የ ተዋህዶ ልጆች
Статистикаመካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ትልቅ ትዕቢት የለም ቅዱስ ባስልዮስ @እንደ ኤፍሬም ባይሆን በአቅሜ በምችለው ማርያምን ማርያም በጣም እወድሻለው @Tekel_21
- Последний пост
- 19 авг. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ስለ ትዕግስት እንዲህ መባሉን ሰምተዋል? ጠቢቡ ሰለሞን ትዕግስተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል ብሏል። ምሳ 16፥3 አባባሉ ከባድና የየማይታመን መስሎ ይታየን ይሆን? ለምን ሞክረን አናረጋግጠውም፡፡ ኃያል ለመባል ብዙ ነገሮች ሊጎድሉንና ላይሳካልን ይችላል። ትዕግስተኛ ስንሆን ካልቻልነው ከኃያል ሰው መብለጥ እንችላለን፥፥ ትዕግስተኛ ስንሆን ካልቻልነው ከኃያል ሰው መብለጥ እንችላለን ማለት ነው። ትዕግስተኛ ከሆንን የማናሳካውና የማናሸንፈው ነገር አይኖርም ካሰብነውም የማንደርስበት ምንም ምክንያት የለም። ትዕግስት ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ከነሱ መካከል እንደሚከተሉት ናቸው፥ ፩ ትዕግስት የመብሰል ምልክት ነው። ፪ ትዕግስት ግልፍተኛ እንዳንሆን ያደርገናል። ፫ የደቂቃዎች ትዕግስት ከፍፃሜ ልክ ፀፀት ታድናለች። ፬ ትዕግስት ቀዝቃዛ ውሃ ነው የጋለውን ያበርዳል። ፭ ትዕግስት እርጋታንና ማስተዋል ያላብሳል። ፮ ትዕግስት ግንዛቤን ያሰፋል። ፯ ትዕግስት እውቀትን ይጨምራል። ፰ ትዕግስት የምንፈልገውን ለማግኘት የምንገብረው ምስዋዕት ነው። ፱ የትዕግስት የመጨረሻ ውጤት ከመከራ በኋላ የሚመጣ እውነተኛ ደስታ ነው። እንግዲህ ልብ እናድርግ መታገስ ማለት መቻል፣ መቻል ማለት እስከ መጨረሻው መቻል ማለት ነው። ታገስ ማለት መጥፎ ሁኔታ የሚያስከትሉትን ነገሮች ንቆ መተው ማለት ነው።
ቆሎ እየበላህ ለውዝ ለውዙን ሚለቅም ሰው መግደል ነው ያለበት 🤣
እግዚአብሔር ጊዜውን ጠብቆ ሊሰጠን ሲመጣ በቦታው እንዳያጣን በትዕግሥት እንጠብቅ ! 🤍🙏🏻 ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @Tekel_21 @Tekel_21 ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══ ❤️ ✉️ ⎙ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ:- ቅጣትን ሳይሆን የቅጣት እናት የሆነውን ኃጥያትን እንፍራ ። መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ 🙏
💖 🕊 💖 [ ሕማማተ እግዚእነ በልሳነ አበው [ የጌታችን መከራ በሊቃውንት አንደበት ] 🕊 የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ አለ ፦ ❝ ታመመ ፤ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ ፣ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፡፡ አይራብም ፣ አይጠማም ፣ አይደክምም ፣ አያንቀላፋም ፣ አይታመምም፣ አይሞትም ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ፡፡ ❞ 💖 🕊 💖 የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ከላከው ሲኖዶሳዊ መልእክት የተገኘ ፦ ❝ እርሱ መቼም መች ከመለኮቱ ሳይለይ የሰውነትን ሥራ ሁሉ ገንዘቡ አደረገ፡፡ ይኸውም መራብ፣ መጠማት ፣ መንገድ በመሔድ መድከም፣ በመስቀል ላይ መሰቀል ፣ በብረት ችንካር መቸንከር ነው፡፡ በሰውነቱ መቸም መች ሰው ነው ፣ በአምላክነቱም ሰውን የፈጠረ ነው፡፡ ግን ከማይከፈል ተዋሕዶ በኋላ መከፈል የለበትም፡፡ ሰው እንደ መሆኑ ስለ እኛ የታመመው የሞተው እርሱ ነው፡፡ በመለኮቱ ግን መቸም መች አይታመምም አይሞትም ፣ ሕማምንና ሞትንም አይቀበልም፡፡ በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው፡፡ ❞ 🕊 [ 🕊 እንኳን አደረሳችሁ 🕊 ] 💖 🕊 💖
ልባም ሴት ምን ዓይነት ናት? ፩. ልባም ሴት ራሷን ለፈጣሪዋ አሳልፋ ትሰጣለች። ፪. ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ ነች በቤት ውስጥ እንደ እንደ አደይ አበባ ትታያለች የቤቱ ውበትም እርሷ ነች። ሁሉ ሲያት ይደሰትባታል ንግግሮችዋ በጨው የተቀመሙ ናቸው ተግባሯ የእውነተኛ ክርስቲያን ተግባር ነው። ፫. ልባም ሴት ለሐሜት ጊዜ የላትም ጊዜዋን በቃለ እግዚአብሔር፣ በጸሎት የተሞላ ነው፡፡ ፬. ልባም ሴት ዓለም ላይ ያለው ልብስ ሁሉ ለሷ እንደማይመጥን ታውቃለች፤ በብልጭልጭ እና በፋሽን አትታለልም ሺህ ወንድ እሷን ፈልጎ ቢመጣ ምንም አይመስላትም ራሷን አታኮራም፣ ውበት ከንቱ ጠፊና ረጋፊ እንደሆነ ታውቃለችና። ፭. ልባም ሴት ሰውን አትንቅም ታጋሽ ነች ቁጣዋም የዘገዬ ነው፤ ለበጎ ሥራ እግሮችዋ ይሮጣሉ ንግግሯ ሁል በጨው እንደተቀመመ በቃለ እግዚአብሔር የታሸ ነው። ፯. ልባም ሴት ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም። (መፅሀፈ ምሳሌ 31 ፥ 12) ፯. ልባም ሴት ብዙ ተስፋ አላት በሚገጥማት ውጣ ውረድ አትጨነቅም ስጋትም አይገጥማትም እግዚአብሔር ከችግሮቿ በላይ ስለሆነ ችግሮችን እንደሚፈታ ታምናልች። ፰. ልባም ሴት ዝም ብላ በምድር ላይ ኖራ አታልፍም ለትውልድ የሚጠቅም ተግባር ሰጥታ ታልፋለች። ፱. ልባም ሴት ዓላማ እንደሌለው እንደ ኖህ አሞራ በወጣችበት አትቀርም፥ በጊዜ ወጥታ በጊዜ ትመለሳለች ፍሬ አልባ በለስም አይደለችም፥ በምታደርገው ነገር ሁሉ እንደ ንብ ታታሪ ነች። ፲. ልባም ሴት ከፈጣሪ የተሰጣት ጊዜ በአግባቡ ትጠቀማለች ያለ አግባቡ የሚባክን ጊዜና ሰዓት የላትም። ፲፩. ልባም ሴት ለማስታረቅ ትሮጣለች እንጂ በሰው ነገር አትገባም፤ ሰነፍ የተባለው ናባል ዳዊትን በሰደበው ጊዜ ዳዊትም ሊያጠፋው ሲሄድ ከመንገድ አቢጊያን አገኛት፥ እርሷም በትህትና ያዘችው ለመነችውም አሳቡንም አስቀየረች፥ ልባም ሴት መጥፎን በበጎ ታስቀይራለች። ፲፪. ልባም ሴት ቂም በቀልን አትይዝም ሆደ ሰፊና አርቆ አሳቢ ሁሉን እንደ አመሉ የምታስተናግድ ትዕግስተኛ ናት። በእውነት! "ልባም ሴት ማን ናት?" ( መፅሀፈ ምሳሌ 31 ፥ 10 - 30 ) በእርግጥም ልባም ሴት ዋጋዋ ከቀይ እንቁ ትበልጣለች። እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ውበት ሽልማት ጌጥ ናት። ሠናይ ቀን 💖 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21
ታዛዥነትና ተዘክሮተ እግዚአብሔር+ አባ ዮሐንስ ኃፂር ከሚታወቅባቸው መልካም ምግባራት መካከል የሚጠቀሱለት ናቸው ታዛዥነትና ተዘክሮተ እግዚአብሔር፡፡ አንደ ቀን አባ ባሞይ ዮሐንስ ኃፂርን የደረቀ እንጨት ተክሎ ለምልማ እስክታፈራ ድረስ ውኃ እንዲያጠጣት አዘዘው፡፡ ያለማንገራገር በትኅትና ሆኖ አሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል ከሚርቅ ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ ውኃ እያመላለሰ ያጠጣ ጀመር፡፡ በሦስተኛው ዓመት ያቺ በትር ለምልማና አብባ ያማረ ፍሬ አፈራች፡፡ አባ ባሞይ በዮሐንስ ታዛዥነት እጅግ ተደሰተ፡፡ ፍሬውን ለቅሞ ለገዳሙ መነኮሳት እንካችሁ ይህ የታዛዥነት ፍሬ ነው እያለ ሰጣቸው፡፡ መነኮሳቱም ይህን ተአምር ባዩ ጊዜ አደነቁ፡፡ ለቅን እና ታዛዥ ሰው ይህን ጸጋ የሰጠ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፡፡ "መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፡፡'' ምሳሌ 12፤2
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌻2017🌻መልካም🌻አዲስ አመት🌻 🌻🌻🌻 መልካም🌻አዲስዓ መት መልካም🌻 አ🌻ዲ🌻ስ መልካም 🌻 ዓ🌻መ🌻ት ለወዳጄ 🌻 ዓ🌻መ🌻ት 🌻🌻🌻🌻 አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት 🌻🌻🌻🌻 🌻መ🌻ል 🌻ካ🌻ም🌻🌻🌻🌻 🌻አ🌻ዲ🌻ስ🌻ዓ🌻መ🌻ት 🌻 🌻 🌻 🌻 🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻 አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት 🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻 🌻 🌻 🌻 🌻🌻አዲስ 🌻🌻🌻አመት 🌻🌻መ🌻ልካም 🌻🌻አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት አዲስ🌻ዓመት 🌻መልካም 🌻 አዲስዓመት 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 አዲስዓመት🌻ለወዳጄ🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌺 ይ🌻ህ🌻🌻አ🌻መ🌻ት🌻🌼 የ🌻ሰ🌻ላ🌻ም🌻🌻አመት🌻🌷 የ🌻ፍ🌻ቅ🌻ር 🌻🌻አመት🌻🌷 የ🌻ሞገስ 🌻 የ🌻ክብር 🌻 የ🌻ሹመት🌻 የ🌻ታላቅነት🌻 🌻ዓመት 🌼 🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌷🌹🥀 🌻ይ🥀ሁ🌹ን🌷ላ🌼ች🌹ሁ 🌾 🌻🥀 🌼 🥀🌹🌺 🌷 🌻የበረከት 🌻 🌻የሹመት 🌻 🌻የምርቃት 🌻 🌻የመግዛት 🌻 🌻የከፍታ 🌷🌻 🌻ዓመት 🌷🌻 🌻 ይሁን 🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌼🌼🌼 🇪🇹ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት 🙏 🕊🌻🌻 🌻🌻🌻 ያሰብነው የሚሳካበት 🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻የካሳ🌻የሰላም🌻የጤና🌻የበረከት🌻🌻 🌻🌹🌾ዓመት 💐🌷ይሁንልን።🌻🕊🌻🌻 🌼@Sky_Sports2🌼 🌼@Sky_Sports2🌼 🌼@Sky_Sports2🌼 🌼🌼🌼🌼
"በዕፀ መስቀሉ " ዝማሬ ዳዊት @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21
ተወዳጆች ሆይ ኑ አባቶቼና ወንድሞቼ እግዚአብሔር ለርስቱ ለመንግሥቱ የለያችሁ ምእመናን ሆይ ኑ፡፡ የልጅነትን ማኅተም ያለባችሁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆይ ኑ፡፡ ልጆቼ ይኽን ለነፍሳችን ድኅነት እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ትምህርት ትማሩ ዘንድ ኑ፤ ጊዜ ሳለልን እንመካከር ዘንድ ኑ፡፡ ኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ነፍሳችንን እንገዛት ዘንድ እንቻኮል፡፡ ዓይነ ልቡናችን ብሩህ ይኾን ዘንድ ኑ በዕንባ እንታጠብ (እናልቅስ)፡፡ ባለጸጋዉም ድኻዉም፣ ልዑላንም ሕዝቦችም፣ ወጣቶችም ጐረምሶችም፣ ሽማግሎችም ሕፃናትም፣ በአጣቃላይ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ከምረረ ገሃነም መዳን የምትሹ ሁላችሁም ኑ፡፡ ከክቡር ዳዊት ጋር ሆነን ምሕረቱ የበዛ ባለጸጋውን እግዚአብሔርን “ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ" አቤቱ ፈጣሪዬ ልመናዬን ሰምተኽ በዓይነ ምሕረትህ እየኝ፤ ተመልከተኝ፡፡ "አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢኑማ ለመዊት" የሞት እንቅልፍ እንዳያንቀላፉ ዓይኖቼን አብራቸው” ብለን እንለምነው /መዝ.13፥3-4/፡፡ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን እንደነበረው እንደ ዓይነ ስዉሩ ሰውም፡- “ተሣሃለኒ ኢየሱስ ወልደ ዳዊት" የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ” ብለን እንጩኽ/ማር.10፥48/፡፡ ዝም እንል ዘንድ የሚቈጡን ቢኖሩም እንደ በርጠሜዎስ ልጅ እንደ ጠሜዎስ ዓይነ ልቡናችንን እስኪያበራልን ድረስ አብዝተን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንጩኽ፡፡ ስለዚኽ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፤ ብሩህ ልቡናንም ገንዘብ እናድርግ፡፡ ገጻችንም ከቶ አያፍርም፡፡ ኑ! ሃይማኖትንና ምግባርን አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማያትን ለመያዝ እንሩጥ። ይኽን ያደረግን እንደኾነም የዚህ ዓለም ነገር ከንቱ ሆኖ ይታየናል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ንቁ እናድርግ፤ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ብንመጣም አይዘጋብንምና ኑ እንፍጠን፡፡ ምሽቱ ቀርቧል፤ ለኹሉም እንደየሥራው የሚከፍለው ልዑለ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊመጣ ነው፡፡ /#ንስሐ - #በቅዱስ_ኤፍሬም /
#ሆያ_ሆዬ_ሆያ_ሆዬ ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ (4) ተገለፀ ሆ በታቦር ላይ ሆ ብርሃኑን ሆ ለእኛ ሊያሳይ ሆ የምሥራች ሆ እልል በሉ ሆ ለሁሉ አባት ሆ ለ አዳኙ ሆ በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው /4/ #አዝ___ ፅልመት ጠፍቶ ሆ ብርሐን ሆነ ሆ በክርስቶስ ሆ ተከወነ ሆ ያን ጨለማ ሆ በአንተ አልፈናል ሆ በክርስቶስ ሆ ሰው ሆነናል ሆ በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው /4/ #አዝ___ ጴጥሮስ ያዕቆብ ሆ ዮሐንስ ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ በ ኢየሱስ ሆ ተመርጠው ነው ሆ በዚህች እለት ሆ ይህን ክብር ሆ ለማየት ሆ በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው /4/ #አዝ ለእኛ በዚህ ሆ ብንኖር ሆ መልካም ነበር ሆ ያውም ክብር ሆ ሦስት ዳስ ሆ እንስራና ሆ እዚህ እንኑር ሆ በምሥጋና ሆ በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው /4/ #አዝ___ ተገለፀ ሆ በታቦር ላይ ሆ ብርሃኑን ሆ ለእኛ ሊያሳይ ሆ የምሥራች ሆ እልል በሉ ሆ ለሁሉ አባት ሆ ለ አዳኙ ሆ በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው /4/ ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት /4/ ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእውነት ያድርሰን በህይወት ያድርሰን በህይወት/2/ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ ይመክራል፦"ደስታና ሰላምን የሚነጥቁ ሦስት የሰይጣን ወጥመዶች አሉ፦ ➛ ስላለፈው መጸጸት፣ ➛ ስለሚመጣው መጨነቅ እና ➛ ስለ ዛሬው አለማመስገን ናቸው"
ደና ዋላችሁ 🙏🙏
👉👉👉 እግዝአብሔር ለ አንተ ሲል ራሱን ዝቅ አደረገ። አንተ ግን ለራስህ እንኳን ስትል ራስህን ዝቅ ማድረግ እንዴት ያቅትሃል ✍✍✍ ቅዱስ መቃርዮስ #አረ ሼር አርጉ ባጌታ ስም 😔🙏 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21
የ ተዋህዶ ልጆች pinned «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ስንክሳር ዘወርኅ ዘሐምሌ ፳፮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ስድስት በዚች ቀን መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና…»
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል" ቀናችንን በጸሎት እንጀምር ስንክሳር ዘወርኅ ዘሐምሌ ፳፮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ስድስት በዚች ቀን መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው ጻድቁ ዮሴፍ አረፈ። ✝ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ✝ ✝ (ፍሬምናጦስ) ✝ ❖ ቅዱስ አባታችን አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በ245 ዓ.ም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ህዳር 26 ቀን ሲወለዱ ታላቅ ብርሃን ከሰማይ ወርዶ ለ7 ቀናት አብርቷል፡፡ ❖ ቅዱሳን መላእክትም ወደ ምድር ወርደው በመወለዳቸው ታላቅ ደስታን አድርገዋል፤ በተወለዱም ጊዜ ✍ ‹‹ለአብ ስግለት ለወልድ ስግደት ለመንፈስ ቅዱስ ስግደት ይገባል፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጡኝ ቅድመ ዓለም ለነበሩ ዛሬም ላሉ ዓለምን አሳልፈው ለሚኖሩ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ብለው ዳግመኛም አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ብለው ፈጣሪያቸውን በአንድነት በሦስትነት አመስግነዋል፡፡ ❖ በሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ አትናቴዎስ በሚገባ ተምረው ካደጉ በኋላ በ257 ዓ.ም ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ስሙ ሜርጵዮስ ከሚባል ከአንድ ነጋዴ ጋር መጡ፡፡ ❖ ከእነሱም ጋር አድስዮስ የሚባል ልጅ ነበር፤ ወደ ሀገራችንም ሊመጡ የቻሉት እንዴት ነው፤ ቢሉ መጀመሪያ ለሰባት ወር በአንድ ሌላ አገር ኖረው ወደ ኢየሩሳሌም ሊመለሱ ሲሉ የበረሃ ሽፍቶች ሜርጵዮስንና ሌሎች መንገደኞችን ገደሏቸውና ሁለቱን ልጆች ማርከው ወስደው ስሙ አልአሜዳ ለሚባል ለአክሱም ንጉሥ ሰጡት፡፡ ✍‹‹ግዝረትና እምነት በእናንተ ዘንድ አለ ነገር ግን ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ መቀበል በእናንተ ዘንድ የለም›› አለው፡፡ ❖ ቅዱስ ሚናስም ‹‹ግዝረትንስ አባቶቻችን ሌዋውያን አመጡ፣ በክርስቶስ ማመንን ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ጃንደረባ አመጣልን፡፡ ❖ ስለ ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ ሐዋርያ ወደ እኛ አልተላከም ነገር ግን ያልከውን ሁሉ የሚያደርግልን የሚባርከንና የሚቀድሰን ጳጳስን ታመጣልን ዘንድ ሊቀ ጳጳሱ ወዳለበት ወደ እስክንድሪያ አገር አንተ ሂድ›› አለው፡፡ ❖ ጥምቀትስ በጃንደረባው በኩል አገራችን ገብቶ ነበር ነገር ግን ገና ስላልተጠናከና ብዙ ሕዝብም አልተጠመቀም ነበርና አባታችን ፍሬምናጦስ አጠናክሮ ያልተጠመቀውን ሁሉ አጥምቆአል፤ ፍሬምናጦስም ወደ እስክንድሪያ ለመሄድ አስቦ ሳለ እንደተኛ ድንግል ማርያም ተገልጣለት። ✍‹‹ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥተሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ›› አለችው፡፡ ❖ እርሱም ቅዱሳኑን ነገሥታት አብርሃንና አጽብሓን አግኝቶ ከእነርሱም ጋር ተማክሮ ወደ እስክንድሪያ ሄዶ በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ታህሳስ 18 ቀን ተሾመ፡፡ ❖ ስሙንም ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አለው፤ ሰላማ ማለት እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስታርቅ ማለት ነው፤ ከሣቴ ብርሃን ማለትም ሃይማኖትን ገልጦ የሚያስተምር ማለት ነው፡፡ ❖ ቅዱስ አትናቴዎስም ከሾመው በኋላ ታቦትና በጣም ብዙ ንዋያተ ቅድሳትንና መገልገያ ዕቃዎችን ሰጥቶ መርቆ በሰላም ወደ ኢትዮጵያ ላከው፡፡ የማር አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ረድኤታቸው በረከታቸው ይደርብን አርኬ ✍️ሰላም ሰላም በቃለ ትፍሥሕት ዕብሎ። እንዘ አዐብዮ ወአሌዕሎ። ሰላማ ኅሩይ ኆኀተ አሚን ወተሣህሎ። አሥረቀ በኢትዮጵያ ለብርሃነ ክርስቶስ ጸዳሎ። እንዘ ላዕሌሃ ጽልመት ወቆባር ሀሎ። @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21
አደራ... ምን እንደጎደለኝ ሳልነግርሽ ታውቂያለሽ ከማንም በላቀ ታስፈልጊኛለሽ። መቋጠሪያው ጠፍቶ የጭንቀቴ ውሉ ድንግዝግዝ ብሎ ይታየኛል ሁሉ። በእቅፍሽ ያቀፍሽው የሰላሙ አለቃ ፍቅር አለ በእጁ ለአለም የሚበቃ። እንደ ዶኪማስ ቤት ጎጆዬን ደግፊ ልጄ ሆይ በይና ልቤን አሳርፊ። የነፍሴንስ ነገር አደራ እመቤቴ በምልጃሽ ይሰራ የዘላለም ቤቴ። @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21
ብራናም ለምኖ፦ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ።ሁሉም አደነቁ። ከነብዩ፤ ከሰማዕቱ፤ ከመጥምቁ በረከት ረድኤት ያሳትፈን ። #መጥምቁ_ዮሐንስ
🌹❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው🌹 ✥##ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን✥አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ✥ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ ✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ ✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ ✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ ✥ይህ ገብርኤል ነው✥ የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ ✥ገብርኤል ነው✥ የአሸናፊና የኃይል መልአክ ✥ገብርኤል ነው✥ ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ ✥ገብርኤል ነው✥ "የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን" ❖አሜን❖ @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21
@እንደ ኤፍሬም ባይሆን በአቅሜ በምችለው ማርያምን ማርያም በጣም እወድሻለው @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21 @Tekel_21