Info Tech
описание
በዚህ ቻናል ስለ የተለያዩ የtechnology ውጤቶች ስለ Cyber security, ስለ hacking እና የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ Share & Join https://t.me/+B9IclNRA1gljNmFk
33 315
подписчиков
Охват к подписчикам
6,1%
ERR
Реакции к просмотрам
0,12%
61 на 45 постов
Пересылки к просмотрам
0,15%
75
Постов в день
0,4
всего 23
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 6 авг.እጅግ አስገራሚ ሰበር ዜና! የኢሎን ማስክ (SpaceX) ሮኬት ጨረቃ ላይ ተከሰከሰ! 🚀 በመላው ዓለም ያሉ የጠፈር ተመራማሪዎችን ያስደነገጠ እና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበ ከባድ አደጋ በህዋ ላይ ተከስቷል! 👇 የተከሰተው አስገራሚ ክስተት ይኸውልዎ 👇 💥 በከፍተኛ ፍጥነት ተጋጨ!፦ ባለፈው ዓመት ወደ ጠፈር ተተኩሶ የነበረው ባለ 4 ቶን ክብደት ያለው የ SpaceX Falcon 9 ሮኬት የላይኛው ክፍል ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ በሰዓት 8,700 ኪሎ ሜትር (በድምፅ ፍጥነት 7 እጥፍ) በሆነ እጅግ ዘግናኝ ፍጥነት በመጓዝ ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 5 ቀን 2026 ዓ.ም ጠዋት ላይ ከጨረቃ ጋር ተጋጭቷል! 🏢 የአምስት ፎቅ ያክላል!፦ ይህ በህዋ ላይ ሲንሳፈፍ የቆየው ግዙፍ የብረት አካል፣ በጨረቃ ላይ በሚገኘው አንስታይን ክሬተር (Einstein Crater) በተባለው ቦታ ላይ ነው ያረፈው። 🕳️ ግዙፍ ጉድጓድ ፈጥሯል!፦ ግጭቱ በጨረቃ ላይ ከ 60 እስከ 100 ጫማ ስፋት ያለው አዲስ ትልቅ ጉድጓድ ሳይፈጥር አልቀረም ተብሏል። 🇨🇱 የቺሊ ቴሌስኮፕ መዝግቦታል!፦ ግጭቱን በአይን ማየት ባይቻልም፣ በቺሊ የሚገኝ ግዙፍ የጠፈር መነፅር (Telescope) ከግጭቱ በኋላ የተነሳውን የሶዲየም እና ሊቲየም የትቢያ ደመና ተመልክቷል! 📢 ሳይንቲስቶች ምን አሉ? ናሳ (NASA) ክስተቱን በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን "በመሬት ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አያመጣም" በማለት አረጋግጧል። ነገር ግን ይህ ክስተት የሰው ልጅ በህዋ ላይ እየጣለው ስላለው የቆሻሻ ክምችት (Space Junk) ትልቅ ማስጠንቀቂያ መሆኑን ባለሙያዎች በጭንቀት እየተናገሩ ይገኛሉ! 🔄 ፎቶዎች በቅርቡ ይፋ ይሆናሉ! የናሳ እና የደቡብ ኮሪያ መንኮራኩሮች በቦታው ላይ ሲያልፉ አዲሱን የጉድጓድ ምስል አንስተው እንደሚልኩ ይጠበቃል።0,98%
- 8 окт. 2025 г.📞True Caller Premium Unlocked 🔓 ✔ ማስታወቂያ የለውም ✔ ስልካችሁን ማን እንዳየ ማወቅ ትችላላችሁ ✔ እምቢ ካላችሁ play store disable አድርጉ መጀመሪያ ✔ ምንም ክፍያ አይፈልግም ✔ የተቆለፈ ምንም ነገር የለውም ✔ ሌላ የምፈልጉት ካለ ኮሜንት ላይ0,29%
- 10 июн.በ AI ምክንያት ከፍተኛ አደጋ (ስጋት) ላይ ያሉ ስራዎች የትኞቹ ናቸው? 📉 ስራችሁ ኮምፒውተር ላይ ተቀምጦ፣ ተደጋጋሚ (Routine) የሆነ የዲጂታል መረጃን ማቀነባበር ከሆነ... AI ከእናንተ በተሻለ ፍጥነት እና ርካሽ ዋጋ ሊሰራው ይችላል!"👇 ⚠️ 1. የዳታ ማስገባት እና ቀላል መዝገብ አያያዝ (Data Entry & Basic Bookkeeping): መረጃዎችን ከወረቀት ወደ ኤክሴል (Excel) መገልበጥ ወይም ደረሰኞችን መመዝገብ ከዚህ በኋላ የሰው ሀይል አይፈልግም። አሁን ያሉት AIዎች (እንደ Claude) በሺዎች የሚቆጠሩ የ PDF ገጾችን እና ደረሰኞችን በሰከንዶች አንብበው፣ አደራጅተው እና አስልተው ማስቀመጥ ይችላሉ። ⚠️ 2. የደንበኞች አገልግሎት (Basic Customer Service / Call Centers): ፓስዎርድ ረሳሁ እቃዬ የት ደረሰ?" ወይም "አገልግሎት አልሰራ አለኝ" ለሚሉ ተደጋጋሚ የደንበኞች ጥያቄ ሰውን ቀጥሮ ማሰራት አብቅቷል። ኩባንያዎች አሁን 24 ሰዓት ያለ እረፍት፣ በሁሉም ቋንቋዎች (በድምፅም ጭምር) ከሰው በማይለይ ትህትና የሚያወሩ የ AI ወኪሎችን (AI Agents) እየተጠቀሙ ነው። ⚠️ 3. መለስተኛ የጽሁፍ ትርጉም እና ኮፒራይቲንግ (Basic Translation & Copywriting): ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ ጽሁፎችን መተርጎም፣ ወይም አጫጭር የብሎግ ጽሁፎችን መጻፍ ብቻውን እንደ ሙያ መቀጠሉ አደጋ ላይ ነው። AI በሰከንዶች ውስጥ የተስተካከለ ሰዋሰው ያለው ጽሁፍ መጻፍ ስለሚችል፣ የትርጉም ስራዎች እና መደበኛ ጽሁፎች ሙሉ በሙሉ ወደ AI እጅ እየገቡ ነው። ⚠️ 4.(Entry-level Coders/Testers):ኮዲንግ (Coding) ከተማርኩ ስራ አላጣም" የሚለው አባባል አሁን እየተቀየረ ነው። እንደ GitHub Copilot ያሉት AIዎች ለሲስተም የሚሆኑ መሰረታዊ ኮዶችን ራሳቸው ይጽፋሉ፣ ስህተቶችንም (Bugs) ፈልገው ያርማሉ። ስለዚህ ጀማሪ ፕሮግራም አድራጊዎች (Junior Developers) ስራ ለማግኘት እጅግ ፈታኝ እየሆነባቸው ነው። ⚠️ 5. መደበኛ የግራፊክስ ዲዛይን (Basic Graphic Design): ቀላል ሎጎዎችን፣ የሶሻል ሚዲያ ፖስተሮችን ወይም የጀርባ ምስሎችን (Backgrounds) ለማስወገድ የግራፊክስ ባለሙያ መፈለግ ቀርቷል። እንደ Canva AI እና Midjourney ያሉት መሳሪያዎች ማንም ሰው የራሱን ዲዛይን በነጻ እንዲሰራ አስችለውታል። ስራችሁ ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ውስጥ ከሆነ መደናገጥ አያስፈልግም፤ ነገር ግን ማደግ (Upskill ማድረግ)ግዴታ ነው! ከ "አድራጊነት" ወደ "አስተዳዳሪነት" መሸጋገር አለባችሁ። ለምሳሌ፦ ተራ ጽሁፍ ተርጓሚ ከመሆን፣ የ AIን ጽሁፍ አርትኦት (Edit) የሚያደርግ እና ስትራቴጂ የሚያወጣ ባለሙያ መሆን! ✍ELA_TECH0,25%
- 31 июл. 2025 г.ሳፋሪኮም እና ፔይፓል ኤምፔሳን ከአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ጋር ለማስተሳሰር ተስማሙ። ሳፋሪኮም ከፔይፓል ጋር በመሆን ኤምፔሳን በፔይፓል አለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ውስጥ ለማካተት አጋር ሲሆን በአጋርነቱ መሰረት 35 ሚሊየን የኤምፔሳ ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። በአጋርነቱ መሰረትም ተጠቃሚዎች የፔይፓል አካውንታቸውን ከኤም ፔሳ ጋር በማስተሳሰር የገንዘብ ዝውውሮችን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል። ለጊዜው አገልግሎቱ በኬንያ በሚገኙ ተጠቃሚዎች ላይ የሚጀመር ሲሆን በሂደት ኤም ፔሳ ወደሚሰራበቸው ሌሎች አካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል። ሳፋሪኮም በኤምፔሳ ሱፐር አፑ ሰዎች በቀጥታ ከፔይፓል ገንዘብ ማውጣት እንዲችሉ የሚያስችል አማራጭንም አካቷል። ሰዎች በቀጥታ የፔይፓል ገንዘባቸውን ከኤምፔሳ ማውጣታቸው በተለያየ መንገድ የሰሩትን ገንዘብ ሳይንዛዛ በቀጥታ እንዲያወጡ ያስችላል። በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ሁለቱን አካውንቶች በማስተሳሰር በቀላሉ የገንዘብ ዝውውሮችን መፈፀም ይችላሉ ተብሏል። ኤም ፔሳ በአፍሪካ ቀዳሚው የሞባይል ገንዘብ መተግበሪያ እንደሆነ ሲዘገብ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን በማፍራት በየዕለቱ ከ1.1 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ዝውውሮችንም ያሳልጣል። ፔይፓል በአለም አቀፍ ደረጃ ከ400 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ሲኖሩት በተለይ ለኦንላይን ስራዎች ዋነኛ የክፍያ አማራጭ ሆኗል። በኬንያ በሚገኘው ኤምፔሳ የሚጀምረው አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያም እንደሚመጣ ሲጠበቅ በርካታ ወጣቶች በኦንላይን ስራዎች ያገኙትን ገንዘብ በቀላሉ እንዲያወጡ ያስችላል። Source: TikvahethMagazine Join https://t.me/infoTech_et0,23%
- 24 мар.በተለያየ category አሪፍ የሆኑ የAI Platforms ✍Perplexity – best for real-time research and fact-checked answers. ✍Jasper – best for consistent branding and marketing content at scale. ✍Copy.ai – best for fast marketing copy and product messaging. ✍Notion AI – best for writing, summarizing, and organizing inside your workfeedbac ✍Grammarly – best for real-time writing feedback and tone correction ✍ChatGPT – best for all-purpose brainstorming, writing, and logic-based tasks. ✍Claude – best for thoughtful writing, document reasoning, and context-heavy tasks ✍Cursor – best for coding inside an AI-native IDE ✍Synthesia – best for turning scripts into polished videos with AI avatars ✍PlayAI – best for creating lifelike AI voiceovers in multiple languages ✍Descript – best for editing audio and video by editing text. ✍Midjourney – best for generating high-quality, stylized AI visuals. ✍Grok – Best for Fact checking and video generation ✍Vapi AI – best for building real-time AI voice agents for phone calls. ✍Gemini — Best for Photo, image generation and editing. ✍Obviously AI – best for running no-code predictions on business data. ✍Make – best for building visual, multi-step automations across tools ✍Intercom – best for AI-powered customer support and live chat. ✍Zapier – best for connecting apps and automating repeatable workflows. ከተዘረዘሩት ውስጥ ነፃ የሆኑ አሉ። የFree አማራጭ ያላቸው አሉ። ክፍያ የሚጠይቁም አሉ። ✍Big habesha0,21%
- 9 июн.ማንኛውንም አፕሊኬሽን ወይም ሶፍትዌር (ለምሳሌ፦ Telegram for Desktop, CapCut, VLC Media Player ወይም WinRAR) ለማውረድ ጎግል (Google) ላይ ፈልገው ያውቃሉ? ሰርች ሲያደርጉ መጀመሪያ የመጣውን ሊንክ ተጭነው ካወረዱ፣ ትልቅ ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ሊሆን ይችላል! በአሁኑ ሰዓት የሳይበር ሌቦች እኛን ለማጥመድ ጎግልን ራሱን በገንዘብ እየገዙት ይገኛሉ። ይህ አደገኛ ስልት በሳይበር ደህንነት "Malvertising" (Malicious Advertising) ይባላል። 🚨 ጥቃቱ እንዴት ነው የሚሰራው? እኛ ጎግል ላይ የአንድ ሶፍትዌር ስም ጽፈን ስንፈልግ፣ ጎግል መጀመሪያ ላይ "Sponsored" ወይም "Ad" (ማስታወቂያ) የሚል ምልክት ያላቸውን ሊንኮች ያመጣልናል። ሌቦቹ የራሳቸውን ቫይረስ ያለበትን ድረ-ገጽ ይፈጥሩና ልክ የእውነተኛው ሶፍትዌር ድረ-ገጽ እንዲመስል ያደርጉታል። ከዚያም ለጎግል ገንዘብ በመክፈል የእነሱ የውሸት ድረ-ገጽ ከእውነተኛው ድረ-ገጽ በላይ መጀመሪያ መስመር ላይ እንዲቀመጥ ያደርጋሉ። 💡 አደገኛው ነገር፦ ሰዎች ጎግል መጀመሪያ ያመጣውን ሊንክ ሁልጊዜ እውነተኛ ስለሚመስላቸው ሳያስተውሉ ይጫኑታል። የሚወርደው ሶፍትዌር በትክክል ስራውን ቢሰራም፣ በጀርባ ግን የስልካችንን እና የኮምፒውተራችንን የባንክ ፓስወርዶች፣ ክሪፕቶ ቫሌቶችን እና የሶሻል ሚዲያ አካውንቶችን ሰርቆ ለሌቦች የሚልክ "Information Stealer" የተባለ አደገኛ ቫይረስ አብሮ ይጫናል። 🛠 ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ? (3 ወርቃማ ህጎች) 1️⃣ "Sponsored" ወይም "Ad" የሚሉትን ሊንኮች ይለፉ፦ ጎግል ላይ ሰርች ሲያደርጉ ከመጀመሪያዎቹ 2 ወይም 3 ሊንኮች አጠገብ Sponsored የሚል ጽሁፍ ካዩ እሱን ይለፉት። ወደ ታች ወረድ ብለው ማስታወቂያ የሌለበትን ኦሪጅናል ሊንክ ይጫኑ። 2️⃣ የድረ-ገጹን ስም (Domain Name) በደንብ ያረጋግጡ፦ ሌቦች እውነተኛውን ስም በማስመስል ይጽፉታል። ለምሳሌ እውነተኛው telegram.org ከሆነ፣ እነሱ telegram-download.org ወይም telgrem.org ሊሉ ይችላሉ። በፊደላት ጨዋታ እንዳይሸወዱ ስሙን ደግመው ያንቡ። 3️⃣ ከይፋዊ የApp Store ማውረድ፦ ከተቻለ ማንኛውንም አፕሊኬሽን ከጎግል ድረ-ገጽ ከመፈለግ ይልቅ በስልካችሁ ላይ ያለውን Google Play Store / App Store ወይም በኮምፒውተራችሁ ላይ ያለውን Microsoft Store በመጠቀም በቀጥታ አውርዱ። የሳይበር ሌቦች ከቴክኖሎጂው እኩል ስልታቸውን እየቀየሩ ስለሆነ ሁልጊዜ በጥንቃቄ መፈለግን ልምድና አድርጉ! ይህንን መረጃ ለወዳጅዎ ሼር በማድረግ ከትልቅ ኪሳራ ይታደጓቸው። 🛡️✨ ✍EthioCyebr0,21%
- 11 окт. 2025 г.ፌስቡክ አካውንት ለጊዜው ለማጥፋት Deactivate ለማድረግ ✅ ፌስቡክ አካውንትዎን ለተወሰነ ጊዜ እረፍት ለመስጠት (Deactivate) እና ሲፈልጉት ለመመለስ (Reactivate) የሚከተሉትን step መጠቀም ይችላሉ። አካውንትዎን ማጥፋት (Deactivate) ማለት ፕሮፋይልዎ እና ይዘቶችዎ ከሰዎች እይታ ይሰወራሉ ማለት ነው፣ ነገር ግን ሲመለሱ ሁሉንም ነገር እንደነበሩ ያገኛሉ። 👉 1. በስልከዎ Facebook አፕሊኬሽን የፌስቡክ አፕሊኬሽኑን ይክፈቱ ከላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ የሚገኘውን የሶስት ሰረዝ ምልክት (☰) ወይም የፕሮፋይል ፎቶዎን ይጫኑ። ወደ ታች ይሸብልሉ እና "Settings & Privacy" (ሴቲንግስ እና ፕራይቬሲ) ከዚያም "Settings" (ሴቲንግስ) የሚለውን ይምረጡ። ከላይኛው ክፍል ላይ ባለው "Account Center" (አካውንት ሴንተር) የሚል ክፍል ስር "Personal details" (የግል መረጃ) የሚለውን ይጫኑ። 👉 "Account ownership and control" (የአካውንት ባለቤትነት እና ቁጥጥር) የሚለውን ይምረጡ። "Deactivation or deletion" (ማጥፋት ወይም መሰረዝ) የሚለውን ይጫኑና ማጥፋት የሚፈልጉትን አካውንትዎን ይምረጡ። "Deactivate account" (አካውንትን ለጊዜው ማጥፋት) የሚለው አማራጭ መመረጡን ያረጋግጡና "Continue" (ቀጥል) የሚለውን ይጫኑ። የይለፍ ቃልዎን (Password) ያስገቡና ለጊዜው የሚዘጉበትን ምክንያቶችን በመምረጥ ሂደቱን ይጨርሱ። 👉 2. በኮምፒውተር (በWeb Browser) ወደ Facebook.com ይሂዱና አካውንትዎን ይክፈቱ። ከላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያለውን የፕሮፋይል ፎቶዎን ይጫኑ። "Settings & Privacy" (ሴቲንግስ እና ፕራይቬሲ) ከዚያም "Settings" (ሴቲንግስ) የሚለውን ይምረጡ። በግራ በኩል ከሚታዩት አማራጮች ውስጥ "Privacy" (ፕራይቬሲ) የሚለውን ይምረጡ (ወይም ከላይ እንደተጠቀሰው "Account Center" ውስጥ ይግቡ)። በ "Your Facebook Information" ክፍል ውስጥ "Deactivation and Deletion" የሚለውን ይፈልጉና ይጫኑ። "Deactivate Account" የሚለውን ይምረጡና "Continue to Account Deactivation" የሚለውን ይጫኑ። የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ፣ አካውንቱን ለጊዜው ማጥፋት የፈለጉበትን ምክንያት ይምረጡና Deactivate ያድርጉ። ፌስቡክ አካውንትዎን ወደነበረበት ለመመለስ (Reactivate) አካውንትዎን ወደነበረበት መመለስ (Reactivate) በጣም ቀላል ነው። ማድረግ ያለብዎት ነገር ቢኖር፡- በማንኛውም ጊዜ ወደ Facebook.com ወይም የፌስቡክ አፕሊኬሽን ይሂዱ። በተለመደው መንገድ ኢሜል አድራሻዎን ወይም ስልክ ቁጥርዎን እና የይለፍ ቃልዎን (Password) በማስገባት Log In ያድርጉ። Share our channel 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/infoTech_et0,20%
- 9 окт. 2025 г.👆👆👆👆👆👆👆👆 ስማርት ስልክ ሲገዙ በደንብ ማየት ያለባችሁ ነገሮች ከዚህ በታች ዘርዘር አድርጌ አስቀምጫቸዋለሁ በደንብ አንብባችሁ ተረዱት። 🧠 Processor (CPU) ምንድን ነው? “Processor (CPU)” የሚባለው በስማርት ስልክ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ክፍል ነው። CPU ወይም “Central Processing Unit” የስልኩ አእምሮ ነው። ስልኩ ሲነሳ(ሲዘጋ)፣ አፕልኬሽኖች ሲከፍቱ(ሲዘጉ)፣ ሁሉንም የሚቆጣጠር ይህ ነው። ⏺ በአጭሩ ፈጣን ፕሮሰሰር ያለው ስልክ= ፈጣን ስልክ ያዘ ማለት ነው። በአንጻሩ ደግሞ ዘገምተኛ ፕሮሰሰር ያለው የሚዘገይ ስልክ ይሆናል ማለት ነው። ⚙️ የፕሮሰሰሩ ክፍሎች CPU ብዙ ክፍሎች አሉት፦ 🔹 (a) Cores – ኮሮች ኮር ማለት እንደ አንድ አእምሮ ክፍል ነው። ⏺ ከፍ ያለ ኮሮች ስልኩን ብዙ ስራ በአንድ ጊዜ እንዲሰራ ያስችለዋል ⏺ ዋና ዋና አይነቶች 💎 Dual-Core (2 cores) → ቀላል ስራዎች ብቻ 💎 Quad-Core (4 cores) → መካከለኛ ደረጃ 💎Octa-Core (8 cores) → በተለይ ዘመናዊ ፈጣን ስልኮች ይጠቀማሉ 🔹 (b) Clock Speed (GHz) እንደ ሰው ፍጥነት ነው። በGHz (Gigahertz) ይመዘናል። 1.8GHz, 2.4GHz, 3.0GHz … እያለ ይቀጥላል። 🏷️ ዋና ዋና የፕሮሰሰር አይነቶች (Android ስልኮች ላይ) ⏺ Qualcomm Snapdragon – በጣም ታዋቂ እና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው። ⏺ Snapdragon 8 Gen 2 / Gen 3 → Flagship (ከፍተኛ ደረጃ) ⏺ Snapdragon 7 Gen 1 / 6 Gen 1 → መካከለኛ ⏺ Snapdragon 4 / 680 → ዝቅተኛ ዋጋ ✅ RAM (ራም) Random Access Memory የተለያዩ መተግበሪያዎችን በተመጣጣኝ ፍጥነት እንዲሰሩ የሚረዳ አስፈላጊ ክፍል ነው። 🔹 1. RAM ምንድን ነው? RAM የስልኩ ጊዜያዊ ማከማቻ Temporary Memory በመሆን ያገለግላል። የስልኩ አፕልኬሽኖች ሲከፍቱ በRAM ውስጥ በጊዜያዊነት ይቀመጣሉ። በመሆኑም ስልኩ በፍጥነት ይሰራ ዘንድ ያግዛል። 🔹 2. በስማርት ስልክ ውስጥ ያለው የRAM መጠን በGB ይለካል። ከ4GB በታች – ለመደበኛ አጠቃቀም ብቻ 6GB–8GB – ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ተጠቃሚ 12GB+ – እጅግ በጣም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲኖር ያግዛል። ✅ የመረጃ ማከማቻ (Storage) ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ መተግበሪያዎች እና ፋይሎችዎን ለማከማቸት የሚጠቀሙበት ቦታ ብዙ መረጃ ለማከማቸት ከፍተኛ መጠን (ለምሳሌ 64GB ወይም 128GB) ያለውን ይጠቀሙ! ✅ 🔋 Battery (ባትሪ) መለኪያ የመያዝ አቅም (Capacity) – mAh (milliampere-hour) የሚለካ ሲሆን ቁጥሩ чем ከፍተኛ ከሆነ ባትሪው የበለጠ ጊዜ ይቆያል። ምሳሌዎች፦ 🔹 3000mAh – ዝቅተኛ፣ ለቀላል ተጠቃሚ 🔹 4000–5000mAh – መካከለኛ እና የተመጣጣኝ ስልኮች 🔹 6000mAh እና ከዚያ በላይ – ብዛት ያላቸውን ሰአታት የሚያቆይ ነው። ስልካችሁ ቪዲዮ፣ ኢንተርኔት በብዛት የሚጠቀሙበት ከሆነ ቢያንስ 5000mAh ወይም ከዚያ በላይ ቢሆን ይመረጣል። 2. ፈጣን መሙያ (Fast Charging) ባትሪ በፍጥነት እንዲሞላ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ነው። የመሙያ ፍጥነት በ “Watt (W)” ይመዘናል። 🔹 10W – ዝቅተኛ ፍጥነት 🔹 18W – መካከለኛ 🔹 33W, 45W, 65W – ፈጣን መሙያ 🔹 100W+ – በጣም ፈጣን (ባትሪ በ30 ደቂቃ ውስጥ ሊሞላ ይችላል) ✅ Charging Port 💎 USB Type-C የዘመናዊ የሚባለው ፖርት ነው። ፈጣን እና ሁለት በኩል የሚገባ ነው። 💎 Micro USB የድሮ ነው፣ አሁን አብዛኛው አይመከርም። 🔹 Screen Display መለኪያዎች የመጠን መለኪያ Size (inches) የማሳያው መጠን በ"inch" ይመዘናል። ለምሳሌ፦ 6.1”, 6.5”, 6.8” ወዘተ። ⏺ ትልቅ ስክሪን ያላቸው ስልኮች ለአጠቃቀም ምቹ ናቸው። ነገር ግን ኃይል ብዙ ይጠቀማል። ⏺ ትንሽ ስክሪን ያላቸው ለእጅ አያይዝ ምቹ ሲሆኑ እና ባትሪን ይቆጥባል። 🟩 ጥራት – Resolution ይህ የማሳያው ጥራትን ያመለክታል። በፒክስል (pixels) ይመዘናል። እንደምሳሌ፦ HD (720p) – ዝቅተኛ ጥራት Full HD (1080p) – መካከለኛ ጥራት FHD+ / 2K / 4K – ከፍተኛ ጥራት (በግምት መጠቀም ለቪዲዮ፣ ጨዋታ እና እይታ ቀለም በጣም ግሩም ነው) 🟩 Refresh Rate (የእንቅስቃሴ ፍጥነት) የ Refresh Rate (የእንቅስቃሴ ፍጥነት) በመሰረቱ የመጀመሪያ ትርጉሙ ማንኛውም ስክሪን በአንድ ሰከንድ ውስጥ የሚያደርገውን screen redraw ብዛት ነው። Refresh Rate መለኪያ በ Hertz (Hz) ይለካል። 60Hz ማለት፦ screen redraw በአንድ ሰከንድ ውስጥ 60 ጊዜ ማለት ነው። 90Hz = በሰከንድ 90 ጊዜ 120Hz = በሰከንድ 120 ጊዜ ⏺ ከፍተኛ Refresh Rate (ለምሳሌ 120Hz) ያለው ስማርትፎን ስክሪን 👉 ምስሎች በቀላሉ ይንቀሳቀሳሉ፣ ዝቅተኛ Refresh Rate (ለምሳሌ 60Hz) 📱 በስማርትፎን ውስጥ 60Hz — መደበኛ ፍጥነት 90Hz — በጥቂት የተሻለ ፍጥነት (smoother scrolling) 120Hz እና ከዚያ በላይ — የፍጥነት ሁኔታ ከፍተኛ ሲሆን ከፍተኛ ባትሪ ይጠቀማል። 🟩 Brightness (ብርሀን) ይህ በውጭ ብርሀን ውስጥ ማሳያውን እንዴት እንደሚታይ ያመለክታል። ከ 800 nits በላይ – በፀሐይ ብርሀን ውስጥ ይታያል። በታች ከዚያ በውጭ ቦታ መመልከት ይከብዳል። 🟩 የመጠበቂያ ቴክኖሎጂ (Screen Protection) አዲስ ስልኮች ብዙ ጊዜ Gorilla Glass 5, 6, Victus ወዘተ ያላቸው ይሆናሉ። ✅ የካሜራ ጥራት መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። የተለያዩ ፎቶዎችዎ እና ቪዲዮዎችዎ ለማንሳትና ለመቅረጽ ጥራቱ በጨመረ ቁጥር ጥራት ያለው ቪዲዮና ፎቶዎችን ማግኘት እንችላለን። ጥራቱ በፒክስል (Megapixels) ይለካል፤ 💎 የካሜራ መገለጫዎች (Specifications) 📏 Megapixel (MP) የካሜራ መጠንን ያመለክታል። ⏺ 8MP – 12MP → መካከለኛ ⏺ 48MP – 64MP → ጥሩ ⏺ 108MP እና ከዚያ በላይ → ከፍተኛ ፎቶ ጥራት 💡 ተጨማሪ ጠቃሚ ሀሳቦች ✅ Network & Connectivity (መረብ እና ግንኙነት) የስማርት ስልክ ዋና ክፍል ነው። ይህ የሚያሳይዎት ስልክዎ እንዴት ከመረብ ጋር (ኢንተርኔት፣ ኮምፒዩተር፣ ሌሎች መሳሪያዎች) ይገናኛል እና የምን ደረጃ ፍጥነት ይሰጣል የሚለውን ነው። 📶 4G LTE ወይም 5G ኔትወርክ 💎 4G LTE (Long Term Evolution)፡ በአሁኑ ሰአት የትኛው ሀገር ላይ የሚሰራ ወቅታዊ የኔትወርክ አይነት ነው። በኢትዮጵያም በብዙ ከተሞች የሚሰራ ነው። ⏺ የሚገዙት ስልክ የኔትወርክ አይነቱ ቢያንስ ቢያንስ 4G መሆን አለበት። የቪዲዮ ስትሪሚንግ፣ መጫወቻ፣ የድምጽ እና የቪዲዮ ኮል ለመጠቀም በቂ ፍጥነት ይሰጣል። ⏺ 5G (Fifth Generation Network)፡ ከ4G በ10 እስከ 20 እጥፍ ፈጣን ነው። 💎 አሁንም በኢትዮጵያ በተወሰኑ ከተሞች ብቻ ነው የሚገኝ። 👉 በአጠቃላይ፣ ከተቻለ 5G የሚያገለግል ስልክ መግዛት ወደፊት አገልግሎት ይጠቅማል።0,17%
- 2 мар.በቅርቡ በብሔራዊ ባንክ የተጣለው የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት እገዳ ተፈጻሚነት አጠራጣሪ መሆኑን ምሁራን ተናገሩ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም (አሐዱ ራድዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል የንግድ መድረኮች አማካኝነት እንደ ባንክ ያሉ ገንዘብ አስተላላፊ ተቋማትን ሳይጠቀሙ “የቀጥታ ሰው-ለሰው” ወይም በእንግሊዘኛው (Peer to Peer) የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይቶች ሕገ-ወጥ ናቸው ሲል እገዳ መጣሉን ተከትሎ አሐዱ ያነጋገራቸው የፋይናንስ ባለሙያዎች መሰል ድርጊቶችን መቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል። ባንኩ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሳ ባወጣው መግለጫ በማንኛውም የንግድ መድረክም ሆነ የክሪፕቶፕ ልውውጥ አገልግሎት ላይ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የገንዘብ ግብይቶች የተከለከሉ መሆናቸውን አመልክቷል። ይሁን እንጂ የግብይቱ ሂደት ድብቅና በቴክኖሎጂ የተመሰጠረ በመሆኑ፣ ማዕከላዊ ባንኩ እገዳውን በተግባር ለማዋልና ለመቆጣጠር አዳጋች እንደሚሆንበት የዘርፉ ምሁራን ስጋታቸውን ገልጸዋል። የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ቆስጠንጢንዮስ በርኸተስፉ፣ “ክሪፕቶ ከረንሲ ድብቅ የገንዘብ ዝውውር በመሆኑ ከብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ውጪ ነው” ሲሉ ለአሐዱ ራድዮ ተናግረዋል። መንግስታት የቴክኖሎጂው ዝውውር ለሕገ-ወጥ ተግባር ይውላል የሚል ስጋት እንዳላቸው የጠቆሙት ዶክተር ቆስጠንጢንዮስ፣ “አንድ ግለሰብ በክሪፕቶ መገበያየት ከጀመረ ከየትኛውንም ሀገር ማንኛውንም ዕቃ መግዛት እንደሚችልና ገንዘቡም በድብቅ የሚቀመጥ በመሆኑ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ ያደርገዋል” ብለዋል። በቴክኖሎጂው አማካኝነት የሀገር ሀብት ሙሉ ለሙሉ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው፣ የክሪፕቶ ዝውውር የባለቤቱ ስም፣ የሚገኝበት ቦታ እና ሌሎች ግላዊ መረጃዎች በግልጽ ሳይታወቁ የሚከናወን በመሆኑ ቴክኖሎጂው ከሀገራት መደበኛ የገንዘብ ፍሰት ውጪ ነው የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል። አክለውም። በክሪፕቶ ከረንሲ ዝውውር እና ግዢ ላይ የመንግስታት፣ የዓለም አቀፍ ባለሐብቶች፣ የእጽ አዘዋዋሪዎች እና የሌሎችም ባለድርሻዎች ተሳትፎ የበዛ ሊሆን እንደሚችል አንስተው በከፍተኛ ጥንቃቄ በድብቅ መከናወኑ ቁጥጥሩን ውስብስብ እና አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ ፋይናንስ መምህር አቶ ፋሲል ጣሰው በበኩላቸው፣ ብሔራዊ ባንክ የክሪፕቶ ከረንሲን ዝውውር አስመልክቶ በቅርቡ ያወጣውን እገዳ ተግባራዊ ለማድረግ ያስቸግራል በሚለው በዶክተር ቆስጠንጢንዮስ ሐሳብ ይስማማሉ። “ክሪፕቶ ከረንሲ የማይታይና የማይታወቅ የገንዘብ ዓይነት በመሆኑ፣ መንግስት ከዝውውሩ ማግኘት ያለበትን ግብር ያሳጣል” ያሉት መምህሩ ባንኩ እንደነዚህ ያሉት መድረኮች ለከፍተኛ የዋጋ መለዋወጥ፣ ለገንዘብ ማጭበርበር እና በሕገ-ወጥ ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ለማድረግ ወይም (Money Laundering) የተጋለጡ በመሆናቸው ሕብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ መክረዋል። በአሁኑ ወቅት ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ለመዘርጋት ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እያጠና መሆኑን የጠቀሰው ብሔራዊ ባንክ፣ ሕጋዊ አሰራር እስከሚዘረጋ ድረስ ማንኛውም በኢትዮጵያ ብር የሚካሄድ የክሪፕቶፕ ከረንሲ ዝውውር በሕግ እንደሚያስጠይቅ ገልጿል። በህይወቴ ጌትነት #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ0,16%
- 5 окт. 2025 г.ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉትን መሳሪያዎች በዝርዝር አብራራለሁ። እነዚህን መሳሪያዎች በሶስት ዋና ዋና ክፍል መሠረታዊ መክፈቻ እና ማገጃ መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ እና የሰርኪዩት መለኪያ መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ለሶፍትዌር ጥገና የሚያገለግሉ መሳሪያዎች። 1. መሠረታዊ መክፈቻ እና ማገጃ መሳሪያዎች እነዚህ ማንኛውም የሞባይል ጥገና ለመጀመር የሚገቡት መሰረታዊ መሳሪያዎች ናቸው። መሳሪያ የሚጠቀምበት ቦታ ሚና ✅ የሞባይል መፍቻ ስብስብ (Mobile Screwdriver Set) ስልኩን ለመፍታት የሚያገለግል ሲሆን ሞባይል ስልኮች የተለያዩ ዓይነት ማሰሮዎች (screws) ስላሏቸው (እንደ ትራይ-ዋንግ፣ ፒኤች፣ ስኩዌር) የተለያዩ ራሶች ያሉት መፍቻ ስብስብ ያስፈልጋል። ✅ ፕላስቲክ ፕራይ ስብስብ (Plastic Pry Tool Set) ስልኩን ለመክፈት የስልኩን አካል (housing) ሳይቀጥቀጥ ለመክፈት ይጠቅማል። በብረት መሳሪያ መክፈት ስልኩን ሊጎዳ ይችላል። ✅ ትዊዘሮች (Tweezers) ትናንሽ ክፍሎችን ለማንሳት ሬዚስተሮች፣ ካፓሲተሮች እና ሌሎች ትናንሽ ክፍሎች ሲነቀሉ ለመቆናጠጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። ✅ የጥገና ቦርድ (Repair Board Holder) የስልኩን ማቀፊያ ለመያዝ የስልኩን ቦርድ (motherboard) በደህንነት ያቆያል እና በጥገና ጊዜ እንዳይጎዳ ይጠብቃል። 2. የኤሌክትሪክ እና የሰርኪዩት መለኪያ መሳሪያዎች እነዚህ የስልኩ ውስጣዊ ችግሮችን ለመፈተሽ እና ለመጠገን የሚጠቀሙባቸው ልዩ መሳሪያዎች ናቸው። ✅ መልቲሜትር (Multimeter) የኤሌክትሪክ ችግሮችን ለመፈተሽ ሬዚስታንስ (Resistance)፣ ቮልቴጅ (Voltage) እና ከረንት (Current) ለመለካት ያገለግላል። የሰርኪዩት ቀጣይነት (continuity) መፈተሽ ይቻላል። ✅ የሙቀት መቀጠያ (Soldering Iron) የተሰበረ ሽቦ ለመገጠም በቦርድ ላይ ያሉ ክፍሎችን ለመግጠም ወይም ለመፍታት ይጠቅማል። ለሞባይል ጥገና የሚመከር የ40-60 ዋት (Watt) መቀጠያ ነው። ✅ ሃውት አየር ገንዳ (Hot Air Rework Station) አይሲ (IC) ቺፖችን ለመቀየር በቦርድ ላይ ያሉ ቺፖችን (ICs) በሙቀት አማካኝነት ለማንቀሳቀስ እና ለመተካት ያገለግላል። በጣም አስፈላጊ ነው። ✅ የመቅለጫ ሽቦ (Solder Wire) እና ፍሉክስ (Flux) በመቀጠያ ሥራ ላይ ፍሉክስ (Flux) የመቅለጫው ጥራት ለማሻሻል ይጠቅማል። የመቅለጫ ሽቦም ክፍሎችን ለማገናኘት ያገለግላል። ✅ የማጉላት መስታወት (Magnifying Glass) / ሙየርስ መነጽር (Microscope) ትናንሽ ክፍሎችን ለማየት በቦርድ ላይ ያሉ ትናንሽ ክፍሎችን፣ ቺፖችን እና ጉድለቶችን በግልጽ ለማየት ይጠቅማል። ✅ ዲሲ ፓወር ስፕላይ (DC Power Supply) የኃይል ችግሮችን ለመፈተሽ ለስልኩ 3.7V የሚሆን ቮልቴጅ በመስጠት ስልኩ ኦፕን (open) ወይም ሾርት (short) መሆኑን ያሳያል። ኃይል ሲያጠፋ የሚሞቅ ክፍል ለመለየት ይረዳል። 3. ለሶፍትዌር ጥገና የሚያገለግሉ መሳሪያዎች የሶፍትዌር ችግሮችን (እንደ መታጠፍ፣ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ችግር) ለመፍታት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች። ✅ ኮምፒዩተር (Computer) ወይም ላፕቶፕ (Laptop) ሶፍትዌር ለማውረድ እና ለመጫን የጥገና ሶፍትዌሮችን (firmware) ለማውረድ እና ስልኩን ለማገናኘት መሠረታዊ ነው። ✅ ዩኤስቢ ኬብል (USB Cable) ስልኩን ከኮምፒዩተር ጋር ለማገናኘት የስልኩን የመተላለፊያ ፕሮቶኮል (data transfer protocol) ማወቅ አለበት። ✅ ፍላሽ ቦክስ (Flash Box) / የጥገና ሳጥን (Medusa Box, Z3X Box ወዘተ.) ሶፍትዌርን ለመጫን ይህ ልዩ መሳሪያ ኮምፒዩተርን ከሞባይል ጋር ለማገናኘት ይረዳል እና የሶፍትዌር ጥገና (firmware flashing) ለማድረግ ያስችላል። 4. ሌሎች ጠቃሚ እቃዎች ✅ የኤሲቲን (Acetone) ወይም ኢዛፕሮፕይል አልኮሆል (Isopropyl Alcohol): ለቦርድ ማፅዳት እና ከሙቀት የተፈጠረውን ዝገት ለማስወገድ። ✅ ጃምፐር ዋየር (Jumper Wire): የተሰበረ የሰርኪዩት መንገድ ለመገጠም። ✅ የፕላስቲክ ማጠፊያ (Plastic Wrap): ስልኩን ከውሃ ለመከላከል በሚጠገንበት ጊዜ ለመጠቅለል። ማስታወሻ፡ ሞባይል ጥገና ትንሽ የቴክኖሎጂ እውቀት የሚጠይቅ ሥራ ነው። መሠረታዊ መሳሪያዎችን ብቻ በመጠቀም ብዙ ችግሮችን (እንደ ባትሪ መቀየር፣ ከቨር መጠገን) መፍታት ይችላሉ። ነገር ግን ለውስጣዊ ችግሮች (እንደ ቺፕ መቀየር) የላይ የተጠቀሱት ሁሉ መሳሪያዎች ያስፈልጉታል። ✍muhammed computer0,14%
- 6 янв.የወደፊቱ የአለማችን የኢንተርኔት አብዮት Starlink ምንድን ነው? Starlink በኤለን መስክ ድርጅት SpaceX የተመሰረተ የሳተላይት ኢንተርኔት project ነው። የዚህ ፕሮጀክት ተቀዳሚ ተልዕኮው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ብዙ ቁጥር ያላቸው Low Earth Orbit (LEO) ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማቅረብ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ዋና ዋና ባህሪያቶች Global Coverage: የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት መላው ፕላኔት የሚሸፍን ሲሆን ይህም ቀደም ሲል የኢንተርኔት ግንኙነት የማያገኙ የአለማችን ክልሎችን ተደራሽ ያደርጋል። High-Speed Internet: ስታርሊንክ ከባህላዊ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የሚወዳደር የብሮድባንድ ፍጥነትን የሚያቀርብ ሲሆን Online Gaming, Video Conferencingና የመሳሰሉ real-time online ስራዎችን በጥሩ ፍጥነት መከወን ያስችላል። Easy Installation: StarLink ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነችና በቀላሉ ከታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምትቻል Dish ሲኖረው ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሷን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ LTE connection ላላቸው የሞባይል ቀፎዎች የፅሁፍና የድምጽ መልዕክት እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሏል። Constant Updates: ስታርሊንክ ተጨማሪ ሳተላይቶችን በማምጠቅ እና ሶፍትዌሩን በማዘመን ኔትወርኩን በየጊዜው እያሰፋ እና እያሻሻለ ይገኛል። አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ብዙ የአለም ክፍሎችን እያካለለ ነው። Disaster Response: አሁን የምንጠቀምባቸውን የኢንተርኔት አቅራቢ ድርጅቶችን infrastructure በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ቢወድሙ communication ይቋረጣል። የስታርሊንክ ሳተላይት ከዚህ ነገር ነጻ ሲሆኑ ለድንገተኛ አገልግሎቶች እና እርዳታ የሚፈልጉ የተጎዱ ሰዎችን በቀላሉ ማግኘት ያስችላል። በአሁኑ ሰአት በተወሰኑ የአለማችን ሃገራት ስራ የጀመረው StarLink ከአፍሪካ ሃገራት ናይጀርያ፣ ጋና፣ ሴራሊዮን፣ ማላዊ፣ ዛምብያ፣ ቦቶስዋና፣ ማዳጋስካር፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ናቸው። ይህን አገልግሎት ለመጠቀም ክፍያው ያን ያክል ውድ የሚባል አይደለም። ከሃገራት ሃገራት ልዩነት ቢኖረውም ለግለሰብ unlimited high-speed ዳታ ለመጠቀም በወር 120 ዶላር መክፈል ይጠይቃል። ለBusiness plan ደግሞ በወር ከ140 እስከ 5000 ዶላር ድረስ ያስከፍላል። ጎረቤቶቻችን ኬንያና ሶማልያ የstarlink service ካላቸው ሃገሮች መካከል ናቸው። ✍️ በሀገራችን በተለይ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ብዙ ሰው የኢንተርኔት አገልግሎት አያገኝም። ይህ ነገር በሃገራችን ቢጀመር ብዙ ሰው የሚጠቀም ይመስላችኋል? ሀሳባችሁን አካፍሉን። ✍ Big habesha0,07%
- 9 янв.ትክክለኛ ሊንኮች‼️ ብሄራዊ ባንክ ሁሉም የባንክ ደንበኞች የፋይዳ መታወቂያ ቁጥራቸውን ማስተሳሰር እንዳለባቸው መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል። ባንክ መሄድ ሳይጠበቅባችሁ የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር ከታች ያሉትን ሊንኮች መጠቀም ትችላላችሁ። ፋይዳ ለማስተሳሰር ትክክለኛ ሊንኮች የሚከተሉት ናቸው። ሲስተም ላይ በነበረ መጨናነቅ ለቀናት ቆይቶ የነበረውም የመዘግየት ችግር በመፈታቱ ፣ ደንበኛ የሆኑበትን ባንክ ከታች በተዘረዘሩት ዝርዝር በመምረጥ ባለ 16 አኃዝ የፋይዳ ቁጥርዎን (FAN/FCN) በመጠቀም ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ማጣመር ይችላሉ። 💸 አቢሲኒያ ባንክ: cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect 💸 አዋሽ ባንክ : fayda.awashbank.com የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ: my.coopbankoromiasc.com/harmonization የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ cbefayda.cbe.com.et ኦሮሚያ ባንክ bfayda.oromiabank.com ወጋገን ባንክ fayda.wegagenbanksc.com.et/harmonization ንብ ባንክ fayda.nibbank.com.et ፀሀይ ባንክ fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home ስንቄ ባንክ : fayda.siinqeebank.com:7443 💸 ዘምዘም ባንክ : fayda.zamzambank.com.et 💸 አማራ ባንክ : fayda.amharabank.com.et Via (አዩዘሀበሻ)0,06%