የሳይኮሎጂ ምክሮች
описание
🔥ድንቅ አዝናኝና አስተማሪ አባባሎች 🔥የሳይኮሎጂ ምክሮችን ለማግኘት ይቀላቀሉ
4 148
подписчиков
Охват к подписчикам
43,5%
ERR
Реакции к просмотрам
0,81%
347 на 21 постов
Пересылки к просмотрам
0,28%
118
Постов в день
0,1
всего 22
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 2 авг.አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች! ምንጩ ያልታወቀ አንድ ማስታወሻ፡- በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡- “እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ! “ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ! “ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ! “አመኔታ” አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ 1. “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡ 2. “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡ 3. “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ 4. “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡ በሉ እንግዲህ፣ ያለፈው አልፏል፣ የባከነው ባክኗል፡፡ የተራረፈውን እንሰባስበውና ሕይወትን እንደገና በአዲስ መልክ እንጀምር፡፡ ዶ/ር እዮብ ማሞ2,19%
- 27 июл.አንዲት ቀበሮ ቀን ሙሉ ምግብ ስትፈልግ ውላ አመሻሽ ላይ አንድ የወይን ዛፍ ታያለች። ቀደም ሲል የበሰለ ወይን ቀምሳ ጣዕሙን ታውቀዋለች በጣም አስጎመዥት ወደ ዛፉ ተጠግታ ቀና ስትል አንድ የሚያምር የበሰለ የወይን ፍሬ አየች። ሆኖም ዛፍ መውጣት አትችልም። .... ፍሬውን ለማግኘት ዘለለች፤ አልቻለችም። እንደገና በኃይል ዘለለች... አሁንም አልደረሰችበትም። ደግማ፣ ደጋግማ ሞከረች... ፍፁም ልትደርስበት አልቻለችም። በመጨረሻም ተስፋ ቆረጣ "እንድያውም ጥሬ ነሽ!" ብላ ትታ ይባላል። ... ብዙ ሰው የሌለውን ያጣጥላል፤ "ትምህርት ምን ይጠቅማል? ሀብት ምን ፋይዳ አለው? ወይም መፃፍ መቻል ምን ያደርጋል?" እያለ እነሱ ስለሌላቸው እናንተ ስላላችሁ የበታችነታቸውን ለመሸፈን የእናንተን ይዞታ ያቃልላሉ። እንዲህ ሲሆን "የእንዲያውም ጥሬነሽ" ተጠቂ እንደሆኑ ገምቶ ማለፍ ያስፈልጋል። የያዛችሁትን ጠበቅ አድርጉ source ማዕደ ጥበብ Join🌼🌼🌼🌼👇 https://t.me/mrtababl1,76%
- 14 авг.የአንተ ህይወት ዋና ተዋናይ ማነው? ብዙዎቻችን ህይወታችንን እንዲያስተካክልልን፣ ካለንበት ‘ጭንቅ’ ውስጥ እንዲያወጣን ወይም “ተነስ” ብሎ ፍቃድ እንዲሰጠን የምንጠብቀው አካል አለ። ወላጆቻችን፣ የትዳር አጋራችን፣ አልያም ድንገት የሚመጣ “እድል”። ሳይኮሎጂ የሚነግረን ግን እውነታው ሌላ መሆኑን ነው። እውነታው ይህ ነው፦ ማንም መጥቶ ህይወትህን ሊያስተካክልልህ አይችልም። ማንም! ካለህበት ሁኔታ “ነጻ” ሊያወጣህ የሚችል ምልክት ወይም ሰው አትጠብቅ። ያንተን ሁኔታ ሊለውጠው የሚችለው አንተ ራስህ ብቻ ነህ። ዛሬ የምናደንቃቸው እና የደረሱበት ቦታ የደረሱ ሰዎች “ሁሉ ነገሬ ተሟልቷል፣ ዝግጁ ነኝ” ብለው አልጀመሩም። እንዴት ጀመሩ መሰለህ? እየፈሩ፣ እርግጠኛ ሳይሆኑ፣ ባዶ እጃቸውን እያሉ፣ እና በራሳቸው እየተጠራጠሩም ቢሆን ያኔ ባላቸው አቅም መጓዝ ጀመሩ። ዛሬ አንተም መወሰን አለብህ፦ ዝግጁ እስክትሆን መጠበቅ ትፈልጋለህ ወይስ በጥርጣሬ ውስጥ ሆነህ እርምጃ መውሰድ? ምርጫው ያንተው ነው! Source psych addis1,69%
- 7 авг.без подписи1,52%
- 17 июл.የዛሬ ቀኑ ደስ ይላል።❤️ መልካም ቀን ይሁንላችሁ።1,48%
- 23 июл.“አንድ ብርጭቆ ውኃ ሰጥቼህ፣ በውስጡ መርዝ ብጨምርበት፣ ከዚያም ስኳር ባዋህድበት... ስኳሩ የመርዙን ኃይል አያስወግደውም። ሊያጣፍጠው ይችላል፣ ነገር ግን አሁንም መርዛማ ነው። ሰዎች ስለ ስነ-ልቦናዊ ስብራት (trauma) የሚሳሳቱት ልክ እንደዚሁ ነው። በሕይወትህ ላይ መልካም ነገሮችን ልትጨምር ትችላለህ፤ አዳዲስ ሰዎችን፣ ስኬትን፣ በራስ መተማመንን፣ ገንዘብን፣ ውበትን ወይም አዳዲስ ልማዶችን... ነገር ግን ከእነዚህ መካከል አንዳቸውም በራሳቸው ጊዜ ያልዳነውን ቁስል አያስወግዱትም። እግርህ ከተሰበረ፣ የፈለገውን ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብታደርግ እግርህን ሊያድነው አይችልም። አእምሮም በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚሰራው። አንዳንድ ጊዜ ህመሙ በየቀኑ አይሰማህም፤ ስለዚህ የጠፋ ይመስለናል። ነገር ግን አልጠፋም፤ ዝም ብሎ ተኝቷል ብቻ። ከዚያም አንድ መጥፎ ተሞክሮ፣ አንድ ዝምታ፣ አንድ አለመቀበል (rejection) ወይም አንድ የሚታወቅ ስሜት... መልሶ ይቀሰቅሰዋል። ስነ-ልቦና ይህንን triggers ብሎ ይጠራዋል። ይህ አንተ ዝም ብለህ ነገሮችን የምታጋንን ሰው ስለሆንክ አይደለም፤ ይልቁንም ትኩረት የሚሹ አሮጌ ቁስሎች ናቸው። ስለዚህ መፈወስ ማለት መርዝ ላይ ስኳር መጨመር አይደለም፤ መፈወስ ማለት ከመጀመሪያውም ህመምተኛ ያደረገህን ነገር ማስወገድ ነው።” የጠቢባን መንገድ https://t.me/mrtababl https://t.me/mrtababl1,44%
- 20 июл.አዕምሮህ ጋሻ ወይስ የገሃዱ ዓለም እንቅፋት? ሳይንቲስቶች በአንድ ወቅት አንድ አስደናቂ ሙከራ አድርገው ነበር። በአንድ ትልቅ የዓሣ ማርቢያ ገንዳ ውስጥ በመካከል ላይ ግልጽ የሆነ የብርጭቆ መክፈያ ግድግዳ አደረጉ። በአንዱ በኩል የተራበ እና ኃይለኛ አዳኝ የሆነ “ፓይክ” (pike) የተባለ ዓሣ፣ በሌላኛው በኩል ደግሞ ትናንሽ ዓሳዎችን አስቀመጡ። ፓይኩ ታዳኝ አሳዎቹን ባየ ቅጽበት በከፍተኛ ፍጥነት ይወረወራል፤ ነገር ግን በቀጥታ የማይታየው የብርጭቆ ግድግዳ ላይ ይጋጫል። ደጋግሞ ይሞክራል፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ጥቃት በተመሳሳይ ውድቀት ይጠናቀቃል። ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ፣ አካሉ የዛለውና የደከመው ፓይክ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጦ ወደ አንዱ ጥግ ያፈገፍጋል። በመቀጠል ሳይንቲስቶቹ ያንን የብርጭቆ መክፈያ ግድግዳ በቀስታ ያነሱታል። አሁን ትናንሾቹ ዓሳዎች በፓይኩ ፊት ለፊት በነጻነት ይዋኛሉ፤ እሱ ግን ዳግመኛ ሊያ'ድናቸው አልሞከረም። በጣም እየተራበ ቢሆንም እንኳን ምግቡን ችላ ብሎ ተኛ። ምክንያቱም እውነተኛው ጋሻ ወይም ከለላ ከእንግዲህ ብርጭቆው አልነበረም፤ በአዕምሮው ውስጥ የታሰረው “አልችልም” የሚለው እምነቱ እንጂ! ከቀናት በኋላ፣ ያ ፓይክ በምግብ ተከቦ እያለ በረሃብ ሞተ። የአዕምሮ እንቅፋት (Mental Barrier) ኃይል እንግዲህ ይህ ነው! ብዙዎቻችን ዛሬ የምንኖረው ልክ እንደዚህ ዓሣ ነው። ትናንት የገጠመን አንድ ውድቀት ወይም ያጣነው እድል፣ ዛሬም ስኬት የማይቻል መሆኑን ያሳምነናል። ነገር ግን ልብ በል፦ ትናንት የከለከለህ መሰናክል ዛሬ ላይኖር ይችላል! የከበበህ ብርጭቆ ተነስቷል። ነገሮች ተቀይረዋል፤ አንተም ተቀይረሃል። ስለዚህ እጅ ከመስጠትህ በፊት አንድ ጊዜ ደግመህ ሞክር! የሚቀጥለው ሙከራህ ሁሉንም ነገር የሚቀይር፣ ታሪክህን የሚያድስ ሊሆን ይችላል። Source psych addis https://t.me/mrtababl1,35%
- 19 июл.በክፍል ውስጥ ተማሪዎች በዘር፣ በቡድን እየተከፋፈሉ መምህሩን አስቸገሩት። መምህሩም ለተማሪዎቹ አንድ ተግባራዊ ትምህርት ለመስጠት "ይቅር የማትሉትን እያንዳንዱን ሰው እያሰባችሁ በየስሙ አንድ አንድ ቲማቲም በከረጢት ውስጥ ክተቱ" አላቸው። ተማሪዎቹም እንደተባሉት አደረጉ። ... መምህሩ በመቀጠል "ይህንን ከረጢት ለሰባት ቀናት በሄዳችሁበት ሁሉ ሳትለዩ ተሸከማችሁ ዙሩ።" አላቸው። ተማሪዎች የተባሉትን ሲያደርጉ ቀናት እያለፉ ሲሄዱ ተማቲሙ መበስበስ በመጀመሩ ሽታው ሰላም ነሳቸው፤ ይባስ ብለው ግማሾች መቋቋም ተስኗቸው ለመጣል ተገደዱ። ሳምንቱ ሲያልቅ ተማሪዎቹ እየተማረሩ ከረጢቱን ይዘው ተመለሱ። ... መምህሩም "በውስጣችሁ ቂምና ጥላቻን ስታቆዩ በልባችሁ ላይ የሚፈጠረው ነገር ልክ እንደዚሁ ነው። ሰዎችን ይቅር አንልም ስንል፣ የጥላቻውን ሸክምና ግማት የምንሸከመው እኛው ራሳችን ነን።" አላቸው። ... ይቅርታ ማድረግ ሌላውን ሰው መጥቀም ብቻ ሳይሆን፣ ራስን ካልተፈለገ የቂምና የጥላቻ ከባድ ሸክም ነፃ ማውጣት ነው። ልባችን የፍቅር እንጂ የበሰበሰ ድንች ማከማቻ መሆን የለበትም። Source ማዕደ ጥበብ1,29%
- 8 авг.በሥነ-ልቦናው ዓለም ከሚያስገርሙኝ ኀልዮቶች (Theories) መካከል በሥነ-ሰብዕ ዕድገት ላይ በስፋት የሚታወቀው ጂያን ፒያዤ Cognitive Development theory አንዱ ነው። በዚህ ንድፈ-ሐሳብ እና የጥናት ውጤት መሠረትም ሕፃናት ወደዚህች ዓለም ከመጡ በኃላ ዓለምን፣ ተፈጥሮን (Physical World) የሚረዱበትን፣ እያወቁ የሚመጡበትን መንገድን ዘርዝሯል። ሕፃናት በለጋነታቸው ምንም ነገር እንደ ስፖንጅ እውቀትን እያዳበሩ አይመጡም፤ ይልቁንስ ሲድሁ፣ ሲነካኩ፣ እሳት ሲፈጃቸው፣ ያንንም-ይሄንንም ሲቀምሱ፣ በሁሉም የስሜት ሕዋሶቻቸው መረጃ ሲቃርሙ ዓለምን የበለጠ እየተረዷት ይመጣሉ። የፅንሰ-ሐሳቡ ባለቤት ፒያዤ ይህ የዕድገት ምዕራፍ እስከ 6 - 8 ዓመት ድረስ ይዘልቃል ይለናል። የዕድገት ምዕራፎች/ደረጃዎች በሕፃናት 1. በስሜት ሕዋሶች በኩል ዓለምን መተዋወቅ (The Sensorimotor stage)፡ በዚህ የዕድገት ምዕራፍ ከውልደት እስከ 2 ዓመት ያለውን ያካትታል። ዓለምን በስሜት ሕዋሶቻቸው በኩል ያገኟታል። መንቀሳቀሳቸው ደግሞ ዋነኛው የመረዳታቸው Pillar ነው። ◦ለድንገቴ ተግባራት አረዳዳቸው እያደገ መሄድ ( Reflexes to intentional Actions) ◦በመሞከርና በመሳሳት መማር (Trial and Error Exploration) ልጆች በዚህ ጊዜ ከተለያዩ ዕቃዎች ጋር እየበጠሱ፣ እየሰበሩ፣ እየጣሉ፣ እየገነጠሉ የሚማሩበት ጊዜ ነው። ◦ አንድ ዕቃ ከነበረበት ቦታ ከዓይናቸው ቢሰወርም እንኳን ዕቃው መኖሩን መረዳት ወይም እዛው ነው የሚገኘው ብሎ ማሰብ (Object permanence) ◦ በአዕምሯቸው የተለያዩ ነገሮችን መሳል የሌለን ነገርንም ቢሆን ለምሳሌ፦ ስልክ ሲይዙ እናታቸውን እየወሩ ሲመስላቸው (Mental Representation) 2. The PreOperational Stage ከ2-7 ዓመት ክልል ውስጥ ለሚገኙ ልጆች ሲኾን ቋንቋን በምልክቶችና ከግዑዝ አካላት ጋር በማያያዝ ወይም በመወከል እየተረዱ ይመጣሉ፤ ምንም እንኳ ያልበሰለ ቢሆንም Abruptly ፩ | ' Symbolic Function ' ሁሉን ነገር በSymbol መወከል፣ መግለፅ ወይም በዐይን የማይታዩ በአካል ያላዩትን በሌላ ዕቃ አስመስሎ መግለፅ። ለምሳሌ፦ በመኪና ፋንታ በማንኛውም ካርቶን ቭቭቭቭቭ.. እያደረጉ በእጅ መንዳት፣ በጎራዴ ቦታ በትንሽ እንጨት መጫወት ወ.ዘ.ተ. ፪ | ' Egocentrism ' ልጆች የሌሎች ሰዎችን ዕይታ/ንቃት (point of view) መረዳት ሲቸገሩ ለምሳሌ፦ የተደበቁ መስሏቸው ወይም አያዩኝም ብለው ፊትለፊት ከሚገኝ ሰው ጀርባ መደበቅ፣ ተደብቄያለሁ ብሎ በማሰብ ፊትን በእጅ መሸፈን.. ፫ | ' Animism ' ልጆች ሕይወት የሌላቸው ነገሮችን ማለትም ዕቃዎች፣ ቁሳቁሶች እና ማንኛውም ነገሮችን ሕይወት እንዳላቸው፣ እንደ ሰው ስሜት እንዳላቸው አድርጎ ማሰብ። ለምሳሌ፦ ፀሐይ እየተከተለቻቸው ሲመስላቸው፣ ደመናው እየተከተላቸው ሲመስላቸው፣ ያደናቀፋቸው ዕቃ እንዲቀጣ በመፈለግ ሲመታ (ቱ.. በል ይኸው መታሁልህ ) ሲባሉ የእውነት ሲመስላቸው ወ.ዘ.ተ. ፬ | ' Centration ' ልጆች ትኩረት የሚሠጡት ትኩረት-ለሳባቸው ሲሆን ለምሳሌ፦ በሁለት ብርጭቆ ላይ ተመሣሣይ መጠን ያላቸው ውሃ ቀድተን ብናስቀምጥ አንዱ ብርጭቆ ቁመቱ ረዘም ያለ እና ጠባብ ሌላኛው አጭርና ሰፊ ቢሆን ልጆች ግን ብዙ ውሃ ያለው ረዥሙ ላይ ነው ብለው ማሰብ.. ፭ | Lack of conservation ስለመጠን እና ብዛት አለመረዳት Source ዋኖስ መስፍን |1,07%
- 14 июл.без подписи1,01%
- 5 авг.ኤአይ (AI)ን እንዴት እንጠቀም ? ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለረጅም ጊዜ እና ያለገደብ መጠቀም የሰዎችን የፈጠራ ብቃት እና ነገሮችን በጥልቀት የመመርመና የማሰብ ክህሎትን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በቅርቡ የወጡ ተከታታይ ጥናቶች አመልክተዋል። በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች መረጃዎችን እና ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በኤአይ (AI) ላይ ጥገኞች ሆነው ማከናወን ሲጀምሩ " ኮግኒቲቭ ሰረንደር " ወይም የአእምሮን የማሰብ ስራ ለቴክኖሎጂ አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ይህም አእምሮ በራሱ ጥረት መረጃዎችን የማቀናበር፣ የመተንተን እና አዳዲስ ሀሳቦችን የማመንጨት የተፈጥሮ ብቃቱ እንዲደክም ያደርገዋል። በተለይ #ወጣቶች እና #ተማሪዎች ለተወሳሰቡ ጥያቄዎች እና ስራዎች ፈጣን ምላሽ ከኤአይ ማግኘት መልመዳቸው የራሳቸውን የአእምሮ አቅም የመጠቀም ተነሳሽነታቸውን እንደሚቀንሰው ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን ቴክኖሎጂውን እየተጠቀሙ አእምሮን ሁል ጊዜ ንቁ፣ ብቁ እና ጤናማ አድርጎ ለማቆየት የሚረዱ በርካታ ሳይንሳዊ መንገዶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። የአእምሮን የአስተሳሰብ ብቃት ላለማጣት ምን አይነት ልምዶች ማዳበር ይቻላል ? - ከኤአይ (AI) የተገኙ ምላሾችን ወይም መረጃዎችን በቀጥታ ወስዶ ከመገልበጥ ይልቅ " ይህ መረጃ ትክክል ነው ? ምን ጎደለው ? አመክንዮአዊ ነው ? " በማለት በራስ አእምሮ መርምሮ፣ መዝኖ መጠቀም። - ማንኛውንም ስራ፣ ጽሑፍ ወይም ፕሮጀክት ከመጀመርዎ በፊት መነሻ ሀሳቦችን እና እቅዶችን በራስ አእምሮ ማመንጨት እና ማስታወሻ መያዝ። ኤአይ ስራውን ለማስጀመር ሳይሆን የተጀመረውን ስራ ለማደራጀት ወይም ለመፈተሽ ብቻ መጠቀም። - የፈጠራ እና የጥልቅ አስተሳሰብን የሚያነቃቁ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስልታዊ ጨዋታዎችን መጫወት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ ለመማር መሞከር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች/ስራዎችን ለኤአይ ሰጥቶ ያለ ምንም ምርመራ፣ ማስተካከያና ደጋግሞ የማንበብ ጥረት በቀጥታ #በመገልበጥ አንዳንዴም እንደራስ ስራ ማስመሰል እየተለመደ መጥቷል። ይህ በጥልቀት ሳያስቡና ሳይመራመሩ በቴክኖሎጂ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን አእምሮን የማሰብ ስራውን እንዲተው በማድረግ፣ እውነታን የመተንተን እና የጥልቅ አስተሳሰብ ብቃትን በከፍተኛ ደረጃ እየገደለው ይገኛል ፤ ሰዎች ትንሽ ስራ እንኳን ለመስራት የማይፈልጉ ስልቹና ሰነፍ እያደረጋቸውም ነው። ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ኤአይ (AI) የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን እንደ ረዳት መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው ነው። ጥቅም የሚኖረውም የሰው ልጅ የራሱን የአስተሳሰብ ልዕልና ጠብቆ ሲቀጥል ብቻ ነው Source (TIKVAH) Join for more https://t.me/mrtababl0,75%
- 11 июл.ጠዋት ከእንቅልፍ ስንነቃ ቀኑን ለማስታወስ ጊዜ የሚወስደው ለምንድነው? ከጠዋት እንቅልፍ ስትነሱ ዛሬ ምን ቀን (ሰኞ፣ ማክሰኞ...) እንደሆነ ወዲያውኑ ሳይሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላ መገንዘብ ብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ነገር ሲሆን እርሱ ብቻውን የስነ ልቦና ወይም የነርቭ በሽታ ምልክት አይሆንም። ከኒውሮሳይንስ አንፃር፦ ይህን ሁኔታ Sleep Inertia (የእንቅልፍ መነሻ ድብደባ) ብለው ይጠሩታል። ከእንቅልፍ ሲነሱ አንጎል በተለይ የፊት አንጎል (prefrontal cortex) ሙሉ በሙሉ ለመንቃት ጥቂት ደቂቃዎች ይፈልጋል። በዚህ ጊዜ ጊዜን፣ ቦታን እና ቀንን የመለየት ችሎታ ለጥቂት ጊዜ ሊዘገይ ይችላል። ከስነ ልቦና አንፃር፦ ይህ ጊዜያዊ የአቅጣጫ መዘግየት (temporary disorientation) ሊሆን ይችላል። የእንቅልፍ እጥረት፣ የስራ ጫና፣ ጭንቀት፣ ወይም ቀኖች ተመሳሳይ ሆነው መቆየታቸው (ለምሳሌ ረጅም ዕረፍት) ይህን ሊያበረክቱ ይችላሉ። መቼ ያሳስባል? ከሚከተሉት ጋር ካብረከተ የሕክምና ግምገማ ማድረግ ይመከራል፦ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ግራ መጋባት (ከ30–60 ደቂቃ በላይ)፣ የማስታወስ ችግር እየባሰ መሄድ፣ ቦታ ወይም ሰዎችን አለማወቅ፣ የንግግር ችግር፣ የእጅ/እግር ድክመት፣ ወይም ሌሎች የነርቭ ምልክቶች ካሉ። https://t.me/mrtababl0,67%