tgindex
ሠናይ ሚዲያ senay midia

ሠናይ ሚዲያ senay midia

Статистика

ኩሉ አመክሩ ወዘሠናየ አፅንኡ (ሁሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ)

Последний пост
18 июн.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
902
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
525
20 постов
Вовлечённость
58,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://vt.tiktok.com/ZSQnSy4gC/

  • #የእለቱ_ሠናይ_መልእክት #ሠናይ_ሚዲያ https://t.me/senaymidya11 https://www.youtube.com/@senaymedia2618

  • #የእለቱ_ሠናይ_መልእክት #ሠናይ_ሚዲያ https://t.me/senaymidya11 https://www.youtube.com/@senaymedia2618

  • без подписи

  • ፍቁረ እግዚእ፦ በብቸኝነት ከእውነት ጋር በፍቅር የመቆም ትእምርት --#ሠናይ_ሚዲያ---- ከእውነት ጋር በብቸኝነት መቆም የተወለደው በእግረ መስቀሉ ሰር በተገለጠው ጽኑ ፍቅር ነው። ያ እውነት ክርስቶስ ነው። ከእውነት ጋር መቆምን  በእግረ መስቀሉ ስር ወልዶ ያሳየን ደግሞ ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ነው። ብዙዎች ክርስቶስን ሰለተአምራቱ ቢከተሉም፥ ቅዱስ ዮሐንስ ግን ሰለመከራ መሰቀሉ ተከተለው። እውነትን መናገር፣ እውነትን መኖርና ከእውነት ጋር በብቸኝነት መቆም፥  በቤተ መንግሥት ወይም  በቤተ ክህነት አይወለድም። መከራ መስቀሉ ዙፋን በሆነበት ቁርጠኝ ልቡና ውስጥ እንጂ። ብዙዎቻችን በእግረ መስቀሉ ስር በመከራ በታተመ ፍቅር ተወልዳ፥ በበዓለ ጵራቅሊጦስ ድክ ድክ ያለችውን ቅድስት ቤተ ክስቲያን ሰለምትሰጠን ሥጋዊ በረከት ብንከተላትም፥ ቅዱስ ዮሐንስ ክርስቶስን ሰለመከራ መሰቀሉ እንደተከተለው ሁሉ፥ ጥቂቶች ሰለመከራዋም እየተከተሏት ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ “ብዙዎች ክርስቶስን ሰለተአምራቱ ቢከተሉም፥ በመከራው የተከተሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው።” ያለው። ክርስቶስ የሚወደው ብቻ ሳይሆን፥ ክርስቶስን የሚወደው ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የክርስቶስን ሕማማተ መስቀሉን ቀርቦ ሰለተመለከተ እና የመስቀሉ ስር ትውስታው አድርጎ ሰለወሰደው፥ ዕድሜ ዘመኑን ቍጽረ ገጽ ሆኖ አሳለፈ። ክርስቶስ የሚወደን ብቻ ሳይሆን፥ ክርስቶስን የምንወድ ብንሆን ኖሮ፥ በዐይን ሕሊናችን እና በእግረ ልቡናችን ቀራንዮን ተጉዘን፣ በተመስጦ ቀርበን፥ ሕማማተ መስቀሉን ዘወትር እያስታወሰን ቍጽረ ገጽ ሆነን መኖር ነበረብን። እኛ ሌላ የዳንኪራ እና የብልጭልጭ ዓለም ላይ ነን። በግላዊ አኗኗራችን ይቅርና በቤተ ክርስቲያንን ሕይወታችን ስንኳን፥ የቧልት እና የፌዝ ነው። ሕማማተ መሰቀልን፣ ግፋዓ ሰማዕታትንና ኃጢአታችንን ዘወትር እያሰብን፥ ማልቀስ ሲገባን፥ በቅንጡ አጀንዳዎች ዙሪያ ተሰባሰበን የምንጓጓጥ ምስኪኖች ነን። ቅዱስ ዮሐንስ የቆመው ብዙዎች የሸሹት፣ የሚቃወሙትና ቤተሰባዊነት በደም ሳይሆን በእምነት “እነኋት እናት”፤ “እነሆ ልጅሽ” ተብሎ በአምላካዊ ቃል በተመሠረተበት ስፍራ ነው። ክርስቲያን የሚቆመው ብዙዎች በሚራኮቱበት የደም ሰፈራ፤ የአጥንት ቆጠራ  በነገሠበት የጉሰኝነት እና የጎጠኝነት ስፍራ አይደለም። ጉሰኞች እና ጎጠኞች ከሚሽሹበት እና ሰማያውያን ቤተስቦች በተወለዱበት ማኀፀን ነው:: እርሱም እግረ መስቀሉ ያረፈበት ቀራንዮ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ ይህን ቢያደርግ፥ ድንግል ማርያም እናት ሆና ተሰጠችው። በቅዱስ ዮሐንስ አማካይነት እናት ሆና የተሰጠችው ድንግል ማርያም፥ እናቱ እንድትሆነው የፈቀደ ሰው ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስን መስሎ፤ ቅዱስ ዮሐንስ በቆመበት የእውነት እና የፍቅር ስፍራ መቆም አለበት። በክርስትና ውስጥ አድርባይነት የለምና። ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ በረከት ሁላችንንም ያሳትፈን። ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም #ሠናይ_ሚዲያ

  • без подписи

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልዑካን ቡድን በአርሲ ጥቃት ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ተወያየ ----ሠናይ ሚዲያ---- በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የተመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ፣ ከሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ኸይረዲን ተዘራ እና ከኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት አሳውቋል። ልዑካን ቡድኑ በምሥራቅ አርሲ በአሰኮ፣ በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በታጣቂዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ በደረሰው የሕይወት ሕልፈትና በጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን መቃጠል የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸዋል። መንግሥት የችግሩን ምንጭ አጣርቶ ዘላቂ ሰላም እንዲያሰፍን፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ እና ወንጀለኞች ለሕግ ቀርበው ቅጣታቸውን እንዲያገኙ ጠይቀዋል። የምሥራቅ አርሲ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕም የተከሰተውን ችግር በቊጥራዊ ማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ በተፈጠረው አደጋ ማዘናቸውን ገልጸው፣ አስቸኳይ አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንና በሪፖርቱ መሠረት እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል። የኦሮሚያ ክልል ኃላፊዎችና የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አመረሮች በበኩላቸው ተጨማሪ አደጋን ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ አጥፊዎችን ለሕግ ለማቅረብና ቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናንን ለመደገፍ በምታደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ፣ የተቃጠለውን ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለመገንባትና መሰል ችግሮች ዳግመኛ እንዳይከሰቱ ለማድረግ ከተጠናከረ ሥራ ጋር በትኩረት እንደሚንቀሳቀሱ አስታውቀዋል። #ወገኔ_ቅድሚያ_ነው #ሃይማኖቴ_ክብሬ_ነው #እንባን_እናክብር #ሠናይ_ሚዲያ

  • без подписи

  • የሰኔ ጾም (ጾመ ሐዋርያት) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ (የግዴታ) ጾሞች አንዱ ነው። ይህ ጾም በየዓመቱ የጰራቅሊጦስ (የመንፈስ ቅዱስ መውረድ) በዓል በዋለ ማግስት በሰኞ ቀን ይገባና ሐምሌ ፭ (5) ቀን በቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት ቀን ይፈታል። የዚህን ጾም መንፈሳዊ ምስጢር፣ ለምን እንደምንጾም እና እነማን መጾም እንዳለባቸው በአመክንዮ እና በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እንደሚከተለው በዝርዝር እንመልከት፦ 1. የሰኔ ጾም (ጾመ ሐዋርያት) ለምን እንጾማለን? እኛ ክርስቲያኖች ይህንን ጾም የምንጾምበት ሦስት ዋና ዋና መንፈሳዊና ታሪካዊ ምክንያቶች አሉን፦ ሀ) የሐዋርያትን አርአያነት ለመከተል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሳለ አይሁድ “ደቀ መዛሙርትህ ለምን አይጾሙም?” ብለው በጠየቁት ጊዜ፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያን ጊዜም ይጾማሉ” (ማቴ 9፥15) ብሎ ትንቢት ተናግሮ ነበር። ጌታችን አርጎ፣ በ፶ኛው (50ኛው) ቀን መንፈስ ቅዱስ በነደደ እሳት አምሳል በሐዋርያት ላይ ከወረደላቸው በኋላ፣ ሐዋርያት ወንጌልን ዓለምን ዞረው ከመስበካቸው በፊት አስቀድመው በጾምና በጸሎት ራሳቸውን አዘጋጅተዋል። እኛም የሐዋርያትን ፍልስፍና እና ፈለግ በመከተል፣ መንፈሳዊ ኃይልን ለማግኘት እንጾማለን። ለ) ለአገልግሎትና ለስብከተ ወንጌል ስኬት ሐዋርያት በጾም ውስጥ ሆነው ሳለ መንፈስ ቅዱስ መመሪያ ይሰጣቸው ነበር። ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ 13፥2-3 ላይ እንዲህ ተጽፏል፦ “እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጾሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። በዚያን ጊዜም ከጾሙና ከጸለዩ እጃቸውንም ከጫኑባቸው በኋላ ሰደዷቸው።” ይህ የሚያሳየው ጾም መለኮታዊ ጥሪን ለመስማትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲከናወን ታላቅ መሣሪያ መሆኑን ነው። እኛም ዛሬ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሰፋ፣ ወንጌል እንዲጸና በዚህ ጾም እንማጸናለን። ሐ) በረከትንና ሰላምን ለማግኘት ሰኔ ወር የክረምት መጀመሪያ፣ ገበሬው ዘር የሚዘራበትና አገር ወደ አዲስ የምርት ወቅት የምትሸጋገርበት ጊዜ ነው። ስለዚህ ሕዝቡ በሥጋውም ሆነ በነፍሱ እግዚአብሔር የሰላምና የበረከት ክረምት እንዲሰጠው፣ ምድር ፍሬዋን እንድትሰጥ በዚህ ጾም ወደ ፈጣሪው ይጮኻል። 2. እነማን ናቸው መጾም ያለባቸው? በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት፣ ይህ ጾም የአዋጅ (የጋራ) ጾም በመሆኑ፦ እያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሁሉ መጾም አለበት፦ ጾሙ “የመነኮሳት ወይም የካህናት ብቻ” ሳይሆን የጠቅላላው ምእመናን ጾም ነው። ሕፃናት የጾም ዕድሜያቸው ከደረሰ (ከ7 ዓመታቸው) ጀምሮ፣ ወጣቶች፣ አባቶችና እናቶች በሙሉ የመጾም ግዴታ አለባቸው። ልዩ ሁኔታዎች (ሕጋዊ ፈቃዶች)፦ እንደማንኛውም ጾም ሁሉ፣ በጣም በጽኑ የታመሙ ሰዎች፣ ነፍሰ ጡር እናቶች እና የሚያጠቡ እናቶች ከነፍስ አባታቸው ጋር በመመካከር በጾሙ ሥርዓት ላይ ቀኖናዊ ማቃለያ ሊደረግላቸው ይችላል። ከዚህ ውጭ ግን ጤነኛ የሆነ ክርስቲያን ሁሉ ሊጾመው ይገባል። 3. የመንፈሳዊ አመክንዮ ሚዛን (Theological Logic) አንዳንዶች “ይህ ጾም የሐዋርያት ከሆነ እኛ ለምን እንጾማለን?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። የአባቶች ትምህርት አመክንዮ፦ እኛ የሐዋርያት ልጆች ነን፤ ቤተ ክርስቲያናችንም "አንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊትና ሐዋርያዊት" (Apostolic) ተብላ በነገረ ሃይማኖት ትታወቃለች። #ሠናይ_ሚዲያ #ሠናይ_ጾም

  • без подписи

  • ❖ ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ❖ ❀❀❀ ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ✿✿ ✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡ 27-29 ✿✿✿ ✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ✿✿✿ ✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ✿✿✿ ✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ✿✿✿ ✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ✿✿ ✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ #ሠናይ_ሚዲያ በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@senay_midea?_r=1&_t=ZS-95TxzBS7HSW በቴሌግራም https://t.me/senaymidya11

  • без подписи

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከ7ኛ ፎቅ ወድቆ የተነሳው ታዳጊ — የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ (አቡ ሰይፈይን) ድንቅ ተአምር! "ሚና በሰዎች ፊት ሞተ… ትንፋሽም ሆነ የልብ ምት አልነበረውም።" ነገር ግን ከአንድ ቅጽበት በኋላ… ተነሳ! አሳለ… ተንቀሳቀሰ… ወደ ሕይወትም ተመለሰ! ይህ በግብፅ ሽሩቅ ከተማ በኦስታዝ ማግዲ ዛኪ (የመንግስት ሰራተኛ) ቤተሰብ ላይ የደረሰ እውነተኛ ታሪክ ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው፦ አደጋው እንዴት ደረሰ? የ16 ዓመቱ ታዳጊ ሚና በ7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቤታቸው ጣራ ላይ ውሾቹን እያጫወተ ነበር። ድንገት ጓደኛው ከመንገድ ሆኖ ሲጠራው ለመስማት ራሱን ዝቅ አደረገ። የጣራው በረንዳ ግንብ (አጥር) አልነበረውም። በዚያች ቅጽበት ሚናን አዞረውና ከሰባተኛ ፎቅ ላይ ቁልቁል ወደ አስፋልቱ ተፈጠፈጠ። "ሞተ" ተባለ… ተስፋ ተቆረጠ! ጎረቤቶች በድንጋጤ ወደ ስፍራው ሲሮጡ ሚና በጀርባው ወድቆ አገኙት። ምንም የሕይወት ምልክት አልነበረውም። ትንፋሽ የለም፣ የልብ ምት የለም፣ እንቅስቃሴ የለም። በዙሪያው የነበሩ ሰዎች ሁሉ "አከተመለት፣ ሞተ" ብለው ተስፋ ቆረጡ። የእምነት ጩኸትና የዘይቱ ተአምር በዚያ የጭንቅ ሰዓት ጎረቤታቸው ወይዘሮ ናጅዋ በሙሉ ልቧ ወደ ሰማይ ጮኸች፦ “የአቡ ሰይፈይን (ቅዱስ መርቆሬዎስ) አምላክ ሆይ ድረስልን!” እያለች ወደ ቤቷ ሮጠች። ከገዳም ያመጣችውን ጥቂት ቅዱስ ዘይት ይዛ ተመለሰች። የሚናን ደረት በዘይቱ ማሸት ሲጀምሩ የታየው ነገር ግን ድንቅ ነበር! ያቺ በጠርሙስ ውስጥ የነበረች ጥቂት ዘይት እንደ ምንጭ መፍለቅ ጀመረች። የሚና አካል ከራስ እስከ እግሩ በዘይቱ ተጠመቀ። ትንሳኤ! ዘይቱ እንደፈሰሰ ሚና በኃይል "ትንፋሽ" ሳበ! ነፍሱ ተመለሰች። እግሩን አነቃነቀ፣ አሳለ፣ ሊቀመጥም ሞከረ። የነበረው ድንጋጤ ሁሉ ወደ ደስታና እልልታ ተቀየረ። "አዲስ ሕይወት ተሰጠው!" እየተባለ ወደ ሆስፒታል ተወሰደ። የሐኪሞች ምስክርነት በሆስፒታል የተደረገለት ምርመራ ሁሉ (CT Scan, Ultrasound, X-ray) ውጤቱ 100% ጤነኛ መሆኑን አረጋገጠ። ከሰባተኛ ፎቅ ወድቆ አንድም ስብራት፣ አንድም የውስጥ ደም መፍሰስ አልተገኘበትም። ሐኪሞቹ በአንድ ድምፅ "ይህ ተአምር እንጂ ሌላ አይደለም" በማለት መሰከሩ። ትምህርቱ ምንድነው? በ“ገደል” አፋፍ ላይ ሳለን… እግዚአብሔር ሩቅ አይደለም። በተስፋ መቁረጥ ደቂቃ ውስጥ ከእውነተኛ ልብ የሚወጣ ጸሎት ሁሉንም ነገር ሊለውጥ ይችላል። እግዚአብሔር አለ… ይጎበኛል… ከማሰብ በላይም ይሰራል! የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ (አቡ ሰይፈይን) በረከትና አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን!

  • አንዳንድ ነገሮች ስለ ዐቢይ ጾም .... በጾም ወራት በሥጋና በነፍስ መካከል ከባድ ጦርነት ይደረጋል። ይህ የጾም ጊዜ ሥጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት፤ የሥጋን ገደብ የለሽ ጩኸት ቀንሰን የነፍስን እስትንፋስ የምናዳምጥበት ጊዜ ነው:: ይህ ወቅት ይህንን የሥጋን ፈቃድን ከየትኛውም ጊዜ በላይ በቆራጥነት ለመፋለም፤ የአሽናፊነታችንን ክንድ የምናነሣበት ጊዜ ነው:: ስለዚህ ክርስቲያናዊ የሕይወት ጉዞ ትግሉ፣ ፈተናውና ጦርነቱ ሁሉ ከገዛ ፈቃድ ጋር ነው፤ ጠላቶቻችን ያሉት በውስጣችን ናቸውና፡፡ እነርሱም ትዕቢት፣ ቅናት፣ ስስት፣ ንፍገት፣ ሐኬት ... ወዘተ ናቸው:: ምናልባትም እነዚህ ኀጢአቶች አብረውን ለዘመናት የተጓዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሆኖም ግን ውጊያው ዛሬ ካልተጀመረ ነገ ባርነቱ አያበቃም፡፡ ሐዋርያው እንደሚለው:- ❝የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው❞ — በማለት የድልና የትንሣኤ እድል ማግኘት የሚቻለው ዛሬን በመጠቀም እንደሆነ ነግሮናል (፪ኛ ቆሮ ፮፥፫)። በውጊያው ውስጥ ድልን የምንቀዳጅበትን ዘዴ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን:- ❝በቀረውስ ወንድሞቼ በጌታና በኀይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ በሙሉ ልበሱ❞ — በማለት መከላከያ መሣሪያችን ምን እንደሆነ ተናግሯል (ኤፌ ፮፥፲፩)። ሕይወታችን ቁጥቋጦ እንደ በዛበት እርሻ ነው፤ በእርሱ ውስጥ ከሚበቅሉት እሾኾች አንዱና የኀጢአቶች ሁሉ አባት ትዕቢት ነው:: ይህም የሌሎች የኀጢአት ቁጥቋጦዎች ዘር፣ ሥርና ግንድ ነው:: ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔርና ከባልንጀራችን ጋር የሚያራርቀንና ስምምነት የሚያሳጣን የትዕቢት መንፈስ ነው:: ሳጥናኤል ከማኅበረ መላእክት የተለየበት ከሰማይ የወደቀበት፣ አዳም ከገነት የተባረረበት ምክንያት ትዕቢት ነው:: እያንዳንዱ ኅብረተሰብ ፍቅርና ሰላም የሚያጣበት ዋነኛ ምክንያት ትዕቢት ነው፡፡ ስለዚህ ከልቡናችን ከሚመነጭ ጠላት ጋር በጥብቅ መዋጋት የምንችለው በጾም ነው:: መጽሐፍ ቅዱስ:- ❝ትዕቢተኛ ሰው ወደ ጥፋት ያመራል፥ ትሑት ሰው ግን ክብርን ይጎናጸፋል❞ — በማለት ክብርን የሚያሳጣ ከእግዚአብሔር የሚነጥል የሰው ቀንደኛ ጠላት ትዕቢት መሆኑን ነግሮናል (ምሳ ፲፰፥፲፪)። ጾሙ «ዐቢይ ጾም» ለምን ተባለ? ፩. ዐቢይ ጾም ማለት ከሁሉም የሚበልጥ ታላቅ ከፍ ያለ ጾም ማለት ሲሆን «ዐቢይ ጾም» የተባለበት ምክንያት ስለብዙ ምሥጢር እንደሆነ አበው ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ይኸውም የመጀመሪያው በብሉይ ኪዳን ለተጾሙ አጽዋማት ማረጋገጫ ምስክር፤ በሐዲስ ኪዳን ለተጾሙ አጽዋማት ደግሞ አብነት በር ከፋች ስለሆነ ነው፤ ጾም በሃይማኖት ለሚኖሩ እግዚአብሔር የሚወደው ቅዱስ ተግባር መሆኑን የሚገልጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጥቅሶች ቢኖሩም ከጥቅሶቹ በላይ ዐቢይ ምስክሩ ተግባራዊ ማስረጃው ይህ ዐቢይ ጾም ነው፡፡ ስለዚህ ለብሉይ ኪዳንም ሆነ ለሐዲሳት ኪዳን አጽዋማት ራስ በመኾኑ ዐቢይ ጾም ተብሏል (ማቴ ፲፩፥፳፯)። ፪. «ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ወአልቦ ኍልቍ ለጥበቢሁ›› የተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመሆኑ ከጿሚው ክብርና ልዕልና የተነሣ በዐቢይ እግዚአብሔር ዐቢይ ጾም ተብሏል:: ቅዱስ ያሬድ:- ❝እስመ ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ለእግዚአብሔር ኵሉ ዓለም ተግባሩ ዐቢይ ውእቱ ወዐቢይ ኀይሉ መርሖሙ ለዕውራን ወሀቤ ሰላም ብርሃን ለጻድቃን ክርስቶስ — የጻድቃን ብርሃን የሰላም ባለቤት ክርስቶስ ዕውራንን መራቸው፣ የእግዚአብሔር ጎይሉ ታላቅ ነው፤ በዓለም ሥራው ሁሉ ታላቅ ነው፤ ኀይሉ ታላቅ ነው እግዚአብሔርታላቅ ነውና❞ — በማለት ታላቅነቱ የባሕርይ ገንዘቡ መሆኑን መስክሯል (መዝ ፵፯፥፩ ፤ ጾመ ድጓ ዘደብረ ዘይት)። ከአዳም ጀምሮ አበው የጾሟቸው አጽዋማት እንደ ዋዜማ እንደ ማስታወቂያ ሆነው ጌታ ለሚጾመው ዐቢይ ጾም መንገድ ጠራጊ አዋጅ ነጋሪ ናቸው:: ሌሎቹ አጽዋማት የተጾሙት በፍጡራን ነው፥ ዐቢይ ጾም የተጾመው ግን በፈጣሪ ነው፤ ሌሎች አጽዋማት ጌታን ለማግኘት የተጾሙ ናቸው፥ ዐቢይ ጾም ግን ራሱ ጌታ በሥጋ ተገልጦ በአካል ተገኝቶ የጾመው ጾም ነው፤ ሌሎቹ አጽዋማት የተጾሙበት ምክንያት ዓለምን የሚያድነው ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል በሚል ተስፋ ደጅ ለመጥናትና ለመማፀን ሲሆን፥ ይህ ጾም ግን ያ ሁሉ ተስፋና ትንቢት ፍጻሜ ያገኘበት ነው። በመስቀሉ ሰላማችን፣ በሞቱም ትንሣኤያችን፣ የተረጋገጠበት ነውና «ታላቅ ጾም» ተብሏል:: ፫. በኀዘን የሚጾም በመሆኑ ይህንኑ ለማሰብ በዚህ በዐቢይ ጾም የከበሮና የጸናጽል ማሕሌታዊ ምስጋናዎች አይቀርቡበትም። ምክንያቱም ከበሮና ጸናጽል የደስታ መዝሙር ማመስገኛ በመሆናቸው ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ ከቆመ ሳይቀመጥ ከጀመረ ሳያቋርጥ ከሰው ተለይቶ ከበአት ተከቶ ዐርባ መዓልት ዐርባ ሌሊት መጸሙን የምናስበው በኀዘን ነው። ምክንያቱም እርሱ ይህን ሁሉ ያደረገው ለራሱ ሳይሆን ለእኛ ነውና የደከመውን ድካም፣ የተራበውን መራብ፤ የተጠማውን መጠማት በኀዘን ከማሰብ ውጭ በምንም ልናስበው አንችልም። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚህ በዐቢይ ጾም የሚባሉ የኀዘን ቀለማት (ምስጋናዎች) በየሰዓቱ ለየቀናቱ ደልድሎ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ማለት ከዘወረደ እስከ በዓለ ትንሣኤ ድረስ ባሉት ቀናት ዐበይት ሊቃውንቱ የሚዘምሩት የየሰዓቱ ምስጋናዎች አሉ። የሌሊት የነግህ፣ የሦስት ሰዓት፣ የስድስት ሰዓት፣ የዘጠኝ ሰዓትና የሠርክ በመባል ይከፈላሉ:: እነዚህ ቀለሞች ቁም ዜማ ሲሆኑ ጣዕመ ዜማቸውም ዘለግ ብለው ከጉሮሮ ሲወጡ የሚያሳዝኑ የሚያስለቅሱ ልብን የሚነኩ ማኅዘኒ ዜማዎች ናቸው:: ሊቃውንቱ ጾም ምዕራፉንና ጾመ ድጓውን እያዋሐዱ እያስተዛዘሉ ግራና ቀኝ እየተቀባበሉ ከቆሙ ሳይቀመጡ ከጀመሩ ሳያቋርጡ በኀዘን፣ በትካዜና በስግደት የሚያመሰግኑበት ታላቅ ጾም ነው:: ዳግመኛም ዐቢይ ጾም ታላቅ የሱባኤ ጾም በመሆኑ ሴቶቹ ጌጣቸውን ወንዶቹ የደስታ የክብር ልብሳቸውን መተው እንደሚገባቸው አባቶቻችን በፍትሕ መንፈሳዊ ደንግገዋል (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭፥፭፻፺፮)። ፬. የደስታ በዓላትን የሚሽር ታላቅ ጾም በመሆኑ ይህ ማለት ዐቢይ ጾምን ከሌሎች አጽዋማት መካከል ልዩ የሚያደርገው ታቦተ ሕግ ወጥቶ በዕልልታ በደስታ የሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት በዐቢይ ጾም ላይ ቢውሉ ጾሙ የኀዘን ጾም እንደመሆኑ መጠን ለጾሙም ሆነ ለበዓሉ ክብር ሲባል ክብረ በዓሉን ከጾሙ በፊት እንዲከበር አባቶቻችን ሥርዐት ሠርተዋል:: ለምሳሌ ቃና ዘገሊላ ታሪኩ የተከናወነው ሚያዚያ ፳፫ ቀን እንደኾነ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፤ ሆኖም ብዙ ጊዜ በዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል በዓሉ የደስታ በዓል ስለሆነ አባቶቻችን በቀኖናቸው ወደ ጥር ፲፪ በማምጣት በጥምቀት ማግስት እንዲከበር አድርገዋል:: አያይዘውም:-

  • без подписи

  • без подписи

  • የነነዌ ሰዎችና እኛ ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? "ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ" ተብለው ተጠርተዋልና። ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሯቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይሁን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- ❝በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች❞ — ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና. ፫፥፬)፡፡ ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ሆነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ሁሉ እንጂ አንዱን ወይም ሁለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ «እንዲህ የሚልስ የት አለ?» ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና «የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል» ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የሆነን ምስክርነት አስቀምጧልና። እንዲህ ሲል፡- ❝እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ❞ — (ዮና. ፩፦፭፣ ፫፥፲) ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ «ከክፉ መንገዳቸው» አለ እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡ እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ሁሉ ማስወገድ ከቻሉ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ «የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል» የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡ የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ሁሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድ የለሽነት ሆኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን - ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከሆነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡ 📖 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ — በእንተ ምክንያተ ሐውልታት እንኳን ለጾመ ነነዌ አደረሳችሁ!

  • без подписи

  • #ጥር ➏ በዓለ ግዝረት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ እና የመጀመሪያው ይህ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት ነው። ሉቃ1 :21 ሊገርዙትም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ በማኅፀን ሳይገረዝ በመልዐኩ እንደተባለው ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ። እመቤታችንም ወደ ወደ ግዝረት ቤት ወሰደችው ገራዡም ምላጩን ይዞ ቀረበ ነገር ግን ምላጩ እጁ ላይ ሳለ ውሀ ሆኖ ፈሰሰ ጌታችንም በተዓምር የተገረዘ ሆኖ ተገኘ ይላል ምነዋ ቢባል ጌታችን ደሙ የሚፈሰው ስጋውም የሚቆረሰው አንዴ እና እርሱም በእለተ አርብ ስለሆነ ብቻ ነው። ጌታችን የሰውን ስርአት ሁሉ ጠብቋል እራሱ እንደተናገረው እኔ ህግን እና ነብያት ልሽር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈፅም እንጂ ልሽር አልመጣሁም። ማቴ 5 :17 ብሎ እንደተናገረው ነው። ከድንግል ማርያም የመወለዱ ሚስጢር ሊመረመር እንደማይችል ሁሉ እናም ሲወለድም ድንግልናዋን እንዳለወጠው ሁሉ ግዝረቱም በማይመረመር ምስጢሩ እንዲሁ ሆነ ። እንደዚሁም በር ተዘግቶ ሳለ ወደ ሀዋርያት እንደገባ ሁሉ ግዝረቱም እንደዚያው ከሰውነቱ ምንም ሳይቆረጥ ህግን ይፈፅም ዘንድ በድንቅ ሚስጢሩ ይህን አደረገ ምክንያቱም የሚገረዝባቸው ምላጮች ቀልጠው እንደ ውሀ ሆነዋልና። በእውነቱ እርሱ የእስራኤል ገዢ ሲሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነውና ። እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት በሰላም አደረሰን ። #_ሰናይ__ቀን ሠናይ ሚዲያ በአዲስ የዩቱብ ቻናል መተናል በብስክራብ በማደረግ ይከታተሉን ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCFZrceurPVvpMGNHzpGdZqA

  • без подписи