- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 27
- Всего постов
- 360
- Тип
- открытый
- Язык
- турецкий
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 231
- 1/48двое суток
- 264
- 1/72трое суток
- 285
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
በውል እርሻ የሚገዛ ምርት ከፍያው በኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) በኩል መፈጸም አለበት ተባለ “ክፍያው በECX በኩል እንድትፈጽሙ መባሉ ግራ እጋብቶናል” ላኪዎች ተጨማሪ ያንብቡ https://shorturl.at/tgfvj #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia #ECX #ContratctfarmingEthiopia #MinisteroftradeandRegionalintegration #KasahunGofe
ፋኦ ከኤልኒንዮ አደጋዎች 4.66 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ 50 ሚሊዮን ዶላር አጣዳፊ ጥሪ አቀረበ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) በኢትዮጵያ በኤልኒንዮ ክስተት ሳቢያ የተከሰተውን የግብርና እና የሰብአዊ ቀውስ ለመከላከል 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አጣዳፊ የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አቅርቧል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ ከሰኔ 2026 እስከ መጋቢት 2027 ባለው ጊዜ ውስጥ 4.66 ሚሊዮን ተጋላጭ ዜጎችን ለመደገፍ የታለመ መሆኑ ተጠቁሟል። የሚጠበቀው የኤልኒንዮ ክስተት በሰኔ-መስከረም የክረምት ወቅት በሀገሪቱ ማዕከላዊ፣ ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ክፍሎች ድርቅ ሊያስከትል ሲችል፣ ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት ደግሞ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ከባድ የጎርፍ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ትንበያዎች ያመለክታሉ። ከሀገሪቱ የገጠር ቤተሰቦች መካከል 82 በመቶ የሚሆኑት በግብርና ላይ ጥገኛ በመሆናቸው፣ የሚጠበቀው የአየር ንብረት መዛባት የሰብል ምርትንና የእንስሳት ሃብትን በእጅጉ አደጋ ላይ ይጥለዋል። ፋኦ አስቸኳይ የቅድመ-ዝግጅት እርምጃዎችን በመተግበር የህዝብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና ድርቅ እና ጎርፍ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጉዳቶች ለመቀነስ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia
በናይሮቢ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ በቤት ኪራይ እጥረት ተዘጋ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ በናይሮቢ የሚገኘው ቢሮው ከአራት ወራት በላይ የቤት ኪራይ ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት መዘጋቱ ተገለጸ። በኪሊማኒ ሰፈር የሚገኘው ይህ ኤምባሲ መዘጋቱ በኬንያ የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያን አገልግሎቶችን እንዳያገኙ አድርጓል። የጁባ መንግሥት ጣልቃ እስኪገባና እዳው እስኪከፈል ድረስ ኤምባሲው ተዘግቶ እንደሚቆይ ተዘግቧል። በዚህም ምክንያት የጉዞ ሰነዶችን ለመውሰድ የመጡ ዜጎች በጸጥታ ሰራተኞች መመለሳቸው ተሰምቷል። የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃናት እንደዘገቡት ኤምባሲው ባለፈው ህዳር ወር 2025ም ችግር አጋጥሞት ነበር። አሁን የተፈጠረው መስተጓጎል የደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ በነዳጅ ላይ ብቻ ጥገኛ በመሆኑ የተከሰተውን ጥልቅ የፊስካል እና የገንዘብ ዝውውር ችግር የሚያሳይ ነው ብለዋል። #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia
без подписи
ቅዳሜ ገበያን በቴሌግራም ያዳምጡ ነሐሴ 8/12/2018 ርዕሰ ጉዳይ 👉 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በሚቀጥሉት 25 መታት ምን ለመስራት አቅዷል መሪ ዕቅዱ ምን አካቷል ❓ ሰፊና ጥልቅ ትንታኔ ይዘናል ‼️ 👉 የብሐራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ጨረታና የባንኮች ፍላጎት መናር ‼️ #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia
አዲሱ የቢሾፍቱ ግዙፉ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ የአሜሪካና ቻይና ፉክክር ዉስጥ አስገብቷል ተጨማሪ ያንብቡ https://h1.nu/1BEpb #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia #Bishoftumegaairport #Ethiopianewairportproject #USChinarivalryEthiopia #EthiopianAirlinesmegaproject #Bishoftuairporttender #Africalargestairport #USChinageopoliticsAfrica #AbbaSamuelairportproject #BoeingEthiopianAirlines #ChinaroadandbridgecorporationEthiopia #Africanaviationnews #Ethiopiainfrastructuredevelopment
ማልደው ባይነሱ፤ በአባ ይደርሱ ዓለም አቀፍ የአየር ትኬት ክፍያዎን በአባ ሞባይል ባንኪንግ ይፈጽሙ! አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር! የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች Website|Facebook|Telegram|Instagram|Twitter|LinkedIn|YouTube #አማራባንክ #AmharaBank
без подписи
ቅዳሜ ገበያን በቴሌግራም ያዳምጡ ነሐሴ 6/12/2018 ርዕሰ ጉዳይ 👉 የብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት በሰዓት ገደብ ከፍተኛ ገንዘብ እየተበደሩ ነው‼️ ምክንያቱ ምን ይሆን ❓ 👉ለሚያበድሩት ምን ያህል ወለድ እያስከፈሉ ነው❓ 👉 በአነስተኛ ባንኮች ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እያሳደረ ነው❓ ሰፊና ጥልቅ ትንታኔ ‼️ 👉ብሐራዊ ባንክስ ምን ይላል❓ ምላሹን ይዘናል‼️ 👉 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአዲሱ በጀት አመት ጨረታ ‼️ #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia
የብሪክስ አባል ሀገራት የክፍያ ስርዓቶችን እና ዲጂታል ገንዘቦችን ለማገናኘት መወያየታቸው ተሰማ የብሪክስ አባል ሀገራት ፈጣን የክፍያ ስርዓቶቻቸውን እና ማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘቦችን (CBDC) እርስ በእርስ ለማገናኘት መወያየት መጀመራቸውን የህንድ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ሳንጃይ ማልሆትራ አስታወቁ። በሙምባይ በተካሄደ ዝግጅት ላይ ንግግር ያደረጉት ገዥው ፣ የድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች ወጪን በእጅጉ መቀነስ ለሁሉም አባል ሀገራት ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ላይ የተለያዩ አማራጮች በውይይት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የዲጂታል ገንዘቦች ትስስር እና የፈጣን ክፍያ ስርዓቶች ውህደት ከቀዳሚ አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ ብለዋል። ዘንድሮ የብሪክስ ስብሰባን ያስተናገደችው ህንድ፣ የዲጂታል ገንዘቦች ትስስር ሀሳብ በጉባኤው አጀንዳ ውስጥ እንዲካተት ቀደም ሲል ለሀገሪቱ መንግስት ማቅረቧ ይታወሳል። ከዚህም ባሻገር የሩፒን አለም አቀፍ ተቀባይነት ለማሳደግ እና የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን በድንበር ተሻጋሪ ንግድ ውስጥ ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም) 👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል። #𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲
Ethiopia’s sesame market is witnessing a notable price surge, with Humera sesame reaching a record 21,000 birr per quintal at the Ethiopian Commodity Exchange (ECX) on August 12. The latest increase reflects stronger market prices amid supply constraints, security challenges and growing competition in the international sesame market. https://url-shortener.me/P4ZD #Ethiopia #Sesame #Agriculture #ECX #EthiopianCommodityExchange #Agribusiness #AgriculturalExports #ExportMarket #CommodityMarket #HumeraSesame #EthiopianExports #FoodSecurity #EconomicReform #EthiopianEconomy #AgricultureNews
без подписи
ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ተጨማሪ ያንብቡ https://shorturl.at/YCffw #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiop #sesame #Ethiopiasesam #Humerasesame #Wollegasesame #EthiopianCommodityExchange #ECX #Sesameprice #Sesameexport #Ethiopiaexports #Agriculturalcommodities #Oilseeds #Agriculturecommoditymarket #exportearnings #Ethiopianagriculture #Sesamefarmers #Sesameproduction #Internationalsesamemarket #Economicreform #agriculturalexports
ብር በ3 በመቶ ተዳከመ ዛሬ በተካሄደው የበጀት አመቱ የመጀመሪያ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የዶላር ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንና ብር በዶላር ፊት የበለጠ መዳከሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው የጨረታ ውጤት አሳይቷል። ለዝርዝሩ https://shorturl.at/NH49y #etbusinessview #Ethiopia #ቅዳሜገበያ #ForexAuction #EthiopianBirr #ForeignExchange #EthiopiaEconomy #NBE
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም) 👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል። #𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲
የዓለም የምግብ ዋጋ በሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ በግብርና ምርቶች አቅርቦት ላይ እየጨመረ የመጣውን ስጋት ተከትሎ የዓለም የምግብ ዋጋ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ታይቶ ወደማታውቀው ከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡ ተገለጸ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋእ) የምግብ ዋጋ መረጃ ጠቋሚ በሐምሌ ወር 0.6 በመቶ ማደጉን አስታውቋል። ይህ ጭማሪ በዋናነት እንደ እህል፣ ስኳር እና የአትክልት ዘይቶች ባሉ ቁልፍ የንግድ ዕቃዎች ላይ በታየው ከፍተኛ የዋጋ ንረት የተከሰተ ነው። በጥቁር ባህር ክልል ውስጥ እየተባባሰ የመጣው የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ወሳኝ የኤክስፖርት መስመሮችን በማስተጓጎሉ፣ ዓለም አቀፍ የስንዴ ዋጋ ከዓመት ዓመት በ10 በመቶ ገደማ እንዲጨምር አድርጓል። በተመሳሳይ, በአውሮፓ የከረረ ሙቀት እና በአሜሪካ ኮርን ቤልት አካባቢ ያለው የማያቋርጥ ድርቅ የምርት ማከማቻ አዝማሚያዎችን እየጎዳው ይገኛል። የአቅርቦት ሰንሰለት ተጋላጭነቶች መቀጠላቸው ለገበያ ተንታኞች ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ መጪው ኤል ኒኖ ክስተት፣ ከፍ ያለ የኃይል ዋጋ እና የማዳበሪያ እጥረት ተዳምረው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሸማቾች ላይ ቀጣይነት ያለው የዋጋ ግሽበት ግፊት እንደሚፈጥሩ ተመላክቷል። #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia #FoodPrices #GlobalFoodCrisis #FAO #Inflation #Agriculture #SupplyChain #ClimateChange #Geopolitics #ElNino #GlobalEconomy
በሞምባሳ ወደብ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አዋጭነት ለመፈተሽ አዲስ ጥናት ሊጀመር ነው የምስራቅ አፍሪካን የንግድ መስመር ከሆኑት ዋና ዋና ማዕከላት አንዱ በሆነው የሞምባሳ ወደብ ውስጥ የዲዝል መኪኖችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመተካት አዋጭነት የሚያጠና አዲስ መርሃ ግብር ሊጀመር ነው። ይህ እርምጃ የተወሰደው በኮሪደሩ ላይ ያለው የጭነት ማጓጓዣ መጠን እያደገ በመምጣቱና ተያያዥ የሆነው የካርቦን ልቀት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነዉ ተብሏል። ለዚህ ስራ ስኬት የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ መርሐ ግብር 190,000 ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል ። በጥናቱ ሰፊ ተሳትፎ ከሚያደርጉት መካከል የሰሜኑ ኮሪደር የትራንስፖርት አስተባባሪ አካል እና የኬንያ ወደቦች ባለስልጣን ይገኙበታል። ጥናቱ በወደቡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ አማራጮች ለመተካት ያለውን ቴክኒካዊ አዋጭነት ይመረምራል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ጥናት የምስራቅ አፍሪካን የንግድ መስመር ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለማዘጋጀትና እስከ 2050 የተጣራ የካርቦን ልቀት መጠን ወደ ዜሮ ለማድረስ ለታለመው አረንጓዴ የትራንስፖርት ስትራቴጂ መሰረት የሚጥል ነዉ ተብሏል። #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia #MombasaPort #ElectricVehicles #GreenTransport #SustainableLogistics #EastAfricaTrade #UNEP #NetZero2050 #EcoFriendlyShipping #KenyaPorts #CleanEnergy
አማራ ባንክ የቁጠባ ወለድ ምጣኔን እስከ 9 በመቶ አሳደገ ተጨማሪ ያንብቡ https://shorturl.at/RFLYI #ቅዳሜገበያ #etbusinessview #Ethiopia #AmharaBank #AmharaBankEthiopia #EthiopianBanking #EthiopiaFinance #BankingSectorET #InterestRates #NationalBankOfEthiopia #NBE #EthiopiaEconomy #MonetaryPolicy #EthiopiaBusiness #EthiopianNews #AddisAbabaBusiness #EthiopiaBiz