- Последний пост
- 2 мая
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የ45 ቀን ቴትራ ኤች ጫጩት ከ15 ቀን በኋላ የሚወጡ መግዛት የሚፈልግ አድራሻ ሰሜን ወሎ ወልድያ 0983888894
የዶሮዎችን የእንቁላል ምርታማነት ለመጨመር የሚረዱ ቁልፍ ዘዴዎች የእንቁላል ምርት መቀነስ በዶሮ እርባታ ትርፋማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማቆየት የሚከተሉትን ነጥቦች መተግበር አስፈላጊ ነው፦ ተገቢውን የመኖ መጠንና ጥራት ማረጋገጥ፦ ዶሮዎች በቂ ፕሮቲን (16% - 18%) እና ካልሲየም ያለው መኖ ማግኘት አለባቸው። ካልሲየም ጠንካራ የእንቁላል ቅርፊት እንዲኖር ይረዳል። የብርሃን ሰዓትን ማስተካከል፦ ዶሮዎች ቀጣይነት ያለው የእንቁላል ምርት እንዲኖራቸው በቀን ውስጥ ከ14 እስከ 16 ሰዓታት ብርሃን ያስፈልጋቸዋል። የተፈጥሮ ብርሃን ሲያንስ ሰው ሰራሽ መብራቶችን በመጠቀም ማሟላት ይቻላል። ንጹህና ቀዝቃዛ ውሃ በበቂ ሁኔታ ማቅረብ፦ እንቁላል በውስጡ ከፍተኛ የውሃ መጠን ስላለው፣ ውሃ ለጥቂት ሰዓታት እንኳን ቢቋረጥ ምርት ላይ ትልቅ ቅናሽ ያስከትላል። ጭንቀትን (Stress) መቀነስ፦ ከፍተኛ ድምጽ፣ የቤት እንስሳት (እንደ ውሻና ድመት) ረብሻ፣ ድንገተኛ የሙቀት ለውጥ እና የሰው መብዛት ዶሮዎች እንዲጨነቁና እንቁላል እንዲያቆሙ ያደርጋል። የዶሮዎችን ጤና መከታተል፦ በተለይ የውስጥ ጥገኛ ትሎች (Worms) እና ቅንቅን ምርታማነትን በእጅጉ ይቀንሳሉ። በየጊዜው ትል ማጥፊያ መድኃኒቶችን መስጠት ያስፈልጋል። የእንቁላል መጣያ(Nesting boxes) ዝግጅት፦ ዶሮዎች ምቹ፣ ጨለምለም ያሉና ንጹህ የመክተቻ ሳጥኖች ካገኙ እንቁላል ከመጣል አይቦዝኑም። ይህ እንቁላል እንዳይሰበርም ይረዳል።
ጠቃሚ የዶሮ በሽታ መድኃንቶች። 1.Amprolium –ኮክሲድዮስስን ለማከም። 2. Tylosin – የመተንፈሻ አካላት በሽታ፣የዶሮዎች ከባድ ጉንፋን CRD ለማከም። 3. Enrofloxacin (Ashnerio)– ለብዙ የባክቴርያ በሽታን ለማከም ለመተንፈሻና የMycoplasma Broad-spectrum antibiotic። 4. Neomycin –ለአንጀት ውስጥ በሽታ፣ለዶሮ ተቅማጥ። 5. Doxycycline –ለመተንፈሻ ችግር፣ለተቅማጥ እጅግ ተመራጭ ነው። 6. Oxytetracycline –ለባክቴርያ በሽታ ቁስልን ለማድረቅ። 7. Sulfadimethoxine _ለኮክሲድዮስስ፣ለባክቴርያ። 8. Ivermectin – የውስጥ ጥገኛን ለማከም፣ለቅንቅን። 9. Erythromycin – ለመተንፈሻ አካላት በሽታ። 10. Flubendazole.የአንጀት ውስጥ ትላትሎችን ለማስወገድ።
без подписи
የእነዚህን ሁለት አእዋፋት ስም የሚነግረኝ? በኛ አገር ተሞክሮስ ወደ ቢዝነስ ብንለውጣቸው ምን መሰናክል ሊገጥመን ይችላል? ምንስ መልካም አጋጣሚ ይኖረናል? እስኪ እንወያይ!
እንደምን አመሻችሁ ተከታታዮቻችን . . . ውይይታችን ተጀምሯል! ውይይቱን ማስታወሻ በመያዝ በጥሞና እና በአንክሮ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። ከርዕሱ ጋር የሚዛመዱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከስር ባለው ኮሜንት መስጫ ሳጥን ላይ ማስፈር ትችላላችሁ! 👇👇👇 የውይይቱን ሊንክ ለሌሎች ጋብዙ! https://t.me/selesera?livestream
ለጀማሪ ዶሮ አርቢ ውጤታማ እንዲሆን የሚረዱ ጥቂት ምክሮች፡ ከመጀመርህ በፊት፡ እውቀትህን አስፋ: ስለ ዶሮ እርባታ በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን ሰብስብ። መጽሃፎችን አንብብ፣ ጽሁፎችን ተመልከት፣ ከሌሎች ልምድ ካላቸው አርቢዎች ተማር፣ በይነመረብ ላይ መረጃ ፈልግ። ስለ ዶሮ ዝርያዎች፣ አመጋገብ፣ በሽታዎች፣ እንክብካቤ እና የገበያ ሁኔታዎች መረዳትህ አስፈላጊ ነው። የቢዝነስ እቅድ አዘጋጅ: ምን ያህል ዶሮዎች እንደምታረባ፣ ምን አይነት ዝርያ እንደምትጠቀም፣ የት እንደምታረባ፣ ወጪዎችህ ምን እንደሚሆኑ እና ምርቶችህን እንዴት ለገበያ እንደምታቀርብ የሚያሳይ ዝርዝር እቅድ አውጣ። ገበያውን መርምር: በአካባቢህ ለዶሮ እና ለዶሮ ተዋጽኦዎች (እንቁላል፣ ስጋ) ያለውን የገበያ ፍላጎት ተረዳ። ተወዳዳሪዎችህ እነማን እንደሆኑ እና የትኞቹ ምርቶች በብዛት እንደሚሸጡ እወቅ። በጀትህን አቅድ: ለዶሮዎች ግዢ፣ ለምግብ፣ ለክትባት፣ ለዶሮ ቤት ግንባታ ወይም ኪራይ እና ለሌሎች ወጪዎች በጀት መድብ። ዶሮዎችን ስታሳድግ፡ ጥሩ ዝርያ ምረጥ: ለምታስበው ምርት (እንቁላል ወይም ስጋ) ተስማሚ የሆነ ጤናማ ዝርያ ምረጥ። ጥሩ ቤት አዘጋጅ: ዶሮዎቹ ምቹ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ቤት ሊኖራቸው ይገባል። ቤቱ በቂ አየር ማናፈሻ፣ ብርሃን እና ሙቀት ሊኖረው ይገባል። ከአዳኞችም መጠበቅ አለበት። ትክክለኛ አመጋገብ ስጥ: ዶሮዎች ለዕድገታቸው እና ለምርታማነታቸው አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ሚዛናዊ ምግብ መመገብ አለባቸው። ንጽህናን ጠብቅ: የዶሮ ቤቱን እና አካባቢውን ንጹህ ማድረግ በሽታዎችን ለመከላከል ወሳኝ ነው። የጤና ክትትል አድርግ: ዶሮዎችህን ለበሽታዎች በየጊዜው ይመርምሩ እና አስፈላጊውን ክትባት ይስጡ። መዝገቦችን ያዝ: ስለ ዶሮዎችህ፣ ስለ ምግብ አወሳሰዳቸው፣ ስለ እንቁላል ምርታቸው፣ ስለ ወጪዎችህ እና ስለ ገቢዎችህ ዝርዝር መዝገብ ያዝ። ይህ መረጃ ለወደፊት እቅድህ እና ትርፋማነትህን ለመገምገም ይጠቅማል። ተጨማሪ ምክሮች፡ በትንሽ ጀምር: ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቂት ዶሮዎችን በማርባት ልምድ ስትቀስም ወደ ብዙ ዶሮዎች መሄድ ትችላለህ። ከሌሎች አርቢዎች ጋር ተገናኝ: ከአካባቢህ ካሉ ሌሎች ዶሮ አርቢዎች ጋር ተገናኝ እና ተማከር። በትዕግስት ስራ: ዶሮ እርባታ ጊዜ እና ትዕግስት የሚጠይቅ ስራ ነው። እነዚህን ምክሮች በመከተል ጀማሪ ዶሮ አርቢ ሆነህ ውጤታማ መሆን ትችላለህ። መልካም ዕድል!
без подписи
እስከ 30 ዶሮ የመያዝ አቅም ያለው ተደራራቢ 2ሜ በ1ሜ የሆነ ከብረት የተሰራ የእንቁላል ጣይ ኬጅ
በዶሮ እርባታ ንግድዎ ውስጥ ትርፋማነትን ለመጨመር የሚያግዙ አንዳንድ ስልቶች 1. ትክክለኛውን የዶሮ ዝርያ ይምረጡ የዶሮ እርባታ ቢዝነሱን በፈለጉበት ዘርፍ መሰረት ምርታማ የሆኑ የዶሮ ዝርያዎችን መምረጥ ያስፈልጋል። ለእንቁላል ጣይ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ቦቫንስ ወይም በቅርቡ ደግሞ ዋይት ሌግሆርን የሚባሉ ዝርያዎች ወደገበያ ስለተቀላቀሉ እነሱን መጠቀም ውጤታማ ያደርጋል። በቀጣይ ስለ ስጋ ዶሮ ዝርዝር መረጃ አቀርብላችኋለሁ። 2. ምግብን እና አመጋገብን ያሻሽሉ ጥራት ያለው ምግብ ፣ጤናማ እድገትን እና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥራት ባለው ምግብ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልጋል። ጥራቱ ያልተረጋገጠ መኖ ምርታማነትን ከመቀነሱም ባሻገር የዶሮዎችን ጤንነት ስለሚጎዳ የመኖ ጥራት የቢዝነሱን ውጤታማነት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። የምግብ አስተዳደር ብክነትን የሚቀንስ እና የንጥረ-ምግብን መጠን ከፍ የሚያደርግ የአመጋገብ መርሃ ግብር ተግባራዊ ማድረግም ያስፈልጋል። ይህ ምን ማለት መሰለህ የሰው ልጅ ቁርስ ምሳ ራት እያለ በሰአት ከፋፍሎ እንደሚመገብ ሁሎ የዶሮዎችም የአመጋገብ ስርአት በሰአት ተከፋፍሎ በቀን መመገብ ያለባቸውን ከ95 እስከ 115 ግራም መኖ ማግኘት መቻል አለባቸው። የሚከተለውን የምገባ ፕሮግራም መከተሉ ይበልጥ ውጤታማ ያደርግሀል። • ጧት 12 ሰአት ላይ 30 – 35 ግራም መኖ • ረፋድ 5 ሰአት ከ25 – 30 ግራም መኖ • ከሰአት 9 ሰአት ከ20 – 25 ግራም መኖ • ወደ ማታ 12 ሰአት ከ20– 25 ግራም መኖ አንድ ዶሮ ማግኘት ከሚገባት መኖ ፍላጎት በላይ ከተመገበች ውጤታማነቷ ላይ ተፅእኖ ስለሚኖረው ምግብ እንዳያንስ እንደሚያሳስበን ሁሉ እንዳይበዛም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ከፍተኛ መኖ መመገብ እንቁላል የመጣል ምጣኔን ይጨምራል የሚባል አባባል ስህተት ነው እንደውም እንቁላል መጣል ይቀንሳሉ። ሌላው የውሀ ፍጆታ መከታተል ሲሆን ጥራቱን የጠበቀ ውሀ ሙቀቱ ከ15°c ያላነሰ እንዲሁም ከ25°c ያልበለጠ ንፁህ ውሀ መስጠት ያስፈልጋል። አንድ ዶሮ በቀን እስከ ግማሽ ሊትር ውሀ ያስፈልጋል። 3. የመኖሪያ ሁኔታዎችን(Improve Housing Conditions) ማሻሻል በቂ ቦታ፦ በጉዝጓዝ ለሆነ እርባታ የዶሮ እርባታዎ ለመንቀሳቀስ በቂ ቦታ ሊኖረው ይገባል። ይህም ጭንቀትን ይቀንሳል እንዲሁም እድገትን ያበረታታል። በካሬ ሜትር ከ6–8 ዶሮ መሆን አለበት። ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን ግን ኬጅ ሲስተም መጠቀም ያስፈልጋል። አየር ዝውውር ፡- ትክክለኛ የአየር ዝውውር ጤናማ አካባቢን ለመጠበቅ እና በመተንፈሻ አካላት በሽታ የመያዝ እድልን ይቀንሳል። የሙቀት ቁጥጥር፡– ዶሮች ውጤት ለማምጣትና ጤናማ ለመሆን አስፈላጊውን ሙቀት ማግኘት አለባቸው። በተፈጥሮ የሚያገኙት ሙቀት እንደተጠበቀ ሁኖ ይህ ካልሆነ በሰው ሰራሽ መልኩ ተጨማሪ ሙቀት መስጠት ያስፈልጋል። ሙቀቱን ከ16°c እስከ 25°c እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል። 4. የባዮሴኪዩሪቲ እርምጃዎችን ይተግብሩ በሽታን መከላከል፡- ዶሮዎችን በመደበኛነት መከተብ እና የበሽታ መከሰትን ለመከላከል ጥብቅ የንጽህና አጠባበቅ ሂደቶችን መከተል ያስፈልጋል። ማግለል፡- የታመሙ ዶሮዎች ማግለል እንዲሁም አዳዲስ ዶሮዎችን ከማስገባትዎ በፊት የበሽታዎችን ስርጭት ለመከላከል ማግለል ያስፈልጋል። 5. ውጤታማ የአስተዳደር ልምዶች መዝገብ መያዝ፡– ስራዎችዎን ለመቆጣጠር እና ለማሻሻል የምግብ ፍጆታን፣ የእድገት መጠን እና የጤና ጉዳዮችን ዝርዝር መዝገቦችን ይያዙ። በተጨማሪም የደንበኛን መረጃ በአግባቡ መያዝ ያስፈልጋል። ሰራተኞችን ቀጣይነት ያለው ስልጠና መስጠትና ራስንም ከዘመኑ ጋር አብሮ ማራመድ እንዲሁም ቴክኖሎጂን ፋርሙ ላይ መጠቀም ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነጥብ ነው። 6. የገቢ አይነቶችን ማብዛት። ተረፈ ምርቶች ለተጨማሪ ገቢ ማመንጫ ማዋል። እንደ ላባ እና ኩስ ያሉ የዶሮ እርባታ ተረፈ ምርቶችን ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። የዶሮ ኩስን ለምሳሌ ወደ ባዮ ጋዝ በመቀየር ለእርባታው የሚያስፈልገውን የሙቀት ፍጆታ ማመንጨት ይቻላል። ከላባቸው የተለያዩ አልባሳት፣ትራስ እንዲሁም ሌሎች ፈጠራ የታከለባቸው ውጤቶችን ማግኘት ይቻላል። 7. የገበያ ስትራቴጂዎች ቀጥታ ሽያጭ፡- የትርፍ ህዳግን ለመጨመር በቀጥታ ለተመጋቢዎች መሸጥ ይህንንም የራስን ሱቅ በማመቻቸት ወይም እንደ ሀገራችን ያልተለመደውን የኦንላይን ሽያጭ መጀመር ይህንንም በሶሻል ሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ቀስ እያሉ ፕላትፎርም ወደ ማመቻቸት ይቀየራል። አቅራቢ መሆን፦ በአካባቢዎ በሚገኝ ምግብ ቤት እና ለመሰል ተጠቃሚዎች ማስረከብ 8. መረጃ መከታተልና ማከማቸት መረጃ ለማንኛውም የንድግ ስራ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የዶሮ እርባታ ቢዝነስ ላይም በተለያየ ዘርፍ መረጃ ያስፈልጋል። ይኸውም የገበያ አዝማሚያዎች፡ የአመራረት እና የግብይት ስልቶችን ለማስተካከል ከገበያ አዝማሚያዎች እና ከሸማቾች ምርጫ ጋር ተያይዞ የለን መረጃ ማነፍነፍ ያስፈልጋል። በየትኛው ወቅት እንቁላል ይፈለጋል፣ በየትኛውስ አይፈለግም፣ ምን አይነት ደንበኛ ምን አይነት እንቁላል ይፈልጋል። በበየትኛው ጊዜ መኖ ይወደዳል፣ የት አካባቢ ርካሽ መኖ ይገኛል። ወደየት አካባቢ ምርቴን ፈላጊ ይኖራል፣ በየትኛው ወቅት በሽታ ይከሰታል እና መሰል መረጃዎችን ማወቅ ማከማቸትና መተንተን ያስፈልጋል። ቀጣይነት ያለው ትምህርት፡ –በዶሮ እርባታ ቴክኒኮች እና አዳዲስ ፈጠራዎች ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ወርክሾፖችን፣ የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን እና ሴሚናሮችን መገኘት እና የተለያዩ ፅሁፎችን ማንበብ ግድ ይላል። እነዚህን ስልቶች መተግበር ስራዎን ለማመቻቸት፣ ወጪዎችን ለመቀነስ እና በመጨረሻም የዶሮ እርባታ ንግድዎን ትርፋማነት ለመጨመር ይረዳዎታል።
እርባታዎ እንዴት ነው? ምን ችግር ገጥሞዎት ነበር? በእርባታዎ ላይ ምን እንርዳዎ?
በሀገራችን የኢንተርኔት መቆራረጥ ምክንያት መረጃ መለዋወጥ እንዲሁም ስራችን ላይ ትኩረት ሰጥተን እንዳንሰራ ሁነን ስለነበር ተደራሽነታችን ተቋርጦ ነበር አሁን ላይ ባገኘነው ወቅታዊ አጋጣሚ አገልግሎታችነንና ምርታችነን ስለምናስቀጥል ወደ ነበረው ግንኙነታችን ተመልሰናል። በአዲሱ አመት ምርታማና ውጤት የምናስመዘግብበት አመት ይሁንልን!
https://youtu.be/-KnlORQC488
без подписи
без подписи
አስቸኳይ በመጠኑ ያገለገለ በጣም ጠንካራ ኬጅ ከእንጨትና ብረት የተሰራ ለአጠቃቀም ምቹ (ኩሳቸው በመሳበያ የሚወጣ) የራሱ መመገቢያና መጠጫ አለው ዶሮወቹ ከኩስ ጋር ምንም ንክኪ የላቸውም ለበሽታ ለመከላከል ተመራጭ ሼድ ውስጥ የሚቀመጥ አዲስ አበባ ባለ 78 ዶሮ = 3500 ባለ 90 ዶሮ = 4000 ፈላጊ call 0934695676 0921629616
በቤትዎ የሚሰራ ቀላል የእንቁላል ማስፈልፈያ እንዴት መስራት ይቻላል ለሚለው የተሞከረ ኢንኩቤተር ነው https://youtu.be/hszQ6PwhXBc
https://youtube.com/channel/UCR-0n3X0HXPAWyz4QDWr66A ይህ የኔ ዩቲዩብ ነው የተለያዩ መረጃዎችን እለቅበታለሁ ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩኝ።
без подписи
Share 'sona africa poultry farm የዶሮ አረባብ ማኑዋል.pdf'