- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Instagram (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 112
- 1/48двое суток
- 128
- 1/72трое суток
- 138
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሐዋሪያው ጳውሎስ መፅሐፍ ያልሆነው የቱ ነው? wave ለመግባት @pluzinf0
✅በቴሌግራም ቆይታችሁ መንፈሳዊ ህይወቶን የሚየሳድጉበት ቻናሎች ልጠቁማችሁ😍 @seer_lewi
በዚህ ዘመን የምንኖር ክርስቲያኖች በጣም የታደልን ነን። ምንም እንኳን ዘመኑ የከፋ፣ አስጨናቂና አንዳንድ ጊዜም ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም እንኳን፣ የጌታችን ዳግመኛ መምጣት ቀርቦ በደጅ ነው። ልባችን ሊናወጥ አይገባም። በመንፈሳዊ ሕይወታችን መንቃት፣ ንሰሐ መግባት፣ መጸለይና የጌታን ማዳን ላልሰሙ መንገር አለብን። ፍርድ የሌለበት ትንሽ ኃጢአት እንደሌለ ሁሉ ከእውነት ልባቸው ንሰሐ በመግባት ወደ ክርስቶስ በመጡ ሰዎች ላይም ሊመጣ ያለ ዘግናኝ ፍርድ ከቶ የለም። ኢየሱስ ከፍሎታልና!! 🌎 በዓለም ነው ያለነው፣ 🌏 ከዓለም ነው በመድኃኒታችን በኩል ወደ እግዚአብሔር ዓለም የተጠራነው። ✴️ ዳሩ ግን ለዓለም ክብር አንኖርም፣ ✴️ወደ ዓለምም አንመለስም፤ የታመንንበትን ጌታን እናውቃለንና። ረጅም መንገድ የሚጓዘ ሰው መድረሻውን ለመድረስ ቢደክመውም እንኳን ለመድረስ ያለመበትን ቦታ ከሩቁ ሲያየው አዲስ ጉልበት ያገኝና እንዴትም ብለው ባለው በሌለው ኃይሉ ጉዞ ይቀጥልበታል። እንደዚሁ ሁሉ እኛም ለሰይጣንና ለጭፍራው ታልፋ በተሰጠች ዓለም ስንኖር በብዙ እንፈተናለን፣ አያሌ ተስፋ ቢሶች እንደሆን የሚያደርጉ ነገሮች ይገጥሙናል። ነገር ግን በዚህ ተስፋ አንቆርጥም። የጠዋት ጤዛ የሚመስል ዞር ስንል የማናገኘው የዓለም ግሳንግስ ትኩረታችንን አይስብም። እስቲ ወዴት እየሄድን እንደሆነ እናስብ? ከማን ጋር ነን መሪና ፍሬን የሌለውን መኪና አስቡት። በቃ ዓለም እንደዚህ ነች አንድ ቀን ከእነ ተሳፋሪዎቿ ገደል ውስጥ ትገባለች። እኛ ግን እንደዚህ አይደለንም! ወደ አብ የሚወስደን መሪያችን ኢየሱስ አለን፤ ከዓለም ጋር እንዳንላተም የሚይዘን እንደ ተስፋ ቃሉ በውስጣችን የታተመ ጌታ መንፈስ ቅዱስ አለን፣ ከሁሉ አስቀድሞ በልጁ በኩል የመረጠን ደ'ሞ አብ አለን። @reiseneh
በመጠን መኖር ሌላ ነገር ሲያምርኝ በመጠን እንድኖር በቃሉ ሚነግርኝ ይመለስልኛል ሰላሜ ይታደስልኛል አቅሜ ያንተ ካንተ ለኔ የተቀበልኩት ኑሮ አይደል ወይ የተካፈልኩት መኖሬን ፍቺ ሰጥተኸዋል ህይወቴን መስመር አሲዘሃል አንተን አጥቶ መኖር አይታሰብም የመኖር ምክንያት ነህ የመኖርም ትርጉም በመጠን መኖር ነው እግዚአብሔር ምያስከብረው ለአንተ መኖር ፈልጋለሁ የአንተን ምሬት እሻለሁ ባንተ መኖሬን ሰላም ውስጤን ይሞላዋል ስም https://t.me/+mVjDGnLkzcxlOGM0 https://t.me/tarikinmamarespritualstories
✅በቴሌግራም ቆይታችሁ መንፈሳዊ ህይወቶን የሚየሳድጉበት ቻናሎች ልጠቁማችሁ😍 @seer_lewi
🙏✝️የማይነገር ውለታህ🛐 ይህ ነው ብዬ የማልገልፀዉ ሰማይ ምድር የከበደዉ በልቤ ታፍኖ መተንፈሻ ያጣዉ ሌላ ምንም ሳይሆን ያንተ ዉለታ ነዉ ምንም በሌለበት ደረቅ ምድረበዳ ያስገባኝ ፍቅርህ ነዉ አቅፎ ካንተ ጓዳ ጓዳህ ያማረ ነዉ ውበት የሞላበት አይገባም ነበር ይሄ ለኔ ህይወት ዛሬ ግን በቤትህ ራሴን አየሁት በላይ በዙፋኑ አንተ ባለህበት ታዲያ ምን ይባላል ለማንስ ይወራል አይገርምም ዉለታህ ከአይምሮ በላይ ነዉ ስራህ እንዴት ላዉራ ልንገርልህ ምንስ ብዬ ልደምድምህ የቃላት ክምር ፊደል የማይፅፍህ የማይነገር ነዉ ኢየሱሴ ዉለታህ በምንም በማንም የማልመልስልህ @ye_getamian_mahiber @ye_getamian_mahiber
без подписи
без подписи
ምንም ብናዝን በዚህ አለም ፈተና አይለውጠውም ለእርሱ ያለንን ምስጋና በመስቀሉ ያለፈውን እያየን በእምነታችን ዛሬም እንፀናለን No matter the sorrows we face in this world, Trials cannot alter the praise we offer Him; Gazing upon what He endured on the cross, We stand firm in our faith today. @SLEHIYWET 👈
"አልረሳኝም" ✝️ አንተ አልረሳኸኝም ሌሎች ሲረሱኝ ፤ ሁሉም በሮች ሲዘጉብኝ ፤ አንተ በርህን ከፈትክልኝ። 🚪🤍 በጨለማ ስራመድ፣ ብርሃኔ ሆንክ፤ በሐዘን ስሰበር፣ መጽናናቴ ሆንክ፤ ዓለም ተስፋ ሰጠችኝ፤ ነገር ግን አታለለችኝ። ሰዎች "እንወድሃለን" አሉኝ፤ ጊዜ ሲቀየር ራቁኝ። እንባዬን ማንም አልቆጠረውም፤ ምናልባት ሰዎች ዋጋዬን አላወቁም፤ 🙏 አባት ሆይ...የጠፋውን ትፈልጋለህ፤የወደቀውን ታነሳለህ፤የተሰበረውን ትጠግናለህ፤የሚያለቅሰውን ታጽናናለህን ። 🤍 🌫ውበት እንደ አበባ ይረግፋል፤ 🌸ገንዘብ ክንፍ አውጥቶ ይበራል፤ 💸ነገር ግን... የክርስቶስ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል። ❤️ አንድ ቀን...ምድር ትቀራለች፤ ጊዜ ያበቃል፤ ዝም ይላሉ ድምፆች :: በዚያ ቀን...ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኝ ይሆን? 📖 ስለዚህ...ዛሬ ልብህን አትደንድን፤ እሱን ይዘክ በፈተና አትፈተን :: "ና... ደክሞህ ከሆነ፣ ሸክምህን ተሸክመህ ከሆነ፣ ወደ እርሱ ና... ያስርፈናልና ።" ✝️🤍 https://t.me/reiseneh
.....ከወዴት ወድቀሻል ዝና ክብር ሞልቶ በረከት በጓዳ ዝናሽ ከፍፍ ብሏል በቤትሽ ጓዳ ችግር አይተሰብም በስጋም በነብስ ንግድሽም ደርቷል ሄድ መለስ ለአምላክ ያለሽ ጽናት ሀሰትን መጥላትሽ ብርቱ እምነት ትጋት ጥንካሬሽ ልቤን አሸነፈው ትዕግስት ሚዛናዊነት በሁሉ ተወዳጅ ማይነጥፍ እውነት ግና ግና ኤፌሶን ማታሽ ተበላሸ ከወዴት ወድቀሻል ያ ሀያል ፍቅርሽን የት ጥለሻል ወደር አልባ ነበር መያያዝሽ መሰረቱ ሀሳዊያንን ታግለሽ መትተሽ ከእውነቱ ዛሬ ምነው ታዲያ ፍቅርሽን ክደሻል የቀድሞ መወደድሽን ለማን ሰተሻል ግንቦችሽ ተናጉ ቅጥሮችሽም ፈርሷል የአፈር ክምር ባድማውን ሞልቷል ነይ ተመለሺ አንቺ የፍቅር ተምሳሌት ንስሀ ግቢ ቀን ሳይመጣ ሌት ከራሴ አኖራለሁ ድል ነሺ ታጋዩን አክሊን አወርሳለሁ የሰማዩን አድሚጪኝ ተመለሺ ከቀደመው ቤትሽ ለአለም ይታይ ያ ብርቱ ፍቅርሽ ✍✍✍በጌታሁን አናሞ✍✍✍ Like Share Forward React @ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/nehinyene
https://t.me/tarikinmamarespritualstories
..............ዘጸአት....... በራስ ቀለም ኑሮ ተራራውን መዞር የዘውትር ተለምዶ ባለንበት መኖር መሄድን ስንሻ ቆመን ተራምደናል ሩቅ እያሰብን ከሰፈር ቀርተናል መጠራታችን ነበር ለሰማይ ቤት የጠፋን ሳለን የተሰጠን ህይወት የመስቀሉን ጣር የአብ ማስታወሻ የደሙ ውጤት ከሰማይ መድረሻ ሆኖ ኖሮ እያለ ሆነን ያልተገኘን በግላችን ድንኳን ታስረን ተቀምጠን ዘመን እንዳያልፍ ከዘመኑ ጋራ ኋላ እንዳይቆጨን ጨለማው ሳይበራ በሚመጣው ዘመን ትላንት አንገኝ ዘጸአት ይሁንልን ክብሩ ነገን ያሻግረን ማለፍ ይሁንልን መፈታት ከእስሩ በመሻገር ቀመር ዘጸአት ለሰፈሩ የተሰቀለውን ጌታ ፊትለፊት ለማየት እንትጋ ለነገ እንለፍ ወደ አብ ቤት ነጻነትን ሰጠን ከእንግዲህ በኋላ መሄድ ሆኖልናል ላናይ ወደ ኋላ ዘጸአት ለሀገሬ ዘጸአት ለቤተክርስቲያን ከሰማይ የመጣው ድንቅ ነው ያ ብርሃን ✍✍በ ጌታሁን አናሞ✍✍ Like Share Forward React @ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/reiseneh
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:8-10,13 (AMH) •••••••••• ⁸ ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥ ⁹ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና። አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥ ¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ........... ¹³ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር። አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
.....መስታወት ከመድረኩ በስተጀርባ ካለው ክፍል የሚወጣው ድምጽ እየረበሸኝ መስበክ አልቻልኩም ነበር፣ ወደ ኋላ ሁለት እርምጃዎች ተራምጄ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን መስኮት ልዘጋው ፈለኩ ግን አልቻልኩም ድራሙ፣ኪውቦርዱ እና ሌሎች የሳውንድ ሲስተም እቃዎች የምስባኩን ጀርባ ማንም እንዳይተላለፍ ዘግተውታል እንደምንም ብዬ ስብከቴን ጨረስኩና ወደ ቤት አመራሁ። ///////___/// ማታ ብቸኝነቱ ሲያስጨንቀኝ የቀን ውሎዬን ለመጻፍ በዘረጋሁት ደብተር ላይ የመጨረሻው ሀረግ ...<< መስታወት >>የሚል ነበር መስታወት የላይኛውን ገጽታ ባለንበት ሁኔታ ሆኖ ለራሳችን ያስተጋባልናል፣ስንስቅ ይስቃል፣እያለቀስን ብንመለከተው መልሶ ያለቅስብናል ፣ እያወራንም ብናየው ንግግራችንን አንድ በአንድ በምላሱና በከናፍሮቹ እንቅስቃሴ የሚደግምልንን ሰው ያሳየናል ግን መስታወቱን ዞር ስናረግ እውነተኛውን ኑሮ እንቀጥለዋለን \\\\\\\|\\\\\\\ ወደ ቤት ስገባ የሚበላ የለም የሚቀመስ ነገር የለም ፣ብቻ እግዚአብሔር ይመስገን በሰው ፊት የደላ የሞላው አገልጋይ ቤቴ ስገባ አንጀቴን አስሬ የማነባ ሰው ከሆንኩ ሰነባብቻለሁ፣ ብታዩ አንድአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጌ እተወውና .....ብዬ ሳስብ የተጠራሁበትን መጠራትና በእኔ ጌታ እየሰራ ያለውን እና ሊሰራ ያለውን ሳየው ሀሳቤን ቀይሬ እንበረከካለሁ ግን እስከመቼ /////....//// ሁሉም ሰው ልክ እንደመስታወቱ በማስመሰል ህይወት የሚኖርለት አንድ የህይወት ክፍል አለው፣ እውነተኛ ማንነቱን በልብስ፣በሜካፕ በጨዋታ ደብቆ በልቡ እያነባ የሚኖር ብዙ ሰው አለ ትዝ ካላችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ሀና የምትባል ሴት አለች ችግሯ ብዙም አይታወቅባትም አንድአንዱ በልማድ ያያታል፣ነገር ግን ባሏ ከሚያደርግላት እንክብካቤ የተነሳ ጉድለቷ ሁሉ ሙሉ ነበር የሚመስለው ነገር ግን ወደ በለተመቅደስ በመጣች ቁጥር እንባ ከአይኗ አይርቃትም ፣አንድ ጊዜ ሀዘኗ በርትቶ የውስጥ ጩኸቷ ከቁጥጥር ውጪ ሲሆንባት ኤሊ ያላትን አስታወሳችኋል አይደል አብዘኞቻችን እንደሷ ነን፣ /....../////.....// ቆይ ግን እስከመቼ ነው እያገለገልኩ የምቸገረው ለአንድ ለራሴ መሆን ያቃተኝስ ለምንድነው ፣ እያልኩ ከራሴ ስከራከር ለካስ እውነተኛ ጥሪ ትግል ይበዛበታል፣ እውነተኛ ክርስትና በህይወት ይፈተናል፣ ከልብ የሆነ እምነት በብዙ መከራዎች ያልፋል፣ ዮሴፍ፣ዳንኤል፣ አብርሃምን አስብ አንተ ከነሱ በምን ትለያለህ ፣ እስቲ ተመልከት ሀዋሪያትን .... የሚል ድምጽ ወደ ልቤ በሀይል ይመጣ ጀመረ /////////......////// ነገር ግን ሀና ይሰሀቅን እንዳገኘች እኛም ከመስታወቱ ግልባጭ እውነተኛ ማንነታችን ጋር እንገናኛለን፣ የዛኔ ነብሳችን ስጋችን እና ሁለንተናችን በእግዚአብሔር ይጸናል ////////....../// እውነት ነው እግዚአብሔር የጠራው ሰው ፈተና ቢበዛበትም ከፈተናው ጋር መንገድን ያሰናዳለታል እምነታችን ከማግኘትና ከማጣታችን ጋር አይወዳደርም፣መጠራታችን ለዘላለማዊ መንግሥት ወራሽ እንድኖሆን እንጂ ለምድራዊ ድሎት አይደለም እውነት ነው በምድር ስንኖር ማግኘት በደስታ መኖር ተገብቶናል፣ ያ ግን የማንነታችን ልኬት መሆን የለበትም ልካችን መጠራታችን ነው፣ መሰረታችን ክርስቶስ ነው አለታችን ጽኑ ነው ስለዚህ በየትኛውም የህይወት ፈተና እምነታችን ሲፈተን እግዚአብሔር ሌላ ክብር ሌላ መንገድ ሌላ መገለጥን ሊያሳየን እያዘጋጀን እንዳለን በማመን ተስፋ እያደረግን ከፊታችን ያለውን እሩጫ በትጋት እንሩጥ አበቃሁ ✍✍✍በ ጌታሁን አናሞ✍✍ Like Share React Join @ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/nehinyene
ቀኑን አስታውሰዋለሁ ጀርባዬን ሰጥቼ በቃ አሁን አድገለያለሁ ያልኩበትን የሚገርመው ግን ምንም እንኳን በትምህርቴ ከፍተኛ ደረጃ ብይዝም፣ራሴን የማስተዳደር አቅም ያለኝ ቢመስለኝም ፣ለወላጆቼ አሁንም ልጅ ነኝ ያደኩ የመሰለኝ ከእኔ እንጂ ለአባቴ አልነበረም እና አንድ ቀን አባቴን ጠየኩ (( በእውነቱ ከሆነ ይሄ ጥያቄ መነሳት የነበረበት ጊዜው አልነበረም)) አባቴ ፣በቃ እኔ ከቤት መውጣት እፈልጋለሁ ፣እንደምታየኝ አሁን አድጌያለሁ ፣ክፉና ደጉን ለይቼ አውቄያለሁ ስለዚህ መርቀህ ሸኘኝ አልኩት አባቴ በጣም አዘነ ስለኔ በጣም ተጨነቀ እኔም በየቀኑ ማደጌን እየነገርኩ ራሴን ችዬ መኖር እንደምችል በመናገር ነዘነዝኩት በስተመጨረሻም አባቴ ፈቀደልኝ በጣም ደስ አለኝ ፣ ከዚህ በኋላ የት ገባህ የት ወጣህ፣ጓደኞችህ ማናቸው ውሎህ አዳርህ የት ነው የሚል በሌለበት በራራራሴ አለም ከራሴ ጋር በነጻነትና በተድላ የምኖርበትን ጣፋጭ ጊዜያትን እያሰብኩ ከቤት ወጣሁ ለጥቂት ቀናት ልቤ እንዳሻኝ ሆንኩ ፣ኋላ ቀስ በቀስ የከበቡኝ ተበተኑ፣አይዞህ እኛ አለንልህ ያሉት ሁሉ ተቀየሩብኝ የያዝኩት ሀብቴ ከእጄ አለቀ አብሮ አጫፋሪዎቼ ሁሉ ብቻዬን ተዉኝ ያኔ ትዝ አለኝ አባቴ ከሱ እንዳልለይ ለምን እንደሚከለክለኝ በየቀኑ ጧትና ማታ አንዴ በምክር አንዴ በቁጣ ሲያሻውም ጎሸም እያረገኝ ሲመክረኝ ሲቀጣኝ ሲገስጸኝ የነበረው ለካስ ካለሱ የመኖር አቅሜን ስለሚያውቀው ነው አሁን አንድ ነገር ገባኝ ይቅርታ መጠየቅ ከዚህ የከፋ ችግር ላይ ወድቄ ነብሴን ከማጣ በቃ አባቴ ዘንድ ልሂድ ልመለስ .....///.... ስፈራ ስቸር ከቤታችን ደጅ ደረስኩ ፣አባቴ አገኘኝ እንደገና አየኝ ፣ልቡ በሀሴት ተሞላ እኔማ ፣ከመች መች ይገለኛል ያጠፋኛል ለብኩን እኔነቴ ዋጋዬን ይሰጠኛል ብዬ ፈርቼ ነበር ለካስ ለካስ ለአባት ሁሌም የሚታየው የጥፋቴ ግዝፈት ሳይሆን የአብራኩ ክፋይ ልጅነቴ ነው ለካስ ለአባቴ የሚታየው ጥፋቴ ሳይሆን ተጸጽቶ የተመለሰ ማንነቴ ነው አሁን ተለውጫለሁ ከአባቴ ጋር በማዕድ እቀመጣለሁ በደሌን ሽሮ ጭራሽ ወራሽ አደረገኝ የርስቱ ተካፋይም ሆንኩ አበቃሁ ✍✍✍ በጌታሁን አናሞ✍✍ Like Share React Join @ https://t.me/reiseneh
💒💒💒💒መንፈሳዊ ቤት⛪️⛪️⛪️⛪️ ✈️ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1ኛ ጴጥሮስ መልእክት 2፡5 እግዚአብሄር ሰው የፈጠረው ከሰው ጋር ህብረትን ለማድረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ የፈጠረው ከሰው ጋር በሚገባ ህብረት ማድረግ እንዲችል ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር የሚኖረው በሰው ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ የሚያድረው በሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር የሚገለጠው በሰው ውስጥ ነው፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ በስፋት መገለጥ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በምድር ላይ መታወቅ ይፈልጋል፡፡ ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡19-20 እግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚናገርበት ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚኖርበት ሰው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር የሚያርፍበት ሰው ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።ዮሐንስ ወንጌል 14፡23 እግዚአብሄር በህይወታችን በስፋት እንዲኖር ፣ ሰዎችን እንዲነካና እንዲደርስ ለእግዚአብሄር መኖሪያ ሆነን በስፋት መሰራት አለብን፡፡ ለእግዚአብሄር መኖሪያ ሆነን በተገነባን መጠን እግዚአብሄር በስፋት በውስጣችን ይገለጣል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሰምተን ባልታዘዝንና ባላደግን ቁጥር እግዚአብሄር በስፋት ሊኖርብን ፣ ሊያርፍብን ፣ ሊናገርብንና ሊመላለስብን አይችልም፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰውእመለከታለሁ። ኢሳይያስ 66፡1-2 ሰው የተሰራ ፣ ሰፊና የተመቻቸ ቤት እንደሚፈልግ ሁሉ እግዚአብሄር በምድር ላይ ለማረፍ ፣ ለመኖር ፣ ለመናገርና ለመስራት በቃሉ የተለወጠ የእግዚአበሄርን ቃል የሚታዘዝ በቃሉ ያደገ እግዚአብሄርን የሚያመልክ ህይወት ይፈልጋል፡፡ ሰው ያልተሰራ ቤት እንደማይመቸው ሁሉ እግዚአብሄርም ያልተሰራ ቤት እንደልቡ ለማረፍ ፣ ፣ ለመሄድና ለመስራት አይመቸውም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል በተሰራንና ባደግን መጠን እግዚአብሄር በስፋት ያርፍብናል ፣ ይኖርብናል እና ይናገርብናል፡፡ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 1ኛ ጴጥሮስ መልእክት 2፡5 https://t.me/reiseneh
መዝሙረ ዳዊት 121:1-8 (AMH) •••••••••• ¹ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ² ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ³ እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። ⁴ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም። ⁵ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል። ⁶ ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት። ⁷ እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል። ⁸ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል። መልካም እለተ ሰንበት
......በክብር አርጓል በራስ ቅል ጎልጎታ አዲስ ነገር ሆኗል የአለም መድሀኒት ኢየሱስ ተገሏል ሲለን እንዳልነበር የአለም መዳኛ በእንጨት ሰቀሉት እንደወንጀለኛ በእውነቱ ከሆነ ሀጥያት የለበትም መስክሯል ጲላጦስ ለፍርድ ቢያቀርቡትም እኔ አላገኘሁም አንዳች እንከን ከእርሱ የገሊላ ሰው ነው ወደ ሆሮዲስ መልሱ ሆኖም ላይቀርለት ተገደለ በቃ የአለምን ሀጥያት በሙቱ ሊያበቃ ሲጀመር ሲመጣ ሲወርድ ከሰማይ ሁሉም ሀጥያት ሰርተው የሰው ልጆችን ሲያይ ከገነት ተባረው ከአምላክ ህልውና ተቅበዝባዥ ኑሮአችንን ከሰማይ አየና እንዳልቻለ አይቶ የበግ የኮርማ ደም የዋኖስ የእርግብ ኃጥያትን ቢከድንም ከአብ ሊያስታርቀን ከቶውን አልቻለም ክርስቶስ መጣና የአብ ብቸኛ ልጅ በደሙ ሊያስታርቅ ሊሆን አማላጅ ሁሉን እየቻለ አቅመ ቢስ ሆኖ ሲመቱ ሲተፉ ሲሰድቡት ጨክኖ የዛሬውን ሳይሆን የነጌን አየና ሀጥያታችንን ወስዶ ሀጥያት ሆነና በእንጨት ሰቀሉት የተረገመ ብለው ሆምጣጤን አጠጡት እጅጉን ጨክነው ቢገባቸው ኖሮ ማን መሆኑንማ ቢያምኑበት በእርሱ በዳኑ ከጨለማ ግና ክፋታቸው ከመስቀል አውርደው መቃብር ከተቱት በድንጋይ ከድነው .......እኔማ ሳስበው ምኔን ወዶልኝ ነው ለሞት የተገባው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ መቃብር የገባው ........አሃሃሃ.... አሁን ገና ገባኝ የመሞቱ ሚስጥር የደም ላብ ሲያልበው በመስቀል ጣር ነብሱን ሳይሰስት ለኔ ላንተ ሲሰጥ ለካስ ሆኖ ኖሯል ከጠላት ሊያስመልጥ .........እናማ ..... እንዲህ ተማከሩ የካህናት አለቃ መቃብሩ ይጠበቅ ይጠንክር ጥበቃ እውን እንዳወራው ገሊላ ላይ ያኔ ስለመነሳቱ ሰምቻለሁ እኔ ኋላ እንደተናገረው የምር ከተነሳ መዘበቻ ሆነን እንዳይገጥመን አበሳ ግድ የለም ይታተም በማህተም ድንጋዩ መክፈት እንደማይቻል ሁሉም ሰው እንዲያዩ ብለው ተመካክረው ልባቸው እየፈራ የኔ ጀግና ኢየሱስ ሞቶ እንኳን ሲያስፈራ መች ይዋሽና እርሱ አደርጋለሁ ካለ በሶስተኛው ቀን እነሳለሁ እንዳለ ይሄ....ው ተመልከቱ መቃብሩ ተከፍቷል ጠባቂዎች እያሉ ዲንጋዩ ተፈንቅሏል ጀግና ሚባል ካለ ጌታዬ ነው ጀግና ሞትን አሸንፎ ድል አድርጓልና አንበሳም ከተባለ እርሱ ነው ሞ አንበሳ ሲኦልን ድል አድርጎ ብቸኛ የተነሳ አቅም እንደሌለው ሞቷል ብዬ ያልኳችሁ በጎልጎታ በእንጨት የተሰቀለላችሁ የኃጥያትን ዋጋ የከፈለላችሁ እርሱ ክርስቶስ ነው የዓለም ሁሉ ቤዛ በሀይል ሳይሆን በፍቅር ሁሉን የሚገዛ ሞተ ቢሉት እንኳን ሞትን አሸንፏል ሲኦልን ድል ነስቶ በክብር አርጓል 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ✍️ተፃፈ በጌታሁን አናሞ✍️ https://t.me/reiseneh
መዝሙረ ዳዊት 119:70-83,85-89,91-92,95-97,99,101,103-105,109-111 (AMH) •••••••••• ⁷⁰ ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል። ⁷¹ ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ። ⁷² ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። ዮድ ⁷³ እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ። ⁷⁴ በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል። ⁷⁵ አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ። ⁷⁶ ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባሪያህ ይሁነው። ⁷⁷ ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር። ⁷⁸ ትዕቢተኞች በዓመፅ ጠምመውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን በትእዛዝህ እጫወታለሁ። ⁷⁹ የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ። ⁸⁰ እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን። ካፍ ⁸¹ ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፤ በቃልህም ታመንሁ። ⁸² መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዓይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ። ⁸³ በጢስ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፤ ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም። ........... ⁸⁵ ኃጢአተኞች ጨዋታን ነገሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም። ⁸⁶ ትእዛዛትህ ሁሉ እውነት ናቸው፤ በዓመፅ አሳድደውኛል፤ እርዳኝ። ⁸⁷ ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም። ⁸⁸ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ። ላሜድ ⁸⁹ አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል። ........... ⁹¹ ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል። ⁹² ሕግህ ተድላዬ ባይሆን፥ ቀድሞ በጐስቍልናዬ በጠፋሁ ነበር። ........... ⁹⁵ ኃጢአተኞች ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፤ ምስክርህን ግን መረመርሁ። ⁹⁶ የሥራህን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው። ሜም ⁹⁷ አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው። ........... ⁹⁹ ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ። ........... ¹⁰¹ ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ። ........... ¹⁰³ ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ። ¹⁰⁴ ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ። ኖን ¹⁰⁵ ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። ........... ¹⁰⁹ ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም። ¹¹⁰ ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፤ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም። ¹¹¹ የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘላለም ወረስሁ።