tgindex
Dn Henok Haile

Dn Henok Haile

Статистика
@henokhaile_dnтурецкий

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመር እጅግ ጥልቅ ናት! #henokhaile #eotc #mahibere_kidus #tewahdomedio #orthodoxmezmur #ኦርቶዶክስ #Janderebaw_media #የአዕላፋት_ዝማሬ

Последний пост
3 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
турецкий
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 773
−1 за 2 дн.
Сутки
−3
−0,17%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 280
20 постов
Вовлечённость
72,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
725
1/48двое суток
830
1/72трое суток
896

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 3 авг.433283

    መድኃኔዓለም ማለት የዓለም መድኃኒት፣ የፍጥረት ሁሉ አዳኝና ታዳጊ ማለት ነው። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና አስተምህሮ መሠረት መድኃኔዓለም የሚለው ስም የጌታችን፣ የመድኃኒታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ግብሩን፣ ፍቅሩንና ቸርነቱን የሚገልጽ ታላቅና ክቡር ስም ነው። ​ መድኃኔዓለም በሰው ልጅ ውድቀትና በኃጢአት ምክንያት የመጣውን የሞት ፍርድ በፍጹም ፍቅሩ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በመሞት ያስወገደ፣ ዓለምን ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ ነፃነት ያሸጋገረ አምላክ ነው። መድኃኔዓለም የኃጢአተኞች መጠጊያና የምሕረት አምላክ ነው። ምንም ያህል ብንበድል እንኳ በተሰበረ ልብ ወደ እርሱ ስንመለስ በክንዱ ታቅፎ የሚቀበል አባት ነው። ​"መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በታላቁ ምሕረትህና አባትነትህ ሀገራችንን፣ ቤተሰባችንንና ሕይወታችንን ጠብቅ፤ የልባችንን እረፍትና ሰላም ስጠን።"

  • "ሕፃን ልጅ እንደ ትልቅ ሰው ሲናገር ያስደንቃል። ትልቅ ሰው እንደ ሕፃን ሲናገር ግን ያሳቅቃል"። ዛሬ ብላቴናው ቂርቆስ፥ "እናቴ ሆይ ገድላችንን እንፈጽም ዘንድ ጨክኚ"። ብሎ እንደ ትልቅ ሰው የተናገረበት ዕለት ነው። ትልቅ ሰው ሆነው እንደ ሕፃን የሚናገሩትን ያሳድግልን።

  • 22 июл.9833410

    ፍቅር ቊስል ነው እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው። እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል። ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው:: ፍቅር የሚታወቀው በተለዋወጥናቸው ቃላት ሳይሆን በታገስነው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነው መሥዋዕትነትና በተካፈልነው ብርሃን ነው። ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤውን ድል ማብሠሪያ መለከት ሳይሆን ፣ የፍቅሩ ማስረጃው ቁስሉ ነበር። Henok Haile

  • 14 июл.1 103132

    በአብርሃም ደጅ የተገለጡ ሥላሴ ብቻ አይደሉም። እኒህ ሁሉ ተገልጠዋል እንጂ። 1ኛ ምስጢረ ሥላሴ፦ "ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ" ዘፍጥረት ምዕ 18፥2 ይህ መገለጥ ምስጢረ ሥላሴ ይባላል። ጥንት ሰውን በአምሳላቸው የፈጠሩ ሥላሴ፥ዛሬም ለአብርሃም በሰው አምሳል ተገልጠዋል። መሆንና መምሰል እንደሚለያይ ልብ ይሏል። 2ኛ ምስጢረ ሥጋዌ/የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር፦ ልጁ ይሥሐቅን ሊሠዋ ወደሞርያም ተራራ ወጥቶ ነበር። በልጁ ፈንታ በግ ሠውቶ ተመለሰ። ዘፍጥረት 22፥1-14። ይህ ምስጢረ ሥጋዌ ይባላል።በእኛ ስለእኛ የሚሰዋው የቀራንዮ በግ- ክርስቶስ ምሳሌውን በዚያ ተራራ አሳይቶናልና። በደጁ ምስጢረ ሥላሴን በልጁ ምስጢረ ሥጋዌን ተረዳን። 3ኛ ምስጢረ ጥምቀት፦ በኋላ ጌታችን የሚጠመቅበትን ዮርዳኖስን ተሻግሮ ሄዶ ካህኑ መልከጼደቅን አግኝቶት ነበር። ይህ ጉዞው የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ተተርጉሟል። ዘፍጥረት 14፥17-20፡፡ 4ኛ ምስጢረ ቁርባን፦ አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ያገኘው ካህን ለሐዲስ ኪዳን ምሳሌ የሆነውን ቁርባን ሰጥቶታል። 5ኛ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን፦ ልጁን ሊሠዋ ወደሞርያ ተራራ በሄደ ጊዜ፥ ልጁ ሞቶ እንደማይቀር እንደሚነሣ ያምን ነበር። ዕብ11፥19::

  • 10 июл.1 11011

    "ጠባቂ እንደሌለው በግ እንዳንኾን አባግዕን በዚያም፥ በዚያም ዘልቀው አራዊት እንዲነጣጠቋቸው ተኵላ እንዳይነጥቀን አለ፤ መናፍቃን እንዳያስክዱን። በሃይማኖት ከኛ የተለዩ አሕዛብ መናፍቃን እንዳይነቅፉን። እኒኽ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ጳጳስ ደግ ንጉሥ የማያስነሣላቸው ሃይማኖታቸው የቀና ባይኾን እንጂ ነው ብለው፤ ሐተታ፦ ሕዝቡ ቢከፉ ባይመለሱ በሕዝቡ ክፋት ዓላዊ ንጉሥ መናፍቅ ጳጳስ ያስነሳባቸዋል። ወያነግሥ ብእሴ መደልወ በእንተ እከየ ሕዝብ እንዲል። ሕዝቡ ግን ደግ ቢኾኑ ቢመለሱ በሕዝቡ ደግነት ደግ ራትዕ ንጉሥ ሃይማኖታዊ ጳጳስ ያስነሳላቸዋል፤ ወያነግሥ ብእሴ ራትዓ በእንተ ሠናይተ ሕዝቡ እንዲል፤ ይኽ ከሞተበት ጀምሮ እስኪ ሾም ድረስ የሚጸልይ ነው።"[ሥርዐተ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ ምዕራፍ ፰፤ ቍ.፷፭-፷፮፤ ገጽ ፷፱]

  • 3 июл.1 287184

    + በእግዚአብሔር መንግሥት አንድ ቀን + ጸአተ ነፍስ (The departure of Soul) ከተሰኘው የኦርቶዶክስ ቴዎሎጂ ምሁራን የጋራ ሥራ የሆነ ዳጎስ ያለ ድንቅ መጽሐፍ መግቢያ ላይ አንድ አባት ስለ አንድ ሰው ታሪክ የጻፉት ነገር በጣም አስገራሚ ነበር:: እጅግ መጥፎ የነበረ አንድ ሰው ድንገት በጠና ይታመምና በአልጋ ላይ ይውላል:: ሕመሙ እጅግ የጠና ቢሆንም የማይገድለው ሆነና ለሠላሳ ዓመታት ተሠቃየ:: በክፉ አመል ላይ ክፉ ሕመም ተጨምሮ ለሌሎችም ችግር ሆነ:: በአልጋው ላይ ሆኖም ደጋግሞ ሰውንም ፈጣሪውንም ይሳደብ ነበር:: ከሠላሳ ዓመታት ሥቃይ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች:: የመንደሩ ሰው ተሰበሰበና ማልቀስ ጀመረ::  "ውይ ተገላገለ" "ይኼ ክፉ አረፈ? ያረፍነውስ እኛም ነን!" እያለ በልቡ እያሸሞረ ቁጭ አለ:: አጅሬው ግን ሞተ ከተባለ ሦስት ሰዓታት ቆይታ በኁዋላ ድንገት እንደ እንቅልፍ ነቃ:: ሰዉ ድንጋጤም ደስታም ተቀላቅሎበት ተቀበለው:: ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሞገደኛው ሰው እንደቀደመው መናከሱን ትቶ ትሑት ለሰው አዛኝ ሆኖ አረፈው:: የጠሉት ሁሉ ይቅርታ እስኪያደርጉለት ድረስ እጅግ መልካም ሰው ሆነ:: አንድ አባት በሰውዬው መለወጥ ተደንቆ ሞቶ በነበረበት ጊዜ ምን እንደገጠመው ጠየቀው:: እርሱም እንዲህ አለ :- "ከሞትሁ በኁዋላ ለሦስት ሰዓታት ያህል በሲኦል ሥቃይ ውስጥ ቆይቼ ነበር:: በሲኦል ካሳለፍሁት የሦስት ሰዓታት ሥቃይ የምድር ላይ የሠላሳ ዓመት ሥቃይ እጅግ ይሻለኛል:: በሲኦል ሦስት ሰዓት ከመቆየት በምድር ላይ የዕድሜ ልክ ሥቃይ ይሻላል" በእርግጥ የሲኦል የአንድ ሰዓት ሥቃይ ከዚህ ዓለም የዐሥር ዓመት ሥቃይ ከበለጠ ከዚህ ዓለም የዕድሜ ልክ ደስታም የመንግሥተ ሰማያት የአንዲት ቀን ደስታ ይበልጣል:: ንጉሥ ዳዊት "ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች" እንዳለ በመንግሥተ ሰማያት አንዲት ቀን መቆየት ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ሺህ ዓመት ከመደሰት ይበልጣል:: “በዚህ ዓለም ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል:: ከብዙ ዘመኖችም አቤቱ ይቅርታህን ማግኘት ይሻላል" 2 መቃ. 13:4 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ #join

  • 28 июн.1 194312

    ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!! "ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች።የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንኳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!

  • https://youtu.be/m-gQFYAacdc?si=GnRrea8w-iQT0bqn

  • видео или голосовое, без подписи

  • 24 июн.1 27015

    የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ! በዚህ የሐዋርያት ጾም ሐዋርያው ጳውሎስን እንዴት እያነበባችሁ ነው?

  • 24 июн.1 38515

    видео или голосовое, без подписи

  • 🎈በምን እጽናናለሁ?🎈በዘማሪ ሚክያስ አረጋዊ 🎈አዲስ መዝሙር 🎈New Mezmur https://youtube.com/watch?v=dJieVgi0-84&si=bRCTL8gCgTZ8RV_m

  • 23 июн.1 2604

    видео или голосовое, без подписи

  • 23 июн.1 25095

    видео или голосовое, без подписи

  • 23 июн.1 341204

    ወጣትነታችንን  የስኬት ለማድረግ በጣም እንፈልጋለን ግን ደግሞ ትልቁ ሀብት እግዚአብሔር ጎሏል ፤ ስለዚህ እርሱን ጨምረን መንገዳችንንን ፣ ሃሳባችንን፣ ህይወታችንን.........ሙሉ እናድርግ ።              #join 👇

  • 21 июн.1 3003

    https://youtu.be/AxSrYl06bBQ?si=VvDZuMJfntueKDvO

  • https://youtu.be/jJio3YQPa_s?si=WT7s7aeFueI4S85c

  • 12 мая2 1104312

    ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው። ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን! join👇

  • 9 мая1 620402

    ኢየሱስ የተነበበባት ፊደላችን ተወለደች። የትኛውም ከአንደበታችን የሚወጣ ቃል ረቂቅ ነው። አይታይም አይጨበጥም። "ኢየሱስ" ብለን በቃላችን ብቻ ብንናገር ስሙ አይዳሰሰም አይታይም። ይህን ስም ማየትና መንካት ከፈለግን የግዱን ኢየሱስ ብለን በፊደል መጻፍ ያስፈልገናል። በወንጌል "እግዚአብሔር መንፈስ ነው" ተብሎ ተጽፏል።መንፈስ ማለት ረቂቅ ማለት ነው። ረቂቁ አምላክ እንዴት ገዘፈ? እንዴት ታየ? በፊደል ስለተገለጠ ነዋ። ፊደል ያልናት ድንግል ማርያምን ነው። ረቂቁ አምላክ ሰው ስለሆነባት ስለታየባት ቤዛ ሊሆነን ግዙፍ ሥጋን ስለነሳባት። እሷ ፊደል ከሆነች ልጇ ወንጌል ነው። ወንጌልን ያለ ፊደል ምን ብለህ ታነበዋለህ? እንዴትስ ታየዋለህ? ወንጌላችን የሚጻፍባት ፊደል ዛሬ ከሐና ማሕፀን ከኢያቄም አብራክ ተገኘች። ሰአሊ ለነ ቅደስት!

  • 11 апр.2 6602924

    “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም፤ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ዲያብሎስን አሰረው፤ አዳምን ነጻ አወጣው፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ኾነ፡፡”

Dn Henok Haile — tgindex