tgindex
ማህደረ ጤና☞mahdere tena

ማህደረ ጤና☞mahdere tena

Статистика

♣በዚ ቻናላችን የምናቀርባቸው ጠቅላላ ጤንነት ሰለ ኮሮና በየቀኑ መረጃ እንሰጣለን 💑 ጤና ነክ እውነታዎች🍇🍉2 : 4 ጤናማ አመጋገብ🍔 4 : 6 የጤና በረከቶች🍓 6 : 8 ልጆችና ጤና👪 8 : 10 ተላላፊ በሽታዎች💀10 : 12 እርግዝና እና ልጅ ማሳደግ 12 : 2 ☞ተቀላቀሉን እና ተጠቀሙበት @mahderetena ለጥያቄዎ በአፋጣኝ መልስ ያገኛሉ 👇👇 @mahderetena_bot

Последний пост
6 авг. 2025 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 983
−4 за 4 дн.
Сутки
−2
−0,10%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 466
20 постов
Вовлечённость
73,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • WHY do kids' teeth grow crooked? Several reasons may cause a child's teeth to grow crooked: Foods consumed. During this period, a baby eats mostly soft foods. If the chewing apparatus doesn't get enough exercise to develop, the maxillofacial bones, lower and upper teeth may grow crooked. Genetic factors. Unbalanced nutrition during pregnancy or while breastfeeding. Lack of minerals or other nutrients in the diet. Bad habits. Finger or nipple sucking may also lead to crooked tooth growth.

  • ✍# የኩላሊት# ህመም# ምልክቶች#✍ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 👉👉👉 የኩላሊት ምልክቶች ሕመም አብዛኛውን ጊዜ ምልክት የለሽ ናቸው። እነዚህ የህመም ምልከቶች ከታዩም ደግሞ ከህሙማን ሕሙማን ይለያያሉ። በተለይ የሕመሙ መጀመሪያ አካባቢ መለየት አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጂ አበይት ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው። ⏩የፊት እብጠት ብዙ ጊዜ የፊት፣ የሆድ እና የእግር እብጠት የኩላሊት ህመም መለያ ናቸው። በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋን በታች ሊከሰት ይችላል፡፡ (ይህ የፔሪኦሮቢታል እብጠት ይባላል) በተለይ በማለዳ ጎልቶ ይታያል። ነገር ግን ሁሉም እብጠት የኩላሊት ሕመምን ያመለክታል ማለት አይደለም። በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ ይችላል፡፡ ⏩ የምግብ ፍላጎት ማጣት ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው። ⏩ከፍተኛ የደም ግፊት አብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል። ⏩ደም ማነስ እና ድክመት የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው ቶሎ መድከም፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት ዋንኛ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃ ላይ አነዚህ ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል። ⏩ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች ⏩ መለስተኛ ደረጃ የጀርባ ህመም ⏩ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ⏩የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። 👉👉👉 በልጆች ላይ ደግሞ በሚገባ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የእግር አጥንት ቀጥ አለማለት የህመሙ መኖር ማሳያ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች ⏩1. የሽንት መጠን መቀነስ የኩላሊት ህመሞ በጣም የተለመደ ነው። ⏩ 2. በመሽናት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት እና የሽንት ቧንቧ ህመም በሽታውን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው። ⏩ 3. የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማውጣት ችግር ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሐኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ 👉👉👉 በዶ/ር ሐመልማል ገበየሁ ምንጭ: ቅዱስ ፓውሎስ hospital

  • ✍️ #ከልክ #ያለፈ #ላብ #ያልበኛል #ምክንያቱ #ምን #ይሆን? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን 👉👉 #ላብ ሰዉነታችንን ለማቀዝቀዝ እና ከሰዉነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማስወገድ በተለይም ሞቃት በሆነ የአየር ንብረት እና እንቅስቃሴ ሲደረግ የነርቭ ስርአታእን ወደ ላብ እጢ መልእክት ሲልክ የሚፈጠር ፈሳሽ ነዉ ሆኖም ግን ከሙቀት እና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዉጪ የሰዉነት ላብ ሲበዛ ከልክ ያለፈ ላብ (Hyperhidrosis) ሲባል የጤና ችግሮች እንዳለ ይጠቁመናል፡፡ከልክ ያለፈ ላብ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ በእጅ መዳፍ፤በእግር መዳፍ(የዉስጥ እግር)ና ብብት ዉስጥ ሲሆን እንደ ጤና ችግር የሚቆጠረዉ የእረስዎን የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን የሚያስተጓጉል ከሆነ ነዉ፡፡ከልክ ያለፈ ላብ  የእለት ከዕለት እንቅስቃሴዎትን ከማስተጓጎሉም በተጨማሪ ማህበራዊ ጭንቀትንና እፍረትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ 👉👉 #ከልክ #ያለፈ #ላብ #የሚያስከትሉ #መንስኤዎች 📌 የስኳር ህመም 📌 የወር አበባ መዛባት 📌 ማረጥ 📌 የላብ አመንጪ እጢ ችግር 📌 የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት 📌 በደም ዉስጥ የስኳር መጠን መቀነስ 📌 የካንሰር ህመም 📌 የልብ ህመም 📌 የነርቭ ችግር 📌 የክብደት መጨመር/ከልክ ያለፈ የስብ ክምችት 📌 ከልክ ያለፈ ጭንቀት 📌 ኢንፌክሽን 📌 መድሐኒቶች እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ድባቴ እና የመርሳት ችግር የሚታዘዙ 👉👉 #ሃኪሞትን ማማከር የሚገባዎት መቼ ነዉ? 📌 ላቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን ካስተስጓጎሎት 📌 ያልተለመደ ከበፊቱ የተለየ ብዙ የሚያልቦት ከሆነ 📌 ምክንያቱን ያላወቁት ማታ ማታ ላብ ካለዎት 📌 ይኸንን ችግር ለማሻሻል ከሚረዱ ዘዴዎች ዋነኛዉ የላብን መመረት የሚቀንሱ መድሀኒቶችን መጠቀም ሲሆን ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ከሆነ ደግሞ ላብን ከመጠን በላይ የሚያመርቱትን የላብ ዕጢዎች ወይም ወደ ላብ ዕጢዎች የሚሄዱትን ነርቮች በቀዶጥገና እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል፡፡ 👉👉 #አጠቃላይ ምክሮች 📌 በየቀኑ መታጠብ፡ ይህን ማድረግዎ በሰዉነትዎ ላይ ያሉትን የባክቴሪያ መጠን ይቀንሳል፡፡ 📌 ሻወር ከወሰዱ በኃላ እግሮትን በደንብ ማድረቅ፡ በጣትዎት መካከል በደንብ ማድረቅ፤ፓዉደር መጠቀም ፡፡ 📌 የሚጠቀሙትን ጫማና ካልሲ መምረጥ፡ ጫማዎትንና የጫማዎትን ሶል ከቆዳ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል፡፡ 📌 ጫማዎትን መቀያየር፡ አንድን ጫማ ከሁለት ቀን በላይ ያለማድረግ፡፡ 📌 የሚጠቀሙት ካልሲ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከጥጥ ወይም ከሱፍ የተሰሩ ካልሲዎች እርጥበትን የመምጠጥ ባህሪይ ያላቸዉ ሲሆን እንቅስቃሴ በጣም በሚያበዙበት ወቅት ደግሞ እርጥበትን በደንብ ሊመጡ የሚችሉ የአትሌት ካልሲ የሚባሉትን መጠቀም ይመረጣል፡፡ 📌 እግሮት አየር እንዲያገኝ ማድረግ፡ በሚመቾት ሰዓት እግሮትን ከጫማ ማዉጣትና ማናፈስ፤እቤት ዉስጥ ደግሞ ባዶ እግር ወይም ነጠላ ጫማ ማድረግ፡፡ 📌 ከጥጥ፤ ሱፍ ወይም ናይለን የተሰሩ ልብሶችን ማዘዉተር፡ እነዚህ አየር በደንብ እንዲዘዋወር ያደርጋሉ፡፡ 📌 ቅባት የበዛባቸዉ ምግቦች እና አልኮል ከመዉሰድ መቆጠብ ፡፡ 📌 ለችግሩ መንስኤ የሆኑ የጤና እክሎችን በወቅቱ መታከም ፡፡ ⏩ #ማንኛውም ከጤና ጋር ተያይዞ ጥያቄ ካሎት ወደ ጥሪ ማዕከላችን በመደወል ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ! ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! ✍ 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ። 🔺 በጤና፣ በግንኙነት፣ በስነ-ልቦና እና አመጋገብ ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት 9102 Ok ብለዉ ይጠቀሙ። 🔺 ቅድመ-ጥንቃቄ ልናደርግላቸው የሚገቡ በሽታዎች የትኞቹ ናቸው? ብዙ ሰዎችን ከሚያጠቁ በሽታዎች እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን? 🔺 ክብደታችንን ለመቆጣጠር አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት? 🔺 ከፍቅረኛ፣ ከቤተሰብ እና ከባልደረባ ጋር በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ የግንኙነት ችግሮችን እንዴት መፍታት እንችላለን? በነዚህ ጉዳዮች ዙርያ የሚያውጠነጥኑ አጭር መልእክቶችን #በ9102 ማግኘት ይችላሉ።

  • ✍#ጨጓራ #ህመም #ለምን #በተደጋጋሚ #ይከሰታል?      ** ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ ቤተሰቦች ለዛሬ የጨጓራ ህመም በተደጋጋሚ እንደሚከሰት እንመለከታለን እነሆ፡- ✅  የጨጓራ ህመም፡- የጨጓራ መቆጣት፣ መብገን ወይም ጨጓራ ላይ ያለው ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስን ያጠቃልላል ይህም የሚሆነው የጨጓራ አሲድ በሚበዛበት ወቅተ ነው፡፡ 👉 👉 #መንስኤው 📌 የጨጓራ ባክቴሪያ  📌 የሀሞት ወደ ላይ መመለስ 📌 የጨጓራ አሲድ መብዛት 📌 መድሀኒቶችን አብዝቶ መውሰድ 📌 የአመጋገብ ስርዓት 📌 ጭንቀት 📌 የአልኮል መጠጥ 👉 👉 #ምልክቶችን 📌 ማቅለሽለሽ 📌 በተደጋጋሚ የጨጓራ መቆጣት 📌 የሆድ መነፋት 📌 የሆድ ህመም 📌 ማስመለስ 📌 የምግብ አለመፈጨት 📌 ትንታ 📌 የምግብ ፍላጎት መቀነስ 📌 ደም የቀላቀለ ትውከት 📌 የሰገራ መጥቆር 👉 👉 #ለምን #በተደጋጋሚ #እንታመማለን? 📌 የአመጋገብ ለውጥ ካላደረግን 📌 ውሀ ከምግብ በፊት የማንጠጣ ከሆነ 📌 ምግብ በስርዓት የማንመገብ ከሆነ 📌 ጭንቀት ካለ 📌 አልኮል ተጠቃሚ መሆን 👉 👉 #ምርመራው 📌 ወደ ሆደ በሚገባ ካሜራ(Endoscopy) መመልከት 📌 የደም ምርመራ 📌 የሰገራ ምርመራ 👉 👉 #መፍትሄው መፍትሄው በአጠቃላይ እንደ መንስኤው እና ምልክቱ ይለያያል ስለዚህ 📌 ለጨጓራ አሲድ መብዛት፡-አሲድ እንዲረጋጋ የሚያደርግ መድሀኒት መጠቀም እና የአመጋገብ ለውጥ ማድረግ ይሆናል 📌 ለጨጓራ ባክቴሪያ፡- ሶስት አይነት መድሀኒቶችን መጠቀም እና የአመጋገብ ለውጥ ማድረግ 📌 አልኮል ማቆም 📌 ውሀ ከምግብ 30 ደቀቃ መጠጣት እንዲሁም ከምግብ 30 በኋላ መጠጣት 📌 ጭንቀትን ማስወገድ

  • Online business...who wants to join? https://hzm123.com/#/register/6276749 You want to join talk to me @kalex27

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ለውፍረት የሚያጋልጡ የጥዋት ልማዶች፡ • ከልክ ያለፈ እንቅልፍ • ቁርስን ያለመመገብ • በፋብሪካ የተቀነባበረ ምግብ መብላት • የጠዋት ፀሀይ አለመሞቅ • በቂ ውሀ ያለመጠጣት • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማድረግ 👍👍@eyugn

  • በፋይበር ንጥረ ነገር የበለፀጉ ምግቦች ማዘውተር የሰውነታችንን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች በቀላሉ እንዳንጋለጥ የረዳል፡፡ @eyugn

  • የስሜት መረበሽን ለማስወገድ ፡ • ከቅርብ ወዳጆ ጋር ጊዜ ማሳለፍ • ከአቅም በላይ አለመሥራት • የማያስደስታቹን ነገር ማስወገድ • ከቤት ወጣ ማለት • በቂ እንቅልፍ መተኛት @eyugn

  • 2017 ena 2018/9 group ያላቹ እንገዛለን አናግሩን @kalex27

  • የስልክ ሱሰኝነት መፍትሄ... ሰዎች በቀን ከ80 እሰከ 150 ጊዜ የእጅ ስልኮቻቸውን እንደሚነካኩ ቢያመለክትም ሰዎችይህ ሁኔታ በጎ ልማድ ወይም በጎ ያልሆነ በሚለው ጉዳይ ስምምነት ላይ አልተደረሱም። ስልክ ጤናማ ግንኙነት፣ ጥሩ የስራ አካባቢ እና ተግባቦታቸው የተሻለ እንዲሆን እንዳደረገላቸው ሰዎች ያምናሉ። ስልክን ሰዎች በተደጋጋሚ ሲጠቀሙ ብዙ መልካም ነገሮች ያመጣላቸውን ያህል ችግሮችን እንደሚያስከትል ይነገራል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ሰዎች ለቴክኖሎጂ ጥገኛ በሚሆኑበት ወቅት እውቀት ፣ የትኩረት ደረጃቸው ላይ እና ማህበራዊ ክህሎታቸው ላይ የተለያዩ ችግሮችን ያስከትላል። በመሆኑ በህይወት የዕለት ከዕለት ውሎ ልምድ በመሆን በጎ ያልሆነ ተፅዕኖ እያሳረፈ የሚገኘውን የስልክ ሱሰኝነት እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለውን የሚከተለውን ይመስላል። 1. የስልክ አጠቃቀምን መከታተል ሰዎች በስልክ ሱሰኝነት በሚጠቁበት ወቅት ለዚህ ምክንያት የሆነው መተግበሪያ(አፕልኬሽን) በሌላ መተግበሪያ መቀየር ያስፈልጋለ። ከዚህ ባለፈ “ስፔስ” እና “ሞመንት” የተሰኙ መተግበሪያዎችን በመጠቀም በቀን ውስጥ ያለን የስልክ አጠቃቀም መከታተል እና ለመጠቀም የሚፈልጉት መጠን ማስቀመጥ እንዲቻል ያደርጋል። 2. ስልክን አዘውትሮ መነካካትን ማቆም በስልክ ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎች መተግበሪያዎች ማለትም ፌስቡክ፣ኢንስታግራም ፣ ፒንቴሬስት እና ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተዘጋጁት ሰዎች ሲጠቀማቸው በቀላሉ ማቆም እንዳይችሉ እና ያለገደብ መረጃዎችን ለተጠቀሚዎች እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው። በመሆኑም ሰዎች በዚህ ምክንያት የእጅ ስልካቸውን መነካካት በቀላሉ ማቆም ስለማይችሉ ብዙ ቁም ነገሮች እና ህይወትን መቀየር የሚቻልበትን ጊዜ እንዲባክን ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ እንደዚህ አይነት የስልክ መተግበሪያዎችን በማጥፋት ውድ ጊዜን ከብክነት መከላከል እንደሚቻል መረዳት ያስፈልጋል ተብሏል። 3.አዕምሮን ማዘጋጀት በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚወጡ የማረጋገጫ መልዕክቶች ለምሳሌ ፎቶ እና ሌሎች መራጀዎች በፌስቡክ ላይ ከጫኑ በኋላ የሚመጡት ማሳወቂያዎች ዶፐሚኔ የተባለውን እና በሰውነታችን ደስታን የሚፈጥረውን ኬሚካል እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል። ከዚህም መራቅ እና አዕምሮን መቆጣጠር እንዲቻል ተመስጦን፣ ዮጋ፣ የአካል እንቅስቃሴ እና ሌሎች አዕምሮን ንቁ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ያስፈልጋል። 4.የመተግበሪያዎችን (አፕልኬሽን) ትክክለኛ አካላዊ ውጤቶችን መጠቀም ዘመናዊ ስልኮች የበዙ እና ለቁጥር አታካች የሆኑ አገልግሎቶች ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ይችላሉ። በስልክ ውስጥ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል የሂሳብ ማሽን፣ ካሜራ ፣ ማስታወሻ መፃፊያ፣ መፃህፍት እና ሌሎችንም ይገኙበታል። በመሆኑም መደበኛ መፃህፍትን እና ማስተዋሻዎችን ፣ የሂሳብ ስራን ከስልክ ውጭ ባሉ መሳሪያዎች በመጠቀም እና ከስልክ ጥገኝነት ነፃ በሆነ መልኩ ለመጠቀም መሞከር ያስፈልጋል። 5.ከጎደኛ ድጋፍን ማግኘት በማንኛው ሁኔታና ጊዜ ከሱስ ለመላቀቅ አስፈላጊው ነገር ሰዎች በችግሩ እንደተጋለጡ አምነው መቀበል ይጠበቅባቸዋል። በዙሪያችን ለሚገኙ ሰዎች የስልክ ሱስን ማቆም እንደሚፈልጉ በማሳወቅ የተለያዩ አስተያየቶች ማግኘት ሰዎች ራሳቸውን ከችግሩ ማውጣት እንዲችሉ ይረዳል። 6. አስፈላጊ ያልሆኑ መልዕክት ማሳወቂያዎችን መዝጋት ሲሆን፥ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ ለበርከታ ሰዓት ስልክ እንዲጠቀሙ የሚያደርጉትን ቀለሞች ወደ ነጭ እና ጥቁር መቀየር ያስፈልጋል ተብሏል። Shares @eyugn

  • без подписи

  • 🍎ለክብደት መቀነስ ሚስጥሩ ምንድን ነው🍊🍊 Shares ዛሬ በክብደት መቀነስ ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ስለክብደት መቀነስም ይሁን ክብደትን ለመቀነስ የሚረዱ ዘዴዎችና ፕሪንስፕሎች(መመሪያዎች) ተመሳይ የሆኑ ምክሮች ሲሁኑ እነሱም ጤናማ የምግብ አመጋገብ ዘዴን መከተል፣የሚመገቡትን የምግብ መጠን መወሰንና ተከታታይ የአካል እንቅስቃሴን ማዘዉተር ናቸዉ፡፡ በየጊዜዉ የተወሰነ ክብደት እየቀነሱ ለመቀጠል ከፈለጉ ከዕለት ተዕለት የአኗኗር እንቅስቃሴዎት ዉስጥ ጤናማ ባህሪያትን በማካተት የአኗኗር ዘይቤዎ አካል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ክብደትን ለመቀነስ ከፈለጉ ምንም አይነት ተዓምር መጠበቅ አያስፈልግም፡፡ጤናማu አኗኗሮትን ለማጠናከርና ቀጣይንት ያለዉ ክብደትን ለመቀነስ ካሰቡ የሚከተሉት 20 ምክሮች እነሆ፡- 1. በየቀኑ ከ30 እስከ 60 ደቂቃዎች የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ 2. በቀን ሦስት ጊዜ ጤናማ ምግብ መመገብ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ አንዱን ወይም ሌላዉን መዝለል መራብን ስለሚያመጣ መክሰስን በብዛት እንዲመገቡ ያደርገዎታል፡፡ ስለዚህ ይህን ከማድረግ መቆጠብ 3. አትክልትና ፍራፍሬ ምግቦችን ማዘዉተር 4. በየጊዜዉ የክብደት ክትትል ማድረግ/መለካት 5. በቀላሉ የሚገኙ ጣፋጭ ምግቦችን በቤት ዉስጥ ያለማስቀመጥ 6. ከቤተሰብ ጋር ሊደረጉ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ማከናወን 7. ጤናማ ምግቦችን በመጀመሪያ መመገብ፡- ለምሳሌ ፓስታና ሰላጣ መመገብ ቢገባዎ አስቀድመዉ ሰላጣዉን በመመገብ የመጥገብ ስሜትዎን ያምጡ 8. ለሚመገቡት ምግብ መጠን ትኩረት መስጠት 9. እንቅስቃሴ ሊፈጥሩ ለሚችሉ ነገሮች እድል መፍጠር 10. ከቤተሰብ ጋር አብረዉ መመገብ ጥሩ ነዉ፡፡ነገር ግን ቴሌቪዥን እያዩ መመገብ ምን ያህልና ምን እየተመገቡ እንደሆነ ለመገመት ስለሚያስቸግርዎ ጥንቃቄ ያድረጉ፡፡ 11. እየተመገቡ ያሉትን ምግብ ማወቅ 12. እንቅስቃሴዎትን ማቀያየር 13. ጭንቀትን መቀነስ 14. የቤት ምግብን መመገብ 15. ጤናማ መክሰስ መመገብ 16. ቀኑን ብዙ ፋይበር ባላቸዉ ምግቦች በመመገብ ይጀምሩ 17. በምሳ ሰዓት ለ10 ደቂቃዎች ወክ ማድረግ 18. ለሳምንቱ የሚጠቀሙበትን የምግብ ፕሮግራግራም/መርሃ ግብር አስቀድሞ ማዉጣት 19. ምግብ ሲያምሮት/የምግብ መጓጓት ካለዎት ሀሳብዎትን ለመርሳት በሌላ ነገር መጠመድ 20. እራስን መሸለም/ማበረታታት 🌟Share🌟 🥀@eyugn🥀

  • የወሲብ ፍላጎት ያለመኖር!! በጣም ብዙ ወይም ከፍተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም አነስተኛ ሲሆን አንድ ሰው ስለ ወሲብ ፍላጎት ሳያስብ ሊቀር ይችላል፡፡ ሌሎች የወሲብ ፍላጎት ባይኖራቸውም በሴክስ ግን ይደሰቱበታል፡፡ ችግሩ በጣም ከባድ ሲሆን ደግሞ የወሲብ ፍላጎት አይኖርም፡፡ ሊከሰት ይችላል ብለው ሲያስቡም ይጨነቃሉ፡፡ አንዳንዴ በማስተርቤሽን፣ የወሲባዊ ፋንታሲና በማንኛውም ግንኙነት የወሲብ ገፅታ ላይ ምንም አይነት ፍላጎት አያሳድርም፡፡ አንድ ሰው ያለው አነስተኛ የወሲብ ፍላጎት የቱንም ያህል አነስተኛ ቢሆን እና በየትኛውም ጊዜ ቢከሰትም አንኳን ይህ ሁኔታ ችግር ሊሆን የሚችለው ግለሰቡ ወይም ተጓዳኞቹ እንደ ችገር ሆኖ ሲያገኙት ብቻ ነው፡፡ ምልክቶቹ በየትትኛውም የወሲባዊ እንቅስቃሴ ላይ ፍላጎት አለመኖር፤ የወሲባዊ እንቅስቃሴዎች ማነስ የወሲባዊ እንቅስቃሴ አለመኖር እና ስነልቦናዊ ችግር ሲፈጠር፤ ስለ ወሲብ የደበዘዘ ስሜት መኖር፤ ግለሰቡ በአካል ወሲባዊ እንቅስቃሴ ቢኖረውም ስነልቦናዊ ፍላጎት ግን አይኖረውም፤ የሴት ብልት መድረቅ ሲከሰት፤፤ የብልት አካባቢ ስሜት ሲቀንስ፤ የወሲባዊ እርካታ ላይ ለመድረስ አለመቻል፤ መንስኤዎቹ እድሜ፡- ወንዶችም ሆነ ሴቶች ሲያረጁ በሰውነታቸው ውስጥ በርካታ ለውጦች ይከሰታሉ፡፡ አንዳንዶቹ ለውጦችም የወሲባዊ ፍላጎትን ሊያውኩ ይችላሉ፡፡ ጾታ፡- ምንም እንኳን ወንዶችም ሆነ ሴቶች የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ቢደርስባቸውም በብዛት የሚከሰተው ግን በሴቶች ላይ ነው፡፡ ማረጥ፡- በሴቶች ዘንድ የማረጥ ምልክቶች የፈሳሽ መቀነስ፣ የኤስትሮጂን መጠን መቀነስ ሲሆኑ ይህም ሴቶችን ለወሲብ ሊያነሳሳ የሚችል ነው፡፡ የሆርሞን መጠን፡- የቴስቴስትሮን መጠን ማነስ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ላይ የወሲብ ፍላጎት መቀነስን ያስከትላል፡፡ የማህፀን አካባቢ ችግሮች፡- በርካታ ሁኔታዎች ሴቶች ወሲብ ሲፈፅሙ እንዳይመቻቸው ሊያደርጋቸው ይችላል፣ እነዚህም የማህፀን አካባቢ ችግሮች፣ የብልት መድረቅ፣ አንደሜትርዮሲ፣ የማህፀን እጢ፣ ኦቫርያን ሲስት፣ በኦፕራሲዮን የተነሳ የተከሰተ ጠባሳ ወዘተ ናቸው፡፡ ከመድኃኒት ጋር መለማመድ፡- የድብርት ስሜትን ለማከም የሚያገለግሉ መድኃኒቶች የወሲብ ፍላጎትን ሊያዳክሙ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ የነዚህ መድኃኒቶች በብዛት የጎን ጠንቃቸው የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ነው፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ችግር የሚያስከትሉት ደግሞ አንዳንድ የኬሞቴራፒ መድኃኒቶች፣ ለደም ግፊት ህመም የሚሰጡ መድኃኒቶችና ለአእምሮ ህመም የሚሰጡ መድኃኒቶች ናቸው፡፡ ድብርት፡- በአጠቃላይ ድብርት ሲከሰት በአብዛኛው የደስተኛነት ስሜት መቀነስ የሚከሰት ሲሆን የወሲብ መነቃቃትንና እንቅስቃሴን የመቀነስ አዝማሚያ አለው፡፡ ጭንቀትና ውጥረት፡- በእነዚህ የደስተኛነት ስሜት ቀናሽ ሁኔታዎች የተነሳ የምትሰቃይ ከሆነ የወሲብ ፍላጎትን በጊዜያዊነት ወይም በዘላቂነት ሊቀንሰው የሚችል ሲሆን ይህም ባለው ጭንቀትና የጥፋተኝነት ስሜት ሊወሰን ይችላል፡፡ ስለወሲብ መጥፎ ተሞክሮ ሲኖር፡- የወሲባዊ ፍላጎት መቀነስ የሚከሰተው ወሲብ ሲደረግ ህመም ከተከሰተ፣ በልጅነት ወቅት ጉዳት ያስከተሉ ሁኔታዎች ከነበሩ ወይም ከፍተኛ የወሲብ ፍራቻ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸው ወይም ወሲብን እንደሀጢያት የሚቆጥሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የወሲብ ፍላጎታቸው አነስተኛ ነው፡፡ ከተጓዳኝ ጋር መለማመድ፡- አንድ ሰው ከወሲብ ተጓዳኝ ጋር በጣም ሲለማመድ የወሲብ ፍላጎቱ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ፍላጎትን ለመጨመር በራስ የሚደረጉ ህክምናዎች፡- ለሁሉም የወሲብ ችግሮች መድኃኒት የግድ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ አንዳንዶቹ መንስኤዎች በአንቺና በተጓዳኝሽ አማካኝነት ሊፈቱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ይከስማሉ፡፡ ስለዚህም ትግስትና መግባባት ብቻ ናቸው የሚያስፈልጉት፡፡ . አንዳንድ ጊዜ ከተጓዳኝ ጋር ስለችግሩ ማውራት በቂ ሊሆን ይችላል፡፡ ለተጓዳኞቻቸው ስለወሲባዊ ፍላጎቶቻቸው የሚያወሩ ሴቶች የሚያረካ የወሲብ ህይወት የማግኘት እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ . ወሲብ ከመፈፀምም በፊት ሪላክሴሽን ቴክኒኮችን መጠቀም፡፡ . በብልት መድረቅ የተነሳ የሚመጡ ለወሲብ የመነሳሳት ችግሮችን ለመፍታት ማለስለሻዎችን መጠቀም . ወሲብ የሚደረግበቴን ፕሮግራም መቀየር፡፡ ይህም ቀስቃሽ ማሳጅ፣ አዳዲስ የወሲብ ፖዚሽኖች፣ የወሲብ አነቃቂ ቪድዮዎችን መጠቀም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ መፃህፍትን መጠቀም ሊሆን ይችላል፡፡ የህክምና መፍትሄዎች ህክምናው የሚወሰነው በመንስኤው ላይ ነው፡፡ ችግሩ የተከሰተው አካላዊ በሆነ ሁኔታ የተነሳ ከሆነ ተገቢው ህክምና እንዲደረግ ሀኪም መጠየቅ፡፡ ይህም መድሀኒቶችን፣ የኑሮ ዘይቤ ለውጥን፣ ኦፕራሲዎን ወይም የምክር አገልግሎት ሊሆን ይችላል፡፡ የሚከተሉት ከተከሰቱ በሀኪም ይታይ ቀድሞ ባልነበረ ሁኔታ ወሲባዊ ግንኙነት ህመም ያለበት ይሆናል፡፡ ተገቢውን ትኩረት የሚፈልግ ኢንፌክሽን ወይም ሌላ ህመም ሆናል፡፡ የአባላዘር ህመም ሊደርስበት የሚችል እድል ካለው፡፡ በሴቶች ላይ ለሚከሰት አነስተኛ የወሲብ ፍላጎት መቀነስ ችግሮች የሚከተሉትን ህክምና መከተል ይቻላል፡፡ የብልት ማለስለሻ ለብልት ድርቀት የሚሆኑና ያለ ሀኪም ማዘዣ የሚገዙ ጄሎች፣ ክሬሞች ናቸው፡፡ ኮንደም የምትጠቀሚ ከሆነ ወተር ቤዝድ ማለስለሻዎች ተመራጭ ናቸው፡፡ እንደ ፔትሮሊየም ጀል፣ ሜኔራል ዘይት ወይም ቤቢ ኦይል ኮላቴክስ ኮንደሞች ጋር መስተጋብር በመፍጠር እንዲቀደዱ ደርጋቸዋል፡፡ ቶፒካል ኤስትሮጅን ለአረጡ ሴቶች የሚታዘዝ ሲሆን በተለይም የብልት መድረቅን የሚያክም ነው፡፡ መድሃኒቶች ቪያግራን ሴቶች ፈፅሞ መውሰድ የለባቸውም. Share @eyugn

  • без подписи

  • ☕️☕️በደንብ እንዲነቁ ከፈለጉ ቡና መጠጣት ያለብዎት 4 ሰዓት ለይ ነው፡፡ ቡናን በመጠኑ የሚወዱ ሰዎች በጨጓራ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ጠባብ መሆኑን ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል፡፡☕️☕️ Join us ☕️healthy365days☕️

  • vitamin A,B6,C,E ena calcium,magnesium,iron,potassium,protein ሎሚ በነዚ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው፡፡ ለጤናችን ያለው ጠቀሜታ • ለስርዓተ ምግብ መፈጨት • ትኩሳትን ለማከም • ለጥርስ ጤንነት • ለፀጉር እንክብካቤ • ለቆዳ ጤንነት •ክብደት ለመቀነስ • የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል @eyugn

  • без подписи