አዶናይ
Статистикаበዚህ ቻናል በኩል የታረደውን የእግዚአብሔር በግ እያከበርን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በውስጥ ሰውነታችንን በሀይል እንበረታለን። መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ነው 🥰 @AdonaiComments_bot
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 044
- 1/48двое суток
- 1 196
- 1/72трое суток
- 1 290
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ስልካቹን ለተወሰኑ ቀናት ዘግታቹት ፣ በአለም ከሚሰማው ጫጫታ ራሳቹን አግልላቹ በጌታ እግሮች ስር በህልውናው ውስጥ ብቻቹን ሆናቹ ስታለቅሱ ራሳቹን ማግኘት አልናፈቃቹም 🙌🏼 ?
ዋናውን ተስፍችንን እንዳትረሱት 🙌🏼 ኢየሱስ ሊወስደን በቅርቡ ይመጣል !
🎙️ፀሎቴ ጋ ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ፣ ከእግሮችህ ስር መድሃኒትን ይዜ እንድነሳ፤ ከዛም ባለፈ ባንተ በራስህ እደነቃለሁ፤ባወኩህ ቁጥር እወድህና እዛው ከርማለሁ። ነፍሴ ጌታዋን ስትናፍቅ የምከፍትላት መዝሙር ነው፤ ይሄን መዝሙር እየሰማቹ ከጌታ ጋር ጊዜ አሳልፉ። @thedayofpentecost @thedayofpentecost
ባወኩህ ቁጥር እወድህና እዛ እከርማለሁ 🙌🏼
ከዛም ባለፈ በአንተ በራስ እደነቃለሁ
ከእግሮችህ ስር መድሀኒትህን ይዤ እንድነሳ . . .
ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ . . .
ልጅ ያሰበው አልሆነም ትዝ ይላቿል ሉቃስ 15 ላይ ያለው የጠፋው ልጅ ታሪክ ? እዚህ ታሪክ ውስጥ የጠፋው ልጅና የአባትዬው የሀሳብ ልዩነት ይገርመኛል፤ ልጅ ከአባቱ የድርሻውን ንብረት ከወሰደ በኃላ ወደ ሩቅ ሀገር ጠፍቶ የልቡን እያደረገ ገንዘቡን ያጠፋል ታዲያ በዚህ ጊዜ ትናንት ከአባቱ ይልቅ ያመነው ገንዘቡ ቀስ በቀስ ሲከዳውና የሚበላው ሲያጣ የግድ ህይወቱን ለማስቀጠል ሲል ትናንት ልጅ በነበረበት ቤት እንደ ባሪያ ለመኖር ይወስናል፤ ተበዳይ አባት ግን ያን ሁሉ ጥፍት ረስቶ ልጄ አንድ ቀን ሊመለስ ይችላል በሚል ተስፋ ለጠፋው ልጁ የእጅ ቀለበት እና ለሰውነቱ ጥሩ ልብስ እያዘጋጀ እንዴት ሮጦ እንደሚያቅፈው ያስባል፤ ታዲያ በመጨረሻ ልጅ የትናንቱን ጥፍት እየሰበ ከወሰነው ባርነት ይልቅ አባት ልጅነቱን እያሰበ የወሰነው ክብር በልጦ ተገኘ። የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች እናንተ ትናንት ላይ ያጠፋቹትን ጥፍት እያሰባቹ ለራሳቹ ከሰጣቹት ስፍራ በላይ ጌታ ልጅነታቹን እያሰበ ያዘጋጀላቹ ያ የክብር ስፍራ ይበልጣል። @thedayofPentecost @thedayofPentecost
ያላቹበትን ችግር ለሰዎች ከመናገራቹና ሰዎች ጋር መፍትሄ ከመፈለጋቹ በፊት መጀመሪያ የከበዳቹን ጉዳይ ምንም ሳታስቀሩ ለእግዚአብሔር ንገሩት ። እግዚአብሔር የሰማው ችግር መፍትሄ አያጣም !
ዛሬ ላይ ነፍሳችን ከደነዘዘችበት ፣ እኛም የግድ የኛ ካልሆነ ብለን ችክ ካልንበት እግዚአብሔር ግን ከማያውቀውና ከሚጠላው ጉዳይ ላይ ጨክነን ሮጠን የምሸሽበትን ፀጋ ጌታ ይስጠን🙏
የ 1 ቀን መጠጥ ለ 1 ቀን ብቻ ነው የሚያሰክረው መጠጥ የሚጠጣ ሰው የሚሰክረው በጠጣው ልክ ነው፤ ለአንድ ቀን የጠጣው መጠጥ ሳምንቱን ሙሉ አያሰክረውም በየቀኑ ለመስከር በየቀኑ መጠጣት ይኖርበታል፤ መንፈስ ቅዱስም ልክ እንዲሁ ነው አንዴ በመንፈስ ተሞልታቹ ሳምንቱ ሙሉ ሳትፀልዩ ሳምንቱን ሙሉ በመንፈስ መቀጣጠል አትችሉም ዘውትር በመንፈስ ለመስከር ዘውትር በፀሎት መትጋት ይኖርባቿል። @thedayofpentecost @thedayofpentecost
አመታዊው የወጣቶች ኮንፍረንስ ደረሰ!🤩🔥 CJ YOUTH ነሃሴ 8-10 🙌 @thedayofpentecost
🎙️ አረስርሰኝ 🙌🏼 እንደ ልጅ ጌታ ፊት የምናቀርባቸው ብዙ የህይወት ጥያቄዎች ቢኖሩንም የቱም ጥያቄያችን ግን ከዚህ አንዱ ጥያቄያችን በላይ አይደለም 😭 ናና አረስርሰን... @thedayofpentecost @thedayofpentecost
መቼም ቢሆን ካለመጀመር መጀመር ይሻላል ብዬ በስተመጨረሻም ቢሆን በ TikTok እና በ Instagram በኩል ሊጠቅሟቹ የሚችሉትን ሀሳቦችን ማካፈል ጀምሪያለሁ። Instagram https://www.instagram.com/manel_erma?igsh=MTl0czEyd25kZ3BiMw== TikTok https://www.tiktok.com/@adonai_el?_r=1&_t=ZS-97ax3Vfzaxm Follow እያረጋቹ 🙌🏼
እኔ ከመንፈስ ቅዱስ አብሮነት ውጪ መኖር እንደማልችል ሰው ሁሉ እንዲያቅልኝ ፈልጋለው... በቃ አልችልም ከህልውናው ውጪ መኖር 😭 የእውነት ነው የምላቹ እኔ ጋር ውድ ናቸው የምላቸው ነገሮች ከእኔ ቢሄዱ ላዝን እችላለሁ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ከእኔ ከራቀ የእኔ እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ገና ሳስበው ውስጤ ይደነግጣል መንፈስ ቅዱስ ሆይ ምንም ያህል ጥቅምህ በደንብ ባይገባንም ፣ ፍቃድህንም ሳናደርግ ቀርተን ብናሳዝንህም ከቤታችን፣ ከህይወታችን እንድትርቅብን ግን አንፈልግም😭 መንፈስ ቅዱስ ይኑር ከእኛ ጋር🔥
የሚጥለን ድካም በእግዚአብሔር ፊት ያልተነገረ ድካም ነው ! ንገሩት 🙌🏼 Instagram https://www.instagram.com/manel_erma?igsh=MTl0czEyd25kZ3BiMw== @thedayofpentecost @thedayofpentecost
ለደቂቃም ቢሆን አንተን የሚሸፍን ህይወት አይኑረኝ...
እግዚአብሔር አብርሃም ቤት ይስሃቅን ባይሰጥም መስዋዕት ይቀርብለታል እግዚአብሔር እዮብ ጋር ዝም ቢልም ይታመናል እግዚአብሔር ሙሴ ቤት የተናገረውን ባይፈፅምም ይመለካል እግዚአብሔር ዳዊት ጋር ቢቀጣም ይወደዳል ይህ እግዚአብሔር በህይወታችን ምንም አይነት ነገር ባያደርግ፣ ጠረተነው ዝም ቢል ፣ ፈልገነው ባይገኝም በኛ ልብ ውስጥ ያለው የአምላክነት ቦታ ግን በፍፁም አይቀንስም ! ባያድንም የሚመለክ አምላክ ነው ያለን ። @thedayofpentecost @thedayofpentecost
አለማወቃችን እንጂ በህይወታችን ያለ እግዚአብሔር ህልውና የኖርንባቸውን ቀኖች ያህል የከሰርናቸው ቀኖች የሉንም ። የኪሳራዎች ሁሉ ኪሳራ ፣ የማጣቶች ሁሉ ማጣት ያለ እግዚአብሔር ህልውና መኖር መጀመር ነው !
🎙️መንፈስ ቅዱስ በህይወቱ በፍፁም ሊክደው የማልችለውን የመንፈስ ቅዱስን አብሮነት እና ምህረት ያየ ሰው ማለት እኔ ነኝ 😭 መንፈስ ቅዱስ የእውነት ወዳጅ መሆን ይችልበታል። @thedayofpentecost @thedayofpentecost