መንፈሳዊ ልብ ወለድ
СтатистикаFADA7B8A Our Group👉 @EOTC21media https://telega.io/?r=ES4WQWVD Welcome to our channel This channel is a spiritual storytelling channel, so please JOIN and follow us.
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 211
- 1/48двое суток
- 241
- 1/72трое суток
- 260
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
በሌላ በኩል ፍቅር ምን ጊዜም በምክንያት ብቻ አይሔድም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ለምን ተዋደዳችው ብለህ ስትጠይቃቸው የምታገኘው መልስ ከፍቅራቸው ጥንካሬ ያንስብሃል። ስለዚህ ሰዎች የሚዋደዱበት እኛ የማንገልጠው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ በገቢ የሚራራቁ፣ በመንፈሳዊ ብስለት የሚራራቁ በዕድሜ የሚራራቁ ሰዎች ተዋደው ሲኖሩ የሚኖሩበት ወቅት አለ፡፡ ይህንን አሁን በምን ትገልጠዋለህ? በምን መሥፈርት…
በሌላ በኩል ፍቅር ምን ጊዜም በምክንያት ብቻ አይሔድም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ለምን ተዋደዳችው ብለህ ስትጠይቃቸው የምታገኘው መልስ ከፍቅራቸው ጥንካሬ ያንስብሃል። ስለዚህ ሰዎች የሚዋደዱበት እኛ የማንገልጠው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ በገቢ የሚራራቁ፣ በመንፈሳዊ ብስለት የሚራራቁ በዕድሜ የሚራራቁ ሰዎች ተዋደው ሲኖሩ የሚኖሩበት ወቅት አለ፡፡ ይህንን አሁን በምን ትገልጠዋለህ? በምን መሥፈርት ተዋደዱ ትላለህ? መቼም እነዚህ ሰዎች በመጀመሪያ ሲጋቡ መሥፈርት አውጥተው ያንን አሟልተው ሊሆን አይችልም። አንድ ሰው ከኔ በገቢ የምታንስ ፣ በመንፈሳዊ ብስለት የምታንስ ፣በእድሜም በጣም የምታንስ አገባለው ብሎ መሥፈርት አያወጣም። ነገር ግን ሁለት የተራራቁ ሰዎች ተጋብተው ደስተኛ ሕይወት ሲመሩ ልታይ ትችላለህ። ብቻ በአጠቃላይ ለማጨት ቀመር የለውም።ዋናውን ነገር ሃይማኖታዊውን ነገር ትጠነቀቃለህ እንጂ በሌላው ማንን እንደምትመርጥ እርግጠኛ መሆንና መናገር አትችልም:: ግንኙነትና የአንተንም ሕሊና የማይጎዳ፣ እግዚአብሔርንም የማያስቀይም እንዲሆን መጠንቀቅ እለብህ ብዙ መሥፈርት ማውጣት ተገቢ አይደለም። ትናንሹን ነገር ዘርዝሮ ካልተሟላ ማለት ከባድ ነው፡፡ አንዳንዴ እንደውም በአእምሮ ከምታስበው ውስጥ ሃምሳ በመቶ ከገጠመልህ ልትቀበለው የምትችልበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ ሌላው አንድ ሰው የማገባት ልጅ ጠጉሯ ረጅም መሆን አለበት ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ ሴቷም እንዲሁ ይህንን ቢመስል ብላ ልታስብ ትችላለች። እንዲህ ማሰብ አይከለከልም፡ ካጋጠመ ጥሩ ነው። ነገር ግን ወንዱ የሚያጫት ልጅ ጠጉሯ ረጅም መሆኑ ብቻ ደስተኛ አያደርገውም ። ማሰብ ያለበት ይሄንን ነው፡፡ ዐይኗ ከዋክብት ቢመስል ጥሩ ቤተሰብ መሥርቶ ለመኖር በራሱ በቂ ነው ወይ? የሚለውን በደንብ ማየት አለበት። ስለዚህ አንድ ሰው ትኩረት ሊያደርግ የሚገባው ጥሩ ቤተሰብ መመሥረትና አለመመሥረቱ በሰላም ለዘለቄታው መኖርና አለመኖሩ ላይ ነው። ተሳታፊ ቁጥር ሁለት፦ ትዳር ረጅም ጊዜ የሚፈልግ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ደግሞ እስከ ሕይወት ፍጻሜ የሚኖሩት ሕይወት ነው። መጻሕፍትን ስንመለከት በጋብቻ ሕይወት ከምድር አልፎ ባልና ሚስት በሰማይ የሚገኙትን ሕይወት እስከ መግለጥ ይደርሳሉ፡፡ ለዚህ ነው የድሮ ሰዎችን ስንመለከት ባል ወይም ሚስት ቀድመው ቢሞቱ የቀረው በሕይወት ያለው ወገን ሚስቱን ወይም ባሏን አጥተው ትዳራቸውን አክብረው ሲኖሩ የሚታዩት፡፡ ለምሳሌ እኛ አገር ሚስቶቻቸው ሞተውባቸው እንኳን ቀለበታቸው ሳያወልቍ ኖረው ያለፉ ባሎች ነበሩ።ባላቸው ሞተውባቸው ቀለበት እንዳደረጉ፤ ሌላ ጋብቻ ሳይፈላጉ፣ በብቸኝነት ኖረው ያለፉ ሚስቶችም ነበሩ፡፡ ባሌ ይህን ቀለበት እንዳደረገው ሞቷል፤እኔም እንዳደረኩት ነው የምሞተው የሚሉ አሉ፡፡ ይሄ እንግዲህ ትዳር ዘላቂ መሆኑን፤ የማይቋረጥ መሆኑን ያሳያል፡፡ ማብቂያ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ልክ እንደ ክርስትና ሕይወት ጉዞ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ክርስትና ሲነሣ በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ መደረግ ያለበትን ነገር ሁሉ አጠናቀቀ ማለት አይደለም፡፡ ክርስትና ከተነሣ በኋላ የክርስትና ሕይወቱን በትግል ማጠናከር አለበት፡፡ ክርስትና ተነሣህ ማለት ጥሩ ክርስቲያን ሆንክ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ጥሩ ክርስቲያን ለመሆን በሩ ውስጥ ገባህ ማለት ነው፡፡ ክርስትና ስትነሣ ዐዋቂ ሆነህ ከተነሣህ ደግሞ አስቀድሞ ማሟላት ያለብህ ነገር አለ። ለምሳሌ ተምረህ ማመን አንዱ ነገር ነው። ለመጠመቅ ሕፃንም ሆነህ ስትነሣ የክርስቲያን ልጅ መሆን አለብህ። እነዚህ የመጠመቂያ መሥፈርቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተሟልተው ስትጠመቅም በቃ ሁሉንም ነገር አሟላህ፣ የሚያስፈልገህ ነገር የለም ማለት አይደለም። ከተጠመክ በኋላም ብዙ የምታሟላቸው ነገሮች አሉ። ከጥምቀት በኋላ በተጋድሎ የምታመጣቸው ብዙ መልካም ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ጥሩ ክርስቲያን የምትባለው ከዚህ ተጋድሎህ በኋላ ነው። በትዳርም መነሻ ላይ የምታስቀምጣቸው መሠረታዊ ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ አስቀድሞ እንደተገለጸው ሃይማኖትህ ነው፡፡ ይሄ የግድ ያስፈልጋል። ከዚህ ውጭ ግን ከመተጫጨት በኋላ የሚመጡ በመጠናናት፤ በመተራረም የሚመጡ በጎ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ እዚህ ላይ ስትጀምር መሥፈርትህ ከተበላሽ መሠረታዊውን ነገር ሳታይ ካጨህ ችግር ይፈጠርብሃል። በቅድሚያ ገንዘብ፣ መልክ ብቻ ከታየና በእነዚህ መሥፈርቶች መሠረት ከታጨ ኋላ ላይ ትዳራቸው መሠረት እንደሌለው ቤት ይሆናል፡፡ እነዚህ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸው።ረጅም ጉዞ አብረው የማይጓዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በጣም ሀብታም መርጦ አገባለሁ የሚል ሰው ያ ገንዘብ አንድ ቀን ቢጎድል ትዳሩ ባዶ ይሆንበታል። መልክ እየተገሳቆለ ቢሔድ ሊጎዳ ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች የግድ መኖር አለባቸው ማለት ተገቢ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ረጅም ርቀት አብረውን የሚጓዙ ነገሮች ደግሞ እሉ። ለምሳሌ ትዕግሥት፤ እምነት፤ ደግነት የምንላቸው የሰው ጠባያት ከሌላው ነገር ይልቅ ዘላቂዎች ናቸው። ከሀብት፣ ከንብረት ይልቅ ከሰው ጋር አብረው የሚዘልቁ እነዚህ ናቸው፡፡ ስለዚህ የበለጠ ትኩረታችን ወደ እነዚህ ነገሮች መሆን አለበት ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ እምነት፣ ተስፋ፥ ፍቅር፥ እነዚህ ጸንተው ይኖራሉ እንዳለ። ትኩረታችን በሚጸኑት ላይ መሆን አለበት፡፡ ፍቅር አለ ወይ? ይህ ግድ ነው።ፍቅራችን ራሱ መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ እንዳንድ ጊዜ ፍቅር የሚመስሉ ነገሮች ስላሉ ይሄንን በደንብ ማጥናት ያስፈልጋል። እምነት አለ ወይ? ማለትም ያስፈልጋልና፡፡ እምነት በሦስት ነገር ይገለጻል፡፡ አንደኛው እጮኛሞች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ነው። ሁለተኛ እርስ በእርሳቸው የሚተማመኑበት መተማመን ነው።ሦስተኛው ሁለቱ በግንኙነታቸው ፣በእጮኝነት ጉዟቸው ላይ ያላቸው እምነት ነው። ተስፋም ያስፈልጋል። ተስፋ ማለት በእግዚአብሔር ታምኖ በውጣ ውረድ ውስጥ ነገን በተስፋ መጠበቅ ነው። ይህ መሠረታዊ ነገር ካለ ቢያጠፋ ወይም ነገ ላስተካክላት እችላለሁ፣ ልገራት እችላለሁ፤ ተግባብተን ወደምንፈልገው አቅጣጫ እንደርሳለን ይባላል፡፡ ሀብት የለንም ሠርተን ልናገኝ እንችላለን፤ አልተማርንም ወደፊት ልንማር እንችላለን ማለትም ይቻላል። ይህ ተስፋ በምድር ብቻ የሚኖር አይደለም፡፡ ከዚያ አልፎ አብረን ጸንተን መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን እንዲሉም የሚያደርግ ነው።ሦስቱ መሠረታዊ ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ሰዎች ቍጭ ብለው ብዙ ነገር ማሰብ የለባቸውም፡፡ እኔ አንድ የማስታውስው ልጅ አለ። ወደ ሠላሳ የሚደርስ ዝርዝር ነጥቦች ያለው መሥፈርት (Criteria) አዘጋጀቶ መምረጥ ከጀመረ በርካታ ዓመታት አልፈዋል። የሚገርመው ይህ ልጅ እስከ አሁን /ውይይቱ አስከተካሔደበት ጊዜ/ አላገባም። እንዲህ ያለ ሰው እግዚአብሔርን ምንም እንከን የሌለው ሰው እንዲፈጥርለት መጠየቅ ነው ያለበት እንጂ፣ ፍጹም የሆነ ሁሉ የተሟላለት ሰው ለማግኘት አይችልም።
1.1.5. መንፈሳዊ ብስለት ተሳታፊ ቍጥር አንድ፦ መንፈሳዊ ብስለት ስንል አራት ነገሮችን ማለት ነው። 1.1.5.1. መንፈሳዊ እውቀት በሌላ መስክ ስለ ጋብቻ የሚባለውና በመንፈሳዊ ሕይወት ስለ ጋብቻ የሚባለው አንድ አይደለም። ለምሳሌ፡- ቤተ ክርስቲያን ውርጃን አትቀበልም፤ መንግሥት ይህን ሊቀበል ይችላል። መንግሥት አብረው ለሚኖሩ ሰዎች ዕውቅና ሊሰጥ ይችላል።ቤተ ክርስቲያን ያለ ቍርባን ለሚደረግ…
አላፊ ዓለም! 🌍 "ዘመኑ አጭር ሆኖአል ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሏቸው እንደሌላቸው ይሁኑ የሚያለቅሱሞ እንደማያለቅሱ፣ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዝችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነውና! ቅዱስ ጳውሎስ @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ከፀና ሃይማኖት ይልቅ ፍቅር ይበልጣል ሃይማኖት ኑሮህ ፍቅር ከሌለህ በሃይማኖቱ አትድንበትም! አባ ገብረ ኪዳን @Official_Dn_henok_haile @Official_Dn_henok_haile
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤” — ያዕቆብ 1፥19 @EOTC21_media @EOTC21_media
ሥነጽሑፍ - ግጥም ! ( ርዕስ - እመቤታችን ) በድንጋሌ ስጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች እመ አምላክ የህሙማን ፈውስ ንፅህት ወብሩክት እመ ብርሃን ሆይ በሃጥያት የነበረች አሻሮ ጥቀርሻ ሲኦል ሲያይ ልትሆን የቀራት አንድ አሙስ የቀራት ለሞት ብኩን ነፍስ የዋጣት የአጢያት ፅልመት እንደትጠራ ብለሽ ፍማ እንደ እነኰይ ጸዓዳ እንደ በረዶ ብሩ እንደ ፀሐይ ሆና ታበራ ዘንድ በአርያም ሰማይ ዕንባሽ እነባ ወልደ እነደ ጐርፍ ዥረት ሲቀንዠቀዠቅ ሲወርድ ከዓይኖችሽ ዕምብርት ምነኛ ርህሩህ ነሽ የኛማ እመቤት በዕንባ የምትዋጀኝ እኔ በድያት አለች አዲሷ ነፍስ ብርሃንሽን ተላብሳ ስትቀርብ በሐሴት ስትዘል እንደ እምቦሳ ኩሩቤል ሱራፌል ሚካኤል ወገብርኤል ነገደ መላእክት ቅዱስ ሰማዕታት ዕፁብ ድንቅ ዕፁብ ድንቅ የደግንት ባህር የርህራሄዋስ ዳር ድንበር ለሰው የላት ፍቅር ወሰኑ የት ይሆን ስፋቱ አይመጠን ምን ልክ አለው እና የርህራሄው ዳር ርህራሄን አይደል የአካልዋ ቅምር ሲሉ አመሰገኑት ቅድስት ወብርክት ቤዛዊት ኩሉ እህት መላእክት ለእስትንፋስ ልቧ ከተስፋ አንደበትዋ ምስጢር አዘነበች ሠርፃ ከዓይኖችዋ በብርሃን ተውቦ የድህነት ዚቅ መልዕክትዋ ሲነበብ ክፋትን አውልቆ ደግነት ማጥለቅ ቤዛዊተ ኩሉ የብርሃን እናት የስርየት መገኛ ፍኖተ ህይወት ባክሽ ማጡ ዋጡኝ ሃጥያት ተናነቀኝ ከገነት አፌ ዘልሎ ወሰደ አጠለቀኝ እንባ አጠለቀኝ ይቅር በይ በአማልጂኝ ልቄቂት ብርሃንሽን አይረቀኝ ይድረሰኝ መንጠቆ እንዳያወጣኝ የብርሃንሽ ክፋይ ሰናፍጭ ታክል ተወርውራ መጥታ ከልቤ መሀል አርፋ ብትቀመጥ ያበቃኝ ነበር የክፋት ግንዲላ በተሠረሠረ አውቀለውሁ ያን ግዜ ቀልሎት በርሮ የደስታ አክናፍ አውጥቶ ጠሻግሮ ቤዛዊተ ኩሉ እመ አምላክ ድንግል ፍቅርሽ በእኛለክቦ ሀዘን ይቅለል ፈሪያ እግዚአብሔር ማዕጣንት ሀገሬን እንዲያጥን “እባክሽ እመቤቴ”ባክሽ አትረቂን ዕንባሽ መፅናኛችን ይሁን መመኪያችን ይቅርታ ፀደል የምህረት ሙዳይ የርህራሄ ማህደር ገነት ሰማይ የዕውራን ብርሃን የህሙማን ምርኩዝ የትሑታን መቅረዝ የአርያም ምዕኩዝ እመ ክርስቶስ የድንግል ቤዛዊትተ ዓለም ባክሽ አትራቂን እመቤቴ ሆይ ሃጥያት ን መፍጨቱ ንሱ በቃ በይ ከመለጁ ስር ልማ እሪ ዋይ እያለች ነፍሳችን ቃተተች ድረሽልኝ ባክሽ ብለ ናፍቆት እየት ተርመጥመጣ ሁሌ ስትዋትት በዕንባሽ ተቤዣያት ባክሽን ታደጊያት ቤዛዊተ ኩሉ ቤዛዊት እንባል ፍቅር በረከትዋ እንድታድለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ! የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሣን የንጽሕተ ንጹሐን ድንግል ማርያምኀ እናትነት፣ ረድኤት፣ በረከት እና አማላጅነት በሁላችን ላይ አድሮ ይኑር። አሜን!! ✍️ዝምተኛው ገጣሚ /ⓟⓞⓔⓜ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ዝምተኛው ገጣሚ➩ @ort_poem ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️ ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት👍
1.1.5. መንፈሳዊ ብስለት ተሳታፊ ቍጥር አንድ፦ መንፈሳዊ ብስለት ስንል አራት ነገሮችን ማለት ነው። 1.1.5.1. መንፈሳዊ እውቀት በሌላ መስክ ስለ ጋብቻ የሚባለውና በመንፈሳዊ ሕይወት ስለ ጋብቻ የሚባለው አንድ አይደለም። ለምሳሌ፡- ቤተ ክርስቲያን ውርጃን አትቀበልም፤ መንግሥት ይህን ሊቀበል ይችላል። መንግሥት አብረው ለሚኖሩ ሰዎች ዕውቅና ሊሰጥ ይችላል።ቤተ ክርስቲያን ያለ ቍርባን ለሚደረግ ጋብቻ ዕውቅና አትሰጥም። እንግዲህ ጋብቻ መንፈሳዊ ዕውቀትን ይጠይቃል ማለት ነው። የልጆች አስተዳደግ መንፈሳዊ ዕውቀትን ይጠይቃል፤ የባል ድርሻ፣ የሚስት ድርሻ ምንድን ነው? ባልና ሚስት ችግሮቻቸውን እንዴት መፍታት አለባቸው? ማነው የችግራቸው የመጀመሪያ ተጠያቂ? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ "እናንተ ግን እንዴት እንደ ዓለማውያን ፍርድ ቤት ትቆማለችሁ ከመኻከላችሁ ሽማግሌ የላችሁምን?" እያለ ይወቅሰናል። /1ቆሮ6፥3-5/። ስለዚህ የመንፈሳውያን የችግር አፈታትና የሌሎቹ ይለያያል፡፡ እኛ ከአካባቢያችን ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረንና የሌላው ወገን ትምህርት ይለያያል። ስለዚህ መንፈሳዊ ዕውቀት ያስፈልጋል፡፡ 1.1.5.2. ራስን መግዛት እርሱ ወይም እርሷ ወደ ጋብቻ ከመግባታቸው በፊት ምን ያህል ራሳቸውን ይገዛሉ? ያ ማለት ጠባይን መግዛትኮ ጠባይን ማረቅ ማለት ነው። እስከ አሁን ድረስ ብቻህን በቤትህ ትኖራለህ፤ ወደ ጋብቻ ስትገባ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ስለዚህ እነዚያ ጠባዮችህን ለመገዛት ምን ያህል መንፈሳዊ ዐቅም አለህ፡፡ ይሄን በልምምድ ማዳበር አይቻልም። ራስህን የምትገዛው በመንፈሳዊ ብስለት ነው፡፡ ጋብቻ ማለት ልቅ ሕይወት አይደለም። አንድ ሰው አገባ ማለት ሚስቱን መቆጣት፤ መሳደብ፣ ማመናጨቅ፣ በኾነው ባልኾነው ማኩረፍ አለባት ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ የራስን ፍላጐት ለሌሎች ለመሠዋት፤ የእርሱን ፍላጐት ለሚስቱ ፍላጐት፥ የእርሷን ፍላጐት ለባሏ ፍላጐት ለመሠዋት፣ አንድ ሁኖ ከመወሰን ሁለት ሆኖ ለመወሰን ፈቃደኛ መሆን ነው፡፡ ሁለት ሆኖ ሲወሰን፣ የመወሰን ድርሻቸው ኀምሳ ኀምሳ ነው፡፡ ከባልና ከሚስት የአንዱ መቃወም ሁኔታዎችን ያፈርስዋል። በኋላ ደግሞ ነገሮች እየጠነከሩ በሚሔዱበት ጊዜ የልጆች መቃወም ውሳኔውን የሚያፈርስበት ጊዜ ይመጣል፡፡ባል መንፈሳዊ አባት ጭምር ነው።ሚስት መንፈሳዊ እናት ጭምር ናት።ሁለቱም ይህንን ደረጃ የሚያገኙት ራስን ከመግዛት በኋላ ነው፡፡ ራስህን አንተ ትገዛለህ፣ ራስህን ለእግዚአብሔር ታስገዛለህ፣ ራስህን ለሚስትህ ታስገዛለህ፡ ራስህን ለትዳርህ ታስገዛለህ፣ መንፈሳዊ ብስለት እነዚህን ዐቅም ማግኘት ነው። 1.1.5.3. ነገሮችን በቀናነት የማየት ችሎታ፦ በጎነት ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ “ዐይንህ መልካም ከሆነች ሰውነትህ መልካም ይሆናል" ማለት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ብስለት መንፈሳውያን ከሚባሉ ሰዎች ይጠፋል፡፡ ለምን? መንፈሳዊነት የምንለው ንስሐ መግባት፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል፣ ማስቀደም፣ መዘመር፣ መማር ብቻ ስለ ሚመስሉን ነው፡፡ እነዚህ ግን ብቻቸውን አይደሉም። እነዚህ በእኛ ሕይወት ውስጥ ለውጥ ማምጣት አለባቸው። ማምጣት ካለባቸው ለውጦች ደግሞ አንዱ በጎነት ነው፡፡ ሚስትህ ብትሳሳት በበጎ ታያታለህ ወይ? ባልሽ ቢሳሳት በበጎ ነው ወይ የምታዪው? በበጎ ማየት ማለት እኮ ሁልጊዜ ስሕተትን ብቻ ማየት አይደለም። አንደኛ፦ ሰው ነው፤ ሊሳሳት ይችላል በሉ /ሁለተኛ/ ምናልባትስ አሳስተውት ከሆነ፣ /ሦስተኛ/ የእኔ ዐይንስ ከሆነ /አራተኛ/ አቅቶትስ ከሆነ ማለት ነገሮችን በበጎ ለማየት መቻል ነው። ነገሮችን በበጎ ማየት ማለት አባቶች እንደሚያስተምሩት፡- /1ኛ/. ነገሮችን ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው፤ /2ኛ/ "የእሳት ፍሕም መከመር ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- “ ጠላትህ ቢራብ አብላው.... ያን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍሕምን ትከምራለህ" /ሮሜ12፥20/ እንዲል። ነገሮችን በበጎ ማየት ከሌለ በጣም ትንሽ ስሕተት መላ ቤተሰብን ታጨቃጭቃለች። እደውላለሁ ብሎ ሳይደውል ቢቀር፤ እመጣለሁ ብላ ሳትመጣ ብታረፍድ፣ አምሽቶ ቢመጣ ያልተናገረውን ቀጠሮ ቢይዝ፣ እነዚህ ትንንሽ ነገሮች ሁሉ በበጎ ካላየናቸው ሊያበጣብጡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ በአገራችን ይሄ ልማድ ባለመኖሩ ነው፣"ሚስቴ እንደምትመኝልኝ እንጂ እናቴ እንደምትመኝልኝ አትስጠኝ" የሚባለው፡፡ እናት ሁልጊዜ፡- "ልጄን መትተውት፤ ገድለውት ይሆናል ነው የምትለው፡፡ ሚስት ደግሞ፤ ተደባድቦ ይሆናል፣ ገድሎ ነው የሚመጣው ነው የምትለው።ይሄ አመለካከት ጥሩ አይደለም።እናት ብቻ አይደለችም እንደዚህ ማሰብ ያለባት፤ሚስተም ባልም እንደዚያ ነው ማስብ ያለባቸው። 1.1.5.4. ችግሮችን ሁሉ በመንፈሳዊነትና በመንፈሳዊነት ብቻ መፍታት በተቻለ መጠን ችግሮችን በመንፈሳዊነት፣ በመወያየት፤ ይቅር በመባባል መፍታት፣ እግዚአብሔርን መሐል በማድረግ መፍታት መቻል ነው፡፡ እስቲ ይለፍ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ነገ የሚያመጣው አይታወቅም ማለት ነው:: መንፈሳዊነት ችግሮችን ከመንፈሳውያን አባቶች ጋር በመመካከር በመንፈሳዊ አጥር ውስጥ ለመፍታት መሞከር ነው። 1.1.6. አካላዊ ብስለት አንድ ሰው በአካል የተስተካከለ አቋም ደረጃ ላይ መድረስ አለበት ሲባል ምን ማለት ነው? ተሳታፊ ቁጥር አንድ፦ ሁላችንም እንደምናውቀው አካላዊ ብቃት ከሥነ ልቡና፣ ከሰውነት ዕድገት ጋር የተያያዘ ነው።ሊቃውንት ለምንድን ነው "ከ18 ዓመት በታች አያግቡ" ብለው የሚከለከሉት? የሰውነት ብስለት ራሱ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ሕፃን ልጅ ጥርስ ሳያወጣ መብላት አይችልም።በእግሩ የማይሔድ ልጅ መሮጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ነገር አስቀድሞ ዕድገት ያስፈልገዋል። ለዚህ ነው ያለ ዕድሜ ጋብቻ የሚወገዘው። እንድ ሰው ሥነ-ልቡናው ማደግ አለበት።ከሕፃንነት ጨዋታ፣ ሁሉን ነገር እንደ ቀልድ ከማየት አልፎ ቍም ነገር የሚባለው ማወቅ አለበት።በገጠር እንደ ምንመለከተው ባሎች ዐዋቂዎች፤ ሚስቶች ደግሞ ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች ስለ ትዳር የሚያስቡት ስለ ጨዋታ በማሰቢያ ጊዜያቸው ነው። ነገር ግን ይህን ሓላፊነት ለመሸከም የሚያስችል አእምሮ የላቸውም።ሰውን ለማስተዳደር፣ ከሌላው ሰው ጋር ለመወያየት የሚችል የሥነ ልቡና ዝግጅት ያስፈልጋል፡፡ ከጋብቻ ጋር የሚያያዙ የሰውነት አካላት /የሥነ ተዋልዶ አካላት/ አሉ። እነዚያ በቂ መሆን መቻል አለባቸው፡፡ ከጋብቻ ጋር የሚመጡ ጉዳዮችን መሸከም፤ መፈጸም መቻል አለበት፡፡ አንዲት ሕፃን ልጅ በሕፃንነቷ ስትደፈር ሥነ-ልቡናዊ ጫና ይፈጥርባታል፡፡ አካሏ ያንን ለመሸከም የሚችል አይደለምና፡፡ ለመውለድ ዐቅም ያስፈልጋል፡፡ በኋላ ጋብቻ የሚያመጣቸውን ሓላፊነቶችን ለመሸከም የሚያስችል አካላዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ ብቃት ያስፈልጋል፡፡ ተሳታፊ ቍጥር ሁለት፦ በርግጥ የአካላዊ ብስለት ችግር ጎልቶ የሚታይ ብዙም የሚያነጋግር አይደለም፡፡ አንድ ሰው ለአካለ መጠን ሳይደርስ ማግባት የለበትም።ምክንያቱም ከሦስት የትዳር ዐላማዎች ሁለቱን ማሳካት የሚችለው ለአካለ መጠን ሲደርስ ስለሆነ ነው፡፡ ሁለቱን ስንል ፈቃደ ሥጋን መፈጸምና ዘር መተካት፣ ልጅ መውለድ የሚባሉት ናቸው፡፡ ቀጣይ ምዕራፍ አንድ ክፍል አስራ አንድ : 👉 "1.2 መተጫጨት..." በሚል ይቀጥላል ..... ለጥያቄና አስተያየት @EOTC21media JOIN አድርጉ👇 @EOTC21_media @EOTC21_media @EOTC21_media
. ስለ 1.1.2ጋብቻ ምን አውቃለሁ? ስለ ጋብቻ ምን አውቃለሁ የሚል ጥያቄ ማንሣትና መመለስ መቻል ያስፈልጋል። ጋብቻ ኑሮ ነው። በሕይወትህ እስከ መጨረሻ የምትኖርበት፤አንዴ ከወሰንክ እስከ መጨረሻ የምትወስንበት ነው፣ በትምህርት ዓለም እንኳን ለሁለትና ለሦስት ዓመት የምትማረውን ክፍለ ትምህርት /ዲፓርትመንት/ ዝም ብለህ መምረጥ የለብህም። ስለዚያ ክፍለ ትምህርት/ዲፓርትመንት/ በሚገባ ማወቅ አለብህ፤…
ምሥጢሬን ላካፍላችሁ " ምዕራፍ ፩ ክፍል ፲ ............................................................ የምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ 1. የቅድመ ጋብቻ ዝግጅት ማጠቃለያ 1.1.ቅድመ ጋብቻ ሊያደርጋቸው የሚገቡት ዝግጅቶች ምንድን ናቸው? 1.1.1. የራስን ሥነ-ልቡና መመርመር ተሳታፊ ቍጥር አንድ መጀመሪያ አንድ ሰው ማግባት የሚፈልገው ለምን እንደሆነ አስቀድሞ ትክክለኛ…
ምሥጢሬን ላካፍላችሁ " ምዕራፍ ፩ ክፍል ፲ ............................................................ የምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ 1. የቅድመ ጋብቻ ዝግጅት ማጠቃለያ 1.1.ቅድመ ጋብቻ ሊያደርጋቸው የሚገቡት ዝግጅቶች ምንድን ናቸው? 1.1.1. የራስን ሥነ-ልቡና መመርመር ተሳታፊ ቍጥር አንድ መጀመሪያ አንድ ሰው ማግባት የሚፈልገው ለምን እንደሆነ አስቀድሞ ትክክለኛ መልስ ማግኘት አለበት፡፡ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ማግባት ይፈልጋሉ፡፡ወላጆቻቸው ሲሞቱባቸው የብቸኝነት ስሜት ስለሚሰማቸው፣ ሚስት ካለኝ የጣፈጠ ምግብን ማግኘት እችላለሁ ብሎም በማሰብ፣ በኢኮኖሚ ከእኔ የተሻለ ነው ብሎ በማሰብ የሚያገቡ አሉ፡፡ ሌሎችም ደግሞ ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ ነው እኮ ማግባት አለብኝ፤ ብለው ብቻ የሚያገቡ አሉ፡፡ ወደ ጋብቻ የሚገቡትንም ሰዎች በማየት ብቻ የሚያገቡም አሉ።በአካባቢያቸው የሚነገሩ አባባሎችን፡ "ቆመ ቀር.... ወዘተ" የሚሉትን በመፍራት ወደ ጋብቻ የሚገቡ አሉ፡፡ ሌላው ደግሞ "ቤት አለኝ፤ መኪና ገዝቻለሁ፣ ጥሩ ሥራ አለኝ፣ የሚቀረኝ ትዳር ነው" ብሎ የሚያገባም አለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ትክክለኛ ምክንያቶች አይደሉም። አንዳንድ ጊዜ ከትዳር በኋላ ለሚከስቱት ችግሮች አንዱ ምንጭ እነኚህ ናቸው።ሙያዋን አይቶ ብቻ ወደ ጋብቻ የገባ ሙያዋ ሲቀየር ጭቅጭቅ ይጀምራል። ምክንያቱም በመጀመሪያ ወደ ትዳር የገባበት ዐላማ ችግር ስላለበት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ለምንድን ነው ማግባት የፈለግኩት? ስሜቴ ስለገፋፋኝ ነው? ወይስ ምንድን ነው ምክንያቴ? ማለት ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው በረከት አንዱ ጋብቻ ነው፡፡ እኔም እራሴን አዘጋጅቼ የዚህ በረከት ተሳታፊ መሆን አለብኝ፣ በጋብቻ የሚመጣውን በረከት ለመሳተፍ፤ የሚፈጠረውን ችግር ለመሸከም ብቁ ነኝ ወይስ አይደለሁም? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ይገባል። መወሰን የምችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁን? ወይስ ገና ነኝ፡፡ ልጆች አፍርቼ ቤተሰብ መሥርቼ መኖር የምችልበት የመንፈስ ጥንካሬ አለኝን? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል፡፡ አጋጣሚዎች በሚያመጡት ነገር ወደ ትዳር የሚገባ ከሆነ ችግር ስለሚፈጠር መጀመሪያ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
አልክድም መሆኔን ድኩም ስሉል ነኝ አልጠነከርኩም ከንብርክክ ተማፅኖዬ ጋር ከደጅህ አልተነጠልኩም። ° ተመልከት ከድቶ ሲተፋኝ ያያዝኩት ምርኩዝ ሲጠፋኝ ዘመመ ቅፅሬ ተናደ በወረት ክንዴ ታጨደ። ° እንግዲህስ ቀኜ ካራቀኝ የዋጥኩት መድህን ካነቀኝ ለብሼ ልብሴ ካረዘኝ በቁሜ ሰው ከገነዘኝ ይቅርብኝ መሸነጋገል አንተው ነህ የምታጸድቀኝ። ° አላዝን አልንገዳገድ ከንግዲህ ማንስ ቢረታኝ፣ ምን ቀረኝ ብዬ ዝላለሁ ሃይልህ ነው የሚያበረታኝ። ° @Zemari_Abel_Mekbeb @Zemari_Abel_Mekbeb @Zemari_Abel_Mekbeb
"ሰላም ለኪ ማርያም፣ ጸጋ የተመላሽ፣ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ በሴቶች ሁሉ መካከል ብፅዕት ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ብፁዕ ነው።" @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
በመንግስትህ ስትመጣ ቢያንስ ፈልጓል ብለህ መቃተቴን ቆጥረህ ከጎንህ አቁመኝ ! ምንም ባልጥር ፣ ምንም ተግባር ባይኖረኝ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ ጌታዬ፤ ካንተ በላይ ሌላ እንዳልፈለኩ ታውቃለህ። ያንተ ባለመሆኔ እኮ ከፍቶኝ ያውቃል ፣ አዎ በድዬሃለው እኮ ግን ደስ እያለኝ አይደለም ፣ እረስቼሃለው በብዙ ትቼሃለሁ ግን አውቄ አይደለም ተታልዬ ነው ! ቢያንስ አንዴ እንኳን እንደ ሰው አሳዝነኸኝ ታውቃለህ፤ የሆነ ቀን ላንተ እኮ ተሰብሬ አልቅሼ አውቃለሁ። ቢያንስ መፈለጌን አይተህ እባክህ ማረኝ ! ፈልጉ ታገኙኛላችሁ ብለሃልና በመፈለጌ ተገኝልኝ !
በጉጉት ስጠብቁት የነበረው ምስጢራዊ አደራ የሚል ድንቅ መንፈሳዊ ልቦለድ ክፍል 18 ስለቆየንባችሁ እንዴ መካሻ ከድሮው እረዘም አድርገን Post አድርገንላችኋል። ተለቋል በዚህ link በመግባት አንብቡ የተለቀቀበት ቻናል👇👇 ኑ Join አድርጉ👇👇👇 ____ @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16
" ከመናገርህ በፊት ÷ የምትናገረዉ ቃል ከዝምታህ የተሻለ መሆኑን መርምር ።'' - ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ - @EOTC21_media @EOTC21_media
መጣችልን እኮ ፍልሰታ ደረሰች እንኳን ደሳላችሁ እሰይ የምስራች❤️🥰 ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን 🙏 @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
አንድ ሴት እግዚአብሔርን ፈራሁ ካለች ክብሯን ጠብቃ ለስጋ ወደሙ መብቃት አለባት ። ስለዚህ እህቴ ሆይ አንድ ወንድ እንጂ ሁሉ የሚያገባሽ አይምሰልሽ ። በማስተዋል የምታደርጊውን ከማታደርጊው ፣ ፈጣሪ የሚፈቅድልሽን ከማይፈቅድልሽ በመመርመር ለዪ ። ለሁሉም ጊዜ አለው ትዕግስት ይኑርሽ ፡፡ ሰው አለባበስን እና ውበትን ያያል ። እግዚአብሔር ግን ልብ እና ኩላሊትን ይመረምራል ፡፡ የጥበብ ሁሉ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና እግዚአብሔርን በመፍራት ኑሪ ። @Official_Dn_henok_haile @Official_Dn_henok_haile
በዚህም ምክንያት በጥያቄው የተገለጠውና ወንድማችን ያነሡት የቅድመ ጋብቻ የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት በሥነ ልቡና ምሁራን በኩል ተቀባይነት እያጣ መምጣቱንም ማስተዋል ይገባል፡፡ አስቀድሞ በጣም አስፈላጊና ለትዳርም መሠረት እንደሆነ ይታመን ነበር። ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ግን ይህ አሳብ ተቀባይነት እያጣ መጥቷል፡፡ ቅድመ ጋብቻ የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት የፍቺን መጠንም ሆነ ከጋብቻ በፊት የሚፈጠረውን ችግር ለመቀነስ አልቻለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከትዳር በፊት የሚፈጠረው የሩካቤ ሥጋ ግንኙነቶችን ታወግዛለች፡፡ ስለዚህ እኅታችን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነትሽ ምንም ዐይነት ያልተረጋገጠና "ፈረንጅ'' ስለፈጸመው ብቻ ትክክል ነው የሚባል መረጃ ቢቀርብልሽ ልትቀበይ አይገባም፡፡ በዚህ ላይ ተቀብለው የተጓዙበት እነርሱም ምን ያህል የማኅበራዊና የመንፈሳዊ ኑሮ ቀውስ ደርሶባቸው እየተቸገሩ እንደሆነ ልታውቂ ያስፈልጋል።በተጨማሪም የእውነተኛ ፍቅር መሠረቱ ቅድመ ጋብቻ የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት አይደለም። እውነተኛ ፍቅር ላላቸውና እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ እርሱ የእርሷን እሷም የእርሱ እንደሆነች መገንዘብ ለሚችሉ ወጣቶች ቅድመ ጋብቻ የሚፈጸም የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት ፈጽሞ ሊያሳስባቸው አይገባም። ሁሉም ነገር በጊዜው ሊሆን ስለሚችል ምንም የሚያስቸኩል ነገር አይኖርምና። ለሁሉም እግዚአብሔር በዚህ ዐላማሽ አንጽቶ ከአሰብሽበት መልካም ነገር ያድርስሽ፡፡ ድንግልም አትለይሽ፡፡ ቀጣይ ምዕራፍ አንድ ክፍል ዐስር: 👉 "ቅድመ ጋብቻ ሊያደርጋቸው የሚገቡት ዝግጅቶች ምንድን ናቸው?..." በሚል ይቀጥላል ..... ለጥያቄና አስተያየት @EOTC21media JOIN አድርጉ👇 @EOTC21_media @EOTC21_media @EOTC21_media