Intrance result.neaea.gov.et
Статистикаመረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም! ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ። የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! @intrancresult ሀሳብ @TheRsultBot
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 137
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 191
- 1/48двое суток
- 218
- 1/72трое суток
- 236
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ውድ የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል። የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ የሚገኙ ሲሆን፥ የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ነው። 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል፣ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው! 🔗አሁኑኑ ይመዝገቡ፡ ethiocoders.et
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል። የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ ዓይነቶችን ለመተግበር እየተደረገ ያለውን ዝግጅት የተመለከተ መመሪያ አስተላልፏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ላይ "የሙያና ቴክኖሎጅ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜያቸው ጋር የተመጣጠነ ሆኖ እንዲሰጥ ይደረጋል" በሚል አቅጣጫ መቀመጡን ያመለክታል። በዚህ መሰረት በየደረጃው የሥራና ተግባር ትምህርት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሁም 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ በሚያስችል መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በተለያዩ የሙያ አይነቶች ከቀለም ትምህርታቸው ጎን ለጎን ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ12 የሙያ አይነቶች እየተሰጠ እንደሚገኝም ሰርኩላሩ ያትታል። ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር እንዲተገበሩ ለተለዩት 11 የሙያ አይነቶች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ ትምህርቶች እንዲሁም ለ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችና የመምህር መምሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል። በመሆኑም እነዚህን ተጨማሪ የሙያ አይነቶች ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ለማስጀመር :- • የክልሉ/የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና እቅዱን ለማከናወን በጀት በመያዝ የሙያ አይነቶችን በትምህርት ቤት እና በተማሪዎች ደረጃ በማስመረጥ፣ • የየሙያ አይነቱ መምህራንን በመቅጠር፣ • የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓት በሂደት በማሟላት፣ • መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን እና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን ትምህርቱን ለማስጀመር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል። የሙያ አይነቶቹ ፦ - ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ፣ - አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ - አልባሳት ቴክኖሎጂ፣ - ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት፣ - ቧንቧ ስራ፣ - ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ - ሰብል አመራረት፣ - ጤና ክብካቤ አገልግሎት፣ - ሆቴል አገልግሎት፣ - ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እንዲሁም ምግብ ዝግጅት ናቸው። ትምህርት ሚኒስቴር 💠 🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ! ✈️https://t.me/Tmhrt_Minister ✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተፈታኞች ቅሬታ በ2018 ዓ.ም አገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ሳይገለፅ በመዘግየቱ ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው። "ፈተናውን ወስደን ከጨረስን ድፍን ሁለት ወራት ሊሞላን ነው" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "ይህን ያህል ጊዜ ውጤት ሳይገለፅ መቆየቱ ተገቢ አይደለም" ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። "ውጤት ሳይገለፅ 57 ቀናት ማለፉ ተገቢ አይደለም፣ ለድባቴና ያልተገባ ጫና ተዳርገናል" ያሉት ተማሪዎቹ፤ "መንግሥት በአስቸኳይ ውጤታችንን ያሳውቀን" ሲሉ ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል። ቲክቫህ የሪሚዲያል ፈተና ወጤት መቼ ይለቀቃል ሲል የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር ከሪሚዲያል ፈተና ውጤት ጋር የተያያዘ የሚያወጡትን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል። ከ53 ሺህ በላይ ተፈታኞች ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሪሚዲያል ፈተና መውሰዳቸውን ይታወቃል ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
አሁን ጀምር ! ከአሁን ጀምሮ ራስህ ላይ ብትሰራ በዚህ አለም የሚኖርህን ቀሪ ቆይታ ማሳመር ትችላለህ፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አብዝተህ ማሰብ አቁም! ትናንትን መቀየር አትችልም፤ ዛሬን መጠንከር ከዛ ነገህን ማሳመር ትችላለህ። ወዳጄ ለምንም ነገር አልዘገየህም አጥብቀህ የምትፈልገውን ነገር አሁን ጀምረው! ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
видео или голосовое, без подписи
ኤአይ (AI)ን እንዴት እንጠቀም ? ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለረጅም ጊዜ እና ያለገደብ መጠቀም የሰዎችን የፈጠራ ብቃት እና ነገሮችን በጥልቀት የመመርመና የማሰብ ክህሎትን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በቅርቡ የወጡ ተከታታይ ጥናቶች አመልክተዋል። በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች መረጃዎችን እና ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በኤአይ (AI) ላይ ጥገኞች ሆነው ማከናወን ሲጀምሩ " ኮግኒቲቭ ሰረንደር " ወይም የአእምሮን የማሰብ ስራ ለቴክኖሎጂ አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ይህም አእምሮ በራሱ ጥረት መረጃዎችን የማቀናበር፣ የመተንተን እና አዳዲስ ሀሳቦችን የማመንጨት የተፈጥሮ ብቃቱ እንዲደክም ያደርገዋል። በተለይ #ወጣቶች እና #ተማሪዎች ለተወሳሰቡ ጥያቄዎች እና ስራዎች ፈጣን ምላሽ ከኤአይ ማግኘት መልመዳቸው የራሳቸውን የአእምሮ አቅም የመጠቀም ተነሳሽነታቸውን እንደሚቀንሰው ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን ቴክኖሎጂውን እየተጠቀሙ አእምሮን ሁል ጊዜ ንቁ፣ ብቁ እና ጤናማ አድርጎ ለማቆየት የሚረዱ በርካታ ሳይንሳዊ መንገዶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። የአእምሮን የአስተሳሰብ ብቃት ላለማጣት ምን አይነት ልምዶች ማዳበር ይቻላል ? - ከኤአይ (AI) የተገኙ ምላሾችን ወይም መረጃዎችን በቀጥታ ወስዶ ከመገልበጥ ይልቅ " ይህ መረጃ ትክክል ነው ? ምን ጎደለው ? አመክንዮአዊ ነው ? " በማለት በራስ አእምሮ መርምሮ፣ መዝኖ መጠቀም። - ማንኛውንም ስራ፣ ጽሑፍ ወይም ፕሮጀክት ከመጀመርዎ በፊት መነሻ ሀሳቦችን እና እቅዶችን በራስ አእምሮ ማመንጨት እና ማስታወሻ መያዝ። ኤአይ ስራውን ለማስጀመር ሳይሆን የተጀመረውን ስራ ለማደራጀት ወይም ለመፈተሽ ብቻ መጠቀም። - የፈጠራ እና የጥልቅ አስተሳሰብን የሚያነቃቁ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስልታዊ ጨዋታዎችን መጫወት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ ለመማር መሞከር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች/ስራዎችን ለኤአይ ሰጥቶ ያለ ምንም ምርመራ፣ ማስተካከያና ደጋግሞ የማንበብ ጥረት በቀጥታ #በመገልበጥ አንዳንዴም እንደራስ ስራ ማስመሰል እየተለመደ መጥቷል። ይህ በጥልቀት ሳያስቡና ሳይመራመሩ በቴክኖሎጂ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን አእምሮን የማሰብ ስራውን እንዲተው በማድረግ፣ እውነታን የመተንተን እና የጥልቅ አስተሳሰብ ብቃትን በከፍተኛ ደረጃ እየገደለው ይገኛል ፤ ሰዎች ትንሽ ስራ እንኳን ለመስራት የማይፈልጉ ስልቹና ሰነፍ እያደረጋቸውም ነው። ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ኤአይ (AI) የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን እንደ ረዳት መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው ነው። ጥቅም የሚኖረውም የሰው ልጅ የራሱን የአስተሳሰብ ልዕልና ጠብቆ ሲቀጥል ብቻ ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ #TikvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia
видео или голосовое, без подписи
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡ በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን፤ ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 የማለፊያ ነጥብ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡ በዚህም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 78,203 ተማሪዎች መካከል 47,307 ተማሪዎች (60.4%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳፍ ሲችሉ፤ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 126,224 ተማሪዎች መካከል 110,566 ተማሪዎች (63.8%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ የ6ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፤ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል። የ8ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se.ministry.et/#/result የ6ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se6.ministry.et/#/result ለተፈታኞች ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
видео или голосовое, без подписи
#AREB በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። በክልሉ 194,374 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 165,342 (85.06%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል። ውጤት ለማየት 👇 https://amhara6.ministry.et/#/result አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡ በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇 @emacs_ministry_result_qmt_bot የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ። ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara6.ministry.et/#/complaint VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ውጤት ትናንት መለቀቁ ይታወቃል። 📝ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ። ለተፈታኞች ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
📌 መቼም ቢሆን እጅ አትስጥ ✓ በወደቅክ ቁጥር ተነስ ✓በተሳሳትክ ቁጥር አስተካክል። ✓ባልተሳካልህ ቁጥር እንደገና ሞክር። ✓ ህይወት ልታሳዝንህ በሞከረች ቁጥር በግድም ቢሆን ፈገግ በል፡፡ Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!! በኦሮሚያ ክልል የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 08 - 09/2018 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል። 👉 የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል። 👉 ፈተናውን ከተቀመጡ 517,209 ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ (50% እና ከዚያ በላይ) በማስመዝገብ ወደ ሚቀጥለው ክፍል የተሸጋገሩት 464,839 (89.9%) ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል። ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል፡ 📍 ወንድ 267,307 ውስጥ 91.2% እና 📍 ሴት 249,902 ውስጥ 88.4% አልፈዋል። በዚሁ መሠረት ውጤት ለማየት ከዚህ በታች የቀረበውን ሊንክ በመክፈት፤ የመፈተኛ ቁጥርዎን (Registration Number) ማስገባት፤ ቀጥሎም የመጀመሪያ ስምዎን በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ትችላላችሁ። ሊንክ፦ https://oromia6.ministry.et ለተፈታኞች ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
ተነስ አድርገው! ትናንሽ የምትላቸውን ተግባራት አትናቃቸው! 5 ደቂቃ መፀለዩ ወይ 10 ደቂቃ ስፖርት መስራቱ ቀላል ይመስላል፤ ግን ትልቁን ጋን የሚደግፈው ትንሹ ጠጠር ነው። ነገ አደርገዋለው ምን ችግር አለው አትበል! ቸልተኝነት ዋጋ ያስከፍልሀል፤ ስለዚህ ተነስና ያሰብከውን አድርግ! ከዛ የአይምሮ ሰላም ታገኛለህ። ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ተቋማት እየገቡ ነው። ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በወረቀት ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የማጠቃለያ ፈተና፣ ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው የመፈተኛ ተቋማት እየገቡ ይገኛሉ። በተለይም በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ሲሆኑ፣ የተማሪዎች አቀባበል እስከ ነገ ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። ከአቀባበሉ በተጨማሪ፣ ተማሪዎች ስለ ፈተናው አሰጣጥ፣ ደንቦች እና አጠቃላይ ሂደት የሚመለከት ገለጻ (Orientation) ይሰጣቸዋል። ከዚህ ቀደም በወረቀት ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ፈተናው እንደሚሰጣቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ አይዘነጋም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሼር አርጉላቸው! Join🔗🔗🔗 https://t.me/intrancresult https://t.me/education_stor