tgindex

ፀዊረ መስቀል

описание

የየእለቱ የወንጌል ክፍል የየበዓላቱ ሥርዓተ ዋዜማ ፤ ሥርዓተ ማኅሌት ፤ #ወረብ፤ መዝሙራት እና ምስባክ በጽሑፍ እና በድምጽ የሚያኝበት............ ቻናል ነው ሼር እያደረጉ ሃይማኖታዊ ድርሻዎን ይወጡ። https://t.me/tsewire @tsewire DM @faya6

19 712
подписчиков
Охват к подписчикам
0,8%
ERR
Реакции к просмотрам
1,12%
51 на 31 постов
Пересылки к просмотрам
0,86%
39
Постов в день
2,6
всего 28

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 14 авг.без подписи4,90%
  • 12 авг.[ነሐሴ 7 ፅንሰታ ለማርያም (የአምላክ እናት የተፀነሰችበት)]3,73%
  • 13 авг.8/12/2018 ማቴዎስ 7:12-26 ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፥ ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና። በጠባቢቱ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር፥ ሰፊ መንገድም አለችና፤ ወደ እርስዋም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። "ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ፥ መንገድዋም ቀጭን ናትና፤ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው። “የበግ ለምድ ለብሰው ወደ እናንተ ከሚመጡ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ናቸው። "ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን፥ ከአሜከላም በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍሬን ያፈራል። መልካምም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት፥ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም። "መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። “እንግዲህ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ ከሚያደርግ በቀር አቤቱ! አቤቱ! የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። «በዚያች ቀን ብዙዎች አቤቱ! አቤቱ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። ያንጊዜ ከቶ አላውቃችሁም፤ ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ። ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል። ዝናም ዘነመ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፉት፤ ነገር ግን አልወደቀም፤ በዐለት ላይ ተመሥርቶአልና....... ሮሜ 9:24-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 4:12-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 16:35-ፍጻሜ 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጐሥዐ) ምስባክ መዝሙር 57:8-9 ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ ትርጉም እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል3,55%
  • 11 авг.+ ማርያማዊ ብሶት + "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ድንግል ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ የተናገረችው የብሶት ንግግር ይኼ ብቻ ነው:: "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ድንግሊቱ እንዲህ ያለችው ምን ቢደርስባት ነው? ጌዴዎን እስራኤል መከራ ሲጸናባቸው "ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን?" ብሎ ነበር:: መሳ. 6:13 ኢያሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ :- ዋይ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን ታጠፋንም ዘንድ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? ብሎ በብሶት አልቅሶ ነበር:: ኢያሱ 7:7 ሙሴም የሕዝቡ አመፅ ሲያስጨንቀው ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? ብሎ ተማርሮ ነበር:: ዘኍ. 11:11 ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ብላ የብሶት ቃል የተናገረችው ግን መከራ ሲደርስባት አልነበረም:: ወደ ግብፅ ስደት እንድትወጣ ሲነገራት "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም:: ግርፋቱንና ሕማሙን ስታይም ኀዘንዋን ዋጥ አድርጋ ቆመች እንጂ "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም:: ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ያለችው ልጅዋ ለሦስት ቀናት ከዓይንዋ በራቀበት ወቅት ነበረ:: "እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን፡ አለችው" ሉቃ. 2:48 ድንግሊቱ ለምን እንዲህ አደረግህብኝ ያለችው ስለ ሌላው መከራዋ ጊዜ ሳይሆን ክርስቶስ ከእርስዋ ዘንድ ስላልነበረባቸው ቀናት ነበር:: እንደርስዋ መንፈሳዊ ስትሆን "ጌታ ሆይ ለምን አስጨነቅኸኝ?" የምትለው እርሱ ከአንተ የራቀ መሆኑ ሲሰማህ ብቻ ነው:: "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ" "አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?" እያልክ የምትጮኸው እግዚአብሔር ከአንተ የራቀ ሲመስልህና የተቀደሰው ማርያማዊ ብሶት ሲሰማህ ነው:: መዝ. 21:1፤10:1 እርሱ ከአንተ ጋር ከሆነ "በሞት ጥላ መካከል እንኩዋን ብትሔድ ክፉውን አትፈራም" ከአንተ የተለየ ሲመስልህ ግን "ጌታ ሆይ ምን አደረግህብኝ" ብለህ በማርያማዊ ብሶት ትጮኻለህ:: ከእርሱ ጋር ሆነህ መከራን መቀበል አይከብድህም:: መሰደድም አያስጨንቅህም:: እርሱ ከአንተ ዘንድ ከጠፋ ግን ብርሃንህ ምርኩዝህ ኃይልህ ጉልበትህ ሁሉ ከአንተ ዘንድ የሉምና ልትጸና አትችልም:: ዝምተኛዋን ድንግል ማርያም በብሶት ማናገር የቻለ አንዳች መከራ አልነበረም:: በበረሃ ከልጅዋ ጋር ከተንከራተተችበት ጊዜ ይልቅ ግን ያለ ልጅዋ ያሳለፈቻቸው ሦስት ቀናት "ልጄ ሆይ ለምን ይሄን አደረግህብኝ" ብላ እንድትጮህ አደረጓት:: ድንግል ሆይ ከአንቺ ዘንድ ለሦስት ቀን የተሰወረው ጌታ ከእኔ ሕይወት ከራቀ ዓመታት እንዳለፉ እያየሽ ይሆን? "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህበት? ነፍሱ ተጨንቃ እየፈለገችህ አይደለምን?" የማትይው ስለምንድን ነው? ለሌላው መከራዬ የምጮኸውን ያህል ከልጅሽ መለየቴ ተሰምቶኝ በማርያማዊ ብሶት እንዳልጮህ በኃጢአት ብርድ ተይዤ መንፈሳዊ ሙቀት በእኔ ዘንድ የለም:: የምበላው የምለብሰው ሲጎድል እንጂ አምላኬን ሳጣ የሚሰማኝ ሰው አይደለሁም:: እኔ ባልጠይቅሽ እንኳን እንደ ቃና ሙሽሮች ጉድለቴን አይተሽ የማትለምኚልኝ ለምንድን ነው? ልጅሽ ወደ ወይን እንዲለውጠው ከእኔ ሕይወት በላይ ውኃ ውኃ ያለ ነገር ከወዴት ሊመጣ? ከልቤስ በላይ የድንጋይ ጋን ከየት ይገኛል? "ንዒ ማርያም"3,51%
  • 13 авг.የቡሄ |ደብረ ታቦር መዝሙሮችን ለማጥናት 👇👇 🎶 ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና 🎶 ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ 🎶 አምላካችን ናና በዓምደ ደመና 🎶 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ 🎶 ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማው 🎶 ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ..... 🎶 እንደ ጸሐይ ፊቱ ሲያበራ 🎶 የታቦር ተራራ ምንኛ ታደለች 🎶 ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ 🎶 እንዲህ አለው ጴጥሮስ 🎶 በክብር ተገለጠ በታቦር 🎶 በደብረ ታቦር /፬/ ለሙሴ እነዚህን ለማጥናት Join አድርጉ join join join Join join join2,86%
  • 13 авг.በልቤ ተፀነሽ ልጅን የተራቡ ሃና ና ኢያቄም አንችን #በመፀነስ እንዳገኙ ሰላም መካንነት ፀንቶብኝ ፤ #ልቤ_ለታወከ ፥ ለእኔ ጉስቁል ልጅሽ ሰላምን እንዳገኝ ፥ በእኔ እደሪ ፤ በልቤ ታተሚ ፤ #በልቤ_ተፀነሺ ።2,59%
  • 12 авг.❀✞ፅንሰታ ለእግዝእትነ ወተስእሎተ ቂሳሪያ ወጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ ወልደቱ ለዮሴፍ ወልደ ራሄል ወናዖድ ንጉሠ ኢትዮጵያ።✞❀ ነሐሴ ፯ #ግጻዌ 🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺 ✝ ዘነግህ ምስባክ ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ።›› ‹‹መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።›› 🌺📖መዝሙር ፹፮፡፩ ✝✝✝ ወንጌል ዘነግህ 🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፩፡፩-፲፯ ፩ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ። ፪ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ ፫ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ፬ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ፭ ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ ፮ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ ፯ ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ ፰ አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤ ፱ ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ ፲ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤ ፲፩ አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ። ፲፪ ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤ ፲፫ ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤ ፲፬ አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤ ፲፭ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤ ፲፮ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ። ፲፯ እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው። ✝✝✝ የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት 🌺📖ወደ ዕብራውያን ሰዎች ፱፡፩-፲፩ ፩ ፊተኛይቱም ደግሞ የአገልግሎት ስርዓትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ ነበራት። ፪ የመጀመሪያይቱ ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው የመስዋዕቱም ኅብስት ነበረባት፤ ፫ ከሁለተኛውም መጋረጃ ወዲያ ቅድስተ ቅዱሳን የምትባለው ድንኳን ነበረች፥ ፬ በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥ ፭ በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ስለ እነዚህም ስለ እያንዳንዳቸው ልንናገር አሁን አንችልም። ፮ ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤ ፯ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ ፰ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል። ፱-፲ ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም። ፲፩ ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥ 🌺📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፪፡፮-፲፰ ፮ በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና። ፯ እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤ ፰ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው። ፱ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ ፲ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል። ፲፩ ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ ፲፪ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። ፲፫ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤ ፲፬ ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ። ፲፭ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤ ፲፮ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ። ፲፯ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ። ፲፰ ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ። 🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፲፡፩-፴ ፩ በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ። ፪ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ። ፫ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፦ ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። ፬ እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ፦ ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው፦ ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ። ፭ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። ፮ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል። ፯ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥ ፰ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው።2,48%
  • 11 авг.без подписи1,62%
  • 13 авг.без подписи1,36%
  • 15 авг.без подписи1,33%
  • 15 авг.без подписи1,32%
  • 12 авг.ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፯ ለነሐሴ ጽንሰታ ለማርያም ሥርዓተ ነግሥ፦ ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ፦ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ፦ ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ፤አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን፤ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት። ዓዲ ዚቅ፦ ለማርያም ዘምሩ፤ለማርያም ዘምሩ፤ መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ። ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። ዚቅ፦ ይትባረክ እግዚአብሔር ወይትአኮት ስሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ብዙኃን፤እስመ መሠረት አንቲ፤ለሕይወተ ኵሉ ዓለም፤ማርያም እምነ ወእሙ ለእግዚእነ ሰአሊ በእንቲአነ። ነግሥ፦ እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ ምጡቅ፤በነፋስ ዓውሎ ወቃለ መብረቅ፤ማርያም አንቲ ሰዋሰወ ወርቅ፤ይቤለኪ አሮን ሌዋዊ በደብተራ ሙሴ ባላቅ፤ታቦት ታቦት እንተ ውስቴታ ኦሪት ውቱረ ይከድንዋ በወርቅ። ዚቅ፦ እምድኅረ ካልዕ መንጦላዕተ ደመና፤ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን፤ወታቦትኒ እንተ ውስቴታ ኦሪት፤ይከድንዋ በወርቅ ውቱረ፤ወውስቴታ መሶበ ወርቅ እንተ መና፤በትረ አሮን እንተ ሠረፀት። መልክአ ማርያም፦ ሰላም ለአእዳውኪ እሳተ መለኮት እለ ገሠሣ፤አውቃፈ ብሩር ወወርቅ ለሥርጋዌሆን ኢኃሠሣ፤ማርያም ድንግል ለመካን ሕንባበ ከርሳ፤አንጽሕኒ እግዝእትየ ለፍትወተ ዓለም እምርኲሳ፤በዲበ ሥጋየ ኢትንብር ነጊሣ። ዚቅ፦ ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ፤አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ። ወረብ፦ 'እም ሐና ወኢያቄም'/፪/ ተወለድኪ/፪/ አላ በሩካቤ ዘበሕግ/፪/ መልክዐ ማርያም፦ ሰላም ለፍልሰተ ስጋኪ ወለተ ንጉሥ ይሁዳ፤ወወለተ ሌዊ እኁሁ ዘሀብተ ክህነቱ አገዳ፤ማርያም ድንግል ምዕዝት ዘእምፅጌረዳ፤በጽሒፍ ኢይፌጽሞ ለስብሐትኪ እንግዳ፤እመ ኮነ በቅድሜየ ስፍሐ ምድር ሰሌዳ። ዚቅ፦ በሩካቤ ዘበሕግ እለ ወለድዋ፤እም ቤተ ክህነት ወመንግሥት ዘኃረይዋ፤ይዕቲኬ ማርያም ይእቲ። መልክዐ ፍልሰታ፦ ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍስሓ ወኑዛዜ፤ኀበ ይረስዕዎ ለላህ ወኢይሄልይዎ ለትካዜ፤ማርያም ህሉት ውስተ ልበ አምላክ እምቅድመ ጊዜ፤ትፍሥሕተሰ ተፈሣሕኩ በፍልሰትኪ ይዕዜ፤ጊዜ ዚአኪ እሬኢ ማዕዜ። ዚቅ፦ ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር፤ወዘእንበለ ትሣረር ምድረ ገነት፤ሀለወት ስብሐት፤ቅድስት ወቡርክት ይእቲ ማርያም፤እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን፤ጽዮን ቅድስት እሞሙ ለሰማዕት፤ወእኅቶሙ ለመላእክት። ምልጣን፦ ማርያም ድንግል እመ መቅድመ ቃል ለክርስቲያን አክሊል፤ለናዖድ ገብርኪ ኲኒዮ ሰዋሰወ ሣህል ማኅፈዱ ለነበልባል፤መርዓት ዘወንጌል። ምልጣን፦ ለናዖድ ገብርኪ ኲኒዮ ሰዋሰወ ሣህል ማኅፈዱ ለነበልባል፤መርዓት ዘወንጌል። እስመ ለዓለም፦ ለልየ በእዴየ ለሐኵዋ ለድንግል፤እንተ እምኔሃ ተሰባዕኩ ይቤ እግዚአብሔር፤መንበሩ ዘኪሩቤል፤ዘኢዮር ማህደሩ፤ዘኢይትነገር ቃል፤ኀደረ ላዕሌሃ። እስመ ለዓለም ዘሰንበት፦ ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር፤ወዘእንበለ ይሣረር (ትሳረር)ምድረ ገነት፤ሀለወት ስብሕት ቅድስት ወቡርክት ይእቲ ማርያም፤እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን፤ጽዮን ቅድስት እሞሙ ለሠማዕት፤ወእኅቶሙ ለመላዕክት። ቅንዋት፦ ማርያምሰ ተሐቱ እምትካት፤ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ፀአዳ፤እስመ በእንቲእሃ ወበእንተ አዝማዲሃ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፀ ይቤ፤ከመ አድኀኖሙ አዳምሃ አቤልሃ፤አብርሃምሃ ይስሐቅሃ ወያዕቆብሃ፤ወፃዕዳነ ነቢያት እለ ከማሆሙ ዓቀቡ ሕግየ፤ከመ በላዕሌሆሙ እሰባሕ እስከ ለዓለም ዓለም። ዓዲ ቅንዋት፦ በትረ አሮን እንተ ሠረፀት፤ወባቲ ይገብሩ ተአምረ፤ውስተ አሕዛብ፤እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ።1,14%