- Последний пост
- 10 нояб.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Update 👉 አዋጁ ፀድቋል‼ 📌ዜጎች ወደ ኋላ 10 ዓመታት ድረስ ያፈሩት ንብረት "ባለንብረቱ" የገቢ ምንጩን ካላረጋገጠ እንደሚወረስ የሚደነግገው አዋጅ ዛሬ ፀድቋል። 📌ንብረቱ የሚወረሰው የባለ ንብረቱ ገቢ እና ዕድገቱ ተሰልቶ መሆኑንም ይጠቁማል። 📌ይሄው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ በሶስት ተቃውሞ ፣በአራት ድምፅ ተአቅቦ ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው። Lezanews https://t.me/lezanews
видео или голосовое, без подписи
የንግድ ምክርቤቱን የቀደመ ስሙን እንዲያጣ አድርገዋል የተባሉ አካላት ተጠያቂ መደረጋቸው ተገልፆል የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) ባለፉት ሁለት ዓመታት ተደርጓል ባለዉ ግምገማ ምክርቤቱ በተጨባጭ የንግድ ማህበረሰብን የሚመጥን ቁመና ላይ አለመሆኑን አስታውቋል ። በምክርቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ተደርገዋል በተባሉ የኦዲት ግኝት ለአሰራር ጥሰት ምክንያት እንደሆኑ የተገለፁ መመሪያዎች እንዲስተካከሉ እና የቀደመ ስሙን ለመመለስ አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት ተግባራዊ ማድረግ ጀምሬያለሁ ብሏል። ከ 480 ሺህ በላይ ነጋጄዎች በአዲስ አበባ ቢኖሩም ከዚህ ውስጥ የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ከአራት ሺ በታች መሆናቸውን የጠቆሙት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ :- ማንኛውም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውን ነጋዴ አባል የማድረግ ስራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል ። capitalethiopia Leza news https://t.me/lezanews
#AddisAbaba የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ !!! በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በ6 ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ። የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል ፤ " ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራው ነው " ብሏል። " ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ ተጀምሯል ፤ አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ተሰርቷል " ብሏል። በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እንደሚሰራ ፤ የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ 6 ክ/ከተሞች በቀጣይ 5 ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ጠቅሷል። ክፍለ ከተሞቹ ፦ - የካ፣ - ለሚ ኩራ፣ - አቃቂ ቃሊቲ፣ - ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ - ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ እንደሆኑ አሳውቋል። ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክፍለ ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ ድረስ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱን ገልጿል። ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል። ምንጭ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን Leza news https://t.me/lezanews
#AddisAbaba በርካታ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ እንዲሸጡ ቀረቡ። አዲስ አበባ ውስጥ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ለሊዝ ጨረታ መቅረቡ ተሰምቷል። የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት ለሊዝ ጨረታ እንደቀረበ አሳውቋል። የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉ ነው የተሰማው። ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታ የቀረቡ መሬቶች መኖራቸው ተነግሯል። ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ 4ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ነው። 143 ሺሕ 140 ካሬ ሜትር መሬት / ቦታ ለሊዝ ጨረታ ሲቀርብ በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ቢሮው መግለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል። ተጨማሪ መረጃ ፦ 🔴 ለአንድ የጨረታ ሰነድ የሚከፈለው የማይመለስ ብር 2,300 ብር ነው ተብሏል። 🔴 የጨረታውን ሰነድ ከጥቅምት 08/2017ዓ.ም እስከ ጥቀምት 21/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በ (2merkato.com link :- https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link:-https://addisland.afrotender.com) ላይ ነው መግዛት የሚቻለው። 🔴 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ እንዳለባቸው ተገልጿል። 🔴 አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ተብሏል። የጨረታ ቁጥር እና የቦታዎቹን ኮድ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች በዚህ ማግኘት ይቻላል : https://www.aalb.gov.et/blogs/detail/72
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#AddisAbaba #ኮንዶሚኒየም 🔵 " ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " - አቶ አበበ አካሉ ⚫ " የ97 ደግሞ የሚባል የለም። እኛ እስከምናውቀው ዘግተናል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ የኮሪደር ስራ ጋር በተያየዘ በርካቶች በልማት ተነሺነት ከኖሩበት አካባቢ ተነስተው ወደ ተለያዩ ጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ምንም እንኳን ተነሺዎቹ መግባታቸው ላይ ቅሬታ ባይፈጥርም ከ97 አንስቶ ሲቆጥቡ የኖሩ ነዋሪዎች መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸው እና አሁን ላይ አስተዳደሩ ቤት የተሰጠ መሆኑ ቅሬታ አሳድሯል። ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በተካሄደ የኮሪደር ስራውን በሚመለከት የውይይት መድረክ ላይ ይኸው ቅሬታና ጥያቄ ተነስቷል። ጥያቄውን ካነሱት አንዱ ፖለቲከኛው አቶ አበበ አካሉ ናቸው። " ሲቆጥቡ የኖሩ ሰዎች ጉዳይ ምን ደረሰ ? አሁን ማህበረሰቡ ምን ያማል ከተማ አስተዳደሩን ' እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው የልማት ተናሺዎችን እያሰፈረ ያለው ' የሚል ሮሮ አለ። ለዚህ ምንድነው ምላሻችሁ ? ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች መቼ ነው የሚደርሳቸው ፤ መቼ ነው የሚኖሩበት ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ ! " ሲሉ ገልጸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ? " የኮንዶሚኒየም ቤት እስኪ ከየት አምጥታችሁ ነው በዚህ ደረጃ ያላችሁ ኃላፊዎች ' በቆጡት ገንዘብ ነው የሚሰራው ' የምትሉት። እነ ንግድ ባንክ ናቸው ብሩን የሚያቀርቡት እስቲ እንነጋገር ትንሽ ወደ መረጃው ጠጋ ብላችሁ ብናወራ ምናለበት።
видео или голосовое, без подписи
" እስከተባለው ጊዜ ካልገባችሁ በዕጣና በሽያጭ ነው ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፈው " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ ውል የሚቋረጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ማስተላለፉ አመልክቷል። " በተለያዩ ጊዜያት በሽያጭ ተላልፈው የቤት ባለቤቶች ውል የተዋዋሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እና ለፀጥታ ስጋት እየሆኑ ይገኛል " ብሏል። ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው እንደሚቋረጥ ገልጿል። ውል ከተቋረጠ በበኃላ #በዕጣ እና #በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ እንደሚተላለፍ ነው ኮርፖሬሽኑ ' ለመጨረሻ ጊዜ ' ሲል ያስጠነቀቀው።
👉ፒያሳ 📍 መኖሪያ ቤት 🏠 | ሱቅ በተለያዩ የካሬ አማራጮች ከ 480,000 ብር ጀምሮ 👉ስቱድዮ 46 ካሬ / 460,000 ብር ጀምሮ 👉ባለ 1 መኝታ 👉ባለ 2 መኝታ 👉ባለ 3 መኝታ 🏠ሱቅ ከ 10%= 900,000 ብር ጀምሮ ከ 10 እስከ 22 ካሬ ☎️ 0944400844
🔈🔈 ታላቅ የምስራች ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ በማስታወቂያ ዋጋ የቤት ባለቤት ይሁኑ🎁🎁 👉100% ለሚከፍል 40% ቅናሽ ከዚህ በፊት 10 አፓርትመንቶችን ገንብተን በማስረከብ እንታወቃለን!! አሁን ደግሞ 🔺ሳር ቤት🔺 📌በካሬ 57,000ብር ከ156 ካሬ ጀምሮ 🔺አያት ፈረስ ቤት🔺 📌 በካሬ 46,800 ብር ከ81 ካሬ ጀምሮ 🔺 አያት ሎሚያድ ሱፐር ማርኬት ጋር🔺 📌በካሬ 52,800 ብር ከ 129 ካሬ ጀምሮ 🔺ሀይሌ ጋርመንት🔺 📌በካሬ 52,800 ብር ከ139 ካሬ ጀምሮ 🔺 አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ🔺 📌 በካሬ 51,000 ብር ከ113 ካሬ ጀምሮ 👉40/60 እና 60/40 አከፋፈል አዘጋጅተናል። 👉100% ለሚከፍል 40% ቅናሽ 👉ቦታ ለመያዝ እና ሳይት ለመጎብኘት አሁኑኑ ይደዉሉ። 👇👇👇👇👇 +251944400844
በአዲስ አበባ ከተማ የ2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦ - በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ - በኮልፌ ቀራንዮ፣ - በአራዳ፣ - በአቃቂ ቃሊቲ፣ - በየካ፣ - በቦሌ፣ - በአዲስ ከተማ፣ - በቂርቆስ፣ - በጉለሌ - በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል። (ዝርዝር የጨረታው መረጃ በPDF ተያይዟል - ይመልከቱ) ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የጨረታ መረጃ ባለቤት አዲስ ልሳን መሆኑን ያሳውቃል።
Addisland.gov.et መልካም ዜና ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዜጎች ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው ከመሬት ጋር የተያያዘ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የኢንተርኔት አንድ መስኮት (AddisLand.gov.et) ይፋ አድርጓል፡፡
видео или голосовое, без подписи
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱ ተነግሯል። ላለፉት 3 ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ በሚል ነበር ከጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 3 ወራት የመሬት አገልግሎት ታግዶ የቆየው። የከተማ አስተዳደሩ አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከመጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን እንዳስታወቀ ጋዜጣው አስነብቧል።
#Update : የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል። በከተማው በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ለጨረታ መቅረባቸው ይታወሳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝሩን የያዘው ፋይል ምንጭ የአ/አ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ መሆኑን ይገልጻል።
видео или голосовое, без подписи