማየት የተለመደ ነው። ብልጥ የሆነ ሰው ሊያስተውል ይገባል። አላህ ማስተዋሉን ይስጠን። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

  • ከሆነ ቦታ እንወጣለን፣ ቦታው ግን ከኛ ዉስጥ አይወጣም፣ ከሆነ ሰው እንርቃለን፣ እሱ ግን በግድ ከኛ ጋር ይኖራል፣ የሆነ አጋጣሚ እናልፋለን፣ ትዝታው ግን አብሮን ይቀራል አይፋታንም፣ የሆነ ነገር ለመርሳት እንሞክራለን፣ እሱ ግን አይለቀንም ይጣበቅብናል፣ ከሆነ ስሜት ሮጠን ለማምለጥ እንሞክራለን፣ እሱ ግን አያራምደንም እግራችንን ይይዘናል፡፡ አንዳንዴ ሕይወት እንዲህ ናት፡፡ ዉጪዉን ስናይ አካባቢው ደስ ቢልም፣ እይታው ማራኪ ቢሆንም፣ የሚያስቸግረን መስኮት መዝጋት ግድ ነው፡፡ መሳአል ኸይር ABX

  • 8 авг.29иС kedmiyaletewhiid

    ​ "ሰዎች ስለ እኔ ምን ይሉ ይሆን?" ​ሀቢቢ.. በሆነ ቦታ ላይ አዲስ ልብስ ለብሰህ ስትወጣ፣ ወይም ሶሻል ሚዲያ ላይ የሆነ ነገር ፖስተህ የሰዎችን 'Like' እና 'Comment' በየደቂቃው "ምን ይሉኝ ይሆን" ብለህ #ተጨንቀህ ታውቃለህ? በሆነ ስብሰባ ወይም ጓደኞችህ ዘንድ ሃሳብህን ለመናገር ፈልገህ "ሰዎች ይስቁብኝ ይሆን? ቢጠሉኝስ? ሞኝ አድርገው ቢያዩኝስ?" በሚል ፍርሃት አፍህ ተቆልፎ ህመሙን በውስጥህ ውጠኸዋል? ​ሁልጊዜ የሰዎችን ፈገግታና ተቀባይነት (Approval) ለማግኘት ስትል ብቻ የራስህን ፍላጎት ደብቀህ፣ የሰዎችን "እሺ" ባይ አገልጋይ ሆነህ ለመኖር ስትጥር እውነተኛ ማንነትህን አጥተኸው ታውቃለህ? ​welcome 😊 ይህ በሳይኮሎጂው ዓለም "Validation Seeking" (የተቀባይነት ጥማት) እና "Spotlight Effect" ይባላል። ​#ሳይኮሎጂ እንደሚያስተምረን፣ አእምሮአችን ሁሉም ሰው እኛን ብቻ በትኩረት የሚያይ፣ ድክመታችንን የሚያስብ እና የሚገመግመን ይመስለዋል። በዚህ ጊዜ እውነተኛ ማንነታችንን ደብቀን ሰዎች ደስ የሚላቸውን "ማስክ" (Mask) እንለብሳለን። የሰዎችን አብሮነትና ሙገሳ እንደ ኦክስጅን እንፈልገዋለን፤ ምክንያቱም በሳይንሱ ተቀባይነት ማጣት አእምሮአችን ውስጥ ልክ እንደ አካላዊ ህመም (Physical Pain) ተደርጎ ስለሚተረጎም ነው። ​የሰዎች ፍርሃትና የ "العزة" (የክብር) ምንጭ በቁርአን መስታወት! ​ይህ የሰዎችን አስተያየት የመፍራትና በነሱ ዘንድ ዋጋ ለማግኘት የመለፋት ስነ-ልቦናዊ በሽታ፣ ቁርአን ውስጥ ጥልቅ በሆነ መንገድ ተተንትኗል። አላህ (ሱ.ወ) የሰዎችን ፍርሃትና የክብር/የተቀባይነትን ፍለጋ ምንጭ ሲገልጽልን እንዲህ ይላል፦ ​وَتَخْشَى النَّاسَ وَاللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَاهُ ​"ሰዎችን ትፈራለህ፤ አላህ ግን ልትፈራው የሚገባህ የበለጠ ተገቢው ነው!" (አል-አሕዛብ፡ 37) ​እና ደግሞ የሰው ልጅ ዋጋውንና ክብሩን ከየት መፈለግ እንዳለበት ሲነግረን፦ ​مَن كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا ​"ክብርንና (የተቀባይነትን ዋጋ) የሚፈልግ ሰው፤ ክብሩ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው!" (ፋጢር፡ 10) ​ተመልከት ሀቢቢ.. ሰዎች ስለ አንተ ያላቸው አስተያየት በየሰከንዱ ይለዋወጣል። ዛሬ የሚያደንቅህ ሰው ነገ ሊጠላህ ይችላል፤ ዛሬ የሚያጨበጭብልህ ነገ ሊሰድብህ ይችላል። የሰዎችን አስተያየት የህይወትህ መሪ ካደረግክ፣ የሰዎች የስሜትና የቃላት እስረኛ ነው የምትሆነው! ​አላህ "እውነተኛ ክብርና ዋጋህ በእኔ እጅ ነው" እያለህ፣ አንተ ግን ያንን ዋጋህን ከሰዎች ኮሜንት፣ ከሰዎች ፈገግታ ወይም ከሰዎች እሺታ ልትገዛ ትደክማለህ። የሰዎችን ፍርሃትና ተቀባይነት ፍለጋ ልብህ ውስጥ ስታስገባ፣ የአላህን ታላቅነት ትረሳዋለህ። ​Listen carefully:- ​እውነተኛ ነፃነት ማለት ሰዎች ስለ አንተ የሚሉትን መጥፎም ሆነ ጥሩ ነገር ከአንተ ማንነት ጋር አለማያያዝ ነው። ሰዎች "አሪፍ ነህ" ስላሉህ አትበልጥም፣ "መጥፎ ነህ" ስላሉህም አታንስም። ዋጋህ የሚለካው ከአላህ ጋር ባልህ ግንኙነት ብቻ ነው። ​ዛሬ በህይወትህ አንድ ውሳኔ ስትወስን ራስህን ጠይቅ፦ "ይህን እያደረግኩ ያለሁት አላህን ለማስደሰት ነው ወይስ የሰዎችን ተቀባይነት ለማግኘት?" ​📖 Quran + Psychology 🧠 ​❤️‍🩹 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah

  • ⚠️ አስተውሉ❗️ በቁርአን ውስጥ "ኸሊሉላህ" ተብሎ የተጠራው ነቢይ ማን ነው?

  • 8 авг.18иС Sle_qelbachn1

    🎉 አስደሳች ዜና!! ♥️የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) ✍️ የኪታቡ ፀሐፊ፡ አቡ ዐብዱረሕማን አኒስ ብኑ ሷሊሕ 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል ባጂ 🗓 መቼ ይጀምራል? ነሐሴ 4 ፣ ሰኞ ⏰ የዘወትር ፕሮግራማችን ቀናት እና ሰዓት፡ ☑️ ቀናት፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ እና ሰኞ ☑️ሰዓት፡ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ⚠️ሐቂቃ ይህ ኪታብ በተለይም በዚህ ዘመን በድብቅ ወንጀል ለተፈተነ፣ ስማርት ስልኮችና ኢንተርኔት ላመጡት የብቸኝነት ፈተና መፍትሔ የሚሰጥ፣ እንዲሁም ጌታችን አላህ ሁሌም እየተመለከተን መሆኑን በማስታወስ ልብን የሚያነቃቃ ድንቅ ኪታብ ነው! 🔴ትምህርቱ ቀጥታ ስርጭት የሚሰጥበት ቻናል፦🔗 ✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1 😬የኪታቡን PDF ለማገኘት:t.me/Sle_qelbachn1/1963

  • የሆነ አካል ላይ የምንሰጠው እርምት የባሱ አካላት የሚያተርፉበት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

  • ~ምንዳዉን ብናውቅ ኖሮ ድሎትን እንደምናጣጥመው ሁሉ ችግርንም ባጣጣምን ነበር።የሙስሊም ሐዘኑም፣ እንባዉም፣ብሶቱም፣ ሀሳቡም፣ጭንቀቱም፣ ድንጋጤዉም፣ መከራዉም፣ ፈተናዉም፣ ህመሙም ... ሁሉ አጅር አለው። አብሽሩ! =t.me/AbuSufiyan_Albenan

  • 6 авг.30иС sunah_channel

    ከወሳኝ ነቢያዊ ዱአዎች ውስጥ ከዘይድ ቢን አርቀም (رضيﷲ عنه)ተይዞ ረሱል (ﷺ) ይህን ዱዓ ያደርጉ ነበር፡‐ ”اللهمَّ إنِّي أعوذُ بك من علْمٍ لا ينفعُ، ومن قلْبٍ لا يخشعُ، ومن نفسٍ لا تشبعُ، ومن دعوةٍ لا يُستجابُ لها“ “አላህ ሆይ! ከማይጠቅም ዕወቀት፥ ከማይፈራ ልብ፥ ከማትጠግብ ነፍስ፥ ተቀባይነት ከሌለው ዱዓም በአንተ እጠበቃለሁ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: (2722) https://t.me/sunah_channel

  • ✍️ ሰላትን የተወ ሰው ነገ የውመል ቂያማ ከማን ጋር ይቀሰቀሳል❓

  • አንተ የለመድካት አፊያ (ጤና) ለሌላው ሰው የዘወትር ዱአው ናትና የተሰጠህን አመስግን! الحمد لله عب العالمين ➥https://t.me/sunah_channel ➥ https://t.me/hammad_tube

  • 4 авг.38иС sunah_channel

    ዐብዱሏህ ኢብኑል ሙባረክ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) እንዲህ ይላሉ፦ “ ከነብይነት በኃላ፣እንደ ሸሪዓዊ ዒልም (ጠቃሚ እውቀትን) ከማሰራጨት የበለጠ ትሩፋት ያለውን አላውቅም።” 📚 [ሲፈት አሥ-ሰፍወህ ሊብኒል ጀውዚይ (4/138)]

  • ቁርአን መቅራት ካልቻላችሁ ማዳመጡም አጅር አለው መቅራት የምትችሉት ደግሞ ለተደቡር እና ሙራጀኣ ለማድረግ ይሆናችኋል። ለቀልቦ ስንቅ ቁርዓን 👇

  • 📙ኪታብ በነፃ ልናስተምራችሁ ነው🎊 በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ🌛 🌟ወላሂ የእውነት ማስታወቂያ ነው ቶሎ ተቀላቀሉ🌟