ĥáĺŵá quotes✍🧕
Статистикаአመታት ወይም ቀናት ሊወስድ ይችላል .... ግን አላህ ሲፈቅድ ሁሉም ነገር ቦታውን ይይዛል ❤️🩹
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 133
- 1/48двое суток
- 152
- 1/72трое суток
- 164
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
. የሆንኩትን አልወደውም ፤ ግን መሆን የምፈልገውን አላውቅም ። ግራ ገብቶኛል ። ልክ የሆነ ቦታ ሊሄድ ፈልጎ ከቤቱ እንደወጣ ተጓዥ ፣ ከዛም መዳረሻው እንደጠፋበት ፤ እንደዛ ነው የሚሰማኝ ። የምመኘው ብዙ ነው ፤ ልይዘው የምፈልገው ብዙ ነው ፤ የማሳደው ብዙ ነው ፤ የምይዘው ግን የለም ።❤️🩹
. እስልምና አስተምሮኛል ሰውን የምትጎዳ ሳትሆን ሰዎች የሚጎዷት መሆን እንደሚሻል የፍጡራንን ልብ ከሰበርኩ ቡኋላ በአላህ ፊት ከመቆም የተሰበረ ልብ ይዤ በአላህ ፊት መቆምን እመርጣለው ❤️🩹
እኔኮ እነሱ መልሰው ማወራት እንዳይችሉ ህብለሰረሰር የሚነካ አፋቸውን ዝም እዲል የሚያደርግ ከ 1ም ብዙ ነገር እኮ አቃለሁ ወረቢ ግን ዝም ሲባሉ ተፈረተዉ እንጂ ለስሜታቸው ተጨንቄ አይመስላቸውም 😏
ብዙ ህመም አለ ቀን በቀን ሚፀና ውስጥህን የሚበላ አስመስሎ ደህና፤ ብዙ ማጣት አለ በሳቅ የሚሸፈን ከፊት ለፊት ደምቆ ከውስጥ የታሰረ በብቸኝነት ከፋን፤ ብዙ እንባ አለ አባሽ የናፈቀው ሰው ማጣት ብቻ ቀኝ ሌት የሚያወርደው። ብዙ ብዙ..............
без подписи
. ያማረ ውዴታ ማለት አሏህ ለመላኢኮች ባለ ግዜ ነው " እገሌን ወድጀዋለሁና ውደዱት " …..🌸 ያ ሰላም 🫠
. The feeling... ደስተኛ አደለንም ደሞም አልከፋንም በቃ it just empty and tired of በሁሉም ነገር❤️🩹
Coffee doesn't fix everything— but it helps. It won't solve your problems, but it'll sit with you while you figure things out. Sometimes, that's enough; a little warmth, a little hope, and one more reason to keep going. - - - - - - -
☀️ ፀሀይ ነሽ እንዳይሉ ምንም አታቃጥይም 🌕 ጨረቃ ነሽ እንዳይሉ በቀንም ታበሪያለሽ ⭐ ኮከብ ነሽ እንዳይሉ ስትስቂ 💡 ብርሀንሽ ኮከቦችን ያጠፋቸዋል ለኔ አለሜ ነሽ my❤️🩹 🫠😊🤭
የሆነ ወንጀል ለመሥራት ባሰብኩ ጊዜ አታሳካልኝ የኔ ጌታ።❤️🩹
. #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ ክፍል 9 💛 (የመጨረሻው ክፍል) እኔና #አሚን ተጋባን፤ አሁን አብረን መኖር ከጀመርን 8 ወራት አልፈዋል። በሰርጌ ቀን በጣም ፈርቼና ተጨንቄ ነበር፣ አሚንንም ጭምር እፈራው ነበር። ራኢድ ግን በሰርጌ ቀን በጣም ረድቶናል፤ ወዲያ ወዲህ ሲልና ሲደክም ነበር የዋለው። እሱ አሁን ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጦልኛል ፤ አሁን እሱ ራሱ አጭቷል፣ ሰርጉም ከ 3 ወር በኋላ ይሆናል። አሚንን አሁን በሙሉ ልቤ እወደዋለሁ፣ እሱም ይወደኛል። ሁለታችንም ለሳቅና ለጨዋታ ልዩ ቦታ አለን፤ መግባባታችንና መጣጣማችን ደግሞ እጅግ ደስ ይላል። አንድም ቀን ተሳስተን ተረድተን አናውቅም፤ ብንኳረፍ እንኳ ከአንድ ሰዓት በላይ አንቆይም። የማላውቀውን ሰው አግብቼ እንዲህ እሆናለሁ ብዬ በፍጹም አልገመትኩም ነበር! ያ በባህሪውና በመግባባታችን የፈራሁት ሰው፣ ህይወቴን ወደ ተሻለ የለወጠ፣ በፊቴ ላይ ፈገግታን የሳለ፣ አንዳንዴ እንደ ህፃን ልጅ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ እናት የምሆንለት ድንቅ ሰው ሆነልኝ። #አሚን የእኔ ነሲብ ሆኖ ወጣ... አህህ፣ ነሲቤ እንዴት ያምራል! እንዲህ ከእሱ ጋር ደስተኛ ሆኜ እንደምኖር፣ እንደምወደውና እሱም የህይወቴ ግማሽና ውድ ሀብቴ እንደሚሆን ማን በገመተ ነበር! አንዳንዴ በህይወታችን ውስጥ የምንፈራቸው ለውጦች ይከሰታሉ፤ ህይወታችን እንደ ድሮው የማይሆን ይመስለናል፤ ግን እንዲያውም ከድሮው የበለጠ ውብ ሊሆን ይችላል። ለእነዚያ ለውጦች አላህን እናመሰግናለን። ዛሬ #በህይወቴ (በአሚንም ህይወት ጭምር) እጅግ አስደሳች ቀን ነው። ምክንያቱም እርጉዝ መሆኔን ካወቅኩ 3 ቀናት ሆኖኛል። ለአሚን አስገራሚ ስጦታ (Surprise) ለማዘጋጀት ወስኛለሁ። አሁን ወደ ቱርክ ለሁለት ሳምንት ለሽርሽር ልንሄድ ስለሆነ ሻንጣዬን አዘጋጅቼ ጨርሻለሁ። አባቴ ጋር ደወልኩ፤ የጥያቄዬን አስገራሚነት አይቶ የ ፕሌኑ ካፒቴን ጓደኛው ስለሆነ እንዲረዳኝ ጠየቅኩት፣ እነሱም ጥያቄዬን አልከለከሉኝም። ወደ አየር ማረፊያ (ኤርፖርት) ሄድን፣ ከቤተሰብ ተሰናብተን እጁን ይዤ ወደ ፕሌኑ ገባን። ፕሌኗ ተነስታ ጥቂት እንደቆየች ካፒቴኑ በከፍተኛ ደስታና ስሜት በሚቀሰቅስ ድምፅ እንዲህ አለ፦ "አህም... አህም... ለአቶ አሚን አብዱራህማን ... እንኳን ደስ ያለህ!" አሚን በግርምት አየኝ! ካፒቴኑም፦ "አባት በመሆንህ እንኳን ደስ አለህ! ልጁ/ልጇ በክብር ይደግ/ትደግ፤ አላህ የዓይን ማረፊያ ያድርግላችሁ!" ብሎ ሳቀ። ይህ ነበር የእኔ አስገራሚ ስጦታ! አሚን በድንጋጤ፣ በደስታና በጭንቀት ተሞልቶ ቆመና ይጮህ ጀመር፦ "#አላህ_ይመስገን!" እያለ። እኔ ዝም ላሰኘው ብሞክርም ተጠግቶ ግንባሬን ሳመኝና በደስታ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ "አላህ ለኔ ያቆያችሁ" አለኝ። በሁኔታው እየሳቅኩና በጣም ተደስቼ ነበር። በጉዞው ሁሉ ሲንከባከበኝ ነበር፤ እሱ ሳይበላ እኔን ያበላኛል። ከደስታው ብዛት የተነሳ በጉዞው ሁሉ ሳይተኛ፣ ፊቱ በፈገግታ ተሞልቶ አደረ። (እንደ እሱ ያለ ሰው በህይወቴ ስለመኖሩ አላህን አመሰግናለሁ። አንተን ላገኘሁበት ነሲብ (ዕጣ ፈንታ) ምስጋና ይግባው፤ አብረኸኝ ስላለህም አላህን አመሰግናለሁ)። ~በህልም፣ በምኞት፣ በቀደርና በነሲብ መካከል... አላህ የጻፈልን እንጂ ሌላ ምንም አይከሰትም። ውብ ነገሮች ሁሌም ከችግር ጀርባ ተደብቀው ይገኛሉ፤ ይሄም አላህ ለትዕግስታችን የሚሰጠን ታላቅ ስጦታ ነው!~ — ተፈፀመ —
. #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ ክፍል 8 💛 ከዚያ ቀን በኋላ #ከራኢድ ጋር በይፋ ተለያየን። ራኢድ የእኔ ዕጣ ፈንታ (ነሲብ) እንዳልሆነና ምንም ብናደርግ አብረን መሆን እንደማንችል ሙሉ በሙሉ አመንኩ። የቱንም ያህል ቢወደኝና ብወደውም፣ ዕድል ከሌለ የለም! ለዚህም አላህን አመሰገንኩ፤ ምክንያቱም በሆነው ነገር ሁሉ ውስጥ ለእኔ የሚበጅ መልካም ነገር እንዳለ ስለማውቅ ነው። #ከአክስቴ ጋር ያለን ግንኙነት እንደ ድሮው ቀጠለ፤ ነገር ግን ራኢድ ከእኛ ራቀ፣ ዳግመኛም ላየው አልቻልኩም። አንደኛ ዓመት ትምህርቴን ጨርሼ ሁለተኛ ዓመት ገባሁ። በትምህርቴ ላይ አተኮርኩ፤ ራኢድ ለእኔ የአክስቴ ልጅ ብቻ ሆነ። ቀናትና ወራት አለፉ፤ ሱሃ ያቺ ጠንካራና ተስፋ ያላት ልጅ ሆና ተመለሰች። አንድ ቀን ክፍሌ ውስጥ ትንሽ እንቅልፍ ልወስድ ጋደም ብዬ ሳለ እናቴ በድንጋጤና በግርምት ተሞልታ ገባች። ደንግጬ ተነሳሁና "ምን ሆነሻል እማዬ?" አልኳት። እናቴ ድምጿን ከፍ አድርጋ፦ "የአሚን እናትና እህቱ ሊመጡ ነው!" አለችኝ። ለምን ቀደም ብለው እንዳልነገሩኝ ቢከፋኝም፣ ተነስቼ ቤቱን በማዘጋጀትና ራሴንም በማስተካከል ተጠመድኩ። የአሚን እናት መጡ። አሚን የ 27 ዓመት ወጣት ሲሆን አባቴ በሚሰራበት ኩባንያ ውስጥ ነው የሚሰራው። አባቱ ስለሞቱ እናቱንና እህቱን የሚንከባከበው እሱ ነው። በጣም ታታሪና ደግ ልጅ በመሆኑ አባቴ እንደ ልጁ ነው የሚያየው። እናቱና እህቱም በጣም ደግ ሰዎች ናቸው። ከእህቱ #ከሰሀር ጋር የቅርብ ጓደኛሞች ሆንን። እነሱ ሄደው አባቴ ሲመለስ እናቴ በደስታ ፈገግ ብላ፦ "የአሚን እናት ሱሃን ለአሚን ትፈልጋታለች!" አለችው። ለአሚን እሺ አልኩ። ድግስ ትልቅ ድግስ ባናደርግም አሁን ኒካሕ ካሰረኝ አንድ ዓመት ሆኗል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ ከአሚን መልካም ነገር እንጂ ክፉ አላየሁም። በቀጥታ አንገናኝም፤ ነገር ግን በእህቱ በሰሀር በኩል ስጦታዎችንና መልእክቶችን ይልካል (ሰሀር ከእኔ በ 3 ዓመት ትበልጣለች)። እኔ በትምህርቴ ብጠመድም እሱ ግን ሁሌም ይረዳኛል። አንድ ቀን አባቴ ጋር ሆኜ አይቶኝ እንደወደደኝና ወዲያውኑ እናቱን እንደላከ ከሰሀር ሰምቻለሁ። አንዳንዴ "ሳላውቀውና ሳልወደው እሺ ማለቴ ስህተት ይሆን?" ብዬ አስባለሁ። እንደ ራኢድ እወደው ይሆን? ወይስ ከዚያ በላይ? አሁንም በመካከላችን የፍቅር ንግግሮች የሉም፤ ያለኝ ነገር ስጦታዎቹና በሰሀር በኩል የሚላክ ሰላምታ ብቻ ነው። አንድ ቀን አክስቴን ለምሳ ጋበዝናቸው። ከታጨሁ በኋላ ራኢድ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤታችን መጣ። ሁላችንም ተገረምን። ከምሳ በኋላ እሱና ሳሚር ሳሎን ተቀምጠው ሳለ ሳሚር ውሃ እንዳመጣለት ጠየቀኝ። ውሃውን ይዤ ስሄድ ራኢድ ብቻውን ነበር። ራኢድ አሁንም እንደተቀየመብኝ ያስታውቅ ነበር። በሩ ላይ ቆሜ ፈገግ አልኩና፦ "ምነው? ተቀይመህብናል እንዴ?" አልኩት። በግድ ፈገግ ለማለት እየሞከረ፦ "እንኳን ደስ አላችሁ፣ መልካም ህይወት ይሁንላችሁ" አለኝ። #እኔም፦ "አሁን ነው ትዝ ያለህ? ሰርጉ እኮ ቀርቧል። ራኢድ እባክህ... እኔን በመጥላትና በመቀየም ምንም አታተርፍም። እኔ አሁን የታጨሁ ሴት ነኝ፤ ያንተ ባህሪ ደግሞ ህሊናዬን እንዲወቅሰኝ እያደረገው ነው። የአጎት ልጅ፣ ያለፈው አልፏል። ዛሬ እኛ ቤተሰብ ብቻ ነን። ከወደድከኝ ሁሉንም ነገር እርሳና አዲስ ገጽ እንክፈት። እኔ አሚንን በማግባቴ አልተሳሳትኩም፣ ምክንያቱም እሱ የኔ ዕጣ ፈንታ (ነሲብ) ነው! 'የጠላችሁት ነገር ለእናንተ መልካም ሊሆን ይችላል' የሚለውን ቃል አስታውስ" አልኩት። #ራኢድም ትንሽ ዝም ብሎ ካሰበ በኋላ ፈገግ አለ፦ "እሺ ሱሃ አትፍሪ። በእውነት መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለሁ። ያደረግሽው ትክክል ነው፤ አንቺ የኔ ሳትሆኚ የአሚን ነሲብ ነሽ። አላህ ያስደስታችሁ። ምን ጊዜም የአክስትሽ ልጅ ነኝ፣ የምትፈልጊው ነገር ካለ እኔ አለሁ" አለኝ። ይህንን ካወራን በኋላ ትልቅ ሸክም ከላዬ ላይ የወረደ መሰለኝ። አሁንም እንደሚወደኝ አውቃለሁ፣ አሳዝኖኛልም፤ ነገር ግን ጥላቻው ስለጠፋ አሁን እኔን እንደ ዘመዱ ብቻ እንደሚያየኝ እርግጠኛ ሆንኩ። ወዲያው ስልኬን አነሳሁና በኢንተርኔት የሰርግ ልብሶችን ማየት ጀመርኩ። ለሰርጌ ጥቂት ወራት ብቻ ነው የቀሩት... ከወዲሁ መጨነቅ ጀምሬያለሁ.......። ይ ቀ ጥ ላ ል...
. #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ ክፍል 7 💛 ግን #ሰናእ ያን ሁሉ መከራ አሳልፎ ለምን በቀላሉ እሺ እንዳልኩና እንዴት እንደረሳሁት በጣም ተገርማለች። እንድተወው ወይም እንድክደው ባትፈልግም፣ በጉጉት ግን ያን ያህል ልቤን የለወጠው ምን እንደነገረኝ ማወቅ ፈለገች። በመልእክቱ የጻፈልኝን ነገርኳት፦ "ድሮ እንዴት እንደምንዋደድ አስታወሰኝ። ያን ረዥም መልእክት እያነበብኩ ወደ ኋላ ተመለስኩ፤ ከእሱ ውጪ ሌላ ሰው መውደድ እንደማልችል ተሰማኝ። ባለፉት ዓመታት ሁሉ ወድጄዋለሁ፣ ወደፊትም እወደዋለሁ። ሊያጣኝ እንደማይፈልግና በተለየንበት ወቅት እኔ የእሱ ነፍስ መሆኔንና ያለ እኔ መኖር እንደማይችል እንደተረዳ ነገረኝ። መልእክቱን ባነበብኩ ቁጥር ፍቅሬ አገገመ፤ እሱን እንደማልረሳውና ለራሴም ሆነ ለሰዎች ስዋሽ እንደነበር አወቁ። በመጨረሻ 'እወድሻለሁ' የሚለውን ቃል ሲጽፍ፣ ሰናእ... ያን ሁሉ በደልና ያን ሁሉ የለቅሶ ቀን ረሳሁት። ከደስታዬ ብዛት የተነሳ ሁሉ ፈራሁ! የፈቀድኩት እሱን ማጣት ስላልፈለግኩ ነው፤ እሱ ትላንቴም ዛሬዬም ነው፣ ከአባቴ ቀጥሎ ያመንኩት ብቸኛ ወንድ እሱ ነው" አልኳት። ሰናእ ዓይኖቿ በዕንባ ተሞልተው እያዩኝ አቀፈችኝ። "ለመሆኑ ሰርጋችን ይፈጸማል? እኛ የዕጣ ፈንታ (ነሲብ) ነን?" ብዬ ጠየቅኳት። ፈገግ ብላ፦ "#ኢንሻአላህ... ግን ሱሃ ስሚኝ፤ ዕጣ ፈንታሽ (ነሲብሽ) ካልሆነ ምንም ብታደርጉ አትጋቡም፣ ስለዚህ እንዳታዝኚ ቃል ግቢልኝ። በአላህ ውሳኔ መርካትና ማመስገን አለብሽ" አለችኝ። #በሰናእ ንግግር ብሰጋም፣ ሁሉም ነገር ግን መልካም እንደሚሆን ተስፋ አደረግኩ። "አልሃምዱሊላህ" ብለን ዝም አልን። የእጮኝነት ቀናችን ደረሰ። ሁላችንም ደስተኞች ነበርን። ለቤተሰብና ለጥቂት ጓደኞቼ ብቻ ትንሽ ድግስ አደረግን። ከ (እጮኝነት) በኋላ ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። #ራኢድም ወደ ድሮው አፍቃሪነቱ የተመለሰ መስሎኝ ነበር። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓይኔ መከፈት ጀመረ። የራኢድን ለውጥ፣ ባህሪውንና ንዴቱን አስተዋልኩ። ያ ሰላማዊ፣ ርኅሩኅና አፍቃሪ የነበረው ራኢድ ጠፍቶ፣ በንዴትና በጭካኔ የተሞላ ሰው ሆነ! ለኔ ያለው ፍቅር እንኳ እንደ ድሮው አይደለም። አንድ ቀን ቁጭ ብዬ አስብኩና እኛ እንደ ድሮ መሆን እንደማንችል ተረዳሁ፤ ራኢድ ሌላ ሰው ሆኗል፣ ከልጅነቴ ጀምሮ የወደድኩት ያ ራኢድ አይደለም። ለመታገስና ለመምከር ሞከርኩ፤ ነገር ግን በወቀስኩት ቁጥር "አንቺ ነሽ የተለወጥሽው፣ #ነገር_ፈላጊ ሆነሻል፣ በትንሽ ነገር ትልቅ ችግር ትፈጥሪያለሽ" እያለ ይነጫነጫል። ኢስቲኻራ ሰገድኩ ዱዓም አደረግኩ። ከሁለት ቀን በኋላ ወደ እናቴ ሄጄ እንዲህ አልኳት፦ "እማዬ፣ መለያየት እፈልጋለሁ!" እናቴ ደንግጣ ጮኸች፤ ምን እንደምፈልግ ሁሉ ግራ ገባት። ሰናእ ግን በድንጋጤ አፈጠጠችብኝ። አባቴ የእናቴን ጩኸት ሰምቶ ምን እንደተፈጠረ ለማየት መጣ። እናቴ በንዴት፦ "ልጅህ መለያየት ትፈልጋለች!" አለችው። አባቴም........ ይ ቀ ጥ ላ ል...
. . #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ ክፍል 6 💛 #ጥቂት ቀናት አለፉ። ለእናቴ ራኢድን እንደማልፈልገውና እሱም እኔን እንደማይፈልግ ነገርኳት። እርግጥ ነው፣ እናቴ "ገና ከጅምሩ አክስትሽ ናት ይሄን ሁሉ ተስፋ የሰጠቻችሁ" እያለች ብታዝንብኝም ሰናእ አረጋጋቻት። ሰናእ ወደ እኔ መጥታ በሃዘኔታ ስታየኝ ተናደድኩ። "ምን ሆነሽ ነው እንዲህ የምታዪኝ?" አልኳት። #ሰናእ አቅፋኝ ይቅርታ ጠየቀችኝ፦ "ሱሃዬ፣ ያኔ የጮህኩብሽ ይበልጥ ተስፋ እንዳታደርጊ ብዬ ነው እንጂ አንቺን ለመጉዳት አልነበረም፤ ከፍቅሬ የተነሳ ነው" አለችኝ። እኔም በደረቅ ፈገግታ፦ "ችግር የለውም፣ ይገባኛል። እኔ ጠንካራ ነኝ፣ ህይወት በአንድ ሰው አትቆምም" አልኳት። እሷ ግን በንግግሬ ተገርማ ዝም አለች። ሳምንታትና ወራት አለፉ። ቀስ በቀስ ራኢድን መርሳት ጀመርኩ። ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ትምህርቴ ላይ አተኮርኩ። "ራኢድን ለዘላለም ረሳሁት" ብዬ ባሰብኩበት በዚያች ምሽት ግን ሁሉም ነገር ተቀየረ። ክፍሌ ውስጥ ስለ ወደፊት ህይወቴ እያሰብኩ ሳለ አባቴ ፈገግ ብሎ ገባ። (የአባቴ ፈገግታ ሁሌም ደህንነትና ሰላም ይሰጠኛል)። "ልጄ፣ ላናግርሽ ፈልጋለሁ" አለኝ። "እሺ አባዬ፣ ጉጉት አደረብኝ" አልኩት። አባቴ ጸጉሬን እያባበሰ፦ "ማሻአላህ አድገሽ የኩራታችን ምንጭ ሆነሻል። አሁን ደግሞ የሚፈልግሽ ሰው መጥቷል" አለኝ። ደነገጥኩ። #አባቴ፦ "አይዞሽ፣ ልጁን አውቀዋለሁ፣ የጥሩ ቤተሰብ ልጅ ነው። ግን ፈቃድሽን ማወቅ እፈልጋለሁ" አለኝ። "አባዬ፣ መጀመሪያ ትምህርቴን ብጨርስ ይሻላል" አልኩት። አባቴ ግን በድጋሚ ፈገግ ብሎ፦ "ለመሆኑ ማን እንደሆነ ማወቅ አትፈልጊም?" አለኝ። ስለ ራኢድ አሰብኩና ልቤ ጠበበ። ለራኢድ ካልሆነ ለሌላ ሰው መሆን እንደማልችል ተሰማኝ። "ማን ነው?" ስል ጠየቅኩት። አባቴ "ራኢድ ነው" ሲለኝ ምድር የምትዞርብኝ መሰለኝ! እንዴት? እሱ እኮ ነው ራሱ ትቶኝ የነበረው! በደስታ ልፈንዳ ወይስ በንዴት ልጮህ ግራ ገባኝ። #አባቴ፦ "ልጄ ተረጋግተሽ አስቢበት፣ እኔ አልገፋፋሽም። ውሳኔሽን ንገሪኝ" ብሎኝ ወጣ። ሰናእ ወዲያው ገብታ ስታየኝ ሁኔታዬን አውቃ በዝምታ ተመለከተችኝ። በጉዳዩ ላይ እያመነታሁ ቀናት አለፉ። እናቴ እንድስማማ ትወተውተኝ ነበር። አክስቴም ወደ እኛ መጥታ ብቻችንን እንድንወያይ ጠየቀችኝ። ስለ ራኢድ ብዙ አወራችልኝ፣ ይቅር እንድለው ለመነችኝ። የድሮ ትዝታችንን ስታነሳብኝ ምንም ቢፈጠር ከራኢድ መለየት እንደማልችል ተሰማኝ። ግን ወዲያውኑ እሺ አላልኩም ነበር። በዚያው ምሽት #ከሰናእ ጋር እያወራን ሳለ ከራኢድ መልዕክት ደረሰኝ። ያ መልዕክት ስለ እሱ ያለቀስኩትን ዕንባ ሁሉ የሚያብስ ነበር። ሁሉንም የድሮ ጣፋጭ ትዝታዎቻችንን ጽፎ "ይቅር በዪኝ፣ ወደ ድሮው ፍቅራችን እንመለስ" ብሎ ተማጸነኝ። በማግስቱ ጠዋት። ከእንቅልፌ ስነቃ ልቤ በደስታ ይዘፍን ነበር። #ራኢድ ወደ እኔ ተመልሷል! ለዘላለም የእኔ ሊሆን ነው! አባቴ አየኝና፦ "ልጄ፣ ዛሬ ፊትሽ ያበራል። ውሳኔሽ ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ። ፈገግ ብዬ፦ "እናንተ ከፈቀዳችሁ እኔም ተስማምቻለሁ" አልኩት። እናቴ በእልልታ ቤቱን አቀለጠችው። ሰናእም በደስታ አቅፋኝ ሳመችኝ። ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት የተመለሰ መሰለኝ። ግን..... ይ ቀ ጥ ላ ል...
. #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ ክፍል 5 💛 #እናቴ በሁኔታው ተበሳጨች፤ ገና ከጅምሩ ነገሩ አልተመቻትም ነበር፣ አሁን ደግሞ ሊያጯት አለመምጣታቸውን ስታይ ይበልጥ ተከፋች። አንድ ቀን እኔ፣ እናቴና ሰናእ ተቀምጠን ሳለ እናቴ ፊቷን አጥቁራ እንዲህ አለችኝ፦ "#ሱሃ፣ ስለ እጮኝነት ከራኢድ ጋር ተነጋግረሻል? እሱ አይፈልግሽም እንዴ? አክስትሽ እኮ እያዞረች ስታዞረን ከረመች፣ አሁን ግን ምን እየጠበቀ ነው? 12ኛ ክፍልን ስትጨርሺ እንደሚያጭሽ ገና ከጅምሩ የታወቀ ነበር። ይሄን ሁሉ ጊዜ ማባከኑ ጥሩ አይደለም ልጄ።" ለእናቴ "#ራኢድ ያውቃል፣ ይመጣል፤ ግን መጀመሪያ እኔና እሱ እንነጋገር፣ ትንሽ ታገሺ" አልኳት። ግን ያ መታገሴ እኔን ይበልጥ ጎዳኝ። ለራኢድ የእናቴን ንግግር ስነግረው በመለሰልኝ መልስ ደነገጥኩ፦ "እውነቱን ለመናገር ሱሃ፣ እኔ አሁን አንቺን ለማጨት ዝግጁ አይደለሁም።" ልቤ በቃጠሎ ተሞላ፤ ወዲያውኑ እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ "እንግዲያውስ የአክስቴ ልጅ፣ ከዛሬ ጀምሮ አንተ ለእኔ የአክስቴ ልጅ ብቻ ነህ! ሌላ ምንም አይደለህም። አንድ ቀን መጥተህ በይፋ ስታጨኝ ያኔ እንገናኝ..." ስልኬን አጠፋሁና ወደ ሰናእ ዘንድ ሄድኩ። ዝም ብዬ አጠገቧ ተቀመጥኩ፤ እሷም ዝም አለች። "ምን ሆንሽ?" ስትለኝ ግን ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ሰናእ ደንግጣ ልታረጋጋኝ ሞከረች። ትንሽ ሲቀልልኝ ሁሉንም ነገር ከ ሀ እስከ ፐ አጫወትኳት። በራኢድ ብትገረምም እኔን ላለማስጨነቅ ስትል "ገና ወጣት ስለሆነ ነው፣ ደግሞም የቤተሰብ ልጅ ስለሆነ ወዴትም አይሄድም" እያለች ምክንያት እየፈለገች አጽናናችኝ። እናታችንንም "ገና ልጅ ስለሆነች አትቸኩሉ" እያልን ለጊዜው አታለልናት። አንድ ቀን #አክስቴ ቤት ሄድን፤ እናቴም ስለ ጉዳዩ አነሳች። እኔ ምንም እንዳልሰማሁ ሆኜ ተቀመጥኩ። አክስቴ ወደ እኔ ዞር አለችና "#ሱሃዬ፣ አሁንም ራኢድን ትወጂዋለሽ?" ስትል ጠየቀችኝ። ያለምንም ማመንታት፦ "መጀመሪያ እሱ አሁንም ይወደኛል ወይስ ያ ያኔ በልጅነታችን የነበረ ስሜት ብቻ ነበር? የሚለውን ማወቅ አለብን" አልኳት። አክስቴ ዝም አለች! ለመጀመሪያ ጊዜ በአክስቴ ላይም ሆነ በራኢድ ፍቅር ላይ ጥርጣሬ አደረብኝ። የአክስቴ ፊት ተለወጠ፣ የተከፋችም መሰለች። #ደግሜ ጠየቅኳት፦ "የልጅነት ብቻ ነበር?" አክስቴ አቅፋኝ እንዲህ አለች፦ "ልጄ፣ ዕጣ ፈንታሽ (ነሲብሽ) ከሆነ ከሃያ ዓመት በኋላም ቢሆን ትጋባላችሁ፤ ካልሆነ ግን......." ንግግሯን አቋረጥኳትና በዕንባ በታጠበ ድምፅ፦ "አሁንማ 'ዕጣ ፈንታ ከሆነ' ሆነ ነገሩ? በቃ ለአላህ ሰጥቼዋለሁ" አልኩ። ሳምንታትና ወራት አለፉ። ከራኢድ ጋር አንዲትም ቃል አንለዋወጥም ነበር። ራኢድም ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ መኖር ቀጠለ። ቤታችን ሲመጣ እንደማንኛዋም የአክስቱ ልጅ ነበር የሚያየኝ። ዓይን ለዓይን ስንጋጭ ድሮ የነበረው የፍቅር እሳት ጠፍቶ ተራ እይታ ብቻ ሆነ። ማመን አቃተኝ፤ ራሴን እያታለልኩ ለሰናእ "አሁንም ይወደኛል ግን አድጎ ስለተለወጠ ነው" እያልኩ ለመከላከል ሞከርኩ። በመጨረሻም #ሰናእ ተቆጣችና ጮኸችብኝ፦ "በቃሽ ሱሃ! ማንን ነው የምታታልዪው? በአላህ ይሁንብኝ ራኢድ እኔን እንደሚያየኝ ነው አንቺንም የሚያይሽ! ያ የድሮው የፍቅር እይታና ንግግር አክትሟል። እባክሽን ራስሽን እወቂ! እሱ አንቺን ትቶሻል፣ አንቺም ተዪው! እሱ ለጥቅሻሽም ሆነ ለናፍቆትሽ ግድ የለውም..." አለችኝ። የአክስቴንም ንግግር አስታወሰችኝ፤ "አንቺን የሚወስድሽ ሰው እድለኛ ነው" ስትለኝ ራኢድን አለማለቷንና ቀስ በቀስ ተስፋ እንድቆርጥ እያደረገችኝ እንደነበር ገለጸችልኝ። ከዛ ቀን ጀምሮ ጠንካራ ለመሆንና ህይወቴን ለመቀጠል ወሰንኩ። ግን ቀላል አልነበረም፤ ትዝታዬ ሁሉ ከራኢድ ጋር ነው፣ እሱ ደግሞ ዘመዴ ስለሆነ ሁሌም ቤታችን አለ። እንዴት ልርሳው? ዕንባዬን አበስኩና "ለምን እንዲህ አደረገኝ?" ብዬ ራሴን ከመጠየቅ ይልቅ "እንዴት ልርሳው?" በሚለው ላይ አተኮርኩ። በዚህ መሃል #ከራኢድ መልዕክት ደረሰኝ። "ይቅርታ አድርጊልኝ፣ አላህ ከእኔ የተሻለ ይስጥሽ" የሚል፤ ችግሩ ግን እኔ እሱን ነበር የምፈልገው! ለኔ ከእሱ የተሻለ አልነበረም፤ እሱ የታመነና ጠንካራ ሆኖ እንዲገኝልኝ ነበር የምፈልገው። መልዕክቱን አየሁት ግን ምንም አልመለስኩለትም ከዛም..... ይ ቀ ጥ ላ ል..
. #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ) ክፍል 4 💛 #ሰናእ በድንጋጤ ፈዘዘች! እኔም በግርምትና በፍርሃት እያየኋት "ምን ሆነሽ ነው ሰናእ?" አልኳት። ሰናእ እየሳቀች፦ "ይሄ ሁሉ ፍቅር ካንቺ ይወጣል? አንቺ አጭር!" አለችኝ። እኔም በሀፍረት እየሳቅኩ "ምነው? ምን ሆንኩ?" አልኳት። #ሰናእ፦ "አይ ይሄማ ፍቅር ነው ልጄ፣ ግን በዚህ ዕድሜሽ እንዲህ ያለ ትልቅ ፍቅር ውስጥ መግባትሽ አስገርሞኛል" አለች። እኔም ፊቴን አዙሬ፦ "ለፍቅር ዕድሜ አለው እንዴ?" አልኩ። በዚህ መሃል ሪሃም መጣችና፦ "ፍቅራችሁ ይለቅላችሁ! ወንድሜ እዛ ክፍል ውስጥ እየታመመ ነው፣ እናንተ ስለ ፍቅር ታወራላችሁ? ሂጂና ባልሽን እዪው ባክሽ" አለችኝ። እኔም ደንግጬ፦ "ወይኔ ምን ሆነ? መተኛት ፈልጎ አልነበረም እንዴ?" አልኩ። ሪሃም፦ "መድኃኒቱን አላጠጣሽውም እኮ! አንቺን ሲያይ ሁሉንም ነገር ቢረሳ እንኳ፣ አንቺ ግን ትወጂዋለሽ አይደል? መድኃኒቱን ማስታወስ ነበረብሽ!" አለች። ወደ #ራኢድ ክፍል ሄጄ በሩ ላይ ቆሜ በዝምታ አየሁት። ራኢድ ሲያየኝ ተገረመ። "እንዴት ነህ?" ስለው "አልሃምዱሊላህ" አለኝ። መድኃኒቱን መውሰዱን ስጠይቀው ሪሃም እንደሰጠችው ነገረኝ። ጥቂት ዝምታ ሰፈነ። ከዚያም ራኢድ ድምፁን ዝግ አድርጎ ጎርነን ባለ ድምፅ፦ "ትወጂኛለሽ?" ሲል ጠየቀኝ። ልመልስለት ብዬ አመነታሁ። ራኢድ ተቀይሞ፦ "ካመነታሽ መልሱ 'አይ' ነው ማለት ነው። በቃ ተኚልኝ፣ አታሳብጂኝ ሱሃ" አለኝ። ትንሽ ቆይቼ በዝምታው መሃል፦ "አዎ!" አልኩት። ራኢድ፦ "ምኑ ነው አዎ?" እኔ በንዴት ዓይኔን አዙሬ፦ "ምን ይመስልሃል?" አልኩት። ራኢድ በንዴት፦ "በጥያቄ አትመልሺልኝ! መልስ ካለሽ ንገሪኝ፣ ካልሆነ ውጪልኝና ልተኛ" አኝ። በንግግሩ ተናድጄ ፊቴን አዙሬ፦ "አዎ እወድሃለሁ! እንዲህ ክፉና ግትር ብትሆንም እወድሃለሁ፤ እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ድረስ ብትከፋም እንኳ መውደዴን እቀጥላለሁ!" አልኩት። ራኢድ በደስታ አልጋው ላይ ሊስተካከል ሲል ህመሙ ተሰማውና "አይይ... እጄ! የአንቺ ነገር!" ብሎ ጮኸ። #ራኢድ፦ "እወድሻለሁ አልሽኝ አይደል?" እኔ በሀፍረት፦ "በቃ ይበቃሃል፣ ዝም በል" አልኩት። ከዚያ ቀን በኋላ ፍቅራችንና ትስስራችን ጨመረ። አክስቴ ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ ይበልጥ ትቀራረበን ነበር። እናቴን ደግሞ "ሱሃ ለራኢድ ትሁን" እያለች ትጎተጉታለች። እናቴም "ዕድላቸው (ነሲባቸው) ከሆነ ለምን አይሆንም" ትላለች። እኔና ራኢድ ግን አክስቴ እስካለች ድረስ በእርግጠኝነት እንደምንጋባ እናምን ነበር። ሪሃም እናቴ ፊት እያጋለጠችኝ ታስቸግረናለች፣ እናቴ ትቆጣለች፣ ሰናእ ደግሞ ትመክረኛለች፣ በተጣላን ጊዜ ታስታርቀናለች... እንዲህ እያልን ዓመታት አለፉ። የሁሉም ነገር መጨረሻ የጀመረበት ቀን መጣ.. . እንዴት ተጀመረ? በማን ምክንያት? በምንስ? የ 12ኛ ክፍል ፈተናዬን ጨርሼ ነበር። በፈተናው ምክንያት ራኢድን ትንሽ ቸል ብዬው ነበር፤ ጊዜዬን በሙሉ በማጥናት ነበር የማሳልፈው። 12ኛ ክፍልን እንደጨረስኩ ራኢድ በይፋ ሊያጨኝ ቃል ገብቶ ነበር። ለዛ ቀን በጣም እጓጓ ነበር፤ የ ሰርግ ልብስ ለብሼ ወደ እሱ ስገባ እያሰብኩ እስቅና አፍር ነበር። ፈተናዬን ጨርሼ ያ ትልቅ ሸክም ከላዬ ላይ የወረደ መስሎኝ ነበር። (ግን ትልቁ ጭንቀት አሁን እንደሚጀምር አላወቅኩም ነበር)። አንድ ቀን #ለራኢድ መልዕክት ላኩለት፤ ምክንያቱም እንደ ድሮው ግድ የሚለውና የሚጨነቅልኝ ሆኖ አላገኘሁትም። "መቼ ነው የምታጨኝ? ለዓመታት የጠበቅኸው ቀን ደረሰ እኮ!" ብዬ በፌዝ ላኩለት። እሱ ግን እንደ ቀልድ በሳቅ emoji መለሰልኝ። እንደ ቀልድ ያየው አልመሰለኝም ነበር፤ ምክንያቱም ሁሌም ስለዚህ ጉዳይ በቁም ነገር ነበር የሚያወራው። ደነገጥኩ፣ ግን ችላ አልኩት። ሳምንታት አለፉ። የራኢድ ቸልተኝነት ግን እየጨመረ መጣ። አልወቅሰውም አልኩ፤ ምክንያቱም እኔም በፈተና ወቅት ቸል ብዬው ነበርና። ግን "አንዴ ብወቅሰው ወደ ቀድሞው ይመለሳል" ብዬ አንድ መልዕክት ላኩለት። መልዕክቱ ትንሽ ሞኝነቱ ቢበዛም፣ ቢወደኝ ኖሮ ግን የውስጤን ይረዳ ነበር። #ራኢድ መልዕክቴን አይቶ ተቀየመ። የዛን ቀን ልቤን የሰበረችው ንግግር እንዲህ የምትል ነበረች፦ "እኔ ራሴ መጀመሪያ ቸል ብዬው ሳለ፣ አሁን ለምን እወቅሰዋለሁ?" ተሳስቻለሁ አልኩ። በትክክልም መጀመሪያ ቸል ያልኩት እኔ ስለነበርኩ ተቀይሞ ይሆናል ብዬ ግንኙነታችንን ላለማበላሸትና ወደ ቀድሞው ፍቅራችን ለመመለስ ወሰንኩ። ግን... ራኢድ ወደ ቀድሞው የሱሃ አፍቃሪነቱ ተመለሰ? የሱሃን ግትርነትና የቃላት መዳፈር ችሎ የሚወደው ራኢድ ተመለሰ? ምንም ያህል የፍቅር ቃላት መናገር ባታውቅም፣ የልቧን መረዳት የሚችለው ያ ራኢድ የት ሄደ? ይ ቀ ጥ ላ ል...
#ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ) ክፍል 2 💛 #ራኢድ፦ "እኔ እዚህ ያለሁት ስለምወድሽ ነው ሱሃ!" እኔ ደንግጬ አፈጠጥኩበት። ያንን ረዥም ምላሴን አውጥቼ ልሰድበው ብሞክርም አንድም ቃል ሊወጣኝ አልቻለም፤ ዝም ብዬ ፈዘዝኩ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን ምላሴ ተመለሰና በንዴት፦ "ቁምጥና ያንሳህ! አንተ ባለጌ!" አልኩት። ራኢድ ቅንድቡን ሰቅሎ ፈገግ አለና፦ "ብትሰድቢኝም ስደቢኝ፤ እኔ ግን እወድሻለሁ፣ አገባሻለሁም!…
. #ዕጣ_ፈንታ( ነሲብ) ክፍል 1 💛 የታሪኩ ዋና ገጸ-ባህሪና ተራኪ ሱሃ: እኔ ሱሃ እባላለሁ፣ ዕድሜዬ 21 ዓመት ነው። ቤተሰቦቼ፦ #ሰናእ፦ የ 25 ዓመት ወጣት፣ ብቸኛና ትልቅ እህቴ ናት። አባቴ #ሰዕድ፦ በ 50ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ፣ የአንድ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ነው። (ኑሯችን የተደላደለና ምስጋና ይግባውና የተሟላ ነው)። እናቴ #ኢብቲሃል፦ በ 40ዎቹ…
እናም በመጨረሻ ከጫፍ እንደርስ እና፤ ለዚህ ነው የኖርነው እንላለን 😔
አላህ ሆይ አንተ ታዉቃለህ አነሱ አያዉቁም አናም፣ጌታዬ🤲 ልቤን ረጋ አድርግልኝ በምታውቀዉ ነገር❤️🩹