መምህር እዮብ ይመኑ ትምህርቶች (Memihir Eyob Yimenu Timhrtoch)
СтатистикаDDAC846A ይህ መንፈሳዊ ገፅ በመምህር እዮብ የሚመራ አይደለም።የእሱን ትምህርት በሚወዱት የተከፈተ ነው። እዚህ ገፅ ላይ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርቶች ይተላለፉበታል።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 186
- 1/48двое суток
- 213
- 1/72трое суток
- 229
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
“የእግዚአብሔር ጆሮዎች ለመስማት ድምፅን የሚጠባበቁ ይመስላቸዋልን? እንዲህስ ካልሆነ ታዲያ የእነርሱ ጮኾ መጸለይ ጎረቤቶቻቸውን የሚያበሳጭ ነገር ከመሆን በቀር ሌላ ምን ጥቅም አለው?” ሊቁ ጠርጠሉስ፣ በእንተ ጸሎት @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
አላፊ ዓለም! 🌍 "ዘመኑ አጭር ሆኖአል ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሏቸው እንደሌላቸው ይሁኑ የሚያለቅሱሞ እንደማያለቅሱ፣ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዝችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነውና! ቅዱስ ጳውሎስ @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን!መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን።መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን።መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገርይሁን።እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔርበዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤” — ያዕቆብ 1፥19 @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋሰው "የሆዱን (የመብልን) ፍላጎት ማሸነፍ ያቃተው ሰው፣ የዝሙትንና የቁጣን መንፈስ አሸንፋለሁ ቢል፣ ገለባ ይዞ እሳትን አጠፋለሁ ብሎ እንደሚሮጥ ሰው ነው።" (ይህ ማለት ራስን መግዛት የሚጀምረው ከትንንሽ ነገሮች፣ ከምንበላውና ከምንጠጣው ነው።) @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
"ሰላም ለኪ ማርያም፣ ጸጋ የተመላሽ፣ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ በሴቶች ሁሉ መካከል ብፅዕት ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ብፁዕ ነው።" @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
በጉጉት ስጠብቁት የነበረው ምስጢራዊ አደራ የሚል ድንቅ መንፈሳዊ ልቦለድ ክፍል 18 ስለቆየንባችሁ እንዴ መካሻ ከድሮው እረዘም አድርገን Post አድርገንላችኋል። ተለቋል በዚህ link በመግባት አንብቡ የተለቀቀበት ቻናል👇👇 ኑ Join አድርጉ👇👇👇 ____ @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16
✨ ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሰርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል ፡፡ ወደ ሰርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሰርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል ፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች ፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው ፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም ፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል ፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
መጣችልን እኮ ፍልሰታ ደረሰች እንኳን ደሳላችሁ እሰይ የምስራች❤️🥰 ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን 🙏 @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ቅዱስ ቊርባንን ከመቀበል በፊት የሚጸለይ ጸሎት አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኵስት ከሆነች ከቤቴ (ከሰውነቴ) ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም፤ እኔ አሳዝኜሃለሁና፡ በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና፡ በአርአያህና በአምሳልህ የፈጠርከው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና፤ ሥራም ምንም ምን የለኝምና። ነገር ግን እኔን ስለመፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፤ ስለ ክቡር መስቀልህም፤ ማሕየዊት ስለምትሆን ስለ ሞትህ፡ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡ እማልድሃለሁም። የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልኩት ጊዜ ለወቀሳና ለመፈራረጃ አይሁንብኝ፤ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ። የዓለም ሕይወት ሆይ፡ በርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም፡ በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት፡ ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም፡ በሰማዕታትና ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን። መጽሐፈ ቅዳሴ፡ ቅዳሴ ሐዋርያት፣ ቁ. 110-112. ቅዱስ ቊርባንን ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፡ ንጹህ ሥጋህንና ክቡር ደምህን ተቀበልሁ፤ ለኃጢአቴና ለበደሌ ሁሉ ማሥተሥረያ ይሁነኝ። ሰውን የምትወድ ወልድ ዋሕድ ሆይ፡ ምስጋናህን በአንደበቴ ምላ፡ {ክብርህን} አመሰግን ዘንድ። ቀድሞ አንተ ሰው የሆንህ፡ በርሱም የተገለጽህ እስከ ዘለዓለሙ ታድነኝ ዘንድ ነውና፤ ስለ ቅዱስ ስምህም ለዘለዓለሙ አዳንከኝ። ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፡ በአገልጋይህ በካህኑ እጅ ሥጋህንና ደምህን አንድ አድርገህ ለሰጠኸኝ ለአንተ ምስጋና ይገባል። አመሰግንሃለሁ፡ እለምንህማለሁ፤ ከምእመናን ጋር አንድ እሆን ዘንድ ከበጎችህም ትቆጥረኝ ዘንድ ተቀበለኝ። አሁንም ኃጢአቴን አትቁጠርብኝ፡ ለእኔ የተሰጠኝን ጸጋህንና በእኔ ያለች ረድኤትህን አመሰግናለሁ። ዳግመኛም ጌታዬ ሆይ፡ ይህ የተቀበልኩት ሥጋህና ደምህ፡ ሥጋዬንና ነፍሴን እንዳያስነቅፍና እንዳያሳድፍ እለምንሃለሁ፡ እማልድህማለሁ፤ ፈጽሞ የሚያድነኝ አንተን መፍራትንም የሚያስረዳኝ ይሁን እንጂ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለአንተ አደላ ዘንድ ያለማቋረጥም አመሰግንህ ዘንድ። አቤቱ ነፍሴን አንጻት፡ ለአንተ መሥዋዕት ትሆን ዘንድ ዳግመኛም አጥራት፤ ልቤ እንዲድን መንፈስ ቅዱስ እንዲያድርበትና እንዲመላበት አድርገው። ሥጋህንና ደምህን አምኜ ከካህናቱ እጅ ተቀብዬአለሁና ለአንተ ምስጋና ይገባል፡ ለዘለዓለሙ አሜን። መጽሐፈ ቅዳሴ፡ ቅዳሴ ሐዋርያት፣ ቁ. 121-124፤ 146-147. @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ወንድሜ! ምንም ያህል ብትወድቅ፣ ምንም ያህል ብትሳሳት፣ ተስፋ አትቁረጥ። ወደ ንስሐ አባትህ ሂድና 'አባቴ ሆይ ደከመኝ እርዱኝ' በላቸው። እርሳቸው በሰጡህ ቀኖና መሠረት ቶሎ ብለህ ወደ ጌታህ ማዕድ ቅረብ። ቁርባን ለቅዱሳን 'ዘውድ' ነው፣ ለኃጢአተኞች ግን 'መድኃኒት' ነው። አንተ ደግሞ ዘውድ ባይገባህ እንኳ መድኃኒት በእጅጉ ያስፈልግሃል። በርታ! የሰይጣንን የ'አይገባህም' ወጥመድ ሰብረህ በንስሐ ወደ ጌታህ ሩጥ። @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ወደ ንስሐ ወደ ቁርባኑ ወደ መዝሙሩ ወደ ቅዳሴው ወደ ምህላው ወደ ማህሌቱ ወደ ሰአታቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ የሚል የልብ ወዳጅ መዳኃኔዓለም ያድላችሁ ይስጣቹ አሜን🙏 @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ሮሜ 12 ¹⁹ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ²⁰ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ²¹ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
"እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ይወዳል፤ በሰውየው ላይ የሚሠራውን ክፉ ሥራ (ኃጢአትን) ግን ይጸየፈዋል። ሐኪም የታመመውን ሰው እንደሚወድና በሽታውን ብቻ አጥብቆ እንደሚዋጋ፣ እግዚአብሔርም ኃጢአተኛውን ከሞት ለማዳን ኃጢአቱን አጥፍቶ ሰውየውን ሕያው ለማድረግ ይፈልጋል እንጂ ሰውን ፈጽሞ አይጠላም።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ይወደናል! @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
"የሰውን ጉድና ድክመት ይዞ መሮጥ የባሪያ ነፍስ ምልክት ነው። ሐሜተኛ ሰው የራሱን ቆሻሻ ቤት ረስተው የሌሎችን መስኮት በመጥረግ ይጠመዳል። የሌሎችን ስም የሚያጠፋ ሰው፣ የራሱን ክብር ከሰማይ ወደ ታች እየወረወረ መሆኑን ልቡ አያውቅም። ንጹሕ ሕሊና ያለው ሰው የሰውን ድክመት በዝምታ ይሸፍናል እንጂ በገበያ ውሎ አያወራም።" ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ፣ @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++ ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ። ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከአንድ ሳምንት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ። አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ። የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!! (*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።) @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ፀሎት ገንዘብን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ገንዘብ ግን ፀሎትን አያመጣም፡፡ ዜና አበው @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
ተከታታይ "ምሥጢሬን ላካፍላችሁ" ምዕራፍ 1 ክፍል 6 ተለቋል የማንበብ ፍቅር ያላችሁ ሁላችሁም እየገባችሁ አንብባችሁ LIKE SHARE አድርጉ ከተመቻችሁ እንቀጥላለን Comment ላይ ሀሳባችሁን ፃፉልኝ በዚህ ቻናል ነው የተለቀቀው👇👇 @EOTC21_media @EOTC21_media @EOTC21_media
መልካም ምኞት! የሰዎች ስኬትና ደስታ አያስቀናህ፤ ይልቁኑ አብረህ ደስ ይበልህ። ለሰዎች መልካም ስትመኝ፣ ያ መልካምነት ቀድሞ ወደ አንተ ቤት ይመጣል። ቅዱስ ባስልዮስ @Eyob_Yimenu @Eyob_Yimenu
በጉጉት ስጠብቁት የነበረው ምስጢራዊ አደራ የሚል ድንቅ መንፈሳዊ ልቦለድ ክፍል 17 ስለቆየንባችሁ እንዴ መካሻ ከድሮው እረዘም አድርገን Post አድርገንላችኋል። ተለቋል በዚህ link በመግባት አንብቡ የተለቀቀበት ቻናል👇👇 ኑ Join አድርጉ👇👇👇 ____ @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16 @Ethio_Orthodox16