tgindex
ከፍልስፍናው ጎራ <<❓>>

ከፍልስፍናው ጎራ <<❓>>

Статистика

<<ደስታን ምን እንደሚያካትት መፈለግህን ከቀጠልክ ፈጽሞ ደስተኛ አትሆንም..! የሕይወትን ትርጉም እየፈለግህ ከሆነ ፈጽሞ ሕይወትህን አትኖርም..! >> አልበርት ካሙ ለማስታወቂያ ሥራ➝ @Naolviva

Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
36 230
−150 за 4 дн.
Сутки
−24
−0,07%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 448
20 постов
Вовлечённость
4,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
449
1/48двое суток
514
1/72трое суток
554

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 6 авг.465236из phylosophy_gora

    በዜሮ ... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና "ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ "ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ  አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ  ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።   "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም  የተናኘ  ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው"  አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ  ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ  ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ  እያሳልኩ ዝም አልኩ። ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ  ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች።  መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ  መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ  የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ  ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው። አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣  የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው  የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን። @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

  • 4 авг.548104из habeshanhustles

    "በአእምሮህ ላይ ሙሉ ሥልጣን አለህ — ከውጭ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ ግን የለህም ይህንን እውነት ከተረዳህ፡ የማይበገር የውስጥ ጥንካሬ ታገኛለህ።" — ማርከስ ኦሬሊየስ (ሜዲቴሽንስ)    በቀላል አባባል ምን ማለት ነው? በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ነገሮች በሁለት ይከፈላሉ፡   ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮች፦  የአየር ጠባይ፣ የሌሎች ሰዎች አስተያየት ወይም ድንገት የሚፈጠሩ መጥፎ አጋጣሚዎች።      በእኛ ቁጥጥር ሥር የሆኑ ነገሮች፦ ለነገሮች የምንሰጠው ምላሽ፣ አስተሳሰባችን፣ ትዕግስታችን እና ቀጣይ እርምጃችን እና ውሳኔዎቻቻን በኛ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ነገሮች ብቻ ናቸው ።   ማርከስ ኦሬሊየስ ሊነግረን የፈለገው፡ እውነታ ይህን ይመስላል  አብዛኛው ጭንቀታችን የሚመጣው ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮችን ለመለወጥ ስንታገል ነው። በዙሪያህ የሚፈጠረውን ነገር ሁልጊዜ መቆጣጠር አትችልም፤ አእምሮህ ውስጥ የሚፈጠረውን ስሜትና ምላሽ ግን ሁልጊዜ የመቆጣጠር ሙሉ መብት አለህ።   ይህን አስተሳሰብ ካዳበርክ በ እርግጥም ውስጣዊ ጥንካሬን ታገኛልህ ፣ የውጫዊው ጩኸት ውስጥህን አይረብሸውም።   🎯 ለዕለት ተዕለት ሕይወት እንዲህ አድርገህ መተግበር ይኖርብሃል በአንድ ነገር ስትበሳጭ፣ ስትጨነቅ  ወይም ግራ ሲገባህ  አልፎም ህይወት ፈተናዎችዋን ስትልክብህ  ቆም በልና አእምሮህን ጠይቅ፡ ·  "ይህ ነገር በእኔ ቁጥጥር ሥር ነው?" ·  መልሱ "አይደለም" ከሆነ፡ ነገሩን ለመቀየር በመጨነቅ ጉልበትህን አታባክን። ይልቁንም ትኩረትህን ምላሽህ ላይ አድርግ። እውነተኛ ጥንካሬና የውስጥ ሰላም የሚገኘው እዚያ ላይ ነው።   በ አንተ ቁጥጥር ስር ከሆነ  ግን ተነስተህ ፍታው !   መቆጣጠር የማትችለውን ለመቆጣጠር ስትሞክር ብቻ ራስህን ስቃይ ውስጥ ድብርት ውስጥ እና ጭንቀት ውስጥ ትከታለህ ።   “ከማርከስ ኦሬልዬስ መዲቴሽን መጽሃፍ የተወሰደ “   ይህ መጽሃፍ በ አማርኛ ተተርጉሞ ቀርቧል ለመውሰድ በውስጥ አናግሩኝ   https://t.me/GREAT_ESKENDER

  • 17 июл.1 399288

    🔊▫️▪️▫️ ሰባተኛ ፎቅ ሰውየው ሰባተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ሆኖ ንፋስ ይቀበላል። አካባቢውን እየቃኘ እያለ አንድ ሰው ምድር ላይ ሆኖ እጁን ሲያውለበልብለት ይመለከታል። በድምፅ መደማመጥ ስላልቻሉ ምድር ያለው ሰውዬ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ያለውን ሰውዬ በምልክት 'ና' ይለዋል። ሰባተኛ ፎቅ ላይ የነበረው ሰውዬ ስለሰውዬው ማንነትና ስለፈለገው ነገር እያሰበ ከፎቁ ይወርዳል። የምድሩ ሰውዬ ጋር እንደደረሰም: ፎቅ ላይ የነበረው: "አቤት ወንድሜ ምን ፈልገህ ነው?" ምድር ላይ ያለው: ፊቱን አሳዛኝ ካደረገ በኋላ "ይቅርታ ጌታዬ አለፋሁዎት አይደል? ለማኝ ነኝ። እስኪ ስለ እግዚአብሔር ብለው ያለዎትን ይመፅውቱኝ" ሲለው ሰውየው ከሰባት ፎቅ ድረስ በቁም ነገር ወርዶ በሰማው ነገር እጅግ ስለተበሳጨ ለማኙን ካልገደልኩ ብሎ አስቸገረ። ትርምሱ በአገላጋዮች ከረገበ በኋላ ለማኙ ላይ እየዛተ ወደነበረበት ፎቅ ይመለሳል። እየተመለሰ እያለ ግን ለማኙ የምሩን ተቸግሮስ ቢሆን እያለ እያሰበ ነበር። መጀመሪያ የነበረበት ሰባተኛ ፎቅ ላይ ደርሶ ወደታች ሲመለከት ለማኙ አሁንም አንጋጦ ሲመለከተው ያያል። ተስፋ ቆርጦ በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ ያፏጭና ለማኙን ይጠራዋል። ለማኙ በደስታ እየተፍነከነከና የሰውዬውን ልብ ያራራለትን አምላክ እያመሰገነ ሰባተኛ ፎቅ ከወጣ በኋላ: ምድር የነበረው : እየተቅለሰለሰ "አቤት የኔ ጌታ?" ቢለው ፎቅ ላይ ያለው (ተለማኝ): "እግዚአብሔር ይስጥልኝ😊!!!" 🗞🗞🗞🗞 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 14 июл.1 20284

    "ራስህን በትክክል የምትወድ ከሆነ ሌላን የምትጎዳ አይነት ሰው አትሆንም "                           / ጉተማ ቡድሀ / ሰውን ለምን እንደሚጎዱ በሚጠየቁበት ሰአት #ሥለምወደው የሚል ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ስህተተኛ ብቻ ሳይሆን ሀሰተኛም ናቸው ። ሰውን ለመጉዳት የምንነሳው ስለምንወደው ሳይሆን የወደድነውን የራሳችን ብቻ ለማድረግ የሚገፋን ራስወዳድነት ሥለሚጫወትብን ነው። ፧ የወደድከው ነገር ሁሉ ያንተ ካልሆነ አጥፋው የሚል ስሜት ውስጥህ ካለ...ስሜትህ ውሸት ነበር ማለት ነው። ፍሬ ከናፍር እወደዋለሁ ያልከው ነገር ያንተነቱን እንጂ እሱነቱን አልወደድከውም ማለት ነው...። አንድን ነገር ስትወደው ተፈጥሮውን አድንቅለት...ነፃ አድርገው በቃ! ያንተ መሆን ያለመሆንን ምርጫ ለሱ ብቻ ተውለት...አንተ የመኖር መብት እንዳለህ ሁሉ የምትወደው ነገርም የመኖር መብት አለው...አንተ የመምረጥ መብት እንዳለህ ሁሉ የወደድከውም የመምረጥ መብት አለው...እዚህ መሀል ማስገደድ ካለ መውደድ የለም...!! ፧ የራስህን አስተሳሰብ ስርአት ባላስያዝክበት ሁኔታ ሌላ ላይ ጣትህን ለመጠቆም እንደማትበቃው ሁሉ ራስህን መውደድህን በትክክል ባላረጋገጥክበት ሁኔታም ሌላን ልትወድ አትችልም ። የፍቅርን ትርጉም የማያውቅ እና ራሱን አፍቅሮ የማያቅ ሰው...ሥላፈቀርኳት የሌላ ሆና ማየት ሥለማልሻ አጠፋኋት ሲል ባደባባይ ይዋሻል...ራስህን አትዋሽ...!! በትክክል ራሱን የሚወድ ሌላን የሚጎዳ ስብዕና የለውም...!! @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

  • 6 июл.1 4332016

    - አንተ ሰው ከየት መጣህ? - ከግብጥ - ምን ይዘህ? - ጭብጥ ጥጥ - በምን አስረህ? - በድጋይ ልጥ - ይህስ ሰው ዋዘኛ ነው! - ዋዘኛስ ክራር ነው - ክራርስ ጥዝ ጥዝ ባይ ነው - ጥዝ ጥዝ ባይስ ንብ ነው - ንብስ ነዳፊ ነው - ነዳፊስ ደጋን ነው - ደጋንስ ጠማማ ነው - ጠማማስ መንገድ ነው - መንገድስ ወሳጅ ነው - ወሳጅስ ውሃ ነው - ውሃስ ብም ብም ባይ ነው - ብም ብም ባይስ ጎሽ ነው - ጎሽስ ዘላይ ነው - ዘላይስ ፌቆ ናት - ፌቆ ስትዘል አግኝቼ በልቼ መጣሁ - ሰባች ጎፈየች? - ሳትታረድ መጣሁ - የሆነስ ሆነና ስምህ ማን ነው? - ላገር አይመች - ማን አወጣልህ? - ጎረቤቶች - የናትህ ስሟ ማን ነው? - ሳልወለድ ሞተች - የሆነስ ሆነና እግዚሀርን አይተኸዋል አላየኸውም? - አዎን አይቸዋለሁ - ቀይ ነው ጥቁር? - ተከናንቦ ነበር - ረጅም ነው አጭር? - ቁጭ ብሎ ነበር ስብሀት @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 5 июл.1 252142

    አስቄአቸው የማላውቅ እኔ ነኝ። ሲያወሩልኝ መስማት ብቻ። የሚወዱኝም በዚህ ነው። "እሱ ሰው ሲናገር ማቋረጥ አይወድም" እባልና። እኔ ግን ማውራት ስለሚደክመኝ ነው አፍ ፣ጥርስ፣ምላስ፣አገጭ፣ ጠቅላላ የፊት ጡንቻ፣ዐይኖች፣ግንባር፣እጅ ወዘተ....እነኝህን ሁሉ በአንድ ጊዜ አነቃንቄ ከእኔ ወደ ሌላ ሰው መረጃ ማስተላለፍ አድካሚ ነገር ይሆንብኛል። ያለማውራቴ ምክንያት ግን በተለያዩ ሰወች የተለያየ ትርጉም ይሰጠዋል:- አክስቴ: "መልኬ በቃኝ ብሎ ነው"እያለች ታሽሟጥጠኛለች። የወጣልኝ አጎዶ። አባባ: "ጨዋ ጨዋነት ነው" ይላሉ ጋሸ: "ትዕቢት ፤ ትዕቢት ነው" ይላል ጓደኛዬ: "መደበር ይወዳል ፣ ደባሪ ነው"ይላል የጓደኛዬ ሴት ጓደኛ : ኩራት። ኩራት ነው። ሲበጣጠስ" ትላለች የጋሸ ሚስት: ፍርሐት ፣ ፍርሐቱ ነው" ትላለች ብቻ ሺህ ትርጉም ይሰጠዋል።    (ህማማትና በገና) @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 5 июл.1 133162

    "በድሮ ጊዜ ቀስት ሲሰራ ቂጡ ላይ ለሚዛን ላባ ይገባለታል፡፡ እና አንድ ጭልፊት ጎኑን በቀስት ተመቶ ከሰማይ ላይ እየወደቀ እያለ ዞር ብሎ የተወጋበትን ቀስት ሲያይ፤ የራሱን ዐይነት ላባ ተሰክቶበት አየ፡፡ ገባህ? በወገንህ እጅ እንደ መጥፋት ቀላልና ከባድ ነገር የለም ማለት ነው፡፡" @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 30 июн.1 384141

    መዝሙረ ሄላም...

  • 29 июн.1 451172

    ተስፋ ተስፋ የመኖር ምክንያት ነው።ሰውን እንዲኖር የሚያደርገው ወይም የሚገፋው መለወጥ አለመለወጡ ሳይሆን የመለወጥ ተስፋው ነው።ቢሆንም ግን ህይወት ተከታታይ መሆኗን መገንዘብ ይጠቅማል።ዛሬ የምኖረው በትናንት ምክንያት ነው። 📓አለመኖር @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

  • 16 июн.1 790194

    <<የዘመኑ ወጣት የአእምሮ በር የለውም። ቢኖረውም የሚያስወጣ እንጂ የሚያስገባ አይደለም። ከራሱ ዓለም ሐሳብ አውጥቶ >> ያልኩት ካልሆነ ይላል እንጂ የሌላውን ሐሳብ አይመዝንም። ሲወለድ ጀምሮ ሁሉን አውቆ የተፈጠረ ይመስለዋል። <<ያለ ብዙ ችግር ያገኘውን እውቀቱን ተፎካካሪ የሌለው ኃይል ያደርጋል። በትንሽ እውቀት ብዙ ነገር ፈታትቶ የሚገጣጥም ይመስለዋል።>> (ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ) @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 15 июн.1 735132

    ጦርነት እየተካሄደ የሚያርስ ገበሬ "ለማን ነዉ?" ሲሉት "አላህ ለሰጠዉ ይሰጣል እኔ ከደረስኩበት እበላለሁ ካልሆነ ደሞ የሚመጡት ይበሉታል" አለ አርሶ ባዶ መሬት ከመተዉ ከዚህ በላይ ምን አሪፍ ሰዉ አለ @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 13 июн.1 8532112

    ሦስቱ ሴቶች የዘላለም መቆያቸው ሲኦል ይሁን መንግስተ ሰማይ ለማወቅ የተረኛ መላዕኩን ምዘና እየጠበቁ ነው። የመጀመሪያዋ  እንስት ቀረበች። በምድር ህይወቷ መነኩሲት ነበረች።  ተረኛው መላዕክ " በምድር ሳለሽ ምን ያህል ግዜ ዘሙተሻል ?"  ይላታል። "አንዲትም ግዜ አልዘሞትኩም። ገዳም የገባሁትም እንዲሁ እንደተፈጠርኩ አንዳች ነገር ሳላጎድል ነው። እዛም የሚፈታተነኝ ቢበዛም ግን ተወጥቼዋለሁ።" መላዕኩም  " ማነህ የ መንግስተ ሰማያትን ቁልፍ ስጣት።" በማለት ትዕዛዝ አስተላለፈ። ሁለተኛዋ ቀረበች "በምድር ህይወትሽ ምን ያህል ግዜ ዘሙተሻል?" "አንዳችም አልዘሞትኩም። ለአቅመ ሄዋን ስደርስም በወግ ማዕረግ ተዳርኩ። ከባሌ ጋር አራት ልጆች ወልደናል። ከአራት ግዜ ውጪ ከባሌም ከማንም ተነካክቼ አላውቅም።"  " የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ ስጣት" አለ መላዕኩም ሦስተኛዋ ቀረበች ። እጅግ የሚያምር አቋምና መልክ አላት። ንቃትና በራስ መተማመኗም የላቀ ነው። ጡቷን በከፊል የሚያሳይ የሙት ልብስና  የዳሌዋንም አስደንጋጭ ውበት የሚያጎላ ፒንክ ታይት ለብሳ ነበር። ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረበላት "በጣም በልጅነቴ ስለጀመርኩ ልከኛ ቁጥራቸውን በግልፅ አላውቀውም። ግን በምድር ህይወቴ ሳለው የወሲብ ቪዲዮ እሰራ ስለነበር ቢያንስ በሁለት ቀን አንዴ የግድ እዘሙታለሁ።" መላዕኩ እያያት ምራቁን ሲውጥ የምራቁ ጉምጉምታ ሰማየ ሰማያት ተሰማ። ከምራቁ እየታገለም  እንዲህ አለ። "ማነህ የክፍሌን ቁልፍ ስጣት!!" ማስታወሻ:  ለአሁናዊ የግል ህይወቱ ደህንነት ሲባል የመላዕኩ ስም አልተጠቀሰም። @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 10 июн.1 526152

    ሕይወት ዘላለማዊ ናት፣ አለመኖርን እንድንኖር ምርጫ እንኳን አልተሰጠንም  አብዛኛው ሰው ሞት አለመኖር ይመስለዋል  በተቃራኒው ግን ሞት ማለት መለየት ብቻ ነው ደግሞም ድልድይ ነው ወደ ትክክለኛ ሕይወት፤ @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 9 июн.1 757305

    ሩሲያ ውስጥ የሚማር የሌላ ሃገር ዜጋ አንድ ተማሪ እንዲህ ይላል፦ "በሩሲያ ውስጥ ለአብዛኞቹ ፈተናዎች ከፍተኛው ውጤት 5 ነው ፡፡ አንድ ተማሪ ማንኛውንም ጥያቄ ካልመለሰ እና የፈተና ወረቀቱን ባዶውን ከመለሰ፣ ከ5 ውስጥ 2 ያገኛል። በሞስኮ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ቀናት ውስጥ ስለዚህ ስርዓት አላውቅም ነበርና በመገረም ዶ / ር ቴዎዶር ሜድራቭን ጠየቅኩ፦ “አንድ ተማሪ ማንኛውንም ጥያቄ ሳይመልስ እርስዎ ከ5 ውስጥ 2 ሲሰጡት ይህ ፍትሃዊ ነው? ለምን ዜሮ አይሰጡትም? ትክክለኛው መንገድ እንደዚያ አይደለምን?" መምህሩ ሲመልሱ፦ "ለሰው ልጅ ዜሮን እንዴት መስጠት እንችላለን? ሁሉንም ትምህርቶች ለመከታተል ከጠዋቱ 1 ሰዓት ለሚነሳ ሰው ዜሮ እንዴት ልንሰጠው እንችላለን? በዚህ በቀዝቃዛ አየር ከእንቅልፉ ተነስቶ፣ የህዝብ ማመላለሻን ተጠቅሞ፣ ፈተናውን በወቅቱ ለማከናወን በመድረሱ እና ጥያቄዎቹን ለመፍታት ሞክሮ እንዴት ዜሮ እንስጠው?  ብዕር፣ የማስታወሻ ደብተር፣  የጥናት ኮምፒተር ገዝቶ ለብዙ ሌሊቶች ላጠና ሰው እንዴት ዜሮ እንሰጠው ??  ሌሎች የሕይወት ዘይቤዎችን ሁሉ ትቶ ትምህርቱን ሲከታተል ለከረመ ተማሪ እንዴት ዜሮ ልንሰጠው እንችላለን? ልጄ! እዚህ አንድን ተማሪ መልሱን ባለማወቁ ብቻ ዜሮ አንሰጠውም፡፡ እኛ ቢያንስ ይህ ሰው ነው ፣ እናም አንጎል አለው የሚችለውን ሞክሯል የሚለውን እውነታ ለማክበር እንሞክራለን፡፡ ምክንያቱም እኛ የምንሰጠው ውጤት በፈተና ወረቀቱ ውስጥ ላሉት ጥያቄዎች ብቻ አይደለም ፣ ይህ የሰው ልጅ ስለሆነ እና ነጥብ ማግኘት ለሚገባው ተማሪ እውነታ አድናቆት እና አክብሮት ማሳየትም ጭምር ነው።" @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 5 июн.1 632105

    እግርህ ስር የሚያደናቅፍህ ድንጋይ ተቀምጦ ዓይንህን ከድንጋዩ ለማሸሽ ብትሞክር ራስህን ማታለልህ በቅፅበት ይገለጥልሀል። ድንጋዩ የሚመታው ዓይንህን ሳይሆን እግርህን ነዋ! ብዙዎች ራሳቸውን በማታለልና በመሸንገል መንገድ ሲሄዱ እውነት እያሰናከለች ስትጥላቸው የምንመለከተውም ለዚህ ነው! @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 5 июн.1 744163

    без подписи

  • 3 июн.1 947184

    ከአልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ (በእውቀቱ ስዩም) በቀደም እኛ ሰፈር እሚገኘው  መሬት አስተዳደር ቢሮ ጎራ አልሁ ፤ ከአስተዳዳሪው ጠረጴዛ ላይ፥ ሜትር፥ ችካልና በሶስት ጎድጓዳ ሳህኖች የተቀመጠ ናሙና አፈር ተደርድሮ ይታያል፤ “ምን  እንርዳዎ ?” አለኝ አስተዳዳሪው፤ “ የሆነች ቀለል ያለች   አምስት ሺ ካሬ መሬት ፈልጌ ነበር “ “የገበሬ መሬት ነው የፈለጉት?” “ የወዛደርም ቢሆን አይደብረኝም፤” “ አዝናለሁ ፤ ለጊዜው የሚሸጥ መሬት የለንም’ ’   “ እኔም የሚሸጥ ሳይሆን የሚሰጥ መሬት ነው የምፈልገው “ “ምንስ ስለሆንክ ነው ላንተ መሬት የሚሰጥህ ?” ሰውየው  ካንቱ ወደ  አንተ የተሸጋገረበት ፍጥነት አስደነቀኝ ፤      ‘  እስካሁን ለናት አገሬ ካደረግሁት አስተዋጽኦ አንጻር ፤ መሬት ብቻ ሳይሆን ፥ የአየር ክልል ቢሰጠኝ አይበዛብኝም” ሰውየው ዘበኞችን ለመጥራት ስልኩን ሲያነሳ፥ ወደ መስኮት እየጠቆምኩ፥ “ እዛ ማዳ  ታጥሮ የበሰበበሰ መሬት ምን ይሰራል ?” “የወጣቶች የስራ ፈጠራ ማእከል ልንገነባበት ነው” አለኝ ፤ “ ከገነባችሁ በሁዋላስ?” “ አልባሌ ቦታ የሚውሉ ወጣቶች ወደ ማእከሉ እንዲገቡ ይደረጋል “ “እሺ  አልባሌውን ቦታ ለኔ  ስጡኝ “  2 በቀደም እኛ ሰፈር እኛ ሰፈር አስፋልት ዳር ያለ ስጋ ቤት ባለቤት ጫማ ያስጠርጋል፤ እኔ ወረፋ እየጠብቅሁ ነው፤ “ ቅድምኮ  የግብረሀይሉ አባላት ሱቄን  በሜትር ለከትውት ሄዱ” አለ ስጋ ሻጩ ፤ “  አይይ ! ሊያፐርሱት ነው ማለት ነው”  አለ ሊስትሮው ፤ “  ሊያፈርሱት እንደሆነ በምን  አወቅህ ?” “ ታደያ በሜትር የለኩት  ልብስ ሊያሰፑለት ነው?” @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 3 июн.1 34692

    ሁላችንም የሰራናቸውን ስህተቶች ለምን እንደፈፀምናቸው በቂ ምክንያት ለመስጠት እና ለማስረዳት የምንጠቀምበት ሀይል፣ትክክለኛ ነገሮችን ለመስራት ከምናውለው መብለጡ አስገራሚ ነው፡፡

  • 1 июн.1 807207

    አንዴ ጓደኛዬ ራሴን አጠፋለሁ ብሎ ተነሳ፡፡ ሁሉም ይመክረው ጀመር፡፡ ግን እሱ አሻፈረኝ አለ - ራሴን አጠፋለሁ አለ፡፡ ቤተሰቦቹ ጨነቃቸው፡፡ አባቱ እየሮጡ መጡና፣ “ይሄን ልጅ አልቻልነውም፤ ከእኛ አቅም በላይ ሆኗል…” አሉኝ፡፡ አባቱ አይወዱኝም ነበር አሁን ግን “ያለው ብቸኛ አማራጭ ይሄ ነው” ብለው አስበዋል… “ችግር የለውም እመጣለሁ” አልኳቸው፡፡ ቤታቸው ሄጄ ነገሩን ከሰማሁ በኋላ “ይሄውልህ…” አልኩት፣ “ሐሳብህ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ትክክል ነው ብዬ አላስብም፡፡ ቢሆንም ግን ራሴን አጠፋለሁ ብለህ ከተነሳህ መቼስ ምን ማድረግ እችላለሁ፡፡ ጓደኛዬ ስለሆንክ ረዳሃለሁ፡፡ ራሴን ካላጠፋሁ ካልክ - ጥሩ !! ውሳኔህ ትክክል አይመስለኝም ምክንያቱም እኔ ባንተ ቦታ ብሆን ጨርሶ ራሴን አላጠፋም ነበር፡፡ ምክንያቱም ሞኝነት ነዋ፡፡ አንዲት ሴት እምቢ ስላለችህ ራስህን ታጠፋለህ ? በሚሊየን የሚቆጠሩ ሴቶች እያሉ አንዲት ሴት እምቢ አለችኝ ብለህ ራስህን ማጥፋት ተገቢ ውሳኔ አይደለም፡፡ በወር ውስጥ ረስተሃት ሌላ ማፍቀርህ አይቀርም ነበር፡፡ ግን ራሴን አጠፋለሁ ካልክ ምን ማድረግ ይቻላል … ጥሩ !! የራስህ ሕይወት የራስህ ነው…” አባትዬው ይህን ሲሰሙ በጣም ተረበሹ፡፡ “ጭራሽ ራስህን አጥፋ ትለዋለዋህ እንዴ … እኛ እኮ ያመጣንህ ይሄን ሐሳቡን ታስተወዋለህ ብለን ነው” አሉ አባትዬው፡፡ “እኛ ምን ስለሆንን ነው የምንረዳው ? እርስዎ ሲወልዱት ጠይቀውታል እንዴ … ወደዚህች ምድር መምጣት ትፈልጋለህ ወይ ብለው ጠይቀውት ነበር ? እና አሁን ለምንድነው ራሴን ላጥፋ ሲል የምትከለክሉት ? ራሴን ላጥፋ ካለ ፍቀዱለት” ወደ ቤቴ ይዤው ሄድኩ… “ና እንሂድ … ራስህን ልታጠፋ አይደለ እስኪ እስከዛው ዘና እንበል፡፡ እንዝናና፡፡ እስቲ አንድ ለሊት አብረን አናሳልፍ፡፡ እኔጋ እድር፡፡ ምናልባት የሆነ ቦታ እንገናኝ ይሆናል ምናልባትም ከዚህ በኋላ መቼም ላንገናኝ እንችላለን” አልኩት፡፡ እኔ ቤት ሆነን ቀስ በቀስ ማሰብ ጀመረ፡፡ ምክንያቱም እኔ በምንም መልኩ ሀሳቡን ለማስቀየር አልፈለግኩም፡፡ “አሁን የሚጮህ ሰዓት እንሙላና እንተኛ…” አልኩት፣ “ሌሊት 10 ሰዓት ሲሆን ተነስተን አንድ የሚያምር ቦታ እወስድሃለሁ፡፡ በጣም የሚያምር ቦታ ነው፡፡ ከዚያ ቦታ ላይ በቀላሉ ዘልለህ ወንዙ ውስጥ መፈጥፈጥ ትችላለህ … ከእኔም ጋር እዛው እንሰነባበታለን” ልክ 10 ሰዓት ላይ ሰዓቱ ሲጮህ ከአልጋው ጎትቼ ሳስነሳው፣ “አንተ ቆይ ምን አረግኩህ…” አለ ጮሆ፤ “ጠላቴ ነህ ወይስ ምንድነው ? በቃ ራሴን ማጥፋት አልፈልግም !!!” “ይሄማ ትክክል አይደለም … አንዴ ወስነህ የለ እንዴ … የምን መወላወል ነው” “እንዴ በቃ ራሴን አላጠፋም !!! እንድሞት ፈልገህ ነው … አልሞትም … በቃ … አልፈልግም … ራሴን አላጠፋም … ሕይወቴን እወዳታለሁ” “እምቢ ካልክ አላስገድድህም” አልኩት… እናም ራሱን አላጠፋም !!! አሁን አግብቶ ልጆች ወልዷል፡፡ መንገድ ላይ ካየኝ መንገድ አሳብሮ ነው የሚጠፋው፡፡ “አሁን ምን ተገኘና ነው” እለዋለሁ መንገድ ላይ ሳገኘው፣ “መቼም አላፈቅርም ብለኸኝ አልነበረም እንዴ … እንደገና አፍቅረህ አረፍከው !!!” እሱም እንዲህ ይለኛል፣ “በዕውነቱ እንኳንም ያቺ ልጅ እምቢ አለችኝ፡፡ ለእኔ አትሆነኝም ነበር፡፡ ታሳብደኝ ነበር፡፡ እኔ አሁን የተሻለች ልጅ ነው ያገባሁት …” @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊

  • 27 мая1 5559

    🙏ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ለኢድ አል አድሃ [አረፋ] በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❤️ EID MUBARAK 🕋 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 @phylosophy_gora🇪🇹 ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን...😊