ናሁ ሰማን(Nahu seman)
Статистикаበስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers የንግስ ዝማሬ ማግኝት ከፈለጉ የyoutube አካውንታንት ይቀላቀሉ። https://youtube.com/@nahu-seman-zema25?s በማድረግ ይጎብኙ።
- Последний пост
- 8 мая
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 38
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ልደታ ለማርያም በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት
без подписи
без подписи
በአንድ ወቅት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ቆሞ ጌታየ ሆይ! አንተ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? ምንስ ባደርግልህ ደስ ትሰኛለህ?...እስቲ ንገረኝ ረጅምና በቁመቴ ልክ የሆነ ከሰም የተሰራ ሻማ እንዳመጣልህ ትፈልጋለህ? አለው። ጌታም መልሶ "ለሻማው መስሪያ የሚሆነው ሰሙም የእኔ ነው፤ ሰሙ የሚገኝበት የማር እንጀራውም የእኔ እኮ ነው"አለው። ሰውየውም መልሶ "ይሁን እንግዲህ ወይ ለሰንበት ቅዳሴ የሚሆን ለሥጋ ወደሙ የሚሆን መገበሪያ ይዤልህ እመጣለሁ አለ። ጌታችንም መልሶ "የሥጋ ወደሙ የሚዘጋጅበት ስንዴም ቢሆን የእኔ እኮ ነው" አለው። ያም ሰው ቀጥሎ "እንግዲውስ ድሆችን ለመርዳት ይሆን ዘንድ 1000,000 ብር እሰጥሃለሁ አለው። ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ " አንተ አለኝ ያልካቸው ነገሮች ሁሉ የእኔ ናቸው፤ ምድርና መላዋ ለእግዚአብሔር ናት ፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ። መዝ.24:1) አለው። ሰውየውም እንዲህ አለ " ጌታዬ ሆይ እሺ ምን እንዳመጣልህ ነው የምትፈልገው? ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ፣ ስለአንተ ብየ ተጠምቻለሁ ፣ ስለአንተ ፍቅር መስቀል ላይ ወጥቻለሁ አለው። እግዚአብሔር ካለን ነገር በፊት እኛን ይፈልገናል። ራሳችንን ሳንሠጠው ብንደክም ብንለፋ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው" (ሉቃ. 10:42) ይለናል ይህም ልባችንን ለእርሱ በቃሉ ለመኖር መሥጠት ነው። እውቀታችንን ሠጥተን ፣ ገንዘባችንን ሠጥተን ፣ ጉልበታችንን ሠጥተን እኛ የእርሱ ካልሆንን ምን ይጠቅማል? ኃጢአት ከእርሱ ለይታናለችና ፣ በንስሐ ልባችንን እንዲንሠጠው በመንፈሳዊ ምሥጢራት ከእርሱ ጋር አንድን እንድንሆን ይሻል። ራሳችንን በንስሐ አቅርበን ልባችንን ለፈጠረን አምላክ እንስጠው። ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
እርቃን_ገላዎች አንብቡት #ሼር ሁለት ወጣት ሴቶች ግማሽ አካላታቸውን ብቻ የሚሸፍን ልብስ ለብሰው ስብሰባ ቦታ ደረሱ ። የስብሰባው መሪ በጥሩ ፈገግታ ተመለከታቸውና እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ። ከዚያም እነዚህ ሴቶች በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሊረሱት የማይችሉትን መልዕክት ተናገራቸው ። ትኩር ብሎ አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው ፣ "ሴቶች ፈጣሪ የፈጠራቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ በሚገባ የተሸፈኑና እንዲሁም ለማየትና ለማግኘት ብዙ ጥረት የሚጠይቁ ናቸው ። ፩ አልማዞችን የት ነው የምታገኙአቸው ? ከመሬት በታች ከብዙ ጥልቀት በኋላ ተሸፍነውና ተደብቀው ። ፪ ወርቆችን የት ነው የምታገኟቸው ? ከማዕድናቶች በታች በትላልቅ ድንጋዮች ተሸፍነው ነው ። እነሱን ለማግኘት ወደታች ብዙ ርቀት ጠንክራችሁ መቆፈር ፣ መስራትና መፈለግ አለባችሁ ከዚያም ፊታቸውን ትኩር ብሎ እያየ ንግግሩን ቀጠለ ። "የእናንተ ሰውነት አስፈሪና ልዩ ነው ። የእናንተ ሰውነት ከአልማዝ ፣ ከወርቅና ከሌሎች የበለጠ ውድና ማራኪ ነው ። ስለዚህ እናንተም በሚገባ ልትሸፈኑ ይገባል ። ንግግሩን ቀጠለ ፣ ይህንን ውድ ሃብታችሁን ልክ እንደ አልማዝና ወርቅ በሚገባ ከሸፈናችሁና በቀላሉ እንዳይገኝ ካደረጋችሁ ታማኞችና አስፈላጊውን የማዕድን ማውጫ መሳሪያዎች ያላቸው ማዕድን አውጪ ድርጅቶች እናንተን ለማግኘትና ለዘመናት የማዕድን ማውጣት ስራቸውን ለመስራት ወደ እናንተ ይጎርፋሉ ። በመጀመሪያ ከሃገራችሁ መንግስት( ቤተሰባችሁ) ጋር ይገናኛሉ ፣ ፕሮፌሽናልና ህጋዊ ፊርማ (ህጋዊ ጋብቻ) ይፈራረማሉ ። ነገር ግን የህንን ውድና ማራኪ ሃብታችሁን በሚገባ ባትሸፍኑትና ባትጠብቁት ሁልጊዜ ህገወጥ ማዕድን አውጪዎች ወደ እናንተ እንዲመጡና ውድ ማዕድናችሁን በህገወጥ መንገድ እንዲያወጡት ትማርካላችሁ ። ከዚያም ምንም ሳይጥሩና ሳይደክሙ በቀላሉ ውድ ሃብታችሁን ይወስዳሉ ማለት ነው ። ስለዚህ ሴቶች እባካችሁ ሰውነታችሁን በሚገባ ሸፍኑ ። ይህን ካደረጋችሁ ፕሮፌሽናሎችና ህጋዊ ማዕድን አውጪዎች እናንተን ያሳድዳሉ ።" እህታቹሁ ፍቅርተ ኢየሱስ እስቲ ሁላችንም ወንዶች እህቶቻቹሁ፤ሚስቶቻችንን ፣ ጓደኞቻችንንና ልጆቻችንን እንድሸፍኑ አስተምራቸው ። የቅዱሳን አምላክ ማስተዋልን ይስጠን🙏 ሰናይ ቀን ተቀላቀሉ ቴሌግራም👇 "...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው" --2ኛ ቆሮ 6፥2
без подписи
ምን ላድርግ..❓ " የዝሙት አሳብ እኔ ሳልፈልገው ይመጣብኛል ከዛም ወደሱ እሳባለሁ.. ምናልባትም ከሃሳብም ዘልዬ የሆኑ ነገሮችን አደርጋለሁ.. ልክ ሲያልፍ መጸጸት እጀምራለሁ.. ምን ላድርግ❓" 1. ሚስት ከሌለህ በጭራሽ ስለ ግንኙነት አታስብ 2. የምታየውን ነገር በጣም ምረጥ.. ፊልም የምታይ ከሆነ ፊልሙ ወደ እንደዚህ አይነት ሙድ ውስጥ የሚከት ነገር በፍጹም ሊኖረው አይገባም.. ትንሽ እንኳን ካለው በቃ አእምሮህ ላይ ተቀምጦ ለወደፊትህም ሌላ ፈተና ይሆንብሃል.. ስለዛ ገና ከጅምሩ አሳቦቹ እንዳይመጡ ተከላከል 3. አንተ ባትፈልገውም አዎ አሳቡ ሊመጣ ይችላል ግን ደግሞ ለዛ አሳብ ተባባሪ አትሁን.. አልወድቅም ብለህ በማሰብ ወይም ማሰቡ ብቻ ችግር የለውም ብለህ ተዘናግተህ በአሳብ ወደዛ አትወሰድ.. ይልቁንም ገና አሳቡ ሲመጣ ራስህን በሌላ ነገር ቢዚ አድርግ.. 4. ፈተናው በጣም የከበደ ሲመስልህ የጌታን የስቅለት ስእል እያየህ እንዲህ ብለህ ተናገር፡ "አዎ ፈተናው ብርቱ ነው.. አንተ ግን ከፈተናዎችም ሁሉ በላይ የበረታህ ነህ" ስለዚህም የመስቀሉን ኃይል ትታጠቃለህ 5. ጦርነት ሜዳ ውስጥ ነህና ሁሌም ክርስቶስ በአንተ ኖሮ እንዲዋጋልህ ፍቀድለት.. እርሱ በአንተ ይኖር ዘንድ ንስሐ እየገባህ ከቅዱስ ምስጢር(ቁርባን) ደጋግመህ ተሳተፍ.. ሁሌም አጫጭርም ቢሆን ጸሎት አድርግ.. እና ደግሞ ብቻችሁን አትሁኑ ከሰው ጋር መቀላቀል ያስፈልጋል "...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው" --2ኛ ቆሮ 6፥2
#ሚያዝያ_8 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ስምንት በዚህች ዕለት የከበሩ ሦስት ሴቶች #ቅዱሳት_አጋሊስ_ኤራኒና_ሱስንያ በሰማዕትነት አረፉ፣ መቶ ሃምሳ ሰዎች በፋርስ ንጉሥ እጅ በአንዲት ቀን በሰማዕትነት አረፉ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳት_አጋሊስ_ኤራኒና_ሱስንያ ሚያዝያ ስምንት በዚህች ዕለት የከበሩ ሦስት ሴቶች በሰማዕትነት አረፉ። የእሊህም ስማቸው አጋሊስ ኤራኒና ሱስንያ ነው። ከተሰሎንቄ ሀገርም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያመልኩ ናቸው። ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ ነበሩ። እሊህም ደናግል በድንግልና በንጽሕና መኖርን ወደው በአንድ ምክር ተስማሙ ጽኑዕ በሆነ ገድልም ተጠመዱ ይልቁንም ያለማቋረጥ ተግተው ይጸልዩና ይጾሙ ነበር። ወደ ገዳሙም ተመልሰው ከመነኰሳቱ ጋራ ያገለግላሉ። ከሀዲ መክስምያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖታትን አምልኮ አቁሞ የንጹሆችን ደም አፈሰሰ። እሊህም ደናግል በአዩ ጊዜ ፈርተው ወደ ተራራ ሸሹ በዚያም በዋሻ ውስጥ ተሸሸጉ በጾምና በጸሎት በመጸመድ ሳይወጡ በዋሻው ውስጥ ኖሩ። አንዲት የክርስቲያን ወገን አሮጊት በየሰባት ቀን ትጐበኛቸውም ነበር የሚአሻቸውንም ትሰጣቸዋለች የእጅ ሥራቸውን ትሸጥላቸውና ከእነርሱ የሚተርፈውን ትመጸውታለች። አንድ ሰውም ከከተማ ወጥታ ወደ ተራራ ሁልጊዜ ስትሔድ አያት ሳታየውም ተሠውሮ በሩቅ ተከተላት ወደ ዋሻውም እስከምትገባ ተመለከተ ከዚያ እስከምትወጣም ተሠውሮ ቆየ በዚያ ቦታ ብዙ ገንዘብ ያላት መስሎታልና። ያቺ አሮጊትም ከዋሻው በራቀች ጊዜ ያ ሰው ገባ ለክብር ባለቤት ሙሽሮቹ የሆኑ የከበሩ አዕናቍ ደናግልን ቁመው ሲጸልዩ አገኛቸው ተሰሎንቄ ከተማ እስኪያደርሳቸውም አሥሮ ጐተታቸው። መኰንኑም ሃይማኖታቸውን በጠየቃቸው ጊዜ ስለ እሳቸው የተሰቀለ የክብር ባለቤት ክርስቶስን የሚያመልኩ ክርስቲያኖች እንደሆኑ በፊቱ አመኑ። መኰንኑም ተቆጥቶ ይገርፉአቸው ዘንድ አዘዘ የሚአሠቃይ ጽኑ ግርፋትም ገረፉአቸው ባልተሰዘዙና ወደ ክህደቱ ባልገቡ ጊዜ ወደ እሳት እንዲጨምሩአቸው አዘዘ። በእሳትም ውስጥ በጣሉአቸው ጊዜ ነፍሳቸውን አሳለፉ በመንግሥተ ሰማያትም የሕይወትን አክሊል ተቀዳጁ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #የፋርስ_ሰማእታት በዚህችም ቀን መቶ ሃምሳ ሰዎች በፋርስ ንጉሥ እጅ በአንዲት ቀን በሰማዕትነት አረፉ። እርሱም ለሀገሩ ቅርብ የሆነ የክርስቲያንን አገር ከበበና ብዙ የሰው ምርኮ ማርኮ ወደ አገሩ ወሰዳቸው ፀሐይን ጨረቃንና ከዋክብትንም ያመልኩ ዘንድ አስገደዳቸው አይሆንም ባሉትም ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡአቸው ዘንድ አዘዘ። ራሶቻቸውንም ቆረጡአቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሕይወትን አክሊል ተቀበሉ፡፡ =>ሚያዝያ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ: ኢራኒና ሱስንያ 2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (ፋርስ (ኢራን) ውስጥ የተሰየፉ) 3.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት 2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ) 3.አባ ብሶይ (ቢሾይ) 4.አቡነ ኪሮስ 5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን 6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡ (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ)
без подписи
የእመቤታችን ድንግል ማርያም የወላጆቿ መቃብር።
#ሚያዝያ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም #ቅዱስ_ኢያቄም ሚያዝያ ሰባት በዚች ቀን የእመቤታችን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም አባትዋ ጽድቅ ኢያቄም አረፈ። ይህም ጻድቅ በሦስት ስሞች ይጠራል እንርሱም ኢያቄም ዮናኪር ሳዶቅ ናቸው እርሱም ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ዘር ነው። ይህም የአልዓዛር የኤልዩድ ልጅ ኢያቄም በትውልድ ሐረግ እስከ ሰሎሞንና እስከ ንጉሥ ዳዊት…
#ሚያዝያ_7 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም #ቅዱስ_ኢያቄም ሚያዝያ ሰባት በዚች ቀን የእመቤታችን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም አባትዋ ጽድቅ ኢያቄም አረፈ። ይህም ጻድቅ በሦስት ስሞች ይጠራል እንርሱም ኢያቄም ዮናኪር ሳዶቅ ናቸው እርሱም ከይሁዳ ነገድ ከዳዊት ዘር ነው። ይህም የአልዓዛር የኤልዩድ ልጅ ኢያቄም በትውልድ ሐረግ እስከ ሰሎሞንና እስከ ንጉሥ ዳዊት የሚደርስ ነው ። ይኸውም በዙፋኑ የሚቀመጥና ለዘላለሙ በእስራኤል ዘሥጋ በእስራኤል ዘነፍስ ነግሦ የሚኖር ከዘሩ ሊሰጠው ጌታ የማለለት ነው። ሚስቱ ሐናም መካን ሆነች ሁለቱም ወደ እግዚአብሔር አዘ ውትረው ይጸልዩና ይማልዱ ነበር። እግዚአብሔርም ልመናውቸውን ተቀበሎ ይችን ጣፋጭ የሆነች መልካም ፍሬን ዓለሙን ሁሉ ከረኃበ ነፍስ ያዳነች ሰጣቸው። መሪር የሆነ ተገዢነትንም ከሁሉ በእርስዋ አስወገደ። ለዚህም ጻድቅ ኢያቄም ለክብር ባለቤት ክርስቶስ አያት መሆን ተገባው ድንቅ ስለ ሆነ ሥጋዊው ከልጁ ስለመወለዱ ነው። እግዚአብሔርም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ደስ በአሰኘው ጊዜ በልቡናው ደስ ብሎት መስዋዕቱን አቀረበ። ከላዩም ከወገኖቹም ልጆች ኀፍረትን አስወገደ። አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጡት ከአስተዋት በኋላ ለእግዚአብሔር እንደተሳሉ ተሸክመው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወስደው አስገቡአት። ጻድቅ ኢያቄም ጥቂት ዘመን ኑሮ በሰላም አረፈ። (ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ) ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ አባታችን ቅዱስ ኢያቄም (ከገድላት አንደበት-የተወሰደ) ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካን ስለነበሩ የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ቀን ጴጥርቃ ቴክታን እንዲህ አላት፡- ‹‹እኅቴ ሆይ! ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን? ልጅ የለን የሚወርሰን አንቺም መካን ነሽ፣ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ወንድሜ ሆይ! አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ›› ብላ ብታሰናብተው ‹‹እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬም እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም፣ ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማኅፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ፣ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ›› አለችው፡፡ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሄዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ ‹‹እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧአችኋል፣ 7 አንስት ጥጆች መውለዳችሁ 7 ሴቶች ልጆችና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ፣ ከቤታችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ፤ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም›› አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ለሚስቱ ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል!›› ብላ ዝም አለች፡፡ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሔሜን ብለው አወጡላት፤ ሔሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ባል አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች፣ በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደችና ቶና አለቻት፣ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፣ ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፣ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሔርሜላ አለቻት፣ ሔርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የወለደቻትን ቅድስት ሐናን ወለደች፡፡ ይኽችም ቅድስት ሐና በሥርዓት አድጋ ለአእምሮ ስትበቃና አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ እነርሱም እጅግ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡ መብዓ ይዘው ለሊቀ ካህኑ ሲሰጡት ሊቀ ካህኑም እንኳ ሳይቀር ‹‹እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መብዓችሁን አልቀበልም›› ብሎ በእጅጉ አሳዝኗቸዋል። በሊቀ ካህኑ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ዛፍ ሥር ተቀመጠው ሳለ እርግቦች ጫጩቶቻቸውን ሲያጫውቱ ተመልክተው ‹‹ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?›› ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን›› ብለው ስዕለት ገቡ፡፡ ዘካርያስም ‹‹እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ የልቦናችሁን ሀሳብ ይፈጽምላችሁ›› ብሎ አሳረገላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐናና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩስ እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም ‹‹ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› አላት፡፡ ‹‹ወፍ›› የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው፤ ‹‹ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን (የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው ዕወቅ ሲል ነው፡፡ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው ምልአቱ ስፍሃቱ ርቀቱ ልእልናው ናቸው፡፡ ቅድስት ሐናም ‹‹እኔም ደግሞ አየሁ እንጂ›› አለችው፡፡ ‹‹ምን አየሽ?›› ቢላት ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ርግብ›› የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፣ ነጭነቱ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡ እነርሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ይልቁንም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ‹‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት› ብሎ ያበሰረ አምላክ ለእኛስ ይልክልን የለምን!›› ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ‹‹ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ ብሎሏችኋል ጌታ›› ብሎ መልአኩ ለሐና ነገራት፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ተፀነሰች፡፡
የእናታች የቅድስት አርሴማ ተጨማሪ መዝሙሮችን ማግኝት ከፈለጉ
✞ 🥰የቅድስ አርሴማ ተወዳጅ መዝሙር🥰 ✞ 1,✞ አርሴማ ✞ 2,✞ ነይ_አርሴማ_ቅድስት ✞ 3,✞ ጽኑ ሰማዕት የእምነት ✞ 4,✞ እናቴ አርሴማ ✞ 5,✞ የብርሃን አክሊል ✞ 6,✞ ተባረኩኝ ጠራኝ ጸሎቷ ✞ 7,✞ አርሴማ ቅድስ አርሴማ ✞ 8,✞ በዙርያችን_ካሉ ✞ 9, ✞ አርሴማ ✞ 10,✞ ታላቅ በሆነው አርሴማ ✞ ✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥ ╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮ ✞ @Nahuseman256✞ ✞ @Nahuseman256 ✞ ╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯ ❕ የመዝሙራቱን ስም(ርዕስ) በመንካት መዝሙሩን ከነ ግጥሙ ያግኙ
ቅዱስ ቶማስ አምላካችን እግዚአብሔር ለሰማይ ለምድሩ በቅድስናቸው ከከበዱ ወዳጆቹ በረከትን ያድለን::
በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጐኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመንኩ አለ። ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት። በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች። =>ሚያዝያ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን አዳምና ሔዋን (የዕረፍታቸው መታሠቢያ) 2.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት (ልደቱ) 3.አባታችን ቅዱስ ኖኅ (ልደቱ) 4.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (የጌታችንን ጐኑን የዳሰሰበት) 5.ቅድስት ማርያም ግብፃዊት (ከኃጢአት ሕይወት ተመልሳ በፍፁም ቅድስናዋ የተመሠከረላት እናት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም 2.እናታችን ሐይከል 3.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 4.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 5.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 6.ቅድስት ሰሎሜ 7.አባ አርከ ሥሉስ 8.አባ ጽጌ ድንግል 9.ቅድስት አርሴማ ድንግል ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶቹም ጸሎት በታጋዮች ጻድቃንም በድል አድራጊዎች ሰማዕታትም ጸሎት ይልቁንም በእመቤታችን ማርያም በአማልጅነቷ ይምረን ዘንድ ወደርሱ እንለምን ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ እና #ከገድላት_አንደበት)
ቅዱስ ዳዊት ታላቅና ገናና የከበረ ንጉሥ ከመሆኑ የተነሣ መንግሥቱ የመሢሕ መንግሥት ምሳሌ ሆኗል፤ መሢሑም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ስም ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶ ይገኛል። (ኢሳ 9፡7፣ ኤር 23፡5-6፣ ኤር 33፡14-17፣ ሕዝ 34፡23፣ ሆሴዕ 3፡5) በሐዲስ ኪዳንም ወንጌላዊያኑ ጌታችንን ‹‹የዳዊት ልጅ›› በማለት ነው መጀመሪያ ነገረ ልደቱን ማውሳት የጀመሩት፡፡ ማቴ 1፡1፡፡ ራሱ ጌታችንም ‹‹እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ›› ብሏል፡፡ ራእ 22፡16፡፡ ቅዱስ ዳዊት 7 ሀብታት የተሰጡት ጻድቅ አባት ነው፡፡ እነዚህም የተሰጡት ሀብታት፡- ሀብተ ክህነት፣ ሀብተ መንግሥት፣ ሀብተ መዊዕ (የማሸነፍ ሀብት)፣ ሀብተ ትንቢት፣ ሀብተ ኃይል፣ ሀብተ በገና (ዝማሬ) እና ሀብተ ፈውስ ናቸው። ቅዱስ ዳዊት 24 ሰዓት ሙሉ የእግዚአብሔር ምስጋና እንዳይቋረጥ መዘምራንን መድቦ እንዲያገለግሉ ያደርግ ነበር፡፡ ራሱም 10 አውታር ባለው በገና ሌት ተቀን በፍጹም ተመስጦ ያመሰግን ነበር፡፡ በመዝሙሩም አጋንንትን ያቃጥል ነበር፡፡ መዝሙረ ዳዊት በውስጡ የያዘው ሚሥጢር እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ አባቶቻችን ዛሬም በዱር በጫካ ሆነው መዝሙረ ዳዊትን አብዝተው ይደግማሉ፡፡ እንኳንስ የሰው ልጅ ይቅርና ‹‹መዝሙረ ዳዊትን›› ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም እግዚአብሔርን ለማመስገኛነት ተጠቅመውበታል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እድሜ ዘመኑን እግዚአብሔርን በማገልገልና በመፍራት ኖሮ በታኅሣሥ 23 ቀን በሰላም ዐርፎ በኢየሩሳሌም ተቀብሯል፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ግብፃዊት_ቅድስት_ማርያም በዚህች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች። ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና። በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት። ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም። የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም። ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሄር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች። በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት። ቤተ ክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ። ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት። ከዚያም በኃላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር። እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች። በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ። በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ ። ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሄርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት። ወደርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው። በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ። ከዚህም በኃላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት። ዓመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት። በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች። ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው ።ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ።ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ። ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት ። ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሄርንም አመስገኑት። መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ
ለአባታችን አዳምም ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሲሆን መላልኤልም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ሲሆነው በተፈጠረባት ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት አረፈ ያረፈባትም ሰዓት ከገነት የወጣባት ናት በዚያን ጊዜም የመላእክት ሠራዊት ከልጆቹ ጋራ ተሰበሰቡ። መልካም አገናነዝም ገነዙት በብዙ ሽቱዎችም መዓዛውን አጣፈጡ። ይህም በገነትና በደብር ቅዱስ ያለ ነው ስጋውንም በፀሐይ መውጫ በኲል በዋሻ ውስጥ አኖሩ የሚያበራ መብራትም አኖሩ ከእርሱም ጋራ ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን አስቀመጡ ዋሻውንም በአዳምና በሔዋን በሴት ቁልፍ ቆልፈው አተሙት። የጥፋት ውኃም እስከ መጣ ድረስ ሴትና ልጆቹ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግሉ ኖሩ። ከዚህ በኃላም ኖኅ በአምላክ ትእዛዝ ደብረ አራራት እስከሚአደርሰው ከእርሱ ጋራ የአባታችን የአዳምን ሥጋ በመርከብ ወሰደው። ከዚያም ሴምና መልከ ፀዴቅ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራቸው ይዘውት ሔዱ ከቀራንዮ ቦታ ደርሰው በዚያ ቀበሩት መልከ ጼዴቅም በዕጣንና በቁርባን ሲያገለግል ኖረ። የእግዚአብሔርም ልጅ መጥቶ ከድንግል ልጁ በተወለደ ጊዜ መድኃኒት በሆነች ሞቱ አድኖ ወደ ቀደመው ርስቱ መለሰው እርሱ ለከበሩ ደጋጎች ነቢያት ለተጋዳዮችም ሰማዕታትና ጻድቃን አባት ነውና ስለ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ዓለም መጥቶ ሰው ሁኗልና። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባታችን_ቅዱስ_ኖኅ (ልደቱ) ዳግመኛም በዚህች ቀን ከአባታችን አዳም ጀምሮ አሥረኛ ትውልድ የሆነ ጻድቁ ኖኅ ልደቱ ነው፡፡ እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ኃጢአት እንደሚበዛና ደጋጎች እንደሚያንሱ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደሚደመሰስ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያይ ሆነ፡፡ ስለዚህም ፊቱ የተቋጠረ ሆኖ ፈጽሞ ያለቅስ ነበር፡፡ ጻድቁ ኖኅ ኖኅም የአቡዚር ልጅ የሆነች ሐይከል የምትባል ሴት አግብቶ ወደ እርሷ ሦስት ጊዜ ቢገባ ሦስት ልጆችን ሴም ካም ያፌትን ወለዳቸው፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከደብር ቅዱስ ዕንጨት ቆርጦ መርከብን እንዲያሠራ ካዘዘው በኋላ አሠራሯን በዝርዝርና በጥልቀት አስረዳው፡፡ የቃየል ልጆችም ኖኅን መርከብ ሲሠራ አይተው ዘበቱበት፡፡ የአዳምንም ሥጋ ወስዶ በውስጡ አኖረ፡፡ ሴም ወርቁን፣ ካም ከርቤውን፣ ያፌት ዕጣኑን ወስደው ወደ መርከብ አስገቡ፡፡ ኖኅም ከልጆቹና 500 ዓመት ድንግልናውን ጠብቆ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስት እንዲያገባ እግዚአብሔር አዘዘው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ እንደሚደመሰስ ከእርሱ ዘር በቀር የሚተርፍ እንደሌለ ነገረው፡፡ ጻድቁ ከሚስቶቻቸው ጋራ ወደ መርከቡ ገባ፡፡ ንጹሐን የሆኑት እንስሳትና አእዋፋት ሴትና ወንድ ሰባት ሰባት፣ ንጹሐን ካልሆኑት ደግሞ ሁለት ሁለት ሴትና ወንድ አስገባ፡፡ ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ የምድርም ምንጮች ሁሉ ተነድለው ራጃጅም ተራራዎችም እስኪሸፈኑ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዘነመ፡፡ ውኃውም በላያቸው 15 ክንድ ከፍ አለና ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሞተ፡፡ ከ150 ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አስቦ ነፋስን በምድር ላይ አመጣና ውኃውን አጎደለ፡፡ ምንጮች ተደፍነው የሰማይ መስኮት ተዘጋ፡፡ መርከቢቱም በ7ኛው በ12ው ቀን አራራት ተራራ ላይ አረፈች፡፡ ከጊዜም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን ከነቤተሰቡ አንድ ላይ ከመርከቡ እንዲወርዱ አዘዘው፡፡ ኖኅም መሠዊያን ሠርቶ ንጹሕ ከሆኑት ሁሉ ወስዶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መልካም መዓዛን አሸተተ፡፡ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳያጠፋ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ምድር ፀንታ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ዘር መከር፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ መዓልትና ሌሊት እንደማይቋረጥ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ግዟት አላቸው፡፡ ኖኅም ምድርን ያርሳት ይቆፍርራትም ጀመር፡፡ ወይንም ተክሎ ከእርሶ ፍሬውን አድርሶ ወይን ጠጥቶ በሰከረና ራሱን በሳተ ጊዜ የከነዓን አባት ካም የኖኅን ራቁትነት አይቶ ሳቀ፣ ሄዶም ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ያፌትና ሴምም ልብስ ወስደው የአባታቸውን ርቃን ሸፈኑ፡፡ ኖኅም ከስካሩ በነቃ ጊዜ ሁሉም ያደረጉትን ዐወቀ፡፡ ‹ከነዓን የተረገመ ይሁን፣ ለወንድሞቹም ተገዥ አገልጋይ ይሁን› ብሎ ከረገመው በኋላ ‹‹የሴም ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም የያፌትን አገር ያስፋ፣ በሴም ቤትም ይደር›› ብሎ መረቃቸው፡፡ አባታችን ኖኅ ‹‹እግዚአብሔር በሴም ቤት ይደር›› ማለቱ የጌታችንን ሰው መሆን በትንቢት መናገሩ ነው፡፡ እርሱም ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ኖረ፡፡ በአጠቃይ ዕድሜው 950 ዓመት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ልበ_አምላክ_ቅዱስ_ዳዊት (ልደቱ) በዚህችም ቀን የሰሎሞን አባት ንጉሡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ልደቱ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነሐሴ 13 ቀን ተጸነሰ፣ በሚያዝያ 6 ቀን በይሁዳ በቤተልሔም ሀገር ተወልደ። 1ኛ ሳሙ 16፡10-11፡፡ ዳዊት ማለት ‹‹ኅሩይ›› ማለት ነው። አንድም ‹‹ልበ አምላክ›› ማለት ነው። ሐዋ 13፡22፡፡ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ነው። አባቱ እሴይ እናቱ ሁብሊ ይባላሉ። ሁብሊ መልከ መልካም ሴት ነበረች። ከጎረቤታቸው ያለ ጎልማሳ መልኳን እያየ በሐጸ ዝሙት ተነደፈ። እሴይ የእሷም ፈቃድ እንደሆነ አውቆ መንገድ እሄዳለሁ ብሎ ስንቁን ይዞ ወጣ። የሄደ መስሎ ከዚያው ውሎ ሲመሽ በልብሱ ተሸፋፍኖ ድምጹን ለውጦ ያንን ሰው መስሎ ገብቶ ከእርሷ ጋር አድሮ ጎህ ሳይቀድ ወጥቶ ሄደ። ዳዊት በዚህ ዕለት ተጸንሷል። በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” (መዝ 50፡5) ማለቱ ስለዚህ ነው። ቅዱሱም ተወልዶ ጉልበቱ ከጸና በኋላ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አድጓል። እረኛና ብላቴና የነበረ ቢሆንም የፍልስጤማውያኑን ኃያል ሰው ጎልያድን በ12 ዓመቱ 5 ጠጠርን ከወንዝ ለቅሞ በወንጭፍ ወርውሮ ገድሏል፡፡ 1ኛ ሳሙ 12፡45-51፡፡ ንጉሥ ሳዖል በጌልቦአ ተራራ በራሱ እጅ ከሞተ በኋላ አስቀድሞ በይሁዳ 7 ዓመት በመላው እስራኤል 33 ዓመት ነግሡዋል፡፡ 2ኛ ሳሙ 2፡4፤ 5፡1-5፡፡‹‹እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል” (1ኛ ሳሙ 13፡14) ተብሎ በእግዚአብሔር የተመረጠና ነገረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ዳግም ምጽዓትን፣ ነገረ ማርያምን፣ ክብረ ቅዱሳንን፣ በስፋትና በጥልቀት የተናገረ የብሉይ ኪዳን ‹‹ወንጌላዊ›› የተባለ ቅዱስ ነቢይ ነው። “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም። ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ…” እያለ የጌታችንን መከራ መስቀል በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 21 (22)፡ 16-18፡፡ “አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”፣ “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ…” እያለ የጌታችንን ዕርገቱንና ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል፡፡ መዝ 46(47)፡4-5፣ መዝ 49(50)፡ 1-5፡፡ “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” እያለ የእመቤታችንን ክብር አይቶ በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 44(45)፡9፡፡
#ሚያዝያ_6 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ስድስት በዚህችም ቀን #የአባታችን_አዳምንና #የእናታችን_ሔዋን መታሰቢያቸውን ነው፣ ከአባታችን አዳም ጀምሮ አሥረኛ ትውልድ የሆነ #ጻድቁ_ኖኅ ልደቱ ነው፣ ንጉሡ ልበ አምላክ #ቅዱስ_ዳዊት ልደቱ ነው፣ በበረሀ የምትኖር #ግብፃዊት_ማርያም አረፈች፣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት #ለሐዋርያው_ቶማስ ተገለጠለት፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱሳን_አዳምና_ሔዋን ሚያዝያ ስድስት በዚህችም ቀን የአባታችን አዳምን የእናታችን ሔዋንን መታሰቢያቸውን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን። ይህን አባታችን አዳምን ሳይፈጥረው አስቀድሞ በሰማይና በምድር ያለውን አዘጋጀለት። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረ መላእክትንም ስለርሱ ፈጠረ። ከዚህም በኃላ በኤዶም ተክልን አዘጋጀለት እርሱም የፍሬው ጣዕም በየራሱ ልዩ ነው የሚአሻውን ሁሉ አከናውኖ እነሆ ከምድር መካከል ይኸውም ጎልጎታ ነው አፈር አንሥቶ በሦስት ሰዓት እርሱን ፈጠረው። ከአራት በሕርያት ይኸውም ውኃ እሳት ነፋስና መሬት ነው በአርአያውና በምሳሌው ራሱን አስመስሎ ፈጠረው በፊቱም እፍ ብሎ የሕይወት መንፈስን አሳድሮ የሚናገርና የሚያስተውል የሚያውቅ አደረገው የብርሃንንም ልብስ አልብሶ ንጉሥ ነብይ ካህን አስተዳደሪ አድርጎ በፈጠረው ሁሉ ላይ ሾመው። ከዚህም በኃላ አይቶ ስማቸውን ይሰይም ዘንድ አራዊትን እንስሳትን የሰማይ ወፎችን ሁሉ ወደርሱ አመጣ። አዳምም መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረው ለሁሉም ስም አወጣላቸው። ከዚህም በኃላ በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣበትና አንቀላፋ ከጐኑም አንድ ዐጥንትን ነሣ ቦታዋንም በሥጋ መላው እግዚአብሔርም ሴት አድርጎ አሰምሮ ሠራት በአዳምም በፊቱ አኖራት። አዳምም ነቅቶ ይቺ ከዐጥንቴ ዐጥንት ከሥጋዬ ሥጋ ናት ሚስት ትሁነኝ ብሎ ተናገረ ስሟንም ሔዋን አላት። አዳምም በጎልጎታ ቁሞ የፈጣሪውን ቃል እየሰማ ሳለ እነሆ ከሚስቱ ከሔዋን ጋራ በፊት በኃላ ሁነው በየነገዳቸው አዳምን ስለ አከበረው መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደመና ተሸክማ ወሰደቻቸው በኤዶም ገነትም አኖራቸው። እግዚአብሔርም አዳምንና ሔዋንን በገነት ካለው ተክል ሁሉ ብሉ ግን ከገነት መካከል ዕፀ በለስን አትቡሉ ከእርሱ በበላችው ቀን ሞትን ትሞታላችሁ አላቸው። አዳምም ገነትን እያረሰና እየቆፈረ ከፍሬዋም እየተመገበ ከመላእክት ጋራ ሲያመሰግን ኖረ። የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ግን ከማዕርጉ በወደቀ ጊዜ በአዳም ጌትነትና ክብር ቀንቶ በእባብ አድሮ ወደሔዋን ሔደ። ያንን ዕፀ በለስንም ትበላ ዘንድ አታለላት አምላክ የመሆንንም ተስፋ አሳደረባትና አሳታት። ያንን ዕፀ በለስንም በአየችው ጊዜ አማራት በልታ ለባልዋም አበላችው ያን ጊዜ የብርሃን ልብሳቸው ከላያቸው ተገፈፈ። እነርሱም ራቁታቸውን እንደሆኑ አውቀው በበለስ ቅጠል ኀፍረተ ሥጋቸውን ሸፈኑ። እግዚአብሔርም ስሕተታቸውን አውቆ አስቀድሞ እባብን ረገመ በእርሷና በሴቲቱ ዘር መካከል ጠላትነትን አጸና። በሔዋንም ላይ በፃር በገዐር ውለጂ ወልደሽም መመለሻሽ ወደባልሽ ይሁን እርሱም ይግዛሽ ብሎ ፈረደባት። አዳምንም እንዲህ አለው ስለ አንተ ምድር የተረገመች ትሁን ጥረህ ግረህ እንጀራህን ብላ አንተ አፈር ነህና ወደ አፈርነት ትመለሳለህ። እግዚአብሔርም የቁርበትን ልብስ አዘጋጅቶ አለበሳቸው ሰባት ዓመት በተድላ ከኖሩ በኃላ በምሽት ጊዜ ከኤዶም ገነት ወጡ። አዳምም በማለዳ ፀሐይ ሲወጣ ነጭ ዕጣን ቀንዓት ሰሊሖት የሚባል ሽቱ ከሎሚ ውኃ ጋር አጠነ። አዳምም በኤዶም ገነት እንደተማረ ምድሪቱን እያረሰና እየቆፈረ ኤልዳ በሚባል ምድር ኖረ። አዳምም ሔዋንን በግብር አወቃት ቃየልን ከእኅቱ ጋር ወለደችለት ከእርሱም በኃላ አቤልን ከእኅቱ ጋራ ወለደችው ቃየልና አቤልም አድገው አካለ መጠን አደረሱ። ወደ እግዚአብሔርም መሥዋዕት በአቀረቡ ጊዜ ጌታ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ ስለዚህም ቃየል ተቆጣ በአቤልም ቀንቶ ገደለው። አዳምም በልጁ በአቤል ሞት እያዘነና እያለቀሰ አራት የዘመን ሱባዔ ኖረ። ከዚህም በኃላ ሴት ተወለደለት በእርሱም መታሰቢያው ጸና ከእርሱም በኃላ ብዙዎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። እግዚአብሔርም ንስሓውንና ልቅሶውን አይቶ የድኅነት ተስፋ ሰጠው። አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ወደ ዓለም መጥቼ ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ ሕፃንም ሆኜ በሜዳህ ውስጥ እድሀለሁ በመስቀሌና በሞቴም አድንሃለሁ አለው። አዳምም ከገነት በወጣ ጊዜ የወሰደውን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ለልጁ ለሴት ሰጠው እንዲህም አለው በኃላ ዘመን የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ ከድንግል ይወለዳል ያን ጊዜ የጥበቡ ሰዎች ይህን ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን እጅ መንሻውን ያመጡለታል እርሱም መዝግቦ በዕቃ ቤት አኖረው። ወደ ኖኅም እስኪደርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ኖረ ከኖኅም የምሥራቅ ሰዎች ወደ ሆኑ የጥበብ ሰዎች እስኪ ደርስ ተላለፈ። እነርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምጥተው ለእግዚአብሔር ልጅ እጅ መንሻ አድረገው አቀረቡለት እመቤታችንም ከእጃቸው ተቀበላ በኃላ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሰጠችው ቅዱስ ጴጥሮስም ለቀሌምንጦስ ሰጠው። አዳምም የሚያርፍበትን ሰዓት በአወቀ ጊዜ ልጁ ሴትን ጠርቶ ከመሞቴ በፊት ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ወደእኔ አቅርባቸው አለው። የአባቱን ቃል ሰምቶ ዕንባው በጉንጩ ላይ እየፈሰሰ ወጣ ወደ አዳምም አቀረባቸው። አዳምም በአያቸው ጊዜ ከእሳቸው ስለ መለየቱ አለቀሰ። እነርሱም ሲያለቅስ በአዩት ጊዜ ሁሉም በአንድነት ወደ እግዚአብሔር በግምባራቸው ተደፍተው አለቀሱ ምድር እንዴት ትሸፈንሃለች ከዐይኖቻችንስ እንዴት ትሠወራለህ አሉ። ከዚህም በኃላ አባታችን አዳም ሁሉን ልጆቹን ባረካቸው መረቃቸው። ልጁን ሴትን እንዲህ አለው ይቺ ዓለም ድካምና ችግርን የተመላች ናትና በእግዚአብሔር እየታመንክ ዕውነትን ንጽሕናን ጠብቅ ሰይጣን ወደ ሚያሳይህ ምትሐቱና ወደ ነገሩ አታዘንብል። በሞትኩ ጊዜም ሥጋዬን ወስዳችሁ ሰሊክ ሚዓ በሚባል ሽቱ ገንዛችሁ በግምጃ ቤት አኑሩኝ የጥፋት ውኃ ይመጣ ዘንድ አለውና ፍጥረት ሁሉ ይሰጥማል ከስምንት ነፍስ በቀር የሚቀር የለም። ልጄ ሆይ ለወገኖችህ ቋሚ ሁነህ እግዚአብሔርን በመፍራት ጠብቃቸው የዕውነት መንገድንም ምራቸው ለስይጣንም እንዳይ ታዘዙና እንዳያጠፋቸው አደራ አስጠብቃቸው። ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ከቃየል ልጆች ለያቸው አንድ ይሆኑ ዘንድ ከቶ አትተዋቸው ወደ ሥራቸውና ወደ ጨዋታቸውም አይቅረቡ። ከዚህም በኃላ ወደ ልጁ ወደ ሴትና ወደ ሔዋን መለስ ብሎ ያንን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከእርሳቸው ጋራ አኑረው ይጠብቁት ዘንድ አደራ አላቸው። እንዲህም አላቸው የጥፋት ውኃ በመጣ ጊዜ ሥጋዬን ከወርቁ ከከርቤውና ከዕጣኑ ጋራ ወደ መርከብ ያስገቡ ከዚያም በኃላ በምድር መካከል ያኑሩት። ከብዙ ዘመናት በኃላም ያቺን አገር ይወርዋታል እሊህንም ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከብዙ ምርኮ ጋር ይወስዱትና አካላዊ ቃል መጥቶ ሰው እስከሚሆን ድረስ በዚያ ይጠበቃል። ነገሥታትም ይዘው መጥተው ይገብሩለታል ወርቁ ስለ መንግሥቱ ዕጣኑ ስለ ክህነቱ ከርቤውም ማሕየዊት ስለሆነች ሞቱ ነው።
🌺እንኳን ለማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ለሱራፌል አምሳላቸው ለሆነ ለኢትዮጵያዊው ለታላቁ ማኅሌታይ ለካህኑ ቅዱስ ያሬድ የተወለደበት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከእናቱ ቅድስት ክርስቲና (ታውክልያ) ከአባቱ ከቅዱስ አብዩድ (ይስሐቅ) በአክሱም በ505ዓ.ም ሚያዝያ 5 ቀን ተወለደ። የቅዱስ ያሬድ ጸሎቱ በረከቱ ረድኤቱ ለዘላለም ይደርብን! 🕯🌺🕯🌺🕯🌺