ስለ ህይወት ቃል... 1ኛ ዮሐንስ 1:1
Статистика1ኛ ዮሐንስ 1 ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመርያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ 2 ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ህይወት እናወራችኋለን፤
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 180
- 1/48двое суток
- 206
- 1/72трое суток
- 222
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🙏✝️የማይነገር ውለታህ🛐 ይህ ነው ብዬ የማልገልፀዉ ሰማይ ምድር የከበደዉ በልቤ ታፍኖ መተንፈሻ ያጣዉ ሌላ ምንም ሳይሆን ያንተ ዉለታ ነዉ ምንም በሌለበት ደረቅ ምድረበዳ ያስገባኝ ፍቅርህ ነዉ አቅፎ ካንተ ጓዳ ጓዳህ ያማረ ነዉ ውበት የሞላበት አይገባም ነበር ይሄ ለኔ ህይወት ዛሬ ግን በቤትህ ራሴን አየሁት በላይ በዙፋኑ አንተ ባለህበት ታዲያ ምን ይባላል ለማንስ ይወራል አይገርምም ዉለታህ ከአይምሮ በላይ ነዉ ስራህ እንዴት ላዉራ ልንገርልህ ምንስ ብዬ ልደምድምህ የቃላት ክምር ፊደል የማይፅፍህ የማይነገር ነዉ ኢየሱሴ ዉለታህ በምንም በማንም የማልመልስልህ @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber
ምንም ብናዝን በዚህ አለም ፈተና አይለውጠውም ለእርሱ ያለንን ምስጋና በመስቀሉ ያለፈውን እያየን በእምነታችን ዛሬም እንፀናለን No matter the sorrows we face in this world, Trials cannot alter the praise we offer Him; Gazing upon what He endured on the cross, We stand firm in our faith today. @SLEHIYWET 👈
በክርስቶስ እግዚአብሔርን ለማስደሰት ከመሞከር ነፃ ወጥተናል። @slehiywet
ጸሎት እንዳንፈተን ሳይሆን እንዳንሸነፍ ሚያደርግ ነው እንጸልይ 🔥 @slehiywet
ውዶቼ አትጨነቁ እሺ በእግዚአብሔር ታማኝ እጆች ላይ ናችሁ እንደለመደው በድንቅ ስራው ያስገርማችኋል ✨ ጠብቁት! @slehiywet
ቀኖቹ እንቆቅልሾች ናቸው፣ የቀኖቹ ባለቤት ግን እግዚአብሔር ነው፣ እግዚአብሔር ደግሞ አባታችን ነው፣ ስለዚህ እርሱ መልሳችን ነው በአንዳች እንጨነቅም። @slehiywet
#ራስህን_አኗሪ NEW ALBUM IS OUT NOW! ተወዳጇ ዘማሪት አዲስ አለም አሰፋ እነሆ በአዲሱ ዓመት አዲስ በረከት ይዛልን መታለች ዩቲዩብ ላይ ገብታችሁ አዳምጡላት ና ተባረኩበት 🤩🌼 16 tracks 🎧❤️ www.youtube.com/@addisalemofficial456 @slehiywet
ውድ የቻናሌ ና ግሩፕ ቤተሰቦቼ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ እያልኩ ቀሪው ዘመናችሁ የምድሩን ነገር ንቃችሁ ኢየሱስን እያወራችሁ ና እያሳያችሁ ምትኖሩበት እንዲሆንላችሁ እየተመኘው እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ በሁሉ ነገር ተከናወኑ ብዬ መልካም ምኞቴን እገልጽላችኋለሁ🌼 በጣም እወዳችኋለሁ ❤️ @slehiywet
ስለ ድነት ጽንፍ ይዘን በጣም እናውራ፣ እንመራመር፣ እንከራከር ስንል ከባድ ና ውስብስብ ሊሆን ይችላል ስንኖረው ግን ቀላል ነው። @slehiywet
ብርቄም ድንቄም ስንቄም ጽድቄም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። @slehiywet
ከጸጋ ወንጌል ወደ ሕግ ባንመለስም ጸጋን ግን በደንብ እንረዳው እስቲ... የዘመኑ ቅድስና እየደበዘዘ እየታየኝ ነው። በኢየሱስ ስም ሚያስብል የደነዘዘ ጊዜ፣ በተለይ ለክርስቲያኖች! @slehiywet
የጌታ ጸጋ ና ሰላም ይብዛላችሁ ውድ ቤተሰቦቼ እነሆ ወዳጃዊ ምክር..😊 ወቃሽ፣ ተቆርቋሪ ና መካሪ ሰው ግብዝ ተብሎ በሚፈረጅበት ከዚያም ሻገር ሲል በሚጠላበት በዚህ አስቸጋሪ ዘመን እኔ ግን እላችኋለሁ ባልንጀሮቻችሁ ላይ ጉድፍ ባያችሁ ጊዜ በፍጹም ዝምታን መርጣችሁ ከመናገር እንዳትሰንፉ የሚያማ ና የሚሳደብ ብዙ ቢሆንም እናንተ ግን በግልጽ ና በፍቅር መምከር ያለባችሁን ሰው ምከሩ፣ ተቆጡ፣ ገስጹ ከእናንተ ሌላ ሚነግረው ሰው አይኖርምና። ውድ የነገዋ ቤተክርስቲያን ተረካቢዎች እናንተም በተቻላችሁ ሁሉ እንከን አልባ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት ዕለት ዕለት ተለማመዱ፣ ንዴትን አስወግዱ፣ ወደ ሕይወታችሁ የሚመጣን ማንኛውንም አሉታዊ ኃይል ንቃችሁ እለፉት፣ በኋላ በእራሳችሁ ትኮራላችሁና። ሰውን ከምትበድሉ ይልቅ እናንተ ብትበደሉ ይሻላል፤ እውነተኛ ፍርድ ከሠማይ ይወርዳልና። ይቅርታን ለመጠየቅ አትቸገሩ፤ አስፈላጊ መስሎ ከታያችሁ ተበድላችሁም ቢሆን እንኳ ይቅርታን ጠይቁ፤ ከማንም ጋር ከፍቅር ውጪ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ። በጸሎት ና በቃሉ እውቀት እደጉ፣ አለኝ ብላችሁ በምታምኑት ጸጋ የእግዚአብሔርን ሕዝብ አገልግሉ፣ በመጠን ኑሩ፣ ብዙ ከመናገር ውስጥ ብዙ ስህተት አይጠፋምና ንግግራችሁ ቁምነገር ና አነስተኛ ይሁን። በዚህ በረከት ባርኬአችሁ አጭር ጽሁፌን ልጠቅልለው ኢየሱስ በሕይወታችሁ ና በእንደበታችሁ ላይ ይብዛ ሙሉ ደስታ ና ትኩረታችሁ በእሱ ላይ ይሁን! እወዳችኋለሁ 🩷 ወንድማችሁ በረከት ነኝ
#ወቀሳ ቤተክርስትያንን ወይም ቤተመቅደስን ላለመዝጋት ሲባል ብቻ አልያም የፈውስ ፕሮግራም የተባለው ጊዜ እንዳይቀር በሚል ብቻ የሚደረጉ ማያንፁ፣ መንፈስ ማይታይባቸው ስጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ ነው፤ እግዚአብሔር እውነተኛ ክብሩን ሚገልጥባቸውን ሰዎች በብዛት እንዲያስነሳ ጸሎቴ ነው። @slehiywet
ገብዝና ያለ ቅድስና እርጅና ነው! @slehiywet
ምናልባት እኛ አልሰማ ብለን ወይም ሰምተን ችላ ያልንበት ጊዜ ከኖረ ነው እንጂ እግዚአብሔር እኛን ሳይናገር ያለፈበት አንድም ጊዜ የለም። @slehiywet
ኢየሱስ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ አንዳች ሀይልም የለም ከእቅፉ ሚለየኝ። አሜሜሜሜሜን! @slehiywet
"እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።(ዕብ 4:16) 👉መዳናችን በጸጋው እንደሆነ ሁሉ ከዳንን በኃላ ያለን ሕይወት በሙሉ የተመሰረተው በጸጋው ላይ ነው። 👉 በዚህ የጸጋ ዙፋን ፊት እምባ ይታበሳል፣ የዛለው ጉልበት ይበረታል፣ የተሰበረው ይጠገናል። ዛሬ በሕይወታችን ላይ አንደተራራ የገዘፉ፣ እንደ ጨለማ የጠቆሩ ችግሮች ካሉን ወደ ጸጋው ዙፋን ይዘናቸው እንምጣ። በዚህ ጸጋ ፊት ቀርቦ ይቅር የማይባል ምንም አይነት ኃጢአት የለም። 👉👀ከዳንን በኋላ ለእኛ የተሰጠውን ሀላፊነት ስንወጣና በመከራ ስናልፍ የሚያግዘን ጸጋው ነው። ለምሳሌ ባዶነት ሲሰማን፣ በራሳችን ተስፋ ስንቆርጥ ረዳት በሚያስፈልገን ጊዜ ወደ ጸጋው ዙፋን በመቅረብ ምህረት እንቀበል ፡፡ እኔ በግሌ በቅርቡ እናቴ አርፋለች እሷ ወደ የምትወደው ጌታ ነው የሄደችው ግን ለእኔ በጣም ከባድ ነበር። ባዶነት ሲሰማኝ፣ በራሴ ተስፋ ስቆርጥ ረዳት በሚያስፈልገኝ ጊዜ ወደ ጸጋው ዙፋን በመቅረብ ብዙ በርትቻለሁ challenge የሚያደርግ ነገር ቢኖርም እንኳን እህቶቼና ወንድሞቼ ወደ ፀጋው ወደ ጌታ መቅረብ እሱን መፈለግ ይሻላል። " ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል። "(ቲቶ 2:12-13) ጸጋው ኃጢአትን እንድንሰራ ፍቃድ አይሰጠንም ይልቁንም ዓለማዊ ምኞትን እንድንክድ እንጂ። በዚህ ዘመን ራሳችንን እየገዛን እግዚአብሔርን በመምሰል በጽድቅ እንድንኖር ጸጋው ያስተምረናል። "ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።"(ሮሜ 6:14) ምክንያቱም "ሥጋ ደግሞ በባሕርይው ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛም መገዛትም ተስኖታል" ስለተባለ (ሮሜ 8:7)። 🗣🗣አንዳንድ ሰዎች ጸጋው ኃጢአትን ለመስራት ላይሰንስ የሚሰጥ ፍቃድ የሚሰጥ ይመስላችኃል ግን አይደለም። "እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም"ይላል (ሮሜ 6:1)። አይደለም የሚለው ቃለ የሚያስረዳው ጸጋው ለኃጢአት ፍቃድ የሚሰጥ እንዳልሆነ ነው። " አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።"(1ኛ ጴጥ 2:16) የተከፈለልንን ጸጋ አውቀን ዓለማዊ ምኞትን ክህደን በጽድቅ እንድንኖር ጸጋው ይርዳን። @Betsitaye 👇👇👇👇👇👇👇 Join now ✝✝✝✝✝✝✝✝ 📥Group : @slehiywetkal 👈 📥Channel : @slehiywet 👈 ✝✝✝✝✝✝✝✝
ለኢየሱስ መኖር ማለት ለእራስ መሞት ወይም በየእለቱ ራስን መግደል ማለት ነው። @slehiywet
አዳምጡት መልካም ፋሲካ! ይሄን እያሰባችሁ ዋሉ
በኢየሱስ ፍቅር አስቀድመህ ካልሰከርክ ና ካላበድክ በዚህ ጊዜ ና ዘመን ሚያሳብድ ነገር ብዙ ነው ወገኔ 😂 ኢየሱስ አሁንም በፍቅሩ ይንደፈን! @slehiywet