tgindex
Mentesnot Kebede
@mentesnotkebede2020ангНиКскиК

~To reach people with Gospel 📖 ~To edify the believes ~I serve in Mercy in Christ Church ⛪ ~mob.0911693190📞

Последний пост
05:40
Последнее чтение
19:24
Постов за неделю
4
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ангНиКскиК
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
676
+7 Са 4 дн.
Сутки
−1
−0,15%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
543
21 постов
Вовлечённость
80,3%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всогО 22
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
91
1/48двое суток
104
1/72трое суток
112

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 05:404831

    ሰኞ 11/12/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል49) እውርና ዲዳ መንፈስ /02/ ማቴ12፡22-32 5. የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች “እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች” ማቴ12፡28 አጋንንት የሰይጣን ጭፍሮች፣ የወደቁ መላእክት ናቸው፡፡ ይህ የመናፍስቱ ዓለም በሥልጣን ተዋረድ የተደራጀ፣ መዋቅር ያለው እርስ በእርሱ አንዱ ሌላውን ሳይቃወም የሚሰራ፣ የጨለማ ኃይላት ናቸው፡፡ እነዚህ መናፍስቶች በዓየር ላይ ሥልጣን ያላቸው ሲሆን ያለ ክርስቶስ የሆነውንና ከኃጢአት በታች የወደቀውን ዓለም በሙሉ በማስጨነቅ የሚገዙ ናቸው “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው” ኤፌ6፡1,2 ይኸው መንፈስ በተደራጀ መንገድ የሚሰራ ስለመሆኑ ጳውሎስ ሲናገር “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” ኤፌ6፡12 ከዚህም የተነሳ ጌታ በዚህ ስፍራ እንዳደረገው ሰውን በማጥቃት፣ ዲዳና ደንቆሮ በማድረግ የሚሰራውን ይህን ኃይል ድል በመንሳት ሰውን ነጻ አወጣ፣ ይህ የሚያሳየው ሌላ ከመናፍስቱ ኃይል በላይ የሚልቅ የእግዚአብሔር ኃይል በመካከላቸው እንደመጣ የሚያለመክት ነው፡፡ ስለዚህ ነው “በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች” በማለት የሚሟገታቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሥልጣን በብሉይ ኪዳን በነበሩ አገልጋዮች ዘንድ አልነበረም፡፡ 6. ኃይለኛውን የማሰር ውጤት “ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል” ማቴ12፡29 መናፍስት ይህን ዓለም በይገባኛል፣ እንደራሱ ንብረት ይዞ ይሰራል፡፡ ሰዎችም በግልጽም እንዲሁም በተለያየ ኃይማኖታዊ ሽፋን እያመለኩ ይሰግዱለታል፡፡ ኃይለኛ በመሆኑ በሰው አቅም የሚደፈር አይደለም፡፡ ሰውን ሁሉ በሞት ፍርሃት አስረው ያኖራሉ “እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ …” ዕብ2፡15 ሰይጣን ድል ሊነሳው ያልቻለ ከሰው ልጆች መካከል አንድ ኃይለኛ ሰው ወደ ዓለም እንደገባ አውቋል ጌታ አርባ ቀን ከጸለየ በኋላ ሊፈትነው ቀረበ፣ ሰውን ሁሉ ያንበረከከበትን ፈተና አቀረበለት ጌታ ግን ፈተናዎቹን በሙሉ ከንቱ በማድረጉ ለጊዜው ሳይወድ በግዱ በሩን ከፍቶ አስገባው ለዚህም ነው ለሰዎች የእግዚአብሔር መንግስት መቅረቡን እያወጀ፣ ሰይጣን በልዩ ልዩ በሽታ ያሰቃያቸውን እየፈወሰ ሲዞር አንዳች ሊያደርገው ያልቻለው፡፡ ጴጥሮስ ሲናገር “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና” ሐዋ10፡38 ኢየሱስ በመጨረሻ በመስቀል ስራው ለዘላለም አለቅነቱንና ሥልጣኑን በመግፈፍ ድል ነሳው ቆላ2፡15 አሁን ሥልጣን በሰማይና በምድር የክርስቶስ በመሆኑ በእርሱ የሚያምኑ በሙሉ የዚህ ስልጣን ተካፋይ ሆኑ በዚህም ቤተክርስቲያን የኃይለኛውን ቤት እየበዘበዘች ትገኛለች፡፡ ጉዳዩ የኃይል ነው፡፡ የጌታ ልጆች ይህን ስልጣን ጸልየው ወይም ተቀድሰው የሚያገኙት ሳይሆን በክርስቶስ የተሰጣቸው በመሆኑ በእምነት ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡ 7. የመሳደብ ኃጢአት አይሰረይም “ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም” ማቴ12፡31 ፈሪሳውያን ዲዳና ደንቆሮ መንፈስ የነበረበትን ሰው ጌታ መንፈሱን አስወጥቶ ነጻ እንዳወጣው፣ እንደፈወሰው በሰሙ ጊዜ በአጋንንት አለቃ ነው አጋንንትን የሚያወጣው በማለት ክፉ ንግግር ተናገሩ፡፡ ይህንን ሲናገሩ እየሰደቡ የነበረው በክርስቶስ አድሮ ይሰራ የነበረውን መንፈስ ቅዱስን ነበር፡፡ ስለዚህም ጌታ በአዲስ ኪዳን ይቅር ስለማይባል አንድ አስከፊ ኃጢአት ተናገረ እርሱም መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ወይም እርሱን መቃወም ነው፡፡ ይህ ኃጢአት አብዛኛውን ጊዜ በአማኝ የሚሰራ ሳይሆን በማያምኑ ሰዎች የሚሰራ ኃጢአት ነው፡፡ ማንም በመንፈስ ቅዱስ እየተሰራ ያለን የጌታን ሥራ መቃወም የለበትም፣ ለምሳሌ የጌታ ልጅ ሆኖ አንዳንድ ጊዜ ከእርሱ አስተምህሮ ውጪ የሆኑ ናቸው ብሎ የሚላቸውን ሰዎች የሰይጣን ናቸው ከማለት በፊት በቃሉ መመርመር፣ ሰዎች ስላሉ ብቻ ከእነርሱ ጋር አብሮ ክፉ ነገር አለመናገር፣ የጌታን መንፈስ ማዳመጥ፣ ጊዜ በመውሰድ ጉዳዩን በሚገባ ማጤን ያስፈልገዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ የመንፈስ ቅዱስን ስራ ለሰይጣን መስጠት ነው፡፡ እንዲህ አይነት ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎች ከዚህ ተግባራቸው ከተመለሱና በዚያ አቋማቸው ጸንተው የህይወት ዘመናቸውን ካልጨረሱ ልክ እንደ ጳውሎስ ባለማወቅ እያደረጉት በመሆኑ ምህረትን ያገኛሉ፡፡ 1ጢሞ1፡13 አንዳንዶች መንፈስ ቅዱስን ሰድቤ ይሆናል ብለው የሚጨነቁ ሰዎች ጭንቀታቸው በራሱ በዚህ ኃጢያት አለመያዛቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ኃጢአት ሰርቶ ይቅር ወደማይባል ደረጃ የደረሰ ሰው ልቡ ስለሚደነድን አይጨነቅም ደግሞም ምንም ዓይነት የጸጸት መንፈስ አይታይበትም፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሼር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ዓርብ 08/12/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል48) የተዓምራት ኃይልና ተቃውሞው /01/ ማቴ12፡22-32 የእግዚአብሔር ኃይል በተገለጠበት ስፍራ ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ አለ፡፡ ለዚህም ደግሞ ሰይጣንና ክፉ ልብ ያላቸው ሰዎች ተቀናጅተው የሚሰሩት ሾል ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጅ ያለበትን ትልቅ ቀውስ ስለሚያውቅ የእርሱን እርዳታ ፈልገው ወደ እርሱ ለሚመጡና ለሚቀርቡ ሁሉ በብዙ ርህራሄ በፈቃደኝነት መፍትሄ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ጴጥሮስ ሲናገር “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና” ሐዋ10፡38 በዚህ ክፍል እውርም ዲዳም የሆነን ሰው ወደ ጌታ አምጥተው ጌታ ኢየሱስ ፈወሰው ስለዚህ ሰውዬው አየ፣ ደግሞም ተናገረ፡፡ ማቴዎስ ተፈወሰ ይላል ሌሎች ወንጌላት ግን ፈውሱ የተከናወነበት ዋንኛ ምክንያት፣ እርሱም አጋንንት ከዚህ ሰው ህይወት በመውጣቱ እንሆነ ይነግሩናል፡፡ ከብዙ ክፉ ነገሮች በስተጀርባ ያለው ዲያቢሎስ መሆኑን እናያለን፡፡ እንደዚህ የዲያቢሎስን መንግሥት ኪሳራ ውስጥ እየከተተ ያለ አገልግሎት መነቀፉ፣ ተቃውሞን ማስተናገዱ የማይቀር እውነታ ነው፣ ለዚህም ተቃውሞ የሚያስከትለውን ውጤትና የጌታን መልስ እናያለን፡- 1. አትጠራጠር “ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና፦ እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ” ማቴ12፡23 ትችት፣ ተቃውሞ፣ ጥርጣሬና አለማመን ባለበት ስፍራ ሁሉ በሌሎች ህይወት የሚያሳድረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ፈውስ ካላስደነቀን ምን ሌላ ነገር ሊኖር ነው፡፡ መቼም ይህ ሰዎችን የሚያስደምም ትሪክ አይደለም፣ ተጨንቆና ታስሮ ለነበረ ሰው መፍትሄ የሰጠ እውነታ እንጂ፡፡ ለዚህ ዓይነት ክፉ ትችትና ነቀፋ ጆሮን የሚሰጥ ሰው እምነቱን ሽባ ያደርግበታል፡፡ ይህንን ታላቅ ነገር ሰዎች እያዩ እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ ለምን ጥርጣሬ? ምክንያቱም በዙሪያቸው ያለው ተጽዕኖ ነው ይህንን የፈጠረው፡፡ ስለዚህ ትችትንና፣ ተቃውሞን ከሚያሰሙ ሰዎች በመራቅ የትኛውንም ነገር በቃሉ ወደ መመዘን መምጣት ይገባል ጳውሎስ ሲናገር “ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ” 1ተሰ5፡21,22 ይህ ነው እምነታችንን የሚገነባው፡፡ 2. መልካም ምላሽ የላቸውም “ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ” ማቴ12፡24 በዓላማ ዓይናቸውን የጨፈኑ፣ በፈቃደኝነት ልባቸውን የዘጉ ሰዎች በምንም መንገድ መልካም ነገር ሊያስቡም ሊናገሩም አይችሉም፡፡ ፈሪሳውያን ይህንን አስገራሚ የፈውስ ምስክርነት ሲሰሙ በአጋንንት አለቃ ነው አጋንንትን የሚያወጣው አሉ፡፡ ለሁሉ ነገር ትችት፣ ለሁሉ ነገር ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎች ፈጽሞ ጤና የሆነ መንፈስ እንደሌላቸው አመላካች ነው፡፡ ይህ ስድብ ነው፣ ስድብ ደግሞ አንዱ የሰይጣን መለያው ነው፡፡ ዮሐንስ በራዕዩ ያየውን ሲናገር “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው። እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ” ራዕ13፡5,6 ዛሬም እንዲህ አይነት ድፍረት የተሞሉና እውነተኛ የጌታ ሾል እየተሰራ፣ ሰዎች ነጻ እየወጡና ሰላም እየሆኑ እያዩ በልብ ድንዳኔና ሌሎች ስለነቀፉአቸው ያለምንም ማስረጃ ከአጋንንት ነው ለማለት የሚደፍሩ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ አደገኛ ድርጊት ነው፣ ሰይጣን ሰውን የሚጠቅም አንዳች ሾል የለውም፡፡ ጌታም ለተከታዮቹ ሲያስጠነቅቅ “ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!” ማቴ10፡15 3. መንግሥት ተለያይቶ አይቆምም “ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም” ማቴ12፡25 ጠቢቡ “አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት” ምሳ26፡4 እንደሚል ጌታ ለስድባቸው ስድብ አልመለሰም ነገር ግን ጨዋነት በተሞላ መንገድ ትልቅ ትምህርት ለዓለም የሰጠ ምላሽ ሰጠ፡፡ አንድነት ኃይል የመሆኑ ጉዳይ አይደለም በቤተክርስቲያን፣ በቤተሰብና በመንግሥት በሰይጣንም መንግሥት ውስጥ እንኳ የሚሰራ የማይለወጥ ዓለማቀፋዊ መርህ መሆኑን ተናገረ፡፡ አንድ ህብረት እርስ በእርሱ ከተለያየ ሊቆም ፈጽሞ አይችልም፡፡ ጳውሎስ በቅዱሳን መካከልም እንኳ ያለ መከፋፈል ጥፋትን ሊያመጣ ችንደሚችል ሲናገር “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” ገላ5፡15 ስለዚህ አጋንንት አጋንንትን ካወጣ መንግሥቱ ልትቆም አትችልም፡፡ የአመጽ ሰራተኞችም የአመጽ ስራቸውን ለመፈጸም ምን ያህል እርስ በእርሳቸው መናበብና መቀባበል ሊኖራቸው እንደሚችል ተናገረ፡፡ 4. ልጆቻቸው ምስክር ይሆኑባቸዋል “እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል” ማቴ12፡27 አንዳንድ የአይሁድ የታልሙድ ጽሁፎች እንደሚያሳዩት አይሁዳውያኑ በክፉ መንፈስ የተያዙ ሰዎችን ነጻ ለማውጣት የሚያደርጉአቸው ልምምዶች አሉ፡፡ ሉቃስም በሐዋርያት ሼል ላይ የዚህን የአጋንንት ማስወጣት ልምምድ በአይሁድ መካከል እንዳለ የጠቆመ አንድ አሳብ ሰንዝሮአል “አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ” ሐዋ19፡13 ስለዚህ ጌታ እንደ ሎጂክ ያነሳላቸው ነገር ቢኖር እኔ አጋንንትን በአጋንንት አለቃ የማስወጣ ከሆነ የናንተን ልጆች ምን ያስወጣሉ ልትሉአቸው ነው? የሚል ሞጋች ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ ልምምድ በኛም አገር በአንዳንድ ኃይማኖቶች ውስጥ አለ፣ አጋንንትን ውጣ እያሉ ሲያስጮሁ፣ አጋንንቱ ይሁን ሰውዬው ባይታወቅም ወጣን እያለ ሲጮህ እናያለን፡፡ መታወቅ ያለበት አጋንንት ሥራውን ባፈረሰ፣ በመናፍስቱ ዓለም ላይ ሥልጣን ባለው በክርስቶስ ስም ካልሆነ በቀር መናፍስት ታዘው አይወጡም፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሐሙስ 07/12/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል47) የእግዚአብሔር ምርጡ አገልጋይ ማቴ12፡15-21 ፈሪሳውያን ኢየሱስን ከመቃወማቸውና ከመጥላታቸው የተነሳ ሊገሉት ተማከሩ፡፡ ይህ አገልጋይ ግን ለላከው፣ እነርሱ አምላካችን ለሚሉት አባቱ ደግፎ የያዘው ምርጡ አገልጋይ ነው ነብዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ “እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል” ኢሳ42፡1 ይላል፡፡ አገልግሎት ከኢየሱስም ጀምሮ ጦርነት በመሆኑ ሰዎች፣ ሁኔታዎች ስለኛ የሚሉትን እያየን ተስፋ መቁረጥ የለብንም ይልቁንም ቃሉና የላከን ስለእኛ የሚለውን በመስማትና በማወቅ ሩጫችንንና አገልግሎታችንን ለመፈጸም መጽናት ያስፈልገናል፡፡ በእውነት እየሄድን ሰዎች ሲገፉንና ሲጠሉን ይህ እንግዳ ነገር አይደለም ጌታም እንዲህ ብሎአል “ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል …” ዮሐ15፡20 በዚህ ክፍል ፈሪሳውያን ኢየሱስ ላይ ሲያደቡ ማቴዎስ ሾለ አገልጋዩ ከትንቢተ ኢሳይያስ ጠቅሶ አስቀድሞ ሾለ እርሱ የተባለውን ይነግረናል፡፡ እነዚህን አሳቦች እንመልከት፡- 1. ለሁሉ መልስ አለው “ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው” ማቴ12፡15 ኢየሱስ ፈሪሳውያን ምን እየተማከሩ እንዳለ ሲረዳ እነሱን ለመመከትና ለመቋቋም ስጋዊ ጦርነት አልከፈተም ነገር ግን ከእነርሱ ፈቀቅ በማለት እርሱ በተላከበት ሾል ላይ ራሱን ጠምዶአል፡፡ ክፉዎች ምንም ያድርጉ የእግዚአብሔር አገልጋይ ራሱን እንዲህ በሚመስል ነገር ሊጠምድ አይገባም ጳውሎስ ሲናገር “ነገር ግን ጠብን እንዲያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፤ የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም” 2ጢሞ2፡23,24 በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ብዙ በሽተኞች ወደ እርሱ ሲመጡ ሲያይ ሁሉንም ፈወሳቸው፡፡ ይህ አስደናቂና ግልጽ ነገር ነው ወደ እርሱ ለመጡ በሽተኞች ሁሉ ያለው ፈቃዱ አንድ ነው እርሱም ፈውስ፣ ደህና መሆን ነው፣ ዛሬም የመይለወጥ ፈቃዱ ይኸው ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን በወንጌላት ውስጥ ወደ አስራ ሰባት የሚሆኑ ሁሉንም ፈወሳቸው የሚሉ ጥቅሶች እናገኛለን (ማቴዎስ 4:23-24፣ 8:16-17፣ 9:35፣ 12:15፣ 14:14፣ 34-36፣ 15:30-31፣ 19:2፣ 21:14፤ ማርቆስ 1:32-34፣ 39፣ 6:56፤ ሉቃስ 4:40፣ 6:17-19፣ 7:21፣ 9:11፤ እና 17:12-17) እርሱ ግን ህዝቡ እንዳይገልጡትና የተደረገላቸውን እየተናገሩ ይበልጥ የጠላቶቹን ቁጣና ቅንዓት እንዳያባብሱ ለማንም እንዳይናገሩ ያዛቸው ነበር፡- 2. ፍርድን ያወጣል “እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም” ማቴ12፡18,19 እግዚአብሔር በነብዩ ሲሳይያስ በኩል ሾለ አገልጋዩ ሲናገር የመረጠው፣ ነፍሱ ደስ የምትሰኝበት እንደሆነ ተናገረ ይህንኑ አሳብ በመገለጥ ተራራ ላይ ለጆሮ በሚሰማ መልኩ “… በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ” ማቴ17፡5 እርሱ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ ለሰው ልጆች፣ ለአህዛብ ሁሉ ፍርድን የሚያወጣ ማለትም በብዙ ለተጨቆኑት፣ ለተጠቁት መፍትሄ የሚሰጥ፣ የመፍትሄ ቃል ያለው ነው፡፡ ስለዚህም ነው ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ በብዙ ርህራሄ ይፈውሳቸው፣ ከመከራቸውና ከአበሳቸው ነጻ በማውጣት ለህዝቡ እረፍትን እየሰጠ ያለው፡፡ እርሱ ከማንም ጋር አይሟገትም አይከራከርም፣ ምንም እንኳ እርሱ የአደባባይ አገልጋይ ቢሆንም እርሱ ከተላከበት ሾል ውጪ በአደባባይ በሌላ ጉዳይ ድምጹ አልተሰማም፡፡ 3. አህዛብ ተስፋ ያደርጉታል “ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ” ማቴ12፡20,21 አይሁዳውያን እንደሚያስቡት የሚመጣው መሲህ የእነርሱ ብቻ ሳይሆን አህዛብ ሁሉ ተስፋ የሚያደርጉት በመንፈስ ነጻ አውጪ ነው፡፡ አስቀድሞ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ ሲሰጠው “… የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” ዘፍ12፡3 ብሎታል፡፡ እርሱ የተቀጠቀጠን ሸንበቆ አይሰብርም፣ ሸንበቆ ከተቀጠቀጠ ቀጥ ብሎ ስለማይቆም ይቆርጡታል እንዲሁም የሚጤስ የጥዋፍን ክር አያጠፋም፣ ዘይቱ ያለቀበት የጧፉ ክር ዝም ብሎ ስለሚጨስ ያደርጉ የነበረው ያንን የሚጤስ ክር እፍ በማለት ያጠፉታል፡፡ ጌታ ግን እጅግ ተስፋ የቆረጡትን፣ የመኖር ተስፋ የሌላቸውን፣ የተረሱትን፣ ቀምበር የተሸከሙትን ነጻ እያወጣ ተስፋቸውን በማደስ የህዝብን ተስፋ ያለመልማል፡፡ ስለዚህ አህዛብ በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ረብዕ 06/12/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 47) ግብዝ የሆነ ተቃውሞ ማቴ12:9- ሰው ባለማወቅ ብቻ ሳይሆን በራስ ወዳድነት ሲመላለስ ሌላውን ሲኮንን፣ ሲቃወም ይገኛል፡፡ አለማወቅም ሆነ ልሾ ወዳድነት ዓይንን ማጨለማቸው ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሼል እንቅፋቶችም ናቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ በማቴ7 ላይ በዓይኑ ግንድ ተሸክሞ ከሌላው ሰው ዓይን ጉድፍ ላውጣ ስለሚል ግብዝ ሰው ምሳሌ ሲሰጥ “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ሾለ ምን አትመለከትም? ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ” ማቴ7፡1-5 ፈሪሳውያን ሰንበትን ስለማክበርና በሰንበት ሼል እንዳይሰራ በመከላከል ወገባቸውን ታጥቀው የሟገታሉ ነገር ግን በቀዳሚነት ሰንበትን የሚጥሱትና የማያከብሩት ራሳቸው ሆነው መገኘታቸውን ጌታ አጋለጠ፡፡ እውነትን በመያዝ የሰዎችን ስውርና ክፉ ገበና መግለጥ እንዲህ ቀላል ነገር አይሆንም ስለዚህም ነው ፈሪሳውያን ኢየሱስን እንዴት እንዲያጠፉት ሲማከሩ የተገኙት “ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት” ማቴ12፡14 እውነትን በአመጻ መከልከል ማለት ይህ ነው ሮሜ1፡18 እንዲህ አይነት ሰው፡- 1. ወጥመድ ያዘጋጃል "እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ፡— “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ብለው ጠየቁት" ማቴ12:10 ከኢየሱስ ፈውሳቸውን ለመቀበል የተለያየ ዓይነት ችግርና በሽታ ያለባቸው ሰዎች እርሱ በተገኘበት ሁሉ ይገኙ ነበርና አንድ እጁ የሰለለች በሽተኛ ሰው በአንዱ ጉባኤ ተገኝቶአል፡፡ ይህንን ተገን በማድረግ እለቱ ሰንበት ሾለ ነበር ሰውዬውን በመፈወስ ሰንበትን ይሽር እንደሆነ ቁጭ ብለው በማስረጃ ለማየትና ለመክሰስ በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት፡፡ ሰንበትን የሰጠ እርሱ ነው “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” ዘጸ20፡8 የሚለው ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ህግን ፈጽሞ በእግዚአብሔር ፊት የጸደቀና ወደ እረፍቱ የገባ አንድም ሰው ስላልተገኘ እግዚአብሔር የራሱን ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ በመስጠት ወደ እረፍቱ ሊያስገባ አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታአል፡፡ አሁን ቀንን በማክበር የሚመጣ እረፍት ስለሌለ እግዚአብሔር ልሹ በስራ ላይ ነው ስለዚህ ነው ጌታ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው” ዮሐ5፡17 ይህንንም በተግባር በማሳየት እረፍትን የማያውቃትን ይህንን ሽባ ሰው በሰንበት ቀን በመፈወስ እረፍት ሰጠው፡፡ የኃይማኖት ሰው ዋና ትኩረቱ ሥርዓት ማስከበር እንጂ ሾለ ሰው ግድ የለውም ስለዚህም ነው ሰውዬውን ለመክሰሻ ለመጠቀም ያሰቡት፡፡ 2. ልሹ ያንን ያደርጋል "እርሱ ግን፡— “ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?" ማቴ12:11 እነዚህ ሰዎች ግብዝ በመሆናቸው የለበሱትን ሽፋን ጌታ ገፈፈባቸው እነርሱ በሰዎች ፊት ጻድቅ ናቸው በጓዳቸው ግን በአደባባይ የሚያወግዙትን የንኑ ነገር በቀዳሚነት የሚያፈርሱና የሚፈጽሙ እነርሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ጌታ ከእናንተ በጉ ጉድጓድ ቢገባበት ማለትም በጉ ችግር ላይ ቢወድቅበት የሰንበትን ህግ ሽሎ በጉን ከጉድጓድ የማያወጣ ማን ነው? እንግዲህ ሰው ከበግ እንዴት አይበልጥ በማለት ሲናገር ጥርሳቸውን ከመንከስ ውጪ ምላሽ አልነበራቸውም፡፡ እነርሱ ጋር ሲሆን ችግር የሌለው ሥርዓት ለሌላው ሲሆን ግን ለእግዚአብሔር ተርቋሪ በመምሰል ይቃወማሉ ሾለ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ጳውሎስ ሲናገር “አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና” ሮሜ2፡1 3. ክፉ ያስባል "ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት" ማቴ12:14 ምን ቢሰበክላቸው፣ ምን ያህል ገበናቸው ቢገለጥ ልባቸው የደነደነ በመሆኑ ወደ ንስሀ አይመጡም፣ መንገዳቸውን ለማስተካከል ፈጽመው አይፈልጉም፡፡ ነገር ግን ክፉ ለማድረግ በልባቸው ቢለዋ ይስላሉ፡፡ የሚመልሱት ስለሌላቸው ከእርሱ ዘወር ብለው እርሱን እንዴት እንደሚገሉት ይመክራሉ፡፡ በእርግጥ እውነት አሸንፋ ትወጣ ዘንድ ዋጋ ታስከፍላለች፣ የማሸነፍ ኃይል ያለው ግን ለእውነት ከቆመው ጋር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ያሰቡትን አሁን ሊፈጽሙት ያልቻሉት ሰዎችን በመፍራት ነው፡፡ በፈሪሳውያኑና በጌታ መካከል ውጥረቱ እየጨመረ እየሄደ ይገኛል፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሰኞ 04/12/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 46) ያለ እውቀት የሚደረግ ተቃውሞ ማቴ12:1-8 የጌታ የኢየሱሰ ደቀ መዛሙርት በመንገድ ሲሄዱ በመራባቸው ያልፉበት ከነበረው እርሻ መካከል እሸት እየሸመጠጡ በሉ በዚህ ጊዜ ይከታተሉአቸው የነበሩ ፈሪሳውያን ከፍ ያለ ወቀሳቸውን ሰነዘሩ “ፈሪሳውያንም አይተው፦ እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት” ማቴ12፡2 እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን የህጉ ጠበቃ አድርገው የሾሙ ነገር ግን ህጉን በሚገባ የማያውቁ፣ ቢያውቁም ትክክለኛውን ፍቺ የማይረዱ ደግሞም የህጉን አንቀጾች ለራሳቸው እንዲመች በማድረግ የራሳቸውን ማብራሪያ የጻፉ በመሆናቸው ህጉን ሰጪ ከሆነው ጌታ ጋር ፊት ለፊት ይላተሙ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የምንፈታበት መንገድ ትክክል ካልሆነ ከጌታ ጋር እንተላለፋለን እንዲህ ዓይነቱ መረዳት ብዙ የህይወት ቀውስም ያስከትላል፡፡ ጌታ ልሹ “… እናንተስ ሾለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሾለ ምን ትተላለፋላችሁ?” ማቴ15፡3 ዛሬም በዘመናችን አንዳንድ ሰው ቃሉን በጥሞና በግሉ ከመንፈስ ቅዱስ አስተማሪነት ሾር ተቀምጦ ከመማር ይልቅ በብዙ ህጸጽ የተሞሉ ማብራሪያዎችን (Commentary) የመጨረሻ ማስረጃ አድርጎ ይቀበላል ነገር ግን ያንን የጻፈ ሰው፣ ሰው እንደመሆኑ በራሳችን ካላስተያየን በቀር እንደ እውነት አድርገን መቀበል አይገባንም፡፡ ፈሪሳውያን እንደዚህ ናቸው የአባቶችን ወግ ከህጉ እኩል በመቀበላቸው ለስህተት ተዳረጉ፡፡ ጌታ ግን የህጉ ባለቤት በመሆኑ አረመው፡- 1. መጽሐፍትን ባለማወቅ "ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን?" ማቴ12:5 በህጉ የተራበ ሰው በአንድ እሸት ባለበት እርሻ መካከል ሲያልፍ ማድረግ ስላለበት ጉዳይ “ወደ ባልንጀራህ እርሻ በገባህ ጊዜ እሸቱን በእጅህ ቀጥፈህ ብላ፤ ወዳልታጨደው ወደ ባልንጀራህ እህል ግን ማጭድ አታግባ” ዘዳ23፡25 በዚህ ጥቅስ መሰረት በብቸኝነት የሚከለክለው ወደ እርሻው ማጭድ ማስገባትን ነው እንጂ ከእሸቱ በእጅ እያሹ መብላትን አልከለከለም፡፡ ፈሪሳውያን ግን በሰንበት ይህንን ማድረግ አልተፈቀደም በማለት ህዝብን ሲያከላክሉበት የነበረውን ማብራሪያቸውን በማንሳት ተከራከሩ ጌታ ግን በመጀመሪያ ዳዊትን በመጥቀስ ዳዊትና አብረውት የነበሩ ሰዎች ከሳውል እየሸሸ በነበረበት ወቅት ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተው ካህናት ብቻ እንጂ እርሱና አብረውት የነበሩት ይበሉት ዘንድ የማይገባውን ህብሰት እንደበሉ ተጽፎአል ይህንን አላነበባችሁም? አላቸው፡፡ በተጨማሪም ካህናቱ ራሳቸው በተቸገሩ ጊዜ በሰንበት ወደ ቤተመቅደስ በመግባት ሰንበትን በማርከስ ማድረግ የሚፈልጉትን ሲያደርጉ እንደ ኃጢአት አልተቆጠረባቸውም ምክንያቱም ሰንበት የተሰራው ለሰው ጥቅም እንጂ እንዲሁ ሥርዓት ብቻ አይደለም ስለዚህ ነው ጌታ “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና” ማቴ12፡8 በማለት የተናገረው፡፡ መጽሐፍትን ባለማወቅ፣ በትክክል አለመተርጎም፣ አንዱን ጥቅስ ከጠቅላላ ከመጽሐፍት ዓላማ ጋር ሳያነጻጽሩ የራስን ትርጓሜ መስጠት ለስህተት ይዳርጋል ስለዚህ ነው ጌታ “… መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ” ማቴ22፡29 ያላቸው፡፡ 2. ከመቅደስ የሚበልጥ መኖሩን ባለማወቅ "ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለ" ማቴ12:6 መንፈሳዊ ዓይኖቹ ያልተከፈቱለት አገልጋይ ትልቅ ቀውስ ያመጣል፡፡ ዛሬ በቤተክርስቲያን ህብረት መካከል የተማሩ በተለይ ስም ያላቸው ሰዎች ሲገኙ የተጠመቁበት ውሃ ከላያቸው ሳይደርቅ የቤተክርስቲያን መሪ ያደርጉአቸውና ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ነገርዋን እንድታጣ ምክንያት ይሆናል ምክንያቱም መንፈሳዊ ሾል መመራት ያለበት መንፈሳዊ በሆኑ ሰዎች ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በዓለም ጥበብ መንፈሳዊ ነገርን መስራት አይቻልም፡፡ ፈሪሳውያን እውር ያሉ ሰዎች በመሆናቸው በዘመናቸው ምን እየሆነ እንዳለ እየተረዱ አይደለም ስለዚህ የቤቱን ባለቤት፣ ሲጠበቅ የነበረውን መሲህ፣ ከካህናቱም ከመቅደስም የሚበልጠውን እርሱን ሲተቹ፣ ሲቃወሙ ተገኙ፡፡ ካህናቱ በመቅደስ ሰንበትን ሲያረክሱ ኃጢአት ካልሆነባቸው ከመቅደስ የሚበልጠው እርሱ የሚያደርገው እንዴት ስህተት ይሆናል?። ዛሬም እንዲሁ በተሳሳቱ ልማዶቻችንና መረዳቶቻችን የእግዚአብሔርን ነገር ስንገፋ እንገኛለን፡፡ የሥርዓት አደገኛነቱ ባለቤቱን መግፋቱ ነው፡፡ 3. ከመስዋዕት ምህረት መብለጡን አለማወቅ "ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁም ነበር" ማቴ12:7 ከምናደርጋቸው የትኛውም መንፈሳዊ ተግባሮቻችን ይልቅ ሰው ይቀድማል፡፡ ሰውን ያልጠቀመ፣ ሰውን መካከለኛ ያላደረገ ሥርዓት ለእግዚአብሔር ክብርም አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን የትኛውም ሥርዓት ሰውን ለመጥቀም ነው፡፡ ለእርሱ ከምናቀርበብለት መሥዋዕት በላይ ለሰዎች የምናደርገውን ምህረት ይወደዋል፡፡ በደጉ ሳምራዊ ታሪክ ውስጥ በወንበዴዎች ተደብድቦ በሞትና በህይወት መካከል የነበረን ሰው ሌዊው እንዲሁም ካህኑ ራሳቸውን የእግዚአብሄር አገልጋይ ብለው እየጠሩ በተሳሳተ መረዳት ይህንን ሰው ጥለውት ሄዱ፡፡ ይህ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ አልነበረም ለሰው ምህረት ያላደረገ፣ በድካሙ ያልደረሰ አገልግሎትና ሥርዓት ፍጹም እግዚአብሔርን አያከብርም፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ ምንም በደል ያላደረጉትን ደቀ መዛሙርቱን ሲተቹ የተገኙ ፈሪሳውያንን የወቀሰው፡፡ ምህረት ከመሥዋዕት ይበልጣል፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ዓርብ 01/12/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 45) ለህጻናት የተገለጠው ጥበብ ማቴ11፡25-30 ለእውነት ጆሮውን የደፈነ፣ ለሰማያዊ ጥበብ ልቡን ያደነደነ የአመጽን ቁልቁለት የሚንደረደር፣ ለጥፋት ራሱን ያዘጋጀ ትውልድ እንዳለ ሁሉ የሰማዩን ብርሃን በብዙ ናፍቆትና አክብሮት፣ በተከፈተ ልብ የሚቀበል ሌላ ትውልድ ደግሞ አለ፡፡ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የራሱ ቅሬታዎች አሉት፡፡ ስለዚህ ጌታ ልሹ “የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው” ማቴ22፡14 በማለት ተናግሮአል፡፡ ጥቂቶች የሚድኑበት ሚስጥር አንዳንዶች እንደሚሉት እግዚአብሔር ለጥፋት ስላዘጋጃቸው ሳይሆን ሰዎች በራሳቸው ፈቃድ ወደእነርሱ የመጣውን ብርሃን ስለገፉት ነው “ብርሃንም ወደ ዓለም ሾለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ሾለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም” ዮሐ3፡19,20 እነዚህ ሰዎች እድሉ ተሰጥቶአቸዋል ነገር ግን ሰዎች የመምረጥ ፈቃድ ስላላቸው መንገዳቸውን በራሳቸው ይመርጣሉ፡፡ እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ ሼል ካልሆነ በቀር ከማንም ጋር ግላዊ ምርጫ የለውም ስለዚህ ነው ጳውሎስ “በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሼል ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን” ኤፌ1፡5 ያለው። ይህን እውነት እንዴት እንደሆነ በዚህ ክፍል እንመለከታለን፡- 1. ከሰው ጥበብ የተሰወረ ነው “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ሾለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና” ማቴ11፡25,26 በመልካም ሥራው ወይም በጥበቡ የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን ሰማያዊ ስጦታ መቀበል አይቻለውም ምክንያተም የእግዚአብሔር እውቀት ከሰው ጥበብ የተሰወረ ነው ምክንያቱም “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ሾለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም” 1ቆሮ2፡14 ስለዚህ ሰው ለመዳን ከእግዚአብሔር ብርሃን ወይም መገለጥ ያስፈልገዋል “የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና… በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና” 1ቆሮ1፡19,21 ይህ በሰዎች ፊት ሞኝ ተደርጎ የተቆጠረ የወንጌል ስብከት ነው ሙት ለሆነው ለሰው መንፈስ ብርሃን የሚሰጠው፡፡ ምርጫ ግን የሰው ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ ህጻናት ለሚላቸው እርሱን ስለተከተሉት ሰዎች ስለተገለጠላቸው ሰማያዊ ሚስጥር ያመሰግናል፡፡ 2. ምንጩ ክርስቶስ ነው “ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም” ማቴ11፡27 በክርስቶስ ያመነ በሙሉ የአብ ስጦታ ነው ምክንያቱም ጌታ ልሹ “የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም …” ዮሐ6፡44 ብሎአል፡፡ ስለዚህ ሁሉ ከአባቴ ተሰጥቶኛል በማለት ተናገረ፡፡ ወልድን ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ ጌታ ሰዎች፣ የሰውን ልጅ ማን ይሉታል በማለት ደቀ መዛሙርቱን በጠየቀ ጊዜ ሁሉም የተሳሳተ ነገር ተናገሩ፣ አላወቁትም ጴጥሮስ ግን “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ” ጌታም ይህን ያወቀው ከራሱ እንዳልሆነ ስለሚያውቅ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ” ማቴ16፡17 አለው፡፡ አዎ ወልድን የሚያውቀው አብ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁ አብን ወልድ ካልገለጠ በቀር ማንም ሊያውቀው አይቻለውም ስለዚህ ነው ዮሐንስ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው” ዮሐ1፡18 በማለት ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዋንኛ ዓላማ የተናገረው፡፡ ክርስትና በክርስቶስ የሚሆን መገለጥ ነው እንጂ በሰው ፍቃድና ጥበብ የሚገኝ አይደለም፡፡ 3. ለነፍስ እረፍት ነው “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” ማቴ11፡28-30 ኃጢአተኛው ሰው ህግን በመፈጸም ወደ እግዚአብሔር ጽድቅ መድረስ አይቻለውም ስለዚህ ነው ከእግዚአብሔር የተሰጠው ህግ በራሱ ሸክም ሆኖበት የሚንገላታ የሆነው፡፡ ጌታ ፈሪሳውያኑን “እናንተ ደግሞ ሕግ አዋቂዎች፥ አስቸጋሪ ሸክም ለሰዎች ስለምታሸክሙ፥ ራሳችሁም በአንዲት ጣታችሁ ስንኳ ሸክሙን ስለማትነኩት፥ ወዮላችሁ” ሉቃ11፡46 አላቸው፡፡ ሰው ሊሸከመውና ሊፈጽመው ያልቻለውን ህግ እርሱ ልሹ ፈጸመው ስለዚህም “የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና” ሮሜ10፡4 ተባለ፡፡ ሰዎች በኃጢአትና በተወሳሰበው የህግ ትዕዛዝ ምክንያት ሸክም ከብዶባቸው ስላሉ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ በማለት ጥሪ የሚያደርገው፡፡ ማንም ይህንን ጥሪ የተቀበለ በሙሉ የነፍስ ሰላም ያገኛል፡፡ ማንም ከህግ ጋር ልቆራኝ ካለ ግን የሚሸከመው ህጉን ብቻ ሳይሆን የህጉን እርግማን ሁሉ ጭምር ነው፡፡ በክርስቶስ ብቻ ከአስጨናቂው ቀንበር ይገላገላል ገላ4:13፡፡ ሰው ከክፉው ጌታ ሾር ነጻ ከወጣ በኋላ በሌላው ነጻ ባወጣው ጌታ ቀንበር ሾር ካልኖረ ቀድሞ ስፍራ የለቀቀው ባሪያዬን በማለት ተመልሶ ይፈልገዋል ስለዚህ በክርስቶስ የዳነ ሰው ከክርስቶስ ልዝብና ቀሊል ከሆነው ቀንበር በታች (በክርስቶስ የህይወት መርህ ሾር) ህይወቱን ሊያስገዛ የግድ ያስፈልገዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን መገዛት ወይም ትህትና የምንማረው ሾለ እኛ ራሱን ዝቅ ካደረገው ከትሁቱና የዋሁ ጌታ ብቻ ነው፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሐሙስ 30/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 44) ጥበብ በልጆችዋ ጸደቀች ማቴ11፡16-24 እንደ ግለሰብም ይሁን እንደ ማህበረሰብ መንፈሳዊ ቸልተኝነት የሚያስከፍለው ዋጋ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር እድል ሲሰጥና መንፈሳዊ እውነትን ለአንድ ህዝብ ሲገልጥ ያ ትውልድ ተጠያቂነት አለበት፡፡ የዕብራውያን ጸሐፊ በመንፈሳዊ ነገር ለሚያፌዙና ለቸልተኞች ሲናገር “ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤ እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው” ዕብ6፡7,8 ብሎአል፡፡ ነገር ግን ምንም ቸልተኞችና ቀልደኞች ቢበዙም የተገለጠላቸውን እውነት የሚያከብሩ፣ ለተገለጠላቸውና ለተረዱት መንፈሳዊ ጥበብ እሺ የሚሉ፣ የሚታዘዙ በመኖራቸው ጌታ ኢየሱስ ጥበብን ገንዘብ ባደረጉአት ልጆችዋ ጸደቀች በማለት ተናገረ፡፡ ጌታም በዚህ ክፍል እንደዚህ ዓይነት ትውልድንና ከተሞችን የነቀፈበትን ሁኔታ እንመለከታለን፡- 1. ምንም የማይጥመው ትውልድ “ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ። እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል” ማቴ11፡16,17 ጌታ ኢየሱስ ሾለ ትውልዱ የገለጠው ምሳሌ እንቢልታ በሚባል የሙዚቃ መሳሪያ ቢመታ፣ ቢደረደር በዘፈን ምላሽ የማይሰጥ፣ ሙሾ ቢወጣለት ዋይ ዋይ የማይል ማለትም በለቅሶ ቦታ አስለቃሾች ቅኔአቸውን እየደረደሩ ቢያለቅሱላቸውም በለቅሶ ምላሽ የማይሰጡ ግራ እንደሚያጋቡ ዓይነት ሰዎች መሆናቸውን በመግለጥ ነው፡፡ ጌታ ይህን ምሳሌ ያነሳው የመጥምቁን ዮሐንስ መልዕክተኞችን ከሸኘ በኋላ ነው፡፡ ከመሲሁ መገለጥ በፊት መልዕክተኛ እንደሚላክ በነቢያት የተነገረለት ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ ወይም ሾለ እርሱ እንደተነገረለት ምግቡም አንበጣና የበረሀ ማር ነበረ በዚህ መልክ የመጣውን ይህንን ነብይ ጋኔል አለበት አሉ፡፡ ከእርሱም በኋላ የሰው ልጅ፣ መሲሁ ደግሞ እየበላና እየጠጣ መጣ ለዚህም የሚሉት ስላላቸው በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ አሉት፡፡ ጠቢቡ ሲናገር “ፌዘኛ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ወደ ጠቢባንም አይሄድም” ምሳ15፡12 ኢየሱስ በነበረበት ዘመን የነበረው ይህ ትውልድ ጥበብን ገንዘብ ለማድረግ ሳይሆን ከነፈሰው ጋር አብሮ የሚነፍስ የራሱ የሆነ አቋም የሌለው በመሆኑ አምላክ ሰው ሆኖ በመካከላቸው እንከን በሌለው ህይወቱ፣ በሰራቸው ተአምራት ለልሹ ሊማርከው አልቻለም ስለዚህ ነበር ጌታ በደብረዘይት ተራራ ላይ መንገዱን ወደ ኢየሩሳሌም ባቀናበት ወቅት “ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥ እንዲህ እያለ፦ ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል። ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤ አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና” ሉቃ19፡41-44 ያላስተዋለ ትውልድ ፍጻሜው ይህ ሆነ፡፡ 2. ተአምር ያለወጠው ትውልድ “በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ፦ ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና” ማቴ11፡20,21 ጌታ ኢየሱስ በብዙ የእስራኤል ከተሞች እየተዘዋወረ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ተዓምራቶች ዋንኛ አላማቸው እንደ ምልክት በመካከላቸው መሲህ መኖሩን የሚያመላክቱ ቢሆኑም ከህዝቡ ብዙዎች ግን በነዚህ ተአምራቶች ንስሃ በመግባት ወደ አዳኛቸው ለመመለሾ ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ አንዳንድ ከተሞችን ወዮልሽ በማለት ሊመጣ የሚችለውን አስከፊ ቀናቸውን ይነግራቸዋል፡፡ እስራኤል ልበ ጠንካራ በመሆናቸው በመካከላቸው የተደረገውን ተአምራት አልጠቀሙበትም ነገር ግን እነዚህ ተዓምራት ከብዙ ዘመናት በፊት በሃጢአተኝነታቸው ተቀጥተው የነበሩ እንደ ሰዶም ባሉ ከተሞች ተደርገው ቢሆን ኖሮ ከብዙ ዘመን በፊት ንስሃ ገብተው በተመለሱ ነበር፡፡ አሁንም ከእናተ ይልቅ እነዚያ ከተሞች በፍርድ ቀን ቅጣት ይቀልላቸዋል አለ፡፡ ይህ የሚሰጠው አንድ ፍንጭ አለ እርሱም በፍርድ ቀን የሁሉም ቅጣት እኩል አለመሆኑን ነው፡፡ 3. ፍርድ የሚጠብቀው ትውልድ “አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል” ማቴ11፡23,24 እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ስለወደደ አንድ ልጁን ለኃጢአት መስዋዕት ይሆን ዘንድ ቢሰጥም የሰው ልጅ ግን ይህንን ፍቅር አላስተዋለም፡፡ ጌታ በምኩራብ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰብክ ከተናገረው አንዱ ስራው “… የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል …” ሉቃ4፡19 ያለው ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከመጣበት ይህ የቤተክርስቲያን ዘመን እስኪያልቅ ድረስ የምህረትና የተወደደች የጌታ አመት ይባላል፡፡ በዚህ ሁሉ ሰፊ ዘመን በብዙ ትእግስት እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ ሲለምን ኖሮአል ነገር ግን ይህ የምህረት ዘመን ያበቃና ጌታ ያልተናገራት ነገር ግን ኢሳይያስ የተናገራት “… አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን …” ኢሳ61፡2 የተባለችው አስከፊዋ ቀን ትመጣለች፣ የምህረት በር ይዘጋል፡፡ እንደ ምህረቱ መጠን ቁጣውም አያድርስ ይሆናል ምክንያቱም እርሱ የፍቅር አምላክ ብቻ ሳይሆን የፍርድም አምላክ ነው፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ረብዕ 29/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 43) ጥርጣሬና መፍትሄው ማቴ11:1-15 ኢየሱስ ሰፊ ወደ ሆነው መከር የተማሩትን በተግባር ይለማመዱ ዘንድ የእርሱን ተተኪ አገልጋዮችን እያሰማራ ይገኛል፡፡ ለዚህም አገልግሎታቸውን እንዴት ማከናወን ይችሉ ዘንድ ረጅም መመሪያዎችን ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ እርሱ ደግሞ ወደ ሌሎች ከተሞች ሄዶ ሊያስምር እየተዘጋጀ ባለበት ሰዓት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ በመምጣት ጥያቄ ጠየቁት፡፡ ጥያቄውም የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? የሚል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚደብቀው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ሰው የሰውን ልክ ይረዳና ያውቅ ዘንድ የአገልጋዮችን ብርታትና ጽድቅ ብቻ ሳይሆን ድካማቸውንና ጥፋታቸውን ሳይቀር ዘግቦልናል፡፡ እግዚአብሔር ይህንን የሚያደርግበትን ምክንያት ጳውሎስ ሲናገር "ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ" 1ቆሮ10:11 ጌታ ኢየሱስ በድንቅ አገልጋይነቱ የመሰከረለት ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ከሁኔታዎችና ከፊቱ ካለው አስፈሪ ጉዳይ የተነሳ የመሰከረለትን መሲህ ለመጠራጠር ሲዳዳው ተገኘ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰዎች ሊንገዳገዱ ቢችሉም ወደ መሾመር የሚመልስ መሳሪያ በእጃቸው ስላለ አይወድቁም፡- 1. ጥያቄ ውስጥ መውደቅ “ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሼል ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና፦ የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው” ማቴ11፡2,3 ሰው የቱንም ያህል መንፈሳዊ ህይወቱ ከፍ ያለ ይሁን ይደክማል፣ ይፈተናል፡፡ ኤልያስ በእግዚአብሔር መንፈስ እጅግ ታላቅ ጀብዱ የሰራ፣ እሳት ከሰማይ ያወረደ ሰው በአንዲት ሴት ዛቻ ሸሽቶ በእግዚአብሔር ፊት በማማረር ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ ወደ ማለት ደርሶአል፡፡ በዚህም በመጥምቁ ዮሐንስ ህይወት የምናየው ይህንኑ እውነት ነው፡፡ ሾለ መሲሁ በብዙ ትህትናና በብዙ ማስረጃ የመሰከረ ሰው ዛሬ በልቡ ጥርጣሬ ገብቶ የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? ወደ ማለት ወረደ፡፡ ፈተና እይታን ያደበዝዛል ሁለት አሳብ መንገድን መንታ አድርጎ ይከፍላል፣ መጠራጠር ጽናት ያሳጣል፣ ሁለት አሳብ ለሰይጣን በር ይከፍታል፡፡ ያዕቆብ ሲናገር “… የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና” ያዕቆ1፡6 ይላል፡፡ ሰይጣን ያገኘንን ፈተና ተጠቅሞ አሳብ ወደ ልብ ያመጣል ትልቁ ዓላማውም የያዝነውንና ያቆመንን የእግዚአብሔር አሳብ በመጠራጠር እንድንጥል ነው፡፡ በአዳምና በሔዋን ያደረገው እንዲሁ ነበር በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተነገረውንና ፈጽሞ የማይለወጠውን ማስጠንቀቂያ እንዲጠራጠሩ ለማድረግ “… በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት” ዘፍ3፡1 ይህ ቃል ሔዋንን በር አስከፈታት፣ በፈተና ጊዜ ስሜታችንን የሚረብሹ አሳቦችን መቀበል አደጋው ይህ ነው፡፡ ዮሐንስ በወህኒ ተጥሎ የሞት ድምጽ ጆሮው ላይ እየጮኸ ባለበት በዚያ ሁኔታ መሲሁ መጥቶ እንዲያስፈታው ጠብቆ ይሆን? እንደሌሎቹ አይሁዳውያን መሲሁ ከሮማውያን ነጻ ያወጣናል በሚል አሳብ ተይዞ ያ እየሆነ ባለመሆኑ ጥርጣሬ ገብቶበት ይሆን? ምንም ይሁን ዮሐንስ በሁለት አሳብ ተጠልፎአል፡፡ ጥሩው ነገር ግን ራሱን ጌታን ጥያቄ መጠየቁ ነው፡፡ 2. መፍትሔው ቃሉ ነው “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤ ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው” ማቴ11፡4-6 ጌታ ኢየሱስ ወደ እርሱ ለመጡ የዮሐንስ መልዕክተኞች የሰጠው ምላሽ እነሱ ከሄዱ በኋላ ሾለ መጥምቁ ዮሐንስ ለልሹ ደቀመዛሙርት የነገራቸውን እጅግ አስገራሚ ምስክርነት አይደለም፡፡ ሾለ እርሱ በነብያቱ የተተነበየለት የሐንስ መሲሁን ፊት ለፊት በማየቱ ምክንያት ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ ብልጫን አግኝቶአል ምንም እንኳን ከሴት ከተወለዱት በሙሉ መካከል እርሱን የሚመስል ባይኖርም በክርስቶስ ያመነ አንድ ታናሽ ሰው ግን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ይበልጠዋል፡፡ ምክንያቱም አንድ አማኝ በክርስቶስ ደም በመታጠብ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነ፣ ከቀደመው ኪዳን በላይ ከፍ ባለ ኪዳን ውስጥ የተገኘ በመሆኑ ይመስላል፡፡ ጌታም ለመልዕክተኞቹ የመለሰላቸው በነቢያት ሾለ መሲሁ የተጻፈውንና እርሱም እያደረገ ያለውን ተግባራት ነው ኢሳ35፡6,7፡፡ በጥርጣሬ፣ በሁለት አሳብ፣ በተንገዳገደ እምነት ውስጥ ላለ ሰው መድሃኒቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው ምክንያቱም “… እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው” ሮሜ10፡17 ሲደክመን እምነታችን ሲንገዳገድብንና በሁለት አሳብ ልባችን ሲያዝብ ማርከሻው ቃሉ በመሆኑ ቃሉን በማንበብና ቃሉን በማሰላሰል ራሳችንን ስንጠምድ እምነታችን ይበረታ ይጀምራል፡፡ 3. ብርቱዎች ይጠበቃሉ "ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መንግሥተ ሰማይ በብዙ ትገፋለች፤ የሚያገኟትም ብርቱዎች ናቸው፤ ነቢያትም፣ የሙሴ ሕግም ሁሉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናግረዋልና" ማቴ11:12-13 በህግና በነቢያት ሲነገርለት የኖረው የእግዚአብሔር መንግሥትና ጽድቁ በቀኑ መጨረሻ በመሲሁ መምጣት ፍጻሜውን አግኝቶአል፡፡ ይህንኑ እውነት ነቢያትም፣ የሙሴ ሕግም ሁሉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናግረውበታል ነገር ግን እስራኤል እንደ አገር፣ እንደ ኪዳን ህዝብ መሲሁን እልል እያለች አልተቀበለችውም፡፡ በዘመኑ የነበሩ የኃይመኖት መሪዎች ገፉት፣ ተቃወሙት ምክንያቱም ኢየሱስ ባገለገለበት ዘመን የህጉ ቃል ተበርዞ በሽማግሌዎች ወግ ተሞልቶ ሾለ ነበር በመጽሐፍት በኩል መሲሁን ሊያስተውሉት አልቻሉም፡፡ ኢየሱስ ሲነግራቸው “እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ሾለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” ዮሐ5፡39 መሲሁ በመጽሐፍት ግልጥ ብሎ ተቀምጦ ሳለ እነርሱ ግን ስለበረዙት መሲሁን ሊያዩት አልቻሉም ጌታም “እናንተስ ሾለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሾለ ምን ትተላለፋላችሁ?” ማቴ15፡3 በማለት ተናግሮአቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ወደ ተሰበከው የእግዚአብሔር መንግሥት የሚገቡ የነዚህን መምህራን ዛቻ፣ ክልከላ፣ የቤተሰቡን ማግለል አልፎ የሄደ ሰው ብቻ ነው፡፡ ዛሬም ክርስቶስን አምኖ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት ፈጽሞ ቀላል አይደለም ነገር ግን ተቃውሞን ሁሉ እንቢ ማለት የቻሉ ብርቱዎች ብቻ ይገቡባታል፡፡ ሰይጣን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግቢያውን በር በአመጽና በተቃውሞ አጥቦት ስላለ በራሳቸው የጨከኑ ብቻ እያገኙት ይገኛሉ፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ማክሰኞ 28/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 42) የወንጌል መልዕክተኛው መመሪያ /06/ ማቴ10:1-42 16. በክርስቶስ አለማፈር "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ" ማቴ10:32,33 ሾለ ክርስቶስ መመስከር በአይሁድ ዘንድ እንደ ከሃዲ በሚያስቆጥርበት፣ ከማህበረሰቡ መገለልን በሚያስከትልበት፣ እንዲሁም ሮማውያን በቅኝ ግዛት በሚገዙባቸው አገሮች በሙሉ ቄሳር ጌታ ተብሎ ስለሚመለክ ኢየሱስ ጌታ ነው ብሎ መመስከር በሰይፍ በሚያስቀላበት በዚያ ዘመን ውስጥ ሾለ ክርስቶስ መመስከር ትልቅ እምነትና መስዋዕትነት ይጠይቅ ነበር፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ የሚለው፡፡ ነፍሱን ለማዳን ብሎ በሰው ፊት የሚክደው ግን ከክርስቶስ ጋር እድል ፈንታ የለውም፡፡ ድነት ልሹ የሚገኘው “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና” ሮሜ10፡9,10 እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ክርስቶስ በአባቱ ዘንድ ሰዎችን የሚክደው ወይም አላውቃችሁም የሚላቸው በሰዎች ፊት መገለልንና ዋጋ ለመክፈል በመፍራት ክርስቶስን በመካድ ምክንያት ነው እንጂ ሾለ እርሱ ለመመስከር በተለያየ ምክንያት መፍራትን አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ሾለ ክርስቶስ ለመመስከር ፍርሃትን ድል መንሳት ያስፈልገናል፡፡ ይህንንም ለማድረግ በመንፈስ ቅዱስ መታገዝ ያስፈልጋል ጳውሎስ ሲናገር “… በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፦ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ” 1ቆሮ12፡3 ስለዚህ አንድ የወንጌል መልዕክተኛ ሾለ ክርስቶስ መመስከር የሚያስከፍለውን ዋጋ ተምኖ መውጣት ያስፈልገዋል፡፡ 17. መስቀል መሸከም "መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ሾለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል" ማቴ10:38,39 የወንጌልን መልዕክት ሰምቶ ማመን ትላንትናም ዛሬም ያንን ሰው ከዓለም ይለየዋል ምክንያቱም ዓለም በሞላው በክፉ ተይዞአል 1ዮሐ5፡19፡፡ ማንም በክርስቶስ ሲያምን ዓለም ይጠላዋል ጌታ ኢየሱስ ሲናገር “ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ሾለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል” ዮሐ15፡19 አለ፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ “በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል” ማቴ10፡34-36 ያለው፡፡ የአንድ አማኝ ስደቱ የሚጀምረው ከቤተ ሰዎቹ ነው፡፡ ነገር ግን ምርጫው የዚያ ሰው ነው፡፡ ከእናቱ፣ ከአባቱ፣ ከእህት ከወንድሞቹ ይልቅ ክርስቶስን ምርጫው ካላደረገ ያ ሰው የክርስቶስ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ሰው በክርስቶስ ካመነ በኋላ የክርስቶስ ፍቅር ህይወቱን ስለሚገዛው ይህንን ፈተና ማለፍ ይችላል፡፡ ክርስትና እንደ ጌታ መስቀል የሚያሸክመው ገና በማለዳ ነው ስለዚህ ነው ኢየሱስ “መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም” ማቴ10፡38 ያለው፡፡ መስቀል መሸከም ማለት ሾለ ክርስቶስ የሚያስከፍለውን የትኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆንን የሚያሳይ ነው፡፡ ሐዋርያት ወንጌል ሲሰብኩ ሰዎች በክርስቶስ ሲያምኑ ስለሚያገኙት ህይወት ብቻ ሳይሆን ወንጌል ስለሚያስከፍለው ዋጋ ይናገሩ ነበር ሐዋ14፡22 ስለዚህ የወንጌል መልዕክተኛ እርሱም ሆነ ወደ ክርስቶስ የሚጠራቸው ሰዎች፣ የክርስቶስ የመሆናቸው ዋንኛ ምልክቱና መለያቸው መስቀል መሸከማቸው ነው፡፡ 18. ብድራት “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል” ማቴ10፡40 የወንጌል መልዕክተኛ እግሮቹ የሰላምና የበረከት ናቸው ሮሜ1015፡፡ በሄደበት ሁሉ ሰዎችን ከጨለማው ስልጣን በማላቀቅ ያንን ሰው ወደ ህይወት፣ ወደ ክብር ያመጣዋል፡፡ ማንም መልዕክተኛውን የሚቀበል የሚቀበለው መልዕክቱን ክርስቶስን ነው፣ ማንም ክርስቶስን ሲቀበል ያ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ያገኛል ምክንያቱም እግዚአብሔርን መገናኘት የሚፈልግ የትኛውም ሰው በክርስቶስ በኩል ካልሆነ በቀር በኃይማኖታዊ ወግና ስርዓት ሊያገኘው አይችልምና ነው፡፡ ክርስቶስ የሌለበት የትኛውም ኃይማኖት በሙሉ ወይም ክርስቶስን እየጠሩ ነገር ግን ክርስቶስን ከሌሎች አካላት ጋር የሚደባልቁ ሁሉ ሰዎችን የሚያከማቹት ለሲኦል ብቻ ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር አያስጠጉአቸውም። በዚሁ ክፍል ማቴ10፡32 ላይ ከነዚህ ታናናሾች የተባሉት የወንጌል መልዕክተኞቹን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የክርስቶስን ወንጌል ለማድረስ ምንም ሳይኖራቸው ከተማና ገጠር ሲንከራተቱ እነሱን በመቀበል የሚመግባቸው፣ ውሃ የሚያጠጣቸው ሁሉ ዋጋውን ያገኛል ዋጋውም ይዘውት የሄዱትን መልዕክት ስለሚቀበል የዘላለምን ህይወት ያገኛል፡፡ ጌታ በመጨረሻ በፍርድ ቀን ለበጎቹም ሆነ ለፍየሎቹ ያላቸው “ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል” ማቴ25፡45 ስለዚህ ለነዚህ ለታናናሾች መልካም ያደረጉ ወደ ዘላለም ህይወት፣ እነሱን ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑት ወደ ዘላለም ቅጣት ይሄዳሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ለድሃ በማብላት በማጠጣትና በማልበስ ወደ ገነት የሚገባ ይመስላቸዋል፡፡ መልካም ማድረግ መልካም ቢሆንም ጌታ እየተናገረ ያለው መልዕክተኞቹን ሾለ መቀበልና ለእነርሱ መልካም ስማድረግ ነው፡፡ ለእነሱ ማድረግ ለክርስቶስ ማድረግ በመሆኑ ያ ሰው ዋጋውን አያጣም፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሰኞ 27/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 41) የወንጌል መልዕክተኛው መመሪያ /05/ ማቴ10:1-42 13. አትፍሩ "እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና" ማቴ10:26 ምንም እንኳ የወንጌል መልዕክተኛ የተላከው እርሱን ወደሚጠሉና እድሉን ካገኙ ሊገሉት ወደ ኋላ ወደማይሉ ተኩላዎች መካከል ቢሆንም ጌታ ግን አትፍሩአቸው አለ፡፡ ምክንያቱም በሰው ያለውንና ሊሆን ያለውን የሚያውቅ ጌታ በመንፈሱ አማካኝነት ከእነርሱ ጋር ስላለ ነው፡፡ ፍርሃት የጠላት ትልቁ መሳሪያ ነው፣ ፍርሃትን ድል ያልነሳና በፍርሃት ላይ ያልነገሠ አማኝ ወንጌልን ለሌሎች ሊያደርስ አይችልም፡፡ ጎልያድ በእስራኤል ልጆች ፊት ቆሞ ሲያቅራራ ለአርባ ቀን ሊገጥመው የደፈረ አንድ ሰው ያልተገኘበት ትልቁ ሚስጥር ከንጉሡ ጀምሮ እስከ ሠራዊቱ ድረስ በሙሉ በፍርሃት በመያዛቸው ነው፡፡ ነገር ግን ዳዊት በመጣ ጊዜ የተናገረው የማንም ሰው ልብ አይውደቅ በሚል አምላኩን በመተማመን ባለ የድፍረት መንፈስ ተሞልቶ ሾለ ነበር ነው፡፡ ድፍረት ከሥጋ አቅም በላይ ትልቅ ኃይል ነው፣ ጎልያድ የወደቀው ጉልበት ባለው ሰው ሳይሆን ድፍረት ባለው ሰው ነው፡፡ ከነበረው እጅግ አስፈሪ ስደት የተነሳ በፍርሃት ተይዞ ለነበረው ለመጋቢው ጢሞቴዎስ፣ ጳውሎስ ሲያስጠነቅቀው “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ሾለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል” 2ጢሞ1፡7,8 አማኝ ሰዎችን ለጥፋት ከሚያነሳሳው ከሰይጣን መንፈስ በላይ ኃይልን ታጥቆአል፣ የሚጠሉትን ለመውደድ በሚያስችል ፍቅር ልቡ ተሞልቶአል እንዲሁም ኃጢአትን ድል ለመንሳት ራስን በመግዛት መንፈስ ተሞልቶአልና ነው፡፡ የተሰጠንን ካላወቅን ያልተሰጠን ፍርሃት ይነግሥብናል፡፡ 14. ለተሳካ አገልግሎት በጓዳ መቆየት "በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ" ማቴ10:27 የወንጌል መልዕክተኛ ለህዝብ የሚያደርሰው መልዕክት አለው፡፡ የጊዜውንና ትክክለኛውን መልዕክት ሊያገኝ የሚችለው ከጌታው ጋር ባለው የጓዳ ግኑኝነት ነው፡፡ በጓዳው ጊዜ የሚወስድ፣ ሚስጥርንም የሰማ ያንን የተቀበለውን በአደባባይ ወይም በብርሃን በብዙ ድፍረት ይሰብካል፡፡ ሐዋርያት አብዛኛዎቻቸው ምድራዊ እውቀት ያልነበራቸው፣ ያልተማሩ ሰዎች ነበሩ ነገር ግን ከጌታ የተማሩ ስለነበሩ እንዲሁም በተሰጣቸው አስተማሪ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ባገኙት ብርሃን በትምህርታቸው ኢየሩሳሌምን ብሎም ዓለምን አጥለቅልቀውታል፡፡ በጓዳ በጨለማ፣ በጆሮ በሹክሹክታ የተሰማው እውነት ሰዎችን እያዳነ፣ እያጽናና፣ የሰይጣንን ውሸት ከሰዎች አእምሮና ልብ ላይ እየገፈፈ ሰዎችን ለክርስቶስ በመማረክ ስራውን እየሰራ ይገኛል፡፡ የአዲስ ኪዳንን አንድ ሶስተኛውን መልዕክት የጻፈው ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ሁሉ አስደናቂ መገለጥ ከየት እንዳገኘው ሲናገር “ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም” ገላ1፡11,12 ብሎአል፡፡ ጌታ ሾለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር “ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና” ዮሐ16፡13,14 የጓዳው ብርሃን የአደባባዩን ጨለማ የመግፈፍ ኃይል አለው፡፡ 15. የትኛውም ነገር በጌታ ይታወቃል "ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል" ማቴ10:29,30 በጌታ የማይታወቅ፣ ከእርሱ ሊሰወር የሚችል አንዳች ሚስጥር የለም እርሱ ሁሉን ያውቃል፡፡ እርሱ ጊዜ፣ ቦታ፣ ሁኔታ አይወስነውም፡፡ እርሱ ምንም እንኳ የዩኒቨርሱ ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት ቢሆንም እጅግ አናሳ ስለሆኑት ሾለ ድንቢጦች ሁሉ ያውቃል፣ ከሰው ልሾ ላይ ያለ ቁጥሩ ሊታወቅ ፈጽሞ የማይቻለውን ጸጉር እንኳ በቁጥር ያውቀዋል፡፡ ታዲያ እንዴት የእርሱን ዘላለማዊ አሳብ ሊፈጽሙ በብዙ አደጋ ውስጥ ያሉ ልጆቹን ይረሳ ዘንድ ይችላል? እርሱ የማይዘሩ፣ የማያጭዱ በጎተራም እህል የማይከቱ የሰማይ ወፎችን ከመገበ ማቴ6፡26 እንዴት ባሪያዎቹን ይረሳል? ነገር ግን የተለያየ ፈተና ሲገጥመን፣ ተግዳሮት ሲያገኘን፣ ማዕበል እንደ ደቀ ማዛሙርቱ ሲያገላታን እግዚአብሔር የረሳን፣ ጌታም የተወን፣ ሾለ እኛ ግድ የማይለው ይመስለናል እርሱ ግን ሾለ እያንዳንዲቱ ጥቃቅን ስለምትባለው ነገር ሁሉ ሳይቀር ግድ ይለዋል፡፡ ስለዚህም ነው ጌታ ለባሪያዎቹ “እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ” ማቴ10፡31 ያለው፡፡ በአንድ ሰው በላ በሆኑ ማህበረሰብ መካከል ወንጌልን ለማድረስ በክርስቶስ ፍቅር የተሞሉ ባልና ሚስት ይገኛሉ፡፡ እነዚህንም ሰዎች እየቀረቡ ቋንቋቸውን እያጠኑ፣ ሲታመሙ በህክምናም እየረዱአቸው ከቆዩ በኋላ በአንድ ወቅት የዚያ ማህበረሰብ ሰዎች እነዚህን ሚሽነሪዎች ሊበሉአቸው ይመክራሉ ይህም ወሬ ለአገልጋዮቹ ይደርሳል እነሱም በፍርሃት አካባቢውን ጥለው ከመሄድ ይልቅ በራቸውን ዘግተው በጌታ ፊት በጾም በጸሎት ይጸልያሉ ነገር ግን ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት፣ ዓመታት አለፉ ነገር ግን ምንም አልሆኑም በመጨረሻም ከብዙ ጊዜ በኋላ ከዚህ ማህበረሰብ መካከል ብዙዎቹ በወንጌል ተማርከው ጌታን እያመለኩ ሳሉ ስለዚያ ወቅት ጉዳይ ይጠይቁአቸዋል፡፡ ሰዎቹም ያሰብነውን ለማድረግ በሌሊት ስንመጣ ነጫጭ ልብስ የለበሱ፣ መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ሁልጊዜ ቤታችሁን ከበው ይጠብቁ ሾለ ነበር እናንተን መንካት አልቻልንም በማለት መለሱ፡፡ ጌታ ሾለ እያንዳንዱ ነገራችን ያውቃል ደግሞም ይጠነቀቃል፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ውድ የዚህ ቻናል ተከታታዮች ሰላም ለናንተ ይሁን። ዓርብ 24/11/2018 እለት በተላለፈው መልዕክት የ2ኛ ቆሮንቶስ 12 የጳውሎስ የሰይጣን መውጊያ ተብሎ ስለተጠቀሰውና በአጭሩ የገጠመው የተቃዋሚዎች ማሰቃየት እንደሆነ ላብራራ ስለሞከርኩት ጉዳይ በተመለከተ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ስለዚህ ክፍል ያላቸውን አተያይ (view) አላካተትኩም ነገር ግን ቀጥታ የጻፍኩት የራሴን መረዳት ብቻ ነው። ይህንን ክፍል በተመለከተ አንዳንዶች የዓይን ህመም ሌሎችም በደፈናው በሽታ ነው ሲሉ፣ ሌሎችም የእግር በሽታ ነው፣ ሌሎችም ወባ ነው ይላሉ። ምንአልባት ይህ ባለማካተቴ ጥያቄ የሆነባችሁ ካላችሁ እንዲህ እንዳታዩት እወዳለሁ፡፡ ይህንን በተመለከተ ወገኖች ደውለው ስለጠየቁኝ ጉዳዩን በዚህ መልክ እንድታዩት ለማለት ነው፡፡ በማስተላልፋቸው መልዕክቶች ካለፉትም ሆነ ወደ ፊት ጥያቄ ቢኖራችሁ ስልኬ በየመልዕቶቹ ግርጌ ስላለ ልትደውሉልኝ ትችላላችሁ፡፡ ስለደወላችሁልኝ ወገኖች ጌታ ይባርካችሁ ለማለት እወዳለሁ ተባረኩልኝ፡፡

  • ዓርብ 24/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 40) የወንጌል መልዕክተኛው መመሪያ /04/ ማቴ10:1-42 10. የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ "በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፣ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና" ማቴ10:20 በግ ሆኖ በተኩላዎች መካከል መገኘት በራሱ በአደጋ ቀጠና ውስጥ መሆኑን ያሳያል፡፡ ነገር ግን የላኪው አብሮነትና ጥበቃ ከአገልጋዩ ጋር ስላለ በሁሉ አቅጣጫ እርሱን መታመንና መደገፍ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ጌታ ልሹ ለደቀ መዛሙርቱ ወንጌልን ወደ ዓለም ሁሉ ይዘው እንዲሄዱ ካዘዛቸው በኋላ “… እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ማቴ28፡20 በማለት ተስፋ ሰጥቶአል፡፡ እንዲሁ በእናንተ የሚኖረው የአባታችሁ መንፈስ የተባለው መንፈስ ቅዱስ አብሮ ስላለ የራስን አሳብ ሳይሆን የእርሱን መሪነት ከተከተልን እርሱ አብሮ ሰራተኛ፣ እርሱ ጠባቂ፣ እርሱ ጥበብ፣ እርሱ ኃይል፣ እርሱ ድፍረት ይሆናል፡፡ ወንጌል ያለ ተቃውሞ ፈጽሞ ወደ ሰዎች አይደርስም ምክንያቱም ጌታ የራሱ አገልጋዮች እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም የእርሱ ሰራተኞች አሉት ጳውሎስ እነዚህን ሰዎች የሰይጣን መውጊያ ብሎ ይጠራቸዋል 2ቆሮ12፡7፡፡ እርሱ በአህዛብ መካከል ድንቅና ተአምር እየሆነ ጎልቶ እንዳይታይና / exalted above measure/ በአማርኛ እንዳልታበይ እንደተባለ ብዙዎች በሚገለጠው ኀይል እየተማረኩ እንዳይድኑ ለማድረግ እነዚህ ሰዎች በጌታ አገልጋየች ላይ መከራንና እንግልትን በማድረስ ሊገቱአቸው ይወዳሉ፡፡ ጳውሎስም በወጣበት ሁሉ እያሰቃዩት ስለተቸገረ ከእርሱ እንዲለይ ጌታን ቢጠይቅም ይህንን ማስቀረት ስለማይቻል ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይሌ በድካምህ ይፈጽማልና እንዳለው ስደትና እንግልት ፈጽሞ ሊቆም የማይችል ጉዳይ ነው፡፡ አገልጋዩን የትም ቦታ /ሸንጎ/ፍርድ ቤት/ ቢያቆሙት እንኳ መንፈስ ቅዱስ በባሪያው አፍ መልስ ይሰጣል፡፡ ጳውሎስም ይህ ስለገባው “ስለዚህ ሾለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና” 2ቆሮ12፡10 በማለት እውነታውን ተቀብሎአል። 11. ከራስ ሰው መጠበቅ "ወንድምም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፣ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ሾለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል" ማቴ10:21,22 የወንጌል ተቃውሞ የመረረ እንደሆነ የምንረዳው የራስ የሥጋ ወንድም፣ እህት፣ እናት አባት፣ የቅርብ ወዳጆች ሁሉ የራሳቸውን ሰው ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ ምን ያህል በጭካኔና በጥላቻ እንደሚሞሉ ስናይ ነው፡፡ ጌታ ወደሰው ህይወት ሲመጣ በሚያምኑና በማያምኑ መካከል የመንፈስ መለያየት ይሆናል ስለዚህ ነው ጌታ “በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም” ማቴ10፡34 ያለው፡፡ የወንጌል ሰራተኛ እንዲህ መጠላቱ ሊደንቅ አይገባም ምክንያቱም ጌታ ልሹ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ሾለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል” ዮሐ15፡18,19 ማለቱን መዘንጋት አይገባም፡፡ ክርስቶስ ግን ከእናትና አባት፣ ከእህትና ከወንድም፣ ከሚስትና ከልጅ፣ ከወዳጅ ዘመድ ሁሉ ይበልጣል፡፡ እኛ ቤተሰብ ቀይረናል ቃሉን ሰምተው ጌታን በህይወታቸው የሚያነግሱ ሁሉ እነርሱ እናት አባት፣ ወንድም እህቶቻችን ናቸው፡፡ ጌታን እህት ወንድሞችህ ይፈልጉሃል ባሉት ጊዜ በዙሪያው ያሉትን እያየ እንዲህ አለ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው እኅቴም እናቴም አለ” ማር3፡35 12. ከክፉዎች መጠበቅ "በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም" ማቴ1023 ቅዱሳን ሁላችን ይህ ዓለም ቤታችን ስላይደ ልባችንን ጥለን መኖር አይገባንም ነገር ግን ወንጌልን ላልዳኑ ቤተሰቦቻችን፣ ለጓደኛ፣ ለዘመድ አዝማድ፣ ለአብሮ ሰታተኞቻችን በመናገር ልንጸና ይገባል ምክንያቱም “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፣ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን” ፊሊ3፡20 ስለዚህ በአንድ ስፍራ ሲያሳድዱን ወደ ሌላው ፈቀቅ እያልን መኖርን መምረጥ ይገባናል፡፡ የወንጌል አገልጋይ ሰዎች በአንድ ስፍራ ቢቃወሙት ወደ ሌላ ስፍራ በመሄድ ስራውን ሊሰራ ይገባል፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሐሙስ 23/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 39) የወንጌል መልዕክተኛው መመሪያ /03/ ማቴ10:1-42 7. የሰላም ሰው "በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ። ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ" ማቴ10:11,12 ወንጌል በቤት፣ ወንጌል በጎረቤት፣ ወንጌል በአካብቢ ብቻ ሳይሆን ወንጌል ወደ ራቁም ሰዎች ነውና እንግዳ በሆኑ ስፍራዎች የወንጌል አገልጋይ ሲገኝ፣ ወንጌልን የሚቃወሙ ብቻ ሳይሆን መልዕክቱን የሚሰሙ፣ እንኳን ደህና መጣህ የሚሉ የሰላም ሰዎችን ጌታ ያዘጋጃል፡፡ ይህ ሰው እስኪገኝ ማሰስ ያስፈልጋል፡፡ ባገኘነው ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ስፍራ ስራውን ለመስራት እንደ ወሳኝ ማእከል ይጠቀምበታል፡፡ ጳውሎስ በፊሊጲሲዩስ ወንጌልን በተናገረ ጊዜ የሰላም ሰው ሊዲያን አገኘ፡፡ ይህች ሴት ልብዋ የተነካ በመሆኑ “እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን” ሐዋ16፡15 እነጳውሎስም በዚህች ሴት ቤት በማረፍ የወንጌል ስራቸውን በመስራት በፊሊጲሲዩስ ቤተክርስቲያንን ለመትከል እንደ ዘር ሆነች፡፡ አገልጋይ እንዲህ ዓይነት በቅን ልብ በራቸውን ከፍተው፣ ያላቸውን ሲያካፍሉ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎችን ላለማሰናከል በብዙ ጥንቃቄ፣ በታማኝነት፣ በእግዚአብሔር ፍርሃት በመመላለስ አገልግሎታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ የራስን ጥቅም መፈለግ፣ የማይገባ ነገር ማድረግ ለወንጌል መሰናክል ከመሆኑም በላይ፣ የተከፈተውን የወንጌል በር እንዲዘጋ ምክንያት እንሆናለን፡፡ ይህንን ካደረግን ወደእዚያ ቤት ሰላም(ሻሎም) ይገባል፡፡ ሻሎም በሁሉ ነገር ሙላት፣ ፈውስ፣ በረከት፣ ደስታና መትረፍረፍ ነው፡፡ 8. ጥንቃቄ "እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ" ማቴ10:16 ይህ የጥበብ ቃል ነው፡፡ ወንጌል ደግሞ ጥበብ ይፈልጋል ምክንያቱም የተላክነው በተኩላዎች መካከል ነው ስለዚህ ነው ጌታ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ በማለት ያስጠነቀቀው፡፡ ሁለቱ ባህሪያት እንደየ ስፍራው ሚዛኑን ጠብቀው ሊገኙ ይገባል፡፡ እንደ እባብ ድምጽ ሳናሰማ፣ ሳንጫጫ፣ በጸጥታ፣ ውስጥ ውስጡን ስራችንን መስራት ያስፈልገናል፡፡ ወደ አንድ ስፍራ ስንገባ ፖስተር መለጠፍ፣ ኮት ከረባት በማድረግ የእግዚአብሔር ሰው ለመባል እዩኝ እዩኝ ማለት፣ ድምጽ ማጉያ ይዞ መዞር እንዲህ ዓይነቱ ተግባር በቀላሉ እንዲቆጡና ለተቃውሞ ሊያነሳሳቸው ይችላል፡፡ ይህ ጥበብ የጎደለውና ያገኘናቸውን የሰላም ሰዎች አላስፈላጊ ዋጋ እንዲከፍሉ፣ ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ የሚያደርግ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ድርጊቶች ችግር የማይፈጥሩባቸው ቦታዎች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን አለጊዜው ተኩላዎች እንዲነሱ ከማድረጉም በላይ የተከልነው ችግኝ በእንጭጩ እንዲከስም ምክንያት ይሆናል፡፡ ሰዎችን ሁሉ አለማመን ያስፈልጋል ምክንያቱም ሰዎች በጌታ እስካልተነኩ ድረስ ተኩላዎች መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም ስለዚህም ብልህ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሌላው ባህርይ እንደ እርግብ የዋህ መሆን ሲሆን ይህ የእርግብ ብቻ ሳይሆን የአንድ በግ ባህሪ፣ የጌታም ባህርይ ነው፡፡ የዋህነት ለሰው ሁሉ ቀላል ሆኖ መገኘት፣ ሰዎችን ለመርዳት ፈቃደኛ መሆን፣ መልካሙን የክርስቶስን ባህርይ ተላብሶ በቅን ልብ የክርስቶስን መልዕክት እያካፈሉ ማገልገል፣ አግባብነት የሌላቸው ባህሪያትን ከህይወት ማራቅ ነው፡፡ 9. ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት "ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ" ማቴ10:17 ጳውሎስ ለፊሊጲሲዩስ ሰዎች ሲናገር “በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ ሾለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ሾለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም” ፊሊ1፡28,29 ወንጌል ተቃዋሚ አለው፡፡ ነገር ግን የወንጌል አገልጋይ የትኛውነንም ዋጋ ለመክፈል አስቀድሞ ራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ ከሰዎች መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ አልፈው ከመጡ መሸሽ ይህ ካልተሳካ ጌታን በመታመን እንገረፍ እንጂ ራስን ለመከላከል በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረስ፣ እኛ እራሳች አመጸኞች ሆነን መገኘት አይገባንም፡፡ እንበደል እንጂ እኛው ራሳችን በደልን አድራሽ ሆነን መገኘት አይገባንም፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ማክሰኞ 21/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 38) የወንጌል መልዕክተኛው መመሪያ /02/ ማቴ10:1-42 4. የመልዕክተኛው መልዕክት "ሄዳችሁም፡— ‘መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች፡’ ብላችሁ ስበኩ" ማቴ10:7 የወንጌል መልዕክተኛ ለአገልግሎት ከመውጣቱ በፊት መልዕክት ሊኖረው፣ የተላከበትን መልዕክት በሚገባ ለታዳሚዎቹ ማቅረብ የሚችል ሊሆን ይገባዋል። የቱንም ያህል የተቀባሁ ነኝ የሚል ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ ሳይረዳ ሲቀር ልሹ በጠላት ወጥመድ ውስጥ ሊወድቅ ሌሎችንም ሊያስት ይችላል። አጵሎስ የተባለ በጸጋ የተቀጣጠለ ሰው እየሰበከ ሳለ አቂላና ጵርስቅላ ወደ ቤት ወስደው በሚገባ የወንጌልን መልዕክትን አስተማሩት ሐዋ18፡26። ለወንጌል ቸኩሎ ከመውጣት በፊት ራስን ማስታጠቅ አትራፊ ያደርጋል። ጌታ የሚሰብኩትን ዋና አሳብ ለደቀ መዛሙርት ሲናገር መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች በማለት ሾለ መንግስቱ መምጣት እንዲሰብኩ ነግሮአቸዋል፡፡ መንግሥተ ሰማይና የእግዚአብሔር መንግሥት የሚሉት ቃላት በተለዋጭነት የሚነገር ቃል እንጂ ሁለቱም አንድ ናቸው። የዚህን መንግሥት መምጣት እንዲያበስሩ ልኮአቸዋል ምክንያቱም ይህ መንግሥት የፍቅሩ ልጅ መንግሥት ነው ማለትም የክርስቶስ መንግሥት ነው። መሲሁ የመጣው የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ሊያቆም እንጂ የእስራኤልን ምድራዊ መንግሥት ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ ለማውጣት ጦረኛና ሞገደኛ መሪ ሆኖ አልመጣም። እስራኤል መሲሁን ሳትቀበል የቀረችውም ለዚህ ነው። የመልዕክታችን ዋና ጭብጥ መንግሥቱ ሊሆን ስለሚገባ ጌታ ከትሳኤው በኋላም አጽንቶ የነገራቸውም ይህንኑ ነው ሐዋ1፡3 5. ኃይልን መግለጥ "ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ" ማቴ10:8 ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸው ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ ይህንን ለማድረግ አስቀድሞ እንዳየነው ጌታ ሥልጣንን ሰጥቶቸዋል ማቴ10፡1፡፡ ዛሬስ እያንዳንዱ አማኝ ይህ ሥልጣን የለውም? ወይስ የጸጋ ስጦታ ላለው አማኝ ብቻ የተሰጠ ነው? እንዲህ አይነቱ አስተሳሰብ ነው በኛ ያለውን የመንፈስ መለቀቅ የገደበው፡፡ ጆን ጂሌክ የተባለ አገልጋይ በፈውስ አገልግሎቱ እጅግ የታወቀ ሰው ነበር እጅግም ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ እየመጡ ፈውሳቸውን ይቀበሉ ነበር ይህ አገልጋይ ብዙ አገልጋዮችን አሰልጥኖ እየሄዱ ለሰዎች እንዲጸልዩና እንዲፈውሱ ይልካቸው ነበር ዋንኛው መርሁ የምትጸልይለት ሰው ሳይፈወስ እንዳትመለስ የሚል ነበር፡፡ እንደሚታወቀው ሾለ ፈውስና ተአምራት ብዙ አመለካከቶች አሉ በሐዋርያት ዘመን አብቅቶአል፣ ሰዎች ሁሉ ይፈወሱ ዘንድ የጌታ ፈቃድ አይደለም ወዘተ… የሚሉ፡፡ ክርስቶስ ግን በመስቀሉ ሾል ለኃጢያት ይቅርታ ብቻ ሳይሆን ማደሪያ ለሚሆነው ለሥጋም ፈውስን አዘጋጅቶአል መዝ103፡3፣ 1ጴጥ2፡24፣ ማቴ8፡16,17፣ ይሁን እንጂ ጌታ አጽንዖት የሰጠው በከንቱ የተቀበላችሁትን በከንቱ ስጡ የሚል ነው፡፡ ምንም እንኳ ለሰራተኛ ደሞዙ ቢገባውም ፈውስንና ተአምራትን በገንዘብ እየተደራደሩ በነጻ የተቀበሉትን ጸጋን መሸጥ ከቃሉ የራቀና እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ 6. አቅርቦቱ "ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፣ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና" ማቴ10፡10 አገልጋይ በላከውና ሁሉን በሚያዘጋጅ አምላክ ላይ ታምኖ መሰማራት ይገባዋል ፡፡ ነገር ግን ለሰራተኛው ወይም ለአገልጋዩ ለስጋው የሚያስፈልገውን ነገር ከእርሱ መንፈሳዊ ጥቅም ካገኙ መልካም ሰዎች ሊያገኝ ይገባዋል ገላ6:6፡፡ ስለዚህ ነው ጌታ በዚሁ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ታናናሽ ብሎ ለጠራቸው አገልጋዮቹ በራቸውን ከፍተው ለሚቀበሉአቸውና የሚያስፈልጋቸውን ለሚያዘጋጁላቸው ሰዎች ይህንን ተስፋ የሰጠው ““እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም” ማቴ10:40-42 “የነብይን ዋጋ” ወይም “የጻድቅን ዋጋ” ወይም “ዋጋውን አያጣም” የተባለው አገልጋዩ የሰበከላቸውን በመቀበላቸው፣ በክርስቶስ በማመን የዘላለም ህይወትንና ፈውስን ስለማግኘታቸው ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ተግባር በተለይ ወንጌል ባልደረሰባቸው ስፍራዎች ለአገልጋዩ ደመወዝ የሚከፍለው አካል በማይኖርበት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን አገልጋዩ የላከው አካል ካለ በጊዜአዊነት ካልሆነ በቀር የክርስቶስን መልእክት ላለማስነቀፍ አገልጋዩ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሰኞ 20/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 37) የወንጌል መልዕክተኛው መመሪያ /01/ ማቴ10:1-42 ጌታ ኢየሱስ “የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት” ብሎ ከተናገረ በኋላ በዚህ ክፍል እርሱ ልሹ የመረጣቸውንና ያሰለጠናቸውን አገልጋዮች እጅግ ሰፊ ወደ ሆነው የመከር ስራ፣ ያስተማራቸውንና በእርሱ አገልግሎት ያዩትን ሁሉ በተግባር ሊያውሉና እንዲለማመዱ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ጠርቶ ሲልክ፣ የወንጌል መልዕክተኛን መመሪያዎች በሰፊው ተዘርዝሮ ሲያሳያቸው እንመለከታለን፡፡ በዚህም አንድ መልዕክተኛ ሊከተላቸው የሚገቡ ውጤታማ የሆኑ መርሆዎችን በዚህ ክፍል እንመለከታለን፡፡ 1. መንፈሳዊ ሥልጣን "አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፣ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው" ማቴ10:1 ጌታ ደቀ መዛሙርቱን የላካቸው በሥልጣን አስታጥቆ ነው፡፡ ሥልጣን ማለት ኃይልን የመጠቀም መብት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ሼል ያለ ኃይል አይሆንም፣ ስለዚህም ነበር ጌታ ከትንሳኤው በኋላ ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ በማለት በጥብቅ ያዘዛቸው ሉቃ24፡49 ጳውሎስም እንዴት እንደተላከ ሲናገር “ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ሾለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ” 1ጢሞ1፡12 የወንጌል አገልግሎት በሰው ጥበብና በሆኑ ስርዓቶች ለማከናውን ከወደድን የምንፈጽመው ኃይማኖታዊ ተግባር ብቻ ይሆናል፡፡ የወንጌል መልዕክተኛ ሲላክ ብቻውን አይደለም የስላሴ አካል የሆነው መንፈስ ቅዱስ አብሮት አለ፡፡ ስለዚህ ይህንን ስንረዳ አጋንንቶችን ለማስወጣት፣ ደዌንና ህማምን ሁሉ ለመፈወስ እምነት ይኖረናል ምክንያቱም ከኛ ኃይል ወጥቶ ስራውን የሚሰራው በእምነት በመሆኑ ነው፡፡ ጌታ ሲናገር ያመኑትም በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ እጃቸውን በድውያን ላይ ይጭናሉ እነሱም ይፈወሳሉ በማለት የተናገረው ማር16፡17,18 ብዙ ሰዎች ኃይል የለኝም ይላሉ ነገር ግን ይህ ስህተት ነው፡፡ ሁላችንም መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶናል፣ በመንፈስ መሞላት ማለት ብዙ ኃይል ማግኘት ማለት ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በሙላት እኛን ሲቆጣጠር ማለት ነው፡፡ እርሱ ስብእና ያለው አካል እንጂ የሚፈስ ወይም የሚጎድል ዘይት አይደለም፡፡ አጋንንትን ማስወጣት ድውያንን መፈወስ ለተለዩ ሰዎች የተሰጠ ሳይሆን ለአማኝ ሁሉ የተሰጠ ነው፡፡ ጌታ አሥራ ሁለቱን ብቻ ሳይሆን ሰባውንም በላከ ጊዜ እነሱም ይህንኑ አድርገዋል፡፡ 2. በጌታ በስም የታወቀ መሆኑ "የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም" ማቴ10:2 የወንጌል ሰራተኛ በሰማይ አምላክ በስም የታወቀ ነው፡፡ እርሱ የእርሱ የሆኑትን በሙሉ በስም ያውቃቸዋል አንዳንድ ሰዎች ጌታ በስም ሲጠራቸው ይደነቃሉ ነገር ግን ስማችን በሰማይ መዝገብ የተጻፈ ነው፡፡ ጌታ የጠራቸውን ሰዎች ማንነት ስንመለከት ሰው ጌታን ይመን እንጂ አልችልም የሚል ቃል እንዳናሰማ የሚያደርገን ነው፡፡ እነዚህ ተራ አሳ አጥማጆች፣ ቀራጮች፣ ድሆችና ያልተማሩ ሰዎች ተጠርተው ታላላቅ ሾል ከሰሩ እኔም እሰራለሁ ብለን ልናምን ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከጌታ ከተቀበሉት ውጪ ከኛ የባሱ ደካሞች ነበሩ ምንም የተለየ ነገር አልነበራቸውም፡፡ ጳውሎስ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለምን እደጠራ ሲናገር “ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ” 1ቆሮ1፡26-30 ሁሉ ከእርሱ ብቻ ነው የሆነው፡፡ 3. የአገልግሎት ክልል "እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፣ እንዲህም አለ፡— “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፣ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤ ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ" ማቴ10:5,6 ጌታ ደቀ መዛሙርቱን ሲልክ ሄደው የሚያገለግሉበትን ስፍራ ከልሎ ነግሮአቸዋል ይህ አስፈላጊ ነገር ነው ጌታ የቱ ጋር ለማ እንደሚፈልገን በትክክል ማወቅ ይኖርብናል ይህ ሲሆን በዚያ ስፍራ እንነግሳለን፣ ስራችን ይሳካልናል፣ እንጠበቃለን ስለዚህ ነበር እነጳውሎስ ወዳልተላኩበት ስፍራ ሊሄዱ ሲሞክሩ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ይከለክላቸው የነበረው “በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም” ሐዋ16፡7 ይህ ለደቀ መዛሙርቱ መርህን ተከትሎ መስራትን እንዲማሩ የሚያደርጋቸው ሥርዓት ነበር፡፡ ይህ ወንጌል ለሰማርያን እንዲደርስ ስላልፈለገ ሳይሆን በነዚህ ስፍራዎች በራሳቸው ጊዜ ስለሚደረሱ ነው፡፡ ጌታ በመጨረሻ ሲልካቸው ግን በወንጌል ሰማርያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ዳርቻ ሁሉ እንደሚካለል ተናግሮአል “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ” ሐዋ1፡8 ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ዓርብ 17/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 36) የመንግሥት ወንጌል ማቴ9፡27-38 ወንጌል የእግዚአብሔር መንግሥት ብስራት፣ ምልካም ዜና ነው፡፡ ይህም ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈጸመውና ባገኘው ድል ላይ የተመሰረተ የጸጋ መልዕክት ነው፡፡ ማንም ይህንን እውነት በእምነት ሲቀበል የሚገባበት የፍቅሩ ልጅ መንግሥት ነው፡፡ ጳውሎስ ሲናገር “እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፣ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን” ቆላ1፡13,14 ይህ መንግሥት መንፈሳዊ ቢሆንም መልዕክቱ ህያው፣ በእምነት የሚቀበሉት ብቻ የሚገቡበት፣ በፍጻሜውም ሁሉን የሚገዛ ዘላለማዊ መንግሥት ነው፡፡ ይህ የመንግሥት ወንጌል በክርስቶስ እየታወጀ የተጀመረ አሁንም በቤተክርስቲያን በኩል ለዓለም ሁሉ እየተሰበከ የቀጠለ ድል አድራጊ መንግሥት ነው፡፡ ይህ የመንግሥት ወነወጌል፡- 1. የማዳን ኃይል “ኢየሱስም ከዚያ ሲያልፍ ሁለት ዕውሮች፦ የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረን ብለው እየጮሁ ተከተሉት። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፣ ኢየሱስም፦ ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፣ ጌታ ሆይ አሉት። በዚያን ጊዜ፦ እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ። ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ” ማቴ9፡27-30 ጳውሎስ እንደተናገረ “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፣ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና” 1ቆሮ1፡18 የእግዚአብሔር የመንግሥቱ ወንጌል የኃይል መልዕት የያዘ ሲሆን በእምነት ለተቀበሉ ሁሉ የሚፈውስ፣ ከእስራት የሚፈታ፣ የሰውን ህይወት የሚለውጥ መልዕክት ነው፡፡ ጌታ ከኢያይሮስ ቤት ከወጣ በኋላ ሁለት እውሮች በመሲሐዊ ስሙ በመጥራት የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን እያሉ እየጮኹ ተከተሉት፣ ጌታም እንደ መስፈርት የጠየቃቸው “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” የሚል ነበር ደጋግመን እንዳልነው እምነት ከዚህ መንፈሳዊ የመንግሥት ወንጌል ልንጠቀም የምንችልበት ብቸኛውና ወሳኙ የሰው ምላሽ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የውስጥም የውጪም ብርሃን የሌላቸው ዕውሮች ናቸው ነገር ግን በዚህ ዓለም ቀመር ፈጽሞ ሊሆን የማይችል የፈውስ ኃይል በእጅ መዳሰስ ብቻ ሃይሉ አገኛቸው፡፡ በእነዚህ ሰዎች ምስክርነትም ብዙ ህዝብ ሲሰበሰብ በዲዳ5መንፈስ የተያዘን ሰው ነጻ ስላወጣው ያ ሰው ተናገረ ይህንን አስደናቂ ኃይል ጥቂቶች ቢያደንቁም የኃይማኖት መሪ ነን ባዮች ግን በአጋንንት አለቃ ነው ይህ የሆነው በማለት ሊያቃልሉ ሞከሩ በዚህም እነዚህን ሰዎች ማን እንደሚዘውር ራሳቸው አጋለጡ፡፡ ዛሬ ይህንን ወንጌል የያዝን እኛ ቀዝቅዘን ወንጌሉን ኃይል አልባ ማድረግ የለብንም ምክንያቱም ሐዋርያት “ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና …” 1ተሰ1፡6 ነው ያሉት፡፡ 2. የእግዚአብሔር የርህራኄ መልዕክት “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፣ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር። ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፣ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው” ማቴ9፡35,36 ይህ ዓለም በክፉ የተያዘ በመሆኑ የሰው ልጆች በሙሉ እረኛ እንደሌላቸው በብዙ ነገር በልዩ ልዩ ደዌና በበሽታ፣ በጭንቀት፣ በክፉ እስራት ታሰረው፣ ሰላም እርቆአቸውና ተጥለው ጌታ አያቸውና አዘነላቸው ምክንያቱም እርሱ መልካም እረኛ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የርህራኄና የምህረት መንግሥት ነው፡፡ የሐይማኖት መሪዎች ግን እንዲህ ዓይነት ልብ የላቸውም ስለዚህም ከእነዚህ ምንደኛ እረኞች አንዳችም ነገር አያገኙም፡፡ ስለዚህ ነው በዘመናት ሁሉ ብዙ የወንጌል አገልጋዮች በዚህ የርህራኄና የምህረት ልብ ተሞልተው ትውልድን ሲያገለግሉ በክፉዎችና በተኩላዎች መስዋዕት እየሆኑ ያለፉት፡፡ ዛሬም ሊታወቅ የሚገባው ነገር አገልጋይ ነኝ ባዮች ነገር ግን በዚህ የርህራኄና የምህረት መንፈስ ያልተሞሉ ሁሉ ይህንን መንግሥት አይወክሉም ምክንያቱም የመንግሥት ወንጌል የምህረትና የርህራኄ ወንጌል በመሆኑ ነው፡፡ 3. የመከሩ ሰራተኞች “በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው” ማቴ9፡37,38 ይህ የወንጌል ሼል በዚህ ዓለም በአንድ በኢየሱስ ብቻ ለህዝብ ሁሉ ስለማይደርስ ጌታ ልሹ አስራ ሁለት ሐዋርያትን በቅርበት እያሰለጠነ የመከሩ ሰራተኞች ይሆኑ ዘንድ እያዘጋጃቸው ነው፡፡ ነገር ግን ሰራተኞች ይበዙ ዘንድ ጌታ ልሹ ለአማኝ ሁሉ የሰጠው የጸሎት አደራ “የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት” የሚል ነው፡፡ ዛሬ የወንጌል አገልጋዮች በሙላት እንዳይነሱ፣ ሰራተኞች ለዚህ ሾል ቀኝ እጃቸውን እንዳይሰጡ የከለከለ ነገር ቢኖር ለነዚህ ሰዎች የሚደረገው ጸሎት አናሳ እንዲሁም ለእንደነዚህ ዓይነት አገልጋዮች የሚደረገው ድጋፍ እጅግ የወረደና አላግባብ የሆነ ዋጋ እንዲከፍሉ መታሰቡ ነው፡፡ ወንጌልን ከሚያስተምርና ጸሐይና ቁር እየበላው ከሚሰብከው አገልጋይ ይልቅ በየጓዳው እውነትነቱና ውሸቱ የማይታወቅ ትንቢት ለሚናገረው የሚደረገው ነገር ልዩነቱ በመስፋቱ ነው፡፡ ለነፍሳት መዳን የሚተጋ የወንጌል አገልጋይ እንቁ ሰው ነው ለዚህ ሰው መጸለይ እርሱን ማገዝ የጌታን የቤት ሾል መወጣት ነው፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሐሙስ 16/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 35) የሚሰራ እምነት ማቴ9:18-26 “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ" ሉቃ4:18 ተብሎ በነብያት እንደተነገረለት ጌታ ኢየሱስ በርኅራሄና በፈውስ መንፈስ ተሞልቶ በህዝብ መካከል ሲመላለስ በወንጌላት እንደተተረከው ብዙዎች በእምነት ፈውሳቸውን ተቀብለዋል፡፡ ጌታም በእምነታቸው የበረቱትንና የተፈወሱትን ልክ ከአስራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም ይፈሳት የነበረችውነን ሴት “እምነትሽ አድኖሻል” እንዳላት እንደ ኢያኢሮስ ያሉትን፣ በእምነታቸው ላይ ፈተና የተደቀነባቸውን ደግሞ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ” እያለ በእምነታቸው እንዲጸኑ ሲናገር እናነባለን ምክንያቱም ያለ እምነት ይህንን የተትረፈረፈ የፈውስ ኃይል መገናኘት አይቻልምና ነው፡፡ የጌታ የፈውስ ኃይል ልዩነት ሳያደርግ ለሁሉ ቀርቦአል፣ ፈውስ ፍጹም ፈቃዱ የሆነ አገልግሎቱ ነው፡፡ የሚያገኙት ግን የታመኑት ብቻ ናቸው፡፡ እምነት ለፈውስ ካለን የጌታ ፈቃድ እውቀት ይመነጫል ምክንያቱም “እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው” ሮሜ10፡17 የተሳሳቱ አሳቦችና ትምህርቶች በሰው ልብ ጥርጣሬን ይሞላሉ፡፡ በዚህ ክፍል እምነት የሚሰራውን ታላቅ ነገር እንመለከታለን፡- 1. ብሩህ ነገር ይታየዋል "ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ፡— “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች” እያለ ሰገደለት" ማቴ9:18 ጌታ ሾለ ጾምና ጸሎት ተጠይቆ እየመለሰ ባለበት ሁኔታ አንድ መኮንን ወይም የምኩራብ አለቃ ሾለ ልጁ ጉዳይ ጌታን ሊለምን በጌታ እግር ሾር እየሰገደ ሲጠይቅ እናያለን፡፡ ይህ ሰው የነበረው እምነት እይታውን እንዴት እንደቀየረውና እምነትም እንዲህ እንደሆነ ያሳየናል፡፡ ይህ ሰው ከባባድና አስጨናቂ የሆኑ ነገሮች ገጥመውታል እርሱ ልሹ የምኩራብ አለቃ እንደመሆኑ በጌታ ፊት ቀርቦ መስገዱ የሚያስከትልበትን አደጋ፣ እንዲሁም ልጁ ከሞት ባልተናነሰ ሁኔታ ውስጥ መሆንዋ የዚህን ሰው ሁኔታ ጨለማ ሊያደርገው ይችላል ነገር ግን በእምነት የተሞላ በመሆኑ ጌታን “ልጄ አሁን ሞተች፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች” በእምነት ተስፋን ይናገራል፡፡ እውነተኛ እምነት ሽንፈት፣ ውድቀት፣ ሞት፣ ተስፋ መቁረጥ አይታየውም፣ ጨለምተኛ ሳይሆን ብሩህ ነገር ይታየዋል በህይወት ትኖራለች ይላል፡፡ ጌታን ከታመንን ልባችንን የሚገዛው፣ አንደበታችንን የሚሞላው እንዲህ ዓይነቱ መንፈስ ነው፡፡ 2. ጌታ ይከተለዋል "ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው" ማቴ9:19 እውነተኛ እምነት ጌታን ያስደስተዋል፣ እውነተኛ እምነት የጌታን እጅ ወደ ነገራችን ያንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህ የምኩራብ አለቃ እምነቱን በዚህ መልክ ከገለጠ በኋላ ጌታ ፈቅዶ ወደ ቤቱ ከእርሱ ጋር ጉዞ ጀመረ፡፡ ሁኔታዎች ፈጥነው ባይለወጡም እንኳ እምነት ካሳየንበት ቅጽበት ጀምሮ ጌታ ወደ ነገራችን እየመጣ ነው፡፡ በዚህ ሰው ህይወት እንደሆነው በመንገድ ላይ አንዲት ሴት ጣልቃ ገብታ ፈውስዋን ስትቀበል ጌታን ስላዘገየችው የዚህ ሰው ችግር እየከፋ ሄዶ ጉዳዩ ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ይመስላል ነገር ግን ጌታ ወደዚያ መሄዱን አልተወም፡፡ ጉዳያችን የዘገየ፣ ችግራችንም ያለቀለት ቢመስልም ጌታ ግን እየመጣ ነው፡፡ የነገሮች መዘግየት ጌታ እንደተወን ሳይሆን የሚያሳየው ይልቁንም እምነታችን ፈተናና ለመቋቋም እንዲችል ተጨማሪ ጊዜ ጌታ እየሰጠን መሆኑን ነው፡፡ 3. የተግባር ሰው ነው "እነሆም፥ ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ደም የሚፈስሳት ሴት በኋላው ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ በልብዋ፡— “ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ፡” ትል ነበረችና" ማቴ9:20,21 እምነት የተግባር ሰው ያደርጋል ምክንያቱም ያዕቆብ እንደተናገረ “ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው” ያዕቆ2፡26 እውነተኛ እምነት ራሱን በስራ ይገልጣል፡፡ በመካከል የገባችው ደም የሚፈሳት ሴት ለብዙ ዘመናት ባልተሳኩ በሙከራዎችና የገንዘብ ኪሳራ ልብዋ የዛለባት ሴት ብትሆንም የጌታን ሼል ከሰማችና በእምነት ከተሞላች በኋላ የልብ እምነትዋን በንግግርና በተግባር ገልጣዋለች፡፡ በአንደበትዋ ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ ትል ነበር እንዲሁም ቢያዩአት ሊወግሩአት በሚችሉ ሰዎች መካከል ደፍራ በመካከላቸው አልፋ የተናገረችውን አደረገችው፣ ቀሚሱን ነካች፡፡ እውነተኛና የሚሰራ እምነት ልባዊ ብቻ ሳይሆን ራሱን በንግግርና በተግባር ያሳያል 2ቆሮ4፡13 4. ፍርሃትን ያሸንፋል "ኢየሱስም ወደ መኰንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ፦ “ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ፈቀቅ በሉ፡” አላቸው። በጣምም ሳቁበት" ማቴ9:23,24 ኢያኢሮስ አሳቡን ሊያስለውጥ፣ ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ የሚያስችል ፈተና ገጥሞታል ጌታ ግን አለ!! ጌታ አሳቡን አለወጠም፡፡ ማርቆስ እንደተረከው ማር5፡35-43 ከቤቱ ሰዎች መጥተው መምህሩን አታድክመው ብላቴናይቱ ሞታለች ሲሉት ጌታ ፈጥኖ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ” በማለት ፍርሃትን ድል ይነሳ ዘንድ ተናገረው፡፡ የሚታየው፣ የሚሰማው ከባድ ሲሆን እምነትን ይፈታተናል፣ ፍርሃት ልብን ሊወር አድብቶ የኛን ምላሽ ይጠብቃል ነገር ግን እምነት ምርጫ ነውና ኢያኢሮስ የጌታን “እመን ብቻ” ያለውን ቃል መረጠ ልቡም ተጠበቀ፡፡ አንደበታች ሽንፈት እያወራ ሰዎች የሚሰጡትን አስተያየት እየተቀበልን፣ በሚታየው ነገር እየፈራን በእምነት ልንዘልቅ አንችልም፡፡ እምነት ፍርሃትን ድል ይነሳል፡፡ 5. ውጤት ያያል "ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች። ያም ዝና ወደዚያ አገር ሁሉ ወጣ" ማቴ9:25,26 እውነተኛ እምነት ውጤት ያመጣል፡፡ ነገሩ ከባድ፣ የዘገየ፣ ብዙ ፈተና ያንዣበበ ሊሆን ቢችልም እምነት ውጤት አለው ብላቴናይቱ ከሞት ተነሳች፡፡ ባለማመን የሚንጫጩና የሚያለቅሱ እንዲሁም በእምነት ላይ የሚስቁ ሰዎች ባሉበት እምነት ለነዚህ ሁሉ ጆሮ የለውም እለዚህ ውጤት ያያል፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ረብዕ 15/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 35) ሁለቱ በአንድ ላይ አይጣጣሙም ማቴ9፡14-17 መጥምቁ ዮሐንስ ከክርስቶስ በፊት የተላከ መንገድ ጠራጊና የህዝቡን ልብ ለመሲሁ በንስሃ የሚያዘጋጅ አገልጋይ ነበር፡፡ እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ በማለት ለተላከበት አገልግሎት ታማኝ ሆኖ እኔ መሲሁ አይደለሁም ነገር ግን ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጫውን ልሸከም የማይገባኝ እርሱ ከኔ ይልቅ ይበረታል እያለ ሊመጣ ያለው መሲሁ እርሱ እንደሆነ በመጠቆም መስክሮአል፡፡ በአገልግሎቱም ለደቀመዛሙርቱ የተለያዩ ነገሮችን ያስተማረ ሲሆን ከነዚህ መካከልም ሾለ ጾምና ጸሎት የሚጠቀስ ነው ሉቃ11፡1,2 ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብይ እንደመሆኑ ትምህርቶቹ በሙሉ ከአሮጌው ኪዳን የተቀዱና በተለያዩ ጊዜአት ፈሪሳውያን ከጨማመሩአቸው ከአባቶች ወግም ጋር የተቀላቀሉ ነበሩ፡፡ የእርሱ ደቀመዛሙርትም ጾምን በተመለከተ የእነርሱ ትምህርት ከፈሪሳውያን ጋር ሲስማማ ነገር ግን ከጌታ ደቀመዛሙርት ጋር ሲለያይ ሲያዩ ጥያቄ ሆኖባቸው ወደ ጌታ በመምጣት ጥያቄ ጠየቁ ጌታም በቅንነት ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሹን ሲሰጥ የመልሱ ጭብጥ “አዲሱ ከአሮጌው ይለያል” የሚል ነበር፡፡ ይህንንም በዚሁ ክፍል በምሳሌ ያስረዳቸውን እንመለከታለን፡- 1. የልማድ ጥያቄ “በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው፦ እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ሾለ ምንድር ነው? አሉት” ማቴ9፡14 እውነትን ለማወቅ፣ በእነሱና በፈሪሳውያን እንዲሁም በጌታ ደቀመዛሙርት መካከል ያዩት ክፍተት ጥያቄ ሆኖባቸው ስላለ እውነታውን ለማወቅ በቅንነት "እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ሾለ ምንድር ነው? በማለት ጠየቁ። በሙሴ ህግ ህዝቡ ሁሉ የሚገደዱበት በዓመት አንድ ጊዜ ለአንድ ቀን የሚጾሙበት የስርየት ቀን አለ ዘሌ16፡29,31 ከዚያ ውጪ ከሕጉ አንጻር ሌሎች ጾሞች ሁሉ በፈቃደኝነት የሚደረጉ ነበሩ። ስለዚህ በማቴ9፡14 ላይ የተጠቀሰው ጾም በሕጉ የታዘዘው አይደለም፤ ይልቅስ ሕጉ ላይ ከተጨመሩት በርካታ «የሽማግሌዎች ወጎች» አንዱ ነበር ማር7፡3 ጌታ ከቃሉ ውጪ ለሆኑ ለሰዎች ወግና ትምህርት ምንም ስፍራ አልነበረውም ስለዚህም ነበር “… እናንተስ ሾለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሾለ ምን ትተላለፋላችሁ?” ማቴ15፡3 በማለት ጠንካራ ጥያቄ የጠየቀው፡፡ ዛሬም በቃሉ የሌለ ብዙ ልማዶች በየቤተክርስቲያኑ አሉ እንዲህ አይነት ነገሮች ቃሉን ከመበረዝ አልፈው ህዝብን ከመንገድ ያስታሉ፡፡ 2. ሙሽራው አለ “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ” ማቴ9፡15 አምላክ ስጋ ለብሶ በህዝቡ መካከል እየተመላለሰ ቢሆንም ሊያዩትና ሊቀበሉት አልቻሉም፡፡ ወደ እርሱ የሚጸለይለት እርሱ በመካከላቸው ሆኖ እያለ እነርሱ ሾለ ጸሎትና ጾም ከእርሱ ጋር ይናገራሉ፡፡ ይህንንም እውነታ ይረዱ ዘንድ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነሱ ጋር እያለ እንዴት ሊያዝኑና ሊያለቅሱ ይችላሉ? በማለት ጠየቀ ይልቁንም በሙሽራው መገኘት ሊደሰቱ ሊበሉ ሊጠጡ ይገባቸዋል ነገር ግን ሙሽራው ከእነሱ በሚወሰድበት ወቅት ይመጣል ያን ጊዜ ይጦማሉ አለ፡፡ ሙሽራው እርሱ ልሹ ሲሆን ሚዜዎቹ የጌታ ደቀመዛሙርት ናቸው፡፡ የሚወሰድበትም ጊዜ ከመስቀል ሞት በኋላ ከእነርሱ የሚለይበት ወቅት ነው፡፡ ጾም ጸሎት በልማድና እንደ ስርዓት የሚደረግ ሳይሆን ለአንድ ዓላማ የሚደረግ መንፈሳዊ አገልግሎት ነው፡፡ ደቀመዛሙርት ጌታ ካረገ በኋላ በጾምና በጸሎት እየተጉ መንፈስ ቅዱስን ጠብቀዋል እንዲሁም በወንጌል ምክንያት ፈተናዎችና ስደቶች ሲገጥሙአቸው ጾመው ጸልየዋል እንጂ በልማድ ቀን ቀጥረው አልጸለዩም፡፡ ክርስትና ከጌታ ጋር ባለ ግኑኝነት በመንፈስ የሚደረግ ህብረት እንጂ እንደ ባህልና ወግ ቀን ተቀጥሮ የሚደረግ ግዴታ የለውም፡፡ 3. አይስማሙም “በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ” ማቴ9፡16,17 ጌታ በብሉይ ኪዳን የነበረውን የህግ አገልግሎት በዋናነት ወደ ፍጻሜ ሊያመጣ ከህግ በታች ሆኖ በመኖር ያለ ነቀፋ ፈጽሞታል፡፡ እርሱ ልሹ “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመምር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመምር አልመጣሁም” ማቴ5፡17 በማለት እርሱ ዋንኛ ስራው ህጉን ወደ ፍጻሜ ማምጣት እንደሆነ ተናገረ እንጂ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ህግን መፈጸም እንደሚገባቸው አንድም ስፍራ አላስተማረም ምክንያቱም ህጉ እንደ ሞግዚት ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ አገልግሎት ነበረው እንጂ የአዲሱ ኪዳን መመሪያ አልነበረም “… ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ” ዮሐ1፡16,17 ስለዚህ ሁለቱን መቀላቀል እጅግ ትልቅ የህይወት ቀውስ እንደሚያመጣ በአቁማዳውና በወይኑ ምሳሌ አስረዳ፡፡ አሮጌ የተቀደደ ልብስ አዲስ እራፊ ጨርቅ ቢጥፉበት፣ በታጠበ ጊዜ አዲሱ አሮጌውን ይበልጥ እንዲቀደድ ያደርገዋል ስለዚህ ሁለቱ ሊዋሃዱና ጥቅም ሊሰጡ አይችሉም እንዲሁም በአሮጌ የመለጠጥ አቅሙን በጨረሰ አቁማዳ ገና እየፈላ ያለን የወይን ጠጅ ቢጨምሩበት አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል ስለዚህ ከብክነት ውጪ ጥቅም አይኖረውም፡፡ ህግ ለጻድቃን አልተሰራም 1ጢሞ1፡11 ጽድቅ የተገኘው በሰው ሾል ሳይሆን በክርስቶስ ሾል ብቻ ነው፡፡ ኑሮአችንም በመንፈስ እንጂ ህግን በመፈጸም ሊሆን አይችልም፡፡ ህጉ የኩነኔና የሞት አገልግሎት ነው፣ አዲሱ አገልግሎት ግን በመንፈስ የሆነ የጽድቅና የህይወት አገልግሎት ነው 2ቆሮ3፡7-11 ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ማክሰኞ 14/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 34) ምህረትን እዳለሁ መስዋዕትን አይደለም ማቴ9፡9-13 ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ኃጢአተኞችን ሊያድን ነው ምክንያቱም ጳውሎስ እንዳለ “… ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል” ሮሜ3፡22,23 ስለዚህ በመልካም በስራው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ የሆነ አንድም የለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች በኃይማኖት እሳቤና በራሳቸው መስፈርት ራሳቸውን ጻድቅ በማድረግ ሌሎችን ይኮንናሉ፣ ቀራጮችና ኃጢአተኞች በማለት ይፈርጃሉ፡፡ ዛሬም ይኸው ዝንባሌ እየተንጸባረቀ በክርስቶስ ዳንን ብለው በሚያስቡ መካከል እንኳን በሌሎች ድካም በመፍረድ፣ ርህራኄ ባለማሳየት ሰዎች የሚያገሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ጽድቅ በክርስቶስ ሼል ከማመን ውጪ በስራ አይገኝም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ራሳቸውን በግብዝነት ጻድቅ ወደሚያደርጉ ሳይሆን ኃጢአተኞች መሆናቸውን ወደ ተረዱ በመሄድ እነደነዚህ ያሉ ሰዎችን ያገለግላል እርሱ ልሹ ለሚቃወሙት “ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው” ሉቃ5፡32 እግዚአብሔር የምህረት አምላክ በመሆኑ የወደቁትንና የሳቱትንም እንኳ በማንሳት ያቆማቸዋል፡፡ በዚህ ክፍልም በክርስቶስ ጥሪና ለኃጢአተኞች በሚያሳየው ርህራኄ ስለሚቃወሙና እርሱ ስላለው አቋም እንመለከታለን፡- 1. ይጠራል “ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው” ማቴ9፡8 ቀራጭ የሚባሉት እስራኤልን በቅኝ ግዛትነት ከሚያስተዳድሩአት ሮማውያን ባለሥልጣናት ጋር በመተባበር ህዝቡን ቀረጥ ለሚያስከፍሉ አይሁዳውያን የተሰጠ ስም ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች እንደ ኃጢአተኛና ከሃዲ ተደርገው በህዝቡ ዘንድ ይቆጠራሉ፡፡ ማቴዎስ ጌታ ኢየሱስ ከጠራቸው ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል አንዱ ሲሆን እርሱም በስራው ቀራጭ ነበር፡፡ ክርስቶስ በምድር የተመላለሰው የእግዚአብሔር አብን ፈቃድ በማድረግ እንጂ በሰዎች ባህልና አመለካከት ባለመሆኑ ብዙ ተቃውሞና ነቀፋ ይሰነዝሩበት ነበር፡፡ ማቴዎስ በቀረጥ ስራው ላይ እያለ ጌታ ኢየሱስ ተከተለኝ በማለት ጥሪ አደረገለት፡፡ ቀራጭነት በሌሎች ዘንድ ቢያስነቅፍም ብዙ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ ያንን ጥቅም ጥሎ ክርስቶስን መከተል ምን ያህል የልብ መነካት እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ በአንዲት የመለኮት ቃል ልቡ ተማርኮ ማቴዎስ ኢየሱስን ለመከተል ሁሉን ትቶ ተነሳ፡፡ ሰዎች የኮነኑት፣ እንደ ኃጢአተኛ የቆጠሩት ማቴዎስ ግን ለዚህ ክቡር ጥሪ ምላሽ በመስጠቱ ከአራቱ ወንጌላት አንዱን የጻፈና ክርስቶስን በማገልገል ሾለ ክርስቶስ የተሰዋ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ለመሆን በቅቶአል፡፡ ጳውሎስ ግን እንዲህ ይላል “ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ” 1ቆሮ1፡26-28 2. አብሮ ይቀመጣል “በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፣ እነሆ፣ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ” ማቴ9፡10 የተነካ ሰው ባየውና በቀመሰው እጅግ በመደነቅ ሌሎችም ያንን ይቀምሱ ዘንድ ከፍተኛ ናፍቆት አለው፡፡ እያንዳንዱ አማኝ በዳነ ማግስት ለብዙዎች ያገኘውን መልካም ነገር በማካፈል ተወዳዳሪ የለውም፡፡ ማቴዎስ ጥሪውን እንደተቀበለ ለጌታ ያለውን ክብር ለማሳየት እንዲሁም በጥሪው ተደንቆ መሳዮቹም ይህንኑ ይካፈሉ ዘንድ ሌሎች ቀራጮችንና በማህበረሰቡ ኃጢአተኞች ተብለው የተፈረጁትን ሁሉ ሰብስቦ ድግስ በመደገስ ጌታ ኢየሱስን በቤቱ ጋበዘ፡፡ ጌታም እንዲህ አይነቱን ግብዣ በብዙ ደስታ በመቀበል ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሊበላ ተቀመጠ፡፡ ኃይማኖት ግብዝ እንጂ ሰዎችን የምንረዳ እንድንሆን አያደርገንም ሰው በምንም ዓይነት በደል ቢገኝ እኛ መንፈሳዊ እንደሆንን የምናስብ ሰዎች በየዋህት መንፈስ ልናቀናው ይገባል እንጂ በሩቅ ቆመን ፈራጅ መሆን አይገባንም ገላ6፡1፡፡ ጨካኝ መሆናችንን ከምናሳይበት አንዱ ነገር ቤተክርስቲያን ዲስፕሊን አረኳቸው ለምትላቸው ሰዎች የሚኖረን እይታ ነው፡፡ ለዚህ ሰው ጌታ ሌላ እድል የለውም? ጌታ ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ምህረቱን ዘጋ? እረ በፍጹም ያ ሰው የመመለስ አዝማሚያ እስካሳየ ድረስ በምህረት የቆምን እኛ ልንራራለት ይገባል፡፡ ዛሬም በግብዛችን ኃጢአተኞች ሊታደሙ የክርስቶስን ፍቅር ይሰሙ ዘንድ እንደ ማቴዎስ እድል ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ 3. መድኃኒት ለበሽተኛ ነው “ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ነገር ግን ሄዳችሁ፦ ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው” ማቴ9፡12,13 ጌታ በድርጊቱ የአይሁድ መምህራን ቢነቅፉትም እርሱ ግን ምን ያህል ድርጊታቸው ከቃሉ ያፈነገጠና ትክክል እንዳይደለ ከሆሴዕ 6፡7 ከመጽሐፍት ጠቅሶ አፋቸውን ይዘጋ ነበር፡፡ ስለዚህ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም በማለት የእግዚአብሔርን አሳብ ይነግራቸዋል፡፡ እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ፣ ሃብትና እውቀት የሌሎችን ጉድለት እንድንድንሞላ እንጂ ካላቸውና ከሞላላቸው ጋር ብቻ ክብርን ልናሰጣጥበት አይደለም ጌታ ለፈሪሳውያን ሲናገር “እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ …” ዮሐ5፡44 አላቸው፡፡ ከተመሳሳያችን ጋር ብቻ ሳይሆን የኛንም እርዳታ ለሚፈጉ ሰዎች ስፍራ ይኖረን ዘንድ ጳውሎስ ሲናገር “ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ” ሮሜ12፡15 ማለቱን መረሳት የለበትም፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190

  • ሐሙስ 09/11/18 የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 32) ክፉ መናፍስትን የሚያበረክክ ኃይል ማቴ8፡28-34 በሥልጣን ወጀቡን አልፈው ከመጡ በኋላ ፊት ለፊት በሰዎች ወይም በነገሮች በስተጀርባ ሆኖ ከሚሰራው ከዲያቢሎስ ጋር በዚህ ክፍል በተጠቀሱት ሁለት ሰዎች ውስጥ ሆኖ ጌታንና ደቀመዛሙርቱ ተገናኙት፡፡ ይህ መንፈስ በአካባቢው የሚያልፉትን ሁሉ የሚያጠቃ በሰው ጉልበት ማንም ሊቆጣጠረውና ሊያሸንፈው የማይችለው ክፉ መንፈስ ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች በመቃብር ስፍራ ወስዶ ራሳቸውን እንዲጎዱ በማድረግ እጅግ ያሰቃያቸዋል፡፡ ማርቆስ አንዱ ላይ ብቻ ሲያተኩር ማቴዎስ ግን ሁለቱም ሰዎች ላይ አተኩሮአል፡፡ ኢየሱስ የመጣው የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን ያን የቀደመውን እባብ ራሱን ሊቀጠቅጥ ወይም ስራውን ሊያፈርስ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ሊረዳው የሚገባ ነገር ቢኖር ከሁሉም ክፉ ነገሮች በስተጀርባ፣ ከበሽታ፣ ከጦርነት፣ ከድህነት፣ ከአመጽና ከክፋትም ሁሉ ጀርባ ያለው እርሱ ሰይጣን ስለዚህ ጳውሎስ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” ኤፌ6፡12 ሰው ያላወቀው እውነተኛ ጠላቱ ይህ ዲያቢሎስ መሆኑን ነው፡- 1. የክርስቶስ ሥልጣን “እነሆም፦ ኢየሱስ ሆይ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልትሣቅየን ወደዚህ መጣህን? እያሉ ጮኹ” ማቴ8፡29 መናፍስቱ ልክ ኢየሱስን ሲያዩ ማርቆስ እንደዘገበው ሮጠው ሰገዱለት ይህ ስግደት የአክብሮት ሳይሆን የፍርሃት ነው፡፡ መነፍስት ክርስቶስን ስለሚያውቁት ተጨንቀው እየጮኹ እኛ ከአንተ ጋር ምን አለን ጊዜአችን ሳይደርስ ልታሰቃየን መጣህብን አሉ፡፡ ሰይጣን እንደተፈረደበት ጊዜም እንደተቀጠረለት ያውቃል፡፡ ስለዚህ አለጊዜው ወደ ጥልቁ እንዳይጥላቸው በመፍራት ጮኹ፡፡ መናፍስት በብቸኝነት ከክርስቶስ ውጪ የሚፈሩት፣ እነርሱንም ድል የነሳ ማንም የለም፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስንና የእርሱ ተከታዮችን አጥብቀው የሚጠሉት ምክንያቱም ጌታ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ “እነሆ፣ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፣ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፣ የሚጐዳችሁም ምንም የለም” ሉቃ10፡19 በማለት በመናፍስቱ ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቶአቸዋል፡፡ ሰይጣን ተሸንፎአል፣ በመስቀሉም ላይ አለቅነቱና ሥልጣኑን ተቀምቶ ተራ ተደርጎአል፣ የእርሱ ብቸኛ ማስፈራሪያ ሽንገላና ውሸት ብቻ ነው፡፡ ጳውሎስ “በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን” 2ቆሮ2፡14 እንዳለ ዛሬ በክርስቶስ ያለን ሁላችን መመላለስ የሚገባን ክርስቶስ ድል በነሳበት በዚያ መንፈስ ሊሆን ይገባል፡፡ የክርስቶስ ድል ድላችን ነው፡፡ 2. የመናፍስት እውንነት “ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር። አጋንንቱም፦ ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን ብለው ለመኑት። ሂዱ አላቸው። እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም፥ የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ በውኃም ውስጥ ሞቱ” ማቴ8፡30-32 መናፍስቱ ከሰዎቹ ሊያስወጣቸው እንደሆነ ስለተረዱ በአካባቢው ወደ ነበሩ እሪያዎች እንዲሰዳቸው ለመኑት ይህ ለምን ለመኑ ደግሞም ኢየሱስ ለምን ፈቀደላቸው የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም፡፡ በመጀመሪያ ጌታ ወደ ጥልቁ ካዘዛቸው ጊዜው ሳይደርስ ወደ ስቃይ ይሄዳሉ፣ ሁለተኛ መናፍስቱ ያለ ሰው ወይም ያለ እንሰሳ አካል ሲሆኑ እጅግ ይሰቃያሉ ጌታ ሲናገር “ርኵስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍትን እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ ባያገኝም፦ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል” ሉቃ11፡24 ስለዚህ ነው ጌታን ወደ እሪያዎቹ እንዲልካቸው የጠየቁት፡፡ እሪያዎቹ ቢሞቱም እንኳ ወደ ጥልቁ ስላልተላኩ ወደ ሌሎች ለመግባት እድል ይኖራቸዋል፡፡ ጌታ ደግሞ የፈቀደላቸው መናፍስት ዝም ብሎ አእምሮ የፈጠራቸው ቅዠት ሳይሆኑ ህያው የሆኑ መንፈሳዊ አካሎች መሆናቸውን ለማሳየት ነው ወደ እሪያዎቹ እንዲገቡ የፈቀደላቸው፡፡ በሌላ ምክንያት ደግሞ የሰው ልጅ በህጉ እርኩስ ከተባለው ከእሪያ በላይ ከፍ ያለ እንደሆነ ለማሳየት ነው የፈቀደላቸው፡፡ 3. የሰዎች ምርጫ “እረኞችም ሸሹ፣ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም በአደሩባቸው የሆነውን አወሩ። እነሆም፣ ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፥ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት” ማቴ8፡33,34 ሰዎቹ ለብዙ ዘመናት ሲያሰቃዩቸው ከነበሩት መናፍስት ነጻ ወጥተውና ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ቁጭ አሉ፣ ልብስም ለበሱ፡፡ ይህ በመሆኑ ሰዎች በዚህ ደስ ሊላቸው ሲገባ የከተማው ሰዎች በእረኞቹ መልዕክት ወደ ክርስቶስ መጥተው ከአገራችን ሂድልን አንፈልግህም አሉት፡፡ ይህንን ያሉት ሰዎች ከሰው ይልቅ ለጥቅምና ለሃብት ትልቅ ስፍራ ስለሚሰጡ ነው፡፡ በአንድ ወቅት እነ ጳውሎስ አንዲት እየጠነቆለች ለጌቶችዋ ትርፍ ታመጣ ከነበረች ሴት ላይ መናፍስቱን በማስወጣታቸው ህዝብ ተሰብስቦ ወገራቸው ሐዋ16፡19 ይህ ለዚያች ከተማ ትልቅ እረፍትና ጥቅም የነበረ ቢሆንም ሰዎች ግን በክርስቶስ ከሚያገኙት መንፈሳዊ አርነት ይልቅ ጊዜአዊ ጥቅም በልጦባቸው በንዴት ጌታን ከአካባቢያቸው እንዲሄድ ምርጫቸው ሆነ፡፡ ጸጋ ይብዛላችሁ Telegram:- @mentesnotkebede2020 👍 Join በማድረግ እየተቀላቀሉን ሌሎችም እንዲሳተፉ ሟር በማድረግ ይሳተፉ Email:- mentesnot_kebede@yahoo.com ስልክ:- 0911693190