tgindex
S

Space Science and Geospatial Institute

1 580
подписчиков
Охват к подписчикам
31,6%
ERR
Реакции к просмотрам
0,07%
19 на 50 постов
Пересылки к просмотрам
0,19%
49
Постов в день
3,9
всего 61

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 3 февр.без подписи0,53%
  • 11 авг.без подписи0,41%
  • 12 янв.ከቻት ጂፒቲ እና ከጉግሉ ጂሚኒ እንደሚበልጥ የተነገረለት አዲሱ የዲፕሲክ ሞዴል ======= SSGI ======= በቻይና ምስረታውን አድርጎ በመላው ዓለም በአጭር ጊዜ ተደራሽ መሆን የቻለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋሙ ዲፕ ሲክ፣ በመጪው የካቲት 'V4' የተባለ አዲስ የኤአይ ሞዴል ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰምቷል። አዲሱ የዲፕ ሲክ ሞዴል በኮዲንግ እና በሶፍትዌር ሥራዎች ላይ ይበልጥ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በበርካቶች ዘንድ እንዲጠበቅ አድርጎታል። ሞዴሉ በኮዲንግ ላይ የሚነሱ ውስብስብ ጥያቄዎችን በተራቀቀ እና በዘመነ መንገድ የሚመልስ በመሆኑ ለኮደርስ ስልጠናዎች እና ፕሮጀክቶች አይነተኛ መፍትሔ ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል። አሁን በሥራ ላይ ከሚገኙት የአሜሪካ ኩባንያዎች እንደ ቻት ጂፒቲ እና ጂሚኒ ጋር የሚወዳደር እና በኮዲንግ አገልግሎት ደግሞ በልጦ የሚገኝ የኤአይ አገልግሎት ዲፕ ሲክ ይዞ እየመጣ ነው፡፡ ሀገራት ለኮዲንግ ስልጠናዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተው በመስራት ላይ በመሆናቸው አዲሱ የዲፕ ሲክ ኤአይ በብዙዎች ዘንድ ተፈላጊ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህም የዲፕ ሲክ 'V4' የተባለው የኤአይ ሞዴል በዓለም አቀፍ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ እንደሚያደርገው ይጠበቃል ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው። #Ebc #Ebcdotstream #SSGI0,36%
  • 14 авг.ዘመኑን የዋጀና የሰለጠነ አገልግሎት አሰጣጥን እውን ለማድረግ የተቀመጡ የሪፎርም አቅጣጫዎች ትርጉም ተሰጥቷቸው እየተሰሩ መሆኑንም አክለዋል፡፡ የክትትል ኮሚቴ አባላቱም በጉብኝቱ ወቅት ባዩት ሁሉ መደሰታቸውን ገልጸው፤ ሪፎርም ያስፈለገው እንደዚህ አይነት ለውጥ በማስመዝገብ ዜጎችን በብቃት በማገልገል ተጠቃሚ ማድረግ እንዲቻል ነው በማለት በሪፎርም ትግበራ አቅጣጫ መሰረት እየተከናወኑ ያሉት እኝህ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። ለተጨማሪ መረጃ:- የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022 Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute Telegram: https://t.me/spacegeospatial ከምድር እስከ ህዋ … SSGI0,31%
  • 2 нояб.ቻይና አጥቢ እንስሳት ሕዋ ላይ መኖር እንደሚችሉ ለማወቅ ጥናት እያደረገች ነው ======= SSGI ======= ኃያላን ሀገራት በሕዋ ላይ የበላይ ለመሆን የሚያደርጉት ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። ቻይናም ለመጀመሪያ ጊዜ በጠፈር ላይ በአጥቢ እንስሳት ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉ ጠፈርተኞችን እና ለጥናቱ የሚያስፈልጉ አይጦችን የያዘ ቡድን ወደ ዓለም አቀፉ የሕዋ የምርምር ጣቢያ መላኳን አስታውቃለች። ጠፈርተኞቹ የስድስት ወራት ተልዕኮ እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በቆይታቸው የተለያዩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ያከናውናሉ መባሉን የሀገሪቷ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ምን አልባትም ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ከመሬት ውጪ ለረጅም ጊዜ መኖር ይችላሉ? የሚለውን ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ፍንጭ ለማግኘት እየጣርኩ ነው የምትለው ቻይና የተለያዩ ምርምሮችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። #EBC #SSGI0,29%
  • 14 авг.እንደ አዕዋፍ በሰማይ የሚበርር፣ እንደ ዓሣ በባሕር የሚዋኝ ዓለምን ያስገረመው አስደናቂው "ስካይ ኤክስ" ቴክኖሎጂ ********* ከሰማይ ከፍታ ወደ ጥልቅ የባሕር ውስጥ ዓለም ያለምንም ችግር መሸጋገር የሚችለው ይህ አዲስ ተሽከርካሪ የቴክኖሎጂውን ዓለም እጅግ እያስደመመ ይገኛል። ታዋቂው የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ 'ቻንግሻ ናይትሃውክ ኢንተለጀንት ቴክኖሎጂ' በሰማይ ላይ የመብረር እና በውኃ ውስጥ የመዋኘት አስገራሚ አቅም ያለውን "ስካይ ኤክስ" (SkyX) የተሰኘ እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ለዕይታ አቅርቧል። ከተፈጥሯዊው በራሪ ዓሣ (Flying fish) ንድፍን በመውሰድ የተሠራው ይህ ተሽከርካሪ፣ በአየር ላይ በሚሆንበት ጊዜ ክንፎቹን ዘርግቶ በአስገራሚ ሁኔታ የሚበር ነው። ወደ ውኃ ውስጥ ሲገባ ደግሞ ክንፎቹን በማጠፍ በቀላሉ መንቀሳቀስ ያስችለዋል። ይህ አስደናቂ ፈጠራ በውኃ ውስጥ በሰዓት እስከ 50 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት መጓዝ የሚችል ሲሆን፣ በአየር ላይ ደግሞ እስከ አንድ ሰዓት ድረስ ያለማቋረጥ የመብረር አቅም አለው። ቴክኖሎጂው በርካታ የዲዛይን ሙከራዎችን እና በእውነተኛ የውኃ ውስጥ ፍተሻዎችን በተሳካ ሁኔታ ያለፈ ሲሆን፣ አሁን ላይ ለተለያዩ ግዙፍ ዓላማዎች እንዲውል ሰፊ ጥናት እየተደረገበት ይገኛል። በተለይም ለድንገተኛ አደጋ አድን ሥራዎች፣ ለውቅያኖስ ጥበቃ እና ክትትል፣ እንዲሁም ለመከላከያ እና ደኅንነት ዘርፎች ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል። #SSGI #SkyX #Innovation #FutureTech #FlyingFish #Technology0,26%
  • 11 авг.без подписи0,22%
  • 16 авг.የጨረቃ ጉዞ ለሁሉም ሰው ክፍት ሊሆን ‼ ቢሊየነሩ ኢሎን መስክ ስፔስ ኤክስ የተሰኘው ኩባንያው የጨረቃ ጉዞን ለጠፈር ተመራማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሰው ክፍት ለማድረግ ማቀዱን ተናገረ። ማስክ "ሙንቤዝ አልፋ" ብሎ በሰየማት የጨረቃ መንደር፣ መሄድ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መጓዝ የሚችልበትን ትልቅ ህልም ይፋ አድርጓል። ኩባንያው ስታርሺፕ የተሰኘው መንኮራኩሩ በጠፈር ላይ ነዳጅ በመሙላት እስከ 100 ቶን የሚደርስ የመኖሪያ እና የግንባታ እቃዎችን ወደ ጨረቃ ማጓጓዝ ይችላል ብሏል። የአሜሪካው የጠፈር ተቋም (ናሳ) ሰዎችን ወደ ጨረቃ ለመመለስ ከስፔስ ኤክስ ጋር እየሰራ ቢሆንም፣ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ፈተና መንኮራኩሩ በጠፈር ላይ እያለ ነዳጅ የመሙላቱ ሂደት እንደሆነ ተገልጻል። ናሳ ሂደቱ መዘገየቱን የጠቆመ ሲሆን፣ አንድን መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ለመላክ ብቻ ከ11 በላይ የነዳጅ ጫኝ መንኮራኩሮች ጉዞ ሊያስፈልግ እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል። ለተጨማሪ መረጃ:- የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት (SSGI) የማህበራዊ ትስስር ገጾች YouTube: https://www.youtube.com/@ssgi Twitter/X: https://twitter.com/ssgi2022 Facebook: https://web.facebook.com/esstiethiopia/?_rdc=1&_rdr LinkedIn: https://et.linkedin.com/company/space-science-and-geospatial-institute Telegram: https://t.me/spacegeospatial ከምድር እስከ ህዋ … SSGI0,20%
  • 11 авг.без подписи0,20%
  • 25 нояб.ሲከሰት አደጋ፣ ሲያልፍ የቱሪስት መስህብ የሚሆነው የተፈጥሮ ክስተት ** ዓለማችን እስከ ዛሬ ድረስ በርካታ እና ታላላቅ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎችን አስተናግዳለች። ዛሬም ቢሆን በዓለም ላይ በየቀኑም ሆነ በተለያዩ ጊዜያት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እና መሰል ጭስ ይከሰታል። ከሰሞኑ በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ በሚገኘው የኤርታሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ የተከሰተው ፍንዳታ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከታዩት ፍንዳታዎች የተለየ እንደነበር መገለጹ የሚታወስ ነው። እንዲህ ዓይነት ፍንዳታዎች ወይም እንቅስቃሴዎች የሚያደርሱት የራሳቸው የሆነ አደጋ መኖሩ ስለማይቀር መጀመሪያ ከአደጋ መራቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊትም ጥብቅ ክትትል እና ምልከታ በማድረግ አደጋውን ቀድሞ ለማወቅ የሚደረገው ጥናት እና ምርምርም በዓለም ላይ ከፍተኛ ነው። በዘርፉ ባለሙያዎች አማካኝነት በፍንዳታው ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው እንዲዘዋወሩ ከማድረግ ጀምሮ ሁሉንም ዓይነት የጥንቃቄ ሥራዎች ይከናወናሉ። ከዚህኛው በተቃራኒ ደግሞ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች በሁሉም ቦታዎች ሊከሰቱ የማይችሉ በመሆናቸው፤ የሚከሰቱባቸው ቦታዎች ለተመራማሪዎችም ሆነ የተፈጥሮ ሂደቶችን ለመመልከት እና ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ሁሉ ትልቅ ዕድል ተደርጎ ይወሰዳል። በተለይ ተጓዥ ቱሪስቶች ለማየት ከሚጓጉላቸው ስፍራዎች መካከል ቀዳሚዎቹ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያለባቸው ቦታዎች ናቸው። በዓለም ላይ አብዛኞቹ ተጓዥ ቱሪስቶች የሚጓዙት ተፈጥሮን ለመመልከት እና የተፈጥሮ ክስተቶችን ለማየት እንደመሆኑ፤ ለእነርሱ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ቦታዎች ቅድሚያ ተመራጭ ናቸው። በአውሮፓውያኑ 2021 በአይስላድ የተከሰተውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መመልከት ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። በወቅቱ በሬይክጃቪክ ተራራ ላይ ተከስቶ የነበረው እሳተ ገሞራ ያስከተለው ጭስ፣ ብናኝ እና አመድ የአየር እና የየብስ ትራንስፖርትን እስከማስተጓጎል ደርሷል። ክስተቱ በወቅቱ አስደንጋጭ የነበረ ቢሆንም፤ በተቃራኒው ደግሞ ተዳክሞ ለነበረው የአይስላንድ ቱሪዝም ማደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከተራራው ላይ የሚፈሰውን የቀለጠ ዓለት ለማየት ቱሪስቶች እስከ ዛሬ ድረስ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ቦታው ይመጣሉ። ይህም የአይስላንድን የቱሪዝም ዘርፍ በእጅጉ ያነቃቃ እና ያሳደገ ሆኗል። በኢንዶኔዥያ፣ ፔሩ፣ ጃፓን እና ሀዋይ የተከሰቱ የእሳተገሞራ ፍንዳታዎች ያስከተሉት አደጋ ቢኖርም፤ እንደ ጎርፍ፣ አውሎ ንፋስ እና ሌሎቹ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ አደጋ ብቻ አስከትለው አላለፉም። ከፍንዳታው በኋላ የሚፈጠሩ ለዓይን ማራኪ የሆኑ መልክዓ ምድሮች፣ እንደ ውሃ የሚፈሰው የቀለጠ ዓለት እና በአንድ ቦታ ተከማችቶ የሚታየው የእሳት ባህር የጎብኚዎችን ቀልብ የሚገዙ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎቹ ውጤቶች ናቸው። እንዲህ ዓይነት ቦታዎችን ለመመልከት ብዙ ተጓዥ ጎብኝዎች ዛሬም ድረስ በየሀገራቱ ይጓዛሉ። ሰዓሊ የሠራው ድንቅ ስዕል የሚመስሉ ፈሰው የደረቁ የዓለት ቅርጾችን መመልከት ከተፈጥሮ አድናቂዎች እስከ ተመራማሪዎች የሚያዘወትሩት ነው። በእርግጥ የመሬት ውስጥ እንቅስቃሴን በተመለከተ የሚደረጉ ጥናቶች አሁንም ቢሆን የተጠናቀቁ እና የሰው ልጅ ያወቃቸው አልሆኑም። እናም እስከዛሬ ድረስ የመሬት ውስጥ እንቅስቃሴዎችን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ሁሉ እሳተ ገሞራ ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ አይጠፉም። አንዳንዴም የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሊከሰት እንደሚችል በሚጠበቅባቸው ቦታዎች ላይ ጎብኝዎች እና ተመራማሪዎች በቀጥታ ለመከታተል ቦታው ድረስ ይጓዛሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያ በአፋር ክልል፣ አፍዴራ ወረዳ፣ ኤርታሌ አካባቢ ኃይሌ ጉብ በሚባለው ቦታ በቅርቡ የፈነዳው አዲስ እሳተ ገሞራ የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሆኗል። ከቀይ ባሕር አልፎ እስከ የመን የደረሰው የፍንዳታው ጭስ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ከፍተኛ ሽፋን የተሰጠው ሆኖ ታይቷል። በ12 ሺህ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደፈነዳ የተነገረለት ይህ እሳተ ገሞራ የፍንዳታው ጭስ ብናኝ በየመን፣ ኦማን፣ ህንድ እና ሰሜናዊ ፓኪስታን መታየቱ ተዘግቧል። እናም ዕድልን ጭምር ይዞ የሚመጣውን ይህን ክስተት እንደ ሌሎች ሀገራት ሁሉ በማስተዋወቅ በቱሪስት መስህብነት ለመጠቀም መሥራት ይገባል። #EBC@spacegeospatial0,13%
  • 17 авг.https://vm.tiktok.com/ZGdxxk5c9/0,00%
  • 14 авг.без подписи0,00%