በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት (Kebena special woreda)
Статистикаእጅ ለእጅ ተያይዘን የልዩ ወረዳችንን ልማት እናፋጥን!!
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 21
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 40
- 1/48двое суток
- 45
- 1/72трое суток
- 49
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ተቀናሽ የሚደረግ ወጪ (Deductible Expenses) (ነሀሴ 06/2018)ማንኛውም ወጪ በግብር ከፋዩ ገቢ ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማስገኘት፣ ለስራው ዋስትና ለመስጠት እና ስራውን ለማስቀጠል በግብር ዓመቱ ውስጥ የተደረገ አስፈላጊ የሆነ ወጪ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ እንደ ወጪ እንደሚያዝ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከላይ የተገለፀው አጠቃላይ አገላለፅ እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈላጊ ወጪዎች የሚከተሉትን እንደሚጨምር ስለተቀናሽ ወጪዎች የወጣው መመሪያ ቁጥር 40/2012 ይደነግጋል፡፡ አስፈላጊ ወጪዎች 👉በነፃ በሚጠቀምበት ወይም በተከራየው ህንፃ ስራውን ሲያከናውን ቤቱን በሰጠው ወይም በአከራዩ ስም በሚታወቀው የመብራት፣የውሀ ወይም የስልክ ቆጣሪ የተጠቀመ እንደሆነ እነዚህ ክፍያዎች በግብር ከፋዩ እንደሚከፈሉ በግልፅ በውል ውስጥ የተካተተ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ እና ወጪው የተከፈለበትን ደረሰኝ ኦሪጅናል ካቀረበ 👉ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ 👉የተመዘገበ የኤክሳይስ ታክስ እንዲሁም ተመላሽ ያልተደረገ ወይም በጊዜው ባለመቅረቡ ተመላሽ የማይደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ 👉የተበላሸ እቃ ዋጋ፣የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው እና የተወገዱ ዕቃዎች ዋጋ እና ለማስወገድ የወጣ ወጪ፣ 👉ግብር ከፋዩ ለንግድ ድርጅቱ እና መኖሪያ ቤት በአንድ የመብራት የስልክ ወይም የውሃ ቆጣሪ የሚጠቀም በሚሆንበት ጊዜ የመብራት፣ ስልክ እና የውሃ ወጪ በወጪ ተቀናሽ የሚያዘው ከወጪው 75 በመቶ ብቻ ይሆናል፡፡ 👉አንድ ግብር ከፋይ የንግድ ስራ እንቅስቃሴው በተቋረጠበት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ወይም ስራ ባላገኘበት ጊዜ ያወጣው ወጪ ለምሳሌ (የቤት ኪራይ ፣የሰራተኛ ደመወዝ፣ መብራት፣ውሃ፣ስልክ፣የመሳሰሉት ወጪዎች ሊሆኑ ይችላሉ) 👉የኃላፊነት አበል ወይም የውክልና አበል 10 በመቶ 👉በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው በቋሚነት ለሚሰራ ድርጅቱ ጥቅም ያደረገውን ትክክለኛ ወጪ ለመተካት በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራው ድርጅት የሚፈፅመው ክፍያ (ወጪው የንግድ ስራ ገቢ ለማስገኘት፣ ለስራው ዋስትና ለመስጠት ወይም የንግድ ስራውን ለማስቀጠል የተደረገ እና በቋሚነት በሚሰራው ድርጅት ሊሰራ የማይችል ከሆነ ብቻ)፡፡ 👉በዲዛይን ለውጥ ምክንያት ህንፃ ፈርሶ ሲገነባ የፈረሰው ህንፃ የመዝገብ ዋጋ 👉የተሽከርካሪ ጎማ የሚሰጠው ከአንድ አመት ያነሰ ከሆነ እንደ አላቂ ዕቃ ተቆጥሮ በተቀነሽ ወጪነት ይያዛል የወለድ ወጪ 👉በብድር የተገኘው ገንዘብ ለንግድ ስራ እንቅስቃሴ መዋሉ ሲረጋገጥ የወለድ ወጪ 👉ግብር ከፋዩ በዱቤ ለሚገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋውን እስኪከፍል ድረስ ወለድ እንደሚከፍል ውል የገባ እንደሆነ የከፈለው የወለድ መጠን 👉ግብር ከፋዩ ህንፃ ለመገንባት ብድር የወሰደ እንደሆነ ህንፃው እስኪጠናቀቅ ድረስ የተከፈለው ወለድ በእርጅና ተቀናሽ የሚካተት ሆኖ ተገንብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ የተከፈለው ወለድ በወጪ ተቀናሽ ይፈቀዳል የምርት ብክነት 👉በሚመለከተው የመንግስት አካል በቀረበ ጥናት መሰረት የሚወሰን በምርት ዝግጅትና አቅርቦት ሂደት የሚያጋጥም ብክነት የመዝናኛ ወጪ 👉የማዕድን ማውጣት እና ፍለጋ፤ የማኑፋክቸሪንግና የግብርናና ሆርቲ ካልቸር ስራ ላይ የተሰማራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብ እና መጠጥ ዋጋ በወጪ የሚያዘው በአንድ ወር የሚያወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ካወጣው አጠቃላይ የደሞዝ ወጪ ከ 30% ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ 👉ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች ወይም ሌሎች የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡ ተቋማት ውስጥ ለተሰማሩ ሰራተኞች ለተቀጣሪዎች የሚያቀርቡት የምግብ እና መጠጥ ወጪ ተቀናሽ የሚያደርገው በአንድ ወር የወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ከወጣው አጠቃላይ የደሞዝ ወጪ 20% ያልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ 👉ከላይ የተገለፁት ተቋማት የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡት በራሳቸው አዘጋጅተው ከሆነ ከምግብ ዝግጅት ጋር በተያያዘ የተደረጉት የግብዓት ወጪዎች ህጋዊ ደረሰኝ/ የግዢ ማስረጃ 👉ከላይ የተገለፁት ተቋማት የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡት በ3ኛ ወገን አማካይነት ከሆነ ወጪው ተቀባይነት የሚኖረው ከአቅራቢው ጋር የተደረገ ውል፣ አገልግሎቱ ስለመገኘቱ ከድርጅቱ በሚቀርብ ማረጋገጫ እና ለአቅራቢው ገንዘቡ ስለመከፈሉ በሚቀርብ ህጋዊ ደረሰኝ መሠረት የማስታወቂያ ወጪ 👉ግብር ከፋይ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚያደርገው የማስተዋወቅ ስራ በገንዘብ ወይም በምርት ወይም በአገልግሎት የሚፈጽመው ክፍያ በወጪ ተቀናሽ የሚያዘው ከጠቅላላ ገቢው (3% በመቶ) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ 👉ለመገናኛ ብዙሀን ወይም ለማስታወቂያ ድርጅት የሚከፍለው ክፍያ ሙሉ በሙሉ በወጪ ተቀናሽነት ይያዛል፡፡ የእርጅና ተቀናሽ 👉ግብር ከፋዩ ገቢውን ለማስገኘት በግብር ዓመቱ ጥቅም ላይ ላዋላቸው ዋጋቸው ለሚቀንስ ሀብቶች እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው የንግድ ሥራ ሀብቶች ዋጋቸው በቀነሰው የገንዘብ መጠን ልክ የእርጅና ቅናሽ ለማድረግ ይፈቀድለታል ለበጎ አድራጎት የሚደረጉ ስጦታዎች 👉 ግብር ከሚከፈልበት ገቢው ላይ ከ10 በመቶ ባልበለጠ (ይህ የሚፈቀደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የክልል መንግስት ካቢኔ ባደረገው ጥሪ መሰረት የአገሪቱን አንድነት እና ሉዓላዊነትን ለማስከበር ወይም ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ለመከላከል ለተመሳሳይ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት የሚውል ከሆነ ነው) #ወቅታዊ_እና_የተሟሉ_መረጃዎችን_ለማግኘት፡- #የቀቤና_ልዩ_ወረዳ_ገቢዎች_ቢሮ_ማህበራዊ_ድረገፆችን_ይቀላቀሉ👇 🌐 Telegram channel https://t.me/kebenearevenujoinch 🌐 YouTube ፔጃችን https://youtube.com/@kebenaspecialworedrevenueoffic?si=DZl-LEhnYaJHxtIL 🌐 ፌስቡክ ፔጃችን https://www.facebook.com/share/19Aj2G9qLd/ 🌐 Instagram https://www.instagram.com/kebenarevenue?igsh=YzljYTk1ODg3Zg== 🌐 የቲክቶክ ገፅ tiktok.com/@kebena.revenue.of 🌐 Email @kebenarevenueoffice100@gmail
видео или голосовое, без подписи
በቀቤና ልዩ ወረዳ የቅድመ-አንደኛ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ ወልቂጤ (ነሀሴ 06/2018 ዓ.ም)፤ የፌደራል ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ፍቃዶ ቀበሌ በልዩ ስሙ ሜልባ መንደር የቅድመ-አንደኛ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አኑረዋል ። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አሰካለ ተክሌ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ከተሰጠው የመንግስት ትራንስፖርት አገልግሎት ባሻገር፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ መሰረት ሰው ተኮር የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። በዛሬው እለትም የህፃናቱን የትምህርት እድል የሚያሻሽልና የወላጆችን እንግልት የሚቀንስ የትምህርት ቤት ግንባታና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል። የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ በበኩላቸው፤ የፌደራል ተቋማት እስከ ታችኛው መዋቅር ወርደው የሚደርጉት ድጋፍ የሚንደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ የትምህርት ቤት ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግና በትምህርት ጥራት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ቀደም ሲል በትምህርት ቤት ርቀት ምክንያት ህፃናት በጊዜ ትምህርት ሳይጀምሩ ይቀሩ እንደነበር አስታውሰው፣ የትምህርት ቤቱ መገንባት ትልቅ እፎይታ እንዳስገኛላቸው ገልጸው ለግንባታው ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። በመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃ ግብሩ ላይ የፌደራልና የልዩ ወረዳው አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። #ወቅታዊ_እና_የተሟሉ_መረጃዎችን_ለማግኘት፡- #የቀቤና_ልዩ_ወረዳ_ገቢዎች_ቢሮ_ማህበራዊ_ድረገፆችን_ይቀላቀሉ👇 🌐 Telegram channel https://t.me/kebenearevenujoinch 🌐 YouTube ፔጃችን https://youtube.com/@kebenaspecialworedrevenueoffic?si=DZl-LEhnYaJHxtIL 🌐 ፌስቡክ ፔጃችን https://www.facebook.com/share/19Aj2G9qLd/ 🌐 Instagram https://www.instagram.com/kebenarevenue?igsh=YzljYTk1ODg3Zg== 🌐 የቲክቶክ ገፅ tiktok.com/@kebena.revenue.of 🌐 Email @kebenarevenueoffice100@gmail
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи