tgindex
አስተምህሮ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

አስተምህሮ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Статистика
Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
1 737
−7 за 2 дн.
Сутки
−7
−0,40%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
956
20 постов
Вовлечённость
55,0%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
223
1/48двое суток
255
1/72трое суток
275

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ ✨ እንኳን አደረሳችሁ❣️🙏

  • “He is not here; for He is risen, as He said.” Matthew 28:6 May this holy feast of the Resurrection renew your faith, strengthen your love, and bring you closer to Christ and to one another. Christ is Risen! Truly He is Risen!✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ Happy Easter🙏

  • ''ጌታ የሰውን ጠላት ሞትን ድል የነሳበት ቀን ይህች ናት ''(ቅ.አርክዎስ)

  • 10 апр.1 017513

    13ቱ ሕማማተ መስቀል 1. ተአስሮ ድኅሪት (የኋሊት መታሰር) 2. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መጎተት) 3.ወዲቅ ውስተ ምድር (በመሬት ላይ መውደቅ) 4. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ እግርመረገጥ) 5. ተገፍኦ ማዕከለ ዓምድ (በዓምዶች መካከል መገፋት) 6. ተጸፍኦ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7. ተቀስፎ ዘባን (የጀርባ መገረፍ) 8. ተኮርዖተ ርዕስ (የራስ መመታት) 9. አክሊለ ሦክ (የእሾህ አክሊል) 10. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11. ተቀንዎ በቅንዋት (በችንካር መቸንከር) 12. ተሰቅሎ በዕፅ (በዕንጨት ላይ መሰቀል) 13. ሰሪበ ሐሞት (ሐሞት መጠጣት)፡፡ 5ቱ ጌታ የተቸነከረባቸው ችንካሮች 1. ሳዶር - ቀኝ እጁ የተቸነከረበት። 2. አላዶር - ግራ እጁ የተቸነከረበት፡፡ 3. ዳናት - ሁለት እግሮቹ የተቸነከረበት፡፡ 4. አዴራ - ደረቱን አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት፡፡ 5. ሮዳስ - ከወገቡ (እምብርቱን) አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት፡፡

  • без подписи

  • 8 апр.921310

    без подписи

  • በጨለማ ብርሃንን ሊይዙ ተማከሩ!!🥺

  • በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ  የውጭ ቃላት አሉ ቀጥታ ሳይተረጓሙ ከዕብራይስጥ፣ቅብጥ፤ግሪክ ቃላት ይገኛሉ። ኪርዬ ኤሌይሶን/ኪርያላይሶን/ ኪርዬ ማለት እግዚኦ ሲሆን ኪርያ ሲሆን ግን እግዝእትነ ይሆናል ኪርያላይሶን የምንለው በተለምዶ ነው እንጂ መባል ያለበት ኪርዬ ኤሌይሶን ነው ትርጉሙም አቤቱ ማረን ማለት ነው። እብኖዲ ማለት አምላክ ማለት ነው። ናይናን ማለት ማረን ይቅር በለን ማለት ነው። ታኦስ የግሪክ ቃል ሲሆን ጌታ አምላክ ማለት ነው። ማስያስ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ መሲሕ ማለት ነው  ትስቡጣ ማለት ዴስፖታ ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግ ገዥ ማለት ነው። ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። ክርስቶስ ማለት መሲሕ ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው። በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ ቀለሞች እንደ ሌላው ጊዜ ወጥ ከግዕዝ የመጡ አይደሉም ይልቁንሙ ከዕብራይስጥ ፣ ከሮማይስጥ ፣ ከግሪክ የተውጣጡ ናቸው። ቅዱስ ያሬድ ይህንን ያደረገበት ምስጢር ጲላጦስ ጌታን ካሰቀለ በኋላ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለውን ቃል በእነዚህ ቋንቋዎች ጽፎ በትራፈ መስቀሉ ላይ ጠርቆት ነበርና ያንን ለማስታወስ ነው።                                      መ/ር ነቢዩ ኤልያስ

  • без подписи

  • без подписи

  • በሰሙነ ሕማማት ኮከብ እስኪወጣ ድረስ ይጹሙ። በእነዚህም ጊዜያት አያጊጡ።

  • የቀጠለ.... እናንተም ቢቻላቹ  በህይወታቹ  ፍቅሩ ዘልቆ እስኪገባቹ  አንድም ጠቢባን እስክትሆኑ አለምም ይህንን ተግባረችሁን አይታ ሞኝ ሰነፍ እስክትላችሁ ከፊት ይልቅ አሁን በጸሎት ተቀዳደሙ(ትጉ) ነው  ። በምን  አይነት ፀሎት  ያልክ እንደሆነ እንደቀደሙት አባቶቻችን  በጽሞና (ብቻን በመሆን )'' ወጽሙናሰ እሙ ለቅድስና ይእቲ እንተ እምኔሃ ይትወለድ ጣዕመ አእምሮ ዘምስጢራተ እግዚአብሔር እንዲል'' ..( ከሰው መለየት የቅድስና እናት (መገኛ)ናትና ሰውን እግዚአብሔርን ወደሚያውቅበት ምስጢርም ታደርሰዋለች ..ይላል ሌላኛው ''አኑም ውስቴትየ አፍቅሮተከ'' በሉት ''ፍቅርህን አሳድርብኝ'' ከመ እፃዕ እም ዝንቱ አለም ..  ፍቅርህን ይዤ  በጽሞና ከዚህ አለም እለይ ዘንድ እርዳኝ በሉት የአንተ እውቀት ለአለም ሞኝነት ነውና በአለም ዘንድ አንተን መረጬ ሞኝ እባል ዘንድ ፍቀድለኝ በሉት ። ''ወንሕነኒ ንስአሎ ለእግዚአብሔር ልዑል  ከመ ንትባደር ወይረስየነ ድልዋነ ለዛቲ እበድ'' ''ለዚህች እበድ ለተባለች ፍቅሩ እንድንበቃ ያደርገን ዘንድ ክቡር እግዚአብሔርን እንለምነው።'' ይቆየን🙏.... ✍️@anu_yeab

  • ''ወይረስየነ ድልዋነ ለዛቲ እበድ'' (ለዚህች እበድ ለተባለች ፍቅሩ እንድንበቃ ያድርገን!) ይህንን ቃል በማር ይስሐቅ አንቀጽ 18 ላይ የምናገኘው ቃልነው ። ይህ ቃል ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር መድረስ እና የ ሐዋርያት ተግባራት እና የእምነት ጽናት ያብራራበት አንቀጹ  ነው እናም  አለም ደግሞ ስለነሱ የሃይማኖት ጥንካሬ የሰጠቻቸው ስያሜ የሚገልጽ  ነው። ሐዋርያት ምን አደረጉ ቢሉ (ወሰጠጡ):-ልብሰ ጣኦትን ቀደዱ አንድም ሕዝቡን ከባእድ አምልኮ አወጡ (ማቴ3÷7) (ወወለጡ) :-ተኩላውን ከመልክዐ አራዊት ለውጠው መልክዐ በግዕ አረጉት አንድም ክፉውን አሳዳጁን በትምህርታቸው መዓዛ ቸር የዋህ አማኝ አረገውታልና ። ''ወበእንተዝ እንዘ እሙንቱ ጠቢባን ዘአፍቀርዋ ለሥርዓት በቋዒት አመሰልዎሙ ከመ አብዳን ''የሐዋ 2÷13 ታድያ እነዚህን በጎ ስርአትን የወደዱ አዋቂዎች በፍቅሩ ጸንተው ቢያዩአቸው እንደ ሰነፍ ሞኝ ታዩ ።ይህስ ስንፍና ከሆነ እኛንም ለዚህ ስንፍና ያብቃን ሲል ወይረስየነ ድልዋነ ..አለ ።

  • ....መንፈሳዊ ህይወት ሊኖረን ይገባል ስንል በሁሉም የተሟላን ሆነን መገኘት አለብን ማለታችን  አይደለም!!'' እንደዛማ ከሆነ ምን ጎሎኝ ፈጣሪን ደጅ እጠናለው ወደሚል ትዕቢት ይመራናል።'' ቅድስና የሚገኘው ሁሌም የጎደለን እንዳለ በማሰብ ያ ደግሞ የሚሞላው በክርስቶስ አምላካችን ብቻ መሆኑን በማወቅ ሁል ጊዜ ወደእርሱ በመቅረብ ነው። ✍️@anu_yeab

  • በሰንበት ቀን  ሰው ስጋውን ብቻ ያሳርፍባት ዘንድ እንደ አይሁድ ተቀምጦ ሊያሳልፋት ፈጽሞ  አይገባም !ይልቅስ የዘለዓለም ማረፊያው የምትሆን መንግስተሰማይን ያገኝባት ዘንድ የሚያበቃ የትሩፋት ስራን ይስራ እንጂ!። ✍️@anu_yeab

  • 22 мар.1 297205

    ታማኝ አገልጋይ ማነው?   ''መኑ ውእቱ ገብረ ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኵሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብረ ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኀ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ።'' ትርጉም:-  ጌታው መልካም ሲሰራ አግኝቶት በገንዘቡ ላይ የሚሾመው ቸር እና ታማኝ አገልጋይ  ማነው ?!ዳግመኛም እግዚአብሔር በታናሹ የታመንህ ደግ እና ታማኝ አገልጋይ ሆይ በብዙ እሾምሃለሁ !ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ገብርሔር ማለት ታማኝ ፣ቸር ፣ለጋስ  አገልጋይ ማለት ነው ። ጌታችን በዚህ ክፍል ታማኝነትን እና የመታመንን በጎ ዋጋ የገለጠበት ደግሞም ስለ ገብርሃካይ (ክፉ አገለጋይ)ነት እና ውጤቱ በምሳሌ ያስተማረበት ነው። (ማቴ 25÷14) በዚህም  ትምህርት ..ምን ተቀብያለሁ የጸጋ ስጦታዬስ ምን  ይሆን ? ምን ያህልስ በተሰጠኝ መክሊት አተረፍኩ ?አቅሜን በሚያውቀው ጌታ ከተሰጠኝ ይልቅ ለሌሎች በተሰጠው ተማርኬ የኔን ቀብሬው ይሆን?? ጌታዬንስ አሳዝኜው ይሆን ? ብለን እራሳችንን የምንፈትሽበት እለት ነው። #ከምድር ላይ ታማኝነትን ከሚያጠፉት ወገን ከመሆን ተጠብቀን በተሾምንበት ነገር(በመክሊታችን) ታማኝ ሆኖ አትርፎ ማለፍን ገንዘብ እናድርግ። #ጸጋ ለሰጠን መታመን በምድር እያለን በሰማይ ለመኖር መሰረት መጣል ነው። ✍️@anu_yeab ቸር ቆዩ🙏✨

  • 8 мар.1 170101

    መዝ ፵፩፥፫—፬ “ እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ፡፡ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ:: አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፡፡” ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል። እኔስ አቤቱ ማረኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት አልሁ።”

  • 28 янв.1 470102

    ‹‹ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና›› በዕብራይስጥ ቋንቋ ሶልያና ማለት ጨረቃ ማለት ነው፤ ይህም መጠሪያ ለቅድስት ድንግል ማርያም ከተሰጡት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ✨እመቤታችን✨ ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ በአይሁድ ክፋት ብዙ መከራና ኃዘን ካሳለፈች በኋላ  በዘመነ ሉቃስ ጥር ሃያ አንድ ቀን በስድሳ ዐራት ዓመቷ ወደ ዘለዓለም ደስታ ትገባ ዘንድ ዐርፋለች፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዲ ብሎ እንደተናገረ... "ለአምላክ እናት ከዚህ አለም ህይወት ለንፅህናዋ በተገባ መንገድ ማለፍ እና ወደ ሰማያዊ ክብር መወሰድ ተገቢ ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ... ''ሕይወትን የወለደች እርስዋ ሞትን እንደ ቅጣት አልቀመሰችም በሰላም አንቀላፋች እንጂ ነፍሷንም ልጇ በእጁ ተቀበላት'' እንዳለ.... እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ።🙏 ✍️@anu_yeab

  • 7 янв.1 91475

    አዳም ሆይ መዳንህን ስታውቅ ምን ተሰምቶህ ይሆን ሄዋን ሆይ መድሀኒት እንተወለደልሽ ስታውቂ ምን ያህል ደስ ብሎሽ ይሆን በዚያን ጊዜ አማኑኤል መወለዱ ሲታወቅ በሲዖል ምን አይነት ደስታ ሆኖ ይሆን። ያንን ደስታ የምንደሰትበት በዓል ያድርግልን🙏 መልካም ገና ይሁንላቹ

  • 7 янв.1 62575

    ''ከህሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምስጢር አንክሮ ይገባል፤ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ስጋ ተዋሀደ የድንግሊቱንም ስጋ መረጠ '' ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም ✨ እንኳን አደረሳችሁ ❣️ ✍️@anu_yeab