የፍቅር ታሪኮች❤️ (ግጥም እና ልብ ወለድ)™
Статистикаምርጥ ምርጥ ልብ ወለድ እና ግጥም ፈላጊዎች ገባ ገባ በሉ ❤️🙏 ሀሳብ ጥያቄ ካልዎት 👉@natisha2020
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 35
- Всего постов
- 57
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 59
- 1/48двое суток
- 67
- 1/72трое суток
- 72
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
❤️🔥የጠፋዉ ሬሳ❤️🔥 🥵ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ💝 ምዕራፍ ሁለት ክፍል 7 ....ወደ ቀልቤ ሳልመለስ ደቂቃዎች ተቆጠሩ የሚሆነውን በማላስተውልበት ሁኔታ ሰከንዳት ብዙ ተጓዙ ነገር ግን በዛሁ አልቀረሁም ያለሁበትን ካስረሳኝ ሰመመን ነቃሁ በደም የተጨማለቀ አይኔን ለመግለጥ ሞከርኩኝ ግን አልቻልኩም ምንም እንኳ ብነቃ አካሌን መዘዝ ተስኖኛል የቅድሙ ቅዝቃዜ ፈፅሞ የለም ግን ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን የኔ መደንዘዝ ነው...ሰውነቴ ስለሚፈጠርበት ነገር ምላሽ ለመስጠት አቅም የለውም ነቅቼም በድን ሆኛለሁ...በዚ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ደቂቃዎች አብዝተው ተጓዙ እናም ሰውነቴን ለማገላበጥ ነቅነቅ ስል ከጭንቅላቴ ጋር እንደ ትራስ የሚመስል ነገር ተሰማኝ በጣም ደነገጥኩኝ ባዶ ወለል ላይ ነበር የተዘረርኩት እና ከየት መጣ ማንስ አመጣው ይሄን ጥያቄ እስክመልስ ድረስ እንቅስቃሴዬን ገታሁ... ደም የተጋገረበትን አይኔን በመዳፌ ለማፅዳት ሞከርኩ ነገር ግን ደርቆ ነበርና ቀላል አልሆነልኝም...ያለውንም ሁናቴ በእጆቼ መዳፍ ለማጣራት እጄን ወደ ትራሱ ሰደድኩት ነገር ግን አስቤ እንደነበረው ትራስ አይደለም...በጣም ደነገጥኩኝ የሰው እግር ነበር እጄን ወደነበረበት መለስኩኝ ልቤ ክፉኛ ተወራጨ አንድም በደስታ አንድም በጭንቀት...ደስታው የሚረዳኝ ሰው የመጣ መሰለኝ ጭንቀቱ ደሞ ያ ሰው ማነው የሚለው ነበር...ከአንደበቴ ቃል አውጥቼ አወራ ዘንድ አልቻልኩም ቃሎቼ ከአንደበቴ ሳይወጡ ከንፈሬ ላይ ይመክናሉ ምላሴ እንደቀድሞው አይታዘዝም ወይ አጠገቤ ያለው ሰው ራሱ ቢያወጋኝ ምን አለ ወይ ደግሞ የአይኔ ሽፋሽፍቶች ከብሌኔ ቢሸሹ ምን ነበር ይህን የኔ ደራሽ ባየሁት አልኩኝ መዳፌ አላረፈም ደጋግሜ ዳሰስኩት ነካካሁት ከናፍሬ ባይሸሽም ነፍሴ ግን ከልቧ እየሳቀች ነው የሆነ ሰው ብቻ መድህኔ ነው ልበለው ያንን አረመኔ ነፍሰ በላ የሰው ስጋ ጥማተኛውን አፈር እንዳስበላው ይሰማኛል ነፍሱንም ስለ ጠፉት ነፍሶች ብሎ እንደቀጣት ውስጤ ይነግረኛል የጓደኞቼን በቀል የስጋቸውን ደም የነፍሳቸውን ሲቃ አንዱ አዳኝ(ላልቶ) የስቃዩን እና የሰቆቃውን ምንጭ እንዳደረቀ ይሰማኛል...አካሌ ከነበረበት ድንዛዜ እየወጣ ነው መሰል ቅዝቃዜው ይሰማኝ ጀምሯል ከቅዝቃዜው ይልቅ ግን ውስጤ ድረስ የተሰማኝ ፀጉሬ መሃል የሚርመሰመሱት ጣቶች ነበሩ ፍፁም ሰላም ሰጡኝ ብዙ ተስፋን ሞሉኝ ፀጉሬ ከዚ በፊት ተዳብሶ እስከማያውቅ እንግዳ ሆነብኝ ጣቶቹ የጭንቅላቴን ቆዳ ሲነኩት ይጎረብጣሉ አይመቹም ግን እስከዛሬ ሲነኩኝ ከነበሩት ከለሰለሱ መዳፎች ይልቅ ልዩ ደስታን ሰጥተውኛል የተለየ ስሜትም አላቸው፡፡ ለማንም አሳልፎ የማይሰጠኝ ብርቱ ክንድ አጠገቤ እንዳለ ነፍሴ አመነች እኔም ተስማማሁ...ጣቶቹ ፀጉሬ መሃል ሲዋኙ እኔ በምናብ ክንፍ እላለሁ በፀደይ ወራት ውስጥ በለመለመ መስክ ላይ ለዘብ ባለች ፀሃይ ታጅቤ ከልካይ በሌለው ሜዳ ላይ ስቦርቅ ይታየኛል ግን ብቻዬን አልነበርኩም አንድ የማላውቀው ግን ደግሞ ደስታዬን እጥፍ ያደረገ ወጣት አብሮኝ አለ አላወራውም እሱም አያወራኝም ግን አንዳችን ላንዳችን ደስታ ነበርን ፀሃይ አዘቅዝቃ ወደ ጎጆዋ ስትገባ እሱ ግን ከኔጋ ነበር ከፀሃይ ብርሃን ይልቅ ለኔ ያስፈልገኛል ግን አላውቀውም አላወራውምም...ከሄድኩበት የሰመመን ደስታ መለስ አልኩኝ በጣቱ ንክኬ በመዳፉ መዳሰስ ሰላም የሚሰጠኝ ይህ ማነው እግሮቹ ላይ ተኝቼ ምንስ ያኩራራኛል እንደ መከታዬ ያሰብኩት ይህ ሰው ማነው? ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ከደባበሰኝ በሗላ እግሩ ከጭንቅላቴ ስር ሲነሳ ተሰማኝ አትሂድ ልለው ብዬ አልቻልኩም... አንደበቴ ታስሯል የክንዱ መፈርጠም ፆታውን ነግሮኛል አይቼ እንዳለየው አይኖቼ ተጋርደዋል ባለሁበት ሆኜ እጄን እየዘረጋሁ ዙሪያዬን ዳሰስኩ አንዳች አልነበረም ግን ከተኛሁበት ለመናሳት ስጥር ድግፍግፍ አድርጎ አነሳኝ አሁንም አጠገቤ እንዳለ ታወቀኝ ጥሎኝም እንዳይሄድ ባለችኝ ኢምንት አቅም ያዝኩት እሱም ከኔ አልሸሸም...ግን ማነው? ክፍል 8ከ20like👍 በኋላ ይቀጥላል‼️ #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
ይነበብ ይሄ መፅሀፍ ጀማው
«የሕሊና ደወል» በታዋቂው ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ የተጻፈ እና በ1966 ዓ.ም. ለንባብ የበቃ ሁለተኛ ልብወለድ መጽሐፍ ነው። ታሪኩ የሚያጠነጥነው ሐዲስ በተባለ ወጣት መምህር ላይ ነው። ከታች ለቂቂያለው መፅሀፉን አንብቡት ትልቅ ትምህርት ታገኙበታላችው
❤️🔥የጠፋዉ ሬሳ❤️🔥 🥵ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ💝 ምዕራፍ ሁለት ክፍል-6 ፡ ...እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ ሲራመድ የእግሩ ዳና ይናገራል...ከዚ ስቃይ ለመገላገል እና የስጋዊ ጉዞዬን እንደጨረስኩ ይሰማኛል እዛው ተቀምጬ እንዳለሁ ፀጉሬን ይዞ እየጎተተ ወደ መሃል አስጠጋኝ...የቆሰለው አካሌ ከወለሉ ጋር በተፈጠረው ፍትጊያ እየተላላጠ ስቃዬን አበዛው በድጋሜ እጅግ ቀዝቃዛ ውሃ ደፋብኝ አቤት ስቃይ ...ወለሉ ላይ ኩርምት ብዬ ተኝቼ አካሌ ይንዘፈዘፋል ትንፋሼ እየተቆራረጠ ልብ ምቴ ሊቆም እንደሆነ ይሰማኛል ግን ዘገየ እኔ ስቃዩን አልቻልኩትም ከበደኝ...ፀጉሬን ከአይኔ ላይ ገለል አድርጌ ስመለከት ጀርባውን ለኔ ሰቶኝ ከአንድ ጠረጴዛ ፊት ለፊት ቆሟል ነገር ግን ምን ያደርግ እንደነበር መለየት አልተቻለኝም ጭንቅላቴ ለአንገቴ እንደ አንዳች ከባድ ሸክም ሆኖበታል... እየደጋገምኩ ለመነሳት ብሞክርም አልቻልኩም...ጤናማ ሆነህ ያደረካቸው ተራ ነገሮች አቅምህ ተሟጦ ስታስባቸው ምነኛ እንደሚናፍቁ አሁን ተረዳሁኝ... አንዳች ክስተት ተፈጥሮ ከዚ ሞት ካጠላበት የተረገመ ቤት ሞቼም ቢሆን በወጣው አልኩኝ...ወለሉ ላይ ተንጋልዬ ሽቅብ ሰውዬውን ስመለከት ያንን ደም የለመደ መጥረቢያ ይዞ ወደኔ እየተራመደ መጣ አጠገቤም ደርሶ መጥረቢያውን መሬት አስደግፎ ይዞረኝ ጀመር ለምን እንደሆነ ምክንያቱን ባላውቅም...ልክ በአይኔ ትይዩ ሲደርስ ጫማውን ስመለከተው ትናንሽ ስጋዎች እና የረጋ የደም ጠብታ ይታይበታል...አሟሟቴን ማሰብ ጀመርኩ "ድንገት ሳላስበው ጭንቅላቴን ሁለት ያረገው ይሆን ወይስ አንገቴን በጥሶ ይጥላዋል?" እያልኩ መልስ አልባ ጥያቄዎችን ራሴን ጠየኩት በተኛሁበት እየዞረኝ ደቂቃዎች ተቆጠሩ... ነገር ግን ሰውዬው እስካሁን አንዳች ነገር አላደረገኝም ይህ ሁኔታ ግራ ሆነብኝ... በድንገት ሌላው ክፍል ባርሳ እንዳለች ትዝ አለኝ ትኑር ትሙት ግን አንዳች አላውቅም...አረመኔው ሰውዬ እንደጨቀነቀው እየተሰማኝ ነው ያለማቋረጥ ዝም ብሎ ይዞረኛል ስሜቱን በደንብ ለመረዳት እንደምንም ክንዴን ተመርኩዤ ቀና ስል ደም ባቆረፈደው ጫማ ከስር ወደላይ በግራ ጉንጬ በኩል ጥርሶቼ የተራገፉ እስኪመስለኝ ድረስ ህመሙ ዘልቆ ተሰማኝ...ከሰውዬው ምት የባሰው ደግሞ ጭንቅላቴን የተቀበለው ወለል ነበር ደም ደም ሸተተኝ አፍንጫዬን ነሰረኝ ጭንቅላቴም መድማት ጀመረ... በዚ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ በድጋሜ ፀጉሬን ይዞ ጎተተኝና ግድግዳ አስደግፎ አስቀመጠኝ ከዛም የመጥረቢያውን ስለት አዞረና የግራ እግሬን ከጉልበቴ በታች ያለውን አጥንቴን ክፉኛ መታኝ ድምፄንም ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ እየደጋገምኩ ጮውኩኝ አምርሬም አነባሁ አጥንቴን ስለመታኝ ህመሙን አልቻልኩትም እግሬን ታቅፌ ወለሉ ላይ ተኛሁኝ እግዜር ምን እስከሆን እየጠበቀኝ እንዳለ ጥያቄ ሆኖብኛል መላ አካሌ ዝሏል ሞት ብቻ ነው የቀረኝ ግን ደሞ ሞቴ በጣም ዘገየ...ሰውዬው አሁንም ፀጉሬን ይዞ ጎትቶ ግድግዳው ላይ አስደገፈኝ ደሜ ከአናቴ ሲንቆረቆር ገላዬ ላይ ይታወቀኛል የእግሬ አጥንት የተሰነጠቀ እስኪመስለኝ ድረስ ይቆረጥመኛል በዚ ስቃይ ውስጥ እያለሁ ቀዝቃዛውን ውሃ በድጋሜ ደፋብኝ ከዛም ፊት ለፊቴ ተንበርክኮ አንገቴን ሲጥ አርጎ አንቆ እየደጋገመ ከግድግዳው ጋር በሃይል ያጋጨኝ ጀመር ከዛም የፊጢኝ ያነቀውን አንገቴን ለቀቀው ወዲያውኑ ተዝለፍልፌ ወለሉ ላይ ተንጋለልኩ ደሜ ያለማቋረጥ እየፈሰሰ በጆሮዬ ስር ይወርዳል የማየው ነገር ሁሉ መሽከርከር ጀመረ... እያዞረኝ እንደሆነም ተሰማኝ ቀስ በቀስ የማየው ነገር እየደበዘዘ መጣ ወዲያውኑም ጭልም አለብኝ ምንም ማየት አልቻልኩም ኩርምትምት እንዳልኩኝ በደም ተጨማልቄና ረጥቤ ራሴን ሳትኩኝ... l ክፍል 7ከ20like👍 በኋላ ይቀጥላል‼️ React react react 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
እሽ እንቀጥል የጠፋው ሬሳ
ትክክለኛ መልስ ካድማስ ባሻገርስ ነው 🙏
видео или голосовое, без подписи
❤️🔥የጠፋዉ ሬሳ❤️🔥 🥵ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ💝 ምዕራፍ ሁለት ክፍል-5 ፡ ...እጆቼን በሃይል ጎትቶ ከተቀመጥኩበት ምንጭቅ አርጎ አነሳኝ በዚ ጊዜ ከብረት ወንበሩ ጋር ተገናኝቶ የነበረው የአካሌ ክፍል እየተቦጫጨቀ ወንበሩ ላይ ቀረ ወለሉ ላይም ወረወረኝ...ጀርባዬ እና ታፋዬ በደንብ የተጎዱ የሰውነት አካሎቼ ናቸው ወንበሩ ዳማ መሰይ ክፍተት ባይኖረውማ ኖሮ ቆዳዬ እንደ ሚገፈፍ አንዳች ጥርጥር የለኝም... ...ስቃዬን ቃላት ችለው አይገልፁትም እዛው ወለሉ ላይ ሆኜ ክፉኛ መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ ጉልበትና ጭንቅላቴን አጋጥሜ ኩርምት ብዬ እየተንከጠቀጥኩኝ ሳለ ይባስ ብሎ አረመኔው ሰውዬ አጥንት ድረስ ዘልቆ ሚሰረስር ቀዝቃዛ ውሃ እላዬ ላይ ደፋብኝ ስቃዬን በእጥፍ አበዛው፡፡ ገና ያልደረቀ ቁስሌ ነፍሴ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ክፉ ህመም ሆነብኝ ምንም ቃል ማውጣት ተስኖኛል ዝም ብቻ ሌላ ምንም ውሃውን እየደጋገመ ይደፋብኝ ጀመር ...አንዳዴ ሞት እየናፈቁ አለማግኘት በፈጣሪ እንደመረሳት ይመስለኛል የሞት መልዓክ ለኔ ሲሆን ዘገየ እንዲ ስሰቃይ እያየ ዝም ብሎኛል አልጠራው ነገር አቤት አይለኝ መፈጠሬን እስክጠላ የደስታም ቀን አሳልፌ የማውቅ እስከማይመስለኝ ድረስ በወለደኝ ማህፀን ተማረርኩ... አይኔ ከመከደን በማይተናነስ ሁናቴ በትንሹ ገርበብ ብሎ ተከፍቶ አንባዬን ዝም ብሎ ይሸኛል ከናፍሮቼ ከጥርሴ ጋር ተስማምተው ይብረከረካሉ በኤሌክትሪክ የተጠበሰው ገላዬ አሁን ብርድ እያቆረፈደው ቁስሉም እየመዘመዘኝ ደቂቃዎች በፀጥታ ተጓዙ... መላ ሰውነቴ ዝሏል ደክሟል ባዘውመም አይለሰማኝም ለመነሳሳት ስሞክር አሀሸየደጋገምኩ መውደቅ ጀመርኩ ቢያቅተኝ እዛው ተንንጋለልኩ....አይኖኖቼን ገጥሜ ቀጣይ ስቃዬን መጠባበቅ ጀመርኩ ሰውዬው ካለሁበት ክፍል ይውጣ አይውጣ ምንም አላውቅም ብቻ ሁሉም ፀጥ ብሏል...አዛው የተኛሁበት መቅረት አልፈለኩም እንደምንም በመሬቱ ላይ ለመንፏቀቅ ሙከራዬን ጀመርኩ ያን ያህል ባልፈጥንም ችዬው መሳቤን ቀጠልኩ ደሜ ከውሃው ጋር ተቀላቅሎ ወለሉን ጋርዶታል...ክንዴ አካሌን መሸከም ተስኖታል እንደዛም ሆኖ አልቆምኩም እየተንፏቀኩ ነው በመሃል እጄን አሟልጮኝ በግንባሬ ወለሉ ላይ አረፍኩኝ ክፉኛ መታኝ...ግን አሁንም አለሁ አየተነፈስኩ... በድጋሜ መንፏቀቄን ቀጠልኩ የክፍሉ ጥግ(ኮርነር) ጋ ሽጉጥ አልኩኝ... ጉልበቴን ከአገጬ አጋጥሜ በእጆቼ እግሮቼን ይዤ ተቀመጥኩኝ የጀርባዬ ቁስል ከግድግዳው ሲነካካ ያለው ህመም በዛ ላይ ቅዝቃዜው...አሁን በጥቂቱም ቢሆን እየተረጋጋሁ ነው ግድግዳው ብርዱን እየተከላከለልኝ ነው አካሌ መንቀጥቀጡን ባያቆምም እንኳ... ትንፋሼን ወደራሴ አካል እየተነፈስኩ ሰውነቴን ለማሞቅ መኮርኩ ግን አልቻልኩም በጡት ማስያዣና በፓንት ብቻ ሆኜ ቁሩ ከበደኝ...እዛው በተቀመጥኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ሰውዬው ግን የለም ቀና ብዬ ክፍሉን ተመለከትኩት ልብሴ ተበጫጭቆ ወለሉ ላይ ታየኝ ትንሽ ቀና ስል ደግሞ የብረቱ ወንበር ላይ ከኔ ተቦጭቆ የቀሩው የሰውነቴ ስጋ ታየኝ አይኔን ወዲያውኑ ከሱ ላይ አነሳሁ መመልከት አልቻልኩም ሌሎች የሚታዩኝ ነገሮች ቢኖሩ የማሰቃያ ስለቶች እና አንድ ጠረጴዛ ብቻ ነው... በድንገት "ግደላት ለምን አትገላትም አንገቷን በጥሰው አካሏን ቆራርጠው ቆዳዋንም ግፈፈው አይኗን መንቅረው ምላሷን ጎልጉለው ጥፍሮቿን ንቀል ጡቷንም ቁረጥ" የሚል ሰቅጣጭ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ንግግር በሴት አንደበት ሲነገር ሰማሁ ትንሿ ሴትዮ መሰለችኝ ልክ ንግግሯን እንዳበቃች እርምጃው ፈጠን ያለ ኮቴ ወዳለሁበት ክፍል ሲመጣ ተሰማኝ.. ክፍል 6ከ20like👍 በኋላ ይቀጥላል‼️ #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
видео или голосовое, без подписи
የጠፋው ሬሳ ይለቀቃል 🔥 ተዘጋጁ 🙌
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ላይክ ሼር በማድረግ አበረታቱን እናመሰግናለን 🙏 ቤተሰብ ምዕራፍ አንድ 23 እና 24 ተለቋል 🤟 ምዕራፍ ሁለት 1 እስከ 4 ተለቋል 🤟 🔥 ፏ በሉ 🔥
መልካም ንባብ ምዕራፍ አንድ ተፈፀመ ምዕራፍ ሁለት ጀምረናል የጠፋው ሬሳ ይቀጥላል መልካም ንባብ በድጋሚ ጥያቄዎችን መልሱ 🙏
❤️🔥የጠፋዉ ሬሳ❤️🔥 🥵ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ💝 ክፍል-4 ከኮቴው ጋር ከብዙ ስለቶች መሀል ስለት ሲፈለግ የሚሰማው ድምፅ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ ከዛም አብዝቶ ወደኔ ተጠጋ አንዳች ድቡልቡል ነገር አፌ ውሴጥ አሰገባ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ አይኔን እስከመጨረሻው ግልጥ አድርጌ ከፈትኩት ነገር ግን ከመብራቱ በቀር አንዳች አልታየኝም አፌ ውስጥ የከተተው ነገር ማሰሪያ ነበረውና ከጭንቅላቴ ጋር የፍጢኝ አሰረው መጮህ እየፈለኩ ግን አልቻልኩም ፍፁም ለስቃይ የታሰበ ነገር ነው አይኖቼን ዘግቼ "የልጅህ የክርስቶስ ደም ከበረዶም ይልቅ ከበደል ያነፃልና በደል መተላለፌን በአሪያም ዛሬም ድረስ ህያው ሆኖ ስለኔ በሚቃትተው ደምህ አንፃኝ በመንግስትህም አስበኝ" ብዬ የመጨረሻ ቃሌን ለአምላኬ በልቤ አንደበት ነገርኩት...አይኔን ከድኜ ሞቴን በመጠባበቅ ነኝ...ድንገት ሰውዬው ቀረብ ብሎ ከላይ የለበስኩትን በመቀስ እየቆራረጠ ከላዬ ላይ ገፈፈው በጡት ማስያዣ ብቻ ቀረሁ በድጋሜ ሱሪዬንም መቅደድ ጀመረ ጫማዬንም አወለቀው ልክ ካልሲዬን ሲያወልቀው እግሬ ላይ ከነበረው ቁስል ጋር ተጣብቆ ነበርና ክፉኛ አመመኝ አሁን እርቃኔን ነኝ ከአይኖቼ የሚፈሰው እንባ ቁልቁል ወደ ጆሮዬ ይምዘገዘጋል...እላዬ ላይ የበራው መብራት ለኔ ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ ሰውነቴን አግሎታል መላ አካሌን ላብ ሲጠምቀኝ ይታወቀኛል...ግን ከዚ ሙቀት ውስጥ እላዬ ላይ የደፋው እጅግ ቀዝቃዛ ውሃ አወጣኝ...የእግሮቼ አውራ ጣቶች ላይ ምን እንደሆን እንጃ ቁንጥጥ አድርጎ እንዲይዘኝ አደረገ...ሰውዬው ከኔ ርቆ ሲሄድ ይሰማኛል ግን ከክፍሉ እንዳልወጣ ተረድቻለሁ በመቀጠልም እንደ ማብሪያና ማጥፊያ አይነት ድምፅ ያለው ነገር ተሰማኝ ቀመቅፅበት መላ አካላቴን ለሰከንዶች ያህል አርገፈገፈኝ ወዲያውኑ አቆመው መተንፈስ አቃተኝ በአፍንጫዬ ብቻ የሚገባው አየር አልበቃሽ አለኝ አሁንም በድጋሜ የማብሪያ ማጥፊያውን ድምፅ ሰማሁት እንደገና አርገፈገፈኝ አሁን ትንሽ ቆየት አድርጎብኛል ከዛም አጠፋው ደም ስሮቼ በአየር እጦት ክፍኛ ተወጥረዋል አይኔ አብዝቶ ፈጠጠ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ከባድ ስቃይ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደፈለኩ የምምገው አየር አብዝቶ ናፈቀኝ ከየትም ላላመጠው ነገር...በዚ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ሰውዬው ሲራመድ በድጋሜ ተሰማኝ ለቅፅበትም ቢሆን ትንሽ መረጋጋት ተሰማኝ...ነገር ግን ብዙ አልቆየም ነበር ያንን ቀዝቃዛ አካልን የሚቆርጥ ውሃ በላዬ ላይ ከለበሰብኝ ከተቀመጥኩበት ብረት ወንበር ጋር የተነካካው የአካሌ ክፍል ውሃ ሲነካው ህመሙን መቻል አቃተኝ...ወዲያውኑ ያንን ማብሪያ ማጥፊያ በድጋሜ ተጫነ ውሃው ስቃዬን አባሰው...ያበራውን ሳያጠፋ እየተርገፈገፍኩኝ ውሃውን ይጨምርብኝ ጀመር ረዘም ላሉ ሰከንዶች ከቀጠለ በሗላ አጠፋልኝ...አሁን ምንም የማረግ አቅም አልነበረኝም አየር የተባለ ጉሮሮዬ ጋር አይደርስም አይኔ ሲገለበጥ ይታወቀኛል ግን ያልጠበኩት ነገር ሆነ ሰውዬው አፌ ውስጥ ያስገባውን ነገር አወጣልኝ ወዲያውኑ አስመለሰኝ እጅግ ፍጥነት ባለው አተነፋፈስ አለከለኩኝ እየደጋገመ ያስመልሰኛል...አልቻልኩም አቅሜ ፈፅሞ ተሟጧል...የክፍሉን ዋናውን መብራት አበራውና አይኔ ላይ ተደንቅሮ የነበረውን አጠፋው ከአንዱ ጥግ ቆሞ አተኩሮ ይመለከተኛል ግራ የተጋባ ይመስላል አይኖቹ አይረገበገቡም የተሰፋፋው ፊቱ ፈፅሞ አይፈታም ደም የለመዱ እጆቹ ርህራሄ የላቸውም የሰው የማይመስለው ልቡ ምህረትን አያውቅም ብቻ ዝም ብሎ ይመለከተኛል ለምን እንደሆነ ለኔ ፍፁም ግራ ነው...እንደዚ እንደተፋጠጥን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ወደራሴ እየተመለስኩ ስመጣ የራሴ ስጋ ሽታ ሸተተኝ በኤሌክትሪክ ሾክ ገላዬ ተጠብሶ ነበር ትንሽ እንደቆየ ገላዬ ላይ ያለው እርጥበት ሲደርቅ ወደኔ መራመድ ጀመረ የተዘቀዘቀውን ወንበር እንደመጀመሪያው አስተካክሎ አስቀጠው ከውንበሩ ጋ የታሰረውን የእጅና የእግር ማሰሪያ ፈታልኝ ከዛም ከፊት ለፊቴ ሁለት እጄን ይዞ እግሩን ከፍቶ ቆመ ጭንቅላቴን መሸከም አቅቶኝ አጎንብሻላሁ እጄን በእጁ እንደያዘ ለሰከንዶች ፀጥ ብሎ ከቆየ በሗላ ሳላስበው... ክፍል 5ከ20like👍 በኋላ ይቀጥላል‼️ #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
_ ❤️🔥የጠፋዉ ሬሳ❤️🔥 🥵ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ💝 ክፍል3 ...አይኔ ያየውን ማመን አቃተኝ "ባርሳ" ነበረች ድንጋጤና ደስታ በአንድ ላይ ተቀላቀሉብኝ ግን አንዲትም ቃል አልተነፈስኩም እሷም እንደኔ የፊጥኝ ታስራለች ፊቷ ላይ የደም ነጠብጣብ ይታየኛል አይን አይኔን እያየች አንባዋ ቁልቁል ወደ ጆሮዋ ይወርዳል አሁን ያለሁበት ሁኔታ ጥሩ ባይሆንም ግን የተስፋ ጭላንጭል ይታየኛል "በአንበሶች ጉድጓድ የተጣለውን ዳንኤልን ያየ አምላክ አይኑም ክንዱም ለኔ እንደማይዝሉ አምናለሁ" ብዬ ለራሴ አውርቼ ባርሳን እያየሁ ጭንቅላቴን ነቀነኩኝ ፊቴን ከሷ ላይ መልሼ በአቧራ ካደፈው መስታወት አሻግሬ ተመለከትኩ አነስ ምትለዋ ሴት የተለያዩ የህክምና መስጫ መድሃኒቶችን ይዛ አረመኔውን ሰውዬ ካላከምኩህ ብላ ትሟገተዋለች እሱ ደግሞ አለመፈለጉን በምልክት ያሳያታል ምን እንደምትለው ለማወቅ ቢቸግርም ብቻ ብዙ ነገር እያወራችው ነው ከወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደ የሆነ ነገር ማብሰልሰል ውስጥ የገባ ይምስላል ግራ እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ የቀኝ እጁን ደግሞ አፉ ላይ አድርጎ ሌባና መሃል ጣቱን ከፍና ዝቅ እያደረገ ይንጎራደዳል ትልቋ ሴትዮ ቁጭ ብላ ትመለከተዋለች ብቻ አንዳች ነገር እያሰበ ነው ትኩረታቸው ወደኛ ሊሆን እንደማይችል በተረዳሁ ጊዜ ወደ ባርሳ ተመለስኩኝ እሷ አሁንም ወደኔ እየተመለከተች ነበር "ባርሳ" ብዬ ጠራሗት እጅግ ዝግ ባለ ድምፅ "ሜርሲ ደና ነሽ ደግሜ አይሻለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከመሞቴ በፊት ስላየሁሽ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ" አለች በእንባ ሳግ በሚቆራረጥና በለዘበ ድምፀት "ሽሽሽሽ እንደዚ አትበይ ባርሳ አይዞሽ ተስፋ አትቁረጪ እስካሁን የቆየሽው ለምክንያት ነው እሱ እኛን ከመግደሉ በፊት ራሳችንን ገለን ልንጠብቀው አይገባም አይዞሽ ባርሳዬ" ስላት ከንፈሯን እየነከሰች እንባዋን ለማቆም መጣር ጀመረች የሷ መበርታት ለኔም አቅም ነው...በድጋሜ አይኔን ወደ ሰዎቹ መለስኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያው አይኔን ወደ ክፍሉ መልሼ የክፍሉን በር ተመለከትኩ ማንም አልመጣም ባርሳን ዝም እንድትል ነግሪያት ለደቂቃዎች ፀጥ አልን ግን አንዳች ነገር አልተከሰተም ለምን እንደው እንጃ ከአይኔ መሰወራቸው ጨንቆኛል "ባርሳ ይሄስ ማነው" ብዬ ጠየኳት አጠገቧ የተኛውን ለማየት ያልተመቸኝን ክፍሉ ውስጥ ያለውን ሌላኛውን ሰው "ባባ ነው" አለችኝ በጣም እንዳዘነች ፊቷ አብዝቶ ይናገራል "ምን ሆኖል በጣም ተጎድቷል እንዴ..." እያልኩኝ ጥያቄዬን ሳልጨርስ ከፍ ባለ ድምፅ "ግደላት" የሚል ድምፅ ሰማሁ አይኔን ወደ መስታወቱ መለስኩኝ ትንሿ ሴትዮ ነበረች ለአረመኔው ሰውዬ ስታወራ የነበረችው ትልቋ ሴት ቁጭ ብላ ትመለከታቸዋለች ወዲያውኑ ሰውዬው እርምጃውን አፍጥኖ በእልህ እኛ ወደነበርንበት ክፍል ሲምዘገዘግ መጣ በሩንም ብርግድ አርጎ ገብቶ ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ ከዛም በራስጌ በኩል ሆኖ የተኛሁበትን አልጋ እየገፋ ወደ ውጪ ይዞኝ ወጣ ባርሳ አይን ላይ ያየሁትን ፍቅርና ፍራቻ ቃል አይገልፅልኝም በትንሿ ሴት መሪነት ወደ ሌላ ክፍል ተወሰድኩኝ ምንም አላልኩኝም ነበር...ክፍሉ ውስጥ ገባሁ እስከዛሬ ያልተመለከትኩት በስለት የተሞላ አስፈሪ እና አሰቃቂ ቦታ ነው ሰውዬው የታሰርኩበትን ቀበቶ መፍታት ጀመረ ልክ እንደጨረሰም አንጠልጥሎ ከአንድ የማይንቀሳቀስ ተለቅ ያለ የብረት ወንበር ላይ አስቀመጠኝ...ወዲያውኑ እጄን ለክንድ ማስቀመጫ ተብሎ ከተሰራበት የወንበሩ ክፍል ጋር አጥብቆ አሰረው ወረድ ብሎም ከመዳፌ ትንሽ ከፍ ብሎ በድጋሜ አሰረኝ እግሬንም እንዲሁ ከወንበሩ ጋር አሰረው አስሮ እንደጨረሰ ከኔ ራቅ ሲል ክፍሉን መመልከት ጀመርኩኝ የተለያዩ የእጅ እና የእግር ጣቶች በየቦታው ተንጠባጥበዋል ጥፍሮችም ጭምር ከተቀመጥኩበት በስተ ቀኝ በኩል ያየሁት ነገር ከምንም በላይ ሰቅጥጦኛል ከአንድ ሰርቢስ ላይ በአንድ ላይ የተቀመጡ የአይን ኳሶች ይታዩኛል በሌላኛው ሰርቢስ ላይ ደግሞ ጆሮና ምላስ ተቀምጧል አጥወለወለኝ አንገሸገሸኝም የማረገውና የምሆነው ጠፋኝ ሆዴ ተላወሰ አስመለሰኝም እዛው በተቀመጥኩበት ራሴ ላይ ለቀኩት ቀና ብዬ ስመለከት ከበላዬ የተለያየ አይነት ቅርፅ ያላቸው መርፌዎች ይታዩኛል ዶክተሮች ለህክምና የሚጠቀሙት መብራትም አለ ሰውዬው ጋውን ለብሶ ወደኔ መጣ የተቀመጥኩበትንም ወንበር ትንሽ ከፍ አድርጎ ወደሗላ አንጋለለው አሁን ካሁን ወደኩኝ ስል ወንበሩ ግን አልወደቀም ነበር አሁን ለመወራጨትም ሆነ ለምንም የማያመች አቀማመጥ ነው ያስቀመጠኝ ዶክተሮች ለቀዶ ጥገና የሚጠቀሙበትን መብራት አበራው አይኔ እሱን መመልከት አልቻለም ነበር ጨፈንኩት ይህ ሰው ሊያሰቃየኝ እንደፈለገ ግልፅ ነው በቀሉን ለመመለስ ይመስላል ከዛም ክፍሉ ውስጥ ይበራ የነበረውን መብራት አጠፋው አይኔን ከፍቼ ግራ ቀኜን ስመለከት አንዳች አልታየኝም የመብራቱ ጉልበት ከፍተኛ ነበር እዛው ባለሁበት አንደበቴን ዘግቼ ፀጥ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ ከሰከንዳት በሗላ ሰውዬው ወደኔ ሲመጣ የእግር ኮቴው ተሰማኝ.. ከፍል 4ከ20like👍 በኋላ ይለቀቃል‼️ #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭_ #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭* 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱 *
видео или голосовое, без подписи