መንፈሳዊ ግጥም ብቻ (✍️ዝምተኛው ገጣሚ)
Статистикаበዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ Comment
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 725
- 1/48двое суток
- 830
- 1/72трое суток
- 896
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሥነጽሑፍ - ግጥም ! ( ርዕስ - እመቤታችን ) በድንጋሌ ስጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች እመ አምላክ የህሙማን ፈውስ ንፅህት ወብሩክት እመ ብርሃን ሆይ በሃጥያት የነበረች አሻሮ ጥቀርሻ ሲኦል ሲያይ ልትሆን የቀራት አንድ አሙስ የቀራት ለሞት ብኩን ነፍስ የዋጣት የአጢያት ፅልመት እንደትጠራ ብለሽ ፍማ እንደ እነኰይ ጸዓዳ እንደ በረዶ ብሩ እንደ ፀሐይ ሆና ታበራ ዘንድ በአርያም ሰማይ ዕንባሽ እነባ ወልደ እነደ ጐርፍ ዥረት ሲቀንዠቀዠቅ ሲወርድ ከዓይኖችሽ ዕምብርት ምነኛ ርህሩህ ነሽ የኛማ እመቤት በዕንባ የምትዋጀኝ እኔ በድያት አለች አዲሷ ነፍስ ብርሃንሽን ተላብሳ ስትቀርብ በሐሴት ስትዘል እንደ እምቦሳ ኩሩቤል ሱራፌል ሚካኤል ወገብርኤል ነገደ መላእክት ቅዱስ ሰማዕታት ዕፁብ ድንቅ ዕፁብ ድንቅ የደግንት ባህር የርህራሄዋስ ዳር ድንበር ለሰው የላት ፍቅር ወሰኑ የት ይሆን ስፋቱ አይመጠን ምን ልክ አለው እና የርህራሄው ዳር ርህራሄን አይደል የአካልዋ ቅምር ሲሉ አመሰገኑት ቅድስት ወብርክት ቤዛዊት ኩሉ እህት መላእክት ለእስትንፋስ ልቧ ከተስፋ አንደበትዋ ምስጢር አዘነበች ሠርፃ ከዓይኖችዋ በብርሃን ተውቦ የድህነት ዚቅ መልዕክትዋ ሲነበብ ክፋትን አውልቆ ደግነት ማጥለቅ ቤዛዊተ ኩሉ የብርሃን እናት የስርየት መገኛ ፍኖተ ህይወት ባክሽ ማጡ ዋጡኝ ሃጥያት ተናነቀኝ ከገነት አፌ ዘልሎ ወሰደ አጠለቀኝ እንባ አጠለቀኝ ይቅር በይ በአማልጂኝ ልቄቂት ብርሃንሽን አይረቀኝ ይድረሰኝ መንጠቆ እንዳያወጣኝ የብርሃንሽ ክፋይ ሰናፍጭ ታክል ተወርውራ መጥታ ከልቤ መሀል አርፋ ብትቀመጥ ያበቃኝ ነበር የክፋት ግንዲላ በተሠረሠረ አውቀለውሁ ያን ግዜ ቀልሎት በርሮ የደስታ አክናፍ አውጥቶ ጠሻግሮ ቤዛዊተ ኩሉ እመ አምላክ ድንግል ፍቅርሽ በእኛለክቦ ሀዘን ይቅለል ፈሪያ እግዚአብሔር ማዕጣንት ሀገሬን እንዲያጥን “እባክሽ እመቤቴ”ባክሽ አትረቂን ዕንባሽ መፅናኛችን ይሁን መመኪያችን ይቅርታ ፀደል የምህረት ሙዳይ የርህራሄ ማህደር ገነት ሰማይ የዕውራን ብርሃን የህሙማን ምርኩዝ የትሑታን መቅረዝ የአርያም ምዕኩዝ እመ ክርስቶስ የድንግል ቤዛዊትተ ዓለም ባክሽ አትራቂን እመቤቴ ሆይ ሃጥያት ን መፍጨቱ ንሱ በቃ በይ ከመለጁ ስር ልማ እሪ ዋይ እያለች ነፍሳችን ቃተተች ድረሽልኝ ባክሽ ብለ ናፍቆት እየት ተርመጥመጣ ሁሌ ስትዋትት በዕንባሽ ተቤዣያት ባክሽን ታደጊያት ቤዛዊተ ኩሉ ቤዛዊት እንባል ፍቅር በረከትዋ እንድታድለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ! የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሣን የንጽሕተ ንጹሐን ድንግል ማርያምኀ እናትነት፣ ረድኤት፣ በረከት እና አማላጅነት በሁላችን ላይ አድሮ ይኑር። አሜን!! ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
ስልክ እና 📶internet ብቻ ካላቹ ONLINE ስራ መስራት ለምትፈልጉ ብቻ በጣም አሪፍ አዲስ ስራ መጣ እኔ እዛ ላይ Agent ነኝ አብረን እንሰራለን እዚህ Group ተቀላቀሉ። 👇👇👇 https://t.me/Online_Dir https://t.me/Online_Dir https://t.me/Online_Dir
без подписи
መምሰል °°°°°°°° ከደጇ ቁሚያለሁ በረከት ለማግኘት ከ'ናቴ ፍልሰታ፣ ማረጓን ያመነ ይኸው ያሰማል መዝሙርና እልልታ። "ማርያም አረገች ማርያም አረገች" እያሉ በደስታ ቀና ብዬ አየሁ የሰማዩን ከፈን፣ ለጠርጣራው ልብሽ ማሳረፊያ 'ሚሆን፥ ከሰጠችሽ ብዬ እንደ ቶማስ ሰበን። አየሽ ሞኝነቴን ከፍቅሬ የተነሳ ላንቺ ምህረት ስሻ፣ ከስንት ዘመን በፊት ያረገች እናቴን እንዳ'ዲስ ሳሳርግ በምናቤ ዋሻ። ግን መጥተሽ ይሆን? ህጻናት በክብር ስጋ እና ደሙን ቀምሰው ሲመለሱ፣ ቆርበሽ ከሆን ብዬ እስክትወጭ አያለሁ ከቤተ መቅደሱ። አየሽ የዋህነቴን በሴት ግዳጅ ታስረሽ መግባት እንደማትችይ እያወ'ኩ ጠንቅቄ፣ ትኖሪያለሽ ብዬ በከንቱ ሳማትር በፍቅርሽ ታንቄ። ግን መጥተሽ ይሆን? እልፍ ሆኖ ሳለ እምነት የተቀባ ነጠላ ያጣፋ፣ ቅጽሩን ሙሉ ብቃኝ አንችን የሚመስል አንድ ውብ ሴት ጠፋ። ተመልከች እብደቴን ተስፋዬ ተሟጦ ለስግደት ስደፋ ከ'ናቴ ስዕል ፊት፣ ወለል ብሎ ታየኝ ያንቺ መሳይ ውብ ፊት፤ ይኸው ተገፈፈ ማጣት ያሳወረው የዓይኔ ላይ ጉድፍ ልክ እንደ ቅርፊት። ቁጭ እሷን!! ቁጭ አንችን!! ሰዓሊ ለነ ቅድስት!! ለማን ነው የሰገድኩት? ግን አንቺ ነሽ? አንቺም አር'ገሻል እንደ እመቤቴ? አበድኩ መሰለኝ የማይሆን ጥያቄ ወጣ ካ'ንደበቴ። ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
ፍልሰታ✍ ፍልሰታ የሁላችን ደስታ ይህው መጣችልን እልማችን ልትፈታ እንደ ልብ ምቴ ነሽ የኔ ትርታ ጥያቄዬ በዝቶ ምንም መልስ ባጣ በሱባኤው ፀሎት እራሴን ላዳምጥ ይህው መጣችልኝ እናቴ ፍልሰታ ልሸሸግ በደጇ ሚስጥሬን ላወራት በፀጥታው ስፍራ በደሌን ልነግራት በዛውም ልታረቅ ከውዱ ልጇ ጋር የዓለምን አሳብ ከእራሴ አውርጄ እራሴን ላዳምጥ በኪዳነምህረት ደጅ ጥላ ስር ሆኜ በፀሎት እና ፆም እንዳመሰግንሽ በቅዳሴው ዜማ ድንግል ላወድስሽ በፍልሰታው ደስታ አስታርቂኝ ከልጅሽ በሉ እንቀበላት መጣለች ፍልሰታ በፆም በፀሎቱ በስግደት እንበርታ በዓለም ተሸንፈን ከቶ እንዳንረታ ኑ እንቀበላት ይህው መጣች ፍልሰታ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🙏🙏 ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
ፍልሰታ ትፈራው ነበረ ያን መልአከሞት የልጅሽን ፅዋ ቅመሽው አላት ይጠፋል ኩነኔ ይጠፋል አበሳ እንደ ፈጣሪያችን ማርያም ስትነሳ እየባረከቻት ኢትዮጵያን በእጆቿ በይባቤ አረገች እሷም እንደ ልጇ ከሰው የተለየች መሆኗን ሲያበስር ሞት በጥር ሆነ ነሃሴ መቃብር አይሁዳዊው ቀንቶ ሲሰርቅ ሥጋዋን የመለኮቱ ሰይፍ ቆርጠው እጁን ብዙው ይጾመዋል የፍልሰታን ፆም ከእህል ተከልክሎ ከሥጋ ከደም ሐዋርያው ፊሊጶስ ትንሣኤዋን ሲሻ ከወንድሞቹ ጋር ዕርገቷንም ሲሻ በስሟ ተነሱ ሊፆሙ በጋራ። የበረከት ፆም ያድርግልን! ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
በጉጉት ስጠብቁት የነበረው ምስጢራዊ አደራ የሚል ድንቅ መንፈሳዊ ልቦለድ ክፍል 18 ስለቆየንባችሁ እንዴ መካሻ ከድሮው እረዘም አድርገን Post አድርገንላችኋል። ተለቋል በዚህ link በመግባት አንብቡ የተለቀቀበት ቻናል👇👇 ኑ Join አድርጉ👇👇👇 ____ @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16
.ጾመ ፍልሰታ ጾመ ፍልሰታ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም <ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል :: ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኔ ወደ ገነት መፍለሱን ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ…
.ጾመ ፍልሰታ ጾመ ፍልሰታ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም <ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል :: ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኔ ወደ ገነት መፍለሱን ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ ኢትዮጵያን መባረኳን ያስተምራሉ፡፡ «ነቢዩ ዕንባቆም የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ፤» ዕንባ. 3፡7 ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት እመቤታችን የኢትዮጵያን አውራጃዎች ለመባረኳ ማስረጃ መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረጉማሉ፤ ያመሠጥራሉ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያን ለእናቱ አሥራት አድርጐ በመሥጠቱ በእርሷ በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሆን የነገረ ድኅነት ምሥጢር በመከናወኑ ኢትዮጵያውያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተለየ ፍቅር አለን፡፡ የአብነት /የቆሎ/ ተማሪዎች በትምህርት ዓለም ከአንዱ ወደሌላው እየተዘዋወሩ /የአብነት/ ትምህርት ሲማሩ በእንተ ስማ ለማርያም፤ ስለማርያም እያሉ፡፡ የእመቤታችን ስም ስንቅ ምግብ ሆኗቸው ይጠቀሙበታል፡፡ ግሼን ደብረ ከርቤ የልጇ ግማደ መስቀል ከከተመበት አምባም የሚጓዙ ምእመናን «አንድ እፍኝ ሽምብራ አልያዝኩም ከቤቴ ስሟ ስንቅ ነው የእመቤቴ» እያሉ በፍቅሯ ተማርከው ግብር ሰፍረው ዕጣን ቋጥረው ሱባዔ እየገቡ ይማፀኗታል፡፡ እርሷም ከልጇ ዘንድ ባገኘችው የመወደድ ሞገስ ምልጃቸውን በመቀበል ጸሎታችውን በማሣረግ የእናትነት ሥራ ሥትሠራላቸው ኖራለች፡፡ ዛሬም እየሠራች ነው፡፡ እመቤታችን ከልጇ ያገኘችውን /የተቀበለችውን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ በዐራቱ ማእዘን «ሰዓሊ ለነ ቅድስት፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን» የማይላት የለም፡፡ በፍቅሯ ተደስተው በአማላጅነቷ ተማምነው «የእመቤቴ ፍቅሯ እንደ ሰማይ ክዋክብት፣ እንደምድር አሸዋ በዝቶልኝ፣ እንደ ልብስ ለብሼው፣ እንደምግብ ተመግቤው» እያሉ ተማጽነው ልመናቸው ሠምሮ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው፣ ቅዱስ ያሬድ ዘኢትዮጵያና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ያዘጋጁላትን፣ አባ ጽጌ ድንግል የደረሱላትን የምስጋና መጻሕፍት በመድገም እመቤታችን ዘወትር መማጸን የቀደምት ኢትዮጵያውያንም የዛሬዎች ገዳማውያንና ምእመናን ዕለታዊ ግብር ነው፡፡ ጌታችን ለቀደሙት ቅዱሳን ሐዋርያት እመቤታችን አማላጅ እና እናት ሆኗ እንድታገለግል በገቢርም በነቢብም ከአደራ ቃል ጋር አስረክቧል፡፡ በገቢር በቃና ዘገሊላ የሰውን ችግር ፈጥና የምትረዳ ርኅርኅሪት እናት አማላጅ መሆኗን አሳይቷል፡፡ «ለዚሁም የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል» ብላ ያቀረበችው ቃለ ምልጃ ምስክር ነው፡፡ እናት ሆኗ እንድታጽናናቸው በቅዱስ ዮሐንስ በኩል ከእግረ መስቀሉ ስር ሰባቱን አጽራሐ መስቀል ሲያስተጋባ ቅዱስ ዮሐንስን ጠርቶ «እኖኋት እናትህ፤ ድንግል ማርያምን ጠርቶ እነሆ ልጅሽ» ዮሐ. 19፡26፡፡ በማለት እመቤታችን የእናት ሥራ ለሁሉም ቅዱሳን ሐዋርያት እንድትሠራላቸው ምእመናንም ልጅ እንዲሆኗት በማያሻማ ቃሉ ተናግሯል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት እመቤታችንን በእናትነት ከተረከቧት ጊዜ ጀምረው ልጇ በዕርገት በአካለ ሥጋ ሲለይ እንደ ልጅ አገልግለዋታል፡፡ በቤታቸው አኑረዋታል፤ ብትሠወርባቸው ፈልገዋታል፡፡ ብትርቃቸው ናፍቀዋታል፡፡ እርሷም ሲጠሯት ታደምጣቸዋለች፣ ሲፈልጓት ትገኝላቸዋለች፡፡ ይኸውም የሆነው ልጇ በአዳምና በልጆቿ ኃጢአት ምክንያት የፈረደውን ለራሱም ያላስቀረውን ሥጋዊ ሞት እናቱ ብትቀምስ በእናትነት የተረከቧት ቅዱሳን ሐዋርያት መካነ ዕረፍት ለይተው በንጹሕ በፍታ ከፍነው በጌቴ ሰማኒ እንደቀበሯት ስለ እመቤታችን የተጻፉ መጻሕፍት በዝርዝር ያስረዳሉ፡፡ የእመቤታችን ሥጋዊ ዕረፍት «ከመ ትንሣኤ ወልዳ» እንደ ልጇ ትንሣኤ ነውና ሙስና መቃብር ሳያገኛት ከሦስት ቀናት ሥጋዊ ዕረፍት በኋላ ከሞት ተነሥታ ወደ ሰማይ ስታርግ በዕለተ ቀብሯ ያልተገኘው ቅዱስ ቶማስ ደመና ጠቅሶ በደመና ሰረገላ ሲመጣ ዕርገቷን ይረዳል፡፡ እማኝ ደግሞ የተከፈነችበትን በፍታ /ጨርቅ/ ይቀበላታል፡፡ ለቅዱስ ቶማስ የተገለጠው የዕረፍቷ ምሥጢር ሌሎች ቅዱሳን ሐዋርያት እንዲገለጥላቸው ቢማጸኑ እመቤታችን ዳግም ተገልጻላቸው፡፡ ትንሣኤዋን ለማየት በቅተዋል፡፡ እነዚህ በቅድስናቸው የተመሠከረላቸው ቅዱሳን እመቤታችንን በሁለት ሱባዔ ማግኘታቸውን መሠረት በማድረግ በቤተ ክርስቲያናችን ከነሐሴ 1-16 በየዓመቱ አንደሚጾም ይታወቃል፡፡ ይህ እመቤታችንን የምንማጸንበት ጾመ ፍልሰታ ቤተ ክርስቲያናችን መፍትሄ የምትፈልግባቸውን ጉዳዮች ለእመቤታችን የምታቀርብበት ሰዓት ነው ብለን እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያ የእመቤታችን አሥራት አገር ስትሆን እመቤታችን ለኢትዮጵያውያን እናት መሆኗ እየተነገረ ለምን በፈተና ውስጥ አለፍን? ልጇ በአሥራት ኢትዮጵያን የሰጠባት ሀገር አባቶች ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው መንፈሳዊነት /ኀይለ መንሳዊ/ ተዘንግቶ ሥጋዊ ጥበብ በቤተ ክርስቲያን መድረክ ሲታይ ምን ይባላል? «እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ» ማቴ. 24፡15፡፡ የተባለው ቀን ደርሶ ይሆንን? ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዓመታት ለገጠማት ችግር መፍትሔ እመቤታችን እጅ ላይ አለ ብለን እናምናለን፡፡ እመቤታችን ብትሠወርባቸው አባቶች ሱባዔ ገብተው እንዳገኟት የፍቅር እናት ናትና ፍቅር አንድነት እንድትሰጠን እርሷን መማጸን፤ የዶኪማስን ጓዳ እንደሞላች የጐደለውን እንድትሞላ ውዳሴዋን እየደገሙ ድንግልን መማጸን ያስፈልጋል፡፡ በውዳሴ ማርያም፣ በጸሎተ ማርያም የሚመካ በጉልበቱ አይመካም፡፡ ጊዜ ረዳኝ ብሎ በወገኖቹ ላይ ግፍ አይፈጽምም፡፡ ስለዚህ በዚህ በወርኀ ጾም እመቤታችን ምልጃዋ ከአገራችን፣ ከቤተ ክርስቲያናችን ጋር እንዲሆን በሱባዔ እንማጸናት፡፡ በጾመ ፍልሰታ ከሊሂቅ እስከ ደቂቅ በማስቀደስ፣ በጾምና በጸሎት ሁለቱን ሳምንታት እንደሚያሳልፉት ይታወቃል፡፡ በሱባዔው የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች የሚወገድበት ምእመናን በበረከት የሚጐበኙበት ቅድስና የሚሰፍንበት መንፈሳዊነት ትልቅ ከበሬታ የሚገኝበት ጾም እንዲሆን ሁሉም ምእመን መትጋት አለበት፡፡ ሁለቱ ሳምንታት በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር እየተገኘን ምሕላ የምናደርስበት፣ የተጣላነውን ይቅር ለእግዚአብሔር፣ የበደልነውን የምንክስበት ጾም መሆን አለበት፡፡ ቀናቱን እየቆጠርን እስከተወሰነው ሰዓት ብቻ መጾም ብቻ በሕይወታችን መሠረታዊ ለውጥ አያመጣም፡፡ እመቤታችን የአገራችን አሥራት የሁላችን እናት በመሆኗ የእናትነት ሥራ እንድትሠራልን በሚገባ ልንማጸናት ይገባል እንጂ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ሱባዔ ብለን ውዳሴ ማርያም በደገመ አፋችን ሰው የምናማ በሰው ሕይወት ገብተን የምንፈተፍት ከሆነ እመቤታችንን አናውቃትም፡ እመቤታችንም አታውቀንም፡፡ ስለዚህ ጾመ ፍልሰታን እስኪ ሁላችን ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ድንግልን በአንድ ድምፅ እንጥራት፡፡ እስኪ ለቅድስና፣ ለንጽሕና ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ እንስጥና የእግዚአብሔርን ብድራት እንጠብቅ፡፡ ጾመ ፍልሰታ መንፈሳዊነት፣ እውነት፣ ቅድስና የጠራ አሠራር፣ በቤተ ክርስቲያን የሚሰፍንበት እንዲሆን እንመኛለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem
መድኃኔዓለም ሆይ፣ የሕይወቴ ብርሃን፣ በጨለማ ጊዜ አንተ ነህ መዳኛዬ። ልቤ ሲደክም እጅህን ዘርግተህ አንሳኝ፣ በፍቅርህ ጥላ ዘላለም አኑረኝ። ኃጢአቴን ይቅር በል፣ ምሕረትህን አብዛልኝ፣ የሰላም መንገድህን ሁልጊዜ አሳየኝ። አንተ የዓለም መድኃኒት፣ የነፍሴ ተስፋ፣ ክብርና ምስጋና ለአንተ ለዘላለም ይሁን። አሜን። ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
እመቤቴ ማርያም የሰላም እናት፣ ለደካሞች ሁሉ የተስፋ ብርሃን። እንባን የምታብስ በርኅራኄ እጅ፣ የፍቅርሽ ጥላ ለልቤ መጠጊያ ነው። ስምሽን ስጠራ ሰላም ይሞላኛል፣ ፍርሃቴ ይርቃል፣ ተስፋዬም ያብባል። ወደ ልጅሽ ክርስቶስ መንገድ አሳዪኝ፣ በእምነት አጽኚኝ፣ በፍቅር አኑሪኝ። የሰማይ ንግሥት፣ የምሕረት እናት፣ ሁሌም ከእኛ ጋር በጸሎትሽ ኑሪ🙏 ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
ከእኛጋ የተለያዩ የOnline ስራዎች መስራት የምትፈልጉ ሰዎች ብቻ ይህን Group Join አድርጉ። 👇👇 https://t.me/Online_Dir https://t.me/Online_Dir
без подписи
ተከታታይ "ምሥጢሬን ላካፍላችሁ" ምዕራፍ 1 ክፍል 8 ተለቋል የማንበብ ፍቅር ያላችሁ ሁላችሁም እየገባችሁ አንብባችሁ LIKE SHARE አድርጉ ከተመቻችሁ እንቀጥላለን Comment ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልኝ በዚህ ቻናል ነው የተለቀቀው👇👇 @EOTC21_media @EOTC21_media @EOTC21_media
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ይቺ ሁለት ሳቲብ ብዙ ነው መዘዟ የሁሉ ታስባ ጥቂት ቀዳዳ ነው የምትሞላው እሷ ይቺ ሁለት ዲናር ከመዳፌ አሳ ለአይን የምትታይ አጋጣብኝለች አገቴን ወደላይ አሳንሳዋለች እግሬን ወደምድር አሳስባኛለች ደጉ እግዚአብሔርን አስጠርታኛለች የድንግልን ሰሞን ብቻ ፈጣሪ ይስጥልን🧠 ያለ የሞላ ጊዜ ለመሳለም እኮን በሩ ማረግጠውን በማጣት አሳባ ይቺ ሁለት ሳቲብ ደጁ አስገባችኝ በሰው ጉድለቴ ለማይሞላው ከርሴ ቀን ሙሉ ዋልኩኝ ሳቲብ ብቻ አይደለች አጀትን መሙያ እሊናዬን አገኘዋት በዲናሩ መሃል ወድቃ ተረጋግጣ ብቻ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ለሰጣቹ ዲናር እግዚአብሔር ይስጥልኝ ለዚች ሁለት ሳቲብ ብላ ነገረችኝ በመቆየቶ እግዝሄርን አስብ🥹 ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
አረ ቤተሰብ ዩቲዩባችን ላይ የተለቀቀውን አዲሱን Video ገብታችሁ እዩልኝ ቪዲዮውን SHARE እና LIKE አድርጉ። 👇👇👇 https://youtu.be/BAWjPbaouAs?si=aF-iSLgUChePAjJG https://youtu.be/BAWjPbaouAs?si=aF-iSLgUChePAjJG
ተከታታይ "ምሥጢሬን ላካፍላችሁ" ምዕራፍ 1 ክፍል 6 ተለቋል የማንበብ ፍቅር ያላችሁ ሁላችሁም እየገባችሁ አንብባችሁ LIKE SHARE አድርጉ ከተመቻችሁ እንቀጥላለን Comment ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልኝ በዚህ ቻናል ነው የተለቀቀው👇👇 @EOTC21_media @EOTC21_media @EOTC21_media
ድንቅ አረገልኝ ገብርኤል ተስፋ ቆርጬ ግራ ገብቶኝ የምጓዝበት ውሉ ጠፍቶኝ በስዕሉ ፊት ቆሜ ሳለሁ በአባቴ ገብርኤል ተጎበኘሁ ከወደቅኩበት አስታውሶኝ ፈጥኖ ደርሶልኝ አነሳኝ ሰዕለቴን ሰምቶ የረዳኝ ከሰዎች እኩል አረገኝ የሦስቱ ሕጻናት መከታቸው ለእናቱ፣ ቂርቆስ አለኝታቸው ለእኔም ጋሻ ነህ ለሕይወቴ ፋና መብራት ነህ ለእምነቴ በሥላሴ ፊት ለእኔ የቆምከው እኔን ልጅህን ያስታረቅከው ለዚህ ውለታህ ምን እላለሁ ዘውትር በእልልታ እዘእምራለሁ ገብርኤል ብዬ እጮሃለው ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
በጉጉት ስጠብቁት የነበረው ምስጢራዊ አደራ የሚል ድንቅ መንፈሳዊ ልቦለድ ክፍል 17 ስለቆየንባችሁ እንዴ መካሻ ከድሮው እረዘም አድርገን Post አድርገንላችኋል። ተለቋል በዚህ link በመግባት አንብቡ የተለቀቀበት ቻናል👇👇 ኑ Join አድርጉ👇👇👇 ____ @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16
የኔ ገብርኤል ጠባቂየ!!😍 አለም ስትገፋኝ ሰውም ሲዞርብኝ እኔን እሚያደክም ችግር ሲበዛብኝ ፈጥነህ እምታድነኝ ከሀዘን ከትካዜ አልፌአለሁ ባንተ ያን የፈተና ግዜ ደግፈህ ያቆምከኝ እንዳልወዛወዝ ተንሸራትቸ እንዳልወድቅ ሁነህ እንደ ምርኩዝ ካምላክ መገናኛ ፅኑ ረዳቴ ባንተ ነው ያለችው እስካሁን ህይወቴ አሁን በህይወቴ ፍርሀት ርቆኛል ባንተ ከታመንኩኝ ምን ይመጣብኛል ጥበቃህ ብርቱ ነው ረዳትነትህም እዚህ አድርሰኸኛል አሻግር ሁሉንም የኔ አለኝታ ትልቁ መመኪያየ የድካሜ ብርታት አባሽ የእምባየ በምሄድበት ሁሉ መንገድ አስተካካይ ለህይወቴ ብርሀን አብርተህ እምትታይ ተስፋ ጥንካሬ መሪ የጉዞየ እማትዘገይብኝ ሳልጨርስ ስምህን ገና ገብርኤል ብየ ምን ያላደረክልኝ ያልዋልክልኝ አለ ከባድ የመሰለኝ ሁሉ ባንተ ነው የቀለለ እንደኔ ሳይሆን እንዳንተ ደግነት አድርጎትህ ብዙ እማያልቅ ቢቆጥሩት ድርድርም የለኝ ባንተ አባቴ እደገፍብሀለሁ በሙሉ እምነቴ የሠልስቱ ደቂቅ የዳንኤል ረዳት ያቀዘቀዝክላቸው የቅዱስ ቂርቆስና የእየሉጣ እሳት ዜናዊ ሀዲስ የብስራቱ መላክ መላይክትን በሰማይ እንዲረጋጉ ያደረክ ፈጣን ነበልባሉ የራማው ልዑል አበርታኝ ልጅህን ለአለም እንዳልታለል እገዛህ አይለየኝ ያላንተ እኔ አይሳካልኝም እግሬም አይራመድ አይኔም አያይም አንተ ነህ መሪየ እስትንፋስ ህይወቴ ባንተ እምታመን ልጅክን እንዳተወኝ አባቴ ወስብሐት ለእግዚአብሔር 🙏 ተመስገን አይደርስ የለም ደረሰ ቀኑ እንኳን ለሀያሉ መላክ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🙏😍። ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧